Forwarded from ግጥም በ ኤዶምገነት
⨳⨳ደጋፊው ሲደገፍ⨳⨳ ልደግፍሽ ሲለኝ እውነቱን ነው ብዬ፣ ሙሉ ሰውነቴን ትከሻው ላይ ጥዬ፣ መድከም መውደቅ የለም እያልኩኝ ስመካ፣ እሱም የተጠጋኝ.... የደገፈኝ መስሎ ሊደገፍ ነው ለካ። 🤔🤔 ✍ኤዶምገነት ፃፈችው @arifgtmbcha
Open in TelegramForwarded from ግጥም በ ኤዶምገነት
⨳⨳ደጋፊው ሲደገፍ⨳⨳ ልደግፍሽ ሲለኝ እውነቱን ነው ብዬ፣ ሙሉ ሰውነቴን ትከሻው ላይ ጥዬ፣ መድከም መውደቅ የለም እያልኩኝ ስመካ፣ እሱም የተጠጋኝ.... የደገፈኝ መስሎ ሊደገፍ ነው ለካ። 🤔🤔 ✍ኤዶምገነት ፃፈችው @arifgtmbcha
Open in TelegramForwarded from ግጥም በ ኤዶምገነት
** በደል የለመደች ያያት የሚገፋት፣ የቀረባት ሁሉ ላይዘልቅ የሚያለፋት፣ ሰው የማይቆይላት ቀርቧት እየሼሸ፣ ጀመርኩት ያለችው እየተበላሸ፣ ብዙ የደከመች ፍቅርን ፍለጋ፣ በወደደቻቸው ልቧ የተወጋ፣ ልክ እንደ ሌሎቹ ... መልክ ሴትነቷ አካሏ 'ሚማሰል፣ ላዳም ያልተሰጠች ሄዋን አለች መሰል። #ኤዶምገነት_ፃፈችው @arifgtmbcha
Open in TelegramForwarded from ግጥም በ ኤዶምገነት
*አታባብሉኝ* አይዞሽ አታልቅሽ አትበሉኝ በሞቴ፣ የገደለው ባሌ የሞተው አባቴ፣ እዴት አላለቅስ እንዴት አላነባ፣ እርሱን እረስቼ ገዳዩን ሳገባ፣ ጠበንጃ ባይጨብጥ ባያነሳ ስለት፣ አባቴን ገሎታል ልቆ ከባልነት፣ በማላቀው ለዛ ፍቅር እየሰጠ፣ በልቤ ሚዛን ላይ አባቴን በለጠ፣ የጀግኖቹ ጀግና የወንዶቹ ቁና፣ የዘመኔ ንጉስ አባቴ ነው እና፣ ከሱ ሚወዳደር ሲመጣብኝ ፍቅር፣ እንዴት አላለቅስ እንዴት አይለኝ ቅር፣ ከእኔ በላይ ወዶኝ ለነብሴ ሲሳሳ፣ አባቴን ሲገለው መውዜር ሳያነሳ፣ ትዳሬን ሲደምቀው ፍቅሩ ከአባ ብሶ፣ እደውም ያንሰኛል ሀዘንና ለቅሶ፣ ካሻችሁ አላቅሱኝ ......... ካልሆነ አትከልክሉኝ አታባብሉኝ ላንባ፣ አባቴን ስለየው ......... ምርቃቱን ይዤ ፍቅሬ ቤት ስገባ። ከተመቻችሁ sher... ✍❤️✍❤️✍❤️ ከኤዶምገነት ፅሁፎች https://t.me/arifgtmbcha https://t.me/arifgtmbcha https://t.me/arifgtmbcha
Open in TelegramForwarded from ግጥም በ ኤዶምገነት
*ወንድሜ* ወንድ ብዬ ወንድም፣ ይገልፅሀል እና ቃላትን ፍለጋ ወደሌላ አልሄድም፣ ያኔ ከምሀፀን ያለመለመኝን ያንን መልካም ቦታ፣ አንተም ፀድቀህበት ምላሹን አተኻል እንደኔው ውለታ፣ ይሄብቻ አይደለም ወንድምነት ወጉ፣ መወለድ ቋንቋ ነው ይላሉ ሲያወጉ፣ ፍቅር የሞላበት የኔና ያንተ አለም፣ በመወለድ ብቻ የፀና አይደለም፣ ሲወጣልህ ስምህ ሲወጣልኝ ስሜ፣ ሲታደለን መኖር ስንሸለም እድሜ፣ ስናድግ ስንበስል ባካል በአምሮ፣ ወትሮ ከነበረው ፍቅራችን ጨምሮ፣ መካሪ ዘካሪ አራሚም አራቂ፣ በኩር ወንድም ጋሻ ሁነኸኝ ጠባቂ፣ መሪ አስተማሪ ጓደኛ ደጋፊ፣ እውቀት ፍቅር ለጋሽ ሁነህልኝ ሰፊ፣ እንደዚህ ነው ብልህ ቃላት ስላልበቃ፣ ምንም የማይገልፅህ ወንደም ነህ በቃ። ከተመቻችሁ sher... ✍❤️✍❤️✍❤️ ከኤዶምገነት ፅሁፎች https://t.me/arifgtmbcha
Open in TelegramForwarded from ግጥም በ ኤዶምገነት
*አንድ ሰው ነበረ* መንገዴን ያቀና በንግግሮቹ፣ ጥበብን የሚያዘንብ ከከናፍሮቹ፣ አፍላገ ፍቅረ ማይ፣ ከሱ የወረደው ከኔላይ የሚታይ፣ በኔ የማይደክም ስጠም የሚያቃና፣ መንፈስ የሚያጀግን እምነት የሚያፀና፣ እኔ ሁለት ሁኜ እስኪመስለኝ ድረስ፣ ሀቁን ብረዳውም ከራሴ ስመለስ፣ እንባዬን ያነባ ሲያመኝ የታመመ፣ ሳዝን ያዘነልኝ ስደክም ያልደከመ፣ ስጠማ የጠማው ስራብ የተራበ፣ ማተቡን የፈታ ገፁን ያነበበ፣ ከጎኔ ያልጠፋ ቃሉን ያከበረ፣ እኔ የሆንኩትን ሁሉ የነበረ ፣፣ አምሳያ የሌለው አንድ ሰው ነበረ🥺። ✍❤️✍❤️✍❤️ ከኤዶምገነት ፅሁፎች @arifgtmbcha @arifgtmbcha @arifgtmbcha @arifgtmbcha
Open in TelegramForwarded from ግጥም በ ኤዶምገነት
⨳*ሻማና ክር***⨳ እኔ ነኝ ክር፣ የሻማ አካል ተደግፌ..... በእሳት ግለት የምሰክር፣ የማቃጥል የማቀልጠው፣ በጭካኔ የምበልጠው፣ ደግ ወዳጄን የምበቀል፣ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል፣ እየሆንኩኝ..... በአንድ ክብሪት የምሰክር፣ ይዛ ሟቿ እኔነኝ ክር፤ እሱ ሻማ፣ ቃጠሎዬን የሚሻማ፣ እሳት ሳዎርድ እንደፀበል፣ ከስር ሆኖ የሚቀበል፣ ያላሸሸኝ ከድጋፉ፣ ደስ የሚለው..... እያቀፈኝ መንጠፍጠፉ፣ እለት ከእት እያለቀ፣ እኔ አጥፊውን የታጠቀ፣ በክፋቴ እየሞተ፣ ላይለዬኝ የዘመተ፣ ያፈቀረኝ እሱ ሻማ፣ የኔን ስካር..... ቃጠሎዬን የሚሻማ፤ ማነው ልኩ፣ በኔ ምክንያት ጠፍቶ መልኩ፣ ውስጤን ፀፀት ውጬን እሳት፣ እየበላኝ..... ባየሁ ቁጥር የሱን ክሳት፣ ጭካኔዬን ሳብሰለስል፣ ስቀጣጠል እስክከስል፣ ቀልጦ ቀልጦ እያለቀ..... እዳልደክም መደገፉ፣ ደግ ሆኖ ነው ወይስ ክፉ¿¿¿ ✍❤️✍❤️✍❤️ ኤዶምገነት ፃፈችው @arifgtmbcha @arifgtmbcha
Open in TelegramForwarded from ግጥም በ ኤዶምገነት
ናፈቀኝ """""""" ወደሰማዩ ሳይ በደመና ምስል፣ ባይኔ ተከሰተ እርሱን የሚመስል፣ ጉብታውን ስቃኝ ተራራ ዳገቱ፣ ተመሳሰለብኝ ከኮራ ደረቱ፣ ንፋስ የሚገፋው ያየሩ መአዛ፣ እርሱን አስታወሰኝ ናፍቆት እየገዛ፣ እያንዳንዱ ነገር ያሳለፍነው ጌዜ፣ ገደለኝ ትዝታው ሆነብኝ ትካዜ፣ ጩኬ የሰደብኩት ያኔ ሲያበሳጨኝ፣ ትውስ አለኝና ባርባር አለኝ ቆጨኝ፣ መጣብኝ ጫዎታው መጣብኝ ሞገሱ፣ ናፈ'ከኝ ብል እንኳን አይሰማኝም እሱ፣ ናፍቆኛል ጨንቆኛል ግን ባይመለስስ፣ ዝም ልበልና ጎርፍ ዕንባዬን ላፍስስ። ኤዶምገነት ፃፈችው @arifgtmbcha @arifgtmbcha
Open in TelegramForwarded from ግጥም በ ኤዶምገነት
***አመድ አፋሽ***** በዛ በብርድ በጨለማ፣ የኔን ጩኸት ጣር ስትሰማ፣ ጉዴን ልታይ ብትል ጠጋ፣ ልብስ የራቀው እርቃን ስጋ፣ ድርቅ የመታው ሚስኪን ከንፈር፣ ደም ያቦካው እርጥብ አፈር፣ የለሊት ቁር የጠዋት ውርጭ፣ ያገረጣው አመዳም ጉንጭ፣ ወዝ የራቀው ደረቅ እንባ፣ ብታስተውል ሀዘን ዋጠህ ውስጥህ ባባ፣ ፈቀድክልኝ ባንተው ጎጆ እንድገባ፣ አዎ ያኔ ከችግር ጋር ተቃቅፌ፣ ለእይታ እንኳን ፍጡራንን አስቀፍፌ፣ ሰማይ ምድሩ ተደፍቶብኝ ስብረከረክ፣ የረዳኸኝ የኔ ጻድቅ አንተ ነበርክ፣ ዛሬ እንዳዲስ ተፈውሶ ያ ህመሜ፣ ያጨቀየኝ የፈሰሰው ቁሞ ደሜ፣ በከፋኝ ቀን ለረገጡኝ እየናቁ፣ ድነት ፈውሴን እዲያዩልኝ በውድቀቴ እዳይስቁ፣ መነሳቴንም እዲያቁ፣ ብጠራቸው በኔው እልፍኝ አጀብ ድግስ፣ ሳሳድዳቸው በህሊና በፀፀት ክስ፣ ብትመጣ ከድግሴ ሳትጠራ፣ ትውስ አለኝ የጭንቁ ቀን ያ መከራ፣ በጨለመኝ በከፋኝ ቀን ብትጠጋም፣ መልካምነት ውለታህን ባልዘነጋም፣ ዛሬ ሳይህ ተናነቀኝ የሀዘን እንባ፣ በል ተመለስ ልሳቅበት ወደ እልፍኜ እዳትገባ፣ ብትመጣም ልትደሰት በኔ ደስታ፣ አስታወስከኝ ያንን ስቃይ ያንን ማታ፣ ስለዚህ ነው የከፋብህ ንፉግ መልሴ፣ ወዳጄ ሆይ ባይመጥንህ ነው ድግሴ፣ አቅም ባጣ ለውለታህ መመለሻ፣ ካድኩህ እና አባረርኩህ እደ ውሻ። ከተመቻችሁ #share_ & #like ✍❤️✍❤️✍❤️ ኤዶምገነት ፃፈችው @arifgtmbcha @arifgtmbcha @arifgtmbcha
Open in Telegram#እሱ . ዝም.. ቢልም፡ እስክንፈራ እስኪጨንቀን፣ ነገራትን ይቀይራል፡ ቃል አውጥቶ ባወራቀን! . #እሱኮ . ተስፋ አቶ መኖር ጠልቶ፡ ተሰላችቶ በዓለም በደል፣ ደስታ እርቆት የኖረውን፡ ያውቅበታል በሳቅ መግደል! #ኤዶምገነት_ፃፈችው @arifgtmbcha
Open in Telegram#ለእኔ ለእውነተኛ_ጓደኝነት . ካየኋቸው ሰዎች መሀል ካረኳቸው ባልንጀራ: ለመታመን የማትከብደኝ ለቅርርብ ማታስፈራ: የሽንገላ የማስመሰል ወዳጅነት የማትሻ: ትሻላለች ክፋ ደጉን የፃፍኩባት ማስታዎሻ። #ኤዶምገነት_ፃፈችው @arifgtmbcha
Open in Telegramምን እየሆንኩ ልጠብቅሽ? ~ ~ ~ ~ ~ ቅድ ሰማይ እየሰፋሁ ራስ ዳሽን እየገፋሁ ወይስ እየሰራሁ የኖኅ መርከብ ሳፈላልግ የሰው ኮከብ.. ምን እየሆንኩ ልጠብቅሽ? እየዘመርኩ? እየዘፈንኩ? እያረመምኩ? ግራ ገባኝ እኮ ያልለየት ድል ነው ያልለየት ምርኮ። ምን ስሆን ልጠብቅሽ? አባይን ስጠልቀው ኤርታሌን ስሞቀው ቆዳዬን እንደጨርቅ ችሎ ቢተኩሰው ተዋነይ ጋር ልሂድ ዕፁን እንዲምሰው። ማን ጋር ልጠብቅሽ? ከጌታዬ ግራ ከጌታዬ ቀኙ በየት ትመጫለሽ ወይ አፍቃሪ ሞኙ። ካብርሃም ቤት አጋር ወይስ ባቢሎን ግንብ ጋር። የት ጋር ትመጫለሽ? በዘመን የት ዘመን? በቦታ የት ቦታ? ከንጉሥ የት ንጉሥ? ከባህር ምን ባህር? ከጫካ የት ጫካ? ከደብር የት ደብር? : ከሶላት ምን ሰዓት? ምን እያረግኩኝ ልጠብቅሽ? ከመላእክት ጋር ስገለፍጥ የዛፍ ቆዳ ስልጥ... ግዙፍ ሆኜ ወይ ረቂቅ ንፋስ ሆኜ ወይስ ደቂቅ.... ወንዝ ሆኜ ወይስ አምባ ደስታ ሆኜ ወይስ ዕምባ... ፀሀይ ግርጌ ወይ ጨረቃ ግጥም ሆኜ ወይ ሙዚቃ... ምን እየሆንኩ ልጠብቅሽ? ኤልያስ ሽታኹን
Open in TelegramForwarded from ግጥም በ ኤዶምገነት
***አስታራቂ መደብ**** በጣራስር ውለው ሁለት አባዎራ፣ አንድ ወንበር ቢያገኙ በእንጨት የተሰራ፣ እኔ ልቅደም እኔ በማለት ሲጋፉ፣ ሲሰበርባቸው ......... ሁለቱም ተስማምተው መደብ ላይ አረፉ። ከተመቻችሁ #share & #like ✍❤️✍❤️✍❤️ ኤዶምገነት ፃፈችው @arifgtmbcha @arifgtmbcha
Open in Telegramሰላም ኤዱ ዜድ እባላለሁ። ይቅርታ ካላስቸገርኩሽ ይቺን ታሪኬን ቻናልሽ ላይ እንድትፖስቺያት ነበረ። የሰዎች ምክር ያስፈልገኛል ብዬ ስላመንኩ ነው። በብዙ ምክንያት እኔ እና እህቴ አንድ ላይ ከቤተሰብ ርቀን ነው የምንኖረው። እኔ ታላቅ ወንድሟ ነኝ እሷ ገና 17 አመቷ ነው 11ኛ ክፍል ናት። ጎበዝ ተማሪ እና ስርአት ያላት ነበረች፤ ግን አሁን እርጉዝ ናት። ግራ የሚያጋባ ነገር ነው፤ እኔ እህቴ በዚህ ልክ ትሳሳታለች ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር። ቤተሰቦቻችን ወደ እኔ ሲልኳት "ለእሷም (ከአንተ ጋር) ከተማ መማር ይሻላታል፤ አንተንም ታነጋግርሃለች፣ አደራ ጠብቃት" ብለውኝ ነበር። ግን እሷ በሙሉ ልብ ከማፈቅረው ሰው አርግዣለሁ፣ ከእሱ ጋር መኖር እፈልጋለሁ አለችኝ። በሰአቱ በጣም ተናድጄ "የራስሽ ጉዳይ" አልኳት፤ ግን ሀሳብ ሆናብኝ ሳያት የወደፊት ህይወቷ እያሰጋኝ ነው። ያስረገዛትን ሰው እንድታስተዋውቀኝ ጠየቅኳት እና አንድ እሷን የሚያክል የ11ኛ ክፍል ተማሪ አምጥታ አስተዋወቀችኝ። ከዛ በኋላ 18 አመቱ እንደሆነ እና የሀብታም ልጅ ስለሆነ ብቻቸውን መኖር እንደሚችሉ እና ከአንተም ወንድምነትህን እንጂ ብር ምናምን አልፈልግም ብላ ነገረችኝ። ሊሆን እንደማይችል ባስረዳትም አልሰማችኝም እና የእህቴ ጉዳይ በጣም አስጨንቆኛል። ለማንም ሰው አላወራሁም፤ ቤተሰብ ቢሰሙ ምን ይሉኛል? "ጠብቃት አደራ" ብለውኝ አሁን እንዲህ ሆነች ለማለት አልቻልኩም። ምን ላድርግ? እህቴንስ ምን ልበላት? በናታችሁ የሆነ ነገር በሉኝ።
Open in Telegram*** ፍቅር አለ ማይረሳ ፣ ሳቅን የሚቀማ ሰላም የሚነሳ ፣ ጭስ የማይደብቀው ፣ መጠጥ የማይፍቀው ፣ . አይንን የሚጋርድ ጆሮን የሚደፍን ፣ አንችሆየ አምባሰል ትዝታን ሚዘፍን ፣ ሌላ ማያሰማ ምክር የማይደንቀው ፣ መልክ ገለመሌ ውበት የማይሞቀው ፣ . ፍቅር አለ አዝጋሚ መቼም የማይጠፋ ፣ ከመጠጥ ከጭስ ከሁሉ ሚከፋ ፣ . ፍቅር አለ ፡፡ #ኤዶምገነት_ፃፈችው @arifgtmbcha
Open in TelegramForwarded from ግጥም በ ኤዶምገነት
አዲስ ነገር የለም """""""""""""""""""""" ከሰማዩ በታች የለም አዲስ ነገር፣ ጊዜ የገዛትን ታሪካዊት ምድር ጠይቋት ትናገር፣ ካንዱጋር ዳንኪራ ከሌላጋር ሀዘን፣ አንዱ ሲረጋጋ አንደኛው መባዘን፣ መጪ ስንቀበል ሌላው ተሰናባች፣ ተወለደ ሲባል እዛጋ ደሞ ሟች፣ የለም አዲስ ነገር ሆኖ እንጂ ለየቅል፣ ጊዜ ንጉስ ሆኖ አውርዶ ሲሰቅል፣ እኛም ሆነንለት ተጎናባሽ አሽከር፣ እንከተላለን .... በመሬት ዙሪያላይ ይዞን ሲሽከረከር፤ በዚች በቆምኩባት ባለሁበት ምድር፣ የወለደ ሲሞት ያሳደገ ሲድር፣ ጥንዶች ሲጫዎቱ የፍቅር ጫዎታ፣ ያረገዘች ስትወልድ ያገባ ሲፈታ፣ አማኝ የገዳም ሰው ወይም በግልባጭ፣ ጠንባዛ ሰካራም አንቡላ አንጫላጭ፣ መፍትሄ ጠፍቶበት ኑሮ ያቀወሰው፣ አይቻለሁ ባይኔ .... ጨርቁን ጥሎ ሲያብድ ጤነኛ ያልኩት ሰው፤ አዲስ ነገር የለም ስጠይቅ እራሴን .... ለምን እንደሆነ አንዱ አለፈ ሲባል ሌላው የሚተካ፣ ሲገባኝ እውነቱ .... ክብ አለም መዞር ነው ሂዎት ማለት ለካ። ✍ኤዶምገነት ፃፈችው @arifgtmbcha @arifgtmbcha
Open in Telegram#አንተን_መውደድ ፏፏቴ ዳር ቁጭ ብሎ ዋሽንትን እንደ ማድመጥ፣ ዜማውን ተከትሎ በደስታ እንደ መስመጥ፣ አይንን ከደን እንዳረጉ የለሆሳስ ውዝዋዜ፣ ቢደጋገም የማይሰለች የሚናፈቅ አይነት ጊዜ፣ ከተፈጥሮ ተዋህዶ ንጹህ ህይወት እንደመልመድ፣ ልክ እንደዛ ሰላም አለው ደስ ያሰኛል አንተን መውደድ፡፡ #ኤዶምገነት_ፃፈችው @arifgtmbcha
Open in Telegram#ይሂድ . ለመሄድ ቀጠሮ ይዞ እያንቀላፋ ያለን ሰው፥ አባብለህ አታስቀረዉም መሄጃዉ ሲደርስ ቀስቅሰው፡፡ #ኤዶምገነት_ፃፈችው @arifgtmbcha
Open in Telegram#ብቻ_ይሳቅ መውዜርም አትስጡት ጎራዴም አትስጡት አይጠቅመውም ለሱ፣ ለመግደል ለመግደል ለመቅጣት ከሆነ ይበቃዋል ጥርሱ፣ ጉልበት የማይጠይቅ ልዩነው ፈገግታው ላየው ቀልብ ይገፋል፣ ለጠላው አይደለም ለወዳጁም ሳይቀር ሳቁ ይጋረፋል! #ኤዶምገነት_ፃፈችው @arifgtmbcha
Open in Telegram