Account

Posts of 📚መንፈሳዊ መጽሐፍት📔

newest first

#4848Text

ከሶስት ቀናት በፊት ከቀድሞው የትምህርት ቤት ጓደኛዬ የተላከልኝ የSMS መልእክት👇 "ሰላም Zed እንዴት ነህ! ይኸውልህ! ትላንትና ምን ተከሰተ መሰለህ ድንገት የስልኬ ስክሪን በራ። የገባውን የጽሑፍ መልዕክት ስመለከት፣ የቀድሞ የትምህርት ቤት ጓደኛዬ ነበረች በትምህርት ቤት ዘመናችን የነበረን ቅርበት የጠበቀ ነበር፤ ከተለያየን በኋላም ቢሆን እንኳ በመካከላችን ያለው ቅርርብ የጠበቀ ነበር። ሆኖም ግን፣ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ በግንኙነታችን ላይ አንድ ያልተጻፈ ሕግ እየተተገበረ መሆኑን በዝምታ አስተውያለሁ። እርሷ ወደ እኔ ብቅ የምትለው ሁልጊዜ በሕይወቷ ውስጥ አንድ ዓይነት ማዕበል ሲነሳ ብቻ ነው። ልቧ ሲሰበር፣ ቤተሰቦቿ ሲያስከፏት፣ ወይም በሥራ ቦታዋ ተስፋ ስትቆርጥ... የስሜት ሸክሟን የምታራግፍበት "የነፍስ ማረፊያ ጣቢያ" አድርጋ እየተጠቀመችብኝ ነው። ሰዓታትን የሚፈጁ ምክሮቼንና ማጽናኛዎቼን ትቀበላለች። ልክ ነፋሱ ጸጥ ሲልና ፊቷ ሲፈካ ግን፣ እንደ ጠዋት ጤዛ ትተናለች። ስለ እኔ ሕይወት፣ ስለ ድካሜ ወይም ስለ ደስታዬ ጠይቃኝ እንኳ አታውቅም። የትናንቱ መልዕክቷም ከቀደሙት የተለየ አልነበረም፦ "ዛሬ በጣም ከፍቶኛል፣ ትንሽ እናውራ?" የሚል ነበር። መልዕክቱን እያነበብኩ ለጥቂት ደቂቃዎች በሃሳብ ተዋጥኩ። መልስ ብሰጣት፣ ዛሬም የእርሷን የስሜት ቁስል ለመጠገን ስል የራሴን ውስጣዊ ሰላም አሳልፌ እንደምሰጥ አውቃለሁ። ዝም ብላት ደግሞ፣ በውስጤ ያለው መንፈሳዊ ሰው "እንዴት የተቸገረችን እህት ችላ ትላለህ? የክርስቶስ ፍቅር የት አለ?" እያለ ይሞግተኛል(በዛላይ ለእርሷ የፍቅር ስሜት አለኝ) በመጨረሻም አን ውሳኔ ወሰንኩ። ይኸውም! መልዕክቱን አንብቤ በዝምታ አለፍኩት። በልቤ ውስጥ ምንም ዓይነት ጥላቻ፣ ቅሬታ ወይም የበቀል ስሜት የለም። እንደውም በጸሎቴ አሰብኳት። ነገር ግን፣ የእርሷን ሕይወት ለማቅናት ስል የራሴን መንፈሳዊና አእምሮአዊ ጤንነት መስዋዕት ማድረግ እንደሌለብኝ አመንኩ። የራሴን ሰላም ለመጠበቅ ስል፣ ለጊዜው እርሷንና ችግሮቿን "ቸል ብዬ ማለፍን" መረጥኩ። አሁን ግን አንድ ጥያቄ በውስጤ እየተመላለሰ ዕረፍት እየነሳኝ ነው ይህ ውሳኔዬ መጽሐፍ ቅዱስ የሚደግፈው "ጤናማ ቸልተኝነት" (ራስን ከአድካሚ ግንኙነት የመጠበቅ ጥበብ) ሊባል የሚችል ነው? ወይስ በመንፈሳዊነት ሽፋን የተሸፈነ ግድየለሽነትና ፍቅር ማጣት ነው? ሌሎችን ለመርዳት ስንል የራሳችንን ውስጣዊ ሰላም እስከ ምን ድረስ ነው መስዋዕት ማድረግ ያለብን? መንፈሳዊ ድንበር የቱ ጋር ነው የሚሰመረው? እባክህ እስቲ የሆነ ነገር በልኝ Zed!🙏 Telegram| Facebook | Instagram  | Twitter(X) |Christian e Library

Open in Telegram
Views6,820−19%vs avg
Forwards—
Reactions62
Comments—
#4847Text

ኢየሱስ አምላክ ከሆነ፣ አምላክ እንዴት ሊሞት ይችላል? ለሚለው ጥያቄ እኛ ክርስቲያኖች ለሙስሊም ወገኖቻችን እንዴት ብንመልስላቸው ጥሩ ይመስላችኋል? በመጀመሪያ ክርስቲያኖች ለዚህ ጥያቄ መልስ ሲሰጡ፣ ከእስልምናው የዓለም አተያይ በመነሳት እንዲወያዩ አበረታታለሁ። መጀመሪያ ላይ ይህ ጥያቄ ብዙ ክርስቲያኖችን ግራ ሊያጋባ የሚችል ይመስላል፤ ነገር ግን የጥያቄው መነሻ መሠረት ስህተት ያለበትና አቋም የታጣበት ነው። ምክንያቱም ሙስሊሞች ለኢየሱስ ብቻ ሲሉ የ"ሞት"ን ትርጓሜ ወደ "መኖር ማክተም" እየቀየሩት ስለሆነ ነው። ጥያቄያቸውም "አምላክ እንዴት መኖር ያቆማል" የሚል ይመስላል። ችግሩ ግን፣ ለክርስቲያኖችም ሆነ ለሙስሊሞች የ"ሞት" ትርጓሜ "መኖር ማቆም" ማለት አይደለም። የሚገርመው፣ ቁርአን ራሱ ይህንን ሐሳብ የሚደግፉ ምሳሌዎችን ይሰጣል፦ "በአላህ መንገድ የሚገደሉትንም 'ሙታን' አትበሏቸው፤ እነርሱ በሕይወት ናቸው፤ ነገር ግን እናንተ አታውቁም (አትገነዘቡም)።" (ሱራ 2፡154) ተመሳሳይ ሐሳብ በሱራ 3፡169 ላይም እናገኛለን፦ "በአላህ መንገድ የተገደሉትን እንደ ሙታን አትቁጠሯቸው፤ እነርሱ በጌታቸው ዘንድ ሕያዋን ናቸው፤ ሲሳይ ይለገሱላቸማል።" እነዚህ ጥቅሶች አንድ ሙስሊም ከራሱ የእምነት ማዕቀፍ ውስጥ ሳይወጣ እንኳ፣ ሞት ማለት "መኖር ማቆም" እንዳልሆነ እንዲረዳ ያደርጉታል። በክርስቲያናዊ ትምህርት ግን የኢየሱስ ሞት ከዚህ በላይ ትልቅና ጥልቅ ትርጉም አለው። ኢየሱስ የሰው ልጅን ባሕርይ የተዋሐደው ለተወሰኑ ዓላማዎች ነበር፦ "ልጆቹ ሥጋንና ደምን ስለ ተካፈሉ፣ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፣ ይህም ዲያብሎስ ነው፣ በሞትም ፍርሃት ዕድሜ ልካቸው በባርነት ታስረው የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፣ እርሱ ደግሞ እንዲሁ በሥጋና በደም ተካፈለ።" (ዕብራውያን 2፡14–15) "የሰው ልጅ እንኳ ሊያገለግለው ሳይሆን ሊያገለግል፣ ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ መጥቷልና።" (ማርቆስ 10፡45) "ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተሞልቶ በእኛ አደረ፤ ከአብ እንደ ተገኘ የአንድያ ልጅ ክብር የሆነውን ክብሩን አየን። ... ማንም እግዚአብሔርን ከቶ አላየውም፤ በአባቱ እቅፍ ያለ አንድያ ልጅ እርሱ ተረከው። (ዮሐንስ 1፡14–18) በነገራችን ላይ እኮ የኢየሱስ መለኮታዊ ማንነቱ ሞቷል አላልንም አይደል እንዴ! ይልቁንም ገንዘቡ አድርጎ የወሰደው ስጋው እንጂ። Telegram| Facebook | Instagram  | Twitter(X) |Christian e Library

Open in Telegram
Views7,500−10%vs avg
Forwards—
Reactions55
Comments—
#4846Photo
Views8,220−2%vs avg
Forwards—
Reactions17
Comments—
#4845Text

በነገራችን ላይ በማሪያም ዘላለማዊ ድንግልና ዙሪያ  ብዙውን ጊዜ የሚያንዣብበው ክርክር በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 19 ላይ፣ ኢየሱስ በመስቀል ላይ እያለ እናቱን ማርያምን ለወዳጁ ደቀ መዝሙር ለዮሐንስ አደራ የሰጠው ኢየሱስ ሌሎች ወንድሞች ቢኖሩት ኖሮ ይህን ማድረጉ የሙሴን ሕግ መጣስ ይሆን ስለነበር ነው ብለው ይከራከራሉ። በመሰረቱ ግን ይህ አመለካከት ጥቂት ግልጽ የሆኑ እውነታዎችን ችላ ብሏል። በመጀመሪያ፣ የኢየሱስ ወንድሞች በዚያን ሰአት እንኳ አያምኑበትም ነበር። እንዲያውም በዮሐንስ 7 ላይ እንደምናየው፣ ይሳለቁበት ነበር፤ ከትንሣኤው በኋላ እንጂ ከዚያ በፊት አላመኑበትም። ከሁሉም በላይ ደግሞ፣ እነርሱ በመስቀሉ ስፍራ  አልነበሩም፤ ዮሐንስ ግን እዚያ ነበር። የኢየሱስ ወዳጅና አማኝ ደቀ መዝሙር የነበረው ዮሐንስ፣ ከማርያም ጋር የነበረው የእምነት አንድነት፣ እንደ እርሷ በኢየሱስ ካላመኑ በስተቀር ከሥጋ ልጆቿ ይልቅ እጅግ የጠበቀ ነበር። ስለዚህ፣ ኢየሱስ እናቱን ለዮሐንስ አደራ መስጠቱ ከአዲስ ኪዳን መረጃዎች ጋር ፍጹም የሚጣጣም ነው። ታዲያ ይህ አስተምህሮ ከየት መጣ? የመጣው ከቀደምት አማኞች ማኅበረሰብ ነውን? ታሪካዊው መልስ ደግሞ "አይደለም" የሚል ነው።ስለ ማርያም ዘላለማዊ ድንግልና የተጻፈው የመጀመሪያው ጽሑፍ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጪ ከሆነውና መናፍቃዊ ተብሎ ከሚታየው "የኢሳይያስ ዕርገት" (11፡8-14) ላይ  የተገኘ ነው። በውስጡም "ማሕፀኗ ከመፀነሷ በፊት እንደነበረው ሆኖ ተገኘ" የሚል ሐረግ ይገኛል። በተመሳሳይ፣ በኖስቲሲዝም ትምህርቶች የተለከፈው "የሰሎሞን መዝሙራት" የተባለው መጽሐፍም፣ ኢየሱስ ሲወለድ ምንም ዓይነት አካላዊ ምጥ እንዳልነበረ ይናገራል። ከሁሉም በላይ ግን፣ የሁለተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ልብ ወለድና አፈ ታሪክ የሆነው "የያዕቆብ ፕሮቴቫንጌሊየም"  ይጠቀሳል። ምንም እንኳን ይህ መጽሐፍ ከክስተቱ ከመቶ ዓመት በኋላ የተፈጠረ የልብ ወለድ ስብስብ ቢሆንም፣ የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ስለ ማርያም ዘላለማዊ ድንግልና እና ስለ ሌሎች ማርያምን የተመለከቱ ትምህርቶች መሰረት የሆነው ከዚሁ መፅሃፍ ነው። ቀደምት የቤተ ክርስቲያን መሪዎችም ቢሆኑ በዚህ ጉዳይ ላይ ጨረሶውኑ የተናገሩት ነገር አልነበረም።  በሁለተኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጨረሻ የነበረው ተርቱሊያን፣ ማርያም መደበኛ የጋብቻ ሕይወት እንደነበራትና ሌሎች ልጆችም እንደወለደች ጽፏል። ከጊዜ በኋላ ግን ኦሪገን የዘላለማዊ ድንግልናን ሐሳብ ማራመድ ጀመረ። በሚቀጥለው መቶ ክፍለ ዘመን አምብሮስ፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት የሌለውን ይህን እምነት ለማጽደቅ የሕዝቅኤልን ቤተ መቅደስ ራዕይ (ሕዝ. 44፡1-3) በመጥቀስ፣ የተዘጋውን በር የማርያም ዘላለማዊ ድንግልና ምሳሌ አድርጎ አቀረበው። ተመልከቱ እንግዲህ በቤተ ክርስቲያን አባቶች አስተያየት ላይ ብቻ መደገፍ ምን ያህል አደገኛ እንደሆነ ሂላሪ የተባለ ሰው በራሱ ሕይወት አሳይቷል። እርሱ በራሱ ዘመን የነበሩትን የማርያምን ዘላለማዊ ድንግልና የሚክዱ ሰዎችን በብርቱ ይቃወም ነበር፤ ነገር ግን እርሱ ራሱ ሌላውን ትልቅ የካቶሊክ ትምህርት የሆነውን "የድንግል ማርያም ያለ ኃጢአት መፀነስ" ዶግማ በግልጽ ይክድ ነበር። Telegram| Facebook | Instagram  | Twitter(X) |Christian e Library

Open in Telegram
Views8,910+6%vs avg
Forwards—
Reactions36
Comments—
#4843Text

በዕብራይስጥ ቋንቋ ውስጥ "ያዘኝ" ወይም "ነበረኝ" ተብሎ የተተረጎመው ግስ "ቃናህ"ነው። ይህ ግስ ደግሞ በዕብራይስጡ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሰፊ የትርጉም ክልል ያለው ሲሆን፣ "መፍጠር" የሚለውንም ትርጉም ይይዛል (ዘፍጥረት 14፥19፣ 22፤ ዘዳግም 32፥6)። እንግዲህ አርዮሳውያን አዲስ ኪዳን ኢየሱስን ከጥበብ ጋር አያይዞ ስለሚያቀርበው፣ ምሳሌ 8፥22 ኢየሱስ የተፈጠረ እንጂ ዘላለማዊ እንዳልሆነ ያረጋግጣል ሲሉ በጣም ብዙ ጊዜ ደጋግመው ሲናገሩ ይሰማል። በእውኑ! ይህ ሐሳብ ወጥነት አለውን? ብሉይ ኪዳንን በአዲስ ኪዳን ብቻ ለመተርጎም መሞከር ጥሩ የትርጓሜ ዘዴ ሊሆን አይችልም። አንድን ምንባብ የምንተረጉመው የምንወደውን የስነ መለኮት አስተምህሮ ለመጠበቅ አልመን ብቻ ከሆነ፣ ያ! ፈፅሞ ሐቀኛ የትርጓሜ ሥራ አይደለም። ደግነቱ፣ ይህን ማድረግ አያስፈልገንም። ጥበብ በእግዚአብሔር የተፈጠረ ነው የሚለው ሐሳብ፣ በብሉይ ኪዳን አመለካከት ውስጥ ጨርሶውኑ ወጥነት የሌለው ነው። ጥበብ የእግዚአብሔር ባሕርይ በሰው መልክ ተመስሎ የቀረበችልን ናት። ጥበብ ያልነበረችበት ጊዜ ነበር ብንል፣ እግዚአብሔር ጥበብ የጎደለው ሆኖ የነበረበት ጊዜ ነበር ልንል ነው። የብሉይ ኪዳን አምላክ ጥበብ የሌለው ሊሆን አይችልም፤ ይህ ሐሳብ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እግዚአብሔር ከሚያቀርበው መግለጫ ጋር አይስማማም። እግዚአብሔር ጥበብ ቢታጣበት ኖሮ፣ ጥበብን ለመፍጠር የሚያበቃ ጥበብ ራሱ ባልነበረውም ነበር። ስለዚህ፣ ኢየሱስን ወደ ሐሳቡ ሳናስገባ እንኳን፣ ቃናህን «ፈጠረ» ብሎ መተርጎም በብሉይ ኪዳን አስተሳሰብ ውስጥ ትርጉም የለውም። አዲስ ኪዳን ኢየሱስን በእውነት ሥጋ የሆነ እግዚአብሔር አድርጎ እንደሚያቀርበው፣ዘላለማዊ መሆን እንዳለበት የሚያምኑ ሰዎች፣ በምሳሌ 8፥22 ያለውን ግስ "አወጣኝ" ወይም "ወለደኝ" ተብሎ መተርጎሙ የተሻለ ነው ብለዋል። በዘፍጥረት 4፥1 ሔዋን ልጇን ቃየንን "ወለደች" በሚለው ቃል የሚታየው ትርጉምም ይህ ነው። የዚህ ቃል ትርጉማዊ ጥላ በጥንቃቄ ሊታይ ይገባል። በዘፍጥረት 4፥1 የተገለጸው ሐሳብ ፅንስ መፈጠር ማለትም አዲስ ሕይወትን መጀመር አይደለም፤ ይህ ሐሳብ በዚያው ቁጥር በሌላ ግስ፣ "ሃራህ"፣ ተብሎ ተገልጿልና። ሔዋን ቃየንን። "አልፈጠረችውም"። ቃየን ቀደም ሲል ከተፀነሰ በኋላ ከማሕፀን ወጣ። ይህም ማለት፣ የጥንት እስራኤላውያን ሕፃን መወለዱን እንደ ፍጥረት አይቆጥሩትም ነበር፤ ምንም እንኳ ይህ ሂደት በሳይንሳዊ መንገድ እንዴት እንደሚፈጸም ባያውቁትም፣ በማሕፀን ውስጥ ሕያው ነገር እንዳለ ግን ያውቁ ነበር። የጥንት እስራኤላውያን ሴቶች ፅንሱ መንቀሳቀስ ሲጀምር ራሳቸውን "እርጉዝ ነን" ብለው ያውቁ ነበር። (እርግጥ ነው፣ የወር አበባ መቋረጥንና ሌሎች የሰውነት ለውጦችን በማየት ብቻ እርግዝናን መጠራጠር ይችላሉ፤ ) ከዚህ አንጻር፣ "ቃናህ" የሚለው ግስ የሕይወት መጀመሪያን ሳይሆን፣ ከማሕፀን የመውጣትን ቅጽበት እንደሚያመለክት አድርገን እንተረጉመዋለን ማለት ነው። ስለዚህ ጥበብ ከመለኮታዊው ማንነት ወጥታ፣ እግዚአብሔር አብን በፍጥረት ሥራ ለመርዳት ተገለጠች። በምሳሌ 8፥22 ያለውን ግስ በዚህ መንገድ መረዳት ከቻልን፣ ኢየሱስ—ጥበብና ልጅ የሆነው—ዘላለማዊ ነው የሚለውን እምነት ያስጠብቃል። በዚህም ምሳሌ 8፥22 የኢየሱስን መለኮትነት አይንደውም፤ ይልቁንም ኢየሱስ በፍጥረት ሥራ የእግዚአብሔር ወኪል እንደሆነ የሚታይበትን መንገድ ለመረዳት ይረዳል እንጂ ጥበብ በምሳሌ 8 ውስጥ እንደ ሰው ተመስላ የቀረበች የግጥም አገላለጽ ናት። በመንገድ ዳር ቆማ ሰዎችን ወደ ጥንቃቄና ጽድቅ ትጠራለች፤ በፍጥረትም ጊዜ ከእግዚአብሔር ጋር እንደነበረችም ማስታወስ አለብን። ስለዚህ በምሳሌ 8 ውስጥ ጥበብን በቀጥታ እንደ ሴት ፆታ መለኮት ወይም ከእግዚአብሔር የተለየ ፍጡር አድርገን ለመውሰድ መድከም የለብንም፤ የአገላለፁ ዓላማ የእግዚአብሔርን ጥበብ በሕያው መልክ ማቅረብ ነው። አዲስ ኪዳን ክርስቶስን ከጥበብ ጋር አያይዞታል፤ ክርስቲያኖችም ይህን ግንኙነት በኋላ ላይ በኢየሱስ በተሟላ መንገድ ተፈጽሞ አይተውቷል። ይህ ግን በምሳሌ 8 ያለው የግጥም ምስል በመጀመሪያ ምን ማለቱ እንደሆነ ከመመርመር አያስቀረንም። Telegram| Facebook | Instagram  | Twitter(X) |Christian e Library

Open in Telegram
Views9,200+10%vs avg
Forwards—
Reactions29
Comments—
#4842Text

ዛሬ ከአንድ ሰው አንድ ቪዲዮ ተልኮልኝ እየተመለከትኩ ነበር! በእስራኤል ሀገር ውስጥ አሁን እየተፈጠረ ያለው ነገር ብዙዎችን በተለይም ክርስቲያኖችን በጣም እያስገረመና እያሳሰበ ይገኛል። ምክንያቱም አንድ እንግዳ ሰው ለጠቅላይ ሚኒስትርነት እየተወዳደረ ሲሆን፣ የሚናገራቸው ነገሮች ከቅዱሳት መጻሕፍት ትንቢቶች ጋር በጣም የተያያዙ ሆነው ተገኝተዋል። ይህ ሰው ስሙ "የሹዋ ቢን ዳዊት" (የኢየሱስ ልጅ ዳዊት) ይባላል። የሚመራው ፓርቲ ስም ደግሞ "ጋን ኤደን"(የኤደን ገነት) ይባላል። ይህ ሰው እራሱን እንደ ኢየሱስ እና እንደ ዳዊት ዘር በመቁጠር፣ እስራኤልን ወደ "ገነት" እንደምትቀየር ቃል እየገባ ይገኛል። የአሁኑን የመንግሥት አወቃቀር ቀይሮ፣ በጥንት ዘመን የነበረውን የሃይማኖት መሪዎች ምክር ቤት(ሳንሄድሪን) እንደገና መመስረት ይፈልጋል። በተጨማሪም፣ በኢየሩሳሌም የሚገኘውን ቤተ መቅደስ መልሶ በመገንባት የካህናት አገልግሎትን ማስጀመር ትልቁ ህልሙ እንደሆነ ጨምሮ ይገልፃል። ሳሳጥረው!፣ ይህ ሰው የኢየሱስን ማንነት ለራሱ በመስጠት ትልቅ ለውጥ ለማምጣት እየሞከረ ነው። ብዙዎች ደግሞ ይህ ሁሉ ነገር የትንቢት ፍጻሜ መቃረቢያ ምልክት ነው ብለው እየተጨነቁና እየተወያዩበት ይገኛል። ቪዲዮው እዚህ ላይ ተያይዟል👉(https://youtu.be/91ThbhfD1J4?is=T5aHl-UmN8y_2tRS) ነገሮች በጣም በፍጥነት እየተቀያየሩ ነው አይደል? እነሆ የምጥ ጣር መጨረሻው ያከተመ ይመስላል! Telegram| Facebook | Instagram  | Twitter(X) |Christian e Library

Open in Telegram
Views9,610+15%vs avg
Forwards—
Reactions32
Comments—
#4839Text

ዛሬ ቀትር ላይ ከአንዲት ኦርቶዶክስ እህት ጋር በቅዱሳን ስዕላት ላይ የከረረ ውይይት አድርገን ነበር። እናም ይህቺ እህት ስዕላቱ ለሃዋሪያቱ ዘመን እጅጉን ቅርብ በነበሩ አመታት እንኳ የተሳሉ ነበሩ ትላለች (የቂሳሪያ ንጉሰ ነገስት የነበረውና የክርስትናን የዕምነት ነፃነት ያወጀው ቆስጠንጢኖስ እንደነበር ይታወቃል እናም የቆስጠንጢኖስ እህትና የክርስትና እምነት ተከታይ  የነበረችው ኮንስታንቲያ የክርስቶስና የጳውሎስ  ምስል ነው ያለችውን ስዕል የቤተ ክርስቲያን አባት ከነበረው ከጳጳሱ አውሴቢዮስ እንዲላክላት በደብዳቤ እንደጠየቀችው የሚገልፅ ታሪክ አለ)እንግዲህ ይህቺ ኦርቶዶክስ እህት የቅዱሳን ስዕላት የቅቡልነት ምንጭ ነው ያለችው ታሪክ ይሄ ነበር። እርግጥ ነው ይህ ይህ የደብዳቤ ጥያቄ ሙሉ እውነት የነበረ ታሪክ ነው ግን ደግሞ ጥያቄው ብቻ የስዕላትን ተቀባይነት እንደ እውነተኛ ምንጭ ተደርጎ ለመወሰድ የአቅም መታጣት ሳይገጥመው አልቀረም፤ ይኸውም! የቤተ ክርስቲያን አባትና የቂሳሪያ ጳጳስ የነበረው የአውሴቢዮስ ምላሽን ጨምራ አልገለፀችም ነበርና😁 እስቲ ምን አለ! አውሴቢዮስ 🗣"እግዚአብሔር በሰማይ ያለውንም ሆነ በታች በምድር ያለውን ምንም አምሳል እንዳይሠራ የሚያዝዝበትን ክፍል ረስተሽ ይሆን? አንቺ ራስሽ በቤተ ክርስቲያን ሰምተሽ ታውቂያለሽን? ወይስ ከሌላ ሰው ሰምተሽ ታውቂያለሽን? እንዲህ ያሉ ነገሮች በዓለም ዙሪያ ካሉ ቤተ ክርስቲያናት ተወግደውና ተከልክለው አይደሉምን? እንዲህ ያሉ ልማዶች ለእኛ ብቻ እንዳልተፈቀዱ የታወቀ አይደለምን?" Eusebius, Epistula ad Constantiam in Nicephorus Hist. eccl. 7.3 PG 20 1545–1548. ለነገሩ ተዉት ኮንስታንቲያ ተብዬዋ ቀንደኛ የአርዮስ ደጋፊም እንደነበረች ከአንዳንድ ቦታዎች ላይ ሰምቻለሁ😉 Telegram| Facebook | Instagram  | Twitter(X) |Christian e Library

Open in Telegram
Views11,500+37%vs avg
Forwards—
Reactions33
Comments—
#4838Text

እስቲ አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ! የማይተዋወቁ ግን ክርስቲያኖች የሆኑ ሁለት ሰዎች በአንድ ስፍራ ነበሩ እንበል በመካከላቸው ደግሞ ሙስሊም የሆነ አንድ ሰውም አለ ብለን እንውሰድ፤ እንግዲህ አንዱ ክርስቲያን ለዚህ ሙስሊም ሰው የእውነትን ቃል እየነገረው ነው፤ እና በመሃል ሌላኛው ክርስቲያን ሰው ሙስሊም አማኝ መስሎ ጣልቃ ይገባል። ከዛን ጥያቄዎችን እያነሳና እየተመለሰለት እንደሆነ እያመነ በጥልቀት ተወያይቶ በመጨረሻም ክርስቶስ አምላክ እንደሆነ በይፋ ሲያምን አሳየ። በዚህ ሁሉ ውስጥ እውነተኛው ሙስሊም ይህን መሳጭና ሳቢ ውይይት አድምጦ ፣ በትክክልም እውነተኛውን የእግዚአብሄር ቃል በሙሉ ልቡ አምኖ ተቀበለ። ክርስታያን ግን ደግሞ ሙስሊም መስሎ ሲወያይ የነበረው ሰው አስመስሎ እውነተኛውን ሙስሊም ወንጌሉን እንዲቀበል መንገድ የጠረገበት መንገድ በከፊልም ይሁን ሙሉ በሙሉ ተገቢ ማለት ነው እንችላለን? እስቲ ሃሳቦቻችሁን ንገሩን! Telegram| Facebook | Instagram  | Twitter(X) |Christian e Library

Open in Telegram
Views11,800+41%vs avg
Forwards—
Reactions28
Comments—
#4837Text

በነገራችን ላይ በስፋት  በወንጌላውያን ፅሁፎች ውስጥ ሲጠቀስ የምንሰማው  "የሰው ልጅ" የሚለው መግለጫ  እንዲሁ በሽልብታና በአጋጣሚ ጨርሶውኑ  የተጠቀስ ቃል አልነበረም፤ እንደውም መግለጫው  ሰዋዊ ማንነቱን ማመልከቱ ነበር ብንል እንኳ ልክ ካለመባል አንተርፍም። "የሰው ልጅ" የሚለው ቃል የጥንታዊያን ወንጌላት ቋንቋ ብቻ አይደለም፤ ይልቁንም ወደ ትንቢተ ዳንኤል ምዕራፍ 7 ስንሄድ፣ የሰማያዊውን መንግሥት ስልጣን የሚረከብ፣ ከሰማይ በደመና የሚመጣ፤ እና ለዘላለም የሚነግስ "የሰው ልጅ"ን እናያለን እንጂ። ይህ ፍጡር ተራ ሰው ብቻ አይደለም፤ እንደውም ከመለኮት ጋር የተያያዘ የክብርና የሥልጣን ባለቤት ነበር። ስለዚህ ኢየሱስ ይህንን ማዕረግ ለራሱ ሲጠቀም፣ እኔ ቀድሞውኑ  ዳንኤል የተናገረው "የሰው ልጅ" ነኝ ማለቱ ነው። ይህ ማለት ኢየሱስ በአንድ በኩል ከእኛ ጋር የሚራራ፣ በምድር ላይ የተገለጠ "ሙሉ ሰው" ሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ ያ የዘላለም የዳንኤል አምላክ መሆኑን በአንድ ጊዜ ማወጁ ነው ማለትም እንችላለን። በእርግጥ አዎ! ይህ ምስጢር ነው ፣ ነገር ግን "ምስጢር" ስል፣ የሰውና የአምላክ ተፈጥሮ በአንድ ሰው ላይ መጣመሩን ማለቴ  እንጂ፣ ይህ አረፋፍዶ ወይም የኋሊት የተፈጠረ ትርጓሜ አልነበረም። በቀረውስ ተባረኩ! Telegram| Facebook | Instagram  | Twitter(X) |Christian e Library

Open in Telegram
Views10,900+30%vs avg
Forwards—
Reactions31
Comments—
#4835Text
Views12,300+47%vs avg
Forwards—
Reactions20
Comments—
#4834Text

በመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች ዘመን ላይ በጣም ዝነኛ ከሆኑ የሮም የህግ ስርአቶች ውስጥ አንዱ "የባሪያ ነፃነት" ማግኛ መንገድ ዋናውና ታዋቂው ነው። ባሪያው ለሮማዊ ጌታው አጅግ ታምኖና ተገዝቶ ከኖረ ምናልባትም ከጌታው የሚቀበለው ውዱ ሽልማት ነፃነቱ ሊሆን ይችላል። በጣም የተለመደው ግን ባሪያው ለጌታው እጅግ ታምኖ ሲገዛ ይከርምና በመጨረሻም በእድሜ ማብቂያ ቀኖቹ ላይ መሞቱ ይሰማል። አንግዲህ የዚህ ምስኪን ባሪያ ሞት የሚመለከተው ጌታውም አይደል? እንግዲያውስ ባሪያው የነበረበትን የእዳ ክምችቶች፣ የክስ ክምችቶችና የቅጣት ክምችቶቹን ህጋዊ በሆነ መንገድ ያቋርጠዋል። እናም ባሪያው ከሞቱ የሚሰጠው ብቸኛ ውለታ ከዚህ ጌታው ህጋዊ በሆነ መንገድ ነፃነቱ እንዲታወጅለት ማድረጉ ላይ ነው። "የሞተ ሰው ከኃጢአት ነጻ ወጥቷል"ሮሜ 6:7" Telegram| Facebook | Instagram  | Twitter(X) |Christian e Library

Open in Telegram
Views13,300+59%vs avg
Forwards—
Reactions36
Comments—
#4833Photo

Forwarded from Her Glow Bar

የመጀመሪያውን 100,000 ብር መቼ ሠራችሁ? 💰✨ እኔ የመጀመሪያዬን 100 ሺህ ብር የሰራውት ያለፈው ዓመት ነው ከምሠራቸው ሥራዎች መካከል በጣም ጥሩ ውጤት ያገኘሁበትና ብዙ ነገር የተማርኩበት ዘርፍ ደግሞ የኦንላይን ቢዝነስ ነው! ዛሬም ብዙ ሰዎች በዚህ ሥራ ገቢ እየፈጠሩ ነው። አሁን የእናንተ ተራ ነው! 🚀 የራሳችሁን ንግድ ለመጀመር እያሰባችሁ ግን ከየት እንደምትጀምሩ ግራ ገብቷችኋል? ኑ፣ አቅጣጫ ላሳያችሁ! ሥራ የምትፈልጉ ወጣቶች፣ ተማሪዎች፣ የቤት እመቤቶች እና ከቅጥር ሥራችሁ በተጨማሪ ገቢ ማግኘት የምትፈልጉ ሁሉ፤ ከዜሮ ጀምራችሁ ኦንላይን ቢዝነስን የተለያዩ እቃዎችን ኦንላይን ላይ ለመሸጥ እንዴት መጀመርና ማስኬድ እንደምትችሉ በተግባር እንማራለን። ባላችሁ የመነሻ ካፒታል ልክ የራሳችሁን ሥራ ለመጀመር የሚያስችላችሁን መንገድ አሳያቹሀለው ምንም መነሻ ብር የለኝም የምትሉም ደግሞ እኔ ጋር ያሉ የተለያዩ እቃዎችን Resell በማድረግ የራሳችሁን ገቢ የምትፈጥሩበትን ሁኔታ አመቻችቼላቿለው። ✨ ትልቅ ለውጥ ለማምጣት ትልቅ ካፒታል ከመጠበቅ ይልቅ፣ በትንሹ ጀምሮ መማርና መሥራት ወሳኝ ነው! 📢 ONLINE BUSINESS CLASS BATCH 6 ምዝገባ ጀምሯል! 📍 ስልጠናው ሙሉ በሙሉ ኦንላይን ነው! ወንድም ሴትም ያላችሁበት ሆናችሁ መማር ትችላላችሁ ትምህርቱም ለ 5 ቀን ይቆያል። 📩 ለምዝገባና ለተጨማሪ መረጃ፦ @SamriiGetu

Open in Telegram
Views11,600+38%vs avg
Forwards—
Reactions30
Comments—
#4832Link preview
Views12,000+43%vs avg
Forwards—
Reactions26
Comments—
#4828Photo
Views10,700+28%vs avg
Forwards—
Reactions14
Comments—
#4826Photo
Views13,000+55%vs avg
Forwards—
Reactions48
Comments—