Forwarded from ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ
+ የሀብት ባርያዎች + ኢኮኖሚያዊ ነጻነት አስፈላጊነቱ የሚያከራክር ባይሆንም ብቻውን ግን የሰውን ልጅ ሙሉ ነጻነቱን ሊሰጠው አይችልም ። የኢክኖሚም ሆነ የፖለቲካ ነጻነት እያላቸው በተግባራቸው ግን ራሳቸውን ለማይረቡ ነገሮች ከማስገዛታቸው የተነሣ የእነዚያ ልማዶቻቸው ባሪያዎች የሆኑ ሰዎች አሉና ። "ሰው ለተሸነፈለት ለእርሱ ተገዝቶ ባርያ ነውና ። " 2ኛ ጴጥ 2፥19 ገጽ 414 እውነት ለመናገር አንዳንዴ ስላለንና ስላገኘን ብቻ ሰዎች ሁሉ መጥፎም እያደረግንም ትክክል እያደረግን እንደሆነ እንዲረዱን እንፈልጋለን ምክንያቱም ደግሞ እየጠቀምኩት ነው እንጂ እየጠቀመን አይደለም የሚል አግባብ ያልሆነ ሀሳብ ስለምንይዝ ግንኙነቶቻችንን ሁሉ ከራስ ቁሳዊ ጥቅም ጋር የተያያዘ የምናደርግ የሚጎለንን ማሰብ እንጂ ያጎደልነውን ሰዎች ያጡብንን ጥሩ ስብእና ማንመለከት ጭፍንነት የተጫነን የበላይነታችን በኪሳችን እንጂ በጭንቅላታችን ያልሆነ ሰዎች አለን ልብ ይስጠን ። "ሀብት ትክክለኛ የሆነ ዋጋ የሚኖረው ለራስ ጥቅም ብቻ ሲውል ሳይሆን የሌሎችን ፍላጎት ለማሟላት ጥቅም ላይ እስከ ዋለ ድረስ ብቻ ነው ። ( ገጽ -412) ገጻቸውን ያስቀምጥኩባቸው ሀሳቦች የተወሰዱት ከሰሞኑን ከወጣው " ቤተክርስቲያን ዘኢትዮጵያ የሥስት ሺህ ዓመት ታሪክ አስተዋጽኦ እና አስተምህሮ በሚል ርዕስ ከተዘጋቸው "ኦርቶዶክሳዊ ነገረ ሰብእ" በሚል ምዕራፍ ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ ያሰፈሩት ነው ። ዲያቆን ፍፁም ከበደ ሕዳር 3 2019 ዓ.ም #ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ
Open in Telegram