የእግዚአብሔርን መልስ ለማግኘት ቅዱስ ቁርባን ይወሰዳል ማለት ነው፡፡ ከዛ በኋላ ችግራችንን ያስወግዳል የሰማይ አባታችን፡፡ 7• ሰባተኛ ስለዘለዓለም ሕይወት ቅዱስ ቁርባን ይወሰዳል፡– ስለምን ይወሰዳል? ስለዘለዓለም ሕይወት፡፡ የዘለዓለም ሕይወት አለህ ማለት ደግሞ ይሄ አጥፊው መንፈስ በሕይወትህ ውስጥ ስፍራ የለውም፡፡ አንተ የዘለዓለም እንጂ የግዜዎች አይደለህም፡፡ ዛሬ በየግዜውራሳችንን እያገለባበጥን፤ ኑሯችንን ሲገለባበጥ፣ ጠባያችንን ሲገለባበጥ፣ ህሊናችንን ሲገለባበጥ፣ አመላችን ሲገለባበጥ፡፡ እንዴት ነው? እየተገለባበጥን እስከ መቸ ነው? ራሳችንን ለማግኘት ለምን አልቻልንም? ሊቆይ የሚችለው ለምን ማግኘት አልቻልንም? የዘለዓለም ሕይወት ከውስጥህ ሲወጣ፤ የሚጠብቅህ ነገር ቢኖር እንዲሁ ትርኪ ሚርኪ የሆነ የመንደር ኑሮ ነው፡፡ የመንደር ኑሮ፤ የግዜ ኑሮ፤ የሰዓት ኑሮ፡፡ ግዜዎች ሲወድቁ አብረህ ትወድቃለህ፤ ግዜዎች ሲጠፉ አብረህ ትጠፋለህ፤ ግዜዎች ሲያርፉ አብረህ ታርፋለህ፤ ግዜዎች ሲሰደዱ አብረህ ትሰደዳለህ፡፡ እንዴት ይሆናል ይሄ? ክርስትያኖች በሰማይ አምላክ ዘንድ ባለ በዘለዓለማዊ ሕይወት መያዝ አለባቸው፡፡ እና ስለ ዘለዓለማዊ ሕይወት ቅዱስ ቁርባን ይወሰዳል ማለት ነው፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አስጀምሮ ላስፈጸመን የሰማዩ አባት ልዑል እግዚአብሔር ክብርና ምስጋና ይግባው አሜን። የእግዚአብሔር ምኅረት ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡ "የሰላምም አምላክ ሰይጣንን ከእግራችሁ በታች ፈጥኖ ይቀጠቅጠዋል። የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።" (ወደ ሮሜ ሰዎች 16: ፥20)። መልካም የነቢያት ጾም ይሁንልን። አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ
Open in TelegramPosts of አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ
የቅዱስ ቁርባን 7 ጥቅሞች 1. አንደኛ ኃጢያትን ለማስተሰረይ፡– ኃጢያት ተሰረየ ማለት ካንተና ከልጆችህ፤ ከቤትና ከኑሮህ፤ ከታሪክህና ከዘመንህ ሁሉ ተወገደ ማለት ነው፡፡ ኃጢያት ተሰረየ ማለት በሚቀጥለው ዘመን ላይ ሊያደርስ የሚችለው ጉዳትና እንቅፋት ቆመ ማለት ነው፡፡ የዲያብሎስ ሽምቅ ውግያና ስልቱ ሁሉ በሕይወትህ ያዘጋጀው መዝገብ ፈረሰ ማለት ነው፡፡ 2. ሁለተኛ የኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር ለሕይወታችን አስፈላጊነት፡– ሁለተኛ እና በጣም ትልቁ በሕይወታችን ውስጥ ፍቅር እንዲኖር የክርስቶስ ሥጋና ደም ያስፈልገናል፡፡ ፍቅር እንዲኖር፡፡ እግዚአብሔር ፍቅር ነው የሚል ቃል በዮሐንስ መልዕክት ላይ ታገኛለችሁ፡፡ እግዚአብሔር ምንድ ነው? ፍቅር ነው፡፡ ታድያ ከእርሱ ጋር እርቅ ሳናደርግ፤ በሰውነታችን ውስጥ ስፍራ ሳይይዝ፤ በባህሪያችን ውስጥ ሳይገባ፤ በሚስጥረ መለኮት የሰጠው ሥጋና ደሙን ሳንቀበል አሁን ከዚህ ትውልድ ፍቅር ይጠበቃል ወይ? እንዴት ይሆናል? እግዚአብሔር ፍቅር ነው፡፡ ፍቅር ሲጠፋ የክርስቶስ ሥጋና ደም ያስፈልገናል፡፡ እንዲህ ብለን ወደሱ እንጠጋለን "አቤቱ ጌታ ሆይ ፍቅር ከህይወቴ ጠፍቷል፡፡" እግዚአብሔር ፍቅር ነው፡፡ ንቁ የሚለው በዚህም ጭምር ላይ ነው፡፡ ከቤተሰብህ ፍቅር ሲጠፋ <ጌታ ሆይ ፍቅር ሁነኝ> ማለት አለብህ፡፡ "በውስጤ ውስጥ እደር ባህርያቴን ለውጠው፤ ሰማያዊ የሆነ ስጦታህን አካፍለኝ፤ የቸርነትህ ጸጋ ከኔ ጋር ይሁን፤ ሁሉ ግዜ በሃሳብህ ባርከኝ፤ ፍቅርህ ከሁሉ በላይ የሕይወቴ ፈር ይሁን" ብለህ ቅዱስ ቁርባን ስትወስድ ፍቅሩን ይመልስልሃል፡፡ በፍቅርህ ውስጥ ጠላት የሆነውን ኃይል ከሕይወትህ ያስወግደዋል፡፡ በዚህ ግዜ እንግዲህ ለአገርህም፣፡ለወገንህም፣ ለህዝብህም፣ ለጎረቤትህም፣ ለጠባይህም፣ ለቤትህም፣ ለገንዘብህም ፍቅር ትሆናለህ ማለት ነው፡፡ ገንዘብ አንተ አፍቅረኸው ሳይሆን ገንዘብ አንተን አፍቅሮ ወደ አንተ ይመጣል፡፡ ኑሮ አንተ አፍቅረኸው ሳይሆን ኑሮ አንተን አፍቅሮ ወደ አንተ ይመጣል፡፡ እንጀራ አንተ ወደኸው ሳይሆን እንጀራው አንተን ወዶ ወደ አንተ ይመጣል፡፡ ግዜ አንተ ወደኸው፤ አንተ አቅደኸው ሳይሆን ግዜው አንተን ለመርዳት ወደ አንተ ይመጣል፡፡ በእያንዳንዱ ግንኝነቶችም ውስጥ ሰማያዊ ፍቅር እስካለህ ድረስ ተፈጥሮዎች ያገለግሉሃል፡፡ እግዚአብሔር ስሙ የተመሰገነ ይሁን፡፡ እግዚአብሔር ፍቅር ነው፡፡ 3. ሦስተኛ ቅዱስ ቁርባን የሚያስፈልገን ሰውነታችን ሲከብደን ነው፡– ሰውነት ሲከብድ፤ መጫን ሲጀምር፤ ውስጣዊ ህይወትህ መረጋጋት ሲያቅተው በዚህ ጊዜ ማቴዎስ ወንጌል ላይ የተናገረው ቃል ትዝ ሊለን ይገባል፡፡ የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 11 መጨረሻው ላይ እንዲህ ይላል ‹‹እናንተ ሸክም የከበዳችሁ ወደኔ ኑ››፡፡ ምን የከበዳችሁ? ሸክም፡፡ የግዜ ሸክም፣ የኑሮ ሸክም፣ የትውልድ ሸክም፣ የዓመታትን ሸክም፡፡ ስንት ዓመታቶች አልፈው፤ ዛሬ እየከበደን እየከበደን የመጣውን ሸክማችንን ማን ይቻለው? እኛ ነን የምችለው? ምድሪቱ ነች የምትችለው? ኑሯችን ነው የሚችለው? ገንዘባችን ነው የሚችለው? ማን ነው የሚችለው?በእርግጥ ተናገሩ ብንባል የፈጠረን አምላክ ይችልልናል ነው የምንለው፡፡ በእውነታና በሕይወት ውስጥ ባለው ትርጉም ውስጥ ግን የሚታይ ምላሽ የለንም፡፡ ስለዚህ በሸለቆ ውስጥ ሆነን ሰማያዊ ነገር አልታይ አለን፡፡ ሲከብደን ቅዱስ ቁርባን ያስፈልገናል፡፡ ምን ማለት ነው እንግዲህ? ሸክም ማራቅያ ነው ማለት ነው፡፡ 4. አራተኛ በረከት ከሕይወታችን ሲጠፋ፡– በረከት ከሕይወታችን ሲጠፋ የበረከት አምላክ ሕይወታችንና ኑሯችን ውስጥ እንዲኖር ቅዱስ ቁርባን ያስፈልገናል፡፡ በረከት ከምናችን ሲጠፋ? ከህይወታችን፣ ከኑሯችንና ከቤተሰባችን ሲጠፋ፡፡ ያኔ አንድ ነገር ገብተዋል ማለት ነው፡፡ የበረከት ጠላት በዙሪያችን አለ ማለት ነው፡፡ እንኪያሳ በበረከት ጎዳና ውስጥ እንጀራን ለብዙ ሺ ህዝብ የመገበ አምላክ ለኛም ሊሰጠን እንደሚችል ልቦናችን ማሳመን መቻል አለብን፡፡ ስለዚህ "ጌታ ሆይ አንተ የበረከት ንጉሥ ነህ የጎደለውን በረከቴ አንተ ሙላልኝ፤ የበረከት ጠላትን ኃይል አርቅልኝ" ብለን እሱ ተማፅነን ቅዱስ ቁርባን ስንወስድ በረከታችን ይመለሳል፡፡ 5• አምስተኛ መልካምና ጥሩ ዘር ለማግኘት፡– መልካም ትውልድ ለማፍራት ቅዱስ ቁርባን ያስፈልጋል፡፡ መልካም ትውልድ፤ የእግዚአብሔር የሆነ ትውልድ፤ የሰማይ አምላክ የሆነ ትውልድ፡፡ ዛሬ በአብዛኛው ከዚህ መንፈሳዊ በረከት ርቆ የተወለደው ቃልቻ ሆነ፤ ጠንቋይ ሆነ፤ መተተኛ ሆነ፡፡ ከዛም ደግሞ አልፎ ተርፎ እንዲሁም የተወለደው የመተተኞች፣ የአስማተኞች መንፈስ መኖርያ ሆነ፤ የዛርና የውቃቤ መጫወቻ ሆነ፤ የክፉ ባህርይና የክፉ ጠባይ መጫወቻ ሆነ፡፡ ይህ ሁሉ ከቤተሰብ መንፈሳዊ ትከሻ አንፃር ያለው ጉዳት ነው፡፡ አብዛኛው ወላጅ እያወረስን ያለው ሰማያዊ ነገርን ሳይሆን፤ ሰማያዊ ስጦታ ሳይሆን፤ ክፉውን ነው የምናወርሰው፡፡ ይህንን ውርስ ለመከላከል ለልጆች ቅዱስ ቁርባን ሊወሰድላቸው ይገባል፡፡ በሁለት አይነት መንገድ፦ ♦ አንደኛ ከመወለዳቸው በፊት ቤተሰቦች ቅዱስ ቁርባን ለሚወለዱት ገና ለሚፀነሱት አስበው ቅዱስ ቁርባን መውሰድ አለባቸው፡፡ ☞ ክፉ መንፈስ አብሯቸው ከማኅጸን ጀምሮ እንዳይወለድ ♦ሁለተኛ ከተወለዱ በኋላ ለልጆቻቸው ቅዱስ ቁርባን መውሰድ የሕይወት መርሃቸው ማድረግ አለባቸው፡፡ ☞ ሕይወታቸውን ከማለዳው ክርስቶስ እንዲመራው። 6• ስድስተኛ ቅዱስ ቁርባን የሚወሰደው የእግዚአብሔርን መልስ ስንፈልግ ፡- ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ስትጀምሩ በፍጹም ከሰው ልጅ ጠባይና ባህሪይ ጋር አትስማሙም፡፡ ስለዚህ ብቸኝነት ይሰማቹሃል፡፡ በዚህ ግዜ "ጌታ ሆይ ዓለሙ ከኔ ሸሽተዋል አንተ ከእኔ ጋር ሁን" ማለት እንጀምራለን፡፡ ልክ በዚህ ወቅት የሕይወት ደስታ እና እርካታ አንድ ሺህ ሰው ከከበበን ይልቅ ለብቻችን ከክርስቶስ ጋር የምንኖረው ኑሮ ያረካል፡፡ ያ አንድ ሺህ ሰው ቢከብህ እየተቸ፤ በጎሪጥ አፉን እያጣመመ፤ ዓይኑን እያጨነቆረ ነው የሚያይህ፡፡ እግዚአብሔር ግን በብቸኝነት ውስጥ ብርሃን ይሰጥሃል፡፡ ይሄ ነው የሱ ልዩ ሞገስ፡፡ መልሱንም በራእይ ወይም በህልም ስንጠብቅ ተገቢ በሆነ ጊዜና ሰዓት እግዚአብሔር ይሰጠናል፡፡ ውስጣችን መቀደስ ሲጀምር ከውጪ ያለውን እግዚአብሔር መሪ ይሆናል ማለት ነው፡፡ እያሱ ህዝቡን ሲመራ፤ በመጽሐፈ እያሱ ምዕራፍ አንድ ላይ አንድ ታላቅ ድምፅ እንሰማለን እንዲህ ሲል ‹‹በሕይወትህ ዘመን ሁሉ ማንም አይቋቋምህም እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፡፡›› በቃ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ ማንም አይቋቋምህም እኔ ከአንተ ጋር ነኝ የሚለውን ድምፅ የሰማው ማን ነው? እያሱ ነው፡፡ የእስራኤልን ህዝብ ወደ ምድረ ርስት ለመውሰድ በሚያደርገው ጉዞ ውስ፤ የርስት ባለቤቶች እንዲሆኑ ለማድረግ ባደረገው ጉዞ ውስጥ፤ ማንም አይቋቋምህም የሚለውን ድምፅ በሕይወቱ ውስጥ እግዚአብሔር ሰጠው፡፡ እኛ የምንወርሰው ነገር አሁን ምን አለ?፡፡ በመሠረቱ እኮ የእግዚአብሔር ህዝብ መስጠት እንጂ፤ እየሰጠ የሚሄድ እንጂ እያጣ፤ እየደኸየ የሚሄድ አይደለም፡፡ እኛ ግን እያጣን፤ እየደኸየን መጣን፡፡ ውስጣችን መጀመርያ እግዚአብሔርን አጣ፡፡ ከዛ በኋላ በዓለም ላይ ባለው ነገር ላይ ምንም ባለቤትነትን አጣን፡፡ ለማንኛውም ነገር ቅጥረኞች ሆንን፡፡ ከሁሉም ደግሞ የሚገርመው እንጀራ በባህሪው ከነክፋቱ፤ ከነተንኮሉ፤ ከነምቀኝነቱ ገዛን፡፡ እግዚአብሔር የሌለበት ስፍራ እንዲህ ይሆናል፡፡ እና ሲከብደን፣ ሲጫነን፤ በአከባቢ፣ በጎረቤት፣ በሀገር ሁሉ ላይ ችግሮች ሲመጡ፤
Open in Telegram38ኛ ዙር እየተቆረጠ ነው። 1ኛ እጣ በገና 2ኛ እጣ የጸሎት መጽሐፍ ነው ያልተያዙ ቁጥሮች 10 15 17 20 33-35 37 39-43 45 46 48-56 58-60 60 ሰው በ200 ብር Awash👉🏦 013200909837300 CBE👉🏦 1000145090176 BOA👉🏦 47056497 ዳሽን ባንክ👉 5085757192011 Tele birr👉🏦 0933143133 አቤኔዘር ገዛኸኝ ስም ስልክ ሪሲት እጣ ቁጥር t.me/abigezenige ላይ ይላኩ t.me/abizeeotcwin join ይደረግ
Open in Telegramማታ ፆም ስንይዝ በልተን ያስተረፍነውን ስጋ ወጥ ጠዋት ከእንቅልፌ ስነቃ እህቴ አሙቃ ልተበላው ስትል ተገጣጠምን ምን እየሆንሽ ነው ልበላው ነዋ ፆም ገብቷልኮ ያምሻል??ስላት እህቴ መልሳ ሳቅ ብላ ይህ ምግብ ማታ በክብር ተበልቷል ዛሬ አንድ ለሊት በማደሩ ግን ማንም ሰው ቢቀርብለት አይበላውም ምክንያቱ ደሞ ፆም ነው!!ፆም አንድም የትላንት ምግባችንን ብቻ ሳይሆን የትላንት የማይመጥኑንን የተሳሳቱ የጎደፉ ማንነታችንን ጭምር መተው ማለት ነው!!ቀድሞውንም የምትለኝን ለማየት እንጂ ልበላው አልነበረም አስተውል ፆም ሲገባ የፆም ምግብ እንዳለ ከቤት ይወጣል የምግብ እቃ የሆነ ሁሉ ይታጠባል ይህንን ወደ እራሳችን ስንቀይረው በሀጥያት የደከመች ስጋችን ሀጥያቶቿን ልክ እንደ ፆም ምግብ አውጥታ ታስወግዳለች ያልታጠበ ሰሀን እንደማይበላበት ሁሉ እኛም ቀድመን በንሰሐ ታጥበን እንቀርባለን በል እኔ እቃውን እስካጣጥብ ተዘጋጅተህ ጠብቀኝ ቤተክርስትያን እንሄዳለን አለቺኝ ልወቅሳት የተነሳሁትን በሚስጥር ቋጥራ አስተምራ መለሰቺኝ ፆም ገብቷል እኛ ከህጉ እንዳንወጣ እግዚአብሔር ይርዳን
Open in Telegramበሕዳር ወር ያሉ የ አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ጉዞዎች ሕዳር 19 ዘብር ገብርኤል ሕዳር 20 ጊሺ ክርስቶስ ሰምራ (ሰሚነሽ ኪዳነምህረት) ሕዳር 21 አዳዲ ማርያም (ጻድቃኔ ማርያም) ሕዳር 29 ሳፈጅ እጨጌ ዮሐንስ ለተጨማሪ መረጃ +251933143133 ይደውሉ። የሁሉም ጉዞ መነሻ ጠዋት 11:30 አዲስአበባ መገናኛ (መስቀል አደባባይ) ነው።
Open in Telegramአቤኔዘር እባላለሁ ያው አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ 🤗 ይህ ፎቶዬ 4ኛ ክፍል ተማሪ ሆኜ የተነሳሁት ነው። ከጀርባ ያለው ቆርቆሮ "እድገት ወላጆቻቸውን ላጡና ለችግር የተጋለጡ ሕጻናት መርጃ ማኅበር" ጊቢ ነው። በዚህ ድርጅት ከ4ኛ ክፍል ጀምሮ ዩኒቨርስቲ ተምሬ እስካጠናቅቅ ድረስ ቆይታ አድርጌያለሁ። በቆይታዬም ከድርጅቱ የትምህርት ቁሳቁስ ያሟላልኝ እና የትምህርት ክፍያዎችን ይከፍልልኝ ነበር፥ እንዲሁም በበዓላት ወቅት አዳዲስ ልብሰና ጫማም ይሰጠናል፥ ከሰኞ እስከ አርብ ምሳ የተለያየ አይነት ምግብም ይመግበን ነበር፥ የመዝናኛ ቦታዎች ይወስደን ነበር፥ የሕክምና ወጪ ይሸፍናል በተለይ ለእኔ ጽድት ያሉ ክራንቾችን ከእንግሊዝ ሀገር ያስመጣልኝ ነበር። ያው በወቅቱ በዚያ ድርጅት ክራንች የሚያስፈልገኝ እኔ ብቻ ስለነበርኩ፤ የድርጅቱ ስፖንሰር አብዛኞቹ በእንግሊዝ ሀገር የሚኖሩ የውጪ ሀገር ዜጎች ናቸው። ድርጅቱ ከ300 በላይ ሕጻናትን አሁንም ድረስ ይዞ እየረዳ ይገኛል። የድርጅቱ አድራሻ አ/አ/ክ/ከ/ል/ወ/3 አብነት አካባቢ ይገኛል። ለአቤኔዘር ዘተዋሕዶ የመኪና ግዢ ቻሌንጅ እንደቀጠለ ነው። እግዚአብሔር ቢፈቅድ በቀጣይ ቀናት live በመግባት የገንዘብ ማሰባሰብ መርሐግብር አከናውናለሁ። 3ሺ የአቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ ቤተሰብ 1ሺ ብር ቢያግዘኝ መኪና እገዛና ራሴንም ቤተሰቤንም ስራ እየሰራሁ ለማገዝ አስቤያለሁ። በአቅማችሁ ድጋፍ በማድረግ ከጎኔ መቆም ለምትፈልጉ፦ * የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE): 1000 510 909 635 * (Telebirr): [+251933143133] የባንክ አካውንት ስም: አቤኔዘር ገዛኸኝ ስሜ Abenezer Gezahegn Sime My name is Abenezer—yes, the one from the "Abenezer Ze-Tewahido" page! 🤗 This photo was taken when I was a 4th-grade student. The corrugated iron structure in the background belongs to the compound of "Idget" (Progress)—an association that supports children who have lost their parents or are facing hardship. I remained with this organization from the 4th grade all the way through to the completion of my university studies. During my time there, they provided all my educational materials and covered my tuition fees. They also gave us new clothes and shoes for holidays, provided various types of lunch from Monday to Friday, took us to recreational spots, and covered our medical expenses. In my case, they even imported high-quality crutches for me all the way from England—at the time, I was the only child in the organization who needed them. Most of the organization’s sponsors are foreign nationals living in England. To this day, the organization continues to support over 300 children. It is located in Addis Ababa, Sub-city 3 (Lideta), in the Abinet area. The fundraising challenge to purchase a vehicle for "Abenezer Ze-Tewahido" is still ongoing. God willing, I will host a live session in the coming days to continue the fundraising efforts. If the 3,000 members of the "Abenezer ZeTewahido" community could each contribute 1,000 Birr, I plan to purchase a vehicle. This would enable me to work and, in turn, support both myself and my family. For those who would like to stand by me by providing support according to your means: * Commercial Bank of Ethiopia (CBE): 1000 510 909 635 * Telebirr: 093 314 3133 Account Name: Abenezer Gezahegn Sime አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ @topfans
Open in Telegramበገና በ200 ብር ብቻ ይሸለሙ። 38ኛ ዙር እጣ 10 13 15 17 20 33 34 35 37 39-43 45 46 48-56 58 59 60 60 ሰው በ200 ብር Awash👉🏦 013200909837300 CBE👉🏦 1000145090176 BOA👉🏦 47056497 ዳሽን ባንክ👉 5085757192011 Tele birr👉🏦 0933143133 አቤኔዘር ገዛኸኝ ስም ስልክ ሪሲት እጣ ቁጥር t.me/abigezenige ላይ ይላኩ t.me/abizeeotcwin join ይደረግ
Open in Telegramይህ ከታች የሚታየው ፎቶዬ በአንድ ወቅት ኩክየለሽ ማርያም ገዳም ሆኜ ለማስታወሻ የተነሳሁት ፎቶ ነው። በሕይወቴ በጣም ደስ ከተሰኘሁባቸው ገዳማት አንዱና የማላወዳድረው ነው። በክራንች ታግዤ ደረጃውን ስወጣና ስወርድ ከላብ ማላብ በስተቀር በሰዓቱ ምንም የድካም ስሜት አልተሰማኝም ነበር። የፊቴ ላብ ግን ከየት እንደመጣ ባላውቅም 😃 ለማንኛውም ለ አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ የመኪና ግዢ ቻሌንጅ 3ሺ ሰው 1ሺ ብር ይሳተፉ። የሚል መርሐግብር እንደቀጠልኩ ነው እስካሁን 100ሺ ብር አካባቢ ነው ያገኘሁት። 3ሺ የፌስቡክ ቤተሰብ የለኝም ወይ?😓 ከ375ሺ ሰው 3ሺ ሰው እጅግ በጣም ትንሽ ነው ግን ከተባበርን ይሆናል በሚል ነው። * የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE): 1000 510 909 635 * (Telebirr): [+251933143133] የባንክ አካውንት ስም: አቤኔዘር ገዛኸኝ ስሜ Abenezer Gezahegn Sime
Open in Telegram41 ጊዜ የሚሰገድ የንስሐ ስግደት share ይደረግ። ስለ ቅድስት ልደታ ብለህ ማረን ስለ አባ ጉባ ብለህ ማረን ስለ ቅዱስ ፋኑኤል ብለህ ማረን ስለ ወንጌላዊው ዮሐንስ ብለህ ማረን ስለ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ብለህ ማረን ጌታ ኢየሱስ ሆይ ማረን ሥላሴ ሆይ ማረን ስለ አቡነ ኪሮስ ብለህ ማረን ስለ አቡነ እስትንፋ ክርስቶስ ብለህ ማረን ስለ ቅድስት እሌኒ ብለህ ማረን ስለ ቅዱስ ያሬድ ብለህ ማረን ስለ ቅዱስ ሚካኤል ብለህ ማረን እግዚአብሔር አብ ሆይ ማረን ስለ አቡነ አረጋዊ ብለህ ማረን ስለ ቅዱስ ቂርቆስ ብለህ ማረን ስለ ቅድስት ኪዳነምህረት ብለህ ማረን ስለ ቅዱስ እስጢፋኖስ ብለህ ማረን ስለ ጸበለ ማርያም ብለህ ማረን ስለ ቅዱስ ገብርኤል ብለህ ማረን ስለ ቅድስት ቤተክርስቲያን ብለህ ማረን ስለ ድንግል ማርያም ብለህ ማረን ስለ ቅዱስ ዑራኤል ብለህ ማረን ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ብለህ ማረን ስለ አቡነ ተክለሃይማኖት ብለህ ማረን ስለ ቅዱስ መርቆሬዎስ ብለህ ማረን ስለ አቡነ ሐብተ ማርያም ብለህ ማረን መድኃኔዓለም ሆይ ማረን አማኑኤል ሆይ ማረን በዓለ ወልድ ሆይ ማረን ስለ መጥምቁ ዮሐንስ ብለህ ማረን ስለ ቅዱስ ራጉኤል ብለህ ማረን ስለ ቅድስት አርሴማ ብለህ ማረን ስለ ወንጌላዊው ዮሐንስ ብለህ ማረን ስለ ቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ብለህ ማረን ስለ ጻድቁ አብርሃም ብለህ ማረን ስለ አቡነ ዘርዓብሩክ ብለህ ማረን ስለ አምስቱ የእመቤታችን ሀዘናት ብለህ ማረን ስለ መላእክቱ ብለህ ማረን ስለ ቅዱሳኑ ብለህ ማረን ስለ ጻድቃን ሰማዕታቱ ብለህ ማረን ስለ ሐዋርያቱ ብለህ ማረን አሜን አቡነ ዘበሰማያት በሰላመ ገብርኤል አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ @abizeeotc
Open in Telegram6. ምሥጢረ ቀንዲል ይህ ቃል የላቲን ቋንቋ ነው ትርጉሙም ፍፁም መብራት ማለት ነው፡፡ ከሰባቱ ሚስራት አንዱ ቀንዲል ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን ዘይት የፈውስ ምልክት ነው፡፡ በደዌ ዳኛ በአልጋ ቁራኛ ተይዘው የሚሰቃዩ ህሙማን ወይም በድንገተኛ አጋጣሚ የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ቁስለኞች እየተቀቡ ይፈወሱ ነበር፡፡ ኢሳ 1፡6 ሉቃ 10፡34 ራዕ 3፡18 ማር 6፡13 ይህ ቅብዓተ በሐዲስ ኪዳን ለሚጠመቁ ከሚደረግ ቅብዐ ሜሮን ጋር ግንኙነት የለውም ራሱን የቻለ ሕሙማነ ሥጋ ብቻ ሳይሆን ሕሙማነ ነፍስ ኃጥአን የሚቀቡት ፈውስ የሚያገኙበት ነው፡፡ ማር 6፡13 ያዕ 5፡13-15 ራዕ 1፡17፡፡ 7. ምሥጢረ ተክሊል ይህ ማለት “ተከለለ” ተቀናጀ ከሚለው የግዕዝ ግስ የተገኘ ነው፡፡ በሥርዓተ ጋብቻ ቅደም ተከተል መሰረት በመተጫጨት እና በቃል ኪዳን የተመሰረተ ጋብቻ በተክሊል ይፈጸማል፡፡ ቤተክርስቲያን ምስክርነት የሚፈጸመው ጸጋ መንፈስ ቅዱስን የሚያሰጥ ስለሆነ ነው፡፡ ክርስቲያናዊ ጋብቻ ትክክለኛነቱም የሚታወቀው በተክሊል ሥጋወ ደሙ ሲፈጸም ነው፡፡ ክርስቲያናዊ ጋብቻ ትክክለኛነቱም የሚታወቀው በትክሊል ሥጋወ ደሙ ሲፈጸም ነው፡፡ ዘፍ 1፡27-28 ፣ 2-18 ማቴ 19-4 እነዚህን ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን አውቀን ተረድተን የእምነታችን ፍጻሜ የሆነውን አምላካችንን ለተፈጠርንለት ዓላማ በመገዛት የነፍሳችንን መዳን ልናረጋግጥ ይገባል፡፡ ለዚህም ቸሩ አምላካችን እግዚአብሔር እንዲረዳን የወላዲተ አማላክ አማላጅነት እንዳይለየን የጻድቃን ፀሎት የቅዱሳን በረከት እንዳይለየን ፈቃዱ ይሁንልን አሜን!!! ይቆየን አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ
Open in Telegramሰባቱ ምስጢራተ ቤተ ክርስቲያን ምሥጢር ማለት ቃሉ የግሪክ ቋንቋ ሆኖ ቃሉ ከግዕዝና ከአማርኛ በቀጥታ የተወረሰ ሲሆን ትርጉሙም ድብቅ ፣ ስውር፣ ሽሽግ፣ ረቂቅ ፣ ለቅርብ ዘመድ ካልሆነ በቀር የማይገለጥ ማለት ነው፡፡ ለሁለት የሚከፈል ሲሆን ይኸውም የፍጡር ሚሥጢርና የፈጣሪ ሚስጥር በመባል ይታወቃል፡፡ የፍጡር ምስጢር ሁለት ይዘት አለው፡፡ የሰውና የመላዕክት ምስጢር ይባላል፡፡ በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚገኘው የፈጣሪ የእግዚአብሔር ሚስጥር ይህ የከበረ የተወደደ የሚናፈቅ የበረከት ስጦታ ነው፡፡ ብርሃነ አለም ሀዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ እንዲህ ሲል በከበረ ቃሉ ገልፆታል፡፡ “እርሱንም ሳታዩት ትወዱታላችሁ አሁንም ምንም ባታዩት በእርሱ /በክርስቶስ/ አምናችሁ የእምነታችሁን ፍጻሜ እርሱን የነብሳችሁን መዳን እየተቀበላችሁ በማይናገርና ክብር በሞላበት ሀሴት ደስ ይበላችሁ”፡፡ በማለት ስውር ረቂቅ ከሆነው ጸጋ እግዚአብሔር የምንሰጠው ሀብት መሆኑን በማብራራት ገልፆታል፡፡ በዚህ መሰረት በቤተክርስቲያናችን ውስጥ ከሚፈጸሙት ሚስጥራት በቁጥር 7 ተወስነው ተቀምጠዋል፡፡ ውሳኔነታቸው ለሰባቱ ሰማያት ስብዐተ እግዚአብሔር ለማይከፈልባቸው ከተሞች ገላጭ ናቸው፡፡ እነዚህ ሰባት ሚስጥራት ቤተክርስቲያን የሚስጥርነታቸው ምክንያት በአይናችን ልናያቸው በእጃችን ልንዳስሳቸው የማንችል ልዩ ልዩ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች በእነዚህ ሚስጥራት አማካኝነት የሚሰጡን ስለሆነ ነው፡፡ አበው ሲናገሩ በንባብ የተሰወረ ብሂል ምስጢር ይባላል ብለው ስውርነቱን ረቂቅነቱን ይናገራሉ፡፡ ሰባቱ ሚስጥራተ ቤተክርስቲያን የሚባሉት እንደሚከተለው ይዘረዘራሉ፡፡ 1. ጥምቀት 2. ሜሮን 3. ቁርባን 4. ክህነት 5. ንስሀ 6. ቀንዲል 7. ተክሊል ናቸው፡፡ በዝርዝር እንመልከታቸው፥ ሼር ያድርጉት! 1. ሚስጢረ ጥምቀት ይህ ምሥጢረ ጥምቀት ከኃጢያት ነፃ የምንሆንበት ከዲያቢሎስ አገዛዝ አርነት የምንወጣበት ከእግዚአብሔር በጸጋ የምንወለድበት የምስጢር አይነት ነው፡፡ በቅሰዱሳት መጻህፍት እንደተገለጸው በነብየ እግዚአብሔር በቅዱስ ሕዝቅሌል ት.ሕዝ 36፡25 “ጥሩ ውሀንም ጥምቀትን እረጫችኋለሁ፡ እናንትም ትጠራላችሁ ከርኩስነታችሁም ሁሉ ከጣኦቶቻችሁ ሁሉ አጠራችኋለሁ አዲስ ልብ እሰጣችኋለው” በማለት የዚህን ምስጢር ክብርነት በረከትነት አምልቶ አስፍቶ ተናገሯል፡፡ በዚህ ሀሳብ ሌሎች ንፁሐን አበው ሀዋርያት ተባብረውታል፡፡ በምልአት ሰብከውታል፡፡ የሐዋ.2፡38 ፣ 1ቆሮ 6፡11 ፣ ዮሐ. 3፡5 ፣ ኤፌ 5፡26 ፣ ገላ 3፡27 ፣ ቲቶ 3፡5 ጥምቀት ዳግመኛ ተወልደን ወደ እግዚአብሔር መንግስት የምንገባበት ምስጢር ነው፡፡ ከመጸሕፍ ቅዱስ ውስጥ ጥምቀት ብዙ ምሳሌዎች ይኖሩታል፡፡ እነሆ ከማየአይኅ የዳነበትን መርከብ ቅዱስ ጴጥሮስ የጥምቀት ምሳሌ እንደሆነ ገልጾታል፡፡ 1ኛ ጴጥሮስ 3፡21 ምዕመናን ከሐጢያት ከጥፋት የሚድኑት በጥምቀት ነውና ቅዱስ ጳውሎስም እስራኤል ከግብጽ የባርነት ቀንበር ተላቀው የኤርትራን ባህር ተሻግረው ወደምድረ ርስት ያደረጉትን ጉዞ የጥምቀትን ምሳሌ አድርጎ አመስጥሮታል፡፡ 1ኛ ቆሮ 10፡1-2 ምዕመናን ባህረ ኃጢያትን ተሻግረው ምድረ ርስተ መንግስተ ሰማያትን የሚወርሱት በጥምቀት ነውና፡፡ ዳግመኛም ይህ ብርሃናዊ ሐዋርያ ጥምቀትን በሞትና በመቃብር ይመስለዋል፡፡ ሮሜ 6፡3-4 ቆላ 2፡12 በሞት ጊዜ ነፍስና ስጋ እንደሚለያዩ በጥምቀትም አሮጌው ሰውነት ይሞታል ይቀበራል አዲስ ሰውነት አዲስ ሕልውናን ይጀምራልና፡፡ 2. ምስጢረ ሜሮን ይህ ቃል የጽርዕ ቋንቋ ነው ትርጉሙም መአዛ ያለው የሚያውድ ፣ የሚጣፍጥ፣ ልብ የሚመስጥ ፣ ጣዕም ያለው መልኩ ጽርየቱ ዘይት ነው፡፡ በግዕዝ ቅብዕ፣ ቅብዐ ሜሮን ይባላል፡፡ ከብዙ እጽዋት ተቀምሞ የሚሰራ ነው፡፡ ሕዝበ እስራኤልን የሚያስተዳድሩ የእግዚያብሔር እንደራሴዎች ነገስታትን መሲሀን የሚባሉት ለዚህ ቅብ ተቀብተው ስለሚነግሱ ነው፡፡ ዘፍ 20፡23 1ኛ ሳሙ 10፡1 ዘዳ 28፡41 1ኛ ሳሙ 9፡6 1ኛ ነገስት 1፡34 ይህ ብቻ አይደለም እግዚአብሔር የሚገለገልባቸው የቤተመቅደስ ነዋያተ ቅድሳትን አስቀድሞ በዚህ መታተም አለባቸው፡፡ ከተቀቡ በኋላ ለቤተ መቅደስ እንጂ ለተራ አገልግሎት አይውሉም ስለ ቅብዐ ሜሮን ቅዱስ መጽሐፍን የፃፉ ሰዎች የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ ቅብዐት ይሉታል፡፡ 2ኛ ቆሮ 1፡21 ዮሐ 2፡20 ቅብዕን በመንፈስ ቅዱስ ማህተምን ይሉታል፡፡ ኤፊ 1፡13 ፣4፡30 ይህ ቅብዓ ማህተመ ሕይወት በመሆኑ ለአገልግሎት ይውላል፡፡ 3. ምሥጢረ ቁርባን ይህ ቃል የሱርስት ቃል ነው፡፡ ትርጉሙም አምኃ ስጦታ ማለት ነው፡፡ ሥጋውና ደሙ የተሰጠን በነፃ ያለ ዋጋ ሳይገባን በችሮታ ነውና፡፡ በቤተክርስቲያን ምሥጢራት ሁሉ መደምደሚ ቅዱስ ቁርባን ነው፡፡ መስዋዕት ማቅረብ የተጀመረው በአዳም ጊዜ ሲሆን ከአዳም እስከ ሙሴ የተነሱ አበው ሁሉ በህገ ልቦና ለእግዚአብሔር መስዋት ይሰው ቁርባን ያቀርቡ ነበር፡፡ መስዋዕታቸው ከእንሰሳ ቁርባናቸው ከእህልና ከአትክልት ማለት ከስንዴ እህል፣ ከወይን ፍሬ የሚቀርብ ነው፡፡ ዘመነ ኦሪት በብሉይ ኪዳን በሙክራብ የተሰዋ እንሰሳት ሁሉ በአዲስ ኪዳን በቤተክርስቲያን ለሚሰዋው ሁሉ የክርስቶስ ሥጋና ደም ምሳሌ ነበር፡፡ መልከ ጼዴቅ ያበረከተው ኅብስተ አኮቴት ጽዋዐ በረከት ለአምላክ የሥጋውና የደሙ ምሳ ሆነው አልፈዋል፡፡ ከምሥጢራት አንዱ መሆኑ ሕብስቱ ተለውጦ የክርስቶስ ሥጋ ጽዋው ተለውጦ የክርስቶስ ደም ሲሆን አይታይም፡፡ ነገር ግን እምነት ያለው ሁሉ በእምነት መነጽር ይመለከተዋል፡፡ ይህ ሳይሆን ሳይታይ የሚወደድን ሕይወት ለማግኘት ከቁርባን በፊት ንስሐ መግባት ለአስራ ስምንት ሰዓት መጾም አለበት፡፡ ንጽሕናውን በጠበቅ አለበት፡፡ መምክረ ካህን ጸንቶ መገኘት ያስፈልጋል፡፡ 4. ምሥጢረ ክህነት ይህ ቋንቋ የግዕዝ ቋንቋ ነው፡፡ ተክህነ አገልገለ ከሚለው ግስ የወጣ ነው፡፡ ክህነት የተጀመረው በአባታች አዳም ነው፡፡ ክህነት የአገልግሎት ስም ሆኖ የቤተክርስቲያን ከፍተኛ መንፈሳዊ ማዕረግ ነው፡፡ እግዚአብሔር አዳምን ፈጥሮ በልጅነት አክብሮ ነብይና ካህን አድርጎ ሾሞ በኦሪት በወንጌል ሥርዓት እስኪወሰን ድረስ ከአዳም ጀምሮ እስከ ሙሴ የነበሩ አበው በበረከት አበው ከእግዚአብሔር እየተሾሙ ትንቢትን ክህነት ከቅዱሱ መንፈስ እየተቀበሉ (እየተሾሙ) በነብይነታቸው ያለውን የሚመጣውን ሲገልጽ ሲያስተምሩ በሀብተ ክህነታቸው መስዋዕት ሲቀርቡ ነበር፡፡ ክህነት በዘመነ ኦሪት ለሌዊ ነገድ ከተሰጠ በኋላ ሲወርድ ሲወራረድ እስከ ክርስቶስ ደርሷል፡፡ ታላቁ ሊቀ ካህናት እየሱስ ክርስቶስ እንደ ብሉይ ኪዳን መስዋዕት እንሰሳ ሳሆን እራሱን መስዋዕት፣ እርሱ ሰዋዒ ሆኖ ወደ መቅደስ ገብቷል፡፡ ዮሐ 20፡22 ማሬ 18፡18 1ኘና ቆሮ 4፡1 ማሬ 28፡20 5. ምሥጢረ ንስሐ ይህ ቃል የግዕዝ ቃል ነው፡፡ ትርጉሙም በሰሩት ኃጢያት መጸጸት ምነው ባልሰራሁት ባላደረኩት ብሎ ማልቀስ ወደ ኃጢያት ላለመመለስ መወሰን፣ በሕጉ ጸንቶ ለመኖር ቃል መግባት፡፡ ክርስቲያን በጥምቀት ከአለም ክፉ ስራዎች ሁሉ የተለየ ነው፡፡ ህይወቱ ለክርስቶስ የተሰጠ ነው፡፡ ሮሜ 12፡1 የመጨረሻው ግቡና ዓላማው ሥርየተ ኃጢያትን ማግኘት እና የዘላለም ሕይወት መወረስ ነው፡፡ አካሉ የመንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ 1ቆሮ 6-19
Open in Telegram" የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፥ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው።" (ወደ ዕብራውያን 13:7)
Open in Telegram