Account
ዶ/ር ምህረት ደበበ እና ዶ/ር እዮብ ማሞ

ዶ/ር ምህረት ደበበ እና ዶ/ር እዮብ ማሞ

👉የዶ/ር ምህረት ደበበ ፣ የዶ/ር እዮብ ማሞ እና የሌሎችም ፦፦፦፦፦፦፦፦ 📖አነቃቂና አስተማሪ የሆኑ ወጎች 👉ስለ አመራር 👉አመለካከት(እይታ) 👉mindset 👉ስለ እድገት.......በስፋት እንዳስሳለን 📚 መፅሐፍት pdf 🎙የመፅሐፍ ትረካ 📖 አስተማሪ የሆኑ ፅሁፎች 👉👉👉contact us @Ay_ayche

Username
@ab_book
Category
Psychology
Country
EthiopiaEthiopia
Subscribers3,881
Avg views per post, 7d294−59.5% vs prev 7d
ERR7.58%last 7 days

Average views per post by day

By publication day

Show as table
DateAvg views per post
Nov 1, 20261,410
Nov 5, 20261,420
Nov 11, 20261,120
Nov 21, 2026726
Nov 27, 2026294

Most viewed this month

  1. 01

    #አንዱ_ለአንዱ_መኖር_የተፈጥሮ_ህግ_ነው! "ተፈጥሮን በተረዳን ቁጥር አዕምሮአችን የመፍጠር አቅሙ እያደገ ይመጣል። ዓለም ላይ ያለው እያንዳንዱ የፈጠራ ስራ ውጤት ተፈጥሮን በጥልቀት ከመረዳት የመነጨ ነው። ተፈጥሮን በጥልቀት ከተረዳን በደንብ ማየት እንችላለን። ተፈጥሮን በሰከነ መንፈስ የተረዳ ሰው የፈጠራ ችሎታውን ከማሳደግ በተጨማሪ ለሌሎች ሰዎች ሕይወት የብርሃን ምንጭ ለመሆን ይጥራል፤ ሁሌም ቢሆን ሰጭ እንጂ ቀማኛ አይሆንም። ልብ በሉ ወንዞች የራሳቸውን ውኃ አይጠጡም፤ እጽዋት የራሳቸውን ንፁህ አየርን አይስቡም፤ ፀሐይና ጨረቃም ቢሆን ለራሳቸው ብርሃን አይሰጡም፤ ውብ አበባዎችም መልካም መዓዛቸውን ለራሳቸው አያሰራጩም። አንዱ ለአንዱ መኖር የተፈጥሮ ህግ ነው። እኛም ወደዚህ ምድር የመጣነው አንዳችን ለአንዳችን ለመኖር እንጅ አንዳችን ለሌላችን የስጋት ምንጭ ወይም ወጥመድ ለመሆን እንዳልሆነ ልንረዳ ይገባል።” “እውቀት እና ጥበብ ተፈጥሮን ከመረዳት ይመነጫሉ። ተፈጥሮን በትክክል የምንወድ ከሆነ በሁሉም ቦታ ላይ ውበት እናያለን፤ እውቀትና ጥበብም እንደ ቢራቢሮ በእየሄድንበት ሁሉ እንቀስማለን። ተፈጥሮን በማወቅ ራሳችንን እናገኛለን። ተፈጥሮ ለሚያዳምጣት ልዩ ቅላፄ ያለው ዜማ አላት። በጥቅሉ የሕይወት ግባችን እኛነታችን ከተፈጥሮ ጋር እንዲዛመድ በማድረግ ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት።" #ስሙር መጽሐፍ የተቀነጨበ join us...      @Ab_book    @Ab_book    @Ab_book

    Text
    Views1.42K
    Forwards—
    Reactions9
    Comments—
  2. 02

    #ከዚህ_ድንቅ_ሰው_ተማር! ⚽️ ክሪስቲያኖ ሮናልዶ እጅግ ድሀ ከሆኑ ቤተሰቦች ተወለደ። የልጅነት ህይወቱ ጉስቁልና የበዛበት ነበር። አባቱ አትክልተኛ ሲሆን፤ የመጠጣት ልማድ ነበረበት። በቂ ገቢ ለቤተሰቡ ማስገኘት የማይችል ነበር። በዚህ የተነሳ ህይወቱን በጉበት ህመም አጥቷል። እናቱ ምግብ አብሳይና የጽዳት ሰራተኛ ነበረች። ያገኘችውን ለቤተሰቧ አብቃቅታ ትጠቀም ነበር። ሮናልዶ “እኔ የተነሳሁት ከምንም ነው። እጅግ ድሃ ከሆነ ቤተሰብ... በዙሪያዬ እንደነበሩት ልጆች አሻንጉሊቶች አልነበሩኝም። የልደትም ሆነ የገና ስጦታ አላገኝም ነበር። ከወንድሜ እና ከሁለት እህቶቼ ጋር ጠባብ ክፍል ውስጥ ነበር የምተኛው።”  ይላል። ⚽️ በዚህ ጊዜ ከቤቱ እየወጣ ከአካባቢው ልጆች ጋር ኳስ በመጫወት ችግሮቹን ወደኋላ በመተው ይጋፈጣል። ትኩረቱን እራሱን ምርጥ እና ተፈላጊ በማድረግ ላይ ያሳርፋል። በዚህም ሁሌም ፊቱ ላይ ፈገግታ የማይታጣበት ተስፈኛ መሆን ቻለ። ሮናልዶ በዚህ ጊዜ ነበር አባቱ በዝቅተኛ ክፍያ አትክልተኝነት ይሰራበት ለነበረው አንደሪና ቡድን መጫወት የጀመረው። ሮናልዶ በዚያ ለጋ እድሜው ችሎታው በግልጽ የሚታይ ቆንጆ ተከፋይ መሆን ጀመረ። ⚽️ በአስራ አንድ አመቱ የዲ ፖርቹጋልን ቀልብ ማረፊያ ሆነ። ባደገ ቁጥር ሁሉም ሰው አቅም እንዳለው አወቀ። ነገር ግን ትንሽ እና በጣም ቀጫጫ በመሆኑ ተፈላጊነቱን ፈተና ውስጥ ከተተው። ሮናልዶም ቀጫጫ መባሉን አይወደውም ነበር። በዚህም ሮናልዱ በአስራ አንድ አመቱ ሰውነቱን ለማሳደግ እና አቅሙን ለመጨማር ከማንም በላይ ጠንክሮ መስራት ጀመረ። በዚህም ሰውነቱን በቶሎ መቀየር ሆነለት። በትምህርት ቤት ውስጥ ከተማሪዎች ሁሉ የታወቀና የሚደነቅ ሆነ። በመምህራኖቹ ፊት ግን ደደብ የሚባል ነበር። ከትምህርት ቤትም እንዲባረር ተደርጓል። ⚽️ ከሚኖርበት ርቆ ሊዝበን የእስፖርት ትምህርት ቤት ሲገባ፤ የህይወቱ ትልቅ ፈተና ሆኖበታል። “እግር ኳስ ሁሉን ነገር ሰጠኝ። ነገር ግን ከቤቴ እንድርቅ አስገድዶኛል” ይላል ሮናልዶ። በ15 አመቱ በሊዝበት መጫወት ሲጀምር ነገሮች ከጅምራቸው ያበቃላቸው መስለው ነበር። ጤናው በልብ ህመም ታወከ። እንዳለመታደል ሆኖ እግር ኳስ እየተሯሯጠ ሊጫወት ይቅርና ለመኖርም መተንፈስ የሚከብደው ሆነ። ⚽️ ከዚያም ቀዶ ጥገና ሲደረግለት ትጉና ተስፈኛ የነበረው ሮናልዶ  ዳግም ጤናውን ሙሉ ለሙሉ ማግኘት ቻለ። ከዚያም እንደለመደው አላማውን ለማሳካት ከማንም በላይ ጥረቱን አጠናክሮ ቀጠለ። በፈረንጆቹ 2003 በ 15 ሚልዮን ዶላር ለማንቺስተር ዩናይትድ ቡድን ኮንትራት ፈረመ። ከዚያም የአለማችን ምርጥ ተጫዋች ለመሆን ራሱን ምቹ ማድረጉ ላይ አመነበት። አሰልጣኝ አሌክስ ፈርጉሰንም ሰባት ቁጥር ማልያን በመተማመን አለበሰው። በ 2009 ሮናልዶ ወደ ሪያል ማድሪድ ቡድን በአለማችን ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በ 94 ሚልዮን ዩሮ ተዘዋወረ። ከዚም በአመቱ በ 100 ሚልዮን ዩሮ ወደ ጁቤንትስ አቀና።  ይህም ከሰላሳ አመት በላይ በዚህ ልክ የተከፈለው የመጀመሪያው ታሪካዊ እግር ኳስ ተጫዋች ለመሆን በቃ። በዚህ ሁሉ መሃል ሮናልዶ ብዙ ስኬቶችን የራሱ ማድረግ ችሏል። ⚽️ እስካሁን ባለው እምነት ሁሌም ጠንክሮ በመስራት እንደሚያምን አለም ያወቀለት ተቀባይነቱ ነው። “እኔ ሁሌም በደጋፊዎች ፊት የሚደነቅና የሚወደድ ለመሆን አይደለም ጥረቴ፤ ልፋቴ የራሴን እርካታ ስለሚያስገኝልኝ-ም ነው።” ይላል ሮናልዶ። ከማንም ወደ (?) ☑️ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ያልተጋፈጠው የችግር ናዳ የለም። አቅሙን በማውራት ሳይሆን በማድረግ ስላሳየ፤ አለም ቁማ የምታጨበጭብለት ታታሪ ለመሆን በቅቷል። አንተስ ጥረትህን አሁን ትጀምረዋለህ ወይስ መቼም የማይመጣልህን ምቹ ጊዜ እየተጠባበክ በቅዠት ራስህን ታዳክማለህ? join us...      @Ab_book    @Ab_book    @Ab_book

    Text
    Views1.41K
    Forwards—
    Reactions9
    Comments—
  3. 03

    #አልፈልግምን_ፈልገው! ለአንድ ነገር ዋጋ ለመስጠት፣ ያ ነገር ያልሆነውን ነገር አለመቀበል አለብን፡፡ ለ X ዋጋ ለመስጠት X ያልሆነውን ውድቅ ማድረግ አለብን፡፡ ያ ‘አለመቀበል’ እሴቶቻችንንና ማንነታችንን ለመጠበቅ ተፈጥሯዊ እና አስፈላጊ አካል ነው። እኛ የምንገለፀው ላንቀበለው በምንመርጠው ነገር በመሆኑ፣ በራሳችን ውድቅ እንዳንሆን በመፍራት ምንም ነገር ‘አንፈልግም’ የማንል ከሆነ በመሰረቱ ምንም አይነት ማንነት የለንም ማለት ነው። በማንኛውም ዋጋ በመክፈል አለመፈለግን ውድቅ የማድረግ፣ ክርክርና ግጭትን የማስወገድ፣ እንዲሁም እና ሁሉንም ነገር ለማስማማት እና ህብር ለመፍጠር ሁሉንም ነገር በእኩልነት ለመቀበል የመሞከር ፍላጎት ጥልቅ እና ስውር ራስን ከፍ አድርጎ የማየት መንገድ ነው። ራሳቸውን ከፍ አድርገው የሚያዩ ሰዎች፣ ሁልጊዜ ጥሩ ስሜት ሊሰማቸው እንደሚገባ ስለሚሰማቸው፣ እነሱንም ሆነ ሌላ ሰውን ሊያሳዝን ይችላል ብለው ስለሚያስቡ ማንኛውንም ነገር ‘አልፈልግም’ ከማለት ይቆጠባሉ። የትኛውንም ነገር ‘አልፈልግም’ ማለት ባለመቻላቸው ምክንያት ዋጋ የሌለውና ለራስ ብቻ ትኩረት የሚሰጥ በፍላጎት የሚገፋ ኑሮ ይኖራሉ፡፡ ግድ የሚሰጣቸው የማይቀረውን የህይወታቸውን ውድቀት በመሸሽና ስቃይን እንዳባረሩ በማስመሰል ለጥቂት ጊዜ ከፍታ ላይ መቆየት ነው፡፡ አለመፈለግ በጣም አስፈላጊና ወሳኝ የሕይወት ክህሎት ነው፡፡ join us...      @Ab_book    @Ab_book    @Ab_book

    Text
    Views1.12K
    Forwards—
    Reactions5
    Comments—
  4. 04

    ጠዋት ስትነሱ! መጀመሪያ የምታስቡት ሃሳብ ምን እንደሆነ በሚገባ ተመልከቱትና ያላችሁበትን የስሜት ሁኔታ ይነግራችኋል፡፡ •  በእለቱ የምታከናውኗቸው ተግባሮቻችሁ ከባድ እንደሆኑ ካሰባችሁ እቅድ የማውጣት ክህሎት ላይ መስራት አለባችሁ፡፡ •  ትናንት ስሜታችሁ ላይ አጉል ተጽእኖ ስለነበረው ሰው ካሰባችሁና ከተረበሻችሁ የሰዎችን ሁኔታ አያያዝ ላይ መስራት አለባችሁ፡፡ •  ምንም የምትሰሩት ስራ እንደሌላችሁ ካሰባችሁ የፈጠራ እና አዳዲስ ነገር የመጀመር አቅማችሁ ላይ መስራት አለባችሁ፡፡ •  ሁኔታችሁ ሊለወጥ እንደማይችል የተስፋ መቁረጥ ሃሳብ ካሰባችሁ የሰዎችን የምክር እገዛ የመጠየቅና የመጠቀም ሁኔታ ላይ መስራት አለባችሁ፡፡ ሃሳቦቻችሁንና እነሱ የወለዷቸው ስሜቶቻችሁን በፍጹም ችላ አትበሏቸው፡፡ ተገቢውን ምላሽ ስጧቸው፡፡ ስላላችሁበት ሁኔታ ሰዎችን መውቀስ አቁሙና አንድ ነገር አድርጉ፡፡ ያላችሁበትን ሁኔታ ለመርሳት ማሕበራዊ ሚዲያ ላይ በመዋል አትደበቁ፡፡ ቀና በሉና ራሳችሁ ላይ ስሩ! join us...      @Ab_book    @Ab_book    @Ab_book

    Text
    Views726
    Forwards—
    Reactions9
    Comments—

Latest posts

#2287Text

“ሰው “ መሆን ወጥ ያለ ቅመም ና ጨው ጣዕም እንደሌለው ሁሉ ደግነት የሌለበት ህይወት ባዶ ነው። ሰለሆነም ዓለማችንን ያቆሟት ጥቂት ጥሩ መአዛ ያላቸው። እንደ ጨው ነገርን የሚያጣፍጡና ከመበላሸት በሚጠብቁ ሰዎች ነው። በእርግጥ አለማችን ቀጥ ብላ ያለችው። ብዙ የወደቁ ሰዎችም ስላሉ ነው። ለዛ ነው ዓለምና ሰው በታሪክና በጊዜ ውስጥ ነው ያሉት የሚባለው። እንደሚታወቀው አንድ ሰው እራሱን የሚረዳው ሌላውን ሰው ሲረዳ ሳይሆን በቅድሚያ ሲረዳ ነው። እኛም ሆንን ሌላው ጥሩ መረዳት የሚያገኘው እኛ ስለራሳችንና ስለሌላው ያለው መረዳት በሌላው ውስጥ መሆኑን ስንገነዘብ ብቻ ነው። ኤማኑል ሌቪነስ የተባለው ስመ ገናና ፍላስፍ የቤተሰቦቹን ታሪክ አስታውሶ። ሌላይኛው ፊት የሚል ሀሳብ አለው ( The face of the other) ። እኔ መኖሬን የማውቀው ጎረቤቴ ቡና ሲጠራኝ ነው። እኔ መኖሬን የማውቀው የአንተን መልክ ሳይ ነው። ይላል ይኸ ማለት ደግሞ አንተን ሌላ ሰው እንዲገድልኸ ወይም ክፉ እንዲያደርግብኸ እንደማትወደው ሁሉ ሌላውም ፊት ስትመለከት እንደዛው ነው የሚፈልገው። አንተ መሞት እንደማትፈልገው ሁሉ ሌላውም ፊት የሚልኸ አንድ ነገር ነው እሱም አትግደለኝ። ሰው መሆን !!! ሰው ሀሳቡን ማጥራት ይችላል። ሰው ምርጫውን ማስተካከል ይችላል። ሰው ሀሳብ መምረጥ ይችላል። በምርጫ መምረጥ ያለብንን መምረጥ እንችላለን ይገባልም ነገር ግን የምርጫ ውጤት አይቀየርም። ምክንያቱም የሰው የመምረጥ አቅም ብቻ ሳይሆን ሰው መሆን በራሱ ግብ ነው። እንጂ ለሆነ ግብ means አይደሉም። ሰው እረቂቅ ፍጥረት ነው። ታላቁ አሰላሳይ አርስጣጢለስ Aristotle, things are contained of both essential and accidental qualities እንደሚለው essential qualityችን ስዎች ነን። በAccidental quality ግን እንለያያለን። ሰውነታችን essential ነው። አማራ፣ ኦሮሞ፣ ትግሪም ብትሆን ሰው ነኸ። ረጅም ወይም አጭር፣ ወፍራም፣ ቀጭን፣ አማራ፣ኦሮሞ accidental ነው። ሰው መሆን ነው essenceu። ሰው መሆን ክብር ነው። ሰው መሆን መመረጥ ነው። ሰው መሆን ፀጋ ነው። ሰው መሆን ምስጢር ነው። ሰወ መሆን መራቀቅ ነው። ሰው መሆን ከራስ፣ ከቤተሰብ፣ ከአካባቢ፣ ከክልል፣ ከሀገር አና ከአህጉር አልፎ አለማቀፍዊነት ነው። ሰው መሆን ከቋንቋና ከነገድ ማለፍ ነው። ሰው መሆን ከገደብ በላይ እንደ ንስር ከፍ ብሎ መብረር ነው። ሰው መሆን ለሌላው ግድ መሰኘኘት ለሌላው መቆረስ ነው። ሰው መሆን ልዮነትንና አንድነትን ማጣመር ነው። ሰውነት ሰውነትን መገንዘብ ነው። ሰው መሆን መታደል ነው። ሰው መሆን ሰው መሆን ነው። ሰው መሆን የፍጣሪ ፎቶ መሆን ነው። ዮናስ ዘውዴ join us...      @Ab_book    @Ab_book    @Ab_book

Open in Telegram
Views294−70%vs avg
Forwards—
Reactions6
Comments—
#2286Text

ጠዋት ስትነሱ! መጀመሪያ የምታስቡት ሃሳብ ምን እንደሆነ በሚገባ ተመልከቱትና ያላችሁበትን የስሜት ሁኔታ ይነግራችኋል፡፡ •  በእለቱ የምታከናውኗቸው ተግባሮቻችሁ ከባድ እንደሆኑ ካሰባችሁ እቅድ የማውጣት ክህሎት ላይ መስራት አለባችሁ፡፡ •  ትናንት ስሜታችሁ ላይ አጉል ተጽእኖ ስለነበረው ሰው ካሰባችሁና ከተረበሻችሁ የሰዎችን ሁኔታ አያያዝ ላይ መስራት አለባችሁ፡፡ •  ምንም የምትሰሩት ስራ እንደሌላችሁ ካሰባችሁ የፈጠራ እና አዳዲስ ነገር የመጀመር አቅማችሁ ላይ መስራት አለባችሁ፡፡ •  ሁኔታችሁ ሊለወጥ እንደማይችል የተስፋ መቁረጥ ሃሳብ ካሰባችሁ የሰዎችን የምክር እገዛ የመጠየቅና የመጠቀም ሁኔታ ላይ መስራት አለባችሁ፡፡ ሃሳቦቻችሁንና እነሱ የወለዷቸው ስሜቶቻችሁን በፍጹም ችላ አትበሏቸው፡፡ ተገቢውን ምላሽ ስጧቸው፡፡ ስላላችሁበት ሁኔታ ሰዎችን መውቀስ አቁሙና አንድ ነገር አድርጉ፡፡ ያላችሁበትን ሁኔታ ለመርሳት ማሕበራዊ ሚዲያ ላይ በመዋል አትደበቁ፡፡ ቀና በሉና ራሳችሁ ላይ ስሩ! join us...      @Ab_book    @Ab_book    @Ab_book

Open in Telegram
Views726−27%vs avg
Forwards—
Reactions9
Comments—
#2284Text

#አልፈልግምን_ፈልገው! ለአንድ ነገር ዋጋ ለመስጠት፣ ያ ነገር ያልሆነውን ነገር አለመቀበል አለብን፡፡ ለ X ዋጋ ለመስጠት X ያልሆነውን ውድቅ ማድረግ አለብን፡፡ ያ ‘አለመቀበል’ እሴቶቻችንንና ማንነታችንን ለመጠበቅ ተፈጥሯዊ እና አስፈላጊ አካል ነው። እኛ የምንገለፀው ላንቀበለው በምንመርጠው ነገር በመሆኑ፣ በራሳችን ውድቅ እንዳንሆን በመፍራት ምንም ነገር ‘አንፈልግም’ የማንል ከሆነ በመሰረቱ ምንም አይነት ማንነት የለንም ማለት ነው። በማንኛውም ዋጋ በመክፈል አለመፈለግን ውድቅ የማድረግ፣ ክርክርና ግጭትን የማስወገድ፣ እንዲሁም እና ሁሉንም ነገር ለማስማማት እና ህብር ለመፍጠር ሁሉንም ነገር በእኩልነት ለመቀበል የመሞከር ፍላጎት ጥልቅ እና ስውር ራስን ከፍ አድርጎ የማየት መንገድ ነው። ራሳቸውን ከፍ አድርገው የሚያዩ ሰዎች፣ ሁልጊዜ ጥሩ ስሜት ሊሰማቸው እንደሚገባ ስለሚሰማቸው፣ እነሱንም ሆነ ሌላ ሰውን ሊያሳዝን ይችላል ብለው ስለሚያስቡ ማንኛውንም ነገር ‘አልፈልግም’ ከማለት ይቆጠባሉ። የትኛውንም ነገር ‘አልፈልግም’ ማለት ባለመቻላቸው ምክንያት ዋጋ የሌለውና ለራስ ብቻ ትኩረት የሚሰጥ በፍላጎት የሚገፋ ኑሮ ይኖራሉ፡፡ ግድ የሚሰጣቸው የማይቀረውን የህይወታቸውን ውድቀት በመሸሽና ስቃይን እንዳባረሩ በማስመሰል ለጥቂት ጊዜ ከፍታ ላይ መቆየት ነው፡፡ አለመፈለግ በጣም አስፈላጊና ወሳኝ የሕይወት ክህሎት ነው፡፡ join us...      @Ab_book    @Ab_book    @Ab_book

Open in Telegram
Views1,120+13%vs avg
Forwards—
Reactions5
Comments—
#2283Text

#አንዱ_ለአንዱ_መኖር_የተፈጥሮ_ህግ_ነው! "ተፈጥሮን በተረዳን ቁጥር አዕምሮአችን የመፍጠር አቅሙ እያደገ ይመጣል። ዓለም ላይ ያለው እያንዳንዱ የፈጠራ ስራ ውጤት ተፈጥሮን በጥልቀት ከመረዳት የመነጨ ነው። ተፈጥሮን በጥልቀት ከተረዳን በደንብ ማየት እንችላለን። ተፈጥሮን በሰከነ መንፈስ የተረዳ ሰው የፈጠራ ችሎታውን ከማሳደግ በተጨማሪ ለሌሎች ሰዎች ሕይወት የብርሃን ምንጭ ለመሆን ይጥራል፤ ሁሌም ቢሆን ሰጭ እንጂ ቀማኛ አይሆንም። ልብ በሉ ወንዞች የራሳቸውን ውኃ አይጠጡም፤ እጽዋት የራሳቸውን ንፁህ አየርን አይስቡም፤ ፀሐይና ጨረቃም ቢሆን ለራሳቸው ብርሃን አይሰጡም፤ ውብ አበባዎችም መልካም መዓዛቸውን ለራሳቸው አያሰራጩም። አንዱ ለአንዱ መኖር የተፈጥሮ ህግ ነው። እኛም ወደዚህ ምድር የመጣነው አንዳችን ለአንዳችን ለመኖር እንጅ አንዳችን ለሌላችን የስጋት ምንጭ ወይም ወጥመድ ለመሆን እንዳልሆነ ልንረዳ ይገባል።” “እውቀት እና ጥበብ ተፈጥሮን ከመረዳት ይመነጫሉ። ተፈጥሮን በትክክል የምንወድ ከሆነ በሁሉም ቦታ ላይ ውበት እናያለን፤ እውቀትና ጥበብም እንደ ቢራቢሮ በእየሄድንበት ሁሉ እንቀስማለን። ተፈጥሮን በማወቅ ራሳችንን እናገኛለን። ተፈጥሮ ለሚያዳምጣት ልዩ ቅላፄ ያለው ዜማ አላት። በጥቅሉ የሕይወት ግባችን እኛነታችን ከተፈጥሮ ጋር እንዲዛመድ በማድረግ ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት።" #ስሙር መጽሐፍ የተቀነጨበ join us...      @Ab_book    @Ab_book    @Ab_book

Open in Telegram
Views1,420+43%vs avg
Forwards—
Reactions9
Comments—
#2282Text

#ከዚህ_ድንቅ_ሰው_ተማር! ⚽️ ክሪስቲያኖ ሮናልዶ እጅግ ድሀ ከሆኑ ቤተሰቦች ተወለደ። የልጅነት ህይወቱ ጉስቁልና የበዛበት ነበር። አባቱ አትክልተኛ ሲሆን፤ የመጠጣት ልማድ ነበረበት። በቂ ገቢ ለቤተሰቡ ማስገኘት የማይችል ነበር። በዚህ የተነሳ ህይወቱን በጉበት ህመም አጥቷል። እናቱ ምግብ አብሳይና የጽዳት ሰራተኛ ነበረች። ያገኘችውን ለቤተሰቧ አብቃቅታ ትጠቀም ነበር። ሮናልዶ “እኔ የተነሳሁት ከምንም ነው። እጅግ ድሃ ከሆነ ቤተሰብ... በዙሪያዬ እንደነበሩት ልጆች አሻንጉሊቶች አልነበሩኝም። የልደትም ሆነ የገና ስጦታ አላገኝም ነበር። ከወንድሜ እና ከሁለት እህቶቼ ጋር ጠባብ ክፍል ውስጥ ነበር የምተኛው።”  ይላል። ⚽️ በዚህ ጊዜ ከቤቱ እየወጣ ከአካባቢው ልጆች ጋር ኳስ በመጫወት ችግሮቹን ወደኋላ በመተው ይጋፈጣል። ትኩረቱን እራሱን ምርጥ እና ተፈላጊ በማድረግ ላይ ያሳርፋል። በዚህም ሁሌም ፊቱ ላይ ፈገግታ የማይታጣበት ተስፈኛ መሆን ቻለ። ሮናልዶ በዚህ ጊዜ ነበር አባቱ በዝቅተኛ ክፍያ አትክልተኝነት ይሰራበት ለነበረው አንደሪና ቡድን መጫወት የጀመረው። ሮናልዶ በዚያ ለጋ እድሜው ችሎታው በግልጽ የሚታይ ቆንጆ ተከፋይ መሆን ጀመረ። ⚽️ በአስራ አንድ አመቱ የዲ ፖርቹጋልን ቀልብ ማረፊያ ሆነ። ባደገ ቁጥር ሁሉም ሰው አቅም እንዳለው አወቀ። ነገር ግን ትንሽ እና በጣም ቀጫጫ በመሆኑ ተፈላጊነቱን ፈተና ውስጥ ከተተው። ሮናልዶም ቀጫጫ መባሉን አይወደውም ነበር። በዚህም ሮናልዱ በአስራ አንድ አመቱ ሰውነቱን ለማሳደግ እና አቅሙን ለመጨማር ከማንም በላይ ጠንክሮ መስራት ጀመረ። በዚህም ሰውነቱን በቶሎ መቀየር ሆነለት። በትምህርት ቤት ውስጥ ከተማሪዎች ሁሉ የታወቀና የሚደነቅ ሆነ። በመምህራኖቹ ፊት ግን ደደብ የሚባል ነበር። ከትምህርት ቤትም እንዲባረር ተደርጓል። ⚽️ ከሚኖርበት ርቆ ሊዝበን የእስፖርት ትምህርት ቤት ሲገባ፤ የህይወቱ ትልቅ ፈተና ሆኖበታል። “እግር ኳስ ሁሉን ነገር ሰጠኝ። ነገር ግን ከቤቴ እንድርቅ አስገድዶኛል” ይላል ሮናልዶ። በ15 አመቱ በሊዝበት መጫወት ሲጀምር ነገሮች ከጅምራቸው ያበቃላቸው መስለው ነበር። ጤናው በልብ ህመም ታወከ። እንዳለመታደል ሆኖ እግር ኳስ እየተሯሯጠ ሊጫወት ይቅርና ለመኖርም መተንፈስ የሚከብደው ሆነ። ⚽️ ከዚያም ቀዶ ጥገና ሲደረግለት ትጉና ተስፈኛ የነበረው ሮናልዶ  ዳግም ጤናውን ሙሉ ለሙሉ ማግኘት ቻለ። ከዚያም እንደለመደው አላማውን ለማሳካት ከማንም በላይ ጥረቱን አጠናክሮ ቀጠለ። በፈረንጆቹ 2003 በ 15 ሚልዮን ዶላር ለማንቺስተር ዩናይትድ ቡድን ኮንትራት ፈረመ። ከዚያም የአለማችን ምርጥ ተጫዋች ለመሆን ራሱን ምቹ ማድረጉ ላይ አመነበት። አሰልጣኝ አሌክስ ፈርጉሰንም ሰባት ቁጥር ማልያን በመተማመን አለበሰው። በ 2009 ሮናልዶ ወደ ሪያል ማድሪድ ቡድን በአለማችን ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በ 94 ሚልዮን ዩሮ ተዘዋወረ። ከዚም በአመቱ በ 100 ሚልዮን ዩሮ ወደ ጁቤንትስ አቀና።  ይህም ከሰላሳ አመት በላይ በዚህ ልክ የተከፈለው የመጀመሪያው ታሪካዊ እግር ኳስ ተጫዋች ለመሆን በቃ። በዚህ ሁሉ መሃል ሮናልዶ ብዙ ስኬቶችን የራሱ ማድረግ ችሏል። ⚽️ እስካሁን ባለው እምነት ሁሌም ጠንክሮ በመስራት እንደሚያምን አለም ያወቀለት ተቀባይነቱ ነው። “እኔ ሁሌም በደጋፊዎች ፊት የሚደነቅና የሚወደድ ለመሆን አይደለም ጥረቴ፤ ልፋቴ የራሴን እርካታ ስለሚያስገኝልኝ-ም ነው።” ይላል ሮናልዶ። ከማንም ወደ (?) ☑️ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ያልተጋፈጠው የችግር ናዳ የለም። አቅሙን በማውራት ሳይሆን በማድረግ ስላሳየ፤ አለም ቁማ የምታጨበጭብለት ታታሪ ለመሆን በቅቷል። አንተስ ጥረትህን አሁን ትጀምረዋለህ ወይስ መቼም የማይመጣልህን ምቹ ጊዜ እየተጠባበክ በቅዠት ራስህን ታዳክማለህ? join us...      @Ab_book    @Ab_book    @Ab_book

Open in Telegram
Views1,410+42%vs avg
Forwards—
Reactions9
Comments—
#2281Text

አንተ ማግኔት ነህ የአዕምሮ አይኖችህን ከከፈትክ እና በውስጥህ ያለውን ሀይል መጠቀም ከቻልክ ወሰን የለሽ ሀብቶች በዙሪያህ እንዳሉ ልታይ ትችላለህ። ህይወትህን በደስታ ለመኖር የሚያስፈልግህን ሁሉ የያዘው የወርቅ ማዕድን በአንተ ውስጥ ነው። ብዙዎች አንቀላፍተዋል ምክንያቱም በውስጣቸው ስላለህ እምቅ ሀይል ስለማያውቁ ነው።  የማግኔትነት ባሕሪ ያለው ብረት የክብደቱ አሥራ ሁለት አጥፍ ያህል ያነሳል። ይህንኑ ብረት ማግኔታማ ባሕሪውን ብታሳጣው ላባ እንኳ አያነሳም። ሁለት ዓይነት ሰዎች አሉ። በራስ በመተማመን ስሜት የተሞሉ ማግኔቲዝድ ሰዎች እና በፍርሃትና በጥርጣሬ የተሞሉ ምንም የማይስቡ ሰዎች። እድሎች ይመጣሉ፣ “ላይሳካልኝ ይችላል፣ ገንዘቤን ላጣ እችላለሁ፣ ሰዎች ይሳቁብኛል” የምትል ከሆነ እድሎቹን ትገፋለህ። በህይወት ውስጥ ብዙ ርቀት አትጓዝም፤ ምክንያቱም ወደፊት ለመሄድ የምትፈራ ከሆነ ባለህበት ብቻ ትቆያለህ። አንተ ማግኔት ነህ... ወደፊት እየተጓዝክ መሳብህን ቀጥል!! ድብቁ አእምሮህ ድብቁ ኃይልህ መጽሐፍ join us...      @Ab_book    @Ab_book    @Ab_book

Open in Telegram
Views1,300+31%vs avg
Forwards—
Reactions4
Comments—
#2280Text

#ዛሬ_የት_እንዳላችሁ_አትጨነቁ! "... እያንዳንዱ ሳይንቲስት የሆነ ቀን ላይ የሚያለቅስ ህጻን ልጅ ነበር፤ እያንዳንዱ ታላቅ ኪነ ሕንፃም የሆነ ቀን ላይ ባዶ ካርታ ብቻ ነበር።  ዛሬ የት እንዳላችሁ መጨነቁ አስፈላጊ አይደለም ነገር ግን ነገ የት እንደምትደርሱ ማለምና ማስኬድ ላይ ነው ትልቁ ቁም ነገር ያለው። ልብ በሉ አልበርት አንስታይን ሲወለድ ከንፅፅር ፅንሰ ሀሳብ ጋር አልተወለደም፤ አይዛክ ኒውተንም የእንቅስቃሴ ህጎቹን በእናቱ ማህፀን ውስጥ ቀምሮ አልወጣም፤ ዱባይ ውስጥ የሚገኘው ስምንት መቶ ሠላሳ ሜትር ገደማ የሚረዝመው “ቡርጅ ካሊፋ” የተሰኘው የዓለማችን ረዥሙ ኪነ ህንፃም ከሆነ ጊዜ በፊት ሕንፃ ሳይሆን ባዶ ካርታ ብቻ ነበር። ሁሉም ነገር ከባዶ ነው የሚጀምረው። ስለዚህ እናንተም በሙሉ ተስፋ ከጣራችሁ እና ዓላማችሁን ለማሳካት ቁርጠኛ ከሆናችሁ ከምንም እና ከየትም ተነስታችሁ የስኬትን ጫፍ መቆናጠጥ ትችላላችሁ” በማለት ሰሎሞን ተሰናብቷቸው ከክፍሉ ራመድ ራመድ ብሎ ወጣ። #ከስሙር_መጽሐፍ_የተቀነጨበ join us...      @Ab_book    @Ab_book    @Ab_book

Open in Telegram
Views1,510+52%vs avg
Forwards—
Reactions10
Comments—
#2279Text

የራስህ ስኬት ሰለባ ነህ! ጆርጅ ኦርዌል፣ “አንድ ሰው አፍንጫው ስር ያለውን ነገር ለማየት የማያቋርጥ ትግል ይጠይቃል፡፡” ይላል። እውነት ነው። እኛም የጭንቀቶቻችን እና የውጥረቶቻችን መፍትሄ ያለው አፍንጫችን ስር ሆኖ እኛ ግን መፍትሄ የማይሆኑ ማሽኖቻችን ላይ እንጣዳለን። ከዚያ  የራቁት ምስሎችንና ማስታወቂያዎችን በማየት ተጠምደን፣ በስፖርት የተገነባ ሰውነት ኖሮን በጣም ከምታምር አማላይ ሴት ጋር ተያይዘን መዞር የማንችለው ለምን እንደሆነ እናስባለን፡፡ ስለ “የመጀመሪያው ዓለም ችግሮች” እንቀልዳለን፣ ነገር ግን የራሳችን ስኬት ሰለባ ሆነናል። ባለፉት ሰላሳ አመታት ውስጥ ከውጥረት ጋር የተያያዙ የጤና ጉዳዮች፣ የጭንቀት፣ የድብርት ችግሮች ጨምረዋል። ምንም እንኳን ሁሉም ሰው ፍላት ስክሪን ቲቪ ያለው እና የገዛውን ዕቃ ቤቱ ድረስ እንዲመጣለት ማዘዝ የሚችል ቢሆንም፣ ባለፉት ሰላሳ አመታት ውስጥ ከውጥረት ጋር የተያያዙ የጤና ችግሮች ቁጥር በሚገርም ፍጥነት አሻቅቧል። በዚህም ምክንያት ችግራችን ቁሳዊ ሳይሆን፣ ህልውና ነው፤ መንፈሳዊ ነው።  ከአሁን በኋላ ስለ ምን ግድ ሊኖረን እንደሚገባን እንኳን እስከማናውቀው ድረስ በጣም ብዙ አስጨናቂ ነገሮች እና በጣም ብዙ እድሎች ያሉን ሆነናል። እኛ ግን በብዛት ከብዙ እድሎች ይልቅ ብዙ አስጨናቂ ነገሮችን እንመርጣለን፡፡ በዚያ ፈንታ እንዴት ብዙ እድሎችን እንምረጥ? join us...      @Ab_book    @Ab_book    @Ab_book

Open in Telegram
Views1,600+61%vs avg
Forwards—
Reactions4
Comments—
#2278Text
Views2,040+105%vs avg
Forwards—
Reactions7
Comments—
#2277Text

እውነታን አምኖ የመቀበል (acceptance) አስፈላጊነት! አንዳንድ ሰዎች የተነሳሳና ስኬታማ ሕይወት ማለት ያሉበትን አስቸጋሪ ሁኔታ እንደሌለ መካድ ይመስላቸዋል፡፡ ይህ አመለካከት ጊዜያዊ የሆነ “ደህና” የመሆን ስሜት ቢሰጠንም የችግራችንን ስር መሰረቱን ግን አይፈታውም፡፡  •  ያላችሁበትን ደስ የማይል የስሜት ሁኔታ አትካዱት፣ ነገር ግን ከሁኔታው ልትወጡ እንደምትችሉ ተስፋችሁን አትጣሉ፡፡ •  ያላችሁበትን የኢኮኖሚ ትግል አትካዱት፣ ነገር ግን ለውጥ ለማምጣት አቅዱና ስሩ፡፡ •  ያላችሁበትን በተለያዩ ምርጫዎች መካከል የመወላወል ሁኔታ አትካዱት፣ ያሏችሁን ምርጫዎች በትኖ በማየትና ምክር በመቀበል መወሰን ላይ ስሩ፡፡ •  አጠገባችሁ ካሉ ሰዎች ጋር አብሮ የመቀጠልን አስቸጋሪነት አትካዱት፣ ራሳችሁን በመለወጥና አቅማችሁን በማዳበር ግን አልፋችሁት መሄድ ላይ ስሩ፡፡ ያላችሁበትን ሁኔታ መቀበል ማለት ለሆነው፣ በመሆን ላይ ላለውና ወደፊትም ለሚሆነው ነገር ሃላፊነትን መውሰድ ማለት ነው፡፡ ይህ ሃላፊነት የመውሰድ ልምምድ ምንም አይነት መፍትሄ ለማምጣት የመጀመሪያው ደረጃ እና መነሻው ነው፡፡ join us...      @Ab_book    @Ab_book    @Ab_book

Open in Telegram
Views1,840+85%vs avg
Forwards—
Reactions8
Comments—

All posts

Connections