ፈንድቃ ምሽት! አንጋፋ የኪነጥበብ ምሽት! (ሼር በማድረግ የጥበብ ግብዣውን ለሌሎችም አድርሱልን።) የ67ኛ ምሽት እንግዳችን፤ በዳንስ ጥበቡ የዓለምን መድረኮች ያደመቀ፣ የኢትዮጵያን ብዝኃ ባህላዊ ውዝዋዜዎች ከዘመናዊ የፈጠራ ጥበብ ጋር ያዋሐደ፣ ለወጣት ከያኒያን የጥበብ መድረክ የፈጠረ፣ የፈንድቃ የባህል ማዕከል መሥራች፣ የበርካታ ዓለም አቀፍ ሽልማቶች ባለቤት፣ የኢትዮጵያ ባህል አምባሳደር፣ መላኩ በላይ ነው! 🔥 ፈንድቃ ምሽት! ሰውነት ቋንቋ ሲሆን፣ ዳንስስ ምን ይናገራል?... ከአዲስ አበባ ጎዳናዎች እስከ ዓለም አቀፍ የጥበብ መድረኮች፣ ከአዝማሪ ቤት ውዝዋዜ እስከ ፈንድቃ የባህል ማዕከል ምሥረታ፣ ከፈንድቃ እስከ ኢትዮከለር፣ ከእስክስታ እስከ TED መድረክ፣ በአጠቃላይ የሕይወትና የጥበብ ጉዞው ላይ እንወያያለን። 🎭 የጥበብ ማዕዳችን ሰፊ፤ ገበታችንም ሙሉ ነው! ግጥም፣ ወግ፣ ሙዚቃ፣ ሂስና ዳንስ እንደተለመደው ዓይነት በዓይነት ተዘጋጅተውላችኋል። 📅 ረቡዕ፣ ኅዳር 23 ቀን 2019 ዓ.ም 🕠 11:30 ሰዓት 📍 አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የባህል ማዕከል፣ ስድስት ኪሎ ግቢ አንድ መድረክ፣ ብዙ ታሪኮች! አንድ መድረክ፣ ሺ ስሜቶች! ሁላችሁም ተጋብዛችኋል! @AAUNEWS1
Open in TelegramViews growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 3 h | 848 |
| 5 h | 888 |
- After 6 hours888
- Total to date888