በውቧ የአፍሪካ መዲና አዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት ዲፕሎማቶች፥ የአፍሪካ ህብረት (AU) ሠራተኞች፣ እና የከተማችን ነዋሪዎች በጋራ የተሳተፉበት ደማቅ የ5 ኪሎ ሜትር ሩጫ ተካሂደ። ይህ ሁነት የአፍሪካዊ አንድነት፣ የወንድማማችነትና እህትማማችነት መንፈስ እንዲሁም የከተማችንን የሰላምና የዲፕሎማሲ ማዕከልነት የሚያረጋገጥ ነው። አዲስ አበባ የአፍሪካ መዲና እንደመሆኗ መጠን፣ የአህጉራችንን ህዝቦች የሚያቀራርቡ እና የወንድማማችነትና እህትማማችነት ትስስርን የሚያጠናክሩ እንዲህ ያሉ ሁነቶችን ተጠናክረው ቀጥለዋል። ውድድሩ የከተማችንን የአብሮነት፣ የሰላምና የዲፕሎማሲ መንፈስ በጉልህ የተንፀባረቀበት ልዩ ሁነት ነው። በከተማችን እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማትና የከተማ ማስዋብ ሥራዎች፤ ለነዋሪዎችም ሆነ በከተማችን ለሚኖሩ ዲፕሎማቶች ምቹ፣ ጽዱ እና ለጤናማ የአኗኗር ዘይቤ ተስማሚ መዲናን መፍጠራቸውን በተግባር የታየበት ነው። አዲስ አበባን ይበልጥ ውብ፣ ሰላማዊ እና ለሁሉም ምቹ የማድረግ ጉዟችን ተጠናክሮ ቀጥሏል።
Open in TelegramPosts of የአዲስ አበባ ሠራተኛና የሥራ እድል ፈጠራ ቢሮ/Addis Ababa Labor and Job Creation Bureau
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የ21ኛውን የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀንን ምክኒያት በማድረግ ልዩ ልዩ የበጎ ፈቃድ ተግባራት ተከናወኑ ። ህዳር 19/2019 ዓ.ም በለሚ ኩራ ክ/ከተማ አስተዳደር “በብዝኃነት የደመቀች፤ በምክክር የፀናች ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን 21ኛውን የኢትዮጵያ የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል ምክኒያት በማድረግ የማዕድ ማጋራትና የደም ልገሳ መርሃ ግብር ተካሂዷል። በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰራተኛና ስራ እድል ፈጠራ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ማቴወስ ለሚ ኩራ የአዲስ አበባ የልማት ስራዎቻችን ማሳያ እንደመሆኗ መጠን እየተሰሩ ያሉ ስራዎችም በብዝሀነት ውስጥ አንድነትን የሚያንጸባርቁ መልካም ስራዎች ለሀገራችን እድገት ወሳኝ መሆናቸውን ጠቅሰው የአቅመ ደካማ ወገኖችን ቤት በማደስ በሁለቱ ሃይማኖት ተቋማት መካከል የታየው የአብሮነት ተግባርም ብዝሃነት የመለያየት ምክንያት ሳይሆን የመረዳዳት ፣የአብሮነትና የፍቅር መሆኑን አመልክተዋል። የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የሴቶች፣ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሶፊያ አለሙ ለሰው ልጅ ሰውን እንደመርዳት አንዱ ሌላው ያጣውን ሞልቶ ተደጋግፎ እንደመኖር ያለ ትልቅነትና የተቸገሩትን እንደመርዳት ያለ ደስታ እንደሌለ ገልጸው የመረዳዳትና የመደጋገፍ ባህላችን ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል ብለዋል። የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አድማሱ ደቻሳ ሀገራችን ኢትዮጵያ በብዙ ማንነቶችና ህብረ ብሔራዊ ቀለማት የደመቀች፣በብዝሃነት የሀገራችን ብልፅግናን ከፍ ለማድረግ ተግታ እየሰራች እንደሚትገኝ ጠቅሰው ከቅርብ አመታት ወዲህ መደጋገፍ ሀገራዊ ባህል ሆኖ በመምጣት ለዚህ ማሳያ በርካታ የአቅመ ደካሞችን ቤት ማደስ ፣በበዓላትና በተለያዩ ጊዜያት ማዕድን በማጋራት እንዲሁም ሌሎች በርካታ በጎ ስራዎች የተሰሩ ሲሆን ዛሬ ላይ የሀይማኖት ተቋማት አንዱ የሌላውን እምነት ተከታዮችን ቤት በማደስአንድነትን፣መቻቻልና መደጋገፍን የሚያጠናክር ተግባራት በመሆናቸው በሌሎች ተግባራትንም አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል። በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፅዮን ደረጀ፣ የበጎ ፈቃድ ተግባር ተስፋን የምናጸናበት፣የተሰፋ ብርሃን የምናበራበት፣አብሮነትን የምንገነባበት፣ የተረፈንን የምንሰጥበት ብቻ ሳይሆን ካለን ላይ ቀንሰን የምናካፍልበት ቅዱስ ተግባር መሆኑን ጠቅሰው አቅመ ደካሞችንና የተቸገሩ ወገኖቻችንን መርዳት የአንድ ቀን የዘመቻ ስራ ብቻ ሳይሆን በማህበረሰብ ልብ ውስጥ መስረጽ ያለበት ተግባር መሆኑንም አውስተዋል። ለሚ ኩራ ኮሚዩኒኬሽን
Open in Telegram