ያሰላም ምርጥ የሰርግ ነሺዳ አልበም አብዱልከሪም (አብዲቾ) 👇👇👇 https://youtu.be/H2W4CiSh14Q https://youtu.be/H2W4CiSh14Q https://youtu.be/H2W4CiSh14Q
Открыть в TelegramПосты канала ﷽ዚክረ መንዙማﷺ
የመካው ክስተት እውነታ‼ ================ [የተሰራጩ የሐሰት ወሬዎች እና የሸሪዓው ሕጋዊ ብይን (ተዕዚር)] |ው ወሬን ቢያመጣላችሁ፣ በስህተት ሕዝቦችን እንዳትጎዱና በሠራችሁት ነገር ላይ ተጸጻቾች እንዳትሆኑ (እውነታውን) አጣሩ።» [አል-ሑጁራት፡ 6]
Открыть в Telegram🍔 በተዕዚር ሥር ምን ምን ቅጣቶች ሊካተቱ ይችላሉ? 🔸 በቃል መገሠጽ እና ማስጠንቀቂያ መስጠት፤ 🔸 ጥፋተኝነትን ማጋለጥ (ተሽሂር)፤ 🔸 የገንዘብ መቀጮ መጣል፤ 🔸 ከሥራ ማገድ ወይም ማባረር፤ 🔸 ግርፋት (ከሐድ ቅጣት በታች በሆነ መጠን)፤ 🔸 እስራት (ከቀናት እስከ ዓመታት ወይም የዕድሜ ልክ)፤ 🔸 እስከ ሞት ቅጣት ድረስ (አል-ቀትሉ ተዕዚራን - القتل تعزيراً)። 4️⃣ ተዕዚር መቼ ወደ ሞት ቅጣት ያድጋል? ℹ️ ብዙዎች «ያላገባ ሰው በሸሪዓ ቅጣቱ መገረፍ እንጂ መገደል አልነበረም፤ ታዲያ ለምን በሞት ተቀጡ?» የሚል ጥያቄ ያነሳሉ። መልሱ ያለው በወንጀሉ ክብደት እና በቦታው ቅድስና ላይ ነው፦ በአራቱም የእስልምና የፊቅህ መዝሃቦች (በተለይም በሐነፊ፣ በማሊኪ እና በሐንበሊ ዑለማዎች፤ እንደ ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ እና ኢብኑል ቀይዩም ባሉ ብርቅዬ የኢስላም ሊቃውንት መሠረት)፦ አንድ ወንጀል በማኅበረሰቡና በዲኑ ላይ የሚያደርሰው ጥፋት (ፈሳድ) እጅግ ከባድ ሲሆን፣ ወንጀለኛው ከጥፋቱ የማይታረም ሆኖ ሲገኝ፣ ወይም የፈጸመው ድርጊት የተቀደሰን መርህ በእጅጉ ያረከሰ ሲሆን መሪው/ዳኛው ወንጀለኛውን በተዕዚር በሞት እንዲቀጣ (ቀትሉ ተዕዚራን) የመበየን ሙሉ ሸሪዓዊ ሥልጣን አለው። ይህ ብይን ተግባራዊ የሚሆንባቸው አጋጣሚዎች፦ 1️⃣ በምድር ላይ ጥፋትን ማስፋፋት (ፈሳድ ፊል-አርድ)፦ ሰዎችን የሚመርዙ አደንዛዥ ዕጾችን በስፋት የሚያዘዋውሩ፣ የስለላና የሀገር ክህደት ወንጀል የፈጸሙ። 2️⃣ ሑርመቱል መካን ወዝ-ዘማን (የተቀደሰ ቦታና ጊዜን ማርከስ)፦ አላህ በተከበረው ቁርኣን ስለ መካ ሐረም እንዲህ ይላል፦ «وَمَنْ يُرِدْ فِيهِ بِإِلْحَادٍ بِظُلْمٍ نُذِقْهُ مِنْ عَذَابٍ أَلِيمٍ» «በእርሱም (በተከበረው መስጂድ) ውስጥ በማዘንበል በደልን የሚሻ ሰው ከአሳማሚ ቅጣት እናቀምሰዋለን።» [አል-ሐጅ፡ 25] ✅በመላው ዓለም ያሉ ከሁለት ቢሊዮን በላይ ሙስሊሞች ፊታቸውን የሚያዞሩበት፣ በምድር ላይ እጅግ የተቀደሰውን የአላህ ቤት ማዕከል አድርጎ ዝሙት መፈጸም ተራ የሥነ-ምግባር ጉድለት ሳይሆን የእስልምናን መሠረታዊ ቅድስና በዓለም ፊት ማርከስና ማዋረድ ነው። ስለዚህ ፍርድ ቤቱ ይህንን ያደረገው በተራ የዝሙት ቅጣት (ሐድ) ሳይሆን፣ ለሌሎችም የማያዳግም ትምህርት እንዲሆን በተዕዚር (Discretionary Capital Punishment) በኩል ነው። በአጭሩ በመካ የተፈጸመው ፍርድ፦ ✅ የዓመታት ዝርዝር ምርመራ የተካሄደበት፣ ✅ የተከሳሾችን የጥፋተኝነት ማስረጃ (የቪዲዮ ምስክርነትን ጨምሮ) ያረጋገጠ፣ ✅ በከፍተኛ የዳኞች ጉባኤ ተመርምሮ የተሰጠ ሕጋዊ ውሳኔ ነው። ✅ ስለዚህ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የሚለቀቁ ስሜት ቀስቃሽና የተሳሳቱ ዘገባዎች፣ «ለሐኒሙን የሄዱ ሙሽሮች ተገደሉ» የሚሉ የፈጠራ ተረቶች የእስልምናን ፍትሕ እና የሐረመይንን ቅድስና ለማጉደፍ የተዘጋጁ የውሸት ፕሮፓጋንዳዎች መሆናቸውን አውቆ ማኅበረሰቡ ሊጠነቀቅና እውነታውን ሊረዳ ይገባል። አላህ በተከበረው ቃሉ እንዳስተማረን፦ «يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِنْ جَاءَكُمْ فَاسِقٌ بِنَبَإٍ فَتَبَيَّنُوا أَنْ تُصِيبُوا قَوْمًا بِجَهَالَةٍ فَتُصْبِحُوا عَلَىٰ مَا فَعَلْتُمْ نَادِمِينَ» «እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አመጸኛ ሰው ወሬን ቢያመጣላችሁ፣ በስህተት ሕዝቦችን እንዳትጎዱና በሠራችሁት ነገር ላይ ተጸጻቾች እንዳትሆኑ (እውነታውን) አጣሩ።» [አል-ሑጁራት፡ 6] 🕋 የሚገርመው አንድ የአሕባሽ አንጃ ይህን ተከትሎ ሳዑዲን እየተቸ ጽፎ መጨረሻ ላይ፤ ሳዑዲ እንዲህ እያደረገች ያለ አግባብ የምትቀጣን ከሆነ፣ ማስተማመኛ እስከምናገኝ ድረስ መካና መዲና ሄደን ከመዘየር ትግራይ ነጃሺና ሐረር ሄደን የአሕባሽ ዶሪሕ እንዘይር እያለ ነበር። ምንም ዐቅል ስለሌላቸው መልስ አያስፈልግም። ሳዑዲ ላይ መጨማለቅ የለም። ሙስሊም ያልሆኑ ወገኖችም ይህንን ክስተት እስልምናን በጭካኔ ለመኮነን ሲጠቀሙበት ነበር። ግን እውነታውን ተጨባጩን ዓለም ሲረዱ፤ ይህ ህግ ይካተትልን ማለት ጀምረዋል። ይህ ህግ ቀድሞ የኢስላም ህግ ስለሆነ እንጂ ቢኖር ኖሮ በጣም ነው የሚፈልጉት። ውስጣቸው ጠንቅቆ ያውቃል። መሰል ህጎች በዋናነት ማስፈራሪያና ማስጠንቀቂያ እንጂ ዝም ተብሎ መስፈርቱን ባላሟላ ላይ ሁሉ ይፈፀማሉ ማለት አይደለም። ግን ሰው እነዚህ ህጎች እንዳሉ ካወቀ፤ ቢፈፅማቸው መተግበራቸው እንደማይቀርለት ስለሚረዳ ከመፈፀም ለመቆጠብ ሙሉ አቅሙን ይጠቀማል። እንጂ በየ ቤተ ክህነቱ በጸበልና ቅዳሴ ስም ዋና ጳጳስ ሳይቀር በይፋ ያገኙትን ሴት ሁሉ መወሰብ የለም። ይሄ ጠንካራ ህግ ቢኖር ኖሮ፤ ለጽድቅ ብላ ቤተ ክርስቲያን የሄደች ሴት በዋናው ቄስ አትጫዎትም ነበር¡ ኸላስ! አላህ የሟቾችን ወንጀል ዐውፍ ይበላቸው። ለቤተሰቦቻቸውም ሶብሩን ይስጣቸው። እኛንም አላህ ከመሰል ወንጀሎች ይጠብቀን።
Открыть в Telegramየመካው ክስተት እውነታ‼ ================ [የተሰራጩ የሐሰት ወሬዎች እና የሸሪዓው ሕጋዊ ብይን (ተዕዚር)] || ✍️ ሰሞኑን በማኅበራዊ ሚዲያ ገጾች ላይ የሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥት ሁለት የባንግላዴሽ ዜጎችን በመካ ከተማ በሞት መቅጣቱን አስመልክቶ እጅግ የተዛቡ፣ የተፈበረኩ እና በእስልምና አስተምህሮና በሳዑዲ ላይ ጥላሸት ለመቀባት የታለሙ መረጃዎች ሲናፈሱ አስተውያለሁ። አንዳንዶች «ለሐኒሙን (ለጫጉላ) ወደ መካ ሄደው ግንባሯን ስለሳመ ተገደ•ሉ»፣ ሌሎች ደግሞ «ባለትዳሮች ሆነው ሳለ በጭካኔ ተገደሉ» እያሉ እውነታውን ገልብጠው አቅርበውታል። 🖊 በዚህ ጽሑፌ የክስተቱን ትክክለኛ ጊዜና ተጨባጭ እውነታ በማስረጃ በማስደገፍ፣ የተሰራጩትን ውሸቶች በማጋለጥ እና በኢስላማዊ የሕግ ሥርዓት (ፊቅህ) ውስጥ ስለ «ሐድ» እና «ተዕዚር» ያለውን እውነታ በወፍ በረር ለመግለፅ እሞክራለሁ። 1️⃣የሳዑዲ ዓረቢያ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር (Ministry of Interior) ይፋ ባደረገው መግለጫ እና የባንግላዴሽ መገናኛ ብዙኃን ባደረጉት የማጣራት ሥራ መሠረት እውነታው የሚከተለው ነው፦ ✅ ማንነታቸውና የመጡበት ዓላማ፦ ✅ በሞት የተቀጡት ግለሰቦች ነዝሩል ኢስላም ዐብዱልበሲር (ብራህማንባሪያ ከተሰኘች የባንግላዴሽ መንደር) እና ሲቲ አኽተር (ከሚርዛፑር፣ ባንግላዴሽ) የተባሉ ናቸው። ✅ ሁለቱም ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ የገቡት በፈረንጆቹ ህዳር 2022 ላይ በጽዳት ሠራተኝነት ተቀጥረው (በቢንላደን/አል-መጃል ኩባንያ ሥር) ለመሥራት እንጂ ለሐጅ ወይም ለዑምራ አልነበረም። ✅ ሁለቱም ተጋቢዎች (ባልና ሚስት) አይደሉም። የነዝሩል አባት ልጁ ያላገባ መሆኑን ለሀገሩ ሚዲያዎች አረጋግጧል፤ ሲቲ አኽተርም በተመሳሳይ ለብቻዋ ለሥራ የሄደች እንጂ ከነዝሩል ጋር ምንም ዓይነት የጋብቻ ትስስር አልነበራትም። ✅ ሁለቱ ግለሰቦች በሥራ ገበታቸው ወቅት ባዳበሩት ግንኙነት፣ በመካ ከተማ በሚገኝ የተቀደሰ የዒባዳ ሥፍራ (በመስጂድ ውስጥ/በተከለለ ደረጃ መወጣጫ ክፍል) (ከሊፍት ባሻገር ለምሳሌ የአደጋ ጊዜ መወጣጫ ደረጃ እንደሚባለው ማለት ነው) ግልጽ የሆነ የዝሙት ወንጀል (ፊዕለል ፋሒሻ) ፈጽመዋል። መርፌና ክር መገናኘት ሳይሆን ፋሒሻ ነው። ✅ ድርጊቱ ሲፈጸም አንድ የሕንድ ዜግነት ያለው ጓደኛቸው በፎቅ ደረጃው ሥር ጥበቃ እንዲያደርግ የተመደበ ሲሆን፣ ይኼው ግለሰብ ድርጊቱን በስልክ ቪዲዮ ቀርፆታል። ✅ በኋላ ላይ ቪድዮውን ከቀረፀው ህንዳዊ ጓደኛቸው ጋር በተፈጠረ አለመግባባት (የተጣሉ ጊዜ) የቪዲዮ ምስሉ በማኅበራዊ ሚዲያና በሰዎች ዘንድ እንዲሰራጭ ተደርጓል። ሲጣሉ የቀረፃቸውን ነውር አሰራጨባቸው። ብዙ ጊዜ በመሰል ደረጃዎች ላይ ካሜራ ስለማይኖር፣ ጓደኛቸው ነው ተደብቆ የቀረፃቸው። ✅ ጥፋቱ የተፈጸመውና ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት በግንቦት/ነሐሴ 2023 ላይ ነበር። ✅ የሳዑዲ የጸጥታ አካላት ሦስቱንም ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር አውለዋል። ቪዲዮውን የቀረፀውና ያሰራጨው የሕንድ ዜጋ በ20 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጥቷል። ✅ በወንጀሉ ዋና ፈፃሚዎቹ ላይ የተደረገው የዳኝነት ምርመራ ለሦስት ዓመታት ከሦስት ወር በላይ ፈጅቷል። ጉዳዩ በጅዳና በመካ ፍርድ ቤቶች ታይቶ፣ ይግባኝ ተብሎ በ13 ዳኞች በከፍተኛ ደረጃ ከተመረመረና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ ካገኘ በኋላ በንጉሣዊ ትዕዛዝ ጸድቋል። እንጂ ዝም ብሎ ድንገት የተከሰተ አይደለም። በእስር ላይ ሳሉም ወላጂቻቸው ጋር ይደዋወሉ ነበር። ✅ ቅጣቱ የተፈጸመው ረቡዕ፣ 3 ጁማዳል አወል 1448 ሂጅሪያ (ኦክቶበር 14 ቀን 2026) በመካ ክልል ነው። 2️⃣ ከዚህ ክስተት በኋላ የተከሰቱ እውነታና ውሸቶችን ስናይ፦ ውሸት 1️⃣፦ «ባለትዳር ነበሩ፤ ለጫጉላ (ለሐኒሙን) ነበር የሄዱት» ⬇️ ይህ ፍጹም ውሸት ነው። የሁለቱም ቤተሰቦች በባንግላዴሽ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት፣ ሁለቱም ተበድረው ወደ ሳዑዲ የሄዱት በዝቅተኛ ደመወዝ የጽዳት ሥራ ለመሥራት ነው። አንዱ ከሌላው ጋር ምንም ዓይነት የትዳር ትስስር የላቸውም። ውሸት 2️⃣፦ «ግንባሯን ስለሳመ ብቻ ነው የተገደሉት» ➡️ ይህ ድንቁርና ወይም ሆን ተብሎ የተፈበረከ ቅጥፈት ነው። በዓመት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ባለትዳሮች፣ አዛውንቶችና ቤተሰቦች ሐጅና ዑምራ ያደርጋሉ። ባል የሚስቱን ግንባር፣ እጅ ወይም ጭንቅላት በፍቅርና በእዝነት መሳም፣ ሚስት የደከማትን ባሏን እግር ደግፋ መተኛት ወይም እጅ ለእጅ ተያይዞ መጓዝ በሐረም ውስጥ በየቀኑ የሚታይ የተለመደ ሰብዓዊና ኢስላማዊ መስተጋብር ነው። እኔም በግሌ ከባለቤቴ ጋር ዑምራ ስንሄድ ፈታ ብለን ተያይዘን ነው የምንንቀሳቀሰው። ሲጀመር ሐላልና ሐራምኮ ያስታውቃል። ሐራም ጥግ ለጥግ መደባበቅ ይፈልጋል፤ ሐላል ግን ነፃነት ነው። ይህ ማለት ግን ባለትዳሮችም ቢሆኑ በህዝብ ፊት መደረግ የሌለበትን ነገር ማድረግ አለባቸው ማለት አይደለም። ከዚያ ውጭ ማንም ሰው የባለቤቱን ግንባር በመሳሙ ምክንያት ታስሮም ሆነ ተቀጥቶ አያውቅም። የእነዚህ ግለሰቦች ክስ ግን «በአምልኮ ሥፍራ ውስጥ የተፈጸመ የብልግና እና የዝሙት ድርጊት – ፊዕሉል ፋሒሻ» መሆኑ በፍርድ ቤቱ በይፋ ተረጋግጧል። ውሸት 3️⃣፦ «በሐጀረል አስወድ (ጥቁሩ ድንጋይ) አጠገብ ተቀርጾ የተሰራጨው ቪዲዮ» 🚫 የዓለም አቀፍ የመረጃ አጣሪዎች (Fact-checkers) እንዳረጋገጡት፣ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ እየተዘዋወረ ያለው ግድያውን የሚያሳይ የተባለው ቪዲዮ በ2015 በተፈጸመ ፍጹም የተለየ ወንጀል የተቀረጸ የድሮ ተንቀሳቃሽ ምስል ነው። ከዚህ ክስተት ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የለውም። 3️⃣ ስለ ጉዳይ ይህን ካልን ዘንድ፤ ለመሆኑ የሸሪዓው ሕጋዊ ብይን በተለይም ሐድ እና ተዕዚር ምንድን ነው❔ ✅ የእስልምና የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ በሦስት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላል፦ ቂሷስ (አጸፋዊ ቅጣት)፣ ሐድ (የተወሰነ ቅጣት) እና ተዕዚር (የዳኛ አስተዳደራዊ/ተግሣጻዊ ቅጣት)። ሀ) ሐድ (الحدود) ምንድን ነው? ✅ «ሐድ» ማለት በቁርኣንና በሐዲሥ ውስጥ የቅጣት መጠኑና ዓይነቱ በቀጥታ የተደነገገ፣ ማንም ሰው (ዳኛም ሆነ መሪ) ሊቀንሰው፣ ሊጨምረው ወይም በይቅርታ ሊተወው የማይችል መለኮታዊ ድንጋጌ ነው። 🍔 ለምሳሌ፦ ➡️ የትዳር አጋር እያለው ዝሙት የፈጸመ (በድንጋይ ተወግሮ መግደል)፤ ➡️ ያላገባ ሰው ዝሙት ቢፈጽም (100 ጅራፍና የአንድ ዓመት ስደት)፤ ➡️ ስርቆት (የእጅ መቆረጥ — መስፈርቶቹ ሲሟሉ)፤ ➡️ ሒራባህ (የመንገድ ላይ ሽብርተኝነትና ዝርፊያ)። ለ) ተዕዚር (التعزير) ምንድን ነው? ✅ «ተዕዚር» ማለት በሸሪዓው ውስጥ የተወሰነ የሐድ ቅጣት ላልተቀመጠላቸው፣ ነገር ግን ኃይማኖትን፣ ሕይወትን፣ አእምሮን፣ ዝርያን ወይም ሀብትን አደጋ ላይ ለሚጥሉ ወንጀሎች በዳኛው ወይም በመሪው (በወልይዩል አምር) ውሳኔ የሚሰጥ አስተማሪና የማስጠንቀቂያ ቅጣት ነው። ✅ የተዕዚር ዓላማ ወንጀለኛውን ማረም፣ ማኅበረሰቡን ከብልሹ አሠራር መጠበቅ እና ወንጀሉ ዳግም እንዳይስፋፋ አጥር ማበጀት ዘጅር ነው።
Открыть в Telegramበአለም ታሪክ ውስጥ በክርስትና ቅዱስ በሚባልበት ስፍራ ቤተክርስቲያን ውስጥ ግብረሰዶማውያንን ( ሴት ለሴት ወንድ ለወንድ) ስታጋባ አይተናል ከዛም አለፍ ብሎ ቄሶቻቸውና ካህናት በአደባባይ በዝሙት ሲንዘላዘሉ አይተናል፣ ታድያ በዝህ የቆሸሸ አስተሳሰባቸው እንዴት ይሄን እውነታ ይቀበሉት? ከ2 ቢልየን በላይ ሙስሊሞች ወደ አንድ ቦታ ተቅጣጭተው በሚሰግዱበት ቅዱስ ስፍራ በዝሙት ስፍራውን ማዋረድ እንደ ቤተክርስቲያን ግብረሰዶማውያንን ማጋባትና በስፍራው እንደፈለጉ እንደ መዘሞት በዝምታ የሚታለፍ ተግባር አይደለም።
Открыть в Telegramሁለተኛ ሚስት እንዳገባ ስታወቅ እራሷን ስታ ወደቀች👇 ኢስላማዊ ድራማ 👇 https://youtu.be/01QWRz5pfNk https://youtu.be/01QWRz5pfNk https://youtu.be/01QWRz5pfNk
Открыть в Telegramሀጂ ኢብራሂም ቱፋ በኦሮምኛ 'አብይ አህመድ አሊን ነብይ ለማለት ምንም አልቀረንም ነበር ... በእስልምና የመጨረሻው ነብይ ስለተላከ ውሳኔያችንን በማሻሻል ወልይ ብለነዋል...." ያሉበት ቪዲዮ ይሄው። በፊት ሃጂ ሙፍቲ ኡመር 'እህህህ....' ብለው ጉሮሯቸውን ሲጠርጉ እንኳን 'በኮድ መንግስትን እየደገፉ ሙስሊሙን እያሳጡ ነው....' ብለው እንደ ሳሙና ምርት አንድ አይነት ፁሁፍ ይዘው የሚወጡት እነ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል ፣ ካሚል ሸምሱ ፣ አቡበከር አህመድ ፣ በድሩ ሁሴን ፣ ያሲን ኑሩ ምናምን ይሄንን ባላየ አልፈውታል ምክንያቱም ግልፅ ነው። ዕድሉን ቢያገኙ እነሱም ይሄን ከማለት ስለማይመለሱ 🙂 https://t.me/ZEKR_MENZUMA YouTube 👇 https://youtube.com/shorts/35AFn05Zt8A?si=neYnH4ztfe8h-tx-
Открыть в Telegramእንዴት ደስ የሚል ፣ ስሜትን የሚፈታተን ቪዲዮው ነው በአላህ ? ለአንድ ሙስሊም ወላጅ ከልጁ ይሄንን 'ቁርዓን ጨርሻለሁ...' የሚለውን ቃል መስማት የሚሰጠው ደስታ ቀላል አይደለም። ከምንም በላይ ነው። በናፍቆት የሚጠብቀው ቀን ነው። የልጁ አነጋገር ፤ ሁኔታው ፣ መሽኮርመሙ አነጋገሩ በሙሉ ግን ልብ ይነካል። ከምንም በላይ ግን.... 'ለአላህ ብዬ እወድሻለሁ...' ያላት ነገር 😑❤ 👇👇👍 https://t.me/ZEKR_MENZUMA https://youtube.com/shorts/9lAq4dtc7kg?si=g03soVvsL9BfAC4H
Открыть в Telegramከአመታት በፊት #መዉሊድ ኢሽቅ ላይ የተፈፀመ የቦም^ ብ ጥቃት👇👇👇 https://youtu.be/Cxm9uhuNyDg?si=tayvr-bksdXT3Lhp ይህንን የቦምብ ጥቃት የፈፀመው አሕመድ ሙስጠፋ ይባላል ። ከባሌ አካባቢ 100 ሺህ ብር ተከፍሎት ይህንን የሽብር ተግባር እንደፈፀመ አምኖ 10 ዓመት ተፈርዶበታል ። ዶክተር ዐብይ ወደ ስልጣን እንደመጡ አካባቢ በፖሊስና ሕብረተሰብ ዝግጅት ለይ ሙሉ ዜናው ቀርቧል❗️
Открыть в Telegramጉዳዮቻችሁን በሚስጥር በመያዝ ታገዙ! በተለይ ከዘመዶቻችሁ ስለ ጤንነትህ፣ ስለ ህይወትህ መረጋጋት፣ ስለ ልጆችህ፣ ስለ ደሞዝህ፣ ስለ እቅዶችህ እንዲሁም ስለተሰጡህ ጸጋዎች (በረከቶች) በማንም ፊት አታውራ ። በአጠገባችሁ፣ በአካባቢያችሁ ወይም በዘመዶቻችሁ መካከል ያሉ ስኬታማ ሰዎችን ተመልከቱ፤ አብዛኞቹ ስኬታማ ሰዎች ምስጢር ጠባቂና ነገራቸውን የሚደብቁ (ድብቆች) ናቸው ። ከዚህም በተጨማሪ ለስኬት ከበቁበት ትልቁ ምክንያት አንዱ የተወለዱበትን አካባቢና ማህበረሰብ ጥለው መሰደዳቸው (መለየታቸው) ነው ። ከአብዛኞቹ ዘመዶቻቸው ዓይን ርቀው ሲሄዱ በአዲሱ አካባቢያቸው ስለእነርሱ የሚያውቅ ስለ እነርሱ የሚያወራ ስለሌለ ለስኬት የሚያግዙ ምቹ ሁኔታዎችን ማግኘት ችለዋል እዚያ የሚከታተሏቸው አይኖች የሉም የሚያቃቸው ሰው የለም ሁሉም ሰው በራሱ ሥራና ስኬት ላይ ብቻ የተጠመደ ስለ ሆነ ነው ። ባደግክበት አካባቢ ግን ምቀኝነት ጣልቃ ገብነቶች ወሬዎች ይበዛሉ ። የነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) ዋነኛ ምቀኞች እነማን ነበሩ ? የገዛ የጎሳቸውና የአጎቶቻቸው ልጆች ነበሩ አቡ ጃህል ለዚህ ግልጽ ማሳያ ነው ይህም የሚያሳየው የቅርብ ሰው ይበልጥ እንደሚቀና ነው፤ ምክንያቱም እራሱን ካንተ ጋር እኩልና አንድ ዓይነት አድርጎ ስለሚያይ፣ ካንተ ጋር የሥጋና የደም ትስስር ስላለው "እሱ እንዴት ተሳካለት? እኔስ ለምን ቀረሁ?" በሚል የውድድር መንፈስ ይነሳሳል ። ምናልባትም ሌሎች ዘመዶች አንተን በአክብሮትና በክብር ሲመለከቱህ እሱን ግን ያን ያህል ስላላዩት የበታችነት ስሜት ሊያድርበት ይችላል ። በነቢዩ ያዕቆብና በነቢዩ ዩሱፍ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ተግሣጽና ትምህርት አለ ያዕቆብ ልጁ ያየውን ሕልም ለወንድሞቹ እንዳይነግራቸው አዞታል፤ ምንም እንኳን እነሱ የነቢይ ልጆች ቢሆኑም የሱፍ ከቅናታቸው መትረፈ አልቻለም ። ስለዚህ ሊደበቅ የሚችለውን ነገር ሁሉ ደብቅ፤ በባንክ ያለህን ገንዘብ፣ የጋብቻ እቅድህን፣ የሥራ እድገትህን፣ የልጆችህን በትምህርት ቤት ያላቸውን ብልጫ... ይህንን ሁሉ በዋትስአፕ ግሩፖችና በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ መለጠፍ ግዴታ አይደለም ። ችግሩ ያለው በተሰጠህ ጸጋ ላይ ሳይሆን፤ "ሰሚው ማን ነው? እንዴትስ ይሰማል? ለምንስ ይሰማል?" በሚለው ላይ ነው። የአንተን ደስታ፣ መረጋጋትና እድገት መሸከም የማይችሉ ሰዎች አሉ። እነዚህ ሰዎች የግድ ክፉዎች ስለሆኑ ላይሆን ይችላል፤ ነገር ግን ራስን ከሌላው ጋር ማወዳደር ለአንዳንድ ሰዎች በጣም ከባድ ስለሚሆንባቸው ነው ። ሰሃባ (የነቢዩ ባልደረባ) ሆኖ ሳለ እንኳ ሌላውን ሰሃባ በዓይን (በክፉ ዓይን/ቡዳ) የነካበት ሁኔታ አለ፤ ስለሆነም ምስጢር መያዝን ልማድ አድርግ ምስጢር መያዝ ማለት ጭካኔ፣ መገለል፣ መኩራት ወይም ሰብአዊነትን መካድ አይደለም ። ማውራት ከፈለግክ መልካም፣ ልቡ ንፁህና እምነት የሚጣልበት፣ በአንተ ደስታ የሚደሰትና በአንተ ሐዘን ያለ ምንም ምቀኝነት የሚያዝን ሰውን መርጠህ አውራ በዚህ ዘመን እንዲህ ዓይነቱን ሰው ማግኘት አይቻልም ካገኘህማ በአላህ ይሁንብኝ አንተ በጣም የታደልክ ነህ ! ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) እንዲህ ብለዋል፦ "ጉዳዮቻችሁ እንዲሳኩላችሁ በሚስጥር በመያዝ ታገዙ፤ ምክንያቱም እያንዳንዱ የጸጋ ባለቤት ተመቃኚ ነውና።" (ሐዲሱ ትክክለኛ መሆኑን አልባኒ አረጋግጠዋል።) በዚህ ሐዲስ ውስጥ በተለይም ፍላጎትህን ወይም ጉዳይህን ለማስፈጸም በምትጥርበት ወቅት ምስጢርህን እንድትጠብቅ ትልቅ ፍንጭ ተቀምጦልሃል በተለይ ጉዳይህ ከመሳካቱ በፊት በሂደት ላይ ባለህበት፣ በምታስብበትና በምታጠናበት ወቅት ድብቅ ሁን ምክንያቱም ጉዳዮችህ ከመጠናቀቃቸው በፊት በቀላሉ ሊበላሹ ለምቀኝነትና ሊጋለጡ ይችላሉ ። ምስጢር መያዝ ምቀኛን፣ ቀናተኛንና በልቡ ውስጥ በሽታ ያለበትን ሰው ለመከላከል እንደ ጋሻ ሆኖ ያገለግላል። አንተን ከሌሎች የምትለይበትን ልዩ ነገር ለሰዎች በማሳየትህ የምታገኘው ምንም ጥቅም የለም፤ መደበቅ የምትችለው ከሆነ ደብቀው፤ መደበቅ የማትችለው ከሆነ ደግሞ በእሱ አትመካ (አትፎክር)። በሸሪዓዊ ዚክሮች (ዱዓዎች) ላይ በርታ፤ ራስህን፣ ቤተሰብህን፣ እና አላህ የለገሰህን ልዩ ጸጋ (ገንዘብ፣ ሥራ፣ ትዳር፣ ውበት፣ ልጆች፣ መልካም ስም) ጠዋትና ማታ በአላህ ጥበቃ ስር አደራ ስጥ ። አላህ ጤና ይስጣችሁ። https://t.me/ZEKR_MENZUMA
Открыть в Telegram🤍يَوْمُ عَرَفَة🤍 በዐረፋ ቀን ሊባሉ ከሚገቡ ምርጥ ዚክሮች ውስጥ:- لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ وَحْدَهُ لَا شَرِيكَ لَهُ، لَهُ الْمُلْكُ وَلَهُ الْحَمْدُ يُحْيِي وَيُمِيتُ وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ، وَفِي رِوَايَةٍ: وَهُوَ حَيٌّ لَا يَمُوتُ. (أَلْفُ مَرَّةٍ) 🧡 "ላ ኢላሃ ኢልለላሁ ወህደሁ ላ ሸሪከ ለሁ፣ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሃምዱ ወሁወ አላ ኩልሊ ሸይኢን ቀዲር።" በአንዳንድ ዘገባ ደግሞ "ወሁወ ሃዩን ላ ያሙት የሚል ተጨማሪ አለ። (1000* ጊዜ) وَسُورَةَ الْإِخْلَاصِ (أَلْفَ مَرَّة) 🧡ሱረቱል ኢኽላስ (አንድ ሺህ (1000×ጊዜ) وَسُورَةَ الْفَاتِحَةِ (مِئَةَ مَرَّة) 🧡ሱረቱል ፋቲሃ (መቶ ጊዜ) وَسُورَةَ الْحَشْرِ (مَرَّة). 🧡ሱረቱል ሐሽር (1* ጊዜ) https://t.me/ZEKR_MENZUMA
Открыть в Telegramእናንተ እዚህ ኢምራን እፎይ እያላችሁ ታወራላችሁ ይህች እህታችን ግን መላዉን ዓለም እያስጨነቀች ነዉ ቲክታክን ተቆጣጥራዋለች ክርስsትናን ብትንትኑን አዉጥታዋለች 💪 ብቻዋን ሆና 20 እየገጠመች ትዘርራቸዋለች ... ዓለም በሙሉ ወደ እስልምና እየተቀየረ ነዉ !! ፎሎ አድርጓት https://www.tiktok.com/@korrathetaymi?_r=1&_t=ZS-96bn5qXQu2i
Открыть в Telegramአክሱም ላይ ዝግ ስብሰባ ተካሂዷል። በስብሰባው በሙስሊሙ ላይ ጫና በመፍጠር የጭቆና ህግችን የያዘ ሰነድ ቀርቧል። የሙስሊም ተወካዮች እና በመንግስት በኩል ደግሞ ምክትል ከንቲባ አበበ እንዲሁም የጸጥታ ዘርፍ ምክትል ኃላፊ ቴዎድሮስ በተጨማሪ የተከማዋ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ተስፋዬ ተገኝተዋል ነገር ግን ውይይቱን በስፋት ሲመሩ የነበሩት ከክርስትና በኩል ያሉት የርዕሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን አስተዳዳሪ ነቡረ እድ ጎደፋ መርሃ መሆናቸው ተነግሯል። ስብሰባው ላይ ምን ተፈጠረ ? 🌐 ለሙስሊሞች ጨቋኝ የሆነ ሰነድ በማዘጋጀት አንብበው እንዲፈርሙ እንዲስማሙ ጫና ተደርጓል። በተዘጋጀው ሰነድም 1️⃣ በትምህርት ቤቶች ላይ ሂጃብ ማድረግን ይከለክላል 2️⃣ ለዘመናት ሲሰግዱበት የነበረው የሹቅ መስጂድ ላይ ጁምዓ እንዳይሰገድ ያግዳል ። 3️⃣ በኪራይ ቤት የሚገኙ መስጂዶች ሙሉ በሙሉ እንዲዘጉ ያውጃል። 4️⃣የአዛን ጥሪ በድምፅ ማጉያ (speaker ) ማድረግ አይቻልም 5️⃣ አስክሬን ይዞ ሲኬድ ዋና አስፋልት መንገድ መጠቀም ይከለክላል ። አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ይናገራል። የሙስሊም ተወካዮች ይህንን ሰነድ ኮፒ ይሰጠን አንብበን እንወስን ቢሉም እንዳይሰራጭ ስለፈሩ ከልክለዋቸዋል። 🔘 በቻልነው መጠን ለወንድሞቻችን ድምፅ ልንሆን ይገባል። አክሱም ላይ ያሉ ሙስሊሞችን ነፃ የማናወጣቸው ከሆነ ኢትዮጵያ የክርስትና ሀገር ናት ሙስሊሞች ሀገራችሁ አይደለም የሚለው የተረት ሀሳብ ከተለያዩ ቦታዎች ብናጠፋም መቅበር ግን አንችልም። አክሱም ላይ ላለው ችግር የምንጮኸው ለእነሱ ብቻ ሳይሆን ለኢስላም እና ለኢትዮጵያዊነታችን ነው። https://t.me/ZEKR_MENZUMA
Открыть в Telegram