'The greatest freedom is to be unable to be wretched. The greatest happiness is to be unable to be unhappy.' Gerhard
Открыть в TelegramПосты канала መልህቅ
ስለነገ መጨነቃችንና መሯሯጣችን የዛሬውን ትጋታችንን እንዳይሰርቅብንና እግዚአብሄርን እንዳያሳጣን እንጠንቀቅ። እግዚአብሄር ካልነበረበት ጉዞ የመጣ ስኬት እንደውም በጣም የከበደውንና እግዚአብሄር ብቻ የሚመልሰውን የነፍስን የማያቋርጥ ፍለጋ አይሞላምና ያኔም ከዜሮ እንጀምራለን። ስለዚህ ከወዲሁ በኢየሱስ እንርካ። ከወዲሁ እሱ ሙላታችን ይሁን። ጨርሰን እንጀምር።
Открыть в Telegramከባለፈው ውይይት አንዱ ድንቅ ያለኝ ነገር ይህንን እውነት ለመቃወም ወንድማችን ማስረጃ ብሎ ያመጣው ክፍል ነው እርሱም ፊልጲሲዩስ 3:8 ላይ ‘.. በሕግ ስለሚገኝ ጽድቅ ብትጠይቁ፥ ያለ ነቀፋ ነበርሁ።’ የሚለው.. እውነት አሁን ከዚህ ክፍል ተነስተን ጳውሎስ በእግዚአብሄር ፊት ያለ አንዳች ሀጥያት ህግጋቱን በሙላት ፈፅሟል ማለት እንችላለን ? ቆይ ጳውሎስ ሀጥያተኛ አይደለምን ? አይደለም ካልን ታድያ ለምን ሰው ሁሉ ሀጥያትን ሰርቷል አለ ? ከራሱ ጋር ሊጋጭ ነው። አዎ ነው ከተባለ ደግሞ መቼም ሀጥያት የሕግ መተላለፍ ነውና በእግዜሩ ፊት በእርግጥም ነቀፋ ነበረበት ስለዚህም ከፍርድ በታች ነው። For that matter ብዙ ሳንለፋ ከሀጥያተኞች ዋና ነኝ ብሎ እራሱ አስቀምጧል። ስለዚህ ይሄ ክፍል አውዱ ሌላ ነው ማለት ነውና መጠቀሱ አንዳች ፋይዳ አይኖረውም። በተረፈ በሕጉ ሊፀድቅ የማይችልበት ምክንያት ጭራሽ በተቃራኒው በሀጥያተኛ የወደቀ ባህሪው ምክንያት ባለመቻሉ እንደሆነ እንደመሰከረልን ከላይ አሳይቻቹሀለው።
Открыть в Telegramጳውሎስ በህግ እንደማይፀደቅ አስተምሯል። ግን ለምንድን ነው በህጉ መፅደቅ ያልተቻለው ? ጳውሎስ መልስ በጣም ግልፅ ነው። ህግ ከእግዚአብሄር ከእራሱ የተቀዳ ነውና በራሱ ሊያፀድቅ ወይም ህይወትን ሊሰጥ ማይችልበት አንዳች ችግር እንደሌለበትና እንደውም ጭራሽ ለህይወት የተሰጠ እንደሆነ ነግሮናል። (ሮሜ 7) ታድያ ችግሩ ማን ጋር ነው ሲባል እኛጋ ያለ ሀጥያተኛ ባህሪ እንደሆነ ሲያስቀምጥ ‘ሕግ መንፈሳዊ እንደ ሆነ እናውቃለንና ፤ እኔ ግን ከኃጢአት በታች ልሆን የተሸጥሁ የሥጋ ነኝ።’ ፤ ‘በእኔ ማለት በሥጋዬ በጎ ነገር እንዳይኖር አውቃለሁና፤ ፈቃድ አለኝና፥ መልካሙን ግን ማድረግ የለኝም።’ ይላል። ለጥቆም ህግ አድርግ አታርግ በማለቱ ሀጥያትን አውቃለሁ ፤ ስለዚህም ‘ኃጢአት .. ምክንያት አግኝቶ ምኞትን ሁሉ በትእዛዝ ሠራብኝ’ ፤ ‘ኃጢአት ምክንያት አግኝቶ በትእዛዝ አታሎኛልና በእርስዋም ገድሎኛል።’ (Rom 7) እንዲሁም ህጉ ማፅደቅ ያልቻለው ከስጋ ድካም የተነሳ ነው (Rom 8) በማለት ህጉን እንዳንፈፅም የሚቋቋመን ሰውነታችን ውስጥ ያለ ሀጥያተኛ ባህሪ ፤ እኛ ጋር ያለ ችግር እንጂ በጭራሽ ከህጉ ጉድለት እንዳልሆነ በግልጥ ይናገራል። በተቃራኒው አቅጣጫም ሄዶ ደግሞ what if ህጉን መፈፀም ብንችልና ብንፈፅም ህይወትን ይሰጠናል ? የሚለውን ጥያቄ ሲመልስ የሚያደርጋቸውና የሚጠይቀውን ሁሉ የሚያሟላ በህይወት ይኖራል ብሎ ቀጥታ አስቀምጧል። (ሮሜ 10:5) ይህን ክፍል የጠቀሰው እግዚአብሄር እራሱ ህጉን በሙላቱ የሚፈፅመው ህይወትን ያገኝበታል ካለበት ከዘሌዋውያን 18:10 መሆኑን መዘንጋት የለብንም። ከዚህም በዘለለ ሮሜና ገላትያ ላይ ቀጥታ ስለፅድቅ እያወራ በህጉ ቃልኪዳኑ የማይወረሰው ህጉ ፍፁም መታዘዝን ስለሚፈልግ እንደሆነ ፤ ለማይፈፅመው ደግሞ እርግማንንና መቅሰፍትን ስለሚያመጣ እንደሆነ አስቀምጧል። እነዚህ ሁሉ ማስረጃዎች እኔ ከኪሴ የመዠረጥኳቸው ሳይሆኑ እራሱ ጳውሎስ ቀጥታ የተናገራቸው ናቸው። ክፍሎቹን ላስቀምጥላቹ። ወደ ሮሜ ሰዎች 3:20 (AMH) •••••••••• ²⁰ ይህም የሕግን ሥራ በመሥራት ሥጋ የለበሰ ሁሉ በእርሱ ፊት ስለማይጸድቅ ነው፤ ኃጢአት በሕግ ይታወቃልና። ወደ ሮሜ ሰዎች 7:7-11 (AMH) •••••••••• ⁷ እንግዲህ ምን እንላለን? ሕግ ኃጢአት ነውን? አይደለም፤ ነገር ግን በሕግ ባይሆን ኃጢአትን ባላወቅሁም ነበር፤ ሕጉ። አትመኝ ባላለ ምኞትን ባላወቅሁም ነበርና። ⁸ ኃጢአት ግን ምክንያት አግኝቶ ምኞትን ሁሉ በትእዛዝ ሠራብኝ፤ ኃጢአት ያለ ሕግ ምውት ነውና። ⁹ እኔም ዱሮ ያለ ሕግ ሕያው ነበርሁ፤ ትእዛዝ በመጣች ጊዜ ግን ኃጢአት ሕያው ሆነ እኔም ሞትሁ፤ ¹⁰ ለሕይወትም የተሰጠችውን ትእዛዝ እርስዋን ለሞት ሆና አገኘኋት፤ ¹¹ ኃጢአት ምክንያት አግኝቶ በትእዛዝ አታሎኛልና በእርስዋም ገድሎኛል። ወደ ሮሜ ሰዎች 8:3 (AMH) •••••••••• ³ ከሥጋ የተነሣ ስለ ደከመ ለሕግ ያልተቻለውን፥ እግዚአብሔር የገዛ ልጁን በኃጢአተኛ ሥጋ ምሳሌ በኃጢአትም ምክንያት ልኮ አድርጎአልና፤ እንደ መንፈስ ፈቃድ እንጂ እንደ ሥጋ ፈቃድ በባንመላለስ በእኛ የሕግ ትእዛዝ ይፈጸም ዘንድ ኃጢአትን በሥጋ ኰነነ። ወደ ሮሜ ሰዎች 10:3-5 (AMH) •••••••••• ³ የእግዚአብሔርን ጽድቅ ሳያውቁ የራሳቸውንም ጽድቅ ሊያቆሙ ሲፈልጉ፥ ለእግዚአብሔር ጽድቅ አልተገዙም። ⁴ የሚያምኑ ሁሉ ይጸድቁ ዘንድ ክርስቶስ የሕግ ፍጻሜ ነውና። ⁵ ሙሴ ከሕግ የሆነውን ጽድቅ የሚያደርገው ሰው በእርሱ በሕይወት እንዲኖር ጽፎአልና። ወደ ገላትያ ሰዎች 3:10-12 (AMH) •••••••••• ¹⁰ ከሕግ ሥራ የሆኑት ሁሉ በእርግማን በታች ናቸውና፤ በሕግ መጽሐፍ በተጻፉት ሁሉ ጸንቶ የማይኖር የማያደርግም ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፎአልና። ¹¹ ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሎአልና ማንም በእግዚአብሔር ፊት በሕግ እንዳይጸድቅ ግልጥ ነው። ¹² ሕግም ከእምነት አይደለም ነገር ግን። የሚያደርገው ይኖርበታል ተብሎአል።
Открыть в Telegramየትላንቱ ውይይት ላይ ላልነበራችሁ ይኅው በአጭሩ 😁 እኔ - ፅደቅ ከሮሜ 1 እስከ 4 ባለው አውድ በ law court Contex ውሰጥ የገባና የኩነኔ ተቃራኒ ሆኖ ጥቅም ላይ የዋለ ነውና legal pronouncement ነው አኖኒ ፦ አዎ ነው እቀበላለሁ እኔ ፦ በዚህ law court ውስጥ እየተገመገመ ያለው ጉዳይ የወራሽነት ጉዳይ ነው አኖኒ ፦ አዎ ነው እቀበላለሁ እኔ ፦ ጳውሎስ ይሄ ወራሽነት የሚገኘው በህግ ስራ ሳይሆን በእምነት ነው ይላል። ለምንድነው ህግ (ያላስወረሰው) ያላፀደቀው ? አኖኒ ፦ በቃ ስለማያፀድቅ ነዋ (yes he actually said that😅) እኔ ፦ አብርሀም በስራው አልፀደቀም ሲል ይሄ ስራ በዛ ሰአት ሊሰራ የሚችለውን ስራ ሁሉ የሚጠቀልል ነው ወይስ የሙሴ ህግን ብቻ ነው ? አኖኒ ፦ የሙሴን ህግ ብቻ ነው እኔ ፦ ግንኮ ሮሜ 4:4 ላይ ‘ለሚሰራ ደሞዝ እንደ እዳ ነው ‘ የሚለው principle በሙሴ ህግ ብቻ የሚገደብ አይደለም ይልቁኑ ይሄን principle የሚያሟሉ ማንኛውም ስራዎችን ሁሉ ይጠቀልላል አኖኒ ፦ አይ አይጠቀልልም ምክንያቱም ለምሳሌ አንድ ባርያ ለጌታው ስራ ሰርቶ ስላስደሰተው ጌታው ራርቶለት ነፃ ሊያወጣው ይችላል ስለዚህ በዚህ አውድ እሱ principle አይሰራም እኔ ፦ እንዴ ከላይ ሮሜ ከ1 እስከ 4 አውዱ law court ውስጥ ያለ መሆኑን ተስማምተን አልነበርንዴ ? እሱን ጥለህ የጌታና የባሪያን relationship ከየት አመጣህ ? በሮሜ 1-4 ውሰጥ ምኑ ጋር ነው ያለው ? ይሄ categorical fallacy አይደለምን ? አኖኒ፦ የጳውሎስን አውድ ጥዬ በፈለኩት በማይገናኝ ሀሳብ Principleኡን መስበር እችላለሁ (emphasis mine😁) እኔ፦ ግን በሎጂክ ህግ አንድን ነገር ለመቃረን እና እንደማይሰራ ለማሳየት ከሁሉ አስቀድመህ በተመሳሳይ አውድ ውስጥ መግባት የለብህም ? አኖኒ ፦ እሱማ አለብኝ እኔ ፦ አሪፍ ታድያ ያ ማለትኮ ጳዎሎስን ያመጣውን መርህም ለመስበርኮ መጀመሪያ በአውዱ መግባት አለብህ ማለት ነው አኖኒ፦ አያይ በቃ በክፍሉ ሽታውም በሌለ በማይገናኝ ሀሳብ Principleኡን መስበር እችላለሁ አለቀ! (emphasis mine😅) እኔ ፦ እሺ እሱን ተወውና ለምንድን ነው የሙሴ ህግ አያፀድቅም የተባለው? አኖኒ ፦ ስለማያፀድቅ ነዋ እኔ ፦ እሱ መልስ አይሆንም አንደኛ circular ይሆናል ሁለተኛ የጳውሎስ claim arbitrary ይሆናል ሌላ ምክንያት መኖር አለበት አኖኒ ፦ አይ በቃ ስለማያፀድቅ ነው አለቀ! በቃ ከሞላ ጎደል ጠቃሚው ፓርት ይኅው ነበር እሱም በዚህ መልኩ አለቀ። ጉዳዩ በጣም Nounce የበዛበት ስለሆነ እዚህ እንደለመድነው ተደማምጠን ለመረዳት ብናወጋ ከዚ በጣም የተሻለ እናወራ ነበር። የተለመደውን ደስ የማይል የቲክቶክ የውይይት አካሄድ አኖኒ ላይ በማየቴ ባዝንም ያም ሆነ ይህ በመጣበት መንገድ አስተናግጄው ባወራንበት ነጥብ ሁሉ ላይ የአስተምህሮውን ጥንካሬ አሳይቻለሁ ብዬ አስባለሁ።
Открыть в TelegramПереслано из Classical Protestant
ሠላሳ ዘጠኙ የአንግሊካን ቤተ ክርስቲያን የሃይማኖት አንቀጾች ትርጓሜ በአማርኛ
Открыть в Telegramበምድረበዳ ያለን የበረሀ ወይራ ሆምጣጤ ምናፈራ ነበርን መራራ ግድ የሚለውም የሌለን ወፍዘራሽ ነበርን የምንወጋ እሾህ በጨለማ ሆነን ከመንገድ ላይ አንስቶ ከልጁ ግንድ ተከለን ገበሬው አብ ይመስገን ቤተሰዎቹ አደረገን … ወገኖቹ አደረገን ታርቀናል በልጁ ታርቀናል እርቅ ከሰማይ ከላይ ሆኖልናል ሮሜና ገላትያን ጠንቅቆ የተረዳ ሰው መዝሙር 😁 በቃ አለቀ ይኅው ነውኮ! https://youtu.be/hVxVKQiOTxI?si=-OgCabfELdBuo4Aq
Открыть в TelegramHappy Reformation Day! ይህን በማሰብ ዛሬ ቅዳሜ Sola Fide ላይ ከአኖኒመስ (Ortho bro ነው 😁) Open Discussion ለማድረግ አስበን ነበር። ባጋጣሚ አልተመቸውምና ነገ አድርገነዋል። ነገ ማታ ሶስት ሰአት ላይ ቲክቶክ ላይ እንገናኝ።
Открыть в Telegramወደ ተሐድሶን መመለስ የጉባኤያዊ የእምነት መግለጫዎች ፣ የእምነት መግለጫና ክርስቲያናዊ የተዋሥኦ ትምህርት ሥልጣን በተሐድሶ እሁድ ጥቅምት 22, 2019 ዓ.ም 9:00 – 1:30 ቦታ: ቅዱስ ማቴዎስ አንግሊካን ቤተ ክርስቲያን፣ 4 ኪሎ (ከገንፊሌ ፓርክ ፊት ለፊት) 1 ቀን ቀረው @Anglicanfaith @zanchor @classical_protestant
Открыть в Telegramወደ ተሐድሶን መመለስ የጉባኤያዊ የእምነት መግለጫዎች ፣ የእምነት መግለጫና ክርስቲያናዊ የተዋሥኦ ትምህርት ሥልጣን በተሐድሶ እሁድ ጥቅምት 22, 2019 ዓ.ም 9:00 – 1:30 ቦታ: ቅዱስ ማቴዎስ አንግሊካን ቤተ ክርስቲያን፣ 4 ኪሎ (ከገንፊሌ ፓርክ ፊት ለፊት) 2 ቀን ቀረው @Anglicanfaith @zanchor @classical_protestant
Открыть в Telegramወደ ሮሜ ሰዎች 4:16 (AMH) ¹⁶ ስለዚህ ከሕግ ብቻ ሳይሆን ከአብርሃም እምነት ደግሞ ለሆነ ለዘሩ ሁሉ, የተስፋው ቃል እንዲጸና እንደ ጸጋ ይሆን ዘንድ በእምነት ነው፤ እርሱም። ለብዙ አሕዛብ አባት አደረግሁህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ ለሙታን ሕይወት በሚሰጥ የሌለውንም እንዳለ አድርጎ በሚጠራ ባመነበት በአምላክ ፊት የሁላችን አባት ነው። ¹⁶ For this reason it depends on faith, in order that the promise may rest on grace and be guaranteed to all his descendants, not only to the adherents of the law but also to those who share the faith of Abraham. ይህ ጳውሎስን ሀሳቡን ጠቅለል አድርጎ ያስቀመጠበትና የሙሉ ምዕራፍ ሙግቱን ለመረዳት በጣም ጠቃሚ የሆነ ጥቅስ ነው። I will elaborate on this further in the upcoming discussion. @zanchor
Открыть в Telegramወደ ተሐድሶን መመለስ የጉባኤያዊ የእምነት መግለጫዎች ፣ የእምነት መግለጫና ክርስቲያናዊ የተዋሥኦ ትምህርት ሥልጣን በተሐድሶ እሁድ ጥቅምት 22, 2019 ዓ.ም 9:00 – 1:30 ቦታ: ቅዱስ ማቴዎስ አንግሊካን ቤተ ክርስቲያን፣ 4 ኪሎ (ከገንፊሌ ፓርክ ፊት ለፊት) 3 ቀን ቀረው @Anglicanfaith @zanchor @classical_protestant
Открыть в Telegramወደ ተሐድሶን መመለስ የጉባኤያዊ የእምነት መግለጫዎች ፣ የእምነት መግለጫና ክርስቲያናዊ የተዋሥኦ ትምህርት ሥልጣን በተሐድሶ እሁድ ጥቅምት 22, 2019 ዓ.ም 9:00 – 1:30 ቦታ: ቅዱስ ማቴዎስ አንግሊካን ቤተ ክርስቲያን፣ 4 ኪሎ (ከገንፊሌ ፓርክ ፊት ለፊት) 4 ቀን ቀረው @Anglicanfaith @zanchor @classical_protestant
Открыть в Telegramየሆነ ጊዜ እያስቸገረ በዝማሬ ያስመለከን ትንሹ ወንድሜ ይኀው መክሬው በቁምነገር ተገልጧል! 😁💪 እየኮመኮማችሁ! https://youtu.be/O6A33OSuKTs?si=v3EcndT1lIUfSLRZ
Открыть в Telegramወደ ተሐድሶን መመለስ የጉባኤያዊ የእምነት መግለጫዎች ፣ የእምነት መግለጫና ክርስቲያናዊ የተዋሥኦ ትምህርት ሥልጣን በተሐድሶ እሁድ ጥቅምት 22, 2019 ዓ.ም 9:00 – 1:30 ቦታ: ቅዱስ ማቴዎስ አንግሊካን ቤተ ክርስቲያን፣ 4 ኪሎ (ከገንፊሌ ፓርክ ፊት ለፊት) 5 ቀን ቀረው @Anglicanfaith @zanchor @classical_protestant
Открыть в Telegramወደ ተሐድሶን መመለስ የጉባኤያዊ የእምነት መግለጫዎች ፣ የእምነት መግለጫና ክርስቲያናዊ የተዋሥኦ ትምህርት ሥልጣን በተሐድሶ እሁድ ጥቅምት 22, 2019 ዓ.ም 9:00 – 1:30 ቦታ: ቅዱስ ማቴዎስ አንግሊካን ቤተ ክርስቲያን፣ 4 ኪሎ (ከገንፊሌ ፓርክ ፊት ለፊት) 6 ቀን ቀረው @Anglicanfaith @zanchor @classical_protestant
Открыть в Telegramወደ ተሐድሶን መመለስ የጉባኤያዊ የእምነት መግለጫዎች ፣ የእምነት መግለጫና ክርስቲያናዊ የተዋሥኦ ትምህርት ሥልጣን በተሐድሶ እሁድ ጥቅምት 22, 2019 ዓ.ም 9:00 – 1:30 ቦታ: ቅዱስ ማቴዎስ አንግሊካን ቤተ ክርስቲያን፣ 4 ኪሎ (ከገንፊሌ ፓርክ ፊት ለፊት) 7 ቀን ቀረው @Anglicanfaith @zanchor @classical_protestant
Открыть в Telegram