Кабинет

Посты канала Youth focus

сначала новые

#3424Превью ссылки
Просмотры528+100%к среднему
Пересылки—
Реакции2
Комментарии—
#3423Фото

ቀስ በል ቦሌ ብራስ አካባቢ በምትገኘው በዚህች የእግረኛ መንገድ በተጓዝኩ ቁጥር እስከዛሬ በእግሮቼ እንዳልተረማመድኩ፣ ዳዴ ጨርሶ ለመራመድ ጥረት የሚያደርግን ልጅ ይመስል ስወላከፍ ራሴን አገኘዋለሁ። በውል ምክንያቱን ባላውቅም እኔ ግን የቀድሞ አረማመዴ አልተቀየረም እንደወትሮው ከሶምሶማ መለስ ባለ ፍጥነት ነው የምራመደው፤ የቀን በቀን ኑሮዬ፣ ኑሮን በእርምጃ ፍጥነት እረታ ይመስል በፍጥነት በመራመድ ቀኖቼን እገፋለሁ፣ በእርግጥ የኔ ብቻ ሳይሆን የአብዛኛው ሰው መገለጫ ከሆነ ሰነባብቷል። ይህን የእግረኛ መንገድ ባየሁ ቁጥር ግን እንዴት በስርአት የኮንክሪት መረማመጃውን መርገጥ እንደሚሳነኝ ጥያቄ ይሆንብኛል፤ ለዚህ ጥያቄዬን መልስ ያገኘሁት ተረጋግተው walk የሚያረጉ አስተውዬ የተመለከትኩ ሰሞን ነው። በከፍተኛው ሩጫ ውስጥ ላለሁት እኔ መረጋጋት እንደሚያስፈልገኝ ጠቁሞኛል፣ ለካስ ሳላውቀው ሁሌ ያለማቋረጥ ስሮጥ መዋል መደበኛ ሆኖ መረጋጋት እንግዳ ሆኖብኛል። አንዳንዴ ቀስ ማለት፣ ከተቻለም ከቀን ቀን ሩጫ ራሳችንን ገለል ማድረግ ያስፈልጋል። ሳሙኤል ከበደ

Открыть в Telegram
Просмотры646+145%к среднему
Пересылки—
Реакции6
Комментарии—