Кабинет
የተሰበሩ ልቦች...

የተሰበሩ ልቦች...

የኔ ቻናል አላማ:- ስነልቦናን የምያንጹ ምክሮች ፣ ፍልስፍናዊ ጽሁፎች ፣ ድርሰቶች ፣ +በተጨማሪ ነፍሳችንን የምያጠቁ ፍቅር ስብራት እንደነዝህ ያሉ ነገሮች ስፍር ቁጥር የላቸውም! ስለዝህ በእነዚህ ነገሮች የቆሰልናቸውን ቁስሎች ለመፈወስ ገና ወደፊት ልመጡ ያሉትንም Haram Relationship ለመከላከል በማሰብ ነው የከፈትኩት! እናም ምስክር ነኝ።

Юзернейм
@yeteseberelib
Подписчики2 936
Просмотров на пост, 7 дн.346за 7 дней
ERR11,78 %за 7 дней

Средние просмотры поста по дням

По дню публикации

Показать таблицей
ДатаПросмотров на пост
4 нояб. 2026 г.1 410
5 нояб. 2026 г.1 670
14 нояб. 2026 г.1 070
27 нояб. 2026 г.346

Самые просматриваемые за месяц

  1. Просмотры1,75 тыс.
    Пересылки—
    Реакции52
    Комментарии—
  2. አንዳንድ ታሪኮች በጆሮ ይሰማሉ አንዳንዶቹ ግን በልብ ውስጥ ይቀረጻሉ:: ከዓመታት በፊት ሹፌር ሳለሁ ተማሪ ልጆችን በማመላልስበት ግዜ ከአንዲት አስተማሪ ጋር ተዋወቅኩ ባህሪዋ ሰውን የምትቀበልበት መንገድና አጠቃላይ ስብዕናዋ ይማርከኝ ነበር አንዳንድ ሰዎች ውበታቸው በፊታቸው ላይ ብቻ አይታይም በአስተሳሰባቸውና በሌሎች ላይ በሚያሳድሩት መልካም ተጽዕኖ ውስጥ ይንጸባረቃል እሷም ከእነዚያ ልዩ ሰዎች አንዷ ነበረች a truly wonderful soul! የልጆች አስተማሪ እንደመሆኗ መጠን በየቀኑ ከቤት ወደ ስራ ስትሄድና ከስራ ወደ ቤት ስትመለስ የሚያጋጥማትን ውጣ ውረድ ለማቃለል ሁልጊዜ በመኪና አደርሳት ነበር:: በመጀመሪያ ቀላል የሰውነት እርዳታ የነበረው ነገር በጊዜ ሂደት ወደ ቅን ጓደኝነት ተቀየረ እንዲህ እያለ ጊዜያት አለፉ.. እኛም በየቀኑ ከምንገናኝባቸው ቀላል ነገሮች በላይ የህይወትን ውስጣዊ ገጽታዎች መካፈል ጀመርን:: አንድ ቀን ግን በጥልቀት እያወራን ሳለ የፊቷ ገጽታ ተለወጠ እንባዋ በአይኖቿ ጠርዝ ላይ ተሰብስቦ በጉንጮቿ ላይ መውረድ ጀመረ ያን ጊዜ የሰው ልጅ የሚደብቀው ሀዘን ከፊቱ ላይ ባይታይም በውስጡ ምን ያህል እሳት እንደሚነድ ተረዳሁ:: "ምን ሆነሽ ነው? ለምን ታለቅሻለሽ?" ብዬ ጠየቅኳት። እሷም የልቧን ሀዘን መደበቅ ሳትችል "ወንድሜ በሊቢያ በስደት ላይ ነው እዚያ እየደረሰበት ያለውን መከራ ሳስብ ልቤ ይሰበራል ከዚያ አውጥቼ ለማዳን በቂ የገንዘብ አቅም የለኝም ምን ላድርግ? በጣም ግራ ገብቶኛል" አለችኝ ለረጅም ጊዜ በውስጧ ደብቃ የቆየችውን አጋራችኝ:: አንድ አረመኔ ሰው ከእሷ ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት sex እንድትፈጽም ጠይቋት ነበር የእሱን አፀያፊ ፍላጎት ከተቀበለች ወንድሟን ከሊቢያ አስመጥቶ እንደሚያድነውም ቃል ገብቶላት ነበር:: እስቲ አስቡት! አንዲት ሴት በራሷ ክብርና በወንድሟ ህይወት መካከል እንድትመርጥ የሚያስገድድ ሁኔታ ውስጥ ስትገባ ምን ያህል የማይታገስ የውስጥ ስቃይ ይደርስባታል? አንድ ወገን በስደት ላይ የሚሰቃይ ወንድም በሌላ ወገን ደግሞ የዚያን ወንድም ህይወት ለማዳን ሁሉንም ነገር ለመስጠት የተዘጋጀች እህት በመካከላቸው ግን የሰውን ስቃይ እንደ መጠቀሚያ የሚያይ ጨካኝ ሰው! ይህንን ስሰማ ልቤ በሀዘን ተሞላ እንባዬንም መቆጣጠር አልቻልኩም የሰውን የተስፋ መቁረጥ ሁኔታ ተጠቅሞ ክብሩን ለመግፈፍ መሞከር ከሰውነት መራቅ ነው! አንድ ሰው የሌላውን ህመም ሲመለከት እርህራሄ ማሳየት እንጂ ቁስሉን ጠልቆ መውጋት የለበትም:: ከዚያ በኋላ ከራሴ ጋር እንዲህ አልኩ፦"ይህች ሴት በዚህ ሁሉ ስቃይ ውስጥ ብቻዋን መተው የለብኝም አንዳንድ ጊዜ ሰው የሚፈልገው ትልቅ ሀብት ሳይሆን በጨለማው ወቅት ከጎኑ የሚቆም ሰው ነው።".. ከዚያም ከጓደኞቼ ጋር ተሰባሰብን የእያንዳንዳችንን አቅም በማዋሃድ የምንችለውን ሁሉ አዋጣን አላማችን ገንዘብ መስጠት ብቻ አልነበረም ተስፋ የቆረጠች ልብን እንደገና ተስፋ እንድታደርግ ማገዝ ነበር:: እውነት ነው አንዳንድ ጊዜ የምንሰጠው ነገር በመጠኑ ትንሽ ሊሆን ይችላል ለተቀባዩ ግን በህይወቱ ከተስፋ መቁረጥ የሚያወጣው ትልቅ በረከት ሊሆን ይችላል:: sometimes a little kindness can make a lifetime difference. Alhamdulillah! ዛሬ ወንድሟ ከስደት ወጥቶ በሰላምና በጥሩ ሁኔታ እየኖረ ነው ያ በእንባ የተጀመረ የሀዘን ዘመን በደስታ ተተክቷል የተሰበረ ልብ ተጽናንቷል የተዘጋ የሚመስል የተስፋ በርም ተከፍቷል:: ነገር ግን ከዚህ ታሪክ የበለጠ በልቤ የተቀረጸው ከዓመታት በኋላ የተፈጠረው አንድ ድንቅ ክስተት ነው:: ያቺ ጓደኛዬ በሰርግ ቀኗ ለእኔ ልዩ የሆነ ስጦታ አዘጋጀች እኔም በጣም ተደነቅኩ በዚያ ደስታ በተሞላበት ቀን የቀድሞውን ታሪካችንን ለባሏ በሙሉ እንደነገረችው አስረዳችኝ ባሏም የሰማው ታሪክ እጅግ እንዳስደሰተው ነገረችኝ በዚያ ቅጽበት የተሰማኝ ደስታ በቀላሉ የሚገለጽ አልነበረም ምክንያቱም የሰውን ችግር ተጋርተህ ስትረዳው አንድ ቀን እሱ ያንን ደግነት በልቡ አስቀምጦ እንደሚያስታውስህ መረዳት እጅግ የሚያስደስት ነው:: የቀድሞውን የችግር ዘመን ሳይረሳ በልቡ ሲያከብርህ ያን ጊዜ የሰው ልጅ ደግነት ምን ያህል ውድ እንደሆነ ትረዳለህ:: ይህ ነው እውነተኛ ጓደኝነት:: ይህ ነው የማይጠፋ የመልካምነት አሻራ:: እናም ይህ ነው የሰው ልጅ ከገንዘብ በላይ ሊያከማች የሚችለው ትልቁ ሀብት:: በህይወት ውስጥ ሰው ብዙ ነገሮችን ይረሳል:: የሰጠኸውን ገንዘብ ያደረግከውን እርዳታ ወይም በአንድ ወቅት ያደረግከውን ትንሽ ውለታ እንኳን ሊረሳ ይችላል ነገር ግን በተሰበረበት ወቅት ከጎኑ የቆመውን ሰው በቀላሉ አይረሳም:: አንዳንድ ጊዜ የሰው ልጅ በህይወቱ የሚያስታውሰው ትልቁ ስጦታ የተቀበለው ገንዘብ ሳይሆን በተስፋ በተቆረጠበት ወቅት የተዘረጋለት እጅ ነው:: ደግነት ኪሳራ አይደለም! ርኅራኄ ድክመት አይደለም ሌላውን ሰው ከችግሩ ጋር ብቻውን እንዳይቀር ማገዝ ደግሞ ከሁሉም በላይ የሰውነት መገለጫ ነው ሰው ሲወድህ ብቻ ሳይሆን በህይወትህ ውስጥ ተስፋ ሲሆንህ ነው እውነተኛ ዋጋው የሚታወቀው:: መልካምነትን አትስስት! ዛሬ ለሌላው የምትዘራው ደግነት ነገ በlifeህ ውስጥ የማትጠብቀው ውብ ትዝታ ሆኖ ሊመለስ ይችላል::.

    Текст
    Просмотры1,73 тыс.
    Пересылки—
    Реакции24
    Комментарии—
  3. Просмотры1,72 тыс.
    Пересылки—
    Реакции21
    Комментарии—
  4. Просмотры1,63 тыс.
    Пересылки—
    Реакции19
    Комментарии—

Новые посты

#4843Текст

አንዳንድ ታሪኮች በጆሮ ይሰማሉ አንዳንዶቹ ግን በልብ ውስጥ ይቀረጻሉ:: ከዓመታት በፊት ሹፌር ሳለሁ ተማሪ ልጆችን በማመላልስበት ግዜ ከአንዲት አስተማሪ ጋር ተዋወቅኩ ባህሪዋ ሰውን የምትቀበልበት መንገድና አጠቃላይ ስብዕናዋ ይማርከኝ ነበር አንዳንድ ሰዎች ውበታቸው በፊታቸው ላይ ብቻ አይታይም በአስተሳሰባቸውና በሌሎች ላይ በሚያሳድሩት መልካም ተጽዕኖ ውስጥ ይንጸባረቃል እሷም ከእነዚያ ልዩ ሰዎች አንዷ ነበረች a truly wonderful soul! የልጆች አስተማሪ እንደመሆኗ መጠን በየቀኑ ከቤት ወደ ስራ ስትሄድና ከስራ ወደ ቤት ስትመለስ የሚያጋጥማትን ውጣ ውረድ ለማቃለል ሁልጊዜ በመኪና አደርሳት ነበር:: በመጀመሪያ ቀላል የሰውነት እርዳታ የነበረው ነገር በጊዜ ሂደት ወደ ቅን ጓደኝነት ተቀየረ እንዲህ እያለ ጊዜያት አለፉ.. እኛም በየቀኑ ከምንገናኝባቸው ቀላል ነገሮች በላይ የህይወትን ውስጣዊ ገጽታዎች መካፈል ጀመርን:: አንድ ቀን ግን በጥልቀት እያወራን ሳለ የፊቷ ገጽታ ተለወጠ እንባዋ በአይኖቿ ጠርዝ ላይ ተሰብስቦ በጉንጮቿ ላይ መውረድ ጀመረ ያን ጊዜ የሰው ልጅ የሚደብቀው ሀዘን ከፊቱ ላይ ባይታይም በውስጡ ምን ያህል እሳት እንደሚነድ ተረዳሁ:: "ምን ሆነሽ ነው? ለምን ታለቅሻለሽ?" ብዬ ጠየቅኳት። እሷም የልቧን ሀዘን መደበቅ ሳትችል "ወንድሜ በሊቢያ በስደት ላይ ነው እዚያ እየደረሰበት ያለውን መከራ ሳስብ ልቤ ይሰበራል ከዚያ አውጥቼ ለማዳን በቂ የገንዘብ አቅም የለኝም ምን ላድርግ? በጣም ግራ ገብቶኛል" አለችኝ ለረጅም ጊዜ በውስጧ ደብቃ የቆየችውን አጋራችኝ:: አንድ አረመኔ ሰው ከእሷ ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት sex እንድትፈጽም ጠይቋት ነበር የእሱን አፀያፊ ፍላጎት ከተቀበለች ወንድሟን ከሊቢያ አስመጥቶ እንደሚያድነውም ቃል ገብቶላት ነበር:: እስቲ አስቡት! አንዲት ሴት በራሷ ክብርና በወንድሟ ህይወት መካከል እንድትመርጥ የሚያስገድድ ሁኔታ ውስጥ ስትገባ ምን ያህል የማይታገስ የውስጥ ስቃይ ይደርስባታል? አንድ ወገን በስደት ላይ የሚሰቃይ ወንድም በሌላ ወገን ደግሞ የዚያን ወንድም ህይወት ለማዳን ሁሉንም ነገር ለመስጠት የተዘጋጀች እህት በመካከላቸው ግን የሰውን ስቃይ እንደ መጠቀሚያ የሚያይ ጨካኝ ሰው! ይህንን ስሰማ ልቤ በሀዘን ተሞላ እንባዬንም መቆጣጠር አልቻልኩም የሰውን የተስፋ መቁረጥ ሁኔታ ተጠቅሞ ክብሩን ለመግፈፍ መሞከር ከሰውነት መራቅ ነው! አንድ ሰው የሌላውን ህመም ሲመለከት እርህራሄ ማሳየት እንጂ ቁስሉን ጠልቆ መውጋት የለበትም:: ከዚያ በኋላ ከራሴ ጋር እንዲህ አልኩ፦"ይህች ሴት በዚህ ሁሉ ስቃይ ውስጥ ብቻዋን መተው የለብኝም አንዳንድ ጊዜ ሰው የሚፈልገው ትልቅ ሀብት ሳይሆን በጨለማው ወቅት ከጎኑ የሚቆም ሰው ነው።".. ከዚያም ከጓደኞቼ ጋር ተሰባሰብን የእያንዳንዳችንን አቅም በማዋሃድ የምንችለውን ሁሉ አዋጣን አላማችን ገንዘብ መስጠት ብቻ አልነበረም ተስፋ የቆረጠች ልብን እንደገና ተስፋ እንድታደርግ ማገዝ ነበር:: እውነት ነው አንዳንድ ጊዜ የምንሰጠው ነገር በመጠኑ ትንሽ ሊሆን ይችላል ለተቀባዩ ግን በህይወቱ ከተስፋ መቁረጥ የሚያወጣው ትልቅ በረከት ሊሆን ይችላል:: sometimes a little kindness can make a lifetime difference. Alhamdulillah! ዛሬ ወንድሟ ከስደት ወጥቶ በሰላምና በጥሩ ሁኔታ እየኖረ ነው ያ በእንባ የተጀመረ የሀዘን ዘመን በደስታ ተተክቷል የተሰበረ ልብ ተጽናንቷል የተዘጋ የሚመስል የተስፋ በርም ተከፍቷል:: ነገር ግን ከዚህ ታሪክ የበለጠ በልቤ የተቀረጸው ከዓመታት በኋላ የተፈጠረው አንድ ድንቅ ክስተት ነው:: ያቺ ጓደኛዬ በሰርግ ቀኗ ለእኔ ልዩ የሆነ ስጦታ አዘጋጀች እኔም በጣም ተደነቅኩ በዚያ ደስታ በተሞላበት ቀን የቀድሞውን ታሪካችንን ለባሏ በሙሉ እንደነገረችው አስረዳችኝ ባሏም የሰማው ታሪክ እጅግ እንዳስደሰተው ነገረችኝ በዚያ ቅጽበት የተሰማኝ ደስታ በቀላሉ የሚገለጽ አልነበረም ምክንያቱም የሰውን ችግር ተጋርተህ ስትረዳው አንድ ቀን እሱ ያንን ደግነት በልቡ አስቀምጦ እንደሚያስታውስህ መረዳት እጅግ የሚያስደስት ነው:: የቀድሞውን የችግር ዘመን ሳይረሳ በልቡ ሲያከብርህ ያን ጊዜ የሰው ልጅ ደግነት ምን ያህል ውድ እንደሆነ ትረዳለህ:: ይህ ነው እውነተኛ ጓደኝነት:: ይህ ነው የማይጠፋ የመልካምነት አሻራ:: እናም ይህ ነው የሰው ልጅ ከገንዘብ በላይ ሊያከማች የሚችለው ትልቁ ሀብት:: በህይወት ውስጥ ሰው ብዙ ነገሮችን ይረሳል:: የሰጠኸውን ገንዘብ ያደረግከውን እርዳታ ወይም በአንድ ወቅት ያደረግከውን ትንሽ ውለታ እንኳን ሊረሳ ይችላል ነገር ግን በተሰበረበት ወቅት ከጎኑ የቆመውን ሰው በቀላሉ አይረሳም:: አንዳንድ ጊዜ የሰው ልጅ በህይወቱ የሚያስታውሰው ትልቁ ስጦታ የተቀበለው ገንዘብ ሳይሆን በተስፋ በተቆረጠበት ወቅት የተዘረጋለት እጅ ነው:: ደግነት ኪሳራ አይደለም! ርኅራኄ ድክመት አይደለም ሌላውን ሰው ከችግሩ ጋር ብቻውን እንዳይቀር ማገዝ ደግሞ ከሁሉም በላይ የሰውነት መገለጫ ነው ሰው ሲወድህ ብቻ ሳይሆን በህይወትህ ውስጥ ተስፋ ሲሆንህ ነው እውነተኛ ዋጋው የሚታወቀው:: መልካምነትን አትስስት! ዛሬ ለሌላው የምትዘራው ደግነት ነገ በlifeህ ውስጥ የማትጠብቀው ውብ ትዝታ ሆኖ ሊመለስ ይችላል::.

Открыть в Telegram
Просмотры1 730+30%к среднему
Пересылки—
Реакции24
Комментарии—
#4841Текст

በአንድ ወቅት በጣም የተጎዳች አንዲት ሴት ከሽማግሌ ጋር ታክሲ ውስጥ ተገናኙ:: በሀዘን የተሞላችው ለምን እንደሆነ ጠየቃት እሷም ከ8 አመት በፊት መደፈሯንና ከዛን ቀን ጀምሮም ራሷን እንደሰው መቁጠር እንዳቆመች ደስታ ሚባል እንደራቃትና በተስፋ መቁረጥ ውስጥ እንደምትኖር ነገረቻቸው፡፡ እሳቸውም :-"ልጄ ከ8 አመት በፊት ነው አደል የተደፈርሽው" በማለት ጠየቋት! እሷም አዎ በማለት መለሰች እሳቸውም መልሰው ታዲያ "ለምን 8አመት ሙሉ ደጋግሞ እንዲደፍርሽ ፈቀድሽለት" በማለት መለሱላት ይባላል፡:: fam look in this game of life we deal with mad obstacles heavy L's stress pure agony & heavy burdens. በህይወታችን ውስጥ ማየት የማንፈልጋቸው ከትዝታችን ሰርዘናቸው ማለፍ የምንመኘቸው በየቀኑ የምንዋጋቸው ሰዎች ሳያውቁን ውስጣችን የሚሰባበርባቸው ከባድ ቀኖች ማየት የማንፈልጋቸው ከትዝታችን ሰርዘናቸው ማለፍ የምንመኘቸው ብዙ ከባድ ነገሮች አሉ ነገር ግን ልክ እንደዚሁ ታሪክ ያለፈውን ስቃይ ራሳችን ቋጥተን ይዘን መኖር የለብንም ቆም ብለን ማለፍ አለብን:: it’s super fu*kin hard አዎ መረሳትም ሆነ መቀበል ከባድ መሆኑን አውቃለሁ but U gotta push through and grind it out! we always say "የተሻለ ስሜት እንዲሰማኝ እፈልጋለሁ" እያልን የተሻለውን ጊዜ እንጠብቃለን። Nah nahh screw that! u gotta own ur horror life embrace the chaos that’s the only way u pull the trigger and defeat it! ያገጠመን አስፈሪ ህይወትና ፈተና ተቀብለን መታገል እንጂ ዝም ብለን መጠበቅ አያዋጣም ያገጠመን አስፈሪ ፈተና ተቀብሎ መታገል እንጂ የተሻለ ቀን ይመጣል ብሎ እጅ ሰጥቶ መቀመጥ አያዋጣም ድል መንሻውም በዚህ መንገድ ብቻ ነው:: ራሳችንን የተለያዩ ሱስ ውስጥ መጥለቅ መፍትሄ አይደለም:: It's just a cheap high, just like using drugs ህመሙን የሚያስወግደው ለአፍታ ብቻ ነው። ከእሱ ውጪ ግን በህይወታችን ላይ ዘላቂ እና ትክክለኛ ለውጥ አያመጣም ታዲያ ለምን ያንን ውብ ሰውነታችንን እንጎዳለን? Why fam why ruin yourself? U might say "ስለ ህመሜ እና ስለ ህይወቴ ምን ታውቃለህ?" and get tight at me ታኮርፉ ይሆናል። Well YES! እኔ የlife ትክክለኛ ሁኔታ ላላውቅ አችላለሁ BUT I know pain ህመም ምን እንደሆነ አውቃለሁ:: የሰው ልብ በቀላሉ እንዴት እንደሚሰበር አውቃለሁ eveybody got scars ምንም እንኳን ሁኔታዎች ቢለያዩም እያንዳንዱ ሰው የየራሱ የከበደ መከራ እና ስብራት አለው:: Don't be ashamed to speak ur mind ሰዎች ጋር ተነጋገሩ አልቅሱ ጮኹ ያላችሁን ውስጣዊ ስሜት ሙሉ በሙሉ አውጡት! But plss stay solid don't lose yourself እናንተ ለዚህ ህይወት በጣም ውድ ናችሁ:: Quick to start. Quick to stop. Quick to hate. Quick to love. Quick to be happy. Quick to be sad. Cuz at the end of the day how far u r grindin' and where you're headin' is way more important than how fast u move. ከየት እንደጀመርክ ወይም ምን ያህል በፍጥነት እንደሄድክ ሳይሆን ጉዞህ ወዴት እንደሆነ ማወቁ ከፍጥነቱ ይበልጣል:: Luv ya'll!

Открыть в Telegram
Просмотры1 840+38%к среднему
Пересылки—
Реакции19
Комментарии—

Все посты