Кабинет

Посты канала የፍቅር ታሪክ 🇪🇹

сначала новые

#9898Фото
Просмотры8 370+355%к среднему
Пересылки—
Реакции16
Комментарии—
#9844Фото
Просмотры7 300+297%к среднему
Пересылки—
Реакции11
Комментарии—
#9281Превью ссылки

‍ .              ♥️●●●ነጠብጣብ●●●♥️             💞እውነተኛ እና አስተማሪ ታሪክ💞                              #ክፍል_5 ...🖊ለመጀመሪያ ጊዜ ዎክ ካደረግን በኋላ ማክሰኞ የኔ እና የኢክራም ዉድ ቀን ሆነች። ማክሰኞ ኢክራም ከሀይማኖታዊ ትምህርት ነፃ የምትሆንበት ቀን ነዉ። ሌሎቹን ቀናት ጁምዓን ሳይጨምር መስጂድ ሀይማኖታዊ ትምህርቶችን ትማራለች። ሁሌም ማክሰኞ አስር ሰዓት ላይ ተገናኝተን እስከ አስራሁለት ሰአት ድረስ አብረን እናሳልፋለን። አስራሁለት ሰዓት ሲሞላ እናቷ ከስራ ስለምትመጣ ወደ ቤቷ እሸኛታለሁ። እናቷ ከስራ አርፍዳ የምትመጣ ቀን ኢክሩ እስከ አንድ ሰአት ድረስ ከኔ ጋር አርፍዳ ወደ ቤቷ ትገባለች። ከኔ ከተለየች በኋላ ወደ ቤቷ ስትገባ እናቷ እስከምትመጣ ድረስ ብቻዋን ቤት ዉስጥ እንደምትቀመጥ ሳስበዉ ለሷ እኔ እታመማለሁ። ከብቸኝነት በላይ ህመም የለም። የሚያዳምጠን ሰዉ ከማጣት በላይ ስቃይ አይኖርም። . አንድ ቀን ከኢክሩ ጋር ሁሌም ወደምንቀመጥበት ከሰፈራችን ትንሽ ዝቅ ብሎ ወዳለዉ ሰፊ የሳር ሜዳ ሄድን። ሜዳዉ ላይ ኳስ የሚጫወቱ ልጆች አሉ። ከሜዳዉ ራቅ ብሎ ደግሞ ልክ እንደኛ የአካባቢዉን ከሰዉ አይን የራቀ መሆን ፈልገዉ የመጡ ጥንዶች ተቀምጠዋል። ሁሌም እንደምናደርገዉ ከክቡ የድንጋይ ቋጥኝ አጠገብ ያሉ መቀመጫዎች ላይ ተቀመጥን። ኢክሩ ድብር ብሏታል። ቀስ ብዬ "ኢክሩዬ ስለምን እያሰብሽ ነዉ?" አልኳት። እንባ እየተናነቃት "ፈዊ እናቴ ላይ ሸክም እንደሆንኩባት እየተሰማኝ ነዉ።" አለችኝ። እየሳቅኩ "ኢክሩዬ እናት ላይ እንዴት ሸክም ይኮናል? እናቶቻችን እኮ ሁሌም እኛን ለመንከባከብ አይታክቱም።" አልኳት። አንገቷን በአሉታ እየነቀነቀች እንዳልተረዳኋት ገልፃልኝ ማብራራቷን ቀጠለች። "ፈዊ እናቴ በጣም ወጣት ናት። አንድ ላይ ብታየን እህትማማቾች እንጂ እናት እና ልጅ አንመስልህም። እሷ የማታገባዉ ባል ጠፍቶ አይደለም ግን እኔን ከእንጀራ አባት ጋር ማኖር ከብዷት ነዉ። እራስ ወዳድ እንደሆንኩ ይሰማኛል ፣ በእናቴ መቅለጥ ነዉ እየፈካሁ ያለሁት።" ንግግሯ በእንባ መታጀብ ጀምሯል። ወይኔ ሰዉ ሲያለቅስም እንዲህ ያምራል? ወንድነቴን አደብ አስገዝቼ በለቅሶ የታጀበ ንግግሯን ማዳመጤን ቀጠልኩ። "ፈዊ እኔ ባገባ እኮ ማማ ያለስጋት አግብታ መኖር ትችል ነበር። ግን እኔ አሁንም እንደ ልጅ እየተጨማለቅኩ የሷን ህይወት እየቀማኋት ነዉ።" ብላ እንባዋን መጥረግ ጀመረች። አሁን የኢክራምን ዉበት ያየ በዚህ ሁሉ ችግር ዉስጥ እየተፈተነች ያለች ይመስለዋል? በፍፁም አይመስለዉም። ኢክሩ ከተረጋጋች በኋላ ጭንቀቷን እንድትረሳዉ ብዬ ስላሳለፍነዉ የፍቅር ታሪክ እንድንጨዋወት ጠየቅኳት። እሷ ከዚህ በፊት ብዙ ያፈቅሯት የነበሩ ልጆች የነበሩ ቢሆንም የሚነገር የፍቅር ታሪክ እንደሌላት ነገረችኝ። እኔ በልጅነቴ ስላፈቀርኳት መርየም ስለምትባል ልጅ አጫወትኳት። ታሪኩን ከነገርኳት በኋላ "ኢክሩዬ ለመርየም ካደረግኳቸዉ ነገሮች ዉስጥ የቱ እንደሚገርመኝ ታዉቂያለሽ?" አልኳት። እንድቀጥልላት ምልክት ሰጠችኝ "ሰባተኛ ክፍል እያለሁ ነዉ። አንድ ቀን ናቲ የሚባል ጓደኛችን አስተማሪ ገርፎት ክፍል ዉስጥ እየተንሰቀሰቀ ያለቅሳል። መርየም እና ጓደኛዋ ናቲን ሲያባብሉት አየሁ። መርየም አይዞህ እያለች ስትንከባከበዉ ሳይ ናቲን መሆን ተመኘሁ። በቀጣዩ ክፍለጊዜ ሰበብ ፈልጌ ከአስተማሪ ጋር ተጣላሁ። ግን አስተማሪዋ አልገረፈችኝም። ተቆጥታኝ አለፈችኝ። እኔ ግን አላማዬ የመርየምን ማፅናኛ ማግኘት ስለነበር ተንሰቅስቄ አለቀስኩ።" ኢክራም ሳቅ እያፈናት "እና መርየም አባበለችህ?" አለችኝ። "ባክህ ዝም በል" አለችኝ ስላት ኢክሩ እንባዋ ከአይኗ እስኪፈስ ድረስ እየተንከተከተች ሳቀች። ኢክሩ ስትስቅ በጣም ታምራለች። በዛ ላይ ደግሞ ሳቋን ሊያጅቡ እንባዎቿ ከዉብ አይኖቿ ሲፈሱ በጣም ለየት ያለ ዉበት አላት። ኢክሩን እንደዛ ቀን ስትስቅ አይቻት አላዉቅም። ሌላም እንደዚህ የሚያስቅ ታሪክ በኖረኝ እና ነግሬያት እንዲህ ስትፍለቀለቅ ባየኋት ብዬ ተመኘሁ። . ከኢክራም ጋር ወንድሟ ሆኜ ሀዘኗን እየተካፈልኳት እና ጭንቀቴን እያማከርኳት ለሁለት ወር ቆየን። አንድ ቀን እንደለመድነዉ ተገናኝተን ተጨዋዉተን ከተለያየን በኋላ ኢክሩ ፌስቡክ ላይ የሚያስደነግጥ መልዕክት ላከችልኝ። "ፈዊ የእኔ እና አንተ ሁሌ መገናኘት ጥቅሙ አልታይሽ ብሎኛል። ቢቀርብን የሚሻል ይመስለኛል።" ይላል መልዕክቷ!! ግራ ገባኝ ኢክሩ ከኔ ጋር ስትሆን ሁሌም ደስተኛ ነበረች። ዛሬ ምን ተገኘና በቃኸኝ አለችኝ? ዉስጤ ተረበሸ። እኔ ሳዉቅ ለሷ ጥሩ ወንድም ነበርኩ። ቢሆንም አልተበሳጨሁባትም በአካል አግኝቼ ላዋራት ወሰንኩ። ደወልኩላት እንደተለመደዉ እየተፍለቀለቀች አናገረችኝ። ላናግራት እንደምፈልግ ነግሬያት በነጋታዉ ሰፈራችን ዉስጥ ያለዉ ቤተ መፅሀፍ ለመገናኘት ተቀጣጠርን። . በነገራችን ላይ የኛ ሰፈሩ ቤተ መፅሀፍ ማንበቢያ ከሚባል ይልቅ የወንድና ሴቶች መቀጣጠሪያ ቢባል የሚገልፀዉ ይመስለኛል። ለማንበብ ከሚመጣዉ ሰዉ በቁጥር የማያንሱ ቤተ መፅሀፍ ተቀጣጥረዉ የሚገናኙ ጥንዶች አሉ። የሰዉ ልጅ ለአንድ አላማ የተለያዩ ቦታዎች ይሄዳል አላልኳችሁም ነበር? ይኸዉ ቤተ መፅሀፍ እንኳ አልተረፈም። መጣበሻ ሆኗል። እኔና ኢክሩ ቤተ መፅሀፍ የተቀጣጠርነዉ እኔ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናዬን የምወስድበት ጊዜ ስለተቃረበ እና በንባብ ተጠምጄ ስለነበር ነዉ። በነጋታዉ ኢክሩ ደዉላ ከቤተ መፅሀፉ እንድወጣ ነገረችኝ። ስወጣ በር ላይ ቆማለች። የቤተ መፅሀፉ አጥር ላይ ወዳለዉ መቀመጫ ሄደን ስለላከችልኝ መልዕክት ማብራሪያ እንድትሰጠኝ ጠየቅኳት። "ፈዊ መገናኘታችን ትርጉሙ አልገባኝም። በስልክ ከተደዋወልን የሚበቃ ይመስለኛል።" አለችኝ። ስታወራ ይብቃን ሳይሆን እንቀጥል የምትል ነዉ የምትመስለዉ። ትኩር ብዬ ተመለከትኳት ፣ በረዥሙ ተነፈስኩና "ኢክሩዬ አብሬሽ በወንድምነት ያሳለፍኩት ጊዜ በጣም ደስ ይል ነበር። አንቺ በቃኝ ካልሽ ግን ዉሳኔሽን አከብራለሁ።" ብዬ እስከ ቤቷ ድረስ እንደተለመደዉ ሸኝቼ ተሰናበትኳት። ከዚህ ቀን ጀምሬ ኢክራም ጋር መደወል አቆምኩ። በሰዓቱ ለፈተና እየተዘገጃጀሁ የነበረ መሆኑ ብዙም ስለ ኢክራም እንዳላስብ ረዳኝ። ሰዉ መለማመጥ አልወድም። ኢክራም ከበቃት በቅቷታል አለቀ። ደግሞ ምንም የተለየ ነገር አልነበረንም። ግን የእኔ እና እሷ የመገናኛ ዉድ ቀን ማክሰኞን በጉጉት ትናፍቅ የነበረችዉ ኢክራም ይብቃን ያለችበት ምክንያት ምንድነዉ? ኢክሩ ልታገባ ነዉ? ፍቅረኛ ልትይዝ ነዉ? ለምን? ምክንያት እንዳለዉ ገብቶኛል። ግን ምን እንደሆነ አላዉቅም።                 #ይቀጥላል... https://t.me/+kahGvq58K6k5ZTU0 ✎ ክፍል ስድስት (6) ይቀጥላል❤️‍🩹 ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ #ሼር♥️ ማድረግ አይርሱ።         ┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿🌺»‌✽‌┉┉┄     

Открыть в Telegram
Просмотры24 500×13к среднему
Пересылки—
Реакции268
Комментарии—
#9252Текст

.              ♥️●●●ነጠብጣብ●●●♥️             💞እውነተኛ እና አስተማሪ ታሪክ💞                              #ክፍል_4 ...🖊የኢክራምን ስልክ የሪም እድሜ ይርዘምና ምንም ሳልለፋ አገኘሁት። በነጋታዉ ኢክራምን ለመጀመሪያ ጊዜ በስልክ ላወራት ደወልኩ። ስታወራ ደስ ትላለች። አዳማጭ ብቻ ሆና አታስጨንቅም። አስራስድስት ደቂቃ አወራን ፣ ከማላዉቃት ሴት ጋር ያዉም ለመጀመሪያ ጊዜ እያወራን ይህን ሁላ ደቂቃ ማናገሬ ገርሞኛል። በሁለተኛዉ ቀን ደዉዬ ስናወራ "ኢክሩ ግን ትኮሪያለሽ አይደል?" አልኳት። "ምነዉ? ምናጠፋሁ?" አለችኝ ግራ እየተጋባች። "አንቺ መች ታስታዉሺኛለሽ፣ ኧረ አንቺም ፈልጊኝ!!" አልኳት። ሁሉም ነገር እኮ በአንድ ወገን በኩል ብቻ ሲሆን ያስጠላል። ሰጥቶ እንደመቀበል የሚያስደስት ነገር የለም። አንዳንዶች ሁሌ እንድትሰጧቸዉ ብቻ ይፈልጋሉ። እነሱ ግን በምላሹ ምንም አይሰጧችሁም። ይሄ የወዳጅነት ትስስርን ይነቀንቃል። እኔም እኔ ብቻ ስደዉል እኔ ብቻ ፈላጊ እንደሆንኩ ስለተሰማኝ ነዉ እንዲህ ያልኳት። ኢክሩ እየተቅለሰለሰች "ኧረ አልኮራም፣ እደዉላለሁ ችግር የለዉም ፈዉዛኔ!!" አለችኝ። ከዚህ ቀን ጀምሮ በተራ መደዋወል ጀመርን። እኔ ዛሬ ከደወልኩ እሷ ነገ ትደዉላለች። በስልክ በምናወራበት ሰአት ስለሷ አንዳንድ ነገሮችን አወቅኩ። አባቷ በህይወት የለም። ወንድምም ሆነ እህት የላትም። ከእናቷ ጋር ብቻቸዉን ነዉ የሚኖሩት። ብቸኛ ወዳጇ ፊልም ነዉ። ሲደብራት ተከታታይ ፊልሞችን ዲሽ ላይ ትከታተላለች። ፊልም ነዉ ያሳደጋት። ፊልም እያየች አድጋ ነዉ እኔም ላይ ቆንጆ ፊልም የሰራችብኝ!! ያየችዉን ነዉ የተገበረችብኝ!! . ኢክራም ታሪኳን ስትነግረኝ ምናልባት በህይወቷ ዉስጥ ያጣችዉን ወንድሟን ሆኜ ብቸኝነቷን ላስረሳት አሰብኩ። የጅንጀና ሙዴ ሁሉ ተጦለበ። በቃ ንፁህ ወንድሟ ለመሆን አለምኩ። አንድ ቀን ማታ ላይ ኡስማን ከሚባል ጓደኛዬ ጋር ወደ ሰፈር እየገባን ስሟን ሳልነግረዉ ታሪኳን አጫወትኩትና ከኔ ይልቅ እሱ ሴት መንከባከብ ስለሚችል እንደዉም ባስተዋዉቃቸዉና እሱ ቢንከባከባት ደስ እንደሚለኝ ነገርኩት። ኡስማን ደግሞ በጣም የምወደዉ መስጂድ የተዋወቅኩት ጓደኛዬ ነዉ። ታሪኳን ከነገርኩት በኋላ እሱም ልቡ ተነክቶ "ፈዉዛኔ እቺን ምርጥ ሀብታም ፈልጎ አሁኑኑ መዳር ነዉ!!" አለኝ። በሰፊዉ እንደምናወራበት ተነጋግረን ከኡስማን ጋር ተለያየን። ከዛ በኋላ ግን ከኡስማን ጋር ስለሷ አዉርቼ አላዉቅም። ኡስማን ወንድ ነዉ ግን እዉነት ለመናገር ለሴት ከንፈሯ ሲያምር ምናምን እንደምንለዉ ፀጉሩ፣ መልኩ በአጠቃላይ የሚያምር ልጅ ነዉ። በጣም ደግሞ ተግባቢ ነዉ። በጣም ብዙ ሴቶች የሚመኙት ወንድ ነዉ። ኢክሩን እንዲንከባከባት ያሰብኩት ከዚህ በፊት ካለዉ ልምድ ተነስቼ ነበር። ዉስጤ ላይ ያደረዉ የወንድምነት መንፈስ ከኔ ሴት በመንከባከብ ለተሻለ ወንድ አሳልፎ እስከመስጠት ወስዶኝ ነበር። የፈጣሪ ጥበብ ግን ይገርማል ትናንተ ስለማላዉቃት አንድ ሴት ዛሬ ከማንም በላይ የምጨነቅ ፍጡር እንድሆን አደረገኝ። . ከኢክራም ጋር ግንኙነታችን ከስልክ በአካል ወደመገናኘት ሊያድግ ቀን ቆረጥን። አርብ ዕለት ማታ አንድ ሰአት ላይ ሰፈራችን በሚገኘዉ አስፓልት ላይ ዎክ ለማድረግ ተቀጣጠርን። ከሴት ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ለመገናኘት ስትቀጣጠሩ የሆነ የሚጨንቅ ነገር አለዉ። ልጅቷ ተጫዋች ናት ወይስ አንገቷን ከማነቃነቅ ዉጪ ምንም የማታወራ ልጉም የሚለዉ ያስጨንቃል። እኔ ግን አንድ ቀን ታክሲ ዉስጥ ስላገኘኋት ነዉ መሰለኝ ብዙም አልተጨነቅኩም። ይልቁንስ ስለዉበቷ ነዉ የማስበዉ ፣ ስትሽኮረመም በአይነህሊናዬ ይታየኛል። ከዛም በስልክ ያወራነዉ ታሪኳ ትዝ ይለኝና ስሜቴን አፍነዋለሁ። ከሴት ጋር ተቀጣጥሮ የመንዘላዘል ልምድ የለኝም። አሁን ግን መንዘላዘልም በሉት ምን ከኢክራም ጋር ለመገናኘት ተቀጣጥሬያለሁ። . ጁምዓ ደረሰ!! ማታ ላይ ኢክራም ከሪም ጋር ሆና የተቀጣጠርንበት ቦታ ላይ ተገናኘን። እኔ ግን ግራ የሚገባኝ ሴቶች ለምንድነዉ የመጀመሪያ ቀን ስትቀጥሯቸዉ ከጓደኛቸዉ ጋር የሚመጡት? እኔ ግን ስገምት ደህንነት የሚሰማቸዉ አይመስለኝም። ምናልባት ወንዱ አደብ ከሌለዉ ስርዓት ለማስያዝ አሊያም አብሮ ለመጮህም ሊሆን ይችላል ሁለት ሆነዉ የሚመጡት። ኢክራም ቤት ስትመለስ ሪም ጋር ነበርኩ ለማለት አቅዳ ነዉ በድፍረት በማታ ያገኘችኝ። ከዛ ቀን በኋላ እስክንለያይ ድረስ በዛ ሰዓት አግኝቼያት አላዉቅም። እስከምሽቱ ሁለት ሰዓት ያመሸነዉ የዛኔ ብቻ ነዉ። ኢክራምን ገና ከሩቅ ሳያት ልቤ "የምን ወንድምነት ነዉ? እያት እስኪ ያስችልሀል?" እያለ ሞገተኝ። ልቤን አደብ አስገዝቼ እነ ኢክራምን ተቀላቀልኳቸዉ። ሁለቱም የለበሱት ሺቲ ነዉ። ኢክራም ከላይ ጃኬት ደርባለች። በጅልባብ ስላልመጣች ጌታዬን አመሰገንኩ። ሺቲ እና ድሪያ ልዩነቱ ምን እንደሆነ አላዉቅም። የልብሱ ስም ሺቲ እንደሚባል ኋላ ላይ ነዉ ኢክሩ ራሷ የነገረችኝ። ንፋሱ የለበሰችዉን ሺቲ ገላዋ ላይ ሲለጥፈዉ የሰዉነቷ ቅርፅ ወለል ብሎ ታየኝ። መጠነኛ መቀመጫ አላት ፣ ወገቧ ከመቀመጫዋ እጅጉን ቀጥኖ ስምንት ቁጥር ሰርቷል። ንፋስን ቅርጿን እንዳይ ስፖንሰር ስላደረገኝ ከልብ አመሰገንኩ። ወዲያዉ ሪም ተሰናብታን ሄደች። እኔና ኢክሩ ብቻ ፣ ማታ ላይ ፣የመንገድ መብራት ባስጌጠዉ ዉብ ጎዳና ላይ አብረን ቀረን። ግን አልተፈራራንም አንዳንችን በአንዳችን መኖር ምቾት ተሰምቶናል። ምናልባት በህይወቴ እስከዛሬ ካደረግኳቸዉ ዎኮች ዉስጥ የህይወቴን ልዩ ታሪክ የመሰረተዉ ዎክ ይሄ ይመስለኛል። "ኢክራም" አልኳት መንገድ መንገዱን እያየሁ። "አቤት ፈዉዛን" አለችኝ አንገቷን ወደኔ አዙራ። "ባለፈዉ ታክሲ ዉስጥ ስንገናኝ ጅልባብ ነበር የለበስሽዉ ዛሬ እንዴት አወለቅሽዉ?" አልኳት። ፈገግ አለች እና እጆቿን እያፋጨች "ጅልባብ ሀይማኖታዊ ልብስ ነዉ!! እስልምና ደግሞ በጋብቻ ካልተሳሰርኩት ወንድ አሊያም ዘመዴ ካልሆነ ሰዉ ጋር እንዲህ እንድሆን አይፈቅድም። በአጭሩ የሀይማኖት ልብስ ለብሼ እምነቴ የከለከለኝን ነገር ላለማድረግ ብዬ ነዉ!! ሀይማኖታችንን ላለማሰደብ!!" አለችኝ። በመልሷ በጣም ደስ ተሰኘሁኝ። እኔም ለጅልባቧ እና ለሀይማኖቷ ባላት ክብር አደነቅኳት። ፈገግ ብዬ "ሁሌም እኔን ስታገኚኝ ጅልባብ ባትለብሺ ደስ ይለኛል።" አልኳት። "ይኸዉ ልክ እንደዚህ በሺቲ እመጣለሁ።" አለችኝ አንገቷን በሀፍረት እየሰበረች በልቤ በጣም ሳቅኩ ፣ ደስ አለኝ!! በሺቲ እመጣለሁ ስላለችኝ አይደለም። ግን በንግግሯ ዉስጥ ከዚህ በኋላም እንገናኛለን የሚል መልዕክት ነበር። "ኢክሩ ባለፈዉ ግን ለምንድን ነበር ታክሲ ዉስጥ እያየሽኝ የሳቅሽዉ?" አልኳት ትልቅ ነገር እንዳስታወሰ ሰዉ ወደሷ እየዞርኩ "እንዴ ፈዉዛኔ ታክሲዉ ዉስጥ ስትቃለድ የነበረዉ እኮ ከሴቶች ጋር ነበር። እኔ ደግሞ በጣም ኮስታራ ስለምትመስለኝ ሴት የምታናግር ራሱ አይመስለኝም ነበር።" አለችኝ ልክ እንደባለፈዉ እየሳቀች ብዙዎች የሚታሰቡት እነሱ እንደሆኑት አይደለም። ተመልካቹ እንደሚስላቸዉ ነዉ። እንደኔ እኮ ተጫዋች የለም ግን ኮስታራ መሰልኳት። ይገርማል!! . ሁለት ሰአት ሊሆን ሲል ከኢክሩ ጋር ተለያየን። ቤቷን ስለማላዉቀዉ እስከቤቷ አልሸኘኋትም። የሰፈራችን መስጂድ ጋር ስንደርስ አዛን እያለ ነበር። አዛን ማለት ሁሌም ከመስጂድ የሚሰማዉ "አላሁአክበር" የሚለዉ የስግደት ሰዓት መድረሱን መጠቆሚያ ድምፅ ነዉ። እሷ በቅያሱ ታጥፋ ሄደች እኔ መስጂድ ገባሁ። መስጂዱ አካባቢ ያሉ ሰዎች እንዳያዩን ሁለታችን

Открыть в Telegram
Просмотры14 100+666%к среднему
Пересылки—
Реакции66
Комментарии—
#9239Текст

.               ♥️●●●#ነጠብጣብ●●●♥️             💞#እውነተኛ_እና አስተማሪ_ታሪክ💞                              #ክፍል_3 ...🖊ሰዉ የራሱ መልካም ጎን እንዳለዉ ሁሉ ደካማ ጎንም ይኖረዋል። ገና ለገና ዛሬ ተለያየን ተብሎ የሰዉን ስም አተላ መቀባት አግባብ ነዉ ብዬ አላምንም። ኢክሩ አብረን እያለን ለኔ መልካም ነበረች። . አስተናጋጇ ፊቴ መጥታ ቆመች ፈገግ ብላ "ፈዉዛን ሳፊዉ!!" አለችኝ። ስሟ ረሂማ ነዉ። ከኢክራም ጋር እዚህ ቤት ስንመላለስ ሁሌም የምታስተናግደን እሷ ነበረች። "ፈዉዛን ሳፊዉ!!" ያለችኝ ወተት በሳፊ ስለምጠጣ መሆኑ አንዱ ምክንያቱ ነዉ። ሰሞኑን ግን ይሄን ቃል የምትጠቀመዉ ብቻዬን ስለምመጣ ነዉ። ያዉ ወተት ሳፊ ሲሆን ያለቡና ብቻዉን አይደል የሚቀርበዉ። ጨዋታዋ ደስ ስለሚለኝ ምንም ጥሩ ስሜት ላይ ባልሆንም ፈገግ ብዬ "ወዬ ረሂማ ኮካ" አልኳት። ሳቋ ወዲያዉ ወዲያዉ ቡፍ ስለሚል ነዉ ኮካ የምላት። "ከወተት ሌላ ምትፈልገዉ ነገር አለ?" አለችኝ። ምን እንደምጠጣ በደንብ ታዉቃለች። "ወተት ብቻ አምጭልኝ ኮካዬ" አልኳት እየሳቅኩ። ምላሷን አዉጥታብኝ ወተቱን ልታመጣ ሄደች። በነገራችን ላይ ከአስተናጋጆች ጋር እንደዚህ ያለ ወዳጃዊ ግንኙነት መመስረት ደስ ይለኛል። ካፌ ብቻ ሳይሆን የትም ስሄድ ፊቴን ከመከስከስ ይልቅ ፈታ ብዬ እየተጫወትኩ ከሰዎቹ ጋር መግባባት ያስደስተኛል። ተጫዋችማ ነበርኩ ኢክሩ ያደረገችኝ ነገር የሆነ አዚማም አደረገኝ እንጂ!! ከኢክሩ ጋር የተዋወቅንበት መንገድ ትንሽ ለየት ይላል። ፈጣሪ እራሱ ተዋወቁ ብሎ ሜዳዉንም ፈረሱንም እንካችሁ እንደማለት ነበር ያመቻቸልን። ከኢክሩ ጋር እንዴት እንደተዋወቅን በደንብ አስታዉሳለሁ!! አዎ በደንብ!! ቀኑ ጁምዓ(አርብ) ቀን ነበር!!ከኢክራም ጋር የተገናኘነዉ የዛሬ ሁለት ዓመት እኔ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናዬን ለመዉሰድ ስዘጋጅ ፣ እሷ ደግሞ የመሰናዶ ትምህርት ቤት መግቢያ ፈተና ለመዉሰድ ስትዘጋጅ ነበር። ይህቺን ዉብ ፈጣሪ ሲያንቀለቅል ታክሲ ዉስጥ ይዞልኝ መጣ። ታክሲዉ ዉስጥ ብቻም አይደለም!! ከታክሲዉም እኔ የተቀመጥኩበት የመጨረሻዉ ወንበር ላይ በመካከላችን አንድ ሰዉ ብቻ እስከሚኖር ድረስ አቀራርቦ አስቀመጠልኝ። በመካከላችን አንድ ሰዉ መኖሩ ፈጣሪ "አንተም የድርሻህን ያህል ጣር እንጂ" ሊለኝ ያደረገዉ ነበር የመሰለኝ። እኔም እሷም ከትምህርት ቤት እየተመለስን ነበር። እሷ የምትማርበት ትምህርት ቤት እኔ ከአራተኛ ክፍል እስከ አስረኛ ክፍል የተማርኩበት ትምህርት ቤት ነዉ። የለበሰችዉን ዩኒፎርም ስመለከት በትምህርት ቤቱ ያሳለፍኩት ትዝታ ወለል ብሎ ይታየኝ ጀመር። ታክሲዉ ዉስጥ የሷን አይነት ዩኒፎርም የለበሱ ተማሪዎች ነበሩ። ከነሱ ጋር የመምህራንን ስም እና ባህሪ እየነገርኳቸዉ ስንሳሳቅ እሷም እየሰረቀች ስታየኝ ተመለከትኩ። ጥሎብኝ ሴት ቀድማ ሳታናግረኝ አላዋራም። ለራሴ ዋጋ ስለምሰጥ ነዉ መሰለኝ ለማንም መርከስ አልፈልግም። የዛን ቀን ግን እየተሽኮረመመች ስትመለከተኝ ሳይ ወዲያዉ ፊቴን ወደሷ አዙሬ እርግጠኛነት በተሞላበት ስሜት "አንቺ የሆነ ቦታ ታዉቂኛለሽ።" አልኳት። እሷም አሁንም ከሳቋ ጋር እየታገለች በአዎንታ ጭንቅላቷን ነቀነቀችልኝ። በሁለታችን መካከል የነበረችዉ ልጅ "በሉ ልውጣላችሁ" ብላ ከታክሲዉ ወረደች። የመዉረጃ ቦታዋ ደርሶ ይሁን የወረደችዉ አሊያም የኛን የማዉራት ፍላጎት ተረድታ አላወቅኩም። ብቻ ለትዉዉቃችን አስተዋፅዖ አበርክታለች። ግን ምናለ ልጅቷ ከመካከላችን ባልወጣች እና እኔና ኢክሩ ሳንተዋወቅ በቀረን። ከነዉበቷም ከነፈገግታዋም ስብራቴ መሆኗ ላይቀር ምናለ ባላወቅኳት። ልጅቷ ከመካከላችን እንደወጣች ኢክራምን የት እንደምታዉቀኝ ጠየቅኳት። መስጂድ የሚዘጋጁ ዝግጅቶች ላይ መድረክ ስመራ እንደምታዉቀኝ ነገረችኝ። . በትርፍ ሰዓቴ መስጂድ ዉስጥ የስነ ፅሁፍ ስራዎችን እሰራለሁ። በእስልምና ሀይማኖት መሰረት የወንዶች መስገጃ ቦታ እና የሴቶች መስገጃ ቦታ የተለያየ ቦታ ላይ ነዉ የሚሆነዉ። እኔ ኢክራምን ከዛ ቀን በፊት አላዉቃትም ነበር። መስጂድ ነዉ የማዉቅህ ስትለኝ ወዲያዉ አደብ ያዝኩ!! የተከበረ ቦታ ላይ ታዉቄማ እዚህ አልረክስም አልኩ በልቤ። ግን ወዲያዉ የጓደኛዬ የአዩብ ፍቅረኛ ሪም ትዝ አለችኝ እና ታዉቃት ከሆነ ብዬ ጠየቅኳት። በጣም የቅርብ ጓደኛዋ እንደሆነች ነገረችኝ። ለማንኛዉም ከሷ ጋር የሚተዋወቁ ከሆነ የእኔ እና የእሷ ነገር እንዳለቀለት አሰብኩ። አዩብ እና ሪም ሲኮራረፉ ሁሌም እኔ ነበርኩ የማስታርቃቸዉ። ሪም ቀርባ ሳታዉቀኝ በጣም ትጠላኝ ነበር። ስንቀራረብ ግን በጣም ወደደችኝ። አዩቤ ደግሞ ቁጡ ስለሆነ ሲጣሉ ለማረጋጋት ግዴታ እኔ መግባት አለብኝ። ስለፍቅር ህይወት እኮ ምንም አላዉቅም ግን እንደ ቀበሌ ሹም በባዶ ገብቼ እለምድባቸዉ ነበር። ኢክራም ስሜን እንደምታዉቀዉ ብገምትም ለወጉ ያክል ፈገግ ብዬ "እንተዋወቅ ፈዉዛን እባላለሁ" አልኳት። አይኖቿን በሀፍረት ሰበር እያደረገች "ኢክራም እባላለሁ" አለችኝ። የመዉረጃ ቦታዋ ከኔ ትንሽ ይቀድም ስለነበር ቀድማኝ ወረደች። የዛን ቀን ከለበሰችዉ ዩኒፎርም ላይ ጥቁር ሰማያዊ ጅልባብ ለብሳ ነበር። ጅልባብ ማለት በአብዛኛዉ ሙስሊም ሴቶች የሚያዘወትሩት እጅንና ፊትን ብቻ የሚያሳይ ሰፊ ልብስ ነዉ። ከወረደች በኋላ ስልኳን እንዳልተቀበልኳት አስታወስኩ። ኩራቴ ተናንቆኝ ነዉ? ለምን ስልኳን አልተቀበልኳትም? አዎን ገባኝ የሪም ጓደኛ ነኝ ስላለችኝ ነዉ ስልኳን ያልተቀበልኳት። የሪም ጓደኛ ከሆነች እኔና ሪም በጣም ስለምንግባባ ስልኳን በቀላሉ ማግኘት እንደምችል ስላሰብኩ ነዉ ዝም ያልኳት። . የዛን ቀን ታክሲ ዉስጥ ኢክራምን ሳወራት የነበራት አይነአፋርነት አሁን ላሉት አይንአዉጣ ሴቶች እና ለአሁን እሷነቷም ጭምር ቢታደል ይበቃ ነበር። የሆነ ከአይናፋርነትም ቀልብ የሚገዛ አይናፋርነት አለ እኮ የእዉነት!! የተመጠነ በዉስጡ ትህትናን እና አክብሮትን ያዘለ አይናፋርነት!! ከተለያየን በኋላ ቤት ገብቼ አረፍ አልኩ። ግን አሁንም የማስበዉ ዛሬ ታክሲ ዉስጥ ስለተዋወቅኳት ቆንጆ ልጅ ነበር። አይናፋርነቷ ፣ ፈገግታዋ ሁሉ ትዝ እያለኝ ብቻዬን ፈገግ አልኩ። ወዲያዉ ራሴን አረጋጋሁት ምንድነዉ ስለማላዉቃት ሴት ማሰብ? በሰዓቱ እኔ የአስራሁለተኛ ክፍል ተማሪ ነኝ። ሀይማኖታዊ መድረኮችን መርቼ ከወረድኩ በኋላ በራሱ የሴቶቹ የፌስቡክ እና የስልክ መልዕክቶች ፈተና ነበር የሚሆኑብኝ። አንዳንዴ ፍላጎታችን ተመሳሳይ ሆኖ ግን የፍላጎታችንን ለማግኘት የተለያየ ቦታ እንሄዳለን። አንዳንድ ሴቶች ሀይማኖታዊ መድረኮች ላይ የሚታዩ ወንዶችን ለመጥበስ በየዝግጅቶቹ ላይ ይገኛሉ። አሁን ላይ እኮ ሁላችንም የመጥበስ መልዕክተኞች ሆነናል። በየትምህርት ቤቱ በየሄድንበት ሁሉ!! ሀይማኖት ቦታ ላይ ያለዉ አጠገቡ ያለችዉን ይጠብሳል ወይ ትጠብሰዋለች። ይሄ ደግሞ ሁሉም ሀይማኖት ላይ ያስተዋልኩት ሀቅ ነዉ። እኔም ብዙ ጊዜ እንደዚህ ያሉ ነገሮች ገጥመዉኛል ግን ፊት አልሰጠኋቸዉም። በየጊዜዉ የማላዉቃቸዉ ሴቶች ልብ የሚያቀልጡ መልዕክቶችን ፌስቡክ ላይ ይልኩልኛል። እኔ ግን ብዙም ግድ አይሰጠኝም ነበር። ታዲያ ቆይ ዛሬ ምን ተገኝቶ ነዉ ስለማላዉቃት ሴት የማስበዉ? ገርሞኛል። ቀልቤን ስርዓት ማስያዝ አለብኝ።

Открыть в Telegram
Просмотры12 200+563%к среднему
Пересылки—
Реакции75
Комментарии—
#9224Текст

‍ ​​.              ♥●●●ነጠብጣብ●●●♥️             💞እውነተኛ እና አስተማሪ ታሪክ💞                            #ክፍል_2 ...🖊ዉስጤ ላይ የሚሰማኝን የመሰበር ስሜት ለማስታመም ሰፈራችን ዉስጥ ወደሚገኘዉ ጭር ያለ ካፌ ሄድኩ። ካፌዉ ሰዉ ስለማይበዛበት ጥንዶች ይመርጡታል። እኔ ካለሁበት ጠረጴዛ ፊት ለፊት ጥንዶች ተቀምጠዉ ያወጋሉ። እሱ ይቀልዳል እሷ ትስቃለች ፣ ፀጉሯ አይኗን ሲሸፍናት እሱ ወዲያዉ በጣቱ ፀጉሯን ወደኋላ ይመልስላታል። አይን ለአይን እየተያዩ ይስቃሉ። ስናፈቅር አለም ሁሉ እጃችን ላይ ያለች ትመስለናለች። የኛ አለም ባፈቀርነዉ ሰዉ ህይወት ዉስጥ ይገደባል። ሀዘናችን ያፈቀርነዉ ሰዉ ሀዘን ይሆናል። ደስታችን ያፈቀርነዉ ሰዉ ደስታ ይሆናል። መለማመዳችን የህይወት መዘዉራችን የአንዳችን በአንዳችን ላይ የተደጋገፈ እንዲሆን ስለሚያደርግ አንዳችን ያለ አንዳችን ጎዶሎ እንደሆንን ይሰማናል። አንዳንዴ ደግሞ ከእዉነት ጋር እንከዳዳለን። ከወደድናት ልጅ የሚበልጡ ቆንጆ ሴቶች ሞልተዉ እኛ ግን አፋችንን ሞልተን ከሷ ሌላ ዉብ ከየት መጥቶ እንላለን። ይህ ከፍቅራችን የሚመነጨዉ ስሜት ላፈቀርነዉ ሰዉ የመልአክነት ዘዉድ ይጭንለታል። ሲሳሳት ስህተቱ አይታየንም። ፍቅር የአእምሮን ምክንያታዊ አስተሳሰብ የሚያደነዝዝ እፅ ሳይሆን አይቀርም። . ከፊት ለፊቴ የተቀመጡት ጥንዶች አሁንም ይሳሳቃሉ። 'ምን እየተባባሉ ይሆን?' ብዬ አስባለሁ። ምናልባት እሱ "ካንቺ ዉጪ ሴት ምድር ላይ አለ እንዴ?" ይላታል ለሱ ከሷ ሌላ ማንም እንደማይጥመዉ ለመግለፅ። እሷ ደግሞ ኩራተኛ ናት እንዳትባልም እሱንም እግረመንገዷን ለማሞገስ "ኧረ ያንተም እናት አሉ።" ትለዋለች ከዛ ሁለቱም በአንዴ ካካካካካ ብለዉ ይስቃሉ። አሊያም እሷ "ፈጣሪ ግን አንተን መጥላት የሚችል አንጀት ፈጥሯል?" ስትለዉ እሱ ደግሞ "የአንቺን ዉበት የሚክድ አንደበት ፈጥሮ እንደሆን ምናልባት እኔንም የሚጠላ አንጀት ፈጥሮ ይሆናል።" እያላትም ሊሆን ይችላል የሚሳሳቁት። በጤነኛ አእምሮ ካሰብነዉ እኮ ምንም አያስቅም። በፍቅር የሚሉት ጉድ ዉስጥ ስንሰምጥ ግን የማያስቀዉ ያስቀናል። ስናፈቅር እኮ የቃላት አደራደራችን እራሱ እንዴት እንደሚያምር። ስነ ፅሁፍ በዞረበት ዞሮ የማያዉቀዉ ራሱ እልም ያለ የስነ ፅሁፍ ሰዉ ይሆናል። ከሌሎች የስነ ፅሁፍ ባለሙያዎች የሚለየዉ እሱ ያፈቀራትን ሴት ለማሞገስ ቃላትን ሲያስዉብ ፣ ሌሎቹ ደግሞ የማትታወቅ ዉብ እንስትን ለመፍጠር አእምሯቸዉን ማስጨነቃቸዉ ነዉ። አሁንም ከፊት ለፊቴ የሚሳሳቁትን ጥንዶች እየተመለከትኩ "ምን እየተባባሉ ይሆን የሚሳሳቁት?" እላለሁ። ምናልባት የሚያስቅ ነገርም ላይሆን ይችላል የሚያወሩት ግን አብረዉ መሆናቸዉ የፈጠረባቸዉ ስሜት በራሱ እንደጅል እያሳቃቸዉ ይሆናል። አዉቀዋለሁ ስሜቱን!! . የእነሱን የዛሬ ደስታ እያየሁ የራሴን ስብራት አስባለሁ። ዛሬ የተገኘሁበት ካፌ ዉስጥ የዛሬን አያድርገዉና እኔም እንደነዚሁ ጥንዶች ግጣሜ ትመስለኝ ከነበረች ሴት ጋር እመላለስ ነበር። አዎን ሊያዉም መቼም የምለያት ከማትመስለኝ ቆንጆ ሴት ጋር ነበር ምመላለሰዉ። ስሟ ኢክራም ይባላል። ረዘም ያለች ናት። ፊቷ ቀላ ያለ ነዉ። አይኖቿ ጠበብ ብለዉ በጣም ያምራሉ። ከንፈሯ ቆንጆ እንደሆነ ያወቅኩት ጓደኛዬ ብሩክ ከነገረኝ በኋላ ነበር። ምናልባት እኔ ያላየሁት የከንፈሯ ዉበት ለጓደኛዬ ለብሩክ እንዴት እንደታየዉ ፈጣሪ ነዉ የሚያዉቀዉ። እኔ ለሷ ከነበረኝ ፍቅር ይልቅ እዝነቴ ይገዝፍ እንደነበር ያወቅኩት አሁን ከተለያየን በኋላ ነዉ። የህይወቷን እያንዳንዷን ገመና አዉቅ ስለነበር በጣም አዝንላታለሁ። አብረን መንገድ ላይ ስንራመድ እንኳ እንቅፋት ነካ ሲያደርጋት ልቤ ተገንጥሎ እስከሚወድቅ ድረስ ነበር የምደነግጠዉ። በጣም ታሳሳኝ ነበር። ሰዉ ግን ለሰዉ ይሄን ያህል ይሳሳል? የኔ የተለየ ነበር። እወዳት ነበር። ዉዴታዬ ሙሉ ለሙሉ የተገነባዉ ደግሞ ለሷ ከነበረኝ እዝነት ነበር። . እንደምታፈቅረኝ ሁሌም ትነግረኝ ነበር። እኔ ለሷ ካለኝ ፍቅር ፣ እሷ ለኔ ያላት ፍቅር እንደሚበልጥ ታወራልኛለች። አዎን እነዛን ውብ አይኖቿን እያስለመለመች "ፈዊዬ አንተ ታፈቅረኛለህ ግን የኔ ድመት እኔ ላንተ ያለኝ ፍቅር ካንተ በጣኣኣኣም ይልቃል።" ትለኛለች። የፍቅሯን ደረጃ ሰማይ ይገልፀዉ ይመስል ወደሰማይ አይኖቿን እየሰቀለች። እኔም "አንቺ ከኔ በላይ እንደምታፈቅሪኝ አዉቃለሁ።" እላት ነበር። ይሄ ግን ለሷ ያለኝን ታላቅ የእምነት ደረጃ የሚያሳይ ነበር። ይህ እምነቴ የመነጨዉ ደግሞ ለሷ ካለኝ ጥልቅ ፍቅር ነበር። በሰዓቱ እሷ ይሄን ስሜቴን ተረድታዉ ይሁን አይሁን አላዉቅም። እንደምታፈቅሪኝ አምናለሁ ከማለት በላይ የእምነት ደረጃ ፣ ከእምነት ጥግ በላይ ደግሞ የመዉደድ ልኬት እንደሌለ ይግባት አይግባት አላዉቅም። በነገራችን ላይ የኔ ድመት የምትለኝ ወተት በጣም ስለምወድ ነዉ። እሷ ደግሞ ቸኮሌት ነብሷ ነዉ። . ትዝታዎቼ እጅጉን አዲስ ናቸዉ፤አላረጁም። የኢክሩ ጅልባብ መሬት እየጠረገ ፣ የጅልባቡን እጄታ በእጇ ይዛ ፣ በጥርሷ ጅልባቡን ነክሳ እያየችኝ የሳቀችበት ቀን አሁን እንደተከወነ ድርጊት ጥርት ብሎ ትዝ ይለኛል። ኢክሩ ግጥም አትወድም ፣ እንደዉም የሆነ ጥፋት ካጠፋች መቀጮዉ ግጥም እኔ ሳነብ ማዳመጥ ነበር። ኢክሩን አጥፍታ አንበርክኬያት አዉቃለሁ። ኢክሩን ተንበርክካ ማየት በራሱ ሀሴት ይሰጣል። ከኢክሩ ሌላዉ የሚጣፍጠኝ ነገር 'ደ' የሚለዉን ፊደል በስርዓት ማለት አትችልም። 'ደ' ስትል ስሰማት ጉረሳት ጉረሳት ነበር የሚለኝ። ግን ማን ይሄ ሁሉ ነገር ነበር ይሆናል ብሎ አሰበ? ማንም!! . ዛሬም ከዚህ ሁሉ ስብራቴ ጋር ለኔ የነበራትን እንክብካቤ እና አክብሮት አልክድም። ሰዉ የራሱ መልካም ጎን እንዳለዉ ሁሉ ደካማ ጎንም ይኖረዋል። ገና ለገና ዛሬ ተለያየን ተብሎ የሰዉን ስም አተላ መቀባት አግባብ ነዉ ብዬ አላምንም። ኢክሩ አብረን እያለን ለኔ መልካም ነበረች። ✎ ክፍል ሶስት (3) ይቀጥላል❤️‍🩹 ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ #ሼር♥️ ማድረግ አይርሱ።         ┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿🌺»‌✽‌┉┉┄

Открыть в Telegram
Просмотры12 100+557%к среднему
Пересылки—
Реакции116
Комментарии—
#9209Видео
Просмотры13 000+606%к среднему
Пересылки—
Реакции9
Комментарии—
#9208Текст

‍ ​​.              ♥●●●ነጠብጣብ●●●♥️             💞እውነተኛ እና አስተማሪ ታሪክ💞                             #ክፍል_1 ...🖊ይገርማል ወደዚህች ምድር ከመጣሁ አስራዘጠኝ ዓመታቶች ነጎዱ ማለት ነዉ? እዚህች ምድር ከመጣሁ በልጅነት እንደ ልጅ ከልጆች ጋር የተጫወትኩበት ፣ የእሳቱ እድሜ ደርሶ ልቤ አብጦ ቤት ማንንም አልታዘዝም ያልኩበት እና ህይወትን ለመረዳት የሚያስፈልጉ ወሳኝ ነጥቦችን የተረዳሁበት እድሜ ነጎደ። አሁን ወደ ሀያኛ አመት ሩጫዉን ተያይዤዋለሁ። በነዚህ ዓመታት ዉስጥ በህይወቴ ዉስጥ ብዙ ሰዎች አልፈዋል። ብዙ የማይረሱ ተወዳጅ እና አናዳጅ ሰዎችን አዉቄያለሁ። አስራ አምስት ዓመታትን መጨረሻዬን በመናፈቅ በትምህርት አሳልፌያለሁ። . አሁን የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ነኝ። ስሜ ፈዉዛን ይባላል። ጠይም እና ተጫዋች ነኝ። ቁምነገር ላይ ቁምነገረኛ ፣ ቀልድ ላይ ደግሞ ምርጥ ቀልደኛ ነኝ። በራሴ በጣም እተማመናለሁ። ብዙ ሰዎች ጢባራም ነህ ይሉኛል። ከሩቅ ሲያዩኝ የሚጠሉኝ ቀርበዉ የሚያዉቁኝ ደግሞ የሚወዱኝ አይነት ሰዉ ነኝ። ስለራሴ እንደዚህ በድፍረት የማወራዉ ብዙዎች ከቀረቡኝ በኋላ ምን ያህል ከሩቅ ሲያዉቁኝ ይጠሉኝ እንደነበር እና ሲቀርቡኝ እና ሲያዉቁኝ በጣም እንደወደዱኝ በተደጋጋሚ ስለሚነግሩኝ ነዉ። ለራሳችን ያለን አመለካከት ከሚገነቡበት መንገዶች አንዱ ሰዎች ስለኛ በሚነግሩን ነገር ላይ የተመሰረተ መሆኑ እሙን ነዉ። ለዛ እኮ ነዉ ቤተሰብ እምነት የሚጥልባቸዉ ልጆች ፣ ሁሌም ጀግንነታቸዉን የሚነግራቸዉ ታዳጊዎች ከከፍታ መሰላል ላይ ቆመዉ የምናየዉ። በአንፃሩ ደግሞ አታዉቅም እየተባሉና ትንሽነታቸዉ እየተነገራቸዉ ያደጉ ልጆች ትንሽ እንደሆኑ ይቀራሉ። በእርግጥ እየተሞገሱ የሚቀሽሙ እንደሚኖሩት ሁላ ከዚህ የትንሽነት ቀንበር አምልጠዉ ታላቅ የሚሆኑ ጥቂቶችም አይጠፉም። . እኔ ፈዉዛን ካመንኩበት ነገር ላይ ወደኋላ ዝንፍ አላዉቅም። እንደወራጅ ዉሀ በተቀደደላቸዉ እንደሚፈሱ ከንቱ ሰዎች አሊያም ወደነፈሰበት እንደሚነፍሱ ገለባዎች አይነት አይደለሁም። ሰዉ ነኝ!! እንቢ የማለት አቅም አለኝ። ከአስተሳሰቤ እና ከማንነቴ ጋር የሚጣረስን ነገር እምቢ ከማለት ወደኋላ አልልም። ሁሌም ቃሙ ሲሏቸዉ ገረባ ሳይቀር የሚያኝኩ ፣ ጠጡ ሲሏቸዉ ፋራ ላለመባል አተላ የሚጋቱ ፣ አጭሱ ሲሏቸዉ ከማን አንሼ ብለዉ ኦ በጭስ ለመስራት አይናቸዉ ተጎልጉሎ እስከሚወጣ የሚያጨሱ ምስኪን፣ እንቢ የማለት ወኔያቸዉ የተሰለበ ፣ የመጣዉ ጎርፍ ሁሉ እያላጋ የሚወስዳቸዉ፣ የማንነታቸዉን ልዕልና ያላከበሩ ሰዎች ያሳዝኑኛል። በእንደዚህ አይነት ሰዎች መካከልም ተከብቤ እነሱ የመጣዉ ጎርፍ ሁላ ሲያላጋቸዉ እኔ በፅናት ቆሜ አዉቃለሁ። ለዛ ነዉ በድፍረት እንቢ የማለት አቅም አለኝ የምለዉ። . በተማርኩባቸዉ ትምህርት ቤቶች ዉስጥ ሁሉ ዝነኛ ነበርኩ። የትምህርት ቤት ክበባት ውስጥ መሳተፍ አዘወትር ነበር። ስነፅሁፍ እወዳለሁ። አንዳንዴ እሞነጫጭራለሁ ብዙ ጊዜ ግን የሌሎችን የስነ ፅሁፍ ስራዎች መድረክ ላይ ማቅረብ ይዋጣልኝ ነበር። እናም ከዚህ ስብዕናዬ ጋር ብዙ ጓደኞችን አፍርቻለሁ። ብሩክ እና ሄኖክ የልጅነት ጓደኞቼ ናቸዉ። ከብሩክ እና ሄኖክ ጋር የተዋወቅነዉ የአምስተኛ ክፍል ተማሪዎች ሆነን ነዉ። አንድ ትምህርት ቤት ከመማራችን በዘለለ ሰፈራችንም አንድ ነበር። ብሩክ በአቋራጭ የሚከብርበትን መንገድ ዘወትር የሚያስብ አይነት ሰዉ ነዉ። የሰዉ ታሪክ ማዳመጥ ይወዳል በተለይ የፍቅር ታሪክ። አንድ ሰዉ የፍቅር ግንኙነት ዉስጥ ገብቶ ካገኘዉ ልምድ ሊያወራ ከሚችለዉ በላይ ብሩክ የፍቅር ግንኙነት ዉስጥ ለመግባት ከመፈለጉ የተነሳ ብዙ ይቀባጥራል። እኔ ከብሩክ ጋር የምካፈለዉ የህይወቴ ጎን የፍቅር ህይወቴን ነዉ። ማዳመጥ ስለሚፈልግ እነግረዋለሁ። ሄኖክ ደግሞ ቀላ ያለ አጭር ቁመት ያለዉ ሚስኪን ልጅ ነዉ። መልካም ልብ አለዉ። ወደ መልካም ነገር የሚጠራዉ ሰዉ ካለ ሁሌም መልካም ለማድረግ ዝግጁ ነዉ። ነገር ግን የኔ የሚለዉ አቋም የለዉም። እኔ ጋር ሲመጣ ከኔ ጋር ያነባል ፣ ከብሩክ ጋር ሲሆን ደግሞ ከሱ ጋር ለመመሳሰል ይሞክራል። ከጊዜያት በኋላ ሄኖክ ሰፈር ቀይሮ ከኛ ሰፈር ትንሽ ራቅ ወዳለ ቦታ ስለሄደ ግንኙነታችን እየቀዘቀዘ መጣ። በአንፃሩ ደግሞ ከብሩክ ጋር በጣም እየተቀራረብን ሄድን። ቀናት ቀናትን እየወለዱ ወራት ከወራት ጋር እየተጋቡ ይኸዉ አስራ ዘጠኝ አመት አልፎኝ ወደ ሀያ ሩጫዉን ተያያዝኩት። . ዛሬ ዉስጤ ላይ የመሰበር ስሜት ይሰማኛል። ሁሌም ጠንካራ ነበርኩ ፣ ዛሬ ግን በህይወቴ ዉስጥ በፍፁም ሊከሰት ይችላል ብዬ የማልጠብቀዉ ነገር ተከስቷል። ዉስጤ የመሰበር ስሜት ይሰማኛል። ለካ የኛ ያልናቸዉ ሰዎች የእምነት ባንዲራችንን ቀድደዉ በተቃራኒ ወገን በኩል ሲሰለፉ ፣ ያመናቸዉን ልባችንን ፊት ሲነሱ ፣ ያጎረሷቸዉን እጆቻችንን ሲነክሱ በጣም ያማል። ህመሙ የልብ ምታችንን ከወትሮዉ በተለየ እንዲመታ ሲያስገድደዉ ፣ አይናችንን ከእንቅልፍ ጋር ሲያጣላዉ ፣ ስሜቱን መግለፅ ሲከብደን ፣ በደፈናዉ ስብራት እንለዋለን። አዎን ሁሉም ቀጥ ብሎ የቆመዉ የህይወት መዘዉራችን ሲናጋ ፣ ምንም ባይገልፀዉም እንኳ መሰበር እንለዋለን። አዎ ዛሬ እኔም ተሰብሬያለሁ። የስብራቴ ሁሉ ምንጭ ደግሞ ከክብር ዙፋኔ ወርጄ አብሬያት የተጫወትኩት ፣ ለማንም ያላረከስኩትን እኔነቴን ያረከስኩላት የህይወቴ ትልቋ ደስታ፣ ስህተት እና ስብራት ኢክራም ናት። ኢክራም ቆንጆዋ!! ኢክራም ሀዘንተኛዋ!! ኢክራም አፍቃሪዋ!!

Открыть в Telegram
Просмотры10 100+449%к среднему
Пересылки—
Реакции122
Комментарии—
#9059Текст

    ♥️ ፅናት ♥️...!!!      .      . 🥀..ክፍል 60..🥀 . . . . ከቆነጃጅቶቹ አንድዋ እና ማየት ሳትችል ቀርታ ያየችውም አክስቴ ናት ማለት ነው" አለ። ፅናት "አዎ በትክክል" አለች። ቤካንም "ስለዚህ እብዱ ቤሎል የእኔ አባት ነበር ቤሎል ሳይሆን ያቤፅ ነበር።" አለ። ያቤፅም "አዎ ልጄ" አለው። ቤካን "እናቴ ማማ እኔን ስትወልጂ በእዛ ስቃይ አልፈሽ ነበር " አለ። በፀሎት "አዎ ልክ ነክ እናትህ ጠንካራ ሴት ናት" አለችው። ቤካንም "የስሜ ትርጉም ድብቅ ፍቅር ነው ሊባኖስም ሊባኖስ የተባችው ስሟን በአምሬላ ቀይረሽ የነገርሽኝ ናት ከቆንጆዎቹ እህትማማቾች ውስጥ ትልቅዋ ልጇን አምሬላ አለቻት። ነገር ግን አምሬላ ስትሞት ለትንሽዋ ቆንጆ ነበር ልጅሽ ሴት ከሆነች አምሬላ በያት ያለቻት አጋጣሚ ስትወልድ ወንድ ወለደችና ማለት አልቻለችም ስለዚህ ቆንጅዬዋ ታላቅ እህቷ አጋጣሚ ሴት ስለወለደች ስሟን አምሬላ አለቻት አምሬላ ማለት ሊባኖስ ናት" አለ። የቤካን እንዲህ ስለ ታሪኩ ማብራሪያ መስጠቱ ሁሉንም አስገርሟቸዋል። ቤካን አሁንም ማውራቱን አላቆመም "ስለዚህ የእኔ ሴት አያት በወንድ አያቴ ወንድ አያቴም በራሱ እጅ ነው የሞቱት ማለት ነው። እና ዶክተር ስለሺ ማለት የእኛ የቤተሰብ ዶክተር ዶክተር ዳመነ ነው። አክስቴ እና እናቴ የሚኖሩበት ቤትም ከአያቴ ሶስና እና ከጋሼ የተሰጣቸው ነው ማለት ነው" አለ። ሶስናም "አዎ ልጄ" አለችው። ቤካን "ይህ ማለት እኮ ባለ ሱቋ ሴት አንቺ ነሽ ማለት ነው አደል? አያቴ" አላት። ሶስና አዎ ልጄ አለችው። ቤካን አሁንም ግርም እያለው "መናገር የማይችለው ሹፌር አሁን በጣም እሩቅ ቦታ ሄዶ መዳኒት ቀማሚው በሰጡት ቤት እየኖረ ነው የእሱስ ትክክለኛ ስም ማንነው" አላት። እናቱ ፅናትም "ማርቆስ" አለችው ቤካን ወደ ፅናት ሄደና "ማማ በይ አሁን ያቺ መልካም ሴት ብለሽ የነገርሽኝ እና ፈዋሽ እና አዳኝ የሆኑት ሰዎች መቃብር ጋር ውሰጅኝ ምክንያቱም ታሪኩ ማብቂያ ላይ ሁለቱ ቆነጃጂቶች ልጆቻቸውን እና ቤተሰባቸውን ይዘው ወደ መልካም ሰዎች መቃብር ይሄዱና ለልጆቻቸው ያሳዩዋቸዋል ብለሻል ከዛ በፊት በፊት እምትኖሩበትን እና የተወለድኩት ቤት ለፓስቲ ጠባሽዋ እንድትኖርበት ስጣችኋታል እዛ እንሂድ " አላት። ፅናትም "እሺ ልጄ" ብላ ወደዛ ሄዱ ደመቁን አግኝተው ሰላም ብለዋት ገቡና ሄዱ። ፅናት ቤካን የተወለደበትን ክፍል አሳይታው ጊቢውን ሁሉ አስቃኝታው ወጡ። ቤካንም " የአክስቴ ባል ቢኒም ፍፁም ነው በቃ አሁን ወደ መቃብር ስፍራው" አለ ቤካን... ፅናትም "እሺ ልጄ በሉ እየመሸ ነው ቶሎ ብለን ወደ መቃብሩ ቦታ እንሂድ" አለች ፅናት። ሁሉም መኪና ውስጥ ገብተው ወደ ሊባኖስ እና ጋሽ በሬሳ መቃብር ቦታ ሄዱ። ቤካን ትንሽዋ ሊባኖስን እጅዋን ይዞ መቃብሩ ፊት ለፊት ቆሞ "ሰላም ሊባኖስ አየሽ ኢቺ የአክስቴ በፀሎት ልጅ ናት" አለና ትንሽዋ ሊባኖስን ስምሽን ንገሪያት አላት። "ሊባኖስ ነው ስሜ እናቴ ባንቺ ስም ነው የጠራችኝ " አለቻት። ቤካንም "እናቴ ታሪኩን ስትነግረኝ መጀመሪያ ላይ ፈርቼሽ ነበር ከዛ ግን መጨሻውን ስሰማ ወደድኩሽ ታሪኩ እውነተኛ መሆኑን ሳቅ ደሞ በአካል ላውቅሽ ፈለኩ " አለና አይኑን ከሊባኖስ መቃብር ነቅሎ ጋሽ በሬሳ ላይ ተክሎ "ጋሼ እርሶም ጥሩ ነበሩ እናቴ ስለ እርሶ ጥበብ እና ስለ ሊባኖስ ከነገረችኝ በኋላ ንግግሪ እና ሀሳቤ እንደ ትልቅ በሳል ልጅ ሆኖል አመሰግናለሁ። እናንተንም ልክ አክስቴ እና እናቴ ልጅ ሆነው ሲንከባከቧቸው እንደነበረው እማማ እየመጣን እናያቹኋለን እናቴ ስለ እማማ ነግራኝ ነበር። እማማን እና አያቶቼን በእየሳምንቱ ቀብራቸው ጋር እየሄድን እንጠይቃቸዋለን ስለ አባቴ እህት ግን ማንም አያቅም " አለ። ሁሉም አለቀሱ ትንሽዋ ሊባኖስ "ቤካን እኔ ግን ይህ ሁሉ በደንብ አልገባኝም" ስትለው። ቤካን "አስረዳሻለው " አላት። በፀሎትም በቃ ኑ ወደቤት እንሂድ" አለችና በፀሎት ቤት ሄዱ እያወሩ እና እየተጫወቱ እራት ደረሰ። የበፀሎት ሰራተኞች እራቱን አቀረቡ እና እየተመገቡ ቤካን "ስለዚህ የትልቅ የጨርቃጨርቅ ባለቤት አጎቴ ፍፁም ነው ስኬታማዋ ሚስቱ አክስቴ እና የትንሽዬዋ ቆንጆ ባል እብዱ ከዛ ደሞ ታታሪው የቢዝነስ ሰው አባቴ ነው" አለ። ፅናትም አዎ ልጄ የእናታችን ህይወት ብቻ ሳይሆን የእኔ እና የእህቴ ህይወትም በፅናት እና በፀሎት የቆመ ነው" አለች።ቤካን  "ቆይ ሰአሊው ደሞ ወደ ውጪ ሀገር ሲሄድ ባለፈው አመት የሞተው ሰአሊው ጓደኛክ ነው እሺ ሊላ ደሞ ደራሲው እሱንም አወኩት እና ሌላ ቅድም ሄደን የተወለድኩት ቤት ያገኘናት ደመቁ ስትይ ስሙዋን ሰምቻለው ማማ እሷ ደሞ ፓስቲ ስሸጡ ምታግዛቹ እና ለመጀመሪያ ጊዜ ማማ እና ባባ አብረው ሲተኙ የያዘቻቸው ናት እና የቆነጃጂቶች ህልም በቁርባን ማግባት ነበር ትልቋ ቆንጆ በአክሊል አገባች  " አለና ግድግዳው ላይ የተለጠፈውን የበፀሎትን የሰርግ ፎቶ አየና "ትንሽዋ ቆንጆ ግን ክብሯን ለምትወደው እና ለልጅዋ አባት ስለሰጠች አልቻለችም ምክንያቱም በተክሊል ለመጋባት ክብርን ለሚያገባት ቢሰጥም ስለማይፈቀድ እና ቆነጃጂቶቹ ብለሽ የነገርሽኝ ታሪክ የራሳቹ ነው እማማ ግን ከአባባ ጋር ለምን ከትዳር በፊት" ሲል ትንሽዋ ሊባኖስ  "ቤካን እየተበላ አይወራም" ስትለው ሁሉም ከልባቸው ሳቁ ቤካንም "ዝም በሉና ብሉ እናቴ እንዳለችው ሊባኖስ እና ጋሺ ለዘላለም በልባችን ይኖራሉ  አለ። ሁሉም በአግራሞት ቤካንን አዩት ቤካንም አታፍጥጡ ትኩረታችሁን ምግቡ ላይ አረጉ አለ። አሁንም በድጋሜ ሳቁ..                  .                  .                  . ➱➱➱ተፈፀመ➱➱➱📜                  .                  .                                  *                 *                 *    እንዴት ነው ታሪኩን . በቀጣይ በአሪፍ ድርሰት እንገናኛለን ሁላችሁም ክበሩልኝ።🙏                     https://vt.tiktok.com/ZSQFWNqcp/

Открыть в Telegram
Просмотры13 700+644%к среднему
Пересылки—
Реакции76
Комментарии—
#9058Текст

    ♥️ ፅናት ♥️...!!!      .      . 🥀..ክፍል 59.. . . ዳኞች እና ታዳሚዎች አጨበጨቡ የሽልማቱ ሰአት ደረሰ። እና ያለ ምንም ተቋውሞ ሰአሊ ቀመር በሚገርም ውጤት አሸነፈና የብር እና የዋንጫ ሽልማት አገኘ። ሁሉም ተደሰቱ ቀመር " በሉ ላድርሳቹ ወደ ቤት" አላቸው የመውጫ በሩ ላይ ሲደርሱ። ያቤፅም " አያስፈልግም ጓደኛዬ እናመሰግናለን መኪና ይዘናል" አለው። ደራሲው መጥቶ ሁሉንም ሰላም አላቸውና "በጣም ጥሩ አሳዛኝ ታሪክ ነበር ያሳለፋችሁት" አላቸው። ስአሊ ቀመረም "ልክ ነው ህይወት ትፈትናለች ግን በእዚህ መጠን ስትፈትን ከባድ ነው በእነሱ ታሪክ እኔም አልፎልኛል እና ህይወቴን የሚቀይር ገንዘብ አግቻለሁ" አለ። በፀሎትም ለሰአሊው ቀመር " ልክ ብለካል አሁን እኛም ያገኘከውን ገንዘብ በጭራሽ አንጋራክም ያንተ ስኬት ለእኛ በቂ ነው" አለች። ፅናትም "እህቴ ልክ ናት እኛ በህይወት አጋጣሚያችን ባገኘናቸው ሰዎች አሳቦ አምላክ በቂ የሆነ ሀብት ከጤና ጋር ሰጥቶናልና ካንተ ደስታክን ብቻ ነው የምንፈልገው።" አለችው። ደራሲ መሀመድ ሳላዲንም "ጥሩ አስተሳሰብ የያዛቹ ናቹሁ እኔ ኑሮዬን ጠቅልዬ ከእዚህ ሀገር ልወጣ ነው።  ባለኝ ጊዜ ሙሉ ታሪካችሁን መስማት ከባድ ነው በእረግጥ በሚገረም መልኩ ሰአሊው ስለ ህይወታቹ ባጭሩ አስረድቷል ግን ደሞ ሙሉን በደንብ ብሰማው ምኞቴ ነው" አላቸው። ያቤፅም "ሁሉን ነገር የፃፍኩበት ማስታወሻ አለኝ እሱን ልሰጥህ እችላለሁ ከዛ ኮፒ አረገክ መውሰድ ትችላለህ  አለው። ደራሲውም ስልኩን ለያቤፅ ሰጥቶት ሄደ። እነ ያቤፅም ወደ ቤታቸው ሄዱ።       ፨፨፨ ከ 8 አመት በኋላ ፨፨፨ አንድ የሚያምር ቤት ሳሎን ውስጥ የፅናት በቬሎ ያገባችበት ፎቶ በትልቁ ግድግዳ ላይ ተሰቅሏል። ፅናት መኝታ ቤት አልጋ ላይ ከልጅዋ ቤካኔ ጋር በትራስ እየተደባደበች (እየተጫወተች) ነው። በድንገት ጨዋታውን አቁመው አልጋው ላይ በጀርባቸው ተንጋለው እኩል "ኡፍፍፍፍ" አሉ ፅናት  "ልጄ" አለችው ቤካንም "አቤት ማማ" አላት። የህይወት ጣእምን በምን ልንለካ እንችላለን " አለችው። ቤካንም "በምንወዳቸው ሰዎች" አላት። "የህይወት መጥፎ  ጣሙዋንስ" ስትለው "በሚፈትኑን ሰዎች" አላት። ፅናት ጎበዝ ልጄ ብላ ግንባሩን ሳመችው። በድንገት ጩከት ሰሙና ተደናገጡ። ቤካን እና ፅናት ተደናግጠው ወደ ሳሎን ሄዱ። በፀሎት ፣ ፍፁም እና ትንሽዬ የምታምር የበፀሎት ልጅ ሳሎን ቁጭ ብለው አገኟቸው። ቤካን "እኔ እና ማማ ጩከት ሰምተን ነበር የመጣነው" ሲል ትንሽዬዋ የበፀሎት ልጅ ሊባኖስ "እናቴ ናት የጮኸችው" አለች። ፍፁምም "አዎ በረንዳ ላይ ውሀ ነበር እሱ አንሸራቷት ነበር ግን እኔ ደግፌ አስቀረዋት" ሲል። ትንሿ ሊባኖስ ከአባትዋ ፍፁም ጋር ሳቁ ቤካንም ሳቀ። ከውጪ የመኪና ክላክስ ተሰማ። ቤካን "ባባ መጣጣ ብሎ ሮጦ ሄደ" ፅናም "ቀስ በል ቤኮ እንዳትወድቅ" አለችው እና ሶፋው ላይ ተቀምጣ "እሺሺ እንዴት ናቹህ" አለቻቸው። በፀሎትም "ደና ነን እህቴ አንቺስ" አለቻት። "እኔን ተይኝ ያው እሁድ ለእኔ ከቤካን ጋር የምዳረቅበት ቀን አደል" አለች። ትንሽዋ ሊባኖስም "ማሚዬ ዛሬ ደብሯታል ልክ እንደ አሻጉሊት ኩርፍ ብላ ተቀምጣ አባቢ ሲያወራት እ ፣አዎ ፣በጣም፣ ልክ ነክ፤ ኧረ እያለች ነው የመጣችው።" አለች። ፍፁም ፅናት እና በፀሎት ሳቁ ፅናት "የእኔ ቅመም" አለቻት። ቤካን ወደ ሳሎን መጣና "ታታታ አባ መጣልኝኝኝ "አለ የያቤፅን እጅ እየጎተተ እያስገባው። "ኦኦኦኦ እስኪ ተመልከቱ የእኔ ቆንጅዬ አማች ከባልዋ እና ከትንሼዬዋ ልእልት (ከልጅዋ) ጋር መታለች። የእኔ ልዩ እና ቆንጅዬ የልጄ እናትም አለች" አለ። ቤካንም "አሀ ቆይ እኔስ" አለው። ያቤፅ ፈገግ ብሎ "ገና መቼ ተናግሬ ጨረስኩኝ ውዱ ልጄ የእኔ ትንሹ ልኡል ቤኮ ደሞ እንደ እሳት ፈጥኖ እየሮጠ ከበር ተቀበለኝ" አለ። ሁሉም ከት ብለው ሳቁ። አሁንም የመኪና ክላክስ ተሰማ። ቤካን "ውይ አያቴ እና ቅድመ አያቴ መጡ" ብሎ እሮጦ ሄደ። ፅናት "ወይ አምላኬ ምን አይነት ቀውስ ልጅ ነው የወለድኩት " ስትል በፀሎት "ኧር የእኔዋ ቃጠሎ ምላሳምስ" አለች። ያቤፅ "በሉ በሉ ከልጆቹ ወረድ መጣው ልብሴን ቀይሬ"  ብሎ ሄደ። ቤካንን ስማ አቅፋው የያቤፅ አያትም ከኋላ እየተከተሉ ተከታትለው ገቡ። ሁሉም ብድግ ብለው ሰላም አሉዋቸው። ቤካን "ውይ አያቴ ሶሲ ዛሬ ደሞ ቆንጅዬ ሆነሽ ፉንጋዋን እናቴን በልጠሻታል " አላት። ሶስና ክትክት ብላ ስቃ "በምን" አለችው። ቤካንም "በፉንጋነት" አለ። ይህ የተለመደ የሚያዝናና የሁለቱ የሁል ጊዜም ንግግር ነው። ቤካን ወደ ያቤፅ አያት ሄዶ አጠገባቸው ተቀመጠና "ቅድም አያቴ ዛሬ ደሞ አምሮብሀል" አላቸው። እሳቸውም በምን አሉት። ቤካንም "በበበ በ በቃ ተወው" ብሎ ምላሱን ነከሰው ይህ ደሞ ቤካን ሁሌም ከቅድመ አያቱ ጋር የሚያደረገው ንግግር ነው። ቤካን እንዲ ነው ልክ እንደ አባቱ ነው ነገሮችን የሚያከናውነው መልኩም አባቱን ቁጭ ነው። ሰራተኛዋ ለፅናት ምሳ እንደደረሰ ምልክት ሰጠቻት። ፅናትም በሉ ተነሱ ምሳችንን እንብላ ምሳ ደርሷል" አለች ሁሉም ተነስተው የመመገቢያ ጠረጴዛ ላይ ተቀመጡ። ቤካን ልክ ሊበሉ ሲሉ "ቆይ ፀሎት" አለ። ሁሉም ፈገግ ብለው ፀልየው መመገብ ጀመሩ። እየበሉ ያቤፅ መጣና "መልካም ምግብ" ብሎ ሊበላ ሲል። ቤካን "ባባ እንዲባርክህ መጀመሪያ ፀልይ" አለው። ያቤፅም ፈገግ ብሎ ፀልዮ መብላት ጀመረ። ትንሽዋ ሊባኖስ "ስማ ቤካን ያንን ታሪክ ትጨረስልኛለህ" አለችው። ቤካንም "ምግብ ላይ ቁጭ ብለሽ ስለተረት መፅሀፍ አታውሪ ብይና ጠይቂኝ " አላት። በፀሎት ሳቀች። "ቤካን ምግብ ክብር ነው አክስቴ አንቺ እና ልጅሽ ዛሬ ገበታ ላይ ጥሩ ፀባይ አላሳያችሁም" አለ። ሁሉም በልተው ጨረሱ እና ከጠረጴዛው ተነሱ።እና ሶፋው ላይ ተቀመጡ። ፅናት እና በፀሎት ሶስና የሰጠቻቸው የየራሳቸው ቤት ውስጥ ነው የሚኖሩት። በፀሎት "ዛሬ እራት እኛ ቤት ነን ከዛ በፊት ለልጆቻችን እና ለእናንተ ከእህቴ  ጋር የምናሳያቹህ ነገር አለ።" አለች። ሁሉም "ምንድነው ምንድነው" አሉ። ፅናትም "እሱን ታይውታላቹ አሁን ለመውጣት ያልተዘጋጀነው እኔ ፣ ልጄ እና ባሌ ነን ስለዚህ ተዘጋጅተን እንመጣለን "በሉ ኑ" አለቻቸው ያቤፅ እና ቤካንን ሁለቱም ፅናትን ተከትለዋት ሄዱ እና ለባብሰው ወጡ። ቤካንም "ልክ እንደ እናቴ እና አክስቴ አይነት ቆንጆ አይቼ አላቅም" አለ። ትንሽዋ ሊባኖስም "እህ እኔስ" ስትለው። ቤካን "አንቺም ቆንጆ ነሽ ያው አንቺንም ይጨምራል ልእልቷ" አላት። ሁሉም በትልቅ መኪና ውስጥ ገብተው በሹፊር መጀመሪያ ወደ ጋሽ በሬሳ ቤት ሄዱ። አሁን የጋሽ በሬሳ ቤት ቤት አደለም አሁን ሁሉም ነገር ተቀይሮ የሀይምሮ ህሙማን ትልቅ ሆስፒታል ሆኗል። የሆስፒታሉ ስም ህይወት ነው። ህይወት የሀይምሮ ህሙማን ድርጅት። ይላል። ፅናት በእዚህ ድርጅት ውስጥ በዋናነት ትሰራለች። ፅናት "ሊባቲ ትንሽዋ እና ቤካን ይህ ሀኪም ቤት ማለት ባለፈው የነገርኳቹ ታሪክ ውስጥ የነበረ የጋሽ በሬሳ ቤት ነው። ጥቂቱን ክፍል እኔ ጋሼ ለሰጡኝ መፅሀፉ መመራመሪያ " ነው አለቻቸው። ቤካንም "እንዴ ማማ የነገረሽን ታሪክ እውነተኛ ነው ማለት ነው " አለ። በፀሎትም "አዎ እናትህ የነገረችህ እውነተኛ ታሪክ እንጂ ተረት አልነበረም " አለችው። ቤካንም "ስለዚህ ቆነጃጂቶቹ እናንተ ናቹሁ። . https://vt.tiktok.com/ZSxTyu1YD/ የመጨረሻ ክፍል 60 አርብ 2:00 ሰአት

Открыть в Telegram
Просмотры10 000+443%к среднему
Пересылки—
Реакции39
Комментарии—
#9057Текст

    ♥️ ፅናት ♥️...!!!      .      . 🥀..ክፍል 58.. . . የፅናትን የክርስትና ጊዜ ደረሰ። ያቤፅ ፣ ፅናት እና በፀሎት በሀዘን ምክንያት የለበሱትን ጥቁር ልብስ አውልቀው ለክርስትናው የሚመጥን ልብስ ሁሉም ለብሰው ክርስትናውን ሞቅ አደረጉት ይህ ደስታ ሁሉም በልባቸው የያዙትን ቁስል አላስረሳ ብሏቸዋል። የሶስና እና የያቤፅ አያት የስራ ባልደረቦች በተሰበሰቡበት እነ ያቤፅ ቤት ነበር። ክርስትናው የተከበረው ዝግጅቱ ሊያልቅ ሲል "ቆይ ቆይ አንዴ" አለ ያቤፅ። ሁሉም ዝም ብለው ግራ በተጋባ ስሜት እያዩት ነው ሶስና ያቤፅን ጠቀሰችው ያቤፅም ፈገግ ብሎ ወደ ፅናት ሄደና ተንበረከከ ፅናት ልጅዋን አቅፋ ቆማለች። ያቤፅ ከተንበረከከበት ከወገብ ሰበር ብሎ "ፅኑ ታገቢኛለሽ" አላት። ሁሉም አጨበጨቡ ፅናት "አዎ ያቤፆ" አለችው። ድግሱ ላይ ያሉ ሁሉ እድለኛ ነው በጣም ውብ ልጅ ነች የፈጣሪ ያለ በጣም ቆንጅዬ ናት ማለት ጀመረ። ያቤፅ ቀለበቱን ፅናት እጅ ላይ አረገላት። በእዚህ መልኩ ዝግጅቱ አበቃ።  በነጋታው ፅናት ልጅዋን ይዛ ከበፀሎት ጋር ተኝታለች። ደመቁ ቤት እያፀዳች ነው። በር ተንኳኳ ደመቁ ሮጥ ሮጥ ብላ ከፈተች ያቤፅ ነበር። ደመቁ "ጉደኛው ልጅ ደና አደርክ" አለችው። ያቤፅም ፈገግ ብሎ " አቤት ደምዬዬዬዬ እንዴት አደርሽ የእኔ ልእልት እና ቆንጅየዋ በፂ ተነስተዋል ልጄስ" አላት። ደመቁም "አይ ማናቸውም አልተነሱም ግባ" አልችው። ያቤፅ ጫማውን አውልቆ በቀስታ ወደ መኝታ ቤት ገባና። "እንዴት አደራቹ ቆነጃጂቶች እና ውዱ ልጄ " አለ። በፀሎት "አንተ ቀውስ እንዴት አደረክ" አለችው። ፅናትም "ደና አደርክ ያቤፆ" አለችው። "አድሬያለሁ ደና ነኝ ከእናንተ ናፍቆት በስተቀር ልጄም ናፍቆኛል በሉ ዛሬ አንድ ቦታ ይዣቹህ እሄዳለሁ ተዘጋጁ" አለ።" የት " አሉ ሁለቱም እኩል። ያቤፅም አትቸኩሉ ሰርፕራይዝ ነው" አላቸው። ልብስ እስኪቀያይሩ ነገራቸው። ያቤፅ ከቤካን ጋር ሲጫወት ቆየ እና ቤካንንም አልብሰው ደመቁን ተሰናብተው ሄዱ። አሁን ፅናት ፣ ያቤፅ፣ ቤካን እና በፀሎት አንድ የስእል አዳራሽ ውስጥ ናቸው። ትንሽ ቁጭ ካሉ በኋላ አንድ ወጣት ልጅ መጣ። ወጣቱ ልጅ በፀሎት እና ፅናትን ገና ሲያያቸው ነበር ከሁለቱም አይኑን ሳይነቅል የቆየው። ቆይቶ ያቤፅን ከዛ ፅናትን ከዛ ደሞ በፀሎትን ጨበጣቸው እና ያቤፅን "እነዚህን ነው አደል ያልከኝ አለው። ያቤፅም "አዎ ልክ ነክ ቀመር እነዚህ ናቸው" አለ። ያቤፅ "ፅኑ በፂ ቀመር ሰአሊው ነው ሰአሊ ጓደኛዬ የባለፈውን ውድድር ሌላ ነገር ስሎ አልፏል አሁን ደሞ እናንተን ሊስላቹ ነው ፍቃዳቹ ከሆነ" አለ። ሁሉቱም "መቼ" አሉ። ቀመር ዛሬ አሁኑኑ ምትሄዱበት ከሌለ" አላቸው። ፅናት "የለም" አለች። ሰአሊውም "እንደዛ ከሆነ ኑ ወደ መሳያ ክፍል"አለና እየመራቸው ወደ ስእሉ መሳያ ወሰዳቸው። የስእል መሳያ ክፍል ውስጥ የተለያዩ  የሚያማምሩ ስእሎች እና ይህ ነው የማይባሉ ሙንጭርጭር ስእሎች አሉ። ሰአሊው ቀመር የመሳያ ቦታውን አመቻቸና "በሉ አሁን ልብስ እሰጣችኋለሁ አለና ስስ እና ነጭ ልብስ ሰጣቸው። ሁለቱም ልብሱን ሲያዩት በጣም እረዥም ነው ግን ገላ ያሳያል አናረግም ብለው ነበር። ግን ሰአሊው እና ያቤፅ እንደምንም አግባብተው አስለበሷቸው ሰአሊው ፅናት ልጅዋንም ይዛ ቢሳሉ ብሎ አሰበ ፅናት እና በፀሎት ጥሩ ሀሳብ ነው ብለው ተስማሙ። ከዛም ቀኑን በሙሉ ቆይተው ፅናትን ፣ በፀሎትን እና ቤካንን ሳላቸው። ስሏቸው ሲጨርስ እየውላቹ ውድድሩ ከነገ ወዲያ ነው። በዝግጅቱ ላይ መታደም ከፈለጋቹ ብሎ ከለበሰው ሸሚዝ ውስጥ ሶስት ትኬት ሰጣቸው። ልክ በሶስተኛው ቀን ትኬቱ ላይ በተፃፈው መሰረት ወደ አመሻሽ 12:35 ላይ ወደ ስእሉ ኢግዝቢሽን  ሄዱ። ሁሉም ሰው በይበልጥ ቀመር የሳለው ስእል ላይ ትኩረቱን አርጓል ያዩት ሰዎችም መልሰው እየመጡ ሲያዩት ነበር። ፅናት በፀሎት እና ያቤፅ ወደ ኤግዚብሽኑ ሲገቡ በጣም አምሮባቸው ነበር። ሰው አይኑን እነሱ ጋር ጣለ ከስእሉ ይልቅ በአካል በጣም ያምራሉ እያሉ ሁሉም ይንሾካሾኩ ነበር የጉብኝቱ ጊዜ አልፎ አሁን ዳኖች ውጤት የሚሰጡበት ጊዜ ደርሷል።  ይህንን ዝግጅት ለየት ያለ ዝግጅት የሚያረገው ስእሎቹ በጥቂት  ታዋቂ ሰዎቸ የሚጎበኝ እና በመጨረሻም በዳኞች ዳኝነት እና በታዋቂ ሰዎች እና ሰአሊዎች የድምፅ ብልጫ የሚካሄድ ነው። አሁን የዳኝነት ሰአቱ ደርሷል እና ፅናት ከበፀሎት እና ያቤፅ ጋር ልጇ ቤካንን አቅፋ ተቀምጣለች። ከኋላዋ አንድ እጅ ሲያርፍባት ታወቃት እና ዞር አለች። ፂሙ ፊቱን ሙልት ያረገው ፀጉሩም እስከ ግንባሩ ጥቅጥቅ ያለ ነው። ሽበት ፂሙ እና ፀጉሩ ላይ ጣል ጣል ብሎበታል። ከተቀመጠበት ተነሰቶ ወደ እነ ፅናት ሄዶ ከፅናት አጠገብ ተቀመጠ። " ሰላም እንዴት ነሽ ደራሲ መሀመድ ሳላዲን እባላለሁ" አላት ፅናት በድምፁ ነበር ያወቀችው።  ፅናት " እኔ አላምንም  በጣም ነው የማደንቅክ እኮ አንተን ለማግኘት በጣም እመኝ ነበር" አለችው። ደራሲውም " እኔም ስላገኘውሽ ደስ ብሎኛል አንቺ እና እህትሽ በጣም ቆንጆ ውቦች ናቹሁ አላህ ከአይን ያውጣቹ ድርስት ላይ ስፅፍ ብዙ ቆነጃጂት ሴቶች በምናቤ ስዬ ፅፊ አቃለሁ ግን በምናቤ የምስላቸው አንዳቸውም እናንተ ጋር አይደርሱም ስእሉ ላይ የተካተተው እሳት በችግር የተፈተናቹ እንደሆነ ያስታውቃል የምርም ይደንቃል " አላት።    ፅናት ወደ ያቤፅ ጠጋ ብላ "ስማ ለሰአሊው የነገርከው ነገር አለ እንዴ ስለ እኛ" አለችው ያቤፅ " አዎ ፅኑዬ አንቺ ታመሽ በነበረበት ወቅት ስቃይሽን መስማት ሲያቅተኝ ሁሌም ለእሱ ሄጄ ስለ እናንተ እማቀውን እነግረው ነበር። ጠንካራ ፣ ስኬታማ እና ቆንጆ ሴቶች ስለሆኑ ለመሳል በጣም ጓጉቻለሁ ብሎኝ ነበር እናም ሳላችሁ" አላት። ፅናት "እሺ ጥሩ" ብላ ወደ ደራሲው ዞር አለችና "ይቅርታ አርግልኝ እና ስእሉን ወደድከው አደል " አለችው። "አዎ በትክክል ወድጄዋለሁ የተፃፈ እና የተኖረ ነገር መፃፍ ከባድ ነው ግን ባልፃፈውም ታሪክሽን ብስማው ደስ ይለኛል።" አላት። ፅናትም "እሺ ጥሩ ታሪኩን እነግርሃለሁ " አለችው። ደራሲውም "በቃ አሁን ፕሮግራሙ ተጀመረ አለና ማየት ጀመረ። ፕሮግራሙ ጀምሮ በዳኞቹ ስእሎቹ እና ታሪካቸው መታየት ጀመረ። ሁሉም ታይተው የሰአሊ ቀመር ተራ ደረሰ። ስእሉን ገና ይዞ ሲመጣ ነበር ሁሉም ሞቅ ያለ ጭብጨባ ያረጉለት። ሰአሊውም ጥሩ አድርጎ ስለ ስእሉ አብራራ በኋላ መጨረሻ ላይ"ለምታይዋቸው ሰዎች ትልቅ አስተዋፆ አረገው ካሉበት ችግር የወጡት ለብቻቸው ሳይሆን በዳር በዳሩ ላይ ላሳያየው በሞከርኩት የተያያዙ ጠንካራ እጆች ነው። ስለ እጆቹ ማወቅ ትፈልጋላቹ ብዬ አስባለሁ" ሲል በጭብጨባ አጀብት። ሰአሊውም ንግግሩን ቀጠለ። በስእሉ ዳር ዳር ላይ በስእሉ ላይ ያሉትን ሴቶች እጅ የያዙ ይመስላል አተኩሮ ላያቸው ማለቴ ነው። እነዚህ እጆች ለእነዚህ እንስቶች ህይወት ትልቅ ቦታ ያላቸው ሰዎች ናቸው ሰማያዊ ቀለም የተተቀምኩት በአሁኑ ሰአት እነዚህ ሰዎች በህይወት ስለሌሉ ነው" አለ።                                        . https://vt.tiktok.com/ZSxTyu1YD/ ክፍል 59 ይቀጥላል ሀሙስ 2:00 ...

Открыть в Telegram
Просмотры8 000+335%к среднему
Пересылки—
Реакции45
Комментарии—
#9056Текст

    ♥️ ፅናት ♥️...!!!      .      . 🥀..ክፍል 57..🥀 . . ዶክተር ከተቀመጠበት ብድግ ብሎ "ቶሎ በሉ በፍጥነት በሩን ክፈቱት" አለ። በፀሎት በፍጥነት ቁልፉን ከ ኪስዋ አውጥታ እየተርበተበተች ከፈተችውና በሩን ብርግድ አርጋ ገባች። ፅናት የምትለብሰውን አልጋ ልብስ ደልድላ ልጅዋን እዛ ላይ አሳርፋዋለች። እና በጣም ተዝለፍልፋለች። ዶክተር ዳመነም በሉ በፍጥነት ለብ ያለ ውሀ ፎጣ እና መቀስ አምጡልኝ መቀሱ ባለፈው ያመጣውት ይሁን አለ። ያላቸውን ሁሉ ያቤፅ እና በፀሎት ተጋግዘው እየተጣደፉ አመጡለት። ዶክተሩም የምግብ መገናኛው እትብቱን ቆርጦ በፎጣ እና ለብ ባለ ውሀ ፅናትን እና ህፃኑን አፀዳዳቸው። ያቤፅ ተደሰተ "ፅኑ ልጅ ወለድሽልኝ ፅኑ ልጅ ሰጠሽኝ" አለ። በፀሎትም "እኔም አክስት ሆኛለሁ" ብላ ፅናትን ሳመቻት። ዶክተር ዳመነም "የወንድ ልጅ እናት ሆነሻል" አላት። ፅናትም "አዎ ልክ ናቹሁ ልጄ ሴት ከሆነች ሊባኖስ ልላት ነበር ግን ደሞ ዶክተሩ ገና እርጉዝ ነሽ ሲለኝ ልጄን ወንድ ከሆነ ቤካን ልለው ነው ያሰብኩት።" አለች። በፀሎትም " ትርጉም አለው ማለቴ ከእራስሽ ጋር የሚገናኝ?" ስትላት። ፅናት "አዎ እህቴ ቤካን ማለት ድብቅ ፍቅር ማለት ነው። ያው በእኔ እና በያቤፅ ድብቅ ፍቅር ውስጥ የተፀነሰ ተፀንሶም የተወለደ ልጅ ነው። ለእዚህ ነው እህቴ" አለቻት። በፀሎት ተገርማ " ከድሮም ብልህ ልጅ ነሽ" አለቻት። ያቤፅም ፅኑዬ " ታገቢኛለሽ አደል" አላት። በፀሎትም " እንዴ እና እንዴት አታገባክም የልጅዋ አባት አደለክ እንዴ" አለችው። ፅናትም " ልክ ነው አይደል ልጄ እእእ" አለች። ልጅዋን በስስት እያየችው። ዶክተር ዳመነ በመገረም ውስጥ ሆኖ በህይወቴ አንዴም ልክ እንደ እናንተ አይነት ሰው አይቼ አላቅም" አለ። ያቤፅም " ልክ ነው ፅኑዬ እስቲ ልጄን ልቀፈው" አለና ወደ ፅናት ተጠጋ። ፅናትም ቀስ አርጋ ሰጠችው። ያቤፅ ልጁን ሲያቅፈው ልብ ውስጥ ሀይል እና ፍቅር ተደምሮ ተሰማው ልጁን እያየው "ቤካን የእኔ ልጅ እንኳን ደህና መጣህ ተመልከት አባትህ እጅ ውስጥ ነህ ሁሌም ቢሆን ባገኘውት አጋጣሚ አንተን ከማቀፍ የሚያግደኝ ነገር አይኖርም በትልቅ ችግር ውስጥ ብሆንም እኔ ያጣሁትን የአባት ፍቅር አላሳጣህም" አለና ከአይኑ ያቀረረው እንባ አርግፎ የህፅኑ ፊት ላይ አረፈ። ህፅኑ ቤካን አለቀሰ ያቤፅም "ውይይ አታልቅስ አታልቅስ አሁኑኑ ለእናትህ እሰጥሀለው" ብሎ ሰጣት። ፅናት እያለቀሰች "ሊቦዬ ጥላን ሄደች አደል" አለች። በፀሎትም "አዎ እህቴ ግን ሊቦቲዬ እንድናዝን አትፈልግም" አለቻት። ያቤፅም "ልክ ነው ህይወትን እምንኖራት አምላክ በቃቹ እስኪለን ድረሰ ነው" አለ። ፅናት ዛሬ ሁለት ነገርን በድል ተወታለች። ሁሉም ሰው በሰአታት ልዩነት ስለ ፅናት ደህንነት ለማወቅ ሲመጡ ነው የምስራቹን ያወቁት የያቤፅ ቤተሰቦች  ፣  ጋሽ በሬሳ እና ማርቆስ ፅናት ጋሽ በሬሳን እና ማርቆስን ስታያቸው ሊባኖስን ይበልጥ አስታውሳ እሪሪ አለች። ያቤፅ አቅፎ አፅናናት።  ጩኸት እና ጭንቀት ቤት ውስጥ የለም። ያለው የሚያለቅስ የህፃን ልጅ ድምፅ ነው። ምንም አይነት የሚሰቃይ የሚንጫጫ ሰው ቤት ውስጥ  የለም። ፅናት በወለደች በነጋታው ሊባኖስ መቃብር ጋር ካልወሰዳችሁኝ አለች። በፀሎት ፣ ያቤፅ እና ሊሎች እንደማይሆን እና መጠንከር እንዳለባት ቢነግሯትም ልሰማ አልቻለችም። ጭራሽ ልጄንም ይዤ ነው ምሄደው አለች። ሊያስቆሟት አልቻሉም ስለዚህ ያቤፅ ከሹፌሩ ማርቆስ ያቤፅ እና ከበፀሎት ጋር ሄዱ። ፅናት ሊባኖስ መቃብር ጋር ሄዳ እሪ አለች። አለቀሰች። አፈሩን በእጅዋ እየዛቀች እላይዋ ላይ ነሰነሰችው ግን ሊወጣላት አልቻለም። ፅናት ብዙ ደቂቆች ሊባኖስ መቃብር ጋር ሄዳ ስታለቅስ ቆየች። የማርቆስ ስልክ ጠራ አነሳው ደነገጠ "ምንድነው?" አለ ያቤፅ ማርቆስም  ስልኩን ላውድ እስፒከር ላይ አረገው። የጋሽ በሬሳ የቤት ሰራተኛ ነበረች። " "ፍቅርተ ነኝ ጋሼ በሬሳ ወድቀዋል አቅምም የላቸውም ኧረ ድረስላቸው ምንም ሰው የለም።" አለች። ሁሉም በፍጥነት ለመድረስ ተደናግጠው ሄዱ በፀሎት እና ያቤፅ ፅናትን ደግፈዋት መኪና ውስጥ ገብተው ማርቆስ በፍጥነት እየነዳ ወደ ጋሽ በሬሳ ከንፈው ደረሱ። ሲደርሱ ጋሽ በሬሳ በእዛ ያማረ እና የተንጣለለ ሳሎን ላይ ተዘርረዋል። ፍቅርተም ውሀ በፎጣ ጭንቅላታቸው ላይ እያረገችላቸው ነው።  ማርቆስ ፈጠን ብሎ ለማንሳት ሞከረ አልከበዱትም ፍራሽ መሳይ ሶፍ ላይ ጋደም አረጋቸው። እያጣጣሩ  የሊባኖስ ሚጢጢ ነይ እስቲ ወደዚህ" አሉዋት። ፅናት በፍጥነት ወደ ጋሽ በሬሳ ተጠግታ ቁጢጥ ብላ ተቀመጠች። ጋሽ በሬሳም የፅናትን እጅ  እንድትሰጣቸው እጃቸውን ዘረጉ ፅናትም እጇን ሰጠቻቸው። " ልጅ ፅናት የልጅ ሊባኖስ ሚጢጢ" አሉዋት። ፅናት " አቤት ጋሼ" አለቻቸው። እሳቸውም " እኔ ወደ ልጅ ሊባኖስ እየቀረብኩ እንደውም እየሄዱኩኝ ነው እና ልጄ ለሊባኖስ መልክት አለሽ" አሉዋት። ፅናት ደነገጠች እና "ማለት ቆይ ይሄ ምን ማለት ነው እርሶም ጥለውን ሊሄዱ ነው" አለቻቸው። በፀሎትም " ይህ ሊሆን አይችልም" አለች። ጋሽ በሬሳም "ለምን አይሆንም እንኳን እኔ እድሜን ጠግቤ አንድ ፍሬዋ ልጅ ሊባኖስ እንኳን የህይወትን ሙሉ ክፍል ሳታይ ልጅ የልጅ ልጅ ሳታይ ሞታ የለ። ልጄ እኔ እኮ ህይወት ልትሰጥ እምችለውን ሁሉ ሰጣኝ ተቀብዬ ኖሬዋለው መልሳ ነጥቃኝ ነው እንጂ መልሳም ሰጥታኝ ግን ሳላጣጥመው" አሉ እና ዝም አሉ። ሊላኛውን እጃቸውን ለበፀሎት እየዘረጉ። በፀሎትም " አይዞት አይሞቱም" ብላ እጃቸውን ያዘቻቸው። ጋሽ  በሬሳም "ልጄ ሰው በቁሙ ሲሞት ነው መጥፎ" አሉ። ማውራት አቅቷቸው ተዳከሙ። ፅናት እና በፀሎት የሊባኖስን የመጨረሻ ቀን የመጨረሻ ሰአት አስታወሱ። ጋሽ በሬሳም "ፅናት ስሚኝ ለልደትሽ  የሰጠውሽን መፅሀፍ በደብ አንብቢው  የመኝታ ቤቴ መሳቢያ አለ እሱ ውስጥ ሙሉ የንብረቴ ወራሽ አርጊሻለው ቤቴን አፍርሰሽ ለሰው የሚሆን ነገር ለሰው የሚጠቅም ነገር ስሪበት አስፈላጊ ከሆነ እዚህ ያሉትን አስክሬኖች ማርቆስ መላ ይላቸዋል" አሉ። ለልጄ ማርቆስም ከከተማ ውጪ ያለውን ቤት አውርሼዋለሁ  ማውራት ደከማቸውና አ አ አአአአ ብለው አይናቸውን እንደከደኑ ቀሩ። ፅናት "አይሆንምምም" ብላ ጮከች። "እርሶም ጨከኑ" አለች። መልስ የለም ሁሉም አለቀሱ አዘኑ መጮህ እና ማዘናቸው ግን የሚወዷቸውን ጋሽ በሬሳ እና የህይወት አስተማሪያቸውን ሊባኖስን አልመለሰላቸውም። አለቀሱ ተጯጯሁ የጋሽ በሬን ቀብርም ፈፀሙት።የተቀበሩት ከሊባኖስ ጎን ነበር። ሀዘን ተፈራርቆባቸዋል። ግን ደሞ ጠንካራ መሆን አለባቸው። ፅናት በአራስነቷ ጊዜ ሁሉም ተረባርበው ነው ያረሷት። ደመቁ ለማንም ሳታወራ ጠፈታ ነበር። ግን ፅናት በወለደች በሳምንቷ  ከየት መጣች ሳትባል ነው የመጣችው ። የሊባኖስን እና የጋሽ በሬሳን መሞት ስትሰማ በተለይ ደሞ በደንብ ለምታቃት ሊባኖስ ተንሰቅስቃ ነው ያለቀሰችው። ከዛ በኋላ ከበፀሎት ጋር ተጋግዘው አረስዋት ያቤፅ ከፅናት ጎን ጠፍቶ አያውቅም ሶስና እና የያቤፅ አያት ለፅናት በግ አረዱላት ሁሉም ማታ ላይ እነ ፅናት ቤት ተሰብስበው ያሳልፉታል ፅናት በእንክብካቤ ታርሳ አራስነቷን ጨረሰች።              .        https://vt.tiktok.com/ZSxTyu1YD/ ይቀጥላል 58 ረቡዕ 2:00

Открыть в Telegram
Просмотры9 240+402%к среднему
Пересылки—
Реакции32
Комментарии—