ዘንድሮ አዲስ ከተዋወቅናቸው በሽታዎች አንዱ: ፎቷችንን በAi እና በፊልተር ኤዲት አድርገን ፖስት ካደረግን በኋላ ሰዎች እንዴት እንደምናምር ወይ እንደማናምር ሲነግሩን ደስ የሚለን ወይ የሚከፋን ነገር🫣 አላህ ዓፊያ ያድርገን🤲 @ychanut
Открыть в TelegramПосты канала 🌷ለማስታወስ ብቻ !!🌹
ንስር እሱ ያረፈበት የከፍታ ቦታ ላይ ቁራ ያረፈ እንደሆነ ቦታዉን ለቆ ይሄዳል ይባላል። ምክንያቱም ቁራ ካረፈበት ያ ከፍታ ትልቅ ከፍታ ነው ብሎ ስለማያስብ። አንዳንድ ጊዜ ሰው ሁሉ ከሚሠራው ነገር ከፍ በልና የተለየ ሥራ ሥራ። @ychanut
Открыть в Telegramድህነት ብቻ ይመስለኝ ነበር ፈተና። ለካ ሀብትም ትልቅ ፈተና ነው። ለአንዳንዱ መመለሻ… ለአንዳንዱ መጥፊያ ነው። ዱንያ ሲመጣ በጣም የሚያፈሉና ባህሪያቸው የሚለዋወጥ፣ መስጂድ መጥቶ መስገድ የሚያስጠላቸውን ሰዎች ሳይ ግርም ብሎኝ ነው። አላህ ያስተካክለን። @ychanut
Открыть в Telegramበዛሬው ዕለት ወንድማችን ሳሂባችን ሀሰን አብደላህ ኢስላም እና ፌሚኒዝም የተሰኘ ቆንጆ መፅሀፍ አስመርቋል ። መፅሀፉ ፌሚኒዝምን እንደ ርዕዩተ-ዓለም እና ንቅናቄ ያለውን አደጋ በሰፊው በመግለፅ ኢስላም እንደ ዲን የሴት ልጅን መብት አስመልክቶ ያስቀመጣቸውን እና ዘመን የማይሽራቸውን ሁቁቆች ያብራራል ። ስለ femininity ፣ Masculinity እና patriarchy በሰፊው ያነሳል ። መጨረሻ አካባቢም ስለወንድና ሴት ትርጓሜ ፣ ስለሴቶች ጥቃትና በደል ፣ ኢስላም ለለከፋና ለሴት ልጅ ደፈራ ያስቀመጣቸው ተግባራዊ መፍትሔዎች ያነሳል ። ብታነቡት ምታተርፉበት ቆንጆ መፅሀፍ ነው ።
Открыть в Telegramከተዘነጉ የረሱል ﷺ አስተምህሮቶች ጎልቶ እየታዩ ካሉት ውስጥ :- 【በአላህና መጨረሻው ቀን የሚያምን መልካምን ይናገር ወይም ዝም ይበል】የሚለው አንዱ ነው። @ychanut
Открыть в Telegramዝምታህንም ሆነ ንግግርህን የሚመረምሩ ለማስደንገጥ፣ ለማስጨነቅ፣ እረፍት ለመንሳት የተፈጠሩ ብቻ የተፈጠሩ የሚመስሉ ፍጡራን አሉ። ሲወዱና ሲያፈቅሩ ራሱ ካልተጨቃጨቁና ነገር ካልጠመዘዙ፣ አቧራ ካላስነሱ የወደዱ አይመስላቸዉም። ሰላምና እርጋታን ትፈልግ እንደሆነ ባንተና በነርሱ መሃል ትልቅ የግንብ አጥር፣ ሰፊ ባህር አድርግ። እንዳይደርሱብህ። በይሉኝታ ታስረህ አይደለም ዘመናትን አንድ ቀን አትኑር። ሕይወት ለባሮች እውቅና የላትምና ነፃነትህን አስከብር። ከዉስጣዊ ሰላም በላይ ምን ዉድ ነገር አለ። @ychanut
Открыть в Telegramእውነተኞች የሆኑ ጓደኞችን ፈልጋችሁ ያዙ። እነርሱ በሰላም ጊዜ ጌጥ በችግር ጊዜ አለኝታ ናቸው። ዑመር ኢብን አል ኸጧብ {ረ.ዐ} @ychanut
Открыть в Telegramያለ ምንም ምክኒያት ከትዳር የሚዘገይን ሰው ዶክተር እንዲያየው እንመክራለን 😌🤝 . . . . . . . . . . . ከማ ቃለ አህሉል ዒልም😋😌 @ychanut
Открыть в Telegramአንድ አሊም ስለ አንድ ሰው እንዲህ ተብለው ተጠየቁ ፦ ይህ ሰው ሌሊት ቆሞ ሲሰግድ ያነጋል ቀን ደግሞ ሰዎችን ሲሳደብ ይውላል ስለዚህ ሰው ምን ይላሉ ? ተባሉ። እሳቸውም እንዲህ ሲሉ መልስ ሰጡ ፦ (ይህ አላህ ለሰዎች እንዲሰራ (እንዲለፋ) ያገራው ሰው ነው ፤ ሌሊት ላይ የሰበሰበውን አጅር ቀን ለሰዎች ሲያከፋፍል ይውላል።) አላህ ይጠብቀን። @ychanut
Открыть в Telegramከምታውቃቸውም ሆነ ከምትዛመዳቸው ሁሉ አብዝቶ የሚወድህ ሰው ማለት ፣ በሌለህበት አስታውሶ ዱዓ የሚያደርግልህ ነው። በልቡ ጥቂት ጥላቻ(ምቀኝነት)ቢኖረው ይሄንን አያደርግምና ፣ እንደነዚህ ያሉትን ያብዛልን። @ychanut
Открыть в Telegramማስታወቂያ ❗️ጤና መግዛት የሚፈልግ ሰው ነበር። ጤናችሁን መሸጥ የምትፈልጉ ከምትሸጡበት ዋጋ ጋር ኮመንት ላይ አስቀምጡ። የሚገዛው ሰው የጠየቃችሁትን ለመክፈል ዝግጁ ነው። ብቻ እናንተ ሙሉ ጤናችሁን ለመሸጥ ፈቃዳችሁን ግለጹ። ዳይ ወደ ኮመንት🤔 ሆስፒታል ላይ ተሆኖ የተፃፈ @ychanut
Открыть в Telegramህይወት ማለት ህመም የሌለበት ጉዞ ሳይሆን፣ በህመም ውስጥም ተስፋን ሰንቆ መጓዝ ነው። እንባ ቢኖርም ፈገግ ማለት፣ ስንወድቅም ዳግም ለመነሳት መዘጋጀት ነው።🌹 @ychanut
Открыть в Telegramልጆቻችን ላይ የመደበኛ ትምህርት ጫና ሲበዛባቸው፣ መጀመሪያ «ጊዜ አይበቃም» በሚል ሰበብ መስዋዕት የምናደርገው አላህ ዘንድም ሆነ ለአስተዳደጋቸው ትልቅ ዋጋ ያለውን የቁርኣን ትምህርታቸውን ነው! እንደ እውነቱ ከሆነ ይኸው «ጊዜ የለም» የሚለው ሰበብ ቁርኣን ላይ ብቻ አይቆምም። የሕይወታችንን ትክክለኛ ሚዛን እና የልጆቻችንን ሰብዕና የሚገነቡ በርካታ ውድ እሴቶችን በዚህ መልኩ እያጣናቸው ይገኛል። በተጠቀሰው ምክንያት ልጆቻችንን ከደም ስራቸው ጋር የተሳሰረውን ማኀበራዊ መሠረት ትተው፣ ከስክሪን እና ከደብተር ጋር ብቻ የተጣበቁ ብቸኞች እንዲሆኑ እናደርጋቸዋለን። የልጅነት አእምሮ በነጻነት የሚያስብበት፣ ከቤት ውጪ ወጥቶ ከተፈጥሮ ጋር የሚጫወትበት እና እውነተኛ ማኀበራዊ ክህሎቶችን የሚያዳብርበት ጊዜ በጥናትና በቱቶሪያል ተተክቷል። ይህም ለስሜታዊ ብስለት እና ለስነ-ልቦና ጥንካሬ አስፈላጊ የሆነውን ነጻነት ይነጥቃቸዋል። አካዳሚክ ውጤት ላይ ብቻ ትኩረት በማድረግ፣ የልጆቻችንን ሥነ-ምግባር፣ ኃላፊነት የመውሰድ ልምድ እና ርኅራኄን የምናስተምርበትን ረጋ ያለ የቤተሰብ ድርሻ ይመናመናል። ልጅን ያለእረፍት ከትምህርት ቤት ወደ ቱቶሪያል፣ ከቱቶሪያል ወደ የቤት ሥራ ማስኬድ፣ የልጁን ተፈጥሯዊ የመማር ፍላጎት ከመግደሉ ባለፈ አእምሮው እፎይታ አግኝቶ ነገሮችን የሚያሰላስልበትን እድል ያጠብበታል። ትልቁ ስህተታችን ቁርኣንን እና መንፈሳዊ እሴቶችን እንደ “ተጨማሪ ሥራ” አድርገን መመልከታችን ነው። እንደ እውነቱ ከሆነ ግን ቁርኣን የአእምሮን ትኩረት፣ ትዕግስትን እና የጊዜ በረካን የሚጨምር ዋና መሠረት እንጂ ጊዜን የሚሻማ ሸክም አይደለም። የቁርኣንን እና የማኀበራዊ እሴቶችን ቦታ በጊዜ እጥረት ሰበብ ስንቀማቸው፣ ውጤታማ ነገር ግን መንፈሱና ማኀበራዊ እሴቱ የጎደለው ትውልድ የመቅረጽ አደጋ ውስጥ እንወድቃለን። ስለዚህ መደበኛ ትምህርትን እና መንፈሳዊ እድገትን ሳናጋጭ፣ ሁለቱንም በጥበብ አስተካክሎ መምራት የዛሬው ወላጅ ትልቁ የስኬት ሚዛን ሊሆን ይገባል። አላህ ያግዘን! @ychanut
Открыть в Telegramሸይጧን እውነትም ሸይጧን ነው ወይ ባለፈው ነገር በሀዘን እንድትዋጥ ያደርግሃል አሊያም መጪው ጊዜ አስከፊ ነው እያለ በስጋት እንድትኖር ያደርግሃል፣ ወዳጄ ሆይ ! በአላህ ላይ ያለህን መተማመን ብርቱ አድርግ። @ychanut
Открыть в Telegramዘመን በመቀየሩ የሚመጣልህ አንዳች ተዓምር የለም ጥንቱኑ ሙደቢሩ የጻፈልህ ቢሆን እንዢ! ጀምበሯ ራሷ ናት፣ በቅሎ እስካሁን አልወለደችም፣ ሰማይም ብር ማዝነብ አልጀመረችም፣ ይልቅየ ነቃ በልና ታገል ጓድ!👌 @ychanut
Открыть в Telegram