Посты канала ጌታዬ ሁለመናዬ!
" እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ #እንደ_ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፥ #አይታክቱም፤ #ይሄዳሉ፥ አይደክሙም።" ❤️🔥 (ኢሳ 40: 31)❤️🔥
Открыть в Telegram❤️🔥 Keep The Faith ❤️🔥 In Christ, you are held by a love stronger than every circumstance! ❣️ #Jesus_my_Everything❣️ https://t.me/YariedDessale
Открыть в TelegramThe Rosary is an opportunity to say THANK YOU JESUS‼ It is a way to say Thank you Jesus and Mary. (Mother Angelica ) የተመረጠው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳን ቀን አሁን ነው።" 2ቀሮ 6፡ 2 “አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፡፡” ማቴ. 6:33 ቤተሰብ ይሁኑን 👇👇👇 https://t.me/YariedDessale/7146 👆👆👆 The Universal Catholic Church Teaching Channel.
Открыть в Telegram“በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል።” —❤️🔥 መዝሙር 23፥4❤️🔥
Открыть в Telegramመስቀሉን ቅዱስ መስቀል የምንለውና ልዩ የሚያደርገው ነገር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስላረፈበት እንዲሁም በመስቀል በስቅላቱ ስለአዳነን ልዩ ያደርገዋል። ‹‹እኔ ግን ለእኔ ከሞተበት እኔም ለዓለም ከሞትሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ የምመካበት ነገር የለኝም፡፡ › ❤️🔥ገላ 6፡14❤️🔥 https://t.me/YariedDessale
Открыть в Telegram❤️🔥"ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል።" ❤️🔥 — (፩ ቆሮንቶስ 10:13)
Открыть в Telegram"በጨነቀኝ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፥ ወደ አምላኬም ጮኽሁ፤ ከመቅደሱም ቃሌን ሰማኝ፥ ጩኸቴም በፊቱ ወደ ጆሮው ገባ።" — ❤️🔥መዝሙረ ዳዊት 18:6❤️🔥
Открыть в Telegram“ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም፤ ባርያ ጌታው የሚያደርገውን አያውቅምና፤ ወዳጆች ግን ብያችኋለሁ፥ ከአባቴ የሰማሁትን ሁሉ ለእናንተ አስታውቄአችኋለሁና።” —❤️🔥 ዮሐንስ 15፥15❤️🔥
Открыть в Telegram"⁷ በውድ ልጁም፥ እንደ ጸጋው ባለ ጠግነት መጠን፥ በደሙ የተደረገ ቤዛነታችንን አገኘን እርሱም የበደላችን ስርየት። ⁸ ጸጋውንም በጥበብና በአእምሮ ሁሉ አበዛልን።" ❤️🔥ኤፌሶን 1❤️🔥 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
Открыть в Telegram“ዕረፉ፥ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ እወቁ፤ በአሕዛብ ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፥ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ።” — ❤️🔥መዝሙር 46፥10❤️🔥
Открыть в Telegramድንግል ማርያም ሀይለ አርያማዊት ናት ወይ? ( አዘጋጅ: ዲያቆን ራዕይ ሳሙኤል) ይሔ ጥያቄ ከሕጻንነቴ ያደከመኝ ጥያቄ ነው ሞኝ የተከለው እንዲሉ ብዙ ተደጋግሞ ይሰማል ያለምንም በቂ ጥናት ጭፍን ነገር ይዞ አንዴ በታተመ መናፍቃንና ማንነታቸው የምትል መጽሐፍ ምክንያት እስኪሰለቸን ተጠይቀናል እንዳው እንዲት ወዳጄ ይሔንን እስኪሰለችህ ሳትጠየቅ ካቶሊክ መሆንህ አይረጋገጥም ብላ ቀልዳ አስቃኝ ነበር። 1) ድንግል ማርያም ከአዳም ኃጢአት ነጻ ነች ማለት ሰው አይደለችም ማለት አይደለም ኢየሱስ ምንም አይነት ኃጢአት የለበትም ሰው ነው አዳምና ሔዋንም ከውድቀት በፊት ሰው ነበሩ ስለዚህ ይሔንን ጠቅሶ ማንም ሰው አይደለችም እንደምንል አድርጎ ሊያሳይ አይችልም። ምክንያታዊም አይደለም ኢየሱስን ሰው እያሉ እሷ ሰው አይደለችም ብንል ስጋውን ከማን ነሳው ልንል ነው ይሔ የአላዋቂ ክስ ነው። 2) በዛሬው እለት በላቲን ስርዓት የሚከበረው የቅድስት ሐና እና የቅዱስ ኢያቄም የእናትና የአባቷ በዓል ነው ከሰው የተወለደ መቼስ ሰው ነው እና ሰው አይደለችም ትላለችሁ እያሉን ይሔን በዓል የምናከብር መሆናችን የተለየ አለም ከሳሾች መሆናቸው ማሳያ ነው። አከባበራቸው ከምስራቁ ወደ ምዕራቡ የተስፋፋ ሲሆን ቢያንስ ቢያንስ በርግጠኝነት እስከ መካከለኛው ዘመን ድረስ በምዕራቡ አለም አከባበራቸው ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ነበር ለዚህም ከጊዜ በኋላ የመጣ ነው ብሎ ማንም ሊከስ አይችልም ማለት ነው። 3) ቤተክርስቲያን ያለ አዳም ኃጢአት መጸነሷን እና የኃጢአት ዝንባሌ እና ኃጢአት እንደሌለባት ብታስተምርም ይሔ ሰው ከመሆኗ የሚለያት ነገር ነው ማለት አይደለም ሰብአዊ ስሜቶች እድገት ሰብአዊ ውስንነት ነጻነት እና ነጻፍቃዷ ሰብአዊ በሐሪ እንደመያዟ ነው ሙሉ በሙሉ የተጠበቀና ያልተነካ። በጸጋ የሆነላት ነገር ደግሞ ከእግዚአብሔር እንጂ ከራሷ አይደለም። ደግሞም እርሷ ራሷ መድኃኒቴ ብላ እንደጠራችው በልጇ የዳነች የተቤዣት ነች ነገር ግን ከሁሉ ላቅ ባለ መንገድ ለመስቀሉ ቅድመ እይት አስቀድሞ በጸጋ ሞልቷታልና። እንዲሁም ሰው ካልሆነች የአምላክ እናት ተብላ በሰብአዊነት አምላክን ወለደች የሚል ዶግማ ልንይዝ ስለማንችል ይሔ ክስ በኛ ላይ ሊቀርብ ቀርቶ ሊታሰብ አይገባም። 4) ቤተክርስቲያን የማርያምን እናትና አባት ከቀኖናዊ ባልሆኑ ጽሁፎች ስማቸውን የወሰደች ሲሆን ኢያቄም ማለት ያሕዌ ያዘጋጃል ማለት ሲሆን እንዲሁም ሐና ማለት ደግሞ ጸጋ ማለት ነው በዕብራይስጥ።ኢያቄም በቋንቋው ውስጥ ትርጉሙ ከኤሊ እና ከኤሊያቄም ጋር እንደሚተሳሰር እና በተለዋዋጭነት ጥቅም ላይ ውሏል በማለት የሉቃስ ወንጌል የዘር አቆጣጠር ላይ ኢያቄም ነው የተጠቀሰው የሚሉም አሉ በትውፊት። በዓላቸውም በላቲኑ ስርዓተ አምልኮ በዛሬው እለት በሊጡርጊያ የሚታሰብ ነው።እናት እና አባት ያለው መልአክ ወይ ከሰማይ የመጣ የለም ኢየሱስም ቢሆን ከእርሷ ስለተወለደ ነው ሰው የተባለው ስለዚህ ይሕ ክስ ልክ አይደለም። 5) ከመጽሐፍ ቅዱስ ጀምሮ ኢየሱስ ሰው መሆኑን የሚያስረዱ ጥቅሶች እንዲሁም የቤተክርስቲያን አባቶች እንደ ኢራንዮስ ኤፍሬም ዮሐንስ አፈወርቅ ዮስጢኖስ ሰማዕቱ ድንግል ማርያምን አዲሲቷ ሔዋን የሔዋን ተሀድሶ ብለው ማለታቸው ከክሱ በተቃራኒው የተከበረ እና የሚጠበቅ ትውፊት ነው። ከአባቶች ደግሞ በልዩነት ጎርጎርዮስ ዘኒሳ ጀርማኑስ ዘቁስጥንጥንያ ፉልበርት ዘቻርተርስ ወዘተ እናትና አባቷን በስም በመጥቀስ የጻፉ አባቶች ናቸው እንዲሁም ነገረ ክርስቶስንና ነገረ ማርያምን የዳሰሱ እንዲሁም የጉባኤያት ውሳኔ እና የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አስተምሕሮ የሆኑ ጽሁፎች እስከ ዘመናችን ድረስ አሉ። በተለይም ከ13ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በዚህ በዓል ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቶቻችንን ጨምሮ በየደብሩ የተሰበኩ ማስረጃወች ጽሁፎችና መልዕክቶች አሉ በተለይም በጣልያን የዛሬው በዓል ትልቅ በአል ተደርጎ ይከበራል በጀርመን ጥንታዊ የመዓድን አውጪወች ባልደረባ ተደርጋ ስለምትወሰድ በትልቁ ቅድስት ሀና በዚሁ እለት ትከበራለች። (ከሳጥኑ ውጪ ከማዕድን አውጪነት ወደ ገበሬነት ከተለወጠ ቤተሰብ የተወለደው ሉተር የመነኮሰው ለቅድስት ሐና ከመብረቅ አደጋ ለመትረፍ ተስሎ እንደነበር ልብ ይሏል)። 6) በጣም የሚያስጠላው ከሳሾቻችን ማስረጃ ሲጠየቁ (ሁሉንም አይደለም) ካቶሊክ ቤ/ያን ራሷን በጊዜ እያሻሻለች ስለመጣች ማስረጃ ስላጠፋች ማግኘት አይቻልም ይሉናል። አንተ አጊኝተኸው እኛ ሳናውቀው ከሚል ድፍረታቸውን ከሚመጥን ቀልድ በቀር ለዚህ መልስ ያስፈልገዋል ብዬ አላስብም። ማስረጃ እና የማረጋገጥ ግዴታ ሲጠየቅ እኮ ማቅረብ አለበት ጋፍኛ ሁለተኛ ክስ ከመክሰስ። ይቅርታ እኮ ያባት ነው አላውቅም ማለትስ ማንን ገድሏል። 7) የልደታ ለማርያም በዓላት በላቲን ጷግሜ 3 በምስራቅ ስርዓት በግንቦት 1 መከበሩ ሰው መሆኗን ያሳያል። 8) በሰለጠነ ዘመን ሰው ጥቂት ፈልጎ ብዙ በሚያገኝበት ዘመንም ያልቆመ ክስ መሆኑ አሳዛኝ ነው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች እና አልፎም መምሕራን ዘንድ ልዩነት ሲባል የሚጠራ ቁጥር አንድ ሐሳብ መሆኑ በዘንድሮ አመት የታተመ መጽሐፍ እንኳን (የኢትዮጵያ የሐይማኖት ተቋማትን የመዝሙር አስተዋጽኦ የሚቃኝ መጽሐፍ) ሐሳቡን ይዞ መገኘቱ እስከዛሬ የቀጠለ ክስ መሆኑን ያሳያል ይሔ ደግሞ እንኳን ላለን ግንኙነት ለእነሱ ለራሱ ውሸት ልክ ባለመሆኑ ሊታረም እና ሊያስታውሉት ይገባል። ድንግል ማርያም ሀይለ አርያማዊት ናት አንልም። ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና ለምኑልን። የበለጠ ማወቅ ለሚፈልግ፦ Catholic Encyclopedia Immaculate Conception /The Encyclopedia Press CCC 491 Fulgens Corona/ Pope Pius XII Ineffabilis Deus/ Pope Pius IX General Audience of 12 June 1996/ Pope John Paul II Catholic Encyclopedia St. Joachim/ The Encyclopedia Press The Gospel of the Nativity of Mary Chapter1/ Unknown author CCC 487 To the 3rd Public Session of the Pontifical Academies (November 7, 1998) 3/ Pope John Paul II Encyclopedic Dictionary of the Christian East Theotokology / Edward G. Farrugia Catholic Encyclopedia St. Joachim / The Encyclopedia Press Catholic Encyclopedia St. Anne / The Encyclopedia Press Catholic Encyclopedia The Blessed Virgin Mary / The Encyclopedia Press Catholic Encyclopedia Apocrypha / The Encyclopedia Press The Gospel of the Nativity of Mary Chapter 1 / Unknown author An Exposition of the Orthodox Faith Chapter 14 / John of Damascus Contra Faustum Book 23. 9 / Augustine of Hippo Catholic Encyclopedia Immaculate Conception / The Encyclopedia Press “አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፡፡”ማቴ. 6:33 ቤተሰብ ይሁኑን 👇 https://t.me/YariedDessale/7136
Открыть в Telegram🌱🔥🌱🌱🔥🌱🌱🔥🌱 →→ ካቶሊክ እና ካቶሊካዊነት →→ ካቶሊክ ማለት ምን ማለት ነው? 🌴በክቡር አባ ምስራቅ ጥዩ (ዶ/ር)🌴 🌱🔥🌱🌱🔥🌱🌱🔥🌱 ❤️🔥 ካቶሊክ የሚለው ቃል የተገኘው ካቶሊኮስ (Catholicos) ወይም ካቶሊኪስሞስ (Catholikismos) ከሚሉት የግሪክ ቃላት ነው፡፡ ትርጓሜውም ሁሉንም የሚያካትት፣ ሁሉንም ግንዛቤ ውስጥ የሚያስገባና የሁሉም የሆነ ማለት ነው፡፡ ወይም ሁሉንም የሚያካትት ማኅበረሰብ እንደማለት ነው፡፡ በእንግሊዝኛው Universal or according to the whole በሚል መልክ ይተረጐማል፡፡ 🌱→→ ካቶሊክ የሚለው ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀመው ማን ነው? ካቶሊክ የሚለው ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀመው የአንጾኪያው ቅዱስ ኢግናጢዮስ ነው፡፡ ካቶሊክ የሚለው ቃል የተጠቀመውም በ107 ዓ.ም. ስሚርና (በዛሪዪቱ ቱርክ) ውስጥ ለምትገኘው ቤተ ክርስቲያን በጻፈው መልእክቱ ውስጥ ነው፡፡ ቅዱስ ኢግናጢዮስ በዚህ መልእክቱ ክርስቲያኖች ከጳጳሳቸው ጋር ምን ዓይነት ግንኙነትና ወዳጅነት ሊኖራቸው እንደሚገባቸው ይመክራል፡፡ ሲመክራቸውም “ኢየሱስ ክርስቶስ በሚገኝበት ቦታ ሁሉ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ትገኛለች፤ እንደዚሁም ጳጳስ በሚገኝበት ቦታ ሁሉ ሕዝቡ መገኘት አለበት” ብሎአል፡፡ ቅዱስ ኢግናጢዮስ “ኢየሱስ ክርስቶስ ባለበት ስፍራ ሁሉ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን አለች” ማለቱ “ኢየሱስ ክርስቶስ የሁሉም ነው፤ በቦታ፣ በዘር፣ በጎሳ፣ በቋንቋ፣ በሕዝብ የተወሰነ አይደለም፤ ሁሉንም ይቀበላል፤ ሁሉም በእርሱ ዘንድ ቦታ አለው፡፡ በአጠቃላይ ለሁሉም የተከፈተ በር አለው” እንደማለት ነው፡፡ እንደዚሁም ቤተ ክርስቲያንም በሁሉም ስፍራ የምትገኝ፣ ሁሉንም የምታካትት፣ በርዋን ከፍታ ሁሉንም የምትቀበል እንደማለት ነው፡፡ 🌱→ → ቅዱስ ኢግናጢዮስ ካቶሊክ የሚለው ቃል እንዲጠቀም ምክንያት የሆነው ምንድን ነው? ቅዱስ ኢግናጢዮስ ካቶሊክ የሚለው ቃል እንዲጠቀም ምክንያት የሆነው ወይም ካቶሊክ የሚለው ፅንሰ ሐሳብ እንዲፈጠር ምክንያት የሆነው ከዚያ በፊት በብሉይ ኪዳን ውስጥ የነበረውን የሰዎች የአኗኗር ሁኔታ ነው፡፡ ይህም የአይሁድ ማኅበረሰብ (እስራኤላውያን) ዝግ ማኅበረሰብ ነበር፡፡ ካቶሊክ ብሎ ቃሉ ሲጠቀም ግን የተከፈተ (ለሁሉም ክፍት የሆነ) እንደማለቱ ነው፡፡ አይሁዳውያን ከሌላ ወገን በትዳር፣ በአምልኮና በማኅበራዊ ሕይወት ሳይተሳሰሩ እርስ በርሳቸው ብቻ ማኅበራዊና ሃይማኖታዊ ሕይወታቸውን አጠናክረው መኖርን የሚመርጡ ነበሩ፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በትምህርቱና በተግባሩ ይህንን የአይሁድ ማኅበረሰብ እንዲከፈትና ሌላውንም እንዲያካትት አደረገው፡፡ ለምሳሌ ከአይሁድ ማኅበረሰብ ውጭ የሆኑትን በመቀበል፣ በመፈውስና እንዲሁም በማኅበረሰቡ ውስጥ ክብርና ቦታ እንዲኖራቸው ማድረጉ ተጠቃሽ ነው፡፡ ቀጥሎም ከጌታ ኢየሱስ ትንሣኤ በኋላ ሐዋርያት በተቀበሉት የጌታ ትእዛዝ መሠረት(ማቴ 28፡19-20) በዓለም በሁሉም አቅጣጫ በመሔድ፣ ሁሉንም ሕዝብ የሚያካትት፣ ለሁሉም የተከፈተና ሁሉንም የሚያቅፍ የክርስቲያን ቤተሰብ አስፋፉ፡፡ ካቶሊካዊነትም እየተቀጣጠለ ሔደ፡፡ ❤️🔥 →→ የእስክንድርያው ቅዱስ ቄርሎስ “ካቶሊካዊት” ማለቱ ምን ማለት ነው? በአራተኛውና በአምስተኛው ክፍለ ዘመን (ከ376 እስከ 444 ዓ.ም.) የኖረው፣ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው፣ የነገረ መለኮት ሊቅ እና የቤተ ክርስቲያን ዶክተር በሚል የሚታወቀው የእስክንድርያው ቅዱስ ቄርሎስ በሚያስተምርበትና በሚጽፍበት ጊዜ ካቶሊክ የሚለው ቃል ተጠቅሞአል፡፡ ቅዱስ ቄርሎስ ለንስጥሮስ በጻፈው ሦስተኛው መልእክቱ ላይ “ካቶሊክ እና ሐዋርያዊት” በሚል የክርስትናን እምነት ሲገልጽና ሲሟገት ነበር፡፡ በዚህ አገላለጹ የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ካቶሊካዊት ማለትም ሁሉንም የምታካትት ዓለም አቀፋዊት ባህርይ የተላበሰች መሆንዋን አመላክቷል፡፡ ❤️🔥→→ መደምደምያ ❤️🔥 በአጠቃላይ በመጀመሪያዎቹ የክርስትና አራት መቶ ዓመታት ካቶሊክ የሚለው ቃል “የአዲስ ኪዳን ሰዎች (የክርስቶስ ተከታዮች) ወሰን ወይም የድንበር ከለላ የላቸውም፤ ሕይወታቸው ከሁሉም ጋር ነው፤ ለሁሉም ክፍት የሆነ ነው፤ በቦታ፣ በዘር፣ በቋንቋ፣ በፆታም ሆነ በኑሮ ሁኔታ አይወሰኑም” ከሚል አኳያ ይጠቀሙበት ነበር፡፡ በተጨማሪም ክርስቶስ ያስተማረው እውነታ ሁሉንም የሚያቅፍ፣ ሁሉንም የሚያካትት፣ ሁሉንም የሚመለከትና ለሁሉም በሁሉም ስፍራ መዳረስ ያለበት እንደሆነ ለመግለጽ ይጠቀሙበት ነበር፡፡ ካቶሊክ የሚለው አሳብም ከዚህ ዘመን ማለትም የአንጾኪያው ቅዱስ ኢግናጢዮስ (በ107 ዓ.ም.) ከተጠቀመበት ጊዜ ጀምሮ በተግባር ላይ የዋለ፣ በኑሮ ሒደት የዳበረና የተስፋፋ ቃል ብቻ ሳይሆን የእምነትና የቤተ ክርስቲያን መጠሪያ ስም ጭምር ነው፡፡ አዘጋጅ: ክቡር አባ ምስራቅ ጥዩ (ዶ/ር) የተመረጠው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳን ቀን አሁን ነው።" 2ቀሮ 6፡ 2 “አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፡፡” ማቴ. 6:33 ቤተሰብ ይሁኑን 👇👇👇 https://t.me/YariedDessale/7134 👆👆👆 The Universal Catholic Church Teaching Channel.
Открыть в Telegram“እኔ እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ እንደ መንገዱ፥ እንደ ሥራው ፍሬ እሰጥ ዘንድ ልብን እመረምራለሁ ኵላሊትንም እፈትናለሁ።” —❤️🔥 ኤርምያስ 17፥10❤️🔥
Открыть в Telegram“እግዚአብሔር አንድ እንደ ሆነ አንተ ታምናለህ፤ መልካም ታደርጋለህ፤ አጋንንት ደግሞ ያምናሉ ይንቀጠቀጡማል።” ❣️ ያዕቆብ 2፥19❣️
Открыть в Telegramጥንታዊ የቤተክርስቲያን አባቶች እነማን ናቸው? ❤️🔥🌱🌱🌱🌱🌱🌱❤️🔥🌱 "ለማንም ቅዱሳት መጻሕፍትን ከዚህ አረዳድ በተቃራኒ ወይም በአባቶች ያለ ልዩነት ከሆነ መስማማት ተቃርኖ ይፈታ ዘንድ የተፈቀደ አይደለም" የትሬንቶ ጉባኤ ፦ አራተኛ ስብሰባ ፣ ስለ ቅዱሳት መጻሕፍት አጠቃቀም አዋጅ። እንኳን ወደዚህ የዩትዩብ ገፅ በደህና መጣችሁ በዚህ ገፅ የሚከተለውን የቤተክርስቲያን ሐሳብ እናገለግላለን እንጋራለን "ቅዱስ ዜማ በቅዱስ መጽሐፍ ተመስግኗል (ኤፌሶን 5:19 ቆላስያስ3:16) ...ቅዱስ ዜማ ከሊጡርጊያ ተግባር ጋር ጥብቅ የሆነ ግንኙነት ካለው በቅድስና ያድጋል፤ በውበት ጸሎትን ይገልጻል ፤ አንድነትን ያስፋፋል ፤ ከፍ ባለ ሥነ-ስርዓትም ቅዱሳት ስርዓቶችን ያበለጽጋል። ቤተክርስቲያንም በእውነት ኪነ ጥበብ የሆኑ ነገሮችን ሁሉ ትቀበላለች ፤ በጥራታቸው ተስማሚና ተገቢ ከሆኑም በመለኮታዊ አገልግሎት ላይ ታውላቸዋለች።" የሁለተኛው ቫቲካን ጉባኤ ስለ ስርዓተ አምልኮ ምዕራፍ 6 ቁጥር 112 ✍️ ጸሐፊ ዲያቆን ራዕይ ሳሙኤል 👇👇👇 https://www.youtube.com/watch?v=xDV21k4Y8Z0 የተመረጠው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳን ቀን አሁን ነው።" 2ቀሮ 6፡ 2 “አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፡፡” ማቴ. 6:33 ቤተሰብ ይሁኑን 👇👇👇 https://t.me/YariedDessale 👆👆👆 The Universal Catholic Church Teaching Channel.
Открыть в Telegram