Кабинет
ወግ ብቻ

ወግ ብቻ

✔በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን። ✔ @getem @serenity13 ✔ @wegoch @Words19 ✔ @seiloch ✔ @zefenbicha Creator @leul_mekonnen1

Юзернейм
@wegoch
Категория
Юмор и развлечения
Страна
ЭфиопияЭфиопия
Подписчики17 100
Просмотров на пост, 7 дн.—за 7 дней
ERR13,57 %в среднем за 30 дней

Новые посты

#5393Текст

ትራስህን ምረጥ ባሻዬ! "ሞባይሌን ከቢሮ ውስጥ ሰረቁኝ" ሲል ፓሰተሩ ለጓደኛው ነገረው። ጓደኛው በሁኔታው አዝኖ ጠየቀው፣ "ማን እንደሰረቀህ አውቀኸዋል?" "አላወቅኩትም" "ታዲያ ምን ችግር አለው። ነገ እሁድ ለስብከት መድረክ ላይ ስትወጣ አሥርቱን ትዕዛዛት ስበክና አትስረቅ የሚለው ቃል ላይ ስትደርስ ጠንከር አድርገህ በቁጣ ስበክ። የዚያን ጊዜ ሌባው ሲደነግጥ ታየዋለህ። ወይም ቢሮ ድረስ መጥቶ ይመልስልሃል" በማግሥቱ የፓስተሩ ጓደኛ ለፓስተሩ ሲደውልለት ስልኩ ጠራ፣ "ሃሎ! ስልክህን እንዴት አገኘኸው?" "ያው የመከርከኝን ምክር ተከትዬ ነዋ!" "አትስረቅ የሚለው ስብከት ሠርቷላ" "አይደለም" "እንዴት?" "አትስረቅ ከሚለው በፊት 'አታመንዝር' የሚለው ቃል ላይ ስደርስ ሞባይሌን የት እንደጣልኩት ትዝ አለኝ!" ባሻዬ! የምትንተራሰውን ትራስ ምረጥ። ያዕቆብ ድንጋይ ተንተርሶ ራዕዩን አገኘ። ሳምሶን የተባለው ሰው ደግሞ የሴት ጭን ተንተርሶ ራዕዩ ተወሰደበት። ትራስህን ምረጥ። የተኛህበትን ቦታ ሳታውቅ ሰውን ለመወንጀል አትነሳ። By Tesfaye H/Mariam @wegoch @wegoch @paappii

Открыть в Telegram
Просмотры2 3200%к среднему
Пересылки—
Реакции72
Комментарии—
#5392Текст
Просмотры7 360+217%к среднему
Пересылки—
Реакции202
Комментарии—
#5390Текст

ወደ ስራ ስሄድ አንድ የስልክ እንጨት ላይ የተለጠፈ ወረቀት አየሁኝ: ጽሁፉ እንዲህ ይላል “እዚህ መንገድ ላይ 50 ብር ጠፍቶብኛል: ያገኘ ሰው ካለ እባካችህን አድራሻዬ በሚቀጥለው መንገድ በቀኝ በኩል ስትታጠፉ ያለው አሮጌ ቤት ነው:: አይኔ እንደፈለግኩኝ አያይም: እድሜዬም ገፍቷል: ልጆችም የሉኝም" ይህንኑ ጽሁፍ ተከትዬ ወደ አሮጌው ቤት ስሄድ አንዲት ሴትዮ ደጃፍ ላይ ተቀምጠዋል: የእግር ኮቴየን ሰምተው "ማነው? ማን ልበል?" አሉኝ "እዚህ መንገድ ላይ 50 ብር አግኝቼ ነው: እሱን ልሰጥ ነው የመጣሁት" ብዬ መለኩላቸው አሮጊቷ እንባ ቀደማቸው - "ልጄ! እስካሁን ድረስ ከ40 በላይ ሰዎች 50 ብር መንገድ ላይ ወድቆ አገኘን ብለውኝ መጥተዋል" ቀጠሉ አሮጊቷ - "እኔ ይህንን ጽሁፍ አልጻፍኩኝም: ጽሁፍ ለመጻፍም ሆነ ለማንበብም አይኔ እሺ አይለኝም" 50 ብሩን በእጃቸው አስጨበጥኳቸው ጽሁፉን ከስልክ እንጨቱ ላይ እንድቀደው ቢነግሩኝም አላደረግኩም: የመጣውን ሰው ሁሉ ይህንኑ ነበር የሚሉት ይህንን ጽሁፍ የጻፈውን ሰው እንዴት እንዳደነቅኩት : እኚህን ሴትዮ ለመርዳት የሄደበት ርቀት በጣም ነው ያደነቅኩት ከሴትዮዋ ቤት ስወጣ አንዲት ወጣት ልጅ አስቆመቺኝ "ወንድሜ! እዚህ መንገድ ላይ 50 ብር አግኝቼ ነበር: የቤቱ አቅጣጫ በየት በኩል እንደሆነ ታውቃለህ እንዴ?" በልቤ እየሳቅኩኝ ቤቱን ጠቆምኳት ሰው መሆኛ መንገዱ ብዙ ነው !! By Zemelak Endrias መልካም አዲስ ዓመት @wegoch @wegoch @paappii

Открыть в Telegram
Просмотры9 520+310%к среднему
Пересылки—
Реакции196
Комментарии—
#5389Превью ссылки
Просмотры7 550+225%к среднему
Пересылки—
Реакции14
Комментарии—
#5388Текст
Просмотры8 170+252%к среднему
Пересылки—
Реакции82
Комментарии—
#5387Текст

ሁሌም የሴቶች ዶርም ድረስ መጥቶ ሸኝቶኝ ሲመለስ ባለማመን ያዩታል። «ሔለን ግን ሙድ እየያዝሽብን ነዋ! ያን ሁሉ ወንድ ያባረርሽው ይሔ ፉንጋ ጋር ለመሆን ነው?» ትላለች አንደኛዋ። «እስኪ ተያት ምን ታውቂያለሽ? ራቁቱን ያዬችው እሷ!» ብላ ሌላኛዋ ታሽካካለች። እኔም አስከፋናት ብለው እንዳይደብራቸው እስቅላቸዋለሁ። ዋና ምክኒያቴን ከሚያውቁብኝ የጠረጠሩት እውነት እንደሆነ እንዲሰማቸው ባደርግ ይሻለኛል። ለሰው ባይመስልም ፉንጋው የፀሎቴ መልስ ብቻ ሳይሆን ጨለማ ክፍል ውስጥ ያገኘሁት ሻማዬ ነው። «ሔሉዬ ሌላ ቅፅል ስም ጠፍቶ ነው 'ሻማዬ' የምትይኝ?» ይለኛል። «ሻማዬ ካላልኩህ ችቦዬ ነው የምልህ...የቱ ይሻልሀል?» «አይ ሻማው ይሁን በቃ!» ይላል እየተቅለሰለሰ። አንዲት ፀበል ለፀበል የምትመላለስ ታላቅ እህት አለችኝ። ሰዎች መንፈስ ይዟት ነው እያሉ ያወራሉ። እኔ ግን ባሏን ፈትታ ከመጣች ቡኃላ የዘመድ አዝማዱን ወሬ አትችለው ብላ እንዳበደች አውቃለሁ። ከዛ ጊዜ ጀምሮ ፀሎቴ አንድና አንድ ብቻ ነው። «ጌታ ሆይ የምወደውን ሳይሆን የሚወደኝን ስጠኝ!» ለዛ ነው ሻማዬ የፀሎቴ መልስ ነው የምለው። የመጀመሪያ ቀን ሰውነቱ በላብ ተጠምቆ፣ እጁ እየተንቀጠቀጠ፣ መተንፈስ አቅቶት እየቃተተ ሲጠይቀኝ እንደማገባው ወስኜ ነበር። የግቢውን ወንዶች ሁሉ መልሼ እሱን የጠበስኩት እነሱ እንደሚሉት የተለዬ ነገር አግኝቼበት አይደለም። ሪስክ መውሰድ ስለማልችል ነው። የፈሪ ሰው ጥቅም?...ቀድሞ አያጠቃም! ግቢ ውስጥ በኔ ምክኒያት ያልደረሰበት ግፍ የለም። ለሁሉም ታዋቂ ካፕሎች ቅፅል ስም ሲሰጡ እኛን ማን ቢሉን ጥሩ ነው? "Beauty And The Beast" ሆሆ! ተረባውን ችሎ አለፍ ሲል ደግሞ መምህራኖች ግሬድ ያበላሹበታል። ጉልበተኞች ዱላ የቀላቀለበት ማስፈራሪያ ያዘንቡበታል። ዘበኞች እንኳን ባቅማቸው ያዋክቡታል። ሁሉም እንደየስልጣኑ ይበድለዋል። «ሻማዬ ከዚህ በላይ እንድትጎዳ አልፈልግም» ስለው «ቀላል ነው ብዬ አልዋሸሽም። ሽልማቴ አንቺ እንደሆንሽ ሳስበው ግን 'ኧረ ያንሰኛል ጨምራችሁ ምቱኝ' ልላቸው ሁላ ያምረኛል!» እያሳዘነ ያስቀኛል። ገፍተው ገፍተው ለራሱ ያለውን አመለካከት እንዳወረዱበት የገባኝ የአመቱ መጨረሻ ላይ ነው። እሱ ተመራቂ ስለነበር ቀጣይ አመት እንደማንገናኝ ገብቶት እያለቀሰ መጣ። «አንተም ስራ ልታገኝ የምትችለው እዚሁ አዲሳባ ነው። እኔም እዚሁ ነው የምማረው! ምን የተለዬ ነገር ተፈጠረና ነው የምታለቅሰው?» «አንድ ነገር ብቻ ቃል ግቢልኝ!» አለ አሁንም እያለቀሰ! «እሺ ምንድን ነው?» «እስክትመረቂ ድረስ የፈለግሽው ወንድ ጋር ሁኚ! ከዛ ቡኃላ ግን ተመልሰሽ ወደኔ ልትመጭ ቃል ግቢልኝ!» ምንም አላልኩትም። በቆመበት ጥዬው ሔድኩ። ምን ባደርገው ነው ሊተማመንብኝ የሚችለው? እኔስ በዚህ ደረጃ ከሚወደኝ ወንድ ውጭ ሌላ ምን እፈልጋለሁ? ከሶስት ቀን ቡኃላ የሻማዬን ልብ ያረጋል ብዬ ያሰብኩትን ትልቅ ውሳኔ ወሰንኩ። ሲያዬው አዲስ እንደተወለደ ህፃን ስቅስቅ ብሎ ማልቀስ ጀመረ። ለነገሩ እኔም ከዛ ያነሰ ግብረመልስ አልጠበኩም። ይሔንን ፊት ለዘላለም እንዳይጠፋ አድርጌ ጀርባዬ ላይ ተነቅሼለት ለቅሶ ሊበዛብኝ ነው? የሚያስቀው እንራራቃለን ብዬ ፊቱን ተነቅሼለት ሌክቸረር ሁኖ እዛው ግቢ ቀረ። የሚያሳዝነው ደግሞ ተማሪዎች በገቡ በመጀመሪያው ሳምንት ሁሉም ስለታቱዬ አወቁ። የፈሪ ትልቁ ችግር?....ምርኮኛ አያያዝ አይችልም! «ለማን ተናግረህ ነው?» ብዬ ሳፈጥበት...አብሮት ሌክቸረር ለሆነ ሰቃይ ጓደኛው ብቻ መናገሩን ነግሮ ይቅርታ ጠየቀኝ። እኔም ከተያዙ ቡኃላ መንፈራገጥ ጥቅም የለውም ብዬ ተውኩት። የግቢው አየር ባንድ ጊዜ ተገለበጠ። ሻማዬ የግቢው ቁጥር አንድ ተፈላጊ ወንድ ሆኖ ቁጭ አለ። እኔ ደግሞ ስወጣ ስገባ የተረባ መለማመጃ ሆንኩ። አንዴ ወጣቶች ተወራርደው አስገድደው ልብሴን ገልጠው፣ ታቱዬን ካዩብኝ ቡኃላ ከሀዘን የወጣሁበት ቀን ትዝ አይለኝም። ሻማዬ ሊጠብቀኝ ቀርቶ ቶሎ ቶሎ ሊያገኘኝ ራሱ ጥረት አያደርግም። እኔ ነኝ የምደውልለት። እንዲያውም አልናገርም ብዬ እንጂ አልፎ አልፎ የግቢው ታዋቂ ሴቶች ከቢሮው ሲወጡ አያለሁ። በአንድ ወቅት ሊነካኝ ከብዶት ሲንቀጠቀጥ የነበረ ሰው፤ ዛሬ መዳፉ ላይ ሲያገኘኝ ጨብጦ ሊያፈርጠኝ ሲዳዳ ባዬው...ለመረዳት ከበደኝ። የሆነ ቀን ጉዳዩን ጨራርሰን እንደተቀመጥን «ሰሞኑን መድሀኒት ስትጠቀሚ አላይሽም! ሌክቸረር ሆነ ብለሽ ልታረግዥብኝ ነውዴ?» አለኝ። በዚች ንግግሩ ታሪኬን ቀዬረው። ትምህርቴን አቋርጨ አዲስ ህይወት ጀመርኩ። ስሜንም ቀየርኩ። ታቱዬን ሙሉ ጥቁር አድርጌ "ብላክ ሆል" ነው እያልኩ መንገር ጀመርኩ። ሰላም ያለው ህይወት ለመኖር የነበረኝ አንድ አማራጭ ነበር። ሁሉንም ሰው ከህይወቴ አስወጥቼ ልጄን ማሳደግ። የዚያኔ እንደዛ ባለኝ ሰዓት ፀባዩ ሲስተካከል እነግረዋለሁ እያልኩ ያረፈድኩባት ፅንስ ነበረችኝ። አሁን አሁን ሳስበው ታሪኬ ረጅም ይመስላል እንጂ አጭር ነው። ይቺው ናት ውጣ ውረዴ! ልጄን እስካሳድግ ድረስ ሁለት ጊዜ ብቻ ነው ከቤተሰቦቼ ጋር የተገናኘሁት። እነሱም እምብዛም ሊያዩኝ አይፈልጉም። መላቀቅ ነው! ይቅሩብኝ ከነምላሳቸው! ምላስ ሽሽት ነው ነው ኑሮዬ! አልፎ አልፎ ስር እንዳይሰድ አድርጌ የወሲብ ግኑኝነት እጀምራለሁ። እነሱም ስለኔ ትንሽ ማወቅ ሲጀምሩ ጥያቸው ዲዲዲዲዲዲ! በዚህ ርዕስ ላይ ከማወራ ይሻለኛል። ልጄ በኔ መልክ ባባቷ ጭንቅላት በመውጣቷ ያገኛት ሁሉ ይወዳታል። እኔም በሷ እየተፅናናሁ እኖራለሁ። በቃ። ይሔን ሁሉ ቁጭ ብዬ የማስበው ዛሬ «አባቴ ማነው?» ብላ ጠይቃኝ ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ ሩጨ የማላመልጣት ሰው ገጠመችኝ። የመመለስ ግዴታ እንዳለብኝ አውቃለሁ።  ግን እንዴት ነው የአ'ምሮ በሽተኛ ሳላደርጋት ስለአባቷ ልነግራት የምችለው? ተረት ላድርገው ይሆን? እምብዛም የማይንቁት...እምብዛም የማያደንቁት የ'ንደኔ አይነቷ ኖርማል ሰው ህይወት እንዴት ነው የሚተረተው? «ተረት ተረት!» «የመሰረት!» «በድድሮሮሮሮ ጊዜ አንዲት ሔለን የምትባል፤ ከብርጭቆዋ ጋር ጨለማ ክፍል ውስጥ የምትኖር ልዕልት ነበረች።» «እእእሽ» «ሁሌም ሌቦች ብርጭቆዬን ይሰርቁብኛል ብላ ስለምትሰጋ ጨለማው ያስፈራት ነበር። ከዛ አንድ ቀን ምን ብታገኝ ጥሩ ነው?» «ምን?» «ሻማ!...በጣም ደስ አላት። ሻማዋን አብርታ እያዬች ደስ አላት። 'ይቺ ሻማ እስካለች አልሰጋም' ስትል አሰበች። ሻማዋ ግን 'እጠፋለሁ' ብላ ትሰጋ ነበር። ንፋስ በመጣ ቁጥር ትንፋሿ ቁርጥ ቁርጥ ይላል። ልዕልቷም ሻማዋን ከንፋስ ለማስጣል ብላ አንድ የሞኝ ውሳኔ ወሰነች!» «ምን አደረገች?» «በብርጭቆዋ ሸፈነቻት።» «ከዛስ?» «ከዛማ ሌባ ይገባል ብላ በር በሩን እያዬች ከኋላዋ ቃቃቃቃቃቃ የሚል ድምፅ ተሰማት። ደንግጣ ስትዞር የምትሳሳላት ብርጭቋዋ ናት። ንፋስ መቋቋም አቅቷት ልትጠፋ የነበረችው ሻማ በሙቀቷ ብርጭቆዋን ሰንጥቃባታለች። ልዕልቲቱ አዘነች። ውሀ አጣጯ ቢመጣም ውሀ መጠጫ እንደሌላት እያሰበች አለቀሰች! አለቀሰች!..» እያለ የሚቀጥል ተረት! ፨፨፨ By Michel azmeraw @wegoch @wegoch @paappii

Открыть в Telegram
Просмотры11 200+383%к среднему
Пересылки—
Реакции216
Комментарии—
#5385Текст

«ዛሬ አትመጭም?» «ዛሬ ማርያም ናት አልነካም!» «ነይ እኔም አልነካሽም!» «አንተማ ወንድ አይደለህ እንዴት ብሎ ያስችልሀል?» «ወንድ ልጅ አያስችለውም ያለሽ ማነው?» «ቢያስችላችሁማ መች ከፍላችሁ ትተኙን ነበር?» (ዝም ብሎ ትንሽ ማሰብ...ከአባባሏ ላይ ስትህት ማጣት...ልመናውን መቀጠል...) «ቆይ እኔ ብዙ ቀን ሳልነካ አልመለስኩሽም?» «እና በራስህ ፍላጎት ነዋ! ቤትህ መጥቼ 'አትንካኝ' ብልህ ግን ለራሴም አያሳምነኝ...አንተም የሌለብህ ሰይጣን መውጣቱ አይቀርም።» «እእእ እና ያሁኑንን ወር ስራ ብትገቢባት ማሪያም ትቀይምሻለች?» «በሀይማኖቴ አታሹፍ!» «አንቺ ነሽ'ኮ እያሾፍሽ ያለሽው። ገላሽን ሽጠሽ እያደርሽ ማሪያምን አልነካም ስትይ አታፍሪም?» «አትግማማብኝ ስልኩን እንዳልዘጋው!» «እንዳታስቢው! ዛሬ ካልመጣሽ ማሪያምን አብዳለሁ። እየቀለድኩ አይደለም። ኃላ ጨርቄን ጥዬ ያዩኝ 'ግብዳ ቁ ላ የሌለው እብድ መጣ' እያሉ ከሚዘባበቱብኝ በጊዜ መጥተሽ ተንከባክበሽ ብታስተኝኝ ይሻልሻል።» (ዝም ብላ ትንሽ ማሰብ...ከአባባሉ ላይ ስጋት ማሽተት...) «ከደረቅክ ደረቅክ ነዋ...ያለ ልብህ አትሰማም።» (በተሸነፈ ድምፅ) «እሽ ነይ አሁን ቤቱን ፏ አድርጌያለሁ። የምትወጂውን ኬክ ገዝቻለሁ። ሻወር ጥዬሽ አልገባም ብዬ ፎጣ አገልድሜ ነው የማወራሽ።» «እሽ መጣሁ። የማሪያም ፀበል ፃዲቅ ልያዝልህ?» «ግዴለም አንቺ ትበቂኛለሽ።» «አይባልም» «እሺ ሌላ ጊዜ ታመጭልኛለሽ የዛሬው ይለፈኝ።» (ስትመጣ ሻወር ወስዷል...ብቻዋን ገብታ መውሰድ...ከዛ በኃላም የባጥ የቆጡን እያወራት መዞር...ማቀፍ የለም...መሳሳም የለም...ወሬ ብቻ...መዞር ብቻ...) «በጣም የሚገርመኝ እኮ ምን እንደሆነ ታውቃለህ? 'አልመጣም' ያልኩህ ቀን እንባ ቀረሽ ልመና ነው የምትለምነኝ። ስመጣ ግን የለመንከኝን ያህል ፈጥነህ ልትነካኝ አትሞክርም። አንዳንዴማ ከነጭራሹም ሳትነካ ትመልሰኛለህ። ከዚህ የምታገኘው እርካታ ምንድን ነው? ማለቴ ይሔ እንዴት ያለ የወሲብ አይነት ነው? የወሲብ አይነት ከሆነስ ባህላችን ይፈቅደዋል ወይ? ሂሂ» «ይሔ ያስቃል።» (ሳይስቅ) «የምሬን ነው። ያስፈራኛል ይሔ አመልህ።» «በጣም የምትወጂው ነገር ምንድን ነው ማርቲዬ?» «ኬክ ነዋ እያወቅከው» «እሺ ቆይ ያልበላሻት ትንሽዬ ኬክ ፍሪጁ ውስጥ ብትኖር ሳትበያት ስለሌላ ነገር ማሰብ ትችያለሽ?» «እንዴት ብዬ?» «የኔም ነገር እንደዛው ነው። በእረፍት ቀኔ አንቺ ከሌለሽ ይጨንቀኛል። ሀሳብ ብቻውን አገኘሁት ብሎ ተመቻችቶ ይተኛብኛል። አንቺ ቤት ካለሽ ግን ስሌላ ነገር ማሰብ አልችልም። ሽፍደቴ ጣልቃ እየገባ ጭንቀቴን ሁሉ ይበትነዋል።» «ኦውውውው የምር እኔ ኬክ የምወደውን ያህል ትወደኛለህ ማለት ነው? እንባዬ መጣ ማሪያምን!» «ኧረ ብዙም ደስ አይበልሽ ላንቺ አይደለም ለገላሽ ነው እንደዛ ያልኩት።» «ሒድ! ምኑ ግማታም ነው በማሪያም? ሸ ርሙጣ!» «ምኗ ነሽ አንቺስ? መሐንዲስ!» «ማሾፍህ ነው?» «በሙያሽ ሰደብሽኝ በሙያዬ ሰደብኩሽ።» «ሰው እንዴት ሰውን 'መሐንዲስ' ብሎ ይሳደባል? መማታት እየተቻለ?» «ሃሃ ቆንጆ ተጫወትሽ አሁን...» «ግን...ግን» «እ?» «ምን አይነት ሀሳብ ቢኖርብህ ነው ይሔን ያህል ለመሸሽ መላ የምትፈልገው?» «ምንም!...ማለቴ እንዲህ ነው ተብሎ የሚነገሩ አይደሉም። ዝምብለው ተራ ነገሮች ናቸው። ብቻ አዕምሮዬ ስራ ፈትቶ አያግኙት!» «አልገባኝም?» «ለማስረዳትም የሚመቹ አይደሉም።» «አንቺ አይገባሽም ደደብ ነሽ የሚል ንቀት ባይኖርብህ የተወሰነ ልታስረዳኝ ትሞክር ነበር።» «ተንኮለኛ ነሽ እንደው። እንዴት ብዬ ልንገርሽ ማርቲዬ? አሁን ባለፈው አንቺ የቀረሽ ቀን እዚህ መታጠፊያዋ ጋ የጀበና ቡና የምትሸጠው ሳቂታዋ ልጅ የለችም? ድንገት ሀሳብ ውስጥ ገብታ ቡና ደፋችብኝ። ተናድጄ 'አቦ ይድፋሽ' ብላት 'ኧረ አሜሜሜን' አለችኝ በተማረረ ድምፅ። ደብሮኝ ዋለ። የባለፈው ባለፈው ደሞ አውሮፓ ያለችው የጎረቤቴን ልጅ እያወራኋት 'መቼ ነው የምትመጭው?' ስላት 'ሀብታም ባል ሳገባ' አለችኝ እየሳቀች። እኔ ግን ሳለቅስ አመሸሁ። የባለፈው ባለፈው ባ...» «ኧረ በቃህ! አንተ ዝም ካልኩህ 'መብራት በርቶባቸው መኪኖቹ ሲቆሙ አለቀስኩ' ትለኛለህ። ምኑ ንፍሮ ነው በማሪያም!» «ይቅርብሽ ብዬ ነበር እኮ እኔም...ራስሽ ነሽ...» «ስቀልድ ነው ተረድቼሀለሁ። ግን የጠበኩት ከድሮ ሚስትህ ጋ የተያያዘ ነገር ነበር!» (ቀጥ ብሎ እይት...ስታዬው አይኑን ስብር...) «ምን ሰምተሽ ነው?» «ምንም» «ባክሽ ታስታውቂያለሽ የሰማሽው ነገር እንዳለ!» (መስኮት መስኮት እያዬ ትክዝ..) «እሺ! ግን አይደብርህማ ቢነሳ?» «አትቅለስለሽ! ሁሌ አይደል እንዴ ልታነሽብኝ የምትሞክሪው? እኔ ሆን ብዬ ርዕስ ስለምቀይርብሽ እንጂ! በይ አውሪውና ይውጣልሽ!!» «ኧረ ማሪያምን እኔ ለዛ አይደለም። ከፈለግክ አለማውራት እንችላለን። እንዲደብርህ አልፈልግም።» «እንደሌላው ሰው ዙሪያጥምጥም አትሒጂ እንጣላለን!» «እሺ! እንትን? ማለቴ ሰራተኛዋ ቆንጆ ነበረች?« (እንደመሳቅ እያለች) «አልነበረችም። አፈር ነች!» «እና ለምን? ማለቴ?..» «ለምንም! በቂ ምክኒያት የለኝም። ሚስቴ ፊልድ ሔደች። በዕረፍት ቀኔ ብቻዬን ሆንኩ። ሀሳብ በዛብኝ። ከሀሳብ ለመውጣት ቁ ላዬን የማስቀምጥበት ጉድጓድ ፈለግኩ። ሰራተኛችንን አገኘሁ። ወጣሁባት። ሚስቴ ያዘችኝ። ተፋታን። ይሔው ቀልዬ እኖራለሁ አንገቴን ደፍቼ። እ? አሁንስ ደስ አለሽ? ወሬኛ!!» «ኧረ ተው እንደሱ አትበል በማሪያም! ሁሉም ሰው ይሳሳታል'ኮ!» «ሃሃ ይልቅ ነይና እቀፊኝ...ደስ ይበልሽ...መጨነቅ ጀመርኩ።» (ተነስታ እቅፍ...አናቱን ወስዳ ጡቶቿ ውስጥ ሽጉጥ...እሱ ተጠጋችኝ ብሎ ሰውነቷን መሳም...እሷ ጆሮው ቀረበኝ ብላ ማንሾካሾክ...) «ያለ ነው። ያጋጥማል። ሁሉም ይጥላህ። ብቻ አንተ ራስህን አትጥላ። ሁሉም ይናቅህ። ብቻ አንተ ራስህን አትናቅ። ሲያስመስሉ ነው'ጂ ተሳስቶ የማያውቅ የለም። ስለማይነግሩን ነው'ጂ ያልወደቀም የለም!!» «መውደቄ መች ከበደኝና ማርቲዬ! የጣለኝ ፈተና ትንሽነት እኮ ነው እንዲህ የሚያደርገኝ። እንደ ዝንብ ቀልሎ ያልተገኘን የሸረሪት ድር ይጥለዋል?... ...ይልቅ እሱን ተይውና ዝምብለሽ እቀፊኝ። ጥብቅ አድርገሽ ያዥኝ። እፉዬ ገላ ነኝ...ከተውሽኝ ንፋስ ይወስደኛል...» (እስኪጨራመት ድረስ አጥብቃ እቅፍፍፍ...በጣቶቿ መሀል ሾልኮ እንዳይንሳፈፍ!) ፨፨፨፨፨ By Michel Azmeraw @wegoch @wegoch @paappii

Открыть в Telegram
Просмотры10 800+366%к среднему
Пересылки—
Реакции106
Комментарии—
#5384Текст

ትንሹ ጆኒ ለአስተማሪዉ እየነገረዉ ነዉ ። እኛ ቤት በጣም ትንሽ ናት ቤታችን እና እናቴ አባቴ እኔ ሁላችንም ምንተኛዉ አንድ አልጋ ላይ ነዉ ። እና ሁሌ ማታ ላይ አባቴ እንደተኛሁ እና እንቅልፍ እንደወሰደኝ ቼክ ያደርገኛል “ ተኝተሀል ?” ብሎ ሲጠይቀኝ “አይ አልተኛሁም “ እለዋለሁ። ከዛ በጥፊ ያጠናግረኝ እና ይገላምጠኛል ብሎ ነገረዉ። አስተማሪዉ ሰማዉ እና “ይኸዉል ዛሬ አባትህ ቼክ ሊያደርገህ ተኝተሀል ብሎ ሲጠይቅህ ዝም በል ትንፍሽ ሳትል እንደተኛ ሰዉ ጨፍነህ  ምንም መልስ እንዳትሰጥ “ ብሎ መከረዉ ። ከዛ በሶስተኛዉ ቀን አስተማሪዉ ህፃን ጆኒን ፊቱ አባብጦ ቀይ ሆኖ ጥግ ቆሞ ያየዋል ። አስደንግጦ “ እረ ምንጉድ ነዉ ፊትህ ምን ሆነህ ነዉ እንዲህ ያበጠዉ “ ብሎ ይጠይቀዋል። ትንሹ ጆኒም “ አባቴ ድጋሚ እንደተኛሁ ቼክ ሊያረገኝ ሲጠይቀኝ አንተ  እንደመከርከኝ እንደተኛ ሰዉ ጭጭ አልኩት ። ከዛ እናቴ እና አባቴ መንቀሳቀስ ጀመሩ እናቴ በጣም በሀይል ትተነፍሳለች እግሯንም ወደላይ እርግጫ እየሰነዘረች ድምፅ ማሰማት ትጀምራለች ። ከዛ አባቴ እናቴን “ እየመጣሽ ነዉ ?” አላት ከዛ እናቴም “ አዉ እየመጣሁ ነዉ አንተስ እየመጣህ ነወ?” ከዛ አባቴ “አዉ አዉ እየመጣሁ ነዉ “! ሲላት የትም ቦታ ብዙ ግዜ ከኔ ዉጪ ጥለዉኝ ስለማይሄዱ ስለዚህ እኔም ድምፄን አዉጥቼ “ ጠብቁኝ እኔም እየመጣሁ ነዉ “ ስላቸዉ አባቴ የሰነዘረብኝ ቡጢ ነዉ እንዲህ ያረገኝ! By Eled Aymen @wegoch @wegoch @paappii

Открыть в Telegram
Просмотры9 590+313%к среднему
Пересылки—
Реакции119
Комментарии—

Все посты

Связи