የሙሥሊሙ ቁጥር በ 10 ዓመት ውስጥ ከ 1.6 ቢልዮን ወደ 2.2 ቢልዮን አሻቅቧል። በእዚህ ፍጥነቱ ኢን ሻ አሏህ! መጪው ዘመን የዲኑ ኢሥላም ነው።
Открыть в TelegramПосты канала ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በጉያዋ የታቀፈቻቸው የጥንቆላ፣ የመተት እና የድግምት መጻሕፍት እነዚህ ናቸው፦ 1. ጥቁር አስማት 2. ጸሎተ ንድራ 3. መብረቀ ሰማይ 4. መጽሐፈ ልፋፈ ጽድቅ 5. ጸሎተ ሐመር 6. መጽሐፈ አልፋ ሰገድ 7. ጸሎተ አይሁድ 8. ጸሎተ ሙሴ 9. ጸሎተ ንድራ ወዓይነ ጥላ 10. የመስቀል አጥር ጸሎት ይህንን ስንላቸው "ሙሴም የግብፆችን ጥበብ ሁሉ ተማረ እርሱ ፋል የሚባል ጥንቆላ ነው" ይሉናል፦ የሐዋርያት ሥራ 7፥22 ሙሴም የግብፆችን ጥበብ ሁሉ ተማረ፥ በቃሉ እና በሥራውም የበረታ ሆነ። የሐዋርያት ሥራ 7፥33 አንድምታ ሙሴ በፈረዖን ቤት ባደገ ጊዜ ፋል የሚባል ጥንቆላ ተምሮ ስለነበረ አንድም ጫማህን ከእግርህ አውልቅ ያለው እግዚአብሔር አምላክ ሙሴን የተማርከውን ጥንቆላህን አውልቀህ ወደ እኔ ና ሲለው ነው። ሙሴ የግብፆችን ጥበብ ጥንቆላ ሁሉ ተምሮ ነበር፦ "ፋል የሚባል ጥንቆላ አንድ ነቢይ ተምሮ ነበር" ማለት ስድብ ነው፦ ውዳሴ ማርያም ዘሠሉስ አንድምታ "ሙሴ ፋል የሚባል ጥንቆላ ተምሮ ነበር" ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom
Открыть в Telegramነጥብ ሁለት "ጎደሎ" ሁለት እና ሦስት ሴት ልጆች ወራሽ ሲሆኑ፦ 1. ⅛ ለሚስት ሲሆን 100,000 × 1 ÷ 8 = 12,500 ይሆናል። 2. ⅔ ለሁለት እና ለሦስት ሴቶች ሲሆን 100,000 × 2 ÷ 3 = 66,600 ይሆናል። 3. ⅙ ለአባት ሲሆን 100,000 × 1 ÷ 6 = 16,666 ይሆናል። 4. ⅙ ለእናት ሲሆን 100,000 × 1 ÷ 6 = 16,666 ይሆናል። ሁሉም ሲደመር፦ 1. 12,500 2. 66,600 3. 16,666 4. 16,666 ----------------------------- = 112,432 ሲመጣ ከ100,000 ውርሱ ላይ ተከፋፍሎ 12,432 ይጎድላል፥ ስሌቱ 112,432 - 100,000 = 12,432 ይሆናል። ምሳሌ፦ ½ ስንል 1 "በሥጥ" بَسْط ስትሆን 2 ደግሞ "መቃም" مَقَام ነው፥ "በሥጥ" بَسْط ማለት "አንሺ"Numerator" ማለት ሲሆን "መቃም" مَقَام ማለት ደግሞ "አካፋይ"Denominator" ማለት ነው። ½ አንድ ሁለተኛ ማለት ከመቶ እጅ ግማሽ 50% ማለት ነው፥ ⅔ ሁለት ሦስተኛ ማለት ከሁለት መቶ እጅ ሲሶ 66.67 % ማለት ነው። 50+66.67 = 116.67 ነው፥ 116.67 ከመቶ ያለፈ ከሁለት መቶ ያነሰ መሆኑ ስህተት ካልሆነ በተመሳሳይ 112,432 ከመቶ ያለፈ ከሁለት መቶ ያነሰ መሆኑ ስህተት አይደለም። ታዲያ 100000 ብሩን ⅛ ለሚስት፣ ⅔ ለሁለት ከሁለት በላይ ለሆኑ ሴት ልጆች፣ ⅙ ለአባት እና ⅙ ለእናት እንዴት አድርገን እናካፍል? "ዐውል" عَوْل የሚለው ቃል "ዐወለ" عَوَّلَ ማለትም "ፈለገ" ከሚለው ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "አስፈላጊ" ማለት ነው፥ በሒሣብ የክፍፍል"Fraction" ሕግ ከፍተኛው የጋራ አካፋይ"Highest Common Factor(HCF) ሲሆን በዐረቢኛ "ዐውል" عَوْل ይባላል። ስለዚህ ⅛ + ⅔ + ⅙ + ⅙ = 24 ነው፥ በዚህ ስሌት ትንሹ የጋራ ብዜት 24 ሲሆን ከፍተኛው የጋራ አካፋይ 27 ነው። በሒሣብ ሕግ ክፍልፋዩ ሲጎድል የምንጠቀመው ከፍተኛው የጋራ አካፋይ ነው፥ ከፍተኛው የጋራ አካፋይ ለማግኘት በአስፈላጊ ጉዳይ የመጣ ነገር "ዐውሊይ" عَوْلِيّ ሲባል የአስፈላጊ ሂደቱ ደግሞ "ኢሥቲእዋል" اِسْتِئْوَال ይባላል። በኢሥቲእዋል ሕግ ⅛ ለሚስት፣ ⅔ ለሴቶች ልጆች፣ ⅙ ለአባት፣ ⅙ ለእናት ሲሆን፦ 1. ሚስት 24 × 1 ÷ 8 = 3 2. ሴት ልጆች 24 × 2 ÷ 3 = 16 3. አባት 24 × 1 ÷ 6 = 4 4. እናት 24 × 1 ÷ 6 = 4 3 + 16 + 4 + 4 = 27 ይሆናል። ይህንን ክፍፍል ስናካፍል በሒሣብ ሕግ ትንሹ የጋራ ብዜት የሆነውን 24 መሠረት አርገን ከፍተኛው የጋራ አካፋይ 27 ስናገኝ ለጎዶሎ መሙያ ነው። ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ"፦ "ክፍፍልን ለሚገባቸው አካፍሉ" ብለዋል፦ ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 85 ሐዲስ 53 "ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ክፍፍልን ለሚገባቸው አካፍሉ"። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ " أَلْحِقُوا الْفَرَائِضَ بِأَهْلِهَا በሒሣቡ 100000 ÷ 27 = 3703 ይሆናል፥ ይህንን ለእያንዳዳቸው ባለድርሻ አካላት ስንሰጥ፦ 1. ለሚስት 3 × 3703 = 11,109 2. ለሴት ልጆች 16 × 3703 = 59,248 3. ለአባት 4 × 3703 = 14,812 4. ለእናት 4 × 3703 = 14,812 ድምሩ 11,109 + 59,248 + 14,812 + 14,812 = 100,000 ይሆናል። ስለዚህ በቁርኣን እና በሐዲስ "አካፍሉ" ስንባል የሒሣብ "ክፍፍል"Fraction" ሕግ ተጠቅመን ትርፍ እና ጎደሎን እናካፍላለን እንጂ በራሳችን ሚጥጢዬ አስተሳሰብ መዝነን የዓለማቱን ጌታ የአሏህን ንግግር ሕፀፅ እና ስሑት ለማስባል መዳዳት አያዋጣም። አምላካችን አሏህ፦ "መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት" ብሎናልና፦ 59፥7 መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት! ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ፡ አሏህንም ፍሩ፡፡ አሏህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡ وَمَا آتَاكُمُ الرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَاكُمْ عَنْهُ فَانتَهُوا ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ ⅛ + ⅔ + ⅙ + ⅙ በቁርኣን ተንዚል የተደረገ ሲሆን ተንፊድ የተደረገው ደግሞ በሥስተኛው ኸሊፋው በዑመር አል ኽጧብ"ረ.ዐ." ጊዜ ነው፥ ይህ ተንፊድ ሙሉ ለሙሉ የሶሓባዎች ኢጅማዕ"Consensus" አለበት። ይህ ደግሞ ከአል ኺላፈቱ አር ሯሺዳህ የተገኘ ሡናህ ነው፥ ነቢያችን"ﷺ"፦ "የእኔን ሡናህ እና የተመሩ የአል ኺላፈቱ አር ሯሺዳህ ሡናህ ተከተሉ! በእርሷም ያዙና በእርሷ ላይ አጥብቁ" ብለውናል፦ ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 42, ሐዲስ 12 አል-ዒርባድ እደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ከእኔ በኃላ ከእናንተ ማንም ቢኖር እና ብዙ ልዩነት ቢያይ የእኔን ሡናህ እና የተመሩ የአል-ኺላፈቱ አር-ሯሺዳህ ሡናህ ተከተሉ! በእርሷም ያዙና በእርሷ ላይ አጥብቁ! መጤ ነገርን አስወግዱ! መጤ ነገር ሁሉ ቢድዓህ ነው፥ ቢድዓህ ሁሉ ጥመት ነው"። فَقَالَ الْعِرْبَاضُ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ... فَإِنَّهُ مَنْ يَعِشْ مِنْكُمْ بَعْدِي فَسَيَرَى اخْتِلاَفًا كَثِيرًا فَعَلَيْكُمْ بِسُنَّتِي وَسُنَّةِ الْخُلَفَاءِ الْمَهْدِيِّينَ الرَّاشِدِينَ تَمَسَّكُوا بِهَا وَعَضُّوا عَلَيْهَا بِالنَّوَاجِذِ وَإِيَّاكُمْ وَمُحْدَثَاتِ الأُمُورِ فَإِنَّ كُلَّ مُحْدَثَةٍ بِدْعَةٌ وَكُلَّ بِدْعَةٍ ضَلاَلَةٌ " የአል ኺላፈቱ አር ሯሺዳህ ሡናህ ደግሞ በረሡል የተደገፈ ሡናህ እንጂ መጤ ቢድዓህ ስላልሆነ የጎደሎ ውርስ በኢሥቲእዋል ሕግ እንዲህ ይፈታል። በሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ሷሊህ አል ዑሰይሚን"ረሂመሁሏህ" የተዘጋጀ ኪታብ "ተስሒሉል ፈራኢድ" تسهيل الفرائض ተመልከቱ! “አሏሁ አዕለም” اَللّٰهُ أَعْلَم አምላካችን አሏህ ለአህሉል ኩፍር ሂዳያውን ይወፍቃቸው! ለእኛም ኢሥቲቃማውን ይወፍቀን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Открыть в Telegramየውርስ ሒሣብ በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። 59፥7 መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት! ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ፡፡ አሏህንም ፍሩ፡፡ አሏህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡ وَمَا آتَاكُمُ الرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَاكُمْ عَنْهُ فَانتَهُوا ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ በሸሪዓህ ቂያሥ ከሚደረጉት እሳቦት አንዱ “ሚራስ” ነው፥ “ሚራስ” مِيرَاثٌ የሚለው ቃል “ወሪሰ” وَرِثَ ማለትም “ወረሰ” ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን “ውርስ” ማለት ነው፥ ይህም ውርስ የሟች መብት፣ ግዴታ እና ሀብት በሕይወት ላሉት ወራሾቹ የሚተላለፍበት መንገድ ነው። ለምሳሌ የውርስ ሒሳብ ሚስት ባል ቢሞትባት ልጅ ካላቸው አንድ ስምንተኛ ⅛ ልጅ ከሌላቸው አንድ አራተኛ ¼ ትወርሳለች፦ 4፥12 ለእናንተም ልጅ ባይኖራችሁ ከተዋችሁት ንብረት ለእነርሱ ለሚስቶች "ከአራት አንድ" አላቸው፡፡ ለእናንተም ልጅ ቢኖራችሁ ከተዋችሁት ንብረት ለእነርሱ "ከስምንት አንድ" አላቸው። ይህም በእርሷ ከምትናዘዙባት ኑዛዜ ወይም ከዕዳ በኋላ ነው፡፡ وَلَهُنَّ الرُّبُعُ مِمَّا تَرَكْتُمْ إِن لَّمْ يَكُن لَّكُمْ وَلَدٌ ۚ فَإِن كَانَ لَكُمْ وَلَدٌ فَلَهُنَّ الثُّمُنُ مِمَّا تَرَكْتُم ۚ مِّن بَعْدِ وَصِيَّةٍ تُوصُونَ بِهَا أَوْ دَيْنٍ አንዲት ሴት ግማሽ አንድ ሁለተኛ ½ ሁለት እና ሦስት ሴት ልጆች ሁለት ሦስተኛ ⅔ ይወርሳሉ፦ 4፥11 ከሁለት በላይም የኾኑ ሴቶች ብቻ ቢኾኑ ለእነርሱ ሟቹ ከተወው ውርስ ድርሻ ሁለት ወይም ከሦስት ሁለት እጁ አላቸው፥ አንዲትም ብትኾን ለእርሷ ግማሹ አላት፡፡ ፡፡ يُوصِيكُمُ اللَّهُ فِي أَوْلَادِكُمْ ۖ لِلذَّكَرِ مِثْلُ حَظِّ الْأُنثَيَيْنِ ۚ فَإِن كُنَّ نِسَاءً فَوْقَ اثْنَتَيْنِ فَلَهُنَّ ثُلُثَا مَا تَرَكَ ۖ وَإِن كَانَتْ وَاحِدَةً فَلَهَا النِّصْفُ እናት እና አባት ከስድስት እጅ አንድ እጅ ⅙ ያገኛሉ፦ 4፥11 ለአባት እና ለእናቱም ለእርሱ ልጅ እንዳለው ከሁለቱ ለእያንዳንዱ ከስድስት አንድ አላቸው፡፡ وَلِأَبَوَيْهِ لِكُلِّ وَاحِدٍ مِّنْهُمَا السُّدُسُ مِمَّا تَرَكَ إِن كَانَ لَهُ وَلَدٌ ۚ በእነዚህ አናቅጽ መሠረት ⅛ ለሚስት፣ ½ ለአንድ ሴት ልጅ ⅙ ለአባት፣ ⅙ ለእናት ነው፥ ለምሳሌ፦ አንድ አውራሽ 100,000 ብር ቢኖረው ⅛ ለሚስት፣ ½ ለአንድ ሴት ልጅ፣ ⅙ ለአባት፣ ⅙ ለማካፈል ሒሣቡን እናስላው! ነጥብ አንድ "ትርፍ" አንዲት ሴት ልጅ ወራሽ ስትሆን፦ 1. ⅛ ለሚስት ሲሆን 100,000 × 1 ÷ 8 = 12,500 ይሆናል። 2. ½ ለአንድ ሴት ልጅ ሲሆን 100,000 × 1 ÷ 2 = 50,000 ይሆናል። 3. ⅙ ለአባት ሲሆን 100,000 × 1 ÷ 6 = 16,666 ይሆናል። 4. ⅙ ለእናት ሲሆን 100,000 × 1 ÷ 6 = 16,666 ይሆናል። ሁሉም ሲደመር፦ 1. 12,500 2. 50,000 3. 16,666 4. 16,666 ----------------------------- =95,832 ሲመጣ ከ100,000 ውርሱ ላይ ተከፋፍሎ 4,168 ትርፍ ይመጣል፥ ስሌቱ 100,000 - 95,832= 4,168 ይሆናል። "አስል" أَصْل የሚለው ቃል "አሶለ" أَصَّلَ ማለትም "መሠረተ" ከሚለው ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "መሠረት" ማለት ነው፥ በሒሣብ የክፍፍል"Fraction" ሕግ ትንሹ የጋራ ብዜት"Lowest Common Multiple(LCM) ሲሆን በዐረቢኛ "አስል" أَصْل ይባላል። ስለዚህ ⅛ + ½ + ⅙ + ⅙ = 24 ነው፥ በዚህ ስሌት ትንሹ የጋራ ብዜት 24 ነው። በመሠረታዊ ጉዳይ የመጣ ነገር "አስሊይ" أَصْلِيّ ሲባል መሠረታዊ ሂደቱ ደግሞ "ኢሥቲእሷል" اِسْتِئْصَال ይባላል። በኢሥቲእሷል ሕግ ⅛ ለሚስት፣ ½ ለአንዲት ሴት ልጅ፣ ⅙ ለአባት፣ ⅙ ለእናት ሲሆን፦ 1. ሚስት 24 × 1 ÷ 8 = 3 2. ሴት ልጅ 24 × 1 ÷ 2 = 12 3. አባት 24 × 1 ÷ 6 = 4 4. እናት 24 × 1 ÷ 6 = 4 ነው። 3 + 12 +4 + 4 = 23 ሲሆን 1 ትርፍ ይኖራል። 24 - 23 = 1 ይሆናል። ነቢያችንም"ﷺ"፦ "ከፈራኢድ የወጣውን ለቅርብ ወንድ ልጅ ይሄዳል" ብለውናል፦ ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 23, ሐዲስ 4 ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "በአሏህ መጽሐፍ በተቀመጠው በአህለል ፈራኢድ መካከል በትክክል አካፍሉ! ከፈራኢድ የወጣውን ለቅርብ ወንድ ልጅ ይሄዳል"። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم " اقْسِمُوا الْمَالَ بَيْنَ أَهْلِ الْفَرَائِضِ عَلَى كِتَابِ اللَّهِ فَمَا تَرَكَتِ الْفَرَائِضُ فَلأَوْلَى رَجُلٍ ذَكَرٍ " "ፈሪዳህ" فَرِيضَة ማለት በዚህ ዐውድ "ክፍፍል"Fraction" ማለት ሲሆን "ፈሪዳህ" فَرِيضَة ለሚለው ብዙ ቁጥር ደግሞ "ፈራኢድ" فَرَائِضِ ነው፥ "ዒልመል ፈራኢድ" عِلْم الْفَرَائِض ማለት "የውርስ ክፍፍል ሕግ" ማለት ነው፥ ስለዚህ ከ 100,000 ላይ የተረፈው 4,168 ወይም ከ 24% ላይ 1% ትርፍ ለቅርብ ወንድ ልጅ ይሆናል።
Открыть в Telegram"እኔ መኪና አለኝ፥ ወደ መኪናዬ እሄዳለው" እያልኩኝ ከዚያ ሰዎች "መኪና ነህ" አሉኝ። ኢየሱስ፦ "እኔ አምላክ አለኝ፥ ወደ አምላኬ እሄዳለው" እያለ ከዚያ ሰዎች "እርሱ አምላክ ነው" አሉት። እኔን "መኪና ነህ" ያሉኝ እና ኢየሱስን "አምላክ ነህ" ያሉት ጤነኞች ናቸው? የክርስትና ውዝግብ
Открыть в Telegramበጀነት መዋለድ አለን? በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 39፥34 “ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ የሚሹት ሁሉ አለላቸው፡፡ ይህ የበጎ አድራጊዎች ምንዳ ነው”፡፡ لَهُم مَّا يَشَاءُونَ عِندَ رَبِّهِمْ ۚ ذَٰلِكَ جَزَاءُ الْمُحْسِنِينَ አምላካችን አሏህ ለወንድ እና ለሴት ባሮቹ በእርሱ ያመኑትን ጀነት ያስገባቸዋል፥ በጀናህ ውስጥ የሚሹት ሁሉ አለላቸው፦ 4፥124 ከወንድ ወይም ከሴት እርሱ አማኝ ኾኖ ከበጎ ሥራዎች አንዳችን የሚሠራም ሰው እነዚያ ገነትን ይገባሉ፡፡ በተምር ፍሬ ላይ ያለችን ነጥብ ያክል እንኳ አይበደሉም፡፡ وَمَن يَعْمَلْ مِنَ الصَّالِحَاتِ مِن ذَكَرٍ أَوْ أُنثَىٰ وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَأُولَٰئِكَ يَدْخُلُونَ الْجَنَّةَ وَلَا يُظْلَمُونَ نَقِيرًا 39፥34 “ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ የሚሹት ሁሉ አለላቸው፡፡ ይህ የበጎ አድራጊዎች ምንዳ ነው”፡፡ لَهُم مَّا يَشَاءُونَ عِندَ رَبِّهِمْ ۚ ذَٰلِكَ جَزَاءُ الْمُحْسِنِينَ 16፥31 “ለእነርሱም በውስጧ የሚሹት ሁሉ አላቸው፡፡ እንደዚሁ አላህ ጥንቁቆችን ይመነዳል”፡፡ لَهُمْ فِيهَا مَا يَشَاءُونَ ۚ كَذَٰلِكَ يَجْزِي اللَّهُ الْمُتَّقِينَ “ተቅዋእ” تَقْوَى ማለት “አሏህ መፍራት” ማለት ሲሆን አሏህን የሚፈሩ ወንድ እና ሴት “ሙተቂን” مُتَّقِين ይባላሉ፥ ለሙተቂን በጀነት ውስጥ ከአሏህ የኾነ ውዴታ ጥንዶች ማግኘታቸው አካላዊ ጸጋ ናቸው፦ 44፥54 ነገሩ እንደዚሁ ነው፥ ሁር ዒን እናጠናዳቸዋለን፡፡ كَذَٰلِكَ وَزَوَّجْنَاهُم بِحُورٍ عِينٍ አማንያን በጀነት ውስጥ የሚፈልጉት ሁሉ አለ ማለት ግን ጀነት ውስጥ መዘወጅ እንጂ ልጅ መውለድ የለም፦ ጃሚዒ አት ቲርሚዚይ መጽሐፍ 38 ሐዲስ 41 "አቢ ረዚን አል ዑቀይሊይ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "የጀናህ ባለቤቶች በጀናህ ውስጥ ልጅ አይወልዱም።"።عَنْ أَبِي رَزِينٍ الْعُقَيْلِيِّ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ " إِنَّ أَهْلَ الْجَنَّةِ لاَ يَكُونُ لَهُمْ فِيهَا وَلَدٌ " . አሏህ የመውለድ ፍላጎት ስለማይሰጣቸው አይወልዱም፥ ፍላጎት ግን ሰቷቸው ልጅን በጀነት ቢፈልጉ እንደ ፍላጎታቸው የሕፃኑ እርግዝናው፣ መወለዱ እና እድገቱ በአንድ ሰዓት ውስጥ ይሆናል፦ ጃሚዒ አት ቲርሚዚይ መጽሐፍ 38 ሐዲስ 41 "ኢብኑ ሠዒድ አል ኹድሪይ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ሙእሚን ልጅን በጀነት ቢፈልግ እንደ ፍላጎቱ እርግዝናው፣ መወለዱ እና እድገቱ በአንድ ሰዓት ውስጥ ይሆናል።"። عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم " الْمُؤْمِنُ إِذَا اشْتَهَى الْوَلَدَ فِي الْجَنَّةِ كَانَ حَمْلُهُ وَوَضْعُهُ وَسِنُّهُ فِي سَاعَةٍ كَمَا يَشْتَهِي " "ሐምል ሁ" حَمْلُهُ "ወድዑ ሁ" وَضْعُهُ "ሢንን ሁ" سِنُّهُ የሚለው የሚጠጋው ወደ ሕፃኑ ነው፥ "ሢንን ሁ" سِنُّهُ ማለት "ዕድገቱ" ማለት ሲሆን የሚያድገው ሕፃኑ ነው። "ወለድ" وَلَد ማለት "ልጅ" ማለት ሲሆን "ሁ" የሚለው ተሳቢ ተውላጠ ስም "ወለድ" وَلَد የሚለውን ተክቶ የመጣ ነው፥ ይህ ሐዲስ ገሪብ ቢሆንም አሏህ ለሙእሚን በሰጠው ፍላጎት የሚፈልጉት ሁሉ እንዳለ ለማመላከት የገባ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያውን ይወፍቃቸው! ለእኛም ኢሥቲቃማውን ይወፍቀን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Открыть в Telegramፍጡር አታምልኩ በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 3፥47 ነገሩ እንዳልሽው ነው፡፡ አሏህ የሚሻውን ይፈጥራል፥ አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ "ኹን" ይለዋል ወዲውኑም ይኾናል" አላት፡፡ قَالَ كَذَٰلِكِ اللَّهُ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ የነገረ ክርስቶስ ጥናት"Christology" ላይ "ታሕታይ ነገረ ክርስቶስ ጥናት"Lower Christology" ማለት በአንፆኪያ የትርጓሜ ትምህርት ቤት ከሰውነት ወደ አምላክነት የሚደረግ አሪስጣጣሊሳዊ ፍልስፍና"Aristotelian Philosophy" መሠረት ያረገ ጥናት ሲሆን ሙግት አዋቅሮ እና አደራጅቶ ድባቅ ለማስገባት ከታሕታይ ነገረ ክርስቶስ መጀመሩ ጥሩ ነው። አንድ አምላክ አለ፥ ይህ አንድ አምላክ ሰውን በማኅፀን የሚፈጥር ነው፦ ኢዮብ 31፥15 እኔን በማኅፀን የፈጠረ እርሱንስ የፈጠረው አይደለምን? በማኅፀንስ ውስጥ የሠራን አንድ አይደለንምን? πότερον οὐχ ὡς καὶ ἐγὼ ἐγενόμην ἐν γαστρί, καὶ ἐκεῖνοι γεγόνασι; γεγόναμεν δὲ ἐν τῇ αὐτῇ κοιλίᾳ. አንዱ አምላክ ከአዳም የጎን አጥንት ያለ ወንድ ሕዋስ እና ያለ ሴት ሕዋስ ሰው መፍጠር ከቻለ ከሴት የአብራክ ሕዋስ ያለ ወንድ ሕዋስ ኢየሱስን መፍጠር ችሏል። ኢየሱስ በትንቢት መነጽር "ከማኅፀን የሠራኝ" በማለት ይናገራል፦ ኢሳይያስ 49፥5 አሁንም በሐሼም ዓይን ከብሬአለሁና፣ አምላኬም ጕልበት ሆኖኛልና፣ ያዕቆብን ወደ እርሱ እንድመልስ እስራኤልንም ወደ እርሱ እንድሰበስብ ባሪያ እሆነው ዘንድ ከማኅፀን የሠራኝ ሐሼም እንዲህ ይላል። וְעַתָּ֣ה׀ אָמַ֣ר יְהוָ֗ה יֹצְרִ֤י מִבֶּ֙טֶן֙ לְעֶ֣בֶד ל֔וֹ לְשׁוֹבֵ֤ב יַֽעֲקֹב֙ אֵלָ֔יו וְיִשְׂרָאֵ֖ל לֹא יֵאָסֵ֑ף וְאֶכָּבֵד֙ בְּעֵינֵ֣י יְהוָ֔ה וֵאלֹהַ֖י הָיָ֥ה עֻזִּֽי׃ የግዕዙ ላይ "ዘፈጠረኒ በውስጠ ከርሰ እምየ" ሲለው ትርጉሙ "ከእናቴ ማሕፀን የፈጠረኝ" ማለት ነው፥ የእነርሱ የሚሊኒየሙ ላይም በግልጽ "የፈጠረኝ" ብለው አስቀምጠውታል። ኢሳይያስ 49፥5 ላይ "የፈጠረኝ" የሚለው ተናጋሪ ኢየሱስ እንደሆነ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ ተናግሯል፦ ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 76 ቁጥር 21 "ዳግመኛም የያዕቆብን ወገን አንድ ለማድረግ እስራኤልን ለማዳን አገልጋይ እሆነው ዘንድ "በማኅፀን የፈጠረኝ" እግዚአብሔር እርሱ ይወደኛልና"። ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 76 ቁጥር 22 "ይህ በቅድስት ድንግል ማርያም የተፈጠረበት ምክንያት እስራኤልን ብቻ ለማዳን አይደለም፥ እስከ ምድር ዳርቻ ያሉን አሕዛብን ለማዳን ነው እንጂ"። ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 76 ቁጥር 19 "ዳግመኛም መድኅን ክርስቶስ ከድንግል ስለመወለዱ በኢሳይያስ አፍ “ብዙ ሥራ እሠራ ዘንድ የያዕቆብንም ወገን አጸና ዘንድ አስራኤልንም አንድ አደርግ ዘንድ ከድንግል ማኅፀን "ተፈጠርኩ" አለ"። ዐማርኛው ላይ "ተጸነስኩ" ቢሉትም ግዕዙ ላይ "ተፈጥረ" ብሎ አስቀምጠውታል፥ "ፍጡረ" ማለት "ፍጡር" ማለት ነው። ስለዚህ ኢየሱስ ከድንግል ማርያም የተፈጠረ ፍጡር ነው፦ ፨ ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 56 ቁጥር 21 "ሰው ስለሆነ "ፍጡር" ቢባል ወዲህ በር ተባለ"። ፨ ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 124 ቁጥር 19 “ወዲህም ከሴት በሥጋ ስለተወለደ "ፍጡር" እንላለን”። ዐማርኛ ላይ "ሰው" ብለው ቢያስቀምጥም ግዕዙ "ፍጡረ" ብሎ አስቀምጦታል፦ "ወዓዲመ ንብሎ "ፍጡረ" እስመ ውእቱ ተወልዶ በሥጋ እም ብእሲት"። ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ በእርግጥ በሥጋ ፍጡር ነው፦ ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 124 ቁጥር 29 "ቃል እርሱ በሥጋ ፍጡር እና ሟች ነው"። ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 35 ቁጥር 6 "ዳግመኛም ሥጋ ስለሆነ ፍጡር ይባላል"። ግዕዙ፦ "ወዓዲመ ይትበሃል "ፍጡረ" በእንተ ዘኮነ ሥጋ" ይለዋል፥ ማኅፀን ውስጥ የተፈጠረው እና የተወለደው መለኮት ሳይሆን ፍጡር ነው፦ ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 38 ቁጥር 25 "መለኮት ፍጡር አይደለም፥ ሥጋ ግን ፍጡር ነው"። ግዕዙ፦ "መለኮትሰ ኢ ፍጡር ውእቱ ወሥጋሰ ፍጡር ውእቱ" ይለዋል፥ "ሥጋ" ሲባል "ሰው" ማለት እንጂ መንፈስ እና ነፍስ የሌለው ቁርበት እና ቅርፊት ማለት አይደለም። ፍጥረትን የፈጠረ አምላክ ነገርን ይሠራል እንጂ እርሱ አይሠራም፥ "ፍጡር" ለተፈጠረ ነገር እንጂ አምላክ አይፈጠርም። ሐሼም ለኢሳይያስ ከመናገሩ በፊት አምላክ አልተሠራም፥ ለኢሳይያስ ከመናገሩ በኃላ አምላክ አይሠራም፦ ኢሳይያስ 43፥10 ከእኔ በፊት "አምላክ አልተሠራም" ከእኔም በኋላ አይሆንም። לְפָנַי֙ לֹא־נ֣וֹצַר אֵ֔ל וְאַחֲרַ֖י לֹ֥א יִהְיֶֽה׃ס "አምላክ አይሠራም" እያለ "አምላክ በሥጋ ተሠራ፣ ተፈጠረ፣ ፍጡር ነው" ማለት ጤናማ ትምህርት አይደለም፥ ሃይማኖተ አበው ላይ "ኢየሱስ ፍጡር ነው" የሚል በቁና ሰፍሮ እያለ "ፍጡር አይደለም፥ ፍጡር አይባልም" ማለት "አሞኛችሁ ዘንድ ዓይናችሁን ጨፍኑ" ማለት ነው። ኢየሱስ ሰው ከሆነ በሙግት አወቃቀር ስሙር ሙግት"Valid Argument" እንደዚህ ነው፦ 1. የሙግት ነጥብ"Premise" አንድ፦ "ሰው ሁሉ ፍጡር ነው"። 2. የሙግት ነጥብ"Premise" ሁለት፦ "ኢየሱስ ሰው ነው"። 3.ድምዳሜ"Conclusion"፦ ስለዚህ ኢየሱስ ፍጡር ነው። መርየም አሏህን፦ "ጌታዬ ሆይ! "ወንድ ያልነካኝ ስኾን ለእኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል" አለች፦ 3፥47 "ጌታዬ ሆይ! "ወንድ ያልነካኝ" ስኾን ለእኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል" አለች፡፡ قَالَتْ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِي وَلَدٌ وَلَمْ يَمْسَسْنِي بَشَرٌ አሏህም በመልአኩ፦ "ነገሩ እንዳልሽው ነው፡፡ አሏህ የሚሻውን ይፈጥራል፥ አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ "ኹን" ይለዋል ወዲውኑም ይኾናል" አላት፦ 3፥47 ነገሩ እንዳልሽው ነው፡፡ አሏህ የሚሻውን ይፈጥራል፥ አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ "ኹን" ይለዋል ወዲውኑም ይኾናል" አላት፡፡ قَالَ كَذَٰلِكِ اللَّهُ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ አሏህ ያለ ወንድ እና ያለ ሴት ዘር አደምን ከአፈር ከፈጠረ እና ሐዋን ያለ ሴት ዘር ከአደም አጥንት ከፈጠረ ዒሣን ካለ ወንድ ዘር ከመርየም ብቻ መፍጠር ይችላል፥ ዒሣ በድንግልና መፀነሱ እና እናቱ መርየም በድንግልና መፅነሷ በእርግጥ ተአምር ናቸው፦ 23፥50 የመርየምን ልጅ እና እናቱን ተአምር አደረግናቸው፡፡ وَجَعَلْنَا ابْنَ مَرْيَمَ وَأُمَّهُ آيَةً 21፥91 እርሷን እና ልጅዋን ለዓለማት ተአምር ያደረግናትን አስታውስ፡፡ وَجَعَلْنَاهَا وَابْنَهَا آيَةً لِّلْعَالَمِينَ ክርስቲያኖች ሆይ! ከማርያም ማኅፀን የተፈጠረውን ፍጡር አታምልኩ! ወደ አሏህ ኑ እና እርሱን በብቸኝነት እናምልክ፥ በዲኑል ኢሥላም የሚመለከው በፈጣሪነቱ ፍጡርነት የሌለበት ኻሊቁ ብቻ ነው። ኻሊቁና አሏህ ሂዳያውን ይወፍቃቸው! ለእኛም ኢሥቲቃማውን ይወፍቀን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Открыть в Telegramሰው አያነብም ብለው ይጫወቱበታል። "ፈጣሪ እና ፍጡር" አይባልም ይሉና ግን በግዕዝ "ፈጣሪ ወፍጡር" ይባላል ይሉናል። ለመሆኑ ሰው ግዕዝ አያውቅም እያላችሁ ለምን በሕዝቡ ትጫወታላችሁ? "ወ" ማለት በግዕዝ እኮ "እና" ማለት ነው፦ ማቴዎስ 2፥21 እርሱም ተነሥቶ ሕፃኑን እና እናቱን ያዘና ወደ እስራኤል አገር ገባ። ግዕዙ፦ ወተንሢኦ ነሥአ ሕፃነ "ወ"እሞ ወቦአ ውስተ ምድረ እስራኤል። ይህንን ከተረዳን "ፈጣሪ ወፍጡር" ማለት "ፈጣሪ እና ፍጡር" ማለት ነው፦ ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 124 ቁጥር 18 "እኛስ ይህን አንድ ወልድን አምላክ እና ሰው፣ ገዥ እና ተገዥ፣ ሠዋዒ እና ተሠዋዒ፣ ፍጡር እና ፈጣሪ ሆኖ እናገኘዋለን"። "ወ" ማለት በግዕዝ "እና" ማለት ከሆነ "ፍጡር ወፈጣሪ" ማለት "ፍጡር እና ፈጣሪ" ማለት ነው። ፈጣሪ አምላክ ሁሉን ዐዋቂ፣ ሁሉን ቻይ፣ የማይሞት፣ የማይተኛ ነው፥ ፍጡር ሰው ደግሞ "ሁሉን ዐላዋቂ፣ ሁሉን የማይችል፣ የሚሞት፣ የሚተኛ ነው። ሁሉን ዐዋቂ እና ሁሉን ዐላዋቂ፣ ሁሉን ቻይ እና ሁሉን የማይችል፣ የማይሞት እና የሚሞት፣ የማይተኛ እና የሚተኛ ማለት እርስ በእርስ ግጭት አይደለምን? ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom
Открыть в Telegramፍትወት በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። 17፥32 ዝሙትንም አትቅረቡ! እርሱ በእርግጥ መጥፎ ሥራ ነውና፥ መንገድነቱም ከፋ። وَلَا تَقْرَبُوا الزِّنَىٰ ۖ إِنَّهُ كَانَ فَاحِشَةً وَسَاءَ سَبِيلًا "ዚና" زِّنَىٰ የሚለው ቃል "ዘነ" زَنَى ማለትም "ዞሞተ" "ተመኘ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ዝሙት"Fornication" "አምሮት" "ፍትወት"Lust" ማለት ነው፥ ዚና "ሸህዋህ" شَهْوَة በሚል ይመጣል። አሏህ በአደም ልጅ ላይ የግድ ማድረግ ያለበትን ከፍትወት ክፍሉን ጽፏል፥ ይህም የዓይን ፍትወት ማየት እና የምላስ ፍትወት መናገር ነው፦ ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 46 ሐዲስ 32 አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "አሏህ በአደም ልጅ ላይ የግድ ማድረግ ያለበትን ከፍትወት ክፍሉን ጽፏል፥ ይህም የዓይን ፍትወት ማየት እና የምላስ ፍትወት መናገር ነው። የነፍስ ፍላጎት እና ምኞት ያ ሊተገበር ወይም ላይተገበር ይችላል"። قَالَ أَبُو هُرَيْرَةَ أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ " إِنَّ اللَّهَ كَتَبَ عَلَى ابْنِ آدَمَ حَظَّهُ مِنَ الزِّنَى أَدْرَكَ ذَلِكَ لاَ مَحَالَةَ فَزِنَى الْعَيْنَيْنِ النَّظَرُ وَزِنَى اللِّسَانِ النُّطْقُ وَالنَّفْسُ تَمَنَّى وَتَشْتَهِي وَالْفَرْجُ يُصَدِّقُ ذَلِكَ أَوْ يُكَذِّبُهُ " "ፍትወት" የሚለው የግዕዝ ቃል እራሱ "ጎምጅታ" "አምሮት" "ምኞት" ማለት ነው፥ "አላ አሐዱ አሐዱ ይትሜከር በፍትወተ እንቲኣሁ ወይወፅእ ኀቤሃ ወይደነግፅ" ሲል ይህንን ታሳቢ አርጎ ነው፦ ያዕቆብ 1፥14 ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ "ምኞት" ሲሳብ እና ሲታለል ይፈተናል። እዚህ ጥቅስ ላይ "ምኞት" ለሚለው በግዕዙ የገባው ቃል "ፍትወት" ነው፥ ፍትወት በተፈጥሮ የተቀመጠ ነገር ሲሆን ሊተገበር ወይም ላይተገበር ይችላል። የተራክቦ ፍትወት አሏህ በሁሉም ላይ እንድናደርግ የጻፈው ነው፥ ይህንን የተራክቦ ፍትወት በትዳር ካደረግን ሐላል ሲሆን ከትዳር ውጪ ካደረግነው ግን ሐራም ነው። የተራክቦ ፍትወት ሊተገበር ላይተገበር የሚችል ነገር ሲሆን ያለ ትዳር በሐራም ተፈልጎ እስካልተሠራ ድረስ መላእክት አይጽፉትም። በሐራም ቢሠራት ግን ቢጤዋን ይጽፋሉ፥ ነገር ግን አንድ ሰው ለአሏህ ሲል በሐራም ከመሥራት ቢመለስ ለእርሱ አንድ ሐሠናህ ይጻፍለታል። በሐላል የፍትወት ተራክቦ መልካም ሥራ ነውና አንድ ሰው በሐላል ለመሥራት በፈለገ ጊዜ ግን ካልሠራት አንድ ሐሠናህ ይጻፍለታል፥ በሐላል ቢሠራ ግን ለእርሱ ከአስር እስከ ሰባ ሐሠናት ይጻፍለታል፦ ኢማም በኻርይ መጽሐፍ 97, ሐዲስ 126 አቢ ሁራይራህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" አሉ፦ "አሏህ ለመላእክት፦ "ባሪያዬ መጥፎ ሥራ ለመሥራት በፈለገ ጊዜ እስካልሠራት ድረስ አትጻፏት፣ ቢሠራት ግን ቢጤዋን ጻፏት፣ ነገር ግን ለእኔ ሲል እርሷን ከመሥራት ቢመለስ ለእርሱ አንድ ሐሠናህ ጻፉለት፣ መልካም ሥራ ለመሥራት በፈለገ ጊዜ ግን ካልሠራት አንድ ሐሠናህ ጻፉለት፣ ቢሠራት ግን ለእርሱ ከአስር እስከ ሰባ ሐሠናት ጻፉለት" ይላቸዋል"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ " يَقُولُ اللَّهُ إِذَا أَرَادَ عَبْدِي أَنْ يَعْمَلَ سَيِّئَةً فَلاَ تَكْتُبُوهَا عَلَيْهِ حَتَّى يَعْمَلَهَا، فَإِنْ عَمِلَهَا فَاكْتُبُوهَا بِمِثْلِهَا وَإِنْ تَرَكَهَا مِنْ أَجْلِي فَاكْتُبُوهَا لَهُ حَسَنَةً وَإِذَا أَرَادَ أَنْ يَعْمَلَ حَسَنَةً فَلَمْ يَعْمَلْهَا فَاكْتُبُوهَا لَهُ حَسَنَةً، فَإِنْ عَمِلَهَا فَاكْتُبُوهَا لَهُ بِعَشْرِ أَمْثَالِهَا إِلَى سَبْعِمِائَةٍ ስለዚህ "ሰው የግድ ዝሙት እንዲያደርግ ተጽፎበታል" የሚል የሚሽነሪዎች የሐሠት ክስ"False Allegation" እንዲህ ድባቅ ይገባል፥ ሐዲሱ ላይ "ዚና" زِّنَىٰ ሲል ወንድ እና ሴት በተራክቦ ከትዳር ውጪ የሚያረጉት ዝሙት ሳይሆን በግልጽ እንደተቀመጠው የዓይን ፍትወት ማየት እና የምላስ ፍትወት እንዲሁ ያ ሊተገበር ወይም ላይተገበር የሚችል የነፍስ ፍላጎት እና ምኞት ነው። በእርግጥ ወንድ እና ሴት በተራክቦ ከትዳር ውጪ የሚያረጉት ዝሙት መጥፎ ሥራ ነውና መጥፎን የሠራ ሰው ብጤዋን ይቀጣል፥ ወንድ እና ሴት በተራክቦ ከትዳር ውጪ የሚያረጉት ዝሙትንማ መጥፎ ሥራ ስለሆነ እና ስለሚያስቀጣ አሏህ "አትቅረቡ" ብሎ ከልክሎናል፦ 40፥40 መጥፎን የሠራ ሰው ብጤዋን እንጂ አይቀጣም፡፡ مَنْ عَمِلَ سَيِّئَةً فَلَا يُجْزَىٰ إِلَّا مِثْلَهَا 17፥32 ዝሙትንም አትቅረቡ! እርሱ በእርግጥ መጥፎ ሥራ ነውና፥ መንገድነቱም ከፋ። وَلَا تَقْرَبُوا الزِّنَىٰ ۖ إِنَّهُ كَانَ فَاحِشَةً وَسَاءَ سَبِيلًا ወንድ እና ሴት በተራክቦ ከትዳር ውጪ የሚያረጉት ዝሙት እንድናደርገው ተጽፎ ቢሆን ኖሮ "አትቅረቡ" ብሎ አይከለክልም ነበር፥ ትእዛዙን ስንተላለፍም አንቀጣም ነበር። "አትቅረቡ" የሚል ክልክለላ የሚሰጠው መቅረብ እና አለመቅረብ ነጻ ፈቃድ እና ምርጫ ያለው አካል ነው፥ ወንድ እና ሴት በተራክቦ ከትዳር ውጪ የሚያረጉት ዝሙት እንድናደርገው የተጻፈ ሳይሆን መንገድነቱም የከፋ ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛን ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Открыть в Telegramየዝሙት ልጅ በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። 35፥18 ኃጢአትን ተሸካሚ ነፍስ የሌላዋን ሸክም አትሸከምም፡፡ وَلَا تَزِرُ وَازِرَةٌ وِزْرَ أُخْرَىٰ "ኸጧእ" خَطَأ "ዒላማን መሳት" "ማመፅ" "ዓመፅ" "ኃጢአት" ማለት ነው፥ ይህ ቋንቋዊ ፍቺ ሲሆን ሸሪዓዊ ፍቺው ደግሞ "አሏህ ያዘዘውን መልካም ነገር አለማድረግ፥ የከለከለውን ክፉ ነገር ማድረግ" "ኸጧእ" خَطَأ ነው፦ 33፥5 በእርሱ በተሳሳታችሁበት ነገርም በእናንተ ላይ ኃጢአት የለባችሁም፥ ነገር ግን ልቦቻችሁ ዐውቀው በሠሩት ኃጢአት አለባችሁ፡፡ አሏህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡ وَلَيْسَ عَلَيْكُمْ جُنَاحٌ فِيمَا أَخْطَأْتُم بِهِ وَلَـٰكِن مَّا تَعَمَّدَتْ قُلُوبُكُمْ ۚ وَكَانَ اللَّهُ غَفُورًا رَّحِيمًا አንድ ሰው ከአሏህ መልእክት ደርሶት ይህንን መልእክት ዐውቆ እና ተረድቶ በዛ መልእክት ማመፅ፣ ማስተባበል፣ መካድ "ኃጢአት" ይሰኛል። በዲኑል ኢሥላም እያንዳንዱ ሰው የራሱ ኃጢአት ይሸከማል እንጂ ወላጅ ለልጅ ወይም ልጅ ለወላጅ ኃጢአትን አያሸከምም፦ 35፥18 ኃጢአትን ተሸካሚ ነፍስ የሌላዋን ሸክም አትሸከምም፡፡ وَلَا تَزِرُ وَازِرَةٌ وِزْرَ أُخْرَىٰ 17፥15 ተሸካሚ ነፍስ የሌላይቱን ኃጢአት አትሸከምም፡፡ መልእክተኛን እስከምንልክ ድረስ የምንቀጣ አይደለንም፡፡ وَلَا تَزِرُ وَازِرَةٌ وِزْرَ أُخْرَىٰ ۗ وَمَا كُنَّا مُعَذِّبِينَ حَتَّىٰ نَبْعَثَ رَسُولًا ይህ ሆኖ ሳለ ለያዥ እና ለገናዥ የማይመቹ ዘለሰኛ ሚሽነሪዎች እንደ ጭቃ እና ጨፈቃ ሊለያዩ የማይችሉትን ቁርኣን እና ሡናህ በቅጡ እና በአግባብ ሳያነቡት "ከዝሙተኛ የተወለደ ልጅ ጀነት አይገባም" ብለው ይህንን ሐዲስ ይጠቅሳሉ፦ ኢማን ኢብኑ ሒባን መጽሐፍ 13 ሐዲስ 3383 ዐብደሏህ ኢብኑ ዐምር እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "የዝሙት ልጅ፣ ጉረኛ፣ ዐመፀኛ እና የመጠጥ ሱሰኛ ወደ ጀናህ አይገባም"። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرٍو ، قَالَ : قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ : " لا يَدْخُلُ الْجَنَّةَ وَلَدُ زِنِيَةٍ ، وَلا مَنَّانٌ ، وَلا عَاقٌّ ، وَلا مُدْمِنُ خَمْرٍ ፨ ሲጀመር "ጁምሁሩል ዑለማእ" جُمْهُور العُلَمَاء የዚህን ሐዲስ ደረጃ ያስቀመጡት "ዶዒፍ" ضَعِيف ብለው ነው። ይህ ዐብደሏህ ኢብኑ ዐምር በትክክል የዘገበው ሐዲስ በሡነን ነሣኢይ ላይ ይገኛል፦ ሡነን ነሣኢይ መጽሐፍ 51 ሐዲስ 134 ዐብደሏህ ኢብኑ ዐምር እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ጉረኛ፣ ዐመፀኛ እና የመጠጥ ሱሰኛ ወደ ጀናህ አይገባም"። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرٍو، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ " لاَ يَدْخُلُ الْجَنَّةَ مَنَّانٌ وَلاَ عَاقٌّ وَلاَ مُدْمِنُ خَمْرٍ " . ፨ ሲቀጥል "የዝሙት ልጅ" ማለት "ዝሙተኛ" ማለት እንጂ "ከሁለት ከማገጡ ሰዎች የተወለደ ሕፃን ልጅ" ማለት አይደለም፥ ምክንያቱም "የዝሙት ልጅ" የሚለው "ጉረኛ" "ዐመፀኛ" እና "የመጠጥ ሱሰኛ" ከሚል ጋር ተደርድሮ የመጣ ቃል ነው። "ዝሙት" በራሱ የሚወልድ "ወላጅ" ስላልሆነ "የዝሙት ልጅ" ማለት "ዝሙተኛ" እንደሆነ በቀላሉ አንድ ናሙና እንመልከት፦ 2፥215 ምንን ለማንም እንደሚለግሱ ይጠይቁካል፥ "ከመልካም ነገር የምትለግሱት ለወላጆች፣ ለቅርብ ዘመዶች፣ ለየቲሞችም፣ ለድሆችም እና "ለ-"መንገደኞች" ነው" በላቸው፡፡ يَسْأَلُونَكَ مَاذَا يُنفِقُونَ ۖ قُلْ مَا أَنفَقْتُم مِّنْ خَيْرٍ فَلِلْوَالِدَيْنِ وَالْأَقْرَبِينَ وَالْيَتَامَىٰ وَالْمَسَاكِينِ وَابْنِ السَّبِيلِ እነዚህ አንቀጽ ላይ "መንገደኞች" ለሚለው የገባው ቃል "ኢብኑ አሥ ሠቢል" ٱبْن السَّبِيل ሲሆን "የመንገድ ልጅ" ማለት ነው፥ "መንገድ" በራሱ "ወላጅ" ስላልሆነ "የመንገድ ልጅ" ማለት "መንገደኛ" ማለት ከሆነ "የዝሙት ልጅ" ማለት "ዝሙተኛ" ማለት ነው፥ የመስኩ ሊሒቃን ያስቀመጡት በዚህ መልክ እና ልክ ነው። አንዲገባችሁ ከራሳችሁ መጽሐፍ ጥቂት ናሙናዎች እንመልከት፦ 2ኛ ሳሙኤል 12፥5 ዳዊትም በዚያ ሰው ላይ እጅግ ተቈጥቶ ናታንን፦ "ሕያው ሐሸምን! ይህን ያደረገ ሰው "የሞት ልጅ" ነው" አለው። 1ኛ ሳሙኤል 20፥31 "የእሴይም ልጅ በምድር ላይ በሕይወት በሚኖርበት ዘመን ሁሉ አንተ እና መንግሥትህ አትጸኑም፤ አሁንም "የሞት ልጅ" ነውና ልከህ አስመጣልኝ" አለው። ዳዊት በራሱ ላይ ሲፈርድ እራሱን "የሞት ልጅ" ሲል ሳኦል ዳዊትን "የሞት ልጅ" ሲል "ሟች" ማለታቸው እንጂ "ሞት" የሚባል "ወላጅ" እያሉ እንዳልሆነ ከተረዳን ዘንዳ ሐዲሱ "የዝሙት ልጅ" ሲል "ዝሙተኛ" ማለቱ እንጂ "ዝሙት" የሚባል "ወላጅ" እያለ እንዳልሆነ እና ከዝሙተኛ ስለሚወለድ ሕፃን እያወራ በፍጹም እንዳልሆነ በቀላሉ መረዳት ይቻላል። የመጨረሻ ናሙና፦ ዮሐንስ 17፥12 መጽሐፉም እንዲፈጸም ከ-"ጥፋት ልጅ" በቀር ከእነርሱ ማንም አልጠፋም። 2ኛ ተሰሎንቄ 2፥3 ክህደቱ አስቀድሞ ሳይመጣ እና የዓመፅ ሰው እርሱም "የጥፋት ልጅ" ሳይገለጥ፥ አይደርስምና። ይሁዳ እና ሐሳዌ መሢሕ "የጥፋት ልጅ" ሲባሉ "ጥፋተኛ" እየተባሉ እንጂ "ጥፋት" የሚባል "ወላጅ" እየተባለ እንዳልሆነ ከተረዳን ዘንዳ ሐዲሱ "የዝሙት ልጅ" ሲል "ዝሙተኛ" ማለቱ እንጂ "ዝሙት" የሚባል "ወላጅ" እያለ እንዳልሆነ እና ከዝሙተኛ ስለሚወለድ ሕፃን እያወራ በጭራሽ እንዳልሆነ በቀላሉ መረዳት ይቻላል። በተለይ "ዝሙት" እና "ጥፋት" ሰው የሚያደርጋቸው ድርጊት እንጂ "ወላጅ" ወይም "አድራጊ" እስካልሆኑ ድረስ የዝሙት ልጅ "ዝሙተኛ" የጥፋት ልጅ "ጥፋተኛ" በሚል መረዳት ይቻላል። የሙሥሊም ኩታ ገጠም ሙግት እንደ እናንተ ማረብረብ እና መወረብ ሳይሆን በእማኝነት እና በአስረጂነት መልስ መስጠት ነው፥ ገንጠል እና ዘንጠል አርጋችሁ ብታመጡትን በአጽንዖት እና በአንክሮት መልስ ሰተናል። "ተመልሷል" ካላችሁ እርማት ውሰዱ! "ተድበስብሷል" ካላችሁ ግብረ መልስ ስጡ! እንጂ ደብተራ እና ዳሞትራ አትሁኑብን! ዲኑል ኢሥላም በዕውቀት እና በሕይወት የሚኖር ሕይወት ስለሆነ ከብሽሽቅ እና ከአሹቅ ሕይወት ወጥታችሁ ወደዚህ ሕይወት እንድትመጡ ስንጠራችሁ ከታላቅ አክብሮት ጋር ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛን ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Открыть в Telegramበምዕራባውያ(አውሮፓውያን) መርሕ ሕፃን ልጅን መምታት በጥብቅ የተከለከለ ነው፥ ሕፃናትን የመታ ሰው የእስር እና የብር ቅጣት ይቀጣል። በባይብል ደግሞ ሕፃን ልጅ መምታት ሐላል ነው፦ ምሳሌ 23፥13-14 ሕፃንን ከመቅጣት ቸል አትበል፥ በበትር #ብትመታው አይሞትምና። በበትር #ትመታዋለህ፥ ነፍሱንም ትታደጋለህ። የምዕራባውያ መርሕ የምትከተሉ ክርስቲያኖች ይህንን ጥቅስ ስታነቡ ምን ይውጣችሁ ይሆን? ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom
Открыть в Telegramዋቄፈና አንዳንዴ አለመናገር መናገር ቢሆንና፥ ባለመናገር የምናገርውን መናገር ብንችል፥ መናገር ቆሞ አለመናገር መናገርን ባስረዳ ነበር። ሃይማኖትን ለፓለቲካ፣ ለጥቅም እና ለስልጣን ማትረፊያ ንግድ ባናደርግ ጥሩ ነው። ዋቄፈና ባዕድ አምልኮ ነው። ለፓለቲካ ስንል "ባህል ነው" "የተፈጥሮ ሥርዓት ነው" የምንል ሰዎች አሏህን እንፍራ! ዱንያህ አጭር ናት፥ ለዱንያህ ብለን አኺራችንን የሚያሳጣ ቃላት አንጠቀም። በማንበብ እራስዎን እና ማኅበረሰብዎን ከሺርክ፣ ከኩፍር፣ ከቢድዓ እና ከኒፋቅ ይጠብቁ! ዲናችንን ዕንወቅ! የበለጠ የሃይማኖት ንጽጽር ከፈለጉ እንግዲያውስ ጎራ ይበሉ፦ https://t.me/Wahidcom
Открыть в Telegramተጠየቅ ዘኦርቶዶክስ ትውፊት እውን ጌታ ዕውር ነውን? ዕውር ሆኖ ከዕውር ጋር ጉድጓድ ይገባልን? የአቡነ ሀብተ ማርያም ገድል ገጽ 163 "ጌታም፦ "ኃይል የምሰጥ እኔ ነኝ፤ ዕውር ዕውርን ቢከተል ሁለቱም ከጉድጓድ እንዲወድቁ #እኔ #ዕውር #ነኝ፤ በሰላም ወደ እውነተኛ መንገድ የምመራ አይደለሁም፤ ስሜ ብርሃን ነው። ማቴዎስ 15፥14 ተዉአቸው፤ ዕውሮችን የሚመሩ ዕውሮች ናቸው፤ #ዕውርም #ዕውርን #ቢመራው #ሁለቱም #ወደ #ጉድጓድ #ይወድቃሉ፡ አለ። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom
Открыть в Telegramተቀባዩ ፍጡር በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 5፥17 እነዚያ "አሏህ እርሱ የመርየም ልጅ አል መሢሕ ነው" ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ لَّقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ አንዱ አምላክ ሕይወትን፣ እስትንፋስን እና ሁሉንም ነገር ለሁሉ "ይሰጣልና፦ የሐዋርያት ሥራ 17፥25 እርሱም ሕይወትን፣ እስትንፋስን እና ሁሉንም ለሁሉ "ይሰጣልና። οὐδὲ ὑπὸ χειρῶν ἀνθρωπίνων θεραπεύεται προσδεόμενός τινος, αὐτὸς διδοὺς πᾶσι ζωὴν καὶ πνοὴν καὶ τὰ πάντα· አንዱ አምላክ ለኢየሱስ ሕይወትን ሰጥቶታል፦ ዮሐንስ 5፥26 አብ በራሱ ሕይወት እንዳለው እንዲሁ ደግሞ ለወልድ በራሱ እንዲኖር ሕይወት ሰጥቶታልና። ὥσπερ γὰρ ὁ Πατὴρ ἔχει ζωὴν ἐν ἑαυτῷ, οὕτως καὶ τῷ Υἱῷ ἔδωκεν ζωὴν ἔχειν ἐν ἑαυτῷ. "ሕይወትን ሰጥቶታልና" የሚለው ይሰመርበት! "ኤዶኬን ዞኤን" ἔδωκεν ζωὴν ማለት "ሕይወት ሰጠው" ማለት ነው። ወልድ በራሱ የራሱ ማንነት እንዲኖረው አብ ለወልድ የሰጠው ሕይወት ነው፥ "አብ ሕይወት አለው" ማለት "አብ ህልውና አለው" ማለት ከሆነ "ወልድ ሕይወት እንዲኖረው" ማለት "ወልድ ህልውና እንዲኖረው" ማለት ነው። እዚህ ዐውድ ላይ "ሕይወት" የተባለው የራስ ሃልዎት"Self existence" ነው፥ እያንዳንዱ ማንኛውም ማንነት የራሱ ሃልዎት አለው። ኢየሱስ በባዶነት የተቀደመ፣ ሕይወት አልባ የነበረ፣ መነሻ እና ጅማሮ ያለው ነው፥ መነሻ እና ጅማሮ ያለው ነገር ደግሞ ፍጡር ነው። "ሁሉንም ነገር ለሁሉ "ይሰጣል" በተባለው መሠረት አንዱ አምላክ ለኢየሱስ ሁሉን ነገር ተሰቶታል፦ ሉቃስ 10፥22 ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል። ኢየሱስ ተቀባይ ፍጡር ስለሆነ ሁሉ ነገር በስጦታ እና በጸጋ ያገኘው ስለሆነ የእርሱ የሆነው ነገር ሁሉ ከአብ የተሰጠው የአብ ነው፦ ዮሐንስ 17፥10 የእኔም የሆነ ሁሉ የአንተ ነው፥ የአንተውም የእኔ ነው። "የእኔም የሆነ ሁሉ የአንተ ነው" የሚለው ይሰመርበት! የመፈወስ፣ ኃጢአትን ይቅር ማለት፣ የማስተማር ሥልጣን ሁሉ በስጦታ ያገኘው ነው፦ ማቴዎስ 28፥18 ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ "ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ"። "ሥልጣን ሁሉ ተሰጠኝ" ካለ በምድር ላይ ኃጢአትን ያስተሰርይ ዘንድ ለሰው ልጅ ሥልጣን የሰጠው አምላክ ነው፦ ማቴዎስ 9፥8 ሕዝቡም አይተው ተደነቁ፥ ለሰውም እንዲህ ያለ ሥልጣን የሰጠ አምላክን አከበሩ። ማቴዎስ 9፥6 ነገር ግን በምድር ላይ ኃጢአትን ያስተሰርይ ዘንድ ለሰው ልጅ ሥልጣን እንዳለው እንድታውቁ። የማቴዎስ ጸሐፊ "ለሰውም እንዲህ ያለ ሥልጣን የሰጠ አምላክን አከበሩ" በማለት አምላክ ኃጢአትን የማስተሰረይ ሥልጣን ለሰው እንደሰጠ ተናገረ፥ ኢየሱስም እራሱን "የሰው ልጅ" በማለት ያስቀምጣል። ኢየሱስ ሲያደርገው የነበረው ሥራ ሁሉ ለመልእክተኛነቱ እና ለነቢይነቱ ማስረጃ ይሆን ዘንድ አምላክ በስጦታ የሰጠው ነው፦ ዮሐንስ 17፥4 እኔ ላደርገው "የሰጠኸኝን ሥራ" ፈጽሜ በምድር አከበርሁህ። ዮሐንስ 5፥36 አብ ልፈጽመው "የሰጠኝ ሥራ"፥ ይህ የማደርገው ሥራ፥ አብ እንደ ላከኝ ስለ እኔ ይመሰክራልና። አምላክ ለኢየሱስ ይፈርድ ዘንድ ፍርድን እና ሥልጣንን ሰጠው፦ ዮሐንስ 5፥27 የሰው ልጅም ስለ ሆነ ይፈርድ ዘንድ ሥልጣን ሰጠው። ዮሐንስ 5፥22 ፍርድን ሁሉ ለወልድ ሰጠው። ἀλλὰ τὴν κρίσιν πᾶσαν δέδωκεν τῷ Υἱῷ, ሰጪው አብ አምላክ ነው፥ ተሰጪው ወልድ የሰው ልጅ ነው። አምላክ ለኢየሱስ ክብር ሰጠው፦ ዮሐንስ 17፥22 የሰጠኸኝን ክብር እኔ ሰጥቻቸዋለሁ። አምላክ ለኢየሱስ የሚናገረውን ንግግር፣ የሚያዘውን ትእዛዝ፣ የሚያስተምረውን ትምህርት ሰጠው፦ ዮሐንስ 17፥8 የሰጠኸኝን ቃል ሰጥቻቸዋለሁና፥ እነርሱም ተቀበሉት። ዮሐንስ 12፥49 እኔ ከራሴ አልተናገርሁምና፥ ነገር ግን የላከኝ አብ እርሱ የምለውን እና የምናገረውን ትእዛዝ ሰጠኝ። ሐዋርያት የአብ በነበሩበት ጊዜ የወልድ አልነበሩም፥ አብ ግን ለኢየሱስ እነርሱን ሰጠው፦ ዮሐንስ 17፥6 ከዓለም ለሰጠኸኝ ሰዎች ስምህን ገለጥሁላቸው። የአንተ ነበሩ ለእኔም ሰጠሃቸው። ሁሉም ነገር የአማኞች ነው፣ አማኞች የክርስቶስ ናቸው፣ ክርስቶስ ደግሞ የአምላክ ነው፦ 1ኛ ቆሮንቶስ 3፥23 ሁሉ ነገር የእናንተ ነው፣ እናንተም የክርስቶስ ናችሁ፣ ክርስቶስም የአምላክ ነው። πάντα ὑμῶν, ὑμεῖς δὲ Χριστοῦ, Χριστὸς δὲ Θεοῦ. "አፓካሊፕስ" ᾰποκᾰλῠψῐς ማለት "ራእይ"Revelation" ማለት ሲሆን ኢየሱስ ካረገ በኃላ በሰማይ ላይ አምላኩ ራእይ ሰጠው፦ ራእይ 1፥1 አምላክ "የሰጠው" የኢየሱስ ክርስቶስ ራእይ ይህ ነው። Ἀποκάλυψις Ἰησοῦ Χριστοῦ, ἣν ἔδωκεν αὐτῷ ὁ Θεός, በትንቢት አምላክ ከመጨረሻው የይሁዳን ንጉሥ ከሴዴቅያስ መጠምጠሚያውን እና ዘውዱን አውልቆ ለሚመጣው መሢሕ እንደሚሰጥ ቃል ገብቷል፦ ሕዝቅኤል 21፥26 መጠምጠሚያውን አውልቅ፥ ዘውዱንም አርቅ፤ ይህ እንዲህ አይሆንም፤ የተዋረደውን ከፍ አድርግ፥ ከፍ ያለውንም አዋርድ። ሕዝቅኤል 21፥27 ባድማ፥ ባድማ፥ ባድማ አደርጋታለሁ፤ ፍርድ ያለው እስኪመጣ ድረስ ይህች ደግሞ አትሆንም፥ "ለእርሱም እሰጣታለሁ"። በትንቢቱ መሠረት ጌታ አምላክ የአባቱን የዳዊትን ዙፋን እና አክሊል ለመሢሑ ይሰጠዋል፦ ሉቃስ 1፥32 ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል። ራእይ 6፥2 አየሁም፥ እነሆም አምባላይ ፈረስ ወጣ፥ በእርሱም ላይ የተቀመጠው ቀስት ነበረው፥ "አክሊልም ተሰጠው"፥ ድልም እየነሣ ወጣ ድል ለመንሣት። ኢየሱስ የዳዊትን ዙፋን፣ ዘውድ እና አክሊል በስጦታ ከአምላኩ ለምኖ የሚያገኘው ጸጋ ነው፦ መዝሙር 2፥8 ለምነኝ፥ አሕዛብን ለርስትህ የምድርንም ዳርቻ ለግዛትህ "እሰጥሃለሁ"። ርስት እና ግዛት ለምኖ የሚቀበል ሰው ፍጡር እንጂ ምን ሊሆን ይችላል? ኢየሱስ የተሰጠው ነገር ሁሉ አብ ለአማኞች ከኢየሱስ ጋር ሁሉ ነገር ይሰጣቸዋል፦ ሮሜ 8፥32 ከእርሱ ጋር ደግሞ ሁሉን ነገር እንዲያው እንዴት አይሰጠንም? አማኞች ከኢየሱስ ጋር ይወርሳሉ፣ ይነግሣሉ፣ ይቀመጣሉ፦ ሮሜ 8፥17 ከክርስቶስ ጋር አብረን ወራሾች ነን። ኤፌሶን 2፥7 በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን። 2ኛ ጢሞቴዎስ 2፥12 ብንጸና ከእርሱ ጋር ደግሞ እንነግሣለን። "አምላክ ለአምላክ ሕይወትን፤ ሥልጣንን፣ ሥራን፣ ፍርድን፣ ክብርን፣ ቃልን፣ ሰዎችን፣ ራእይን፣ ዙፋንን፣ አክሊልን፣ ዘውድን፣ ርስትን፣ ግዛትን ሰጠው" ማለት ትርጉም ይሰጣልን? ሁሉን ነገር በስጦታ እና በጸጋ ከአምላኩ የተቀበለን ይህንን መሢሕ "ፈጣሪ ነው" ያሉ በእርግጥ ካዱ፦ 5፥17 እነዚያ "አሏህ እርሱ የመርየም ልጅ አል መሢሕ ነው" ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ لَّقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይወፍቃችሁ! ለእኛም ኢሥቲቃማህ ይወፍቀን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Открыть в Telegramመለኮታዊ ክፍልፍልነት በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 112፥1 በል «እርሱ አሏህ አንድ ነው»። قُلْ هُوَ اللَّهُ أَحَدٌ "ሙረከብ" مُرَكَّب ማለት "ውቅር" "መነጣጠል" "ክፍልፍ"Complex" ማለት ሲሆን "ተርኪብ" تَرْكِيب ማለት "ክፍልፍልነት"Complexity" ማለት ነው፥ በኢሥላም ሥነ መለኮት "ተርኪብ ኢላሂይ" تَرْكِيب إِلٰهِيّ ማለት "መለኮታዊ ክፍልፍልነት"Divine Complexity" ማለት ነው። ተርኪብ ኢላሂይ በኢሥላም ኢንካር የተደረገ እሳቤ ነው፥ "ኢንካር" إِنْكَار ማለት "ውግዝ"Anathema" ማለት ሲሆን አሏህን የአካል ውቅር፣ ክፍልፍል እና ድምር አርጎ መውሰድ "ተርኪብ ኢላሂይ" ነው። በክርስትና ሥነ መለኮት "መለኮታዊ ነጠላነት" የሚባል እሳቤ ቢኖረውም "መለኮታዊ ነጠላ" የሚባለው አብ ነው፥ አምላክን በአካል ሦስት ማድረግ በራሱ መለኮታዊ ክፍልፍልነት ሲሆን ይህ መከፋፈል በቀጰዶቅያ ሥነ መለኮት"Cappadocian Theology" ጎልቶ ታይቷል። ለምሳሌ፦ አንደኛው የቀጰዶቅያ አበው ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ የአካላት መከፋፈል እንዳለ ነግሮናል፦ "ሦስቱ በትክክል ሲከፈሉ ክፍፍሉ የአካላት እንጂ የአምላክነት አይደለም"። Orations (Gregory Nazianzen) Oration 37 Number XXII(22) የአካል መከፋፈል ካለ ይህ አስተምህሮት ነጠላነት ሳይሆን ክፍልፍልነት ነው። "ሚያ ኡሲያ ትሬይስ ሒፓስታቴይስ" μία οὐσία, τρεῖς ὑποστάσεις ማለት "አንድ ባሕርይ ሦስት አካላት" ማለት ነው፥ "ሒፓስታቲስ" ὑπόστασις ማለት "የባሕርይ በተናጥል የሆነ ምሳሌ"Particular example of Essence" ማለት ሲሆን ኡሲያ እና ሒፓስታቲስ እንደሚለያዩ ሁለተኛው የቀጰዶቅያ አበው ባስሊዮስ ዘቂሳሪያ እንዲህ አስቀምጧል፦ "በባሕርይ እና በአካል መካከል ያለው ልዩነት በአጠቃላይ እና በተናጥል መካከል ካለው ልዩነት ጋር ተመሳሳይ ነው" Letters (St. Basil of Caesarea) Letter 236 Number 6 "ኮይኖን" Κοινόν ማለት "ጥቅል"General" ማለት ሲሆን "ኢድዮን" ῐδῐον ማለት "ተናጥል"Particular" ማለት ነው፥ "ኡሲያ ጥቅል ነው፥ ሒፓስታቲስ ተናጥል ነው" የሚል ክፍፍል ሥላሴን መለኮታዊ ክፍልፍልነት ያረገዋል። "አይቲያ" αἰτῐᾱ ማለት "መንስኤ"Cause" ማለት ሲሆን አብ ወልድን በማስገኘት የወልድ መንስኤ ነው፥ "አፓቴሌስማ" αποτέλεσμα ማለት "ውጤት"Effect" ማለት ሲሆን ወልድ በመገኘት የአብ ውጤት ነው። ሦስተኛው የቀጰዶቅያ አበው ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ እንዲህ ይለናል፦ "እነዚህን ነገሮች ስንናገር አብ ያለ ልደት መኖሩን መካድ አንፈልግም፥ አንድያ ልጅ የሆነው አምላክ ተወለደ የሚለውን አባባል ለመቀበል ፈቃደኛ አለመሆን ምንም ዓላማ የለንም። በተቃራኒው የኋለኛው ተወልዷል፥ የፊተኛው ግን አልተወለደም"። Against Eunomius (Gregory of Nyssa) Book VII(7) Number 5 "አፖዶሲስ" ἀπόδοσις ማለት "ቀደማይ"Antecedent" ማለት ሲሆን "ፕሮታሲስ" πρότᾰσῐς ማለት "ደኃራይ"Consequent" ማለት ነው፥ እንደ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ ሥነ መለኮት አብ እና ወልድ በጊዜ ባይቀዳደሙም በሁኔታ ግን አብ ፊተኛ ወልድ ኃለኛ በመሆን ይቀዳደማሉ። ይሩማሲስ ዘስትሪዶን"Jerome of Stridon" በውጪው አገራት "ጄሮም" የሚባለው የላቲን አባት፦ አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ በአካል የተከፋፈሉ መሆናቸውን አስተምሯል፦ "በዚያ ሁኔታ አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ በባሕርይ ሳይሆን በአካል የተከፋፈሉ መሆናቸውን ያውቅ ነበር"። Dialogue Against the Luciferians (Jerome) Number 12 አብ ወላዲ ገቢር"Active" ከሆነ ወልድ ደግሞ ተወላዲ ተገብሮት"Passive" ከሆነ እልም ያለ ክፍፍል ነው። ጠርጡሊያኖስ ዘካርቴጅ ወልድ የአብ "ክፍል" መሆኑን ይናገራል፦ "አብ አጠቃላይ ባሕርይ ነው፥ ነገር ግን ወልድ የአጠቃላዩ መገኘት እና ክፍል ነው" Against Praxeas (Tertullian), Chapter 9 ይህ የሥላሴ እሳቤ ጠንሳሽ ጠርጡሊያኖስ ኢየሱስን "በህልውና መንገድ በደረጃ ሁለተኛ ነው" ብሎታል፦ "በባሕርይ ሳይሆን በህልውና መንገድ በደረጃ ሁለተኛ ነው"። Apology (Tertullian) Chapter 21 ቀለሜንጦስ ዘእስክንድርያ ስለ ኢየሱስ "ወልድ ሁለተኛ ነው" በማለት ደረጃውን ተናግሯል፦ "በአብ ፈቃድ ሁሉ ነገር በእርሱ የሆነው ወልድ ሁለተኛ ነው"። The Stromata (Clement of Alexandria) Chapter 14 አርጌንስ ዘእስክንድርያ ኢየሱስን "ሁለተኛ አምላክ" ብሎ ያስተምር ነበር፦ "ቢሆንም እኛ "ሁለተኛ አምላክ" ብለን ልንጠራው እንችላለን"። Origen Against(Contra) Celsum, Book 5 chapter 39 ዮስጢንዮስ ሰማዕቱ ኢየሱስ በደረጃ ሁለተኛ እንደሆነ እና ሌላ አምላክ እና ጌታ እንደሆነ ይናገራል፦ "በምክንያት የራሱ የእውነተኛ አምላክ ልጅ መሆኑን ተምረን እና በሁለተኛ ደረጃ ይዘን እንሰግድለታለን"። The First Apology (St. Justin Martyr) Chapter 13 Number 6 "ሌላ አምላክ" እና ጌታ ለሁሉን ነገር ፈጣሪ ይገዛል"። Justin Martyr, Dialogue with Trypho, chapter 56 አውሳብዮስ ዘቂሳሪያ ኢየሱስን "ሁለተኛ ጌታ" ይለዋል፦ "ሙሴ ከአብ ቀጥሎ ሁለተኛ ጌታ መሆኑን በግልፅ ያውጃል"። Church History (Eusebius) Book I(1) Chapter 2 Number 9 ወደ አገራችን ጎራ ስንል ደግሞ ሥላሴን ሦስት አማልክት አርገው አስቀምጠውልናል፦ ሰይፈ ሥላሴ ዘሐሙስ ምዕራፍ 5 ቁጥር 22 "ሠለስቱ አማልክት ልዑላን አሐዱ ሥልጣነ ምልክናሆሙ" ትክክለኛ ትርጉሙ "የአምላክነታቸው ሥልጣን አንድ የሆነ ሦስቱ አማልክት ልዑላን ናቸው" የሚል ነው። ስንቀጥል፦ መልክአ ሥላሴ ቁጥር 39 "ሰላም ለአእጋሪክሙ እለ ውስተ ገነት አንሶሰዋ፤ ሥሉስ ቅዱስ አማልክተ አዳም ወሔዋ"። ትክክለኛ ትርጉሙ "ሥሉስ ቅዱስ ሆይ! የአዳም እና የሔዋን አማልክቶቻቸው እንደመሆናችሁ" የሚል ነው። ግዕዝ አያነቡም ብላችሁ ሕዝቡን ለምን ትጫወቱበታላችሁ? "መለኮት ነጠላ አንድ ነው" ከሚል እሳቤ በተቃራኒው አምላክ እና ሰውን አንድ ውሕድ"Composition" ሆነ የሚል እሳቤ እራሱ መለኮታዊ ክፍልፍልነት ነው፦ ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 39 ቁጥር 23 "ፈጣሪ ከፍጡር በተዋሐደ ጊዜ አንድ አካል በመሆን የጸና አንድ ባሕርይ ሆነ"። በዲኑል ኢሥላም ግን አሏህ እርሱ የማይከፋፈል፣ የማይለያይ፣ የማይነጣጠል አንድ ነጠላ ምንነት እና ማንነት ነው፦ 112፥1 በል «እርሱ አሏህ አንድ ነው»። قُلْ هُوَ اللَّهُ أَحَدٌ "አሐድ" أَحَد ማለት "የማይከፈል አንድ" ማለት ሲሆን አሏህ በማንነቱ ሆነ በምንነቱ አንድ ነው። ከዚህ ቀደም ስለ መለኮታዊ ነጠላነት የጦመርኩትን መጣጥፍ ስላለ ይመልከቱ፦ https://t.me/Wahidcom/4203 አንድ አምላካችን አሏህ እርሱን አምልከው ከሚሞቱ ባሮቹ ያድርገን! አባጣ እና ጎርባጣ ከሆነው ከሺርክ ሕይወት ይጠብቀን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Открыть в Telegramአሏህ አምሳያ የለውም በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። 16፥74 ለአሏህ አምሳያዎችን አታድርጉ፡፡ فَلَا تَضْرِبُوا لِلَّهِ الْأَمْثَالَ አምላካችን አሏህ የሰማያት እና የምድር በሁለቱም መካከል ላለው ሁሉ ጌታ ነው፥ ለእርሱ ሞክሼ የለውም፦ 19፥65 እርሱ የሰማያት እና የምድር በሁለቱም መካከል ላለው ሁሉ ጌታ ነውና አምልከው! እርሱን በአምልኮቱ ላይ ታገስ፡፡ ለእርሱ ሞክሼን ታውቃለህን? رَّبُّ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَمَا بَيْنَهُمَا فَاعْبُدْهُ وَاصْطَبِرْ لِعِبَادَتِهِ ۚ هَلْ تَعْلَمُ لَهُ سَمِيًّا "ሠሚይ" سَمِيّ ማለት "ሞክሼ" ማለት ሲሆን አምላካችን አሏህ ከፍጥረት የሚመስለው ምንም ነገር የለም፦ 42፥11 የሚመስለው ምንም ነገር የለም፡፡ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡ لَيْسَ كَمِثْلِهِ شَيْءٌ ۖ وَهُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ እዚህ አንቀጽ ላይ "ሚስሊ" مِثْلِ የሚለው የግሥ መደብ ነው፥ "ሚስል" مِثْل ወይም "ሚሳል" مِثَال የስም መደብ ሲሆን "አምሳያ" "ምሳሌ" ማለት ነው። ለአሏህ ምንም ዓይነት አምሳል የለውም፥ ለእርሱ አንድም ብጤ የለውም፦ 114፥4 «ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም»። وَلَمْ يَكُن لَّهُ كُفُوًا أَحَدٌ "ኩፉው" كُفُو ማለት "ወደር" "እኩያ" "አቻ" "ቢጤ" "አምሳያ" "ተፎካካሪ" "ባላንጣ" ማለት ሲሆን እርሱ የሚተካከለው አቻ እና እኩያ እንዲሁ የሚመሳሰለው አምሳያ እና ቢጤ የለውም። በዲኑል ኢሥላም ለአሏህ አምሳያዎችን ማድረግ ሺርክ ነው፦ 16፥74 ለአሏህ አምሳያዎችን አታድርጉ፡፡ فَلَا تَضْرِبُوا لِلَّهِ الْأَمْثَالَ እዚህ አንቀጽ ላይ "አምሳያዎች" ለሚለው የገባው ቃል "አምሳል" أَمْثَال ሲሆን "ሚስል" مِثْل ወይም "ሚሳል" مِثَال ለሚለው ብዙ ቁጥር ነው፥ ስለዚህ አሏህ ምሳሌ ወይም አምሳል የለውምና አከሌ "በአሏህ አምሳል ወይም ምሳሌ ተፈጠረ" የሚል ትምህርት በዲናችን የለም። በባይብል ግን ሰው የተፈጠረው በአምላክ ምሳሌ ወይም አምሳል እንደሆነ ይናገራል፦ ዘፍጥረት 1፥26 አምላክም፦ “ሰውን በመልካችን እና እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር" አለ። וַיֹּאמֶר אֱלֹהִים נַעֲשֶׂה אָדָם בְּצַלְמֵנוּ כִּדְמוּתֵנוּ ልብ ብላችሁ እንደሆነ "መልክ" ለሚለው የገባው ቃል "ጼሌም" צֶלֶם " ሲሆን "ምሳሌ" ለሚለው የገባው ቃል "ድሙት" דְּמוּת ነው፥ በግሪክ ሰፕቱአጀንት "መልክ" ለሚለው የገባው ቃል "ኤይኮን" εἰκών ሲሆን "ምሳሌ" ለሚለው የገባው ቃል ደግሞ "ሆሞዮሲስ" ὁμοίωσις ነው፦ ዘፍጥረት 1፥26 አምላክም፦ “ሰውን በመልካችን እና እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር" አለ። καὶ εἶπεν ὁ Θεός· ποιήσωμεν ἄνθρωπον κατ᾿ εἰκόνα ἡμετέραν καὶ καθ᾿ ὁμοίωσιν, በዐረቢኛው ባይብል ላይ "መልክ" ለሚለው የገባው ቃል "ሱራህ" صُورَة ሲሆን "ምሳሌ" ለሚለው የገባው ቃል ግን "ሚሳል" مِثَال ነው፦ ዘፍጥረት 1፥26 አሏህም፦ “ሰውን በመልካችን እና እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር" አለ። ثُمَّ قَالَ اللهُ: «لِنَخلِقِ النَّاسَ عَلَى صُورَتِنَا وَكَمِثَالِنَا "አምሳል" የግዕዝ ቃል ሲሆን "ምሳሌ"Similar" ማለት ነው። "አሏህ አደምን በመልኩ ፈጠረ" የሚል ሐዲስ ላይ አለ፥ በዚህ ነጥብ ላይ ከዚህ ቀደም የጦመርነው መጣጥፍ ስላለ ይመልከቱ፦ https://t.me/Wahidcom/4073 ነገር ግን "ሰው በአሏህ አምሳል" ተፈጠረ የሚል አስተምህሮት በዲናችን የለም፥ ምክንያቱም አሏህ አምሳያ የለውም። በተጨማሪ፦ ያዕቆብ 3፥9 በእርሱም(በአንደበት) እንደ አምላክ "ምሳሌ" የተፈጠሩትን ሰዎች እንረግማለን። καὶ ἐν αὐτῇ καταρώμεθα τοὺς ἀνθρώπους τοὺς καθ’ ὁμοίωσιν Θεοῦ γεγονότας· እዚህ አንቀጽ ላይ "ምሳሌ" ለሚለው የገባው ቃል ደግሞ "ሆሞዮሲስ" ὁμοίωσις እንደሆነ ልብ አድርግ! አንዲት ሙሥሊም እኅታችን ባለማወቅ ስለ ሰው "አሏህ በአምሳሉ የፈጠረውን ፍጡር" ብላ ስትናገር ሙሥሊሞች "አሏህ አምሳያ የለውም፥ አሏህ ሰውን በአምሳሉ ፈጠረ" የሚል ትምህርት ባይብል ላይ እንጂ ቁርኣን ላይ ወይም ሐዲስ ላይ የለም" ሲሉ ዐላዋቂ ክርስቲያኖች ደግሞ "አሏህ አደምን በመልኩ ፈጠረ" የሚለውን ሐዲስ ያለ ቦታው እና ዐውዱ ጠቅሰዋል። ቅሉ እና ጥቅሉ ግን "መልክ" ማለት እና "ምሳሌ" ማለት ይለያያል፥ አሁንም ቢሆን "አሏህ ሰውን በአምሳሉ ፈጠረ" የሚል ትምህርት ቁርኣን እና ሐዲስ ላይ የለም። "አሏህ ሰውን በአምሳሉ ፈጠረ" የሚል ሙግት ሥነ አምክኖአዊ ሕፀፅ"Logical fallacy" አለበት፥ የሙግቱ ድምዳሜ በማስረጃ አልባ ስለተደመደመ ከመረጃ አልባ የመጣ ሕፀፅ"Argument from silence fallacy" ከመሆን ባሻገር በማንለው እና በማናምንበት ሙግት ዐዋቅሮ እና አደራጅቶ መሞገት ቁልመማዊ ሕፀፅ"Straw man fallacy" ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይወፍቃችሁ! እኛንም ኢሥቲቃማህ ይወፍቀን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Открыть в Telegramቡጢ በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። 22፥11 ከሰዎች በጫፍ ላይ ሆኖ አሏህን የሚያመልክ ሰው አለ። وَمِنَ النَّاسِ مَن يَعْبُدُ اللَّهَ عَلَىٰ حَرْفٍ "ቡጢ"Boxing" ማለት "አምስት ጣቶችን በማጠፍ እና በመኮርመት ፊት ላይ ድብደባ ማሳረፍ" ማለት ነው፥ ቡጢ ከሥነ ጥበብ"Art" ቢሆንም ሥረ መሠረቱ ግን ዐረማዊ ልማድ"Pagan Custom" ነው። የሮማዊ የትግል፣ የድብድብ፣ ጦርነት አምላክ "ማርስ"Mārs" ሲባል የእርሱ ሥነ ጥበብ "የማርስ ሥነ ጥበብ"Martial art" ተብሎ ይታወቃል፥ ይህ የዐረማዊ ልማድ ከዛ ጀምሮ ዛሬ ላይ በእያንዳንዱ ሕይወት ውስጥ እንደ ጤናማ ስፓርት መታየቱ ማፈር እና መክሰር ነው። ውጪው የትጉኅ እና የታታሪ ሰው መገለጫ ቢመስልም ውስጡ ግን መብረድ እና መንደድ ያለበት ስሜታዊ ጉዳይ ነው፥ በዲኑል ኢሥላም ሰውን በቡጢ ፊቱን መምታት እና መደብደብ ሐራም ነው፦ ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 49 ሐዲስ 41 ቁጥር 2559 አቢ ሁረይራህ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ከእናንተ አንዱ በሚጋደልበት ጊዜ ፊትን ከመምታት ይቆጠብ"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ " إِذَا قَاتَلَ أَحَدُكُمْ فَلْيَجْتَنِبِ الْوَجْهَ ". ይህ በሆነበት አግባብ ቡጢን ከዲን ጋር አያይዞ ጮቤ መርገጥ ምን ያህል ወጥ የረገረ ነገር መሆኑ ከወዲሁ የታወቀ ነው፥ ፊትን መቶ እና ደብድቦ በሚያስሸልም የሐራም ውድድር ላይ አምላካችን አሏህ ጣልቃ አይገባም። ምንም ነገር የሚከናወነው እና የሚሆነው አሏህ ፈቅዶ ቢሆንም በጉዳዩ ላይ ጣልቃ ይገባል ማለት አይደለም፥ በአሏህ ፈቃድ ዙሪያ ከዚህ ቀደም የጦመርኩትን መጣጥፍ መመልከት ይቻላል፦ https://t.me/Wahidcom/4231 ብጥር እና ንጥር አድርገን ስንመለከተው ቡጢ የግሪክ ወሮም ዐረማዊ ልማድ እና የምዕራባውያን እሴት እና እሳቦት እንዲህ እርዮት አና አብዮት ነው፥ የዐረማዊ ልማድ የሚሰነፍግ እና የሚያጥነገንግ መሆኑ እየታወቀ ግን በዚህ ሂደት ውስጥ ዲንን ቁማር አርጎ ማስያዝ ደግሞ እጅግ ሲበዛ ክፉኛ ነገር ነው፦ 22፥11 ከሰዎች በጫፍ ላይ ሆኖ አሏህን የሚያመልክ ሰው አለ። ታዲያ መልካም ነገር ቢያገኘው በእርሱ ይረጋል፥ መከራ ብታገኘው በፊቱ ላይ ይገለበጣል፡፡ የቅርቢቱን ዓለም እና የመጨረሻይቱን ዓለም ከሰረ፡፡ ይህ እርሱ ግልጽ ኪሳራ ነው፡፡ وَمِنَ النَّاسِ مَن يَعْبُدُ اللَّهَ عَلَىٰ حَرْفٍ ۖ فَإِنْ أَصَابَهُ خَيْرٌ اطْمَأَنَّ بِهِ ۖ وَإِنْ أَصَابَتْهُ فِتْنَةٌ انقَلَبَ عَلَىٰ وَجْهِهِ خَسِرَ الدُّنْيَا وَالْآخِرَةَ ۚ ذَٰلِكَ هُوَ الْخُسْرَانُ الْمُبِينُ ሊክድ ወይም ሊያምን ጫፍ ላይ ሆኖ አሏህን እያመለከ ሲሳካለት ዲኑን አጥብቆ የሚይዝ ሳይሳካለት ከዲን የሚገለበጥ የቅርቢቱን ዓለም እና የመጨረሻይቱን ዓለም ከሰረ፥ ስለዚህ ሐራም የሆነውን ቡጢ ይቅርና ማንኛውን ነገር በፉክክር እና በውድድር የሚደረግ ነፍሥያህ ጉዳይ ውስጥ የአሏህ እጅን አስገብቶ ቁማር መጫወት ግልጽ ኪሳራ ነው። የዓለማቱን ጌታን አሏህን ሁለት ሰዎች በሚያደርጉት ነፍሢያህ"Egocentric" ውድድር እና ፉክክር ውስጥ የአሏህን አሕካም ማስገባት ቂልነት እና ዕብደት ነው፥ ከዘር፣ ከዘውግ፣ ከቀለም፣ ከቋንቋ፣ ከብሔር፣ ከባህል ፉክክር እና ውድድር ወጥተን ሊላሂ በሚደረግ ድርጊት"Theocentric" የዓለማቱን ጌታን አሏህ ያግዘናል እጁም አለበት። "ዐውራህ" عَوْرَة ማለት "ሐፍረተ ገላ" ማለት ሲሆን ዐውራህ የሚገለጠው በቤት ውስጥ ከፈጅር በፊት፣ በዝሁር እና ከዒሻእ በኋላ ሦስት ጊዜያት ነው፦ 24፥58 ለእናንተ የኾኑ ሦስት የሐፍረተ ገላ መገለጫ ጊዜያቶች ናቸውና፡፡ ثَلَاثُ عَوْرَاتٍ لَّكُمْ ۚ لَيْسَ عَلَيْكُمْ እዚህ አንቀጽ ላይ "ሐፍረተ ገላ" ለሚለው የገባው ቃል "ዐውራት" عَوْرَات ሲሆን "ዐውራህ" عَوْرَة ለሚለው ብዙ ቁጥር ነው፥ ይህም ለባለ ትዳሮች ብቻ ሲሆን ነገር ግን አደባባይ ላይ ሐፍረተ ገላን ከፍቶ ለዛውም ለዓለም ሕዝብ ማሳየት ምን ያህል ሐራም መሆኑን ለመረዳት አያዳግትም። ስለዚህ ቡጢ ሰውን የሚጎዳ፣ ቁማር እና ሐፍረተ ገላ የሚታይበት ስለሆነ ሐራም ነው። እንደ ጥቅል ለመረዳት በፉክክር እና በውድድር ውስጥ የአሏህ ቀደማይ ፈቃድ"Antecedent Will" የሌለበት ቢሆንም ማንኛውምን ግጥሚያ የሚያሸንፈው ጠንክሮ የተለማመደ፣ ስልት ያለው እና የተሻለ ዝግጅት ያደረገው ሰው መሆኑ የአሏህን ደኃራይ ፈቃድ"Consequent Will" ነው። በቡጢ ሰውን የሚጎዱትን አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣቸው! እኛንም ሰውን ከመጉዳት ይጠብቀን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Открыть в Telegram16ኛው ክፍለ ዘመን በፕሮቴስንታንት አውራ አስረገጥ ተሓድሶ"Magisterial Reformation" የተጀመረው ተቃውሞ አምስት ብቻዎች"Five solae" አዋቅሯል፥ እነዚህ አምስት ብቻዎች የሚባሉት፦ 1ኛ. መጽሐፍ ብቻ"Sola Scriptura" 2ኛ. እምነት ብቻ"Sola Fide" 3ኛ. ጸጋ ብቻ"Sola Gratia" 4ኛ. ክርስቶስ ብቻ"Solus Christus" 5ኛ. ክብር ለአምላክ ብቻ"Soli Deo Gloria" ናቸው። "ክብር ለአምላክ ብቻ"Soli Deo Gloria" በሚል ማዕቀፍ ውስጥ ከአምላክ ውጪ ለሌላ ነገር ስግደት ሆነ ክብር ክልክል መሆን ይካተታል፥ ነገር ግን የቲክ ቶክ ፕሮቴስታንት የሙሥሊም ሙግት ሲያንቆራጥጧቸው ለማምለጥ "ለዳዊት የአክብሮት ስግደት ተሰግዶለታል" ብለው አረፉት። ቆይ "የአክብሮት ስግደት" የሚለው ትምህርታችሁ በአንቀጸ እምነታችሁ ከሌለ ከሙግት ለማምለጥ ለምን መዋሸት አስፈለገ? ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom
Открыть в Telegramየበላይነት ስሜት"superiority complex" እና የበታችነት ስሜት"inferiority complex" ሁለቱም በሽታዎች ናቸውና የሥነ ልቡና ህክምና ያስፈልጋቸዋል። ላዕላይ በራስ መተማመን"over confidence" ለንቀት፣ ለትዕቢት እና ለውድቀት ይዳርጋል፥ ታኅታይ በራስ መተማመን"under confidence" ለባዶነት፣ ለብቸኝነት እና ለጥፋተኝነት ስሜት ይዳርጋል። አምላካችን አሏህ እርሱ ባስቀመጠልን አኽላቅ እና አደብ የምንሰተር ያርገን! ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom
Открыть в Telegram