ሌሊቱ ረዝሞ የነፍስን ጓዳ በጨለማ ቢሸፍነውም፣ የማለዳ መምጣት ግን የማይቀር የተፈጥሮ ቃል ኪዳን ነው። ማለዳ በቀን መቁጠሪያ የሚለካ የሰዓት ሽግግር ብቻ አይደለም። ይልቁንም የጨለማው መሸነፍ፣ የዝምታው መሰበርና የመንፈስ ዳግም መወለድ ምስጢር ነው። በሱፊዎች መንፈሳዊ ጉዞ «ማለዳ» የልብ መንቃትን ይወክላል። በእንቅልፍና በመንቃት መካከል ባለው በዚያች ስስ የንጋት ቅጽበት፣ ነፍስ ከስጋዊ ጫጫታ ርቃ ከፈጣሪዋና ከእውነተኛ ማንነቷ ጋር ትገናኛለች። የንጋቱ ቀዝቃዛ ነፋስ የልብን አቧራ ጠርጎ ሲያነሳ፣ የትናንቱ ህመምና ናፍቆት ወደ ብርሃን ይቀየራሉ። እሱባለው በዜማው እንደሚያንጎራጉረው፣ «ማለዳዬ» የምንለው የምንወደውን ሰው ወይም የምንናፍቀውን እውነት ብቻ አይደለም። ማለዳዬ ማለት በውስጣችን ያለው ያልጠፋ ተስፋ ነው። በዝምታ ውስጥ የሚሰማ ውብ ዜማ፣ በጨለማ ውስጥ የሚያበራ የፍቅር ፋኖስ ነው። ሰው የራሱን ማለዳ የሚያገኘው ወደ ውጭ ሲመለከት ሳይሆን ወደ ውስጥ ሲጠልቅ ነው። ፍቅር የልብን በር ሲያንኳኳ፣ ዝምታው ራሱ ቋንቋ ይሆናል። ናፍቆቱም ከስቃይነት ወጥቶ ወደ ጣፋጭ ጸሎት ይለወጣል። ያኔ ሌሊቱ ምንም ያህል ቢረዝም፣ ፀሐይዋ በውስጣችን ስለምትወጣ ሁልጊዜም ማለዳ ነው። "እሱቤ ግን ግጥሞቹ" ……❤️🦋…… ሃሳብ አላቸው ……ያስባሉ !!
Открыть в TelegramПосты канала ትዝታዊ🐣
ከAsteraceae ወገን ሆነው አንዱ ለፀሃይ ፊቱን ሲሰጥ ፣ አንዱ ከፀሃይ ፊቱን ነስቶ፣ ሌላው በእጆች እንክብካቤ ፣ ሌላው በዱር በገደል አድጎ ………አንዱ ለሆድ አንዱ ለነፍስ ተስፋ አለው……… አደይ አበባና ና ሱፍ አበባን ምን ለያቸው ? እጂ ውስጥ ውብ ናቸው እላለው ?………ቢሆንም ቢሆንም ነፍስ የሚናፈቅ ትወዳለች ትንሿን አደይን ታሸታለች ……… ቢሆንም ቢሆንም ቀጠሮ ደስ ይላል ……… ወራቶች ሁሉ አፍቅረዋት መስከረም ያገባትን ማየት ይናፍቃል ……… አደይ ………🌼 መልካም አዲስ አመት ይባላል ግን ኣ ?
Открыть в Telegramጊዜ ለተስፋ መቁረጥ ያበድራል! እንደ ደንቡ ለመኖር እንፍገመገማለን ይላሉ፤ ለመሆኑ የዚህች ዓለም ደንብ ከውሸት በቀር ምን አለው? እኛስ ከጊዜ ኪስ ውስጥ ሕይወትን ለመበደር ለምን እንላተማለን? ጊዜ እኮ ራሱ ባዶ እጁን የቆመ ለማኝ ነው! ጊዜ ኃያል የሚሆነው…በውስጡ የእውነትን ፀሐይ፣ የመለኮትን ተስፋ አቅፎ ሲመጣ ብቻ ነው……… ካልሆነማ ያለ ፍቅርና ያለ ተስፋ፣ ጊዜ ያን ያህል ኃይል የለውም…ባዶ የሰከንዶች ዝገት፣ ነፍስ የሌለው ጥላ ነው! ጊዜ የሚገዛው ተስፋ የቆረጡትን ብቻ ነው፤ ነጻ የወጣች ነፍስ ግን ከጊዜ በላይ ትበራለች…………
Открыть в Telegram🤔…… ሳስበው ሳስበው በደጋፊ ብዛት ትክክል የምንሆንበት ዘመን ላይ ደርሰናል🤔 "መስረቅክን " ደጋፊክ ከተስማማበት ፣ የተሰረቀበት ሰው ሌባ ነው …… ይመስለኛል ተከታይ መሰብሰብ ከሃቅ በላይ ሳይነግስ አልቀረም………እምም tizta/@tiztawe
Открыть в Telegramበመጨረሻም፥ ዕድል እና ትክክለኛ ጊዜ በአጋጣሚ የሚከሰቱ አይደሉም። እነሱ ተአምራዊ ጊዜያትን የሚፈጥሩ የቁርጠኛ እና ቀላል ምርጫዎች ውጤቶች ናቸው። ጽኑ መሆን፣ ያለምንም ጥርጣሬ ውሳኔዎችን ማድረግ... ትክክለኛውን ጊዜ የሚፈጥረው ይህ ነው። እሱ እኔ ከፈለግኳት በላይ ይፈልጋት ነበር። እኔም የበለጠ ደፋር መሆን ነበረብኝ። ጥፋቱ የትራፊክ መብራቱ አልነበረም። የጊዜውም ማለፍ አልነበረም። ጥፋቱ የእኔ ማቅማማት ነበር።" #tizta🦋#
Открыть в Telegram🦋…………… እኔ እና እኔ ብዙ ትዝታ አለን የማልረሳቸው በቀናት ክምር ውስጥ መአት ሀሳቦች መአት ደሞ አለመሆኖች፣ . ኖሬ ኖሬ ለማለት ብዙ እድሜዬ ባይሄድም፤ ትዝታው አልቀረልኝም ፤ የማስታውስው ወደኋላ የሚመልሰኝን በአቅሜ ይዣለው . . ልቤ ደከመ ፣ ጉልበቴ አለቀ ፣ መልኬ ረገፈ ፣ ጸጉሬ ሳሳ ፣ ይኼን ሁሉ ባልልም በአቅሜም ቢሆን እኔ ከኔ ጋ የተጓዝኩት ትዝታ አለኝ፤ . ነገም ደሞ ነገ ሆኖ ዳግም ትዝታን ሊሰራ እቺን ታክል ኑሬ ቋጥሬ በትናንት መሀረብ ያስቀመጥኩት እኔ ከ እኔ ጋ ትዝታ አለኝ…
Открыть в Telegramበዚህ አጋጣሚ በሃሳብ ነፃነት በጣም ማምን ሴት ነኝ😁 "እናትሽን ስንጠላት እኮ" ብትሉኝ እንዴት የኔ እናት ትጠላለች ብዬ ጦር ከመማዘዝ የህሊና እስር ቤት ከተላቀኩ ቆይቻለው (ማትችሉት መንካት ነው)፣ ……… እኔ የምንም ነገር አምላኪ አይደለውም እምነቴ እውነት ነው ፣ የምወደውን መጥላት ትችላላቹ እንዴት እንደወደደድኩት ሃሳብ አለኝ ፣ እንዴት እንደጠላቹት ሃሳብ ካላቹ ለመነጋገር አልፈራም 😁😉 ………ሚዛናዊነት ይለምልም✌️
Открыть в Telegramበዚህ አጋጣሚ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ላይ ቁጭ ብለን መሬቴ ላይ እኔ ማፈልገው የሃይማኖት ተቋም አይገነባም ማለት ድንቁርና ነው !! ወገን ከስንት ሺ ዓመታት በፊት እኮ ተዋውሰው ፀልየዋል ፣ ሰግደዋል !!!……, ቅድስና ርህራሄ ውስጥ ነው ያለው !……!! አምላክም ሚገለጥልክ በፈጠረው መሬት ሳይሆን በሰራከው ቅዱስ ማንነትክ ውስጥ ነው !
Открыть в Telegram