Кабинет

Посты канала Isaiah 48 Apologetics

сначала новые

#1592Текст

🚩 የእግዚአብሔር መልአክና ጌዴዎን (ክፍል 13) ባለፈው ክፍል ላይ መለኮት የሆነው የእግዚአብሔር ልጅ በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር መልአክ በመባል ይገለጥ እንደነበር እና በዚህ መንገድ ከተገለጠባቸው አጋጣሚዎች አንዱ የሆነውን የጌዴዎንን ታሪክ ማየት ጀምረን ነበር። ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ለመግለጽ እንደሞከርነው መልአክ የሚለው ቃል በዕብራይስጥ "ማልአኽ/מַלְאַ֥ךְ" በግሪክ ደግሞ "አንጌሎስ/ἄγγελος" ሲሆን ትርጉሙ መልእክተኛ ማለት ነው። የመልእክተኝነት ግብር ያለው የትኛውም አካል መልአክ/መልእክተኛ ተብሎ ይጠራል። የመልእክተኛው ባህርይ ሰዋዊ ይሁን፥ የፍጡራን መናፍስት ይሁን መለኮታዊ ይሁን የሚታወቀው በአውዱ ነው። እንጂ አንድ አካል መልአክ ስለተባለ ብቻ ከፍጡራን መናፍስት አንዱ ነው ማለት አይደለም። የእግዚአብሔር ልጅም መልአክ የተባለው የአባቱ መልእክተኛ ስለነበር እንጂ ፍጡር ስለሆነ አይደለም። እግዚአብሔር ቢፈቅድ ከባለፈው ክፍል በመቀጠል የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ የእግዚአብሔር መልአክ በመባል ለጌዴዎን የተገለጠበትን ክስተት ማየት እንቀጥላለን፦ "ጌዴዎንም የእግዚአብሔር መልአክ እንደ ሆነ አየ፤ ጌዴዎንም። አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ #ወዮልኝ፤ የእግዚአብሔርን #መልአክ ፊት ለፊት #አይቻለሁና አለ" (መሳ 6:22) ባለፉት ተከታታይ ክፍሎች ጌዲኦን እንዴት በኦሪት ላይ ከተዘገበው የያዕቆብ ታሪክ ለእግዚአብሔር መልአክ መሥዋዕት ማቅረብ እንደሚቻል እያየን ነበር። ባለፈው ክፍል ላይ በዘፍ 35:1-13 ላይ እግዚአብሔር ያዕቆብን ወደ ቤቴል ሄዶ ከወንድሙ ከዔሳው በሸሸ ጊዜ ለተገለጠለት እግዚአብሔር መሠዊያ እንዲሰራ ካዘዘው በኋላ እንዴት ለቤተሰቦቹና አብረውት ለነበሩት ሰዎች ንጹሐን እንዲሆኑ እንግዳ አማልክትንም ከመካከላቸው እንዲያስወግዱ እንደነገራቸው፥ ከዚያም ከእነርሱ ጋር ወደ ቤቴል እንደሄደ፥ ወደ ቤቴል ከደረሰ በኋላም መሠዊያን እንደሠራ፥ የቦታውንም ስም ኤልቤቴል ብሎ እንደጠራው፥ ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር ከሁለት ወንዞች መካከል እንደገና እንደተገለጠለትና እንደባረከው፥ ብዙ ነገሮችንም ቃል እንደገባለት፥ ከዚያም ከእርሱ ተነጋግሮ ከጨረሰ በኋላ ወደ ላይ እንደወጣ ለማየት ሞክረናል። በዘፍ 28:11-19 እና በዘፍ 31:10-13 መሰረት በዘፍ 35 ላይ ለያዕቆብ የተገለጠለት እግዚአብሔር የእግዚአብሔር መልአክ ነው። በዚህ ክፍል ላይ ቀጥሎ የሆነውን ነገር ለመመልከት እንሞክራለን፦ " #ያዕቆብም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር በተነጋገረበት ቦታ #የድንጋይ_ሐውልት ተከለ፤ የመጠጥ መሥዋዕትንም በእርሱ ላይ አፈሰሰ፥ #ዘይትንም_አፈሰሰበት" (ዘፍ 35:14) ያዕቆብ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ተነጋግሮ ወደ ላይ ከወጣ በኋላ በዚያ ቦታ የድንጋይ ሐውልት ተከለ፥ የመጠጥ መሥዋዕት እና ዘይት አፈሰሰበት። በዘፍ 28:11-19 እና በዘፍ 31:10-13 መሰረት በዚህ ቦታ ላይ ከያዕቆብ ጋር ተነጋግሮ ወደ ላይ የወጣው እግዚአብሔር የእግዚአብሔር መልአክ ነው። ከዚህም ባሻገር እንደ ብሉይ ኪዳን አስተምህሮ እግዚአብሔር ተብሎ ተጠርቶ ወደ ላይ ሊወጣ ወይም ሊያርግ በሚችል መልኩ የሚገለጠው የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑ (መሳ 13:20-22) ለዚህ እውነት ተጨማሪ ማረጋገጫ ነው። ስለዚህ ለያዕቆብ በዚህ መልኩ ከተገለጠለት በኋላ ያዕቆብ የድንጋይ ሐውልት ያቆማል፥ በላዩም ዘይት ያፈስስበታል። በዘፍ 35:14 ያዕቆብ የድንጋይ ሐውልት አቁሞ ዘይት ያፈሰሰበት ለመጀመሪያ ጊዜ እግዚአብሔር በቤቴል ከተገለጠለት በኋላ እንዳደረገለት ነው (ዘፍ 28:18) ነገር ግን ያን ጊዜ ሐውልት አቁሞለት የነበረው እግዚአብሔር የእግዚአብሔር መልአክ ነበር (ዘፍ 31:11-13) ስለዚህ አሁንም በዘፍ 35:14 ላይ ያንኑ ነገር በድጋሚ ማድረጉ በዚህ ቦታ ላይ የተገለጠለት እግዚአብሔር ያ የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን በግልጽ ያረጋግጣል። ሲቀጥል በዘፍ 35:14 ላይ ያዕቆብ ባቆመው ሐውልት ላይ ዘይት አፍስሶ ነበር። ይህ በጣም አስፈላጊ ነጥብ ነው። ምክንያቱም በኦሪት አስተምህሮ የዘይት መሥዋዕት ቁርባን ተብሎ ተጠርቷል። ለምሳሌ፦ "40 ከአንዱ ጠቦትም ጋር የኢን መስፈሪያ አራተኛ እጅ በሆነ ተወቅጦ #በተጠለለ_ዘይት የተለወሰ የኢፍ መስፈሪያ አሥረኛ እጅ መልካም ዱቄት፥ ደግሞ ለመጠጥ ቍርባን የኢን መስፈሪያ አራተኛ እጅ የወይን ጠጅ ታቀርባለህ 41 ሁለተኛውንም ጠቦት በማታ ታቀርበዋለህ፥ እንደ ማለዳውም #የእህልና የመጠጥ #ቍርባን ታደርግበታለህ፤ ለእግዚአብሔር ጣፋጭ ሽቱ እንዲሆን የእሳት ቍርባን ይሆናል" (ዘጽ 29:40-41) በዚህ ቦታ ላይ ለእግዚአብሔር ስለሚቀርብ የእህል ቁርባን እናነባለን። የእህሉ ቁርባን ብዙ ነገሮችን ያካተተ ሲሆን ካካተታቸውም ነገሮች አንዱ ዘይት ነው። ይህ ዘይት የእህል ቁርባን እንደሆነ ያረጋግጣል። በዚህ ቦታ ላይ #የእህል_ቁርባን ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጥ ቃል "מִנְחַ֨/ሚንኻ" የሚለው የዕብራይስጥ ቃል ነው (H4503) ሌላ ምሳሌ፦ "ማናቸውም ሰው #የእህል_ቍርባን ለእግዚአብሔር ሲያቀርብ ቍርባኑ ከመልካም ዱቄት ይሁን፤ #ዘይትም_ያፈስስበታል፥ ዕጣንም ይጨምርበታል" (ዘሌ 2:1) በዚህ ቦታ ላይም ለእግዚአብሔር ስለሚቀርብ የእህል ቁርባን እናነባለን። ማንኛውም ሰው የእህል ቁርባን ሲያቀርብ በመልካሙ ዱቄት ላይ ዘይት ሊያፈስስበት እንደሚገባ ይናገራል። ይህ ዘይት የእህል ቁርባን እንደሆነ ያረጋግጣል። በዚህ ቦታ ላይም #የእህል_ቁርባን ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጥ ቃል "מִנְחַ֨/ሚንኻ" የሚለው የዕብራይስጥ ቃል ነው (H4503) ✍️ ስለዚህ በዘፍ 35:14 እና በዘፍ 28:18 ላይ ያዕቆብ ተገልጦለት ለነበረው እግዚአብሔር/የእግዚአብሔር መልአክ ሐውልት አቁሞ ዘይት ሲያፈስስበት የእህል ቁርባን ወይም "מִנְחַ֨/ሚንኻ" እያቀረበ ነበር። ዘይት የእህል ቁርባን ወይም "מִנְחַ֨/ሚንኻ" ነውና። ይህ ጌዴዎን ለምን ለእግዚአብሔር መልአክ ቁርባን ለማቅረብ እንዳልተቸገረ በሚገባ ያረጋግጣል። "ወደ አንተም እስክመለስ ድረስ፥ #ቍርባኔንም አምጥቼ እስካቀርብልህ ድረስ፥ እባክህ፥ ከዚህ አትላወስ አለው። እርሱም። እስክትመለስ ድረስ እቆያለሁ አለ" (መሳ 6:18) ጌዴዎን የተገለጠለት አካል የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን በጠረጠረ ጊዜ እርሱ መሆኑን ለማረጋገጥ ያቀረበለት ቁርባን ነው። በመሳ 6:18 ላይ #ቁርባን ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጥ ቃል ያው ራሱ "מִנְחַ֨/ሚንኻ" የሚለው ቃል ነው። ጌዴዎን እንደ ኦሪት ትዕዛዝ መሰረት (ዘዳ 6:6-9) የኦሪትን ቃል ያውቅ ስለነበር (መሳ 6:13) ለእግዚአብሔር መልአክ የእህል ቁርባን ወይም "מִנְחַ֨/ሚንኻ" ማቅረብ እንደሚፈቀድ በኦሪት ላይ ካለው ከያዕቆብ ታሪክ አውቋል። ያዕቆብ ሁለት ጊዜ ለእግዚአብሔር መልአክ ዘይት እንዳፈሰሰ፥ ዘይት ደግሞ የእህል ቁርባን እንደሆነ በሙሴ መጻሕፍት ተጽፏል። ስለዚህ በኦሪት መሰረት ለእግዚአብሔር መልአክ የእህል ቁርባን ማቅረብ ይቻላል፥ ደግሞም ቀርቧል ማለት ነው። ስለዚህ ይህን የሚያውቀው ጌዴዎን የተገለጠለት አካል የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን ማረጋገጥ በፈለገ ጊዝ የእህል ቁርባን አቀረበለት። በቀጥታ "..ቁርባኔን እስካቀርብልህ.." ያለው ለዚህ ነው። ይህ የእግዚአብሔር ልጅ/መልአክ መሥዋዕት የሚቀርብለት አምላክ መሆኑን ከማረጋገጥ ባሻገር ከጥንት ጀምሮ በአባቶች በወጥነት ሲመለክ የነበረው የብሉይ ኪዳኑ እግዚአብሔር መሆኑን በማያሻማ አኳሃን ያረጋግጣል። ▶️ ይቀጥላል

Открыть в Telegram
Просмотры3 750−14%к среднему
Пересылки—
Реакции14
Комментарии—
#1590Текст

🚩 የእግዚአብሔር መልአክና ጌዴዎን (ክፍል 12) ባለፈው ክፍል ላይ መለኮት የሆነው የእግዚአብሔር ልጅ በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር መልአክ በመባል ይገለጥ እንደነበር እና በዚህ መንገድ ከተገለጠባቸው አጋጣሚዎች አንዱ የሆነውን የጌዴዎንን ታሪክ ማየት ጀምረን ነበር። ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ለመግለጽ እንደሞከርነው መልአክ የሚለው ቃል በዕብራይስጥ "ማልአኽ/מַלְאַ֥ךְ" በግሪክ ደግሞ "አንጌሎስ/ἄγγελος" ሲሆን ትርጉሙ መልእክተኛ ማለት ነው። የመልእክተኝነት ግብር ያለው የትኛውም አካል መልአክ/መልእክተኛ ተብሎ ይጠራል። የመልእክተኛው ባህርይ ሰዋዊ ይሁን፥ የፍጡራን መናፍስት ይሁን መለኮታዊ ይሁን የሚታወቀው በአውዱ ነው። እንጂ አንድ አካል መልአክ ስለተባለ ብቻ ከፍጡራን መናፍስት አንዱ ነው ማለት አይደለም። የእግዚአብሔር ልጅም መልአክ የተባለው የአባቱ መልእክተኛ ስለነበር እንጂ ፍጡር ስለሆነ አይደለም። እግዚአብሔር ቢፈቅድ ከባለፈው ክፍል በመቀጠል የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ የእግዚአብሔር መልአክ በመባል ለጌዴዎን የተገለጠበትን ክስተት ማየት እንቀጥላለን፦ "ጌዴዎንም የእግዚአብሔር መልአክ እንደ ሆነ አየ ጌዴዎንም አቤቱ አምላኬ ሆይ #ወዮልኝ የእግዚአብሔርን #መልአክ ፊት ለፊት #አይቻለሁና አለ" (መሳ 6:22) ባለፉት ተከታታይ ክፍሎች ጌዲኦን እንዴት በኦሪት ላይ ካለው የያዕቆብ ታሪክ ለእግዚአብሔር መልአክ መሥዋዕት ማቅረብ እንደሚቻል እንዳወቀ እያየን ነበር። ባለፈው ክፍል ለማየት እንደሞከርነው በዘፍ 35:1 ላይ ያዕቆብ በታዘዘው መሰረት መሠዊያ የሰራለት አምላክ በዘፍ 31:10-13 ላይ የተገለጠለት የእግዚአብሔር መልአክ ነው። ስለዚህ ያዕቆብም መሠዊያ እንደሰራ ከታዘዘ በኋላ ቤተሰቡንና ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሁሉ እንግዶችን አማልክት ከመካከላቸው እንዲያስወግዱ፥ ንጹሐንም እንዲሆኑ፥ ልብሳቸውንም እንዲለውጡ ይነግራቸዋል (ዘፍ 35:2) ከዚያም በመከራው ጊዜ ለሰማው በሄደበት መንገድ ከእርሱ ጋር ለነበረው እግዚአብሔር መሠውያንን እንደሚያደርግ ይገልጽላቸዋል። ከዚያም በእጆቻቸው የነበሩትን እንግዶች አማልክትና በጆሯቸው ያሉትን ጉትቾች ሰጡት እርሱም በሴኬም አጠገብ ባለችው አድባር ዛፍ በታች ቀበራቸው (ዘፍ 35:4) ተነስውም ሄዱ የእግዚአብሔርም ፍርሃት በዙሪያቸው ባሉት ከተሞች ሁሉ ወደቀ የያዕቆብንም ልጆች ለማሳደድ አልተከተሏቸውም (ዘፍ 35:5) ከዚያም እርሱና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሰዎች እግዚአብሔር እንዳዘዘው በከነዓን ምድር ወዳለችው ወደ ሎዛ መጡ፥ እርሷም ቤቴል ናት (ዘፍ 35:6) ከዚያም አድርግ እንደተባለው በዚያ በቤቴል ከወንድሙ ፊት ሸሽቶ በነበረበት ጊዜ ተገልጦለት ለነበረው እግዚአብሔር መሠዊያ ሰራ፥ የዚያንም ቦታ ስም አልቤቴል አለው (ዘፍ 35:7) ኤልቤቴል ማለት "የእግዚአብሔር ቤት አምላክ" ማለት ነው። ከዚያም፦ " #እግዚአብሔርም ለያዕቆብ ከሁለት ወንዞች መካከል ከሶርያ ከተመለሰ በኋላ #እንደ_ገና ተገለጠለት ባረከውም" (ዘፍ 35:9) ያዕቆብ መሠዊያውን ከሰራ በኋላ እግዚአብሔር እንደገና ተገለጠለት። እንደገና ተገለጠለት ማለት ምን ማለት ነው? እንደገና ተገለጠለት ማለት ከዚህ በፊት ተገልጦለት ነበር ማለት ነው። ስለዚህ እንደገና ሲል የትኛውን መገለጥ እያመለከተ ነው? በዘፍ 35:1 ላይ እግዚአብሔር ያዕቆብን ከወንድምህ ከዔሳው በሸሸህ ጊዜ ለተገለጠልህ እግዚአብሔር መሠዊያ ስራ ብሎት ነበር። እግዚአብሔር ለያዕቆብ ከወንድሙ ከዔሳው በሸሸ ጊዜ የተገለጠለት በዘፍ 28:11-19 ነው። ስለዚህ ያኔ በዘፍ 28:11-19 የተገለጠለት እግዚአብሔር ነው አሁን በዘፍ 35:9 ላይ እንደገና የተገለጠለት ማለት ነው። እንደገና ሲል ልክ እንደ ዘፍ 28:11-19 ተገለጠለት ማለት ነው። በዘፍ 28:11-19 ለያዕቆብ የተገለጠለት አምላክ ግን የእግዚአብሔር መልአክ ነው (ዘፍ 31:10-13) ስለዚህ በዘፍ 35:9 ላይ የተገለጠለት እግዚአብሔር ያ የእግዚአብሔር መልአክ ነው ማለት ነው። ✍️ በዘፍ 35:9 ላይ ለያዕቆብ የተገለጠለት እግዚአብሔር የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑ በዘፍ 35:7 ላይ ያዕቆብ የሰራው መሰዊያ ለእርሱ መሆኑን በማያሻማ ሁኔታ ያረጋግጣል! ጌዴዎን ከእርሱ በፊት የተጻፈውን ይህን የኦሪት ቃል ስለሚያውቅ (መሳ 6:13) ለእግዚአብሔር መልአክ መሥዋዕት ማቅረብ አልቸገረውም። ወደ ያዕቆብ ታሪክ ስንመለስ፥ በዘፍ 35:9 ላይ እግዚአብሔር/የእግዚአብሔር መልአክ ከተገለጠለት በኋላ ይባርከዋል። ስሙ እስራኤል እንደሆነና ያዕቆብ ተብሎ መጠራት እንደሌለበት (ዘፍ 35:10) ሁሉን ቻይ አምላክ እርሱ እንደሆነ እና እንዲበዛ፥ እንዲባዛ፥ የሕዝብና የአሕዛብ ማህበር ከእርሱ እንደሚሆን፥ ነገሥታትም ከጉልበቱ እንደሚወጡ (ዘፍ 35:11) ለአብርሃም እና ለይስሐቅ የሰጣትን ምድር ለእርሱ እንደሚሰጠው፥ ከእርሱም በኋላ ለዘሩ ምድሪቱን እንደሚሰጥ (ዘፍ 35:12) ቃል ይገባለታል። ከዚያም ቃል ከገባለት በኋላ ያ የተገለጠለት እግዚአብሔር ወደ ላይ ወጣ፦ " #እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ከተነጋገረበት ስፍራ ወደ #ላይ_ወጣ" (ዘፍ 35:13) መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን የሞላ መለኮት ነው (ኤር 23:24 መዝ 139:8) ስለዚህ ከየት ነው ወደ ላይ የወጣው? በሁሉ ቦታ ያለ አምላክ እንዴት ወደ ላይ ወጣ ሊባልለት ቻለ? በዚህ ቦታ ላይ እግዚአብሔር ወደ ላይ ወጣ የተባለው እግዚአብሔር እየተባለ ያለው አካል የእግዚአብሔር መልአክ በመሆኑ ነው። እንደሚታወቀው የእግዚአብሔር መልአክ በሰው አምሳል ይገለጣል (ዘፍ 32:24-30 ኢያ 5:13-15 ዘኁ 22:23) ስለዚህ ወደ ላይ ሊወጣ ወይም ሊያርግ በሚችልበት መልኩ የሚገለጠው እርሱ ነው። ስለዚህ በዚህ ቦታ ላይ እግዚአብሔር እየተባለ ያለው እርሱ ስለሆነ ወጣ ሊባልለት ችሏል። ወደ ላይ ወጣ ወይም ዐረገ ሊባልለት የሚችለው የእግዚአብሔር መልአክ ለመሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ግልጽ ማስረጃ ይሰጠናል፦ "ነበልባሉም ከመሠዊያው ላይ ወደ ሰማይ በወጣ ጊዜ #የእግዚአብሔርም_መልአክ በመሠዊያው ነበልባል ውስጥ #ዐረገ ማኑሄና ሚስቱም ተመለከቱ በምድርም በግምባራቸው ተደፉ" (መሳ 13:20) በዚህ ቦታ ላይ የእግዚአብሔር መልአክ ለማኑሄና ለሚስቱ ከተገለጠ በኋላ በመሠዊያው ነበልባል ውስጥ እንዳረገ እናያለን። እነርሱን ካነጋገራቸው በኋላ ሲሰወርባቸው፥ የተሰወረባቸው ወደ ላይ በመውጣት ወይም በማረግ ነው። በዚህ ቦታ ላይ "ዐረገ" ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጥ ቃል "יַּ֥עַל/ይዓል" የሚለው ቃል ሲሆን በዘፍ 35:13 ላይ "ወደ ላይ ወጣ" ተብሎ የተተረጎመው ራሱ የዕብራይስጥ ቃል ነው (Strong's H5927) ስለዚህ ሊያርግ ወይም ሊወጣ በሚችልበት መንገድ ለሰዎች የሚገለጠው የእግዚአብሔር መልአክ ነው ማለት ነው። ይህ በዘፍ 35:13 ላይ ለያዕቆብ የተገለጠውና ያዕቆብም መሠዊያ የሰራለት እግዚአብሔር ያ በዘፍ 31:10-13 ላይ የቤቴል አምላክ እኔ ነኝ ያለው የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን በሚገባ ያረጋግጣል። ስለዚህ ጌዴዎን የእግዚአብሔር መልአክ ሲገለጥለት እርሱ መሆኑን ለማረጋገጥ መሥዋዕት ለማቅረብ አልተቸገረም። ምክንያቱም የእግዚአብሔር መልአክ መሥዋዕት እንደሚቀርብለት ከያዕቆብ ታሪክ ያውቃልና። ከዚህ በተጨማሪም ካነጋገረው በኋላ ሲሰወርበት (መሳ 6:21) የተገለጠለት የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን በይበልጥ አረጋገጠ። ያዕቆብ መሠዊያ ከሰራለት በኋላም እንዲሁ ተሰውሮበታልና (ዘፍ 35:13) ▶️ ይቀጥላል

Открыть в Telegram
Просмотры4 130−6%к среднему
Пересылки—
Реакции13
Комментарии—
#1589Текст

🚩 የእግዚአብሔር መልአክና ጌዴዎን (ክፍል 11) ባለፈው ክፍል ላይ መለኮት የሆነው የእግዚአብሔር ልጅ በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር መልአክ በመባል ይገለጥ እንደነበር እና በዚህ መንገድ ከተገለጠባቸው አጋጣሚዎች አንዱ የሆነውን የጌዴዎንን ታሪክ ማየት ጀምረን ነበር። ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ለመግለጽ እንደሞከርነው መልአክ የሚለው ቃል በዕብራይስጥ "ማልአኽ/מַלְאַ֥ךְ" በግሪክ ደግሞ "አንጌሎስ/ἄγγελος" ሲሆን ትርጉሙ መልእክተኛ ማለት ነው። የመልእክተኝነት ግብር ያለው የትኛውም አካል መልአክ/መልእክተኛ ተብሎ ይጠራል። የመልእክተኛው ባህርይ ሰዋዊ ይሁን፥ የፍጡራን መናፍስት ይሁን መለኮታዊ ይሁን የሚታወቀው በአውዱ ነው። እንጂ አንድ አካል መልአክ ስለተባለ ብቻ ከፍጡራን መናፍስት አንዱ ነው ማለት አይደለም። የእግዚአብሔር ልጅም መልአክ የተባለው የአባቱ መልእክተኛ ስለነበር እንጂ ፍጡር ስለሆነ አይደለም። እግዚአብሔር ቢፈቅድ ከባለፈው ክፍል በመቀጠል የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ የእግዚአብሔር መልአክ በመባል ለጌዴዎን የተገለጠበትን ክስተት ማየት እንቀጥላለን፦ "ጌዴዎንም የእግዚአብሔር መልአክ እንደ ሆነ አየ፤ ጌዴዎንም። አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ #ወዮልኝ፤ የእግዚአብሔርን #መልአክ ፊት ለፊት #አይቻለሁና አለ" (መሳ 6:22) ባለፉት ተከታይ ክፍሎች ጌዴዎን ለእግዚአብሔር መልአክ መሥዋዕት ማቅረብ እንደሚቻል ያወቀበትን የኦሪት ክፍል መመልከት ጀምረን ነበር። ይህ የኦሪት ክፍል ዘፍ 35:1 ሲሆን በዚያ ክፍል ላይ ያዕቆብ ወደ ቤቴል ሄዶ ከወንድሙ ከዔሳው በሸሸ ጊዜ ለተገለጠለት እግዚአብሔር መሠዊያ እንዲሰራ የታዘዘበት ታሪክ ተዘግቧል። ያዕቆብ ከወንድሙ ከዔሳው በሸሸ ጊዜ እግዚአብሔር ለእርሱ የተገለጠበትን ታሪክ የምናገኘው በዘፍ 28:11-19 ነው። እግዚአብሔር በሕልም ለያዕቆብ ይገለጥለታል (ዘፍ 28:12-13) ከተገለጠለት ድንጋይን ሐውልት አድርጎ ያቆመውና ዘይት ያፈስስበታል (ዘፍ 28:18) የዚያንም ቦታ ስም ቤቴል ብሎ ይጠራዋል (ዘፍ 28:19) ከዚያም በዚያ በቤቴል ለተገለጠለት እግዚአብሔር ስዕለትን ይሳላል (ዘፍ 28:20-22) ይህ ከሆነ ከረዥም ጊዜ በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ በሕልም ተገልጦ "ሐውልት የቀባህበት በዚያም ለእኔ ስዕለት የተሳልክበት የቤቴል አምላክ እኔ ነኝ" ይለዋል (ዘፍ 31:10-13) ይህ በዘፍ 28:11-22 ያዕቆብ ከወንድሙ ከዔሳው በሸሸ ጊዜ በቤቴል የተገለጠለት አምላክ የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን ያሳያል። ስለዚህ በዘፍ 35:1 ላይ "ተነስተህ ወደ ቤቴል ሂድ በዚያም ኑር፥ ከወንድምህ ከዔሳው በሸሸህ ጊዜ ለተገለጠልህ እግዚአብሔር መሠዊያ ስራ" ሲል ለእግዚአብሔር መልአክ መሠዊያ ስራ ማለት ነው። በዘፍ 35:1 ላይ መሠዊያ እንዲሰራለት የታዘዘው እግዚአብሔር የእግዚአብሔር መልአክ ለመሆኑ ተጨማሪ ሰዋሰዋዊ (Grammatical) ማስረጃ አለ። እንመልከተው፦ "እግዚአብሔርም ያዕቆብን አለው። ተነሥተህ ወደ ቤቴል ውጣ፥ በዚያም ኑር፤ ከወንድምህ ከዔሳው ፊት በሸሸህ ጊዜ ለተገለጠልህ #ለእግዚአብሔርም መሠውያውን አድርግ" (ዘፍ 35:1) በዘፍ 35:1 ላይ "ከወንድምህ በሸሸህ ጊዜ ለተገለጠልህ እግዚአብሔር" በሚለው ሀረግ ውስጥ #እግዚአብሔር ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጥ ቃል "אֵל֙/ኤል" የሚለው ቃል ሲሆን (Strong's H410) አምላክ ማለት ነው። በዘፍጥረት መጽሐፍ ውስጥ ይህ ቃል በተደጋጋሚ ለእግዚአብሔር እንደ መጠሪያ ጥቅም ላይ የዋለ ቃል ሲሆን በዚህ ቦታ ላይ መጠቀሱ እግዚአብሔር እየተባለ ያለው የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን ያረጋግጣል። ምክንያቱም በዘፍ 31:10-13 ላይ የእግዚአብሔር መልአክ "..የቤቴል አምላክ እኔ ነኝ.." ሲል የተጠቀመው ቃል ይህን ቃል ነው። "11 #የእግዚአብሔርም_መልአክ በሕልም። ያዕቆብ ሆይአለኝ፤ እኔም። እነሆኝ አልሁት 12 እንዲህም አለኝ። ዓይንህን አቅንተህ እይ፤ በበጎችና በፍየሎች ላይ የሚንጠላጠሉት የበጎችና የፍየሎች አውራዎች ሽመልመሌ መሳዮችና ዝንጕርጕሮች ነቁጣ ያለባቸውም ናቸው፤ ላባ በአንተ ላይ የሚያደርገውን ሁሉ አይቼአለሁና 13 ሐውልት የቀባህበት በዚያም ለእኔ ስእለት የተሳልህበት #የቤቴል_አምላክ_እኔ_ነኝ፤ አሁንም ተነሥተህ ከዚህ አገር ውጣ፥ ወደ ተወለድህበትም ምድር ተመለስ" (ዘፍ 31:11-13) "የቤቴል አምላክ እኔ ነኝ" በሚለው ሀረግ "አምላክ" ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጥ ቃል ዘፍ 35:1 ላይ ያለው ራሱ "אֵל֙/ኤል" የሚለው ቃል ነው (Strong's H410) ዘፍ 31:11-13 ላይ ግን ሲጠቀስ ከውስን መስጻምር ወይም definite article ጋር ነው። ስለዚህ "הָאֵל/ሀ ኤል" ወይም "The God" ማለት ነው። በኢንግሊዘኛው ትርጉም ላይም "The God of Bethel" ተብሎ ተተርጉሟል። በዘፍ 35:1 እና በዘፍ 31:10-13 መካከል ካለው አውዳዊ/contextual አንድነት ባሻገር ይህን አይነት ሰዋሰዋዊ/grammatical አንድነት መኖሩ ያዕቆብ መሠዋት የሰራለት እግዚአብሔር የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን ያረጋግጣል። ✍️ በዘፍ 35:1 ላይ እግዚአብሔር በሶስተኛ መደብ የተናገረውም ለዚህ ነው። እግዚአብሔር አምላክ በዘፍ 35:1 ላይ ያዕቆብን መሠዊያ እንዲሰራ ሲያዝዘው "ለእኔ ስራልኝ" አላለውም። በሶስተኛ መደብ "ለተገለጠልህ እግዚአብሔር መሠዊያ ስራ" ነበር ያለው። በሶስተኛ መደብ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ስራ ያለው እግዚአብሔር ብሎ እየጠራ ያለው ልጁ/መልአኩ ስለነበር ነው። እግዚአብሔር አምላክ ለልጁ ለኢየሱስ ክርስቶስ አምልኮ እንዲቀርብ ያዘዘበት የብሉይ ኪዳን ክፍል ነው። ባለፉት ተከታታይ ክፍሎች ለማየት እንደሞከርነው ጌዴዎን ከእርሱ በፊት የተጻፉትን ቅዱሳት መጻሕፍት የሚያውቅ ሰው ነው (መሳ 6:13) ምክንያቱም በኦሪት ላይ እስራኤላውያን የኦሪትን ቃል በሙሉ በዕለት ተዕለት ኑሯቸው እንዲጫወቱት፥ እንዲያሰላስሉት በእግዚአብሔር ቃል ታዝዘዋልና (ዘዳ 6:6-9) ጌዴዎንም ይህንኑ ያደርግ ስለነበር ከእርሱ ዘመን በፊት የተጻፈውን ኦሪት ያውቃል። ስለዚህ አሁን ባየነው የኦሪት ክፍል ላይ የእግዚአብሔር መልአክ መሥዋዕት እንደቀረበ ያውቅ ነበር። ይህ ማለት ለእግዚአብሔር መልአክ መሥዋዕት ማቅረብ እንደሚቻል ያውቃል ማለት ነው። ስለዚህ ይህን ስለሚያውቅ የእግዚአብሔር መልአክ ሲገለጥለት እርሱ መሆኑን ለማረጋገጥ መሥዋዕት አቀረበለት። ይህ የእግዚአብሔር መልአክ መለኮት መሆኑን በሚገባ ያረጋግጣል። ወደ ያዕቆብ ታሪክ ስንመለስ፥ ያዕቆብ ወደ ቤቴል ሄዶ መሠዊያ እንዲሰራ ከታዘዘ በኋላ ቤተሰቡንና ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሁሉ እንግዶችን አማልክት ከመካከላቸው እንዲያስወግዱ፥ ንጹሐንም እንዲሆኑ፥ ልብሳቸውንም እንዲለውጡ ይነግራቸዋል (ዘፍ 35:2) ከዚያም በመከራው ጊዜ ለሰማው በሄደበት መንገድ ከእርሱ ጋር ለነበረው እግዚአብሔር መሠውያንን እንደሚያደርግ ይገልጽላቸዋል። የመከራዬ ጊዜ የሚለው በዘፍ 32 ላይ ወንድሙ ዔሳው ወደ እርሱ የመጣበትን ክስተት ሲሆን፥ በዚያ ጊዜ ጸሎቱ ሰምቶ ያዳነው አምላክ የእግዚአብሔር መልአክ ነው (ዘፍ 32:9-12 ዘፍ 32:24-30) እንዲሁም በሄደበት ሁሉ ከእርሱ እንደሚሆን ቃል የገባለት የእግዚአብሔር መልአክ ነው (ዘፍ 28:15/ዘፍ 31:11-13) ይህ በዘፍ 35:1 ላይ ከተሰጠው ትዕዛዝ ባሻገር በእርግጥም መሠዊያ እየሰራ የነበረው ለእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን ያረጋግጣል። ▶️ ይቀጥላል

Открыть в Telegram
Просмотры5 950+36%к среднему
Пересылки—
Реакции17
Комментарии—
#1588Текст

🚩 የእግዚአብሔር መልአክና ጌዴዎን (ክፍል 10) ባለፈው ክፍል ላይ መለኮት የሆነው የእግዚአብሔር ልጅ በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር መልአክ በመባል ይገለጥ እንደነበር እና በዚህ መንገድ ከተገለጠባቸው አጋጣሚዎች አንዱ የሆነውን የጌዴዎንን ታሪክ ማየት ጀምረን ነበር። ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ለመግለጽ እንደሞከርነው መልአክ የሚለው ቃል በዕብራይስጥ "ማልአኽ/מַלְאַ֥ךְ" በግሪክ ደግሞ "አንጌሎስ/ἄγγελος" ሲሆን ትርጉሙ መልእክተኛ ማለት ነው። የመልእክተኝነት ግብር ያለው የትኛውም አካል መልአክ/መልእክተኛ ተብሎ ይጠራል። የመልእክተኛው ባህርይ ሰዋዊ ይሁን፥ የፍጡራን መናፍስት ይሁን መለኮታዊ ይሁን የሚታወቀው በአውዱ ነው። እንጂ አንድ አካል መልአክ ስለተባለ ብቻ ከፍጡራን መናፍስት አንዱ ነው ማለት አይደለም። የእግዚአብሔር ልጅም መልአክ የተባለው የአባቱ መልእክተኛ ስለነበር እንጂ ፍጡር ስለሆነ አይደለም። እግዚአብሔር ቢፈቅድ ከባለፈው ክፍል በመቀጠል የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ የእግዚአብሔር መልአክ በመባል ለጌዴዎን የተገለጠበትን ክስተት ማየት እንቀጥላለን፦ "ጌዴዎንም የእግዚአብሔር መልአክ እንደ ሆነ አየ፤ ጌዴዎንም። አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ #ወዮልኝ፤ የእግዚአብሔርን #መልአክ ፊት ለፊት #አይቻለሁና አለ" (መሳ 6:22) ከዚህ በፊት በነበሩት ተከታታይ ክፍሎች ላይ የእግዚአብሔር መልአክ ለጌዴዎን ከተገለጠለት በኋላ በእርግጥም የተገለጠለት የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን ለማረጋገጥ ቁርባን እንዳቀረበለት አይተናል (መሳ 6:18-19) ስለዚህ ጌዴዎን ለእግዚአብሔር መልአክ መሥዋዕት ሊቀርብ እንደሚችል ያውቅ ነበር ማለት ነው። ይህን እንዴት ሊያውቅ ቻለ ከተባለ ከኦሪት ነው። እንደ ኦሪቱ ትዕዛዝ መሰረት (ዘዳ 6:6-9) ጌዴዎን ከእርሱ በፊት የተጻፉትን ቅዱሳት መጻሕፍት የሚያውቅ ሰው ስለነበር ማለት ነው (መሳ 6:13) ስለዚህ በኦሪት ላይ የቱ ጋር ነው ለእግዚአብሔር መልአክ መሥዋዕት የቀረበው? እንመልከተው፦ "10 እንዲህም ሆነ፤ በጎቹ በጎመጁ ጊዜ ዓይኔን አንሥቼ በሕልም አየሁ፤ እነሆም፥ በበጎችና በፍየሎች ላይ የሚንጠላጠሉት የበጎችና የፍየሎች አውራዎች ሽመልመሌ መሳዮችና ዝንጕርጕሮች ነቁጣ ያለባቸውም ነበሩ። 11 #የእግዚአብሔርም_መልአክ በሕልም። ያዕቆብ ሆይ አለኝ፤ እኔም። እነሆኝ አልሁት 12 እንዲህም አለኝ። ዓይንህን አቅንተህ እይ፤ በበጎችና በፍየሎች ላይ የሚንጠላጠሉት የበጎችና የፍየሎች አውራዎች ሽመልመሌ መሳዮችና ዝንጕርጕሮች ነቁጣ ያለባቸውም ናቸው፤ ላባ በአንተ ላይ የሚያደርገውን ሁሉ አይቼአለሁና 13 #ሐውልት_የቀባህበት በዚያም #ለእኔ_ስእለት_የተሳልህበት #የቤቴል_አምላክ_እኔ_ነኝ፤ አሁንም ተነሥተህ ከዚህ አገር ውጣ፥ ወደ ተወለድህበትም ምድር ተመለስ" (ዘፍ 31:10-13) ባለፉት ተከታታይ ክፍሎች ላይ እንዴት እግዚአብሔር በዘፍ 35:1 ላይ ለያዕቆብ ተነስቶ ወደ ቤቴል እንዲሄድ፥ በዚያም እንዲኖር፥ ከወንድሙ ከዔሳው በሸሸ ጊዜ ለተገለጠለት እግዚአብሔር መሠዊያ እንዲሰራ እንዳዘዘው ለማየት አይተናል። ያዕቆብ ከወንድሙ ከዔሳው የሸሸበት ታሪክ በዘፍ 27:1-45 የሚገኝ ሲሆን እንዴት በረከቱን በእናቱ ምክር በረከቱን እንደሰረቀው፥ በኋላ ላይም ሊገድለው ማሰቡን ሲረዳ ከወላጆቹ ተለይቶ በሁለቱ ወንዞች መካከል ወደ አለው ወደ አጎቱ ምድር ሸሽቶ እንደሄደ ለማየት ሞክረናል (ዘፍ 28:1-10) በመንገድ ላይ ሳለም ወደ አንድ ስፍራ እንደ ደረሰ፥ ጸሐይ ጠልቃ ነበርና ድንጋይ ተንተርሶ በዚያ እንዳደረ (ዘፍ 28:11) ለማየት ሞክረናል። ተኝቶ ሳለም ሕልም እንዳለመ፥ በሕልሙም በሰማይና በምድር መካከል መሰላለል ተተክሎ እንዳየና፥ በመሰላሉ ላይም የእግዚአብሔር መላእክት ሲወጡና ሲወርዱ እንደተመለከተ (ዘፍ 28:12) ለማየት ሞክረናል። ከዚያም በመሰላሉ ላይ እግዚአብሔር ተገልጦለት የአባቱ የአብርሃምና የይስሐቅ አምላክ እንደሆነ ይነግረዋል (ዘፍ 28:13) ከዚያም የተለያዩ ነገሮችን እንደሚያደርግለት ቃል ይገባለታል (ዘፍ 28:13-15) ከዚያም ያዕቆብ ከእንቅልፉ ተነስቶ ተንተርሶት የነበረውን ድንጋይ ወስዶ ሐውልት አድርጎ ያቆመዋል፥ በላዩም ዘይት ያፈስስበታል። ያንንም ስፍራ ቤቴል ብሎ ይጠራዋል። ከዚያ በፊት የቦታው ስም ሎዛ ነበርና (ዘፍ 28:16-19) ከዚያም በመቀጠል በዚያ በቤቴል ለተገለጠለት አምላክ ስዕለትን ይሳላል (ዘፍ 28:20-22) ✍️ ስለዚህ ይህ በቤቴል የተገለጠለት አምላክ ማነው? በዘፍጥረት 28 የምናነበው ክስተት ካለፈ በኋላ በዘፍ 31 ላይ የላባ ልጆች ያዕቆብ የአባታችን የሆነውን ነገር ሁሉ ወሰደ ይህን ሁሉ ክብር ከአባታችን ከብት አገኘ ሲሉ ይሰማል (ዘፍ 31:1) ያዕቆብም የላባን ፊት አየ ከእርሱ ጋር እንደ ድሮው አልሆነም (ዘፍ 31:3) ስለዚህ ከላባ ጋር አብረው መቀጠል የማይችሉበት ሁኔታ ተፈጠረ። በዚያን ጊዜም በዘፍ 31:10-13 እንደምናነበው የእግዚአብሔር መልአክ በሕልም ተገለጠለት። ከዚያም ሐውልት የቀባህበት በዚያም ለእኔ ስዕለት የተሳልህበት የቤቴል አምላክ እኔ ነኝ፥ ተነስተህ ከዚህ ሀገር ውጣ ወደ ተወለድህበትም ምድር ተመለስ አለው። ይህ የእግዚአብሔር መልአክ በዘፍጥረት 28 ላይ በቤቴል ለእርሱ የተገለጠለት እግዚአብሔር መሆኑን ያረጋግጣል። በዘፍ 31:10-13 ላይ የእግዚአብሔር መልአክ "..ሐውልት የቀባህበት.." ይላል። ያዕቆብ ሐውልት የቀባው በዘፍ 28:18 ነው። ቀጥሎም "..በዚያም ለእኔ ስዕለት የተሳልህበት.." ይላል። ያዕቆብ ስዕለት የተሳለው በዘፍ 28:20 ነው። ቀጥሎም "..የቤቴል አምላክ እኔ ነኝ.." ይላል። ለያዕቆብ በቤቴል አምላክ የተገለጠለት በዘፍ 28:13/ዘፍ 28:19 ነው። በስተመጨረሻም "..ወደ ተወለድህበት ምድር ተመለስ.." ይለዋል። ለያዕቆብ ወደዚህች ምድር እመልስሃለሁ ያለው በዘፍ 28:15 ላይ የተገለጠለት አምላክ ነው። በዘፍ 31:10-13 የእግዚአብሔር መልአክ እነዚህን ነገሮች በሙሉ ነኝ ማለቱ ያለ ምንም ጥርጥር ያዕቆብ ከወንድሙ ከዔሳው በሸሸ ጊዜ በቤቴል የተገለጠለት አምላክ መሆኑን ያረጋግጣል። ✍️ ስለዚህ በዘፍ 35:1 ላይ ያዕቆብ መሠዊያ ስራለት የተባለው እግዚአብሔር ማን እንደሆነ ግልጽ ይሆናል፦ "እግዚአብሔርም #ያዕቆብን አለው። ተነሥተህ ወደ #ቤቴል ውጣ፥ በዚያም ኑር፤ #ከወንድምህ_ከዔሳው ፊት #በሸሸህ ጊዜ #ለተገለጠልህ #ለእግዚአብሔርም_መሠውያውን አድርግ" (ዘፍ 35:1) በዘፍ 35:1 ላይ ያዕቆብ ወደ ቤቴል ሄዶ መሠዊያ እንዲሰራለት የታዘዘው እግዚአብሔር ከወንድሙ ከዔሳው በሸሸ ጊዜ ለተገለጠለት እግዚአብሔር ነው። ያዕቆብ ከወንድሙ ከዔሳው በሸሸ ጊዜ እግዚአብሔር የተገለጠለት ታሪክ የተዘገበው በዘፍ 28:11-22 ነው። ነገር ግን ያ በዘፍጥረት 28 የተገለጠለት አምላክ ማነው ስንል በዘፍ 31:10-13 መሰረት የእግዚአብሔር መልአክ ነው። ስለዚህ ያዕቆብ መሠዊያ እንዲሰራለት የታዘዘው እግዚአብሔር የእግዚአብሔር መልአክ ነው ማለት ነው። የእግዚአብሔር መልአክ በቀጥታ እግዚአብሔር ተብሎ መጠራቱ፥ በቀጥታ አምላክ ነኝ ማለቱ፥ መሠዊያ ለእርሱ መሰራቱ በባህርይው መለኮት መሆኑን ያሳያል። ከዚያም ባሻገር ጌዴዎን እንዴት ለእግዚአብሔር መልአክ መሥዋዕት ሊቀርብ እንደሚችል እንዳወቀ ግልጽ ያደርጋል። በዚህ የኦሪት ክፍል ላይ ለእግዚአብሔር መልአክ መሥዋዕት ቀርቧልና። ▶️ ይቀጥላል

Открыть в Telegram
Просмотры5 500+26%к среднему
Пересылки—
Реакции9
Комментарии—
#1585Текст

🚩 የእግዚአብሔር መልአክና ጌዴዎን (ክፍል 9) ባለፈው ክፍል ላይ መለኮት የሆነው የእግዚአብሔር ልጅ በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር መልአክ በመባል ይገለጥ እንደነበር እና በዚህ መንገድ ከተገለጠባቸው አጋጣሚዎች አንዱ የሆነውን የጌዴዎንን ታሪክ ማየት ጀምረን ነበር። ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ለመግለጽ እንደሞከርነው መልአክ የሚለው ቃል በዕብራይስጥ "ማልአኽ/מַלְאַ֥ךְ" በግሪክ ደግሞ "አንጌሎስ/ἄγγελος" ሲሆን ትርጉሙ መልእክተኛ ማለት ነው። የመልእክተኝነት ግብር ያለው የትኛውም አካል መልአክ/መልእክተኛ ተብሎ ይጠራል። የመልእክተኛው ባህርይ ሰዋዊ ይሁን፥ የፍጡራን መናፍስት ይሁን መለኮታዊ ይሁን የሚታወቀው በአውዱ ነው። እንጂ አንድ አካል መልአክ ስለተባለ ብቻ ከፍጡራን መናፍስት አንዱ ነው ማለት አይደለም። የእግዚአብሔር ልጅም መልአክ የተባለው የአባቱ መልእክተኛ ስለነበር እንጂ ፍጡር ስለሆነ አይደለም። እግዚአብሔር ቢፈቅድ ከባለፈው ክፍል በመቀጠል የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ የእግዚአብሔር መልአክ በመባል ለጌዴዎን የተገለጠበትን ክስተት ማየት እንቀጥላለን፦ "ጌዴዎንም የእግዚአብሔር መልአክ እንደ ሆነ አየ፤ ጌዴዎንም። አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ #ወዮልኝ፤ የእግዚአብሔርን #መልአክ ፊት ለፊት #አይቻለሁና አለ" (መሳ 6:22) ባለፉት ክፍሎች ላይ የእግዚአብሔር መልአክ ለጌዴዎን ከተገለጠለት በኋላ ጌዴዎን ያ የተገለጠለት አካል የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን ለማረጋገጥ ቁርባን እንዳቀረበለት አይተናል (መሳ 6:18-19) የተገለጠለት አካል የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን ለማረጋገጥ ምልክት ይሆን ዘንድ ያቀረበለት ቁርባን ወይም መሥዋዕት ነው። ስለዚህ ከዚህ ክስተት በፊት እንኳ ለእግዚአብሔር መልአክ መሥዋዕት ሊቀርብ እንደሚችል ያምን ነበር ማለት ነው። እንዲህ ባያምን ኖሮ ቁርባን ባላቀረበለት ነበር። ጌዴዎን እንዴት ለእግዚአብሔር መልአክ መሥዋዕት ማቅረብ ይቻላል ብሎ ሊያምን ቻለ? ጌዴዎን ለእግዚአብሔር መልአክ መሥዋዕት ሊቀርብ እንደሚችል ያመነበት ምክንያት ከእርሱ በፊት ተጽፎ በነበረው ኦሪት ላይ ለእግዚአብሔር መልአክ መሥዋዕት ቀርቦ ስለነበር ነው። ጌዴዎን ደግሞ ከእርሱ በፊት ስለተጻፉት ቅዱሳት መጻሕፍት ያውቅ ስለነበር (መሳ 6:13) ኦሪት ላይ እንዳለው ለእግዚአብሔር መልአክ ቁርባን ወይም መሥዋዕት አቅርቧል። ✍️ ከባለፈው ክፍል በመቀጠል ኦሪት ላይ የቱ ጋር ለእግዚአብሔር መልአክ መሥዋዕት እንደቀረበ እናያለን፦ "11 ወደ #አንድ_ስፍራም ደረሰ፥ ፀሐይም ጠልቃ ነበርና ከዚያ አደረ፤ በዚያም ስፍራ #ድንጋይ አነሣ፥ ከራሱም በታች ተንተርሶ በዚያ ስፍራ ተኛ 12 #ሕልምም አለመ እነሆም #መሰላል #በምድር ላይ ተተክሎ፥ ራሱም ወደ #ሰማይ ደርሶ፥ እነሆም #የእግዚአብሔር_መላእክት ይወጡበት ይወርዱበት ነበር 13 እነሆም፥ #እግዚአብሔር በላይ ቆሞበት ነበር፥ እንዲህም አለ የአባትህ #የአብርሃም አምላክ #የይስሐቅም አምላክ እኔ #እግዚአብሔር ነኝ፤ ይህችን አንተ የተኛህባትን #ምድር ለአንተም ለዘርህም #እሰጣለሁ 14 ዘርህም እንደ ምድር አሸዋ ይሆናል እስከ ምዕራብና እስከ ምሥራቅ እስከ ሰሜንና እስከ ደቡብ ትስፋፋለህ፤ የምድርም አሕዛብ ሁሉ በአንተ #በዘርህም_ይባረካሉ 15 እነሆም እኔ #ከአንተ ጋር ነኝ፥ በምትሄድባትም መንገድ ሁሉ #እጠብቅሃለሁ፥ ወደዚችም ምድር #እመልስሃለሁ የነገርሁህን ሁሉ እስካደርግልህ ድረስ #አልተውህምና 16 ያዕቆብም ከእንቅልፉ ተነሥቶ በእውነት እግዚአብሔር በዚህ ስፍራ ነው እኔ አላወቅሁም ነበር አለ 17 ፈራ፥ እንዲህም አለ ይህ ስፍራ እንዴት ያስፈራ፤ ይህ ስፍራ የእግዚአብሔር ቤት ነው እንጂ ሌላ አይደለም፤ ይህም የሰማይ ደጅ ነው 18 ያዕቆብም ማልዶ ተነሣ፥ ተንተርሶት የነበረውንም #ድንጋይ ወስዶ #ሐውልት አድርጎ አቆመው፥ በላዩም #ዘይትን አፈሰሰበት 19 ያዕቆብም ያንን ስፍራ #ቤቴል ብሎ ጠራው አስቀድሞ ግን የዚያች ከተማ ስም ሎዛ ነበረ" (ዘፍ 28:11-19) ባለፈው ክፍል ላይ እግዚአብሔር አምላክ በዘፍ 35:1 ላይ ለያዕቆብ ወደ ቤቴል ሄዶ ከወንድሙ ከዔሳው በሸሸ ጊዜ ተገልጦለት ለነበረው እግዚአብሔር መሠዊያ እንዲሰራ እንዳዘዘው ተመልክተናል። ከዚያም ባሻገር በዘፍ 27:1-45 እና በዘፍ 28:1-10 ላይ ያዕቆብ እንዴት የወንድሙን የዔሳውን በረከት አታልሎ እንደወሰደና በኋላ ላይም ወንድሙ እንዳይገድለው ወደ አጎቱ ወደ ላባ ምድር የሸሸበትን ታሪክ ለማየት ሞክረናል። ከላይ ባለው በዚህ ክፍል ላይ ወደ አጎቱ ወደ ላባ ምድር እየተጓዘ በነበረበት ሰዓት ምን እንደተከሰተ እናነባለን። እርሱም እየተጓዘ በነበረበት ጊዜ ወደ አንድ ቦታ ደረሰ ጸሐይ ጠልቃ ስለነበር በዚያ ስፍራ ድንጋይ ተንተርሶ አደረ (ዘፍ 28:11) ከዚያም ሕልም አልሞ በሕልሙ መሰላል በሰማይና በምድር መካከል ተተክሎ በመሰላሉ ላይም የእግዚአብሔር መላእክት ሲወጡበትና ሲወርዱበት አየ (ዘፍ 28:12) በዚያም እግዚአብሔር በመሰላሉ ላይ ቆሞ ይገለጥለታል፥ የአባቶቹ የአብርሃምና የይስሐቅ አምላክ መሆኑንም ይነግዋል (ዘፍ 28:13) ከዚያም ከቁ.13-15 ላይ ይህችን ምድር ለእርሱና ለዘሩ እንደሚሰጠው፥ ዘሩ እንደምድር አሸዋ እንደሚበዛ፥ በአራቱም አቅጣጫ እንደሚስፋፋ፥ የምድር አሕዛብ ሁሉ በዘሩ እንደሚባረኩ፥ ከእርሱ ጋር እንደሚሆን፥ በሚሄድበት መንገድ ሁሉ እንደሚጠብቀው፥ ወደዚያችም ምድር እንደሚመልሰው፥ የነገረውን ነገር ሁሉ እስኪያደርግለት ድረስ እንደማይተወው ቃል ገባለት። በዚያን ጊዜም ያዕቆብ ከእንቅልፉ ተነስቶ ተንተርሶት የነበረውን ድንጋይ ወስዶ ሐውልት አድርጎ አቆመው፥ በላዩም ዘይት አፈሰሰበት። ያንንም ስፍራ ቤቴል ብሎ ጠራው። ከዚያ በፊት የቦታው ስም ሎዛ ነበርና (ዘፍ 28:16-19) ከዚያም ያዕቆብ በዚህ በቤቴል ለተገለጠለት አምላክ ስዕለት ይሳላል፦ "20 ያዕቆብም እንዲህ ብሎ #ስእለት ተሳለ #እግዚአብሔር_ከእኔ_ጋር_ቢሆን፥ በምሄድባትም በዚች #መንገድ_ቢጠብቀኝ፥ የምበላውንም #እንጀራ የምለብሰውንም #ልብስ ቢሰጠኝ 21 ወደ አባቴ #ቤትም በጤና #ብመለስ፥ እግዚአብሔር #አምላኬ ይሆንልኛል 22 ለሐውልት የተከልሁት ይህም ድንጋይ የእግዚአብሔር ቤት ይሆናል፤ ከሰጠኸኝም ሁሉ ለአንተ #ከአሥር እጅ #አንዱን_እሰጥሃለሁ" (ዘፍ 28:20-22) ያዕቆብ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ቢሆን፥ በሚሄድበት በዚህ መንገድ ቢጠብቀው፥ የሚበላውን እንጀራና የሚለብሰውን ልብስ ቢሰጠው፥ ወደ አባቱም ቤት በጤና ቢመለስ እግዚአብሔር አምላኩ እንደሚሆነውና ከሰጠው ሁሉ ከአስር እጅ አንዱን እንደሚሰጥ ተሳለ። የያዕቆብ ስዕለት በሙሉ ቀድሞ እግዚአብሔር ቃል በገባለት ነገር የተመሰረተ ነው። ከአንተ ጋር እሆናለሁ፥ እጠብቅሃለሁ ስላለው (ቁ.15) ወደዚህችም ምድር እመልስልሃለሁ (ቁ.16) ስላለው በተነገረው ቃል መሰረት እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ቢሆን፥ ቢጠብቀኝ፥ ወደ አባቴም ቤት በጤና ብመለስ በማለት ስዕለት ተስሏል። ✍️ ስለዚህ ያዕቆብ ከወንድሙ ከዔሳው በሸሸ ጊዜ እግዚአብሔር የተገለጠለት በዚህ ቦታ ነው። ከዚያ በፊት የቦታው ስም ቤቴል አልነበረም። እግዚአብሔር ከተገለጠለት በኋላ ግን ያዕቆብ ቦታውን ቤቴል ብሎ ጠርቶታል። ስለዚህ በዘፍ 35:1 ላይ ወደ "ቤቴል ውጣ በዚያም ኑር ከወንድምህ ከዔሳው በሸሸህ ጊዜ ለተገለጠልህ እግዚአብሔር መሠዊያ ስራ" ሲል በዘፍ 28:11-19 ላይ በቤቴል ለተገለጠልህ እግዚአብሔር መሠዊያ ስራ ማለት ነው። ይህ በቤቴል የተገለጠለት አምላክ ግን ማነው? ▶️ ይቀጥላል

Открыть в Telegram
Просмотры6 380+46%к среднему
Пересылки—
Реакции11
Комментарии—
#1584Текст

🚩 የእግዚአብሔር መልአክና ጌዴዎን (ክፍል 8) ባለፈው ክፍል ላይ መለኮት የሆነው የእግዚአብሔር ልጅ በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር መልአክ በመባል ይገለጥ እንደነበር እና በዚህ መንገድ ከተገለጠባቸው አጋጣሚዎች አንዱ የሆነውን የጌዴዎንን ታሪክ ማየት ጀምረን ነበር። ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ለመግለጽ እንደሞከርነው መልአክ የሚለው ቃል በዕብራይስጥ "ማልአኽ/מַלְאַ֥ךְ" በግሪክ ደግሞ "አንጌሎስ/ἄγγελος" ሲሆን ትርጉሙ መልእክተኛ ማለት ነው። የመልእክተኝነት ግብር ያለው የትኛውም አካል መልአክ/መልእክተኛ ተብሎ ይጠራል። የመልእክተኛው ባህርይ ሰዋዊ ይሁን፥ የፍጡራን መናፍስት ይሁን መለኮታዊ ይሁን የሚታወቀው በአውዱ ነው። እንጂ አንድ አካል መልአክ ስለተባለ ብቻ ከፍጡራን መናፍስት አንዱ ነው ማለት አይደለም። የእግዚአብሔር ልጅም መልአክ የተባለው የአባቱ መልእክተኛ ስለነበር እንጂ ፍጡር ስለሆነ አይደለም። እግዚአብሔር ቢፈቅድ ከባለፈው ክፍል በመቀጠል የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ የእግዚአብሔር መልአክ በመባል ለጌዴዎን የተገለጠበትን ክስተት ማየት እንቀጥላለን፦ "ጌዴዎንም የእግዚአብሔር መልአክ እንደ ሆነ አየ፤ ጌዴዎንም። አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ #ወዮልኝ፤ የእግዚአብሔርን #መልአክ ፊት ለፊት #አይቻለሁና አለ" (መሳ 6:22) የእግዚአብሔር መልአክ ጌዴዎን ያቀረበለትን መሥዋዕት ተቀብሎ ከተሰወረ በኋላ ጌዴዎን ለእርሱ ተገልጦ የነበረው ማን እንደሆነ አወቀ። ጌዴዎን ለእርሱ ተገልጦ የነበረው አካል እንደ አምላክ ሲያነጋግረው (መሳ 6:14 መሳ 6:16) ማንነቱን ለማረጋገጥ ቁርባንን እንደ ምልክት አቅርቦለታል (መሳ 6:17-18) ባለፈው ክፍል ላይ ለማየት እንደሞከርነው የእግዚአብሔር መልአክ መጀመሪያ ለጌዴዎን ተገልጦ ሲያነጋግረው ተራ ሰው የሚያነጋግረው መስሎት ነበር። በኋላ ግን እርሱን እንደ አምላክ ሲያነጋግረው የእግዚአብሔር መልአክ ይሆን እንደሆነ በመጠርጠር ምልክትን ጠይቆታል። ምክንያቱም በአምስቱ የኦሪት መጻሕፍት እና በኢያሱ መጽሐፍ በሰው አምሳል ተገልጦ እንደ አምላክ የሚናገረው ደግሞም ራሱን ከእግዚአብሔር በአካል የሚለየው የእግዚአብሔር መልአክ ነውና። ስለዚህ በእርግጥም የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን ለማረጋገጥ ቁርባኑን እንደ ምልክት አቀረበለት። ያን ያቀረበለትን ቁርባን ተቀብሎት ሲሰወር የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን አረጋገጠ። ነገር ግን ጌዴዎን ቁርባንን ለምን እንደ ምልክት አቀረበለት? ጌዴዎን ቁርባንን እንደ ምልክት ያቀረበው ያ የተገለጠለት አካል የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን ለማረጋገጥ ነው። ስለዚህ ለእግዚአብሔር መልአክ ቁርባን ወይም መሥዋዕት ሊቀርብ ይችላል የሚል መረዳት አለው ማለት ነው። ለእግዚአብሔር መልአክ ቁርባን ወይም መሥዋዕት ሊቀርብ ይችላል የሚለውን መረዳት ከየት አገኘው? በኦሪት ሕግ በግልጽ እንደተቀመጠው ከእግዚአብሔር በቀር ለማንም መሥዋዕት ማቅረብ ከልክል ነው (ዘጽ 22:20) ታዲያ ጌዴዎን ከጅምሩ ለእግዚአብሔር መልአክ ቁርባን ወይም መሥዋዕት ሊቀርብ ይችላል ብሎ እንዴት ሊያምን ቻለ? ጌዴዎን ለእግዚአብሔር መልአክ ቁርባን ወይም መሥዋዕት ሊቀርብ እንደሚችል ሊያምን የቻለው ከእርሱ በፊት በተጻፈው በኦሪት ውስጥ ስለ እግዚአብሔር መልአክ ከተባለው ነገር የተነሳ ነው። ከጌዴዎን ዘመን በፊት በተጻፈው ኦሪት ውስጥ ለእግዚአብሔር መልአክ መሥዋዕት ቀርቧል። ጌዴዎን ደግሞ ስለ ቀደሙት መጻሕፍት እውቀት ስለነበረው (መሳ 6:13) ያ የተገለጠለት አካል የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን ሲጠረጥር እርሱ መሆኑን ለማረጋገጥ መሥዋዕት አቅርቦለታል። ለእርሱ መሥዋዕት ሊቀርብ እንደሚችል ያውቃልና። በኦሪት ውስጥ የቱ ጋር ነው ለእግዚአብሔር መልአክ መሥዋዕት የቀረበው? ነጥብ በነጥብ እንመልከተው፦ "እግዚአብሔርም ያዕቆብን አለው። ተነሥተህ ወደ #ቤቴል ውጣ፥ #በዚያም ኑር፤ ከወንድምህ ከዔሳው ፊት በሸሸህ ጊዜ #ለተገለጠልህ #ለእግዚአብሔርም_መሠውያውን አድርግ" (ዘፍ 35:1) በዚህ ስፍራ ላይ እግዚአብሔር አምላክ ለያዕቆብ ተነሥቶ ወደ ቤቴል እንዲወጣ፥ በዚያም እንዲኖር፥ ከወንድሙም ከዔሳው ፊት በሸሸ ጊዜ ለተገለጠለት ለእግዚአብሔር መሠዊያ እንዲያደርግ ሲነግረው እናነባለን። ይህ ቃል የእግዚአብሔር መልአክ መሠዊያ ተሰርቶለት መሥዋዕት የሚቀበለው እግዚአብሔር መሆኑን ያረጋግጣል። ክፍሉ ብዙ ሀሳቦችን የያዘ ክፍል በመሆኑ እያስተላለፈ ያለውን ሀሳብ ለመረዳት ከዚህ ምዕራፍ በፊት ያሉትን ምዕራፎች መረዳት ያስፈልጋል። ያዕቆብ ከወንድሙ ከዔሳው ሸሽቶ ወደ ቤቴል እንደሄደ በዘፍ 35:1 ላይ ተገልጿል። ያዕቆብ ከወንድሙ ከዔሳው የሸሸበትን ታሪክ የምናገኘው በዘፍጥረት ምዕራፍ 27 ሲሆን ወደ ቤቴል የሄደበትን ታሪክ ደግሞ በዘፍጥረት ምዕራፍ 28 ላይ እናገኘዋለን። በዘፍ 27:1-41 ያዕቆብ ወንድሙን ዔሳውን አታልሎ በረከቱን የወሰደበትን ታሪክ እንመለከታለን። ከዚያም በኋላ ዔሳው እርሱን ሊገድለው በልቡ አሰበ (ዘፍ 27:41) እናታቸው ርብቃም ይህ የታላቁ ልጇ የዔሳው ቃል በደረሰላት ጊዜ ታናሹ ልጇን ያዕቆብን አስጠርታ አስመጥታው ወንድሙ ዔሳው ሊገድለው እንደሚፈቅድ ነገረችው (ዘፍ 27:42) ከዚያም ቃሏን ሰምቶ በመነሳት ወደ ካራን ምድር ወደ ወንድሟ ወደ ላባ ሄዶ የወንድሙ ቁጣ እስኪበርድ፥ ቁጣውም ከእርሱ እስኪመለስና ያደረገበትንም እስኪረሳው ድረስ በዚያ ጥቂት ቀን እንዲቀመጥና ከዚያም ልካ እንደምታስመጣው ነገረችው (ዘፍ 27:43-45) ከዚያም ይስሐቅ ያዕቆብን ጠራው ባረከውም ከከነዓናውያን ሴቶችም እንዳያገባ አዘዘው (ዘፍ 28:1) ይልቁንም ተነስቶ ወደ እናቱ አባት ወደ ባቱኤል ቤት ወደ ሁለቱ ወንዞች መካከል ሄዶ ከእናቱ ወንድም ከላባ ሴቶች ልጆች ሚስትን እንዲያገባ ነግሮት ሁሉንም የሚችል አምላክ ለብዙ ሕዝብ ጉባኤ እንድትሆን ይባርክህ ያፍራህ ያብዛህ በማለት ባረከው (ዘፍ 28:2-3) እንዲሁም ስደተኛ ሆነህ የተቀመጥህባትን እግዚአብሔርም ለአብርሃም የሰጣትን ምድር ትወርስ ዘንድ የአብርሃምን በረከት ለአንተ ይስጥ ለዘርህም እንዲሁ እንደ አንተ በማለት ይባርከዋል (ዘፍ 28:4) ከዚያም ይስሐቅ ያዕቆብን ሰደደው ያዕቆብም የያዕቆብና የዔሳው እናት የርብቃ ወንድም የሆነው የሶርያዊ ባቱኤል ልጅ ላባ ወዳለበት ወደ ሁለቱ ወንዞች መካከል ሄደ (ዘፍ 28:5) ከቤርሳቤህም ወጥቶ ወደ ካራን ሄደ (ዘፍ 28:10) ይህ የእግዚአብሔር መልአክ መሥዋዕት የሚቀበለው አምላክ መሆኑን እንዴት ያሳያል? ▶️ ይቀጥላል

Открыть в Telegram
Просмотры6 270+43%к среднему
Пересылки—
Реакции13
Комментарии—
#1583Текст

🚩 የእግዚአብሔር መልአክና ጌዴዎን (ክፍል 7) ባለፈው ክፍል ላይ መለኮት የሆነው የእግዚአብሔር ልጅ በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር መልአክ በመባል ይገለጥ እንደነበር እና በዚህ መንገድ ከተገለጠባቸው አጋጣሚዎች አንዱ የሆነውን የጌዴዎንን ታሪክ ማየት ጀምረን ነበር። ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ለመግለጽ እንደሞከርነው መልአክ የሚለው ቃል በዕብራይስጥ "ማልአኽ/מַלְאַ֥ךְ" በግሪክ ደግሞ "አንጌሎስ/ἄγγελος" ሲሆን ትርጉሙ መልእክተኛ ማለት ነው። የመልእክተኝነት ግብር ያለው የትኛውም አካል መልአክ/መልእክተኛ ተብሎ ይጠራል። የመልእክተኛው ባህርይ ሰዋዊ ይሁን፥ የፍጡራን መናፍስት ይሁን መለኮታዊ ይሁን የሚታወቀው በአውዱ ነው። እንጂ አንድ አካል መልአክ ስለተባለ ብቻ ከፍጡራን መናፍስት አንዱ ነው ማለት አይደለም። የእግዚአብሔር ልጅም መልአክ የተባለው የአባቱ መልእክተኛ ስለነበር እንጂ ፍጡር ስለሆነ አይደለም። እግዚአብሔር ቢፈቅድ ከባለፈው ክፍል በመቀጠል የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ የእግዚአብሔር መልአክ በመባል ለጌዴዎን የተገለጠበትን ክስተት ማየት እንቀጥላለን፦ "ጌዴዎንም የእግዚአብሔር መልአክ እንደ ሆነ አየ፤ #ጌዴዎንም። አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ #ወዮልኝ፤ #የእግዚአብሔርን_መልአክ ፊት ለፊት #አይቻለሁና አለ" (መሳ 6:22) የእግዚአብሔር መልአክ ጌዴዎን ያቀረበለትን መሥዋዕት ተቀብሎ ከተሰወረ በኋላ ጌዴዎን ለእርሱ የተገለጠው የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን አውቆ አቤቱ አምላኬ ሆይ ወዮልኝ የእግዚአብሔርን መልአክ ፊት ለፊት አይቻለሁና ብሏል። ጌዴዎን የተገለጠለት የእግዚአብሔር መልአክ "እኔ የእግዚአብሔር መልአክ ነኝ" ሳይለው እንኳ የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን አውቋል። ይህ ሊሆን የቻለው የእግዚአብሔር መልአክ በተገለጠለት ጊዜ ከሆነው ነገርና ከእርሱ በፊት ስለተጻፉት ቅዱሳት መጻሕፍት ከነበረው እውቀት የተነሳ ነው (መሳ 6:13) የእግዚአብሔር መልአክ ለጌዴዎን ሲገለጥለት የተገለጠለት በትር በያዘ የሰው አምሳል ሲሆን (መሳ 6:21) ሲያነጋግረው የነበረውም እንደ አምላክ ነው (መሳ 6:14 መሳ 6:16) በአምስቱ የኦሪት መጻሕፍትና በመጽሐፈ ኢያሱ ውስጥ ደግሞ በሰው አምሳል ተገልጦ እንደ አምላክ የሚናገረው የእግዚአብሔር መልአክ ነው። ስለዚህ በዚህ መልኩ የተገለጠለት ይህ አካል መሥዋዕቱን ተቀበሎ ሲሰወር የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን አወቀ። ከዚህ ባሻገር ግን ጌዴዎን ለእርሱ የተገለጠው አካል የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን ያወቀበት ሌላ መንገድ አለ፦ " #የእግዚአብሔርም_መልአክ ለእርሱ ተገልጦ። አንተ ጽኑዕ ኃያል ሰው፥ #እግዚአብሔር_ከአንተ_ጋር_ነው አለው" (መሳ 6:12) በዚህ ቦታ ላይ የእግዚአብሔር መልአክ ለጌዴዎን ሲገለጥለት "አንተ ጽኑዕ ኃያል ሰው እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው" እንዳለው እናነባለን። በዚህ ቦታ ላይ ለጌዴዎን የተገለጠለት አካል "እኔ ከአንተ ጋር ነኝ" ሳይሆን ያለው በሶስተኛ መደብ "እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው" ነበር ያለው። ስለዚህ ተናጋሪው ራሱን በማንነት ደረጃ ከእግዚአብሔር ለይቷል ማለት ነው። በሶስተኛ መደብ እግዚአብሔር ብሎ የሚጠቅሰው ሌላ አካል/ማንነት አለ ማለት ነው። ንግግሩ ሲቀጥል እርሱ ራሱ እንደ አምላክ ቢናገርም (መሳ 6:14 መሳ 6:16) እዚህ ቁ.12 ላይ ግን ራሱን በአካል ከእግዚአብሔር በመለየት ስለ እግዚአብሔር በሶስተኛ መደብ ተናግሯል። ይህ ለጌዴዎን ተገልጦ ሲያነጋግረው የነበረው አካል የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን ያረጋግጣል። ምክንያቱም በአምስቱ የኦሪት መጻሕፍት እና በመጽሐፈ ኢያሱ ውስጥ እርሱ ራሱ እንደ አምላክ እየተናገረ ደግሞም እግዚአብሔርን በሶስተኛ መደብ በመጥቀስ በማንነት ደረጃ ራሱን ከእግዚአብሔር የሚለየው የእግዚአብሔር መልአክ ነው። ለምሳሌ፦ 1) የእግዚአብሔር መልአክ ለአጋር ተገልጦ "ዘርሽን አበዛለሁ" በማለት እንደ አምላክ አነጋግሯታል (ዘፍ 16:10/ዘፍ 13:16) ደግሞም በዚያው አውድ ላይ በሶስተኛ መደብ "እግዚአብሔር መቸገርሽን ሰምቷል" (ዘፍ 16:11) በማለት እግዚአብሔርን በሶስተኛ መደብ በመጥቀስ በማንነት ደረጃ ራሱን ከእግዚአብሔር ለይቷል 2) የእግዚአብሔር መልአክ ለአጋር ልጇን እስማኤልን "ታላቅ ሕዝብ አደርገዋለሁ" በማለት እንደ አምላክ አነጋግሯታል (ዘፍ 21:18/ዘፍ 46:3) ደግሞም በዚያው አውድ ላይ በሶስተኛ መደብ "እግዚአብሔር የብላቴናውን ድምጽ ባለበት ሰምቷል" (ዘፍ 21:17) በማለት እግዚአብሔርን በሶስተኛ መደብ በመጥቀስ በአካል ራሱን ከእግዚአብሔር ለይቷል 3) የእግዚአብሔር መልአክ ለአብርሃም "አንድ ልጅህን ለእኔ አልከለከልህምና" በማለት እንደ አምላክ አነጋግሮታል (ዘፍ 22:12/ዘፍ 22:1-2) ደግሞም በዚያ አውድ ላይ በሶስተኛ መደብ "እግዚአብሔር በራሴ ማልሁ ይላል" (ዘፍ 22:16) በማለት እግዚአብሔርን በሶስተኛ መደብ በመጥቀስ በማንነት ራሱን ከእግዚአብሔር ለይቷል 4) የእግዚአብሔር መልአክ ለኢያሱ ተገልጦ "የቆምህበት ስፍራ ቅዱስ ነውና ጫማህን አውልቅ" በማለት እንደ አምላክ አነጋግሮታል (ኢያ 5:15/ዘጽ 3:5-6) ደግሞም በዚያው አውድ ላይ በሶስተኛ መደብ "እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ መጥቻለሁ" (ኢያ 5:14) በማለት እግዚአብሔርን በሶስተኛ መደብ በመጥቀስ በአካል ደረጃ ራሱን ከእግዚአብሔር ለይቷል ይህን ሁሉ የሚያውቀው ጌዴዎን ለእርሱ የተገለጠው አካል ራሱን በማንነት ከእግዚአብሔር ለይቶ በሶስተኛ መደብ "እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው" (መሳ 6:12) ካለው በኋላ እርሱ ራሱ "ልኬሃለሁ" (መሳ 6:14) ደግሞም "እኔ ከአንተ ጋር ነኝ" (መሳ 6:16) በማለት ራሱ እንደ አምላክ ሲያነጋግረው በዚህ መልኩ ከጥንት ጀምሮ ለአባቶቻቸው ሲገለጥና እነርሱን ሲያነጋግር የነበረው የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን አወቀ። ስለዚህ በጠየቀው ምልክት መሰረት በእርግጥም እርሱ መሆኑን ሲያረጋግጥ ወዮልኝ የእግዚአብሔርን መልአክ አይቻለሁና አለ። ይህ የእግዚአብሔር መልአክ በባህርይው መለኮት መሆኑን ከማረጋገጥ ባሻገር ያለ ምንም መቋረጥ ከጥንት ጀምሮ ለነበሩት የብሉይ ኪዳን አባቶች ሲገለጥ የነበረው የብሉይ ኪዳኑ አምላክ መሆኑን በማያሻማ አኳሃን ያረጋግጣል። ✍️ የእግዚአብሔር መልአክ ለምንድነው እርሱ ራሱ እንደ መለኮት እየተናገረ ደግሞም ራሱን በማንነት ለይቶ በሶስተኛ መደብ ስለ እግዚአብሔር የሚናገረው? እርሱ ራሱ እንደ አምላክ የሚናገረው በባህርይው መለኮት በመሆኑ ነው። በባህርይው አምላክ በመሆኑ በመጀመሪያው መደብ በቀጥታ እንደ መለኮት መናገር ይችላል። ራሱን በአካል ለይቶ በሶስተኛ መደብ ስለ እግዚአብሔር የሚናገረው ደግሞ አባቱ እግዚአብሔር አብን ለማመልከት ነው። የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ "የእግዚአብሔር መልአክ" ይባል የነበረው የአባቱ የእግዚአብሔር አብ መልእክተኛ ስለነበር ነው። ስለዚህ ስለ አባቱ ስለ እግዚአብሔር አብ ሲናገር በሶስተኛ መደብ "እግዚአብሔር" በማለት ይናገራል። ይህ የእግዚአብሔር መልአክ በባህርይው አምላክ መሆኑን ከማሳየት ባሻገር አንዱ መለኮት ከአንድ በላይ አካል ወይም ማንነት (Person) መሆኑን ያሳያል። ▶️ ይቀጥላል

Открыть в Telegram
Просмотры6 720+54%к среднему
Пересылки—
Реакции14
Комментарии—
#1582Текст

🚩 የእግዚአብሔር መልአክና ጌዴዎን (ክፍል 6) ባለፈው ክፍል ላይ መለኮት የሆነው የእግዚአብሔር ልጅ በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር መልአክ በመባል ይገለጥ እንደነበር እና በዚህ መንገድ ከተገለጠባቸው አጋጣሚዎች አንዱ የሆነውን የጌዴዎንን ታሪክ ማየት ጀምረን ነበር። ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ለመግለጽ እንደሞከርነው መልአክ የሚለው ቃል በዕብራይስጥ "ማልአኽ/מַלְאַ֥ךְ" በግሪክ ደግሞ "አንጌሎስ/ἄγγελος" ሲሆን ትርጉሙ መልእክተኛ ማለት ነው። የመልእክተኝነት ግብር ያለው የትኛውም አካል መልአክ/መልእክተኛ ተብሎ ይጠራል። የመልእክተኛው ባህርይ ሰዋዊ ይሁን፥ የፍጡራን መናፍስት ይሁን መለኮታዊ ይሁን የሚታወቀው በአውዱ ነው። እንጂ አንድ አካል መልአክ ስለተባለ ብቻ ከፍጡራን መናፍስት አንዱ ነው ማለት አይደለም። የእግዚአብሔር ልጅም መልአክ የተባለው የአባቱ መልእክተኛ ስለነበር እንጂ ፍጡር ስለሆነ አይደለም። እግዚአብሔር ቢፈቅድ ከባለፈው ክፍል በመቀጠል የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ የእግዚአብሔር መልአክ በመባል ለጌዴዎን የተገለጠበትን ክስተት ማየት እንቀጥላለን፦ "ጌዴዎንም የእግዚአብሔር መልአክ እንደ ሆነ አየ፤ #ጌዴዎንም። አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ #ወዮልኝ፤ #የእግዚአብሔርን_መልአክ ፊት ለፊት #አይቻለሁና አለ" (መሳ 6:22) የእግዚአብሔር መልአክ የቀረበለትን መሥዋዕት በእሳት ተቀበሎ ከተሰወረ በኋላ ጌዴዎን ተገልጦለት የነበረው የእግዚአብሔር መልአክ እንደነበር አይቶ አቤቱ አምላኬ ሆይ ወዮልኝ የእግዚአብሔርን መልአክ ፊት ለፊት አይቻለሁና ማለቱን በዚህ ቦታ ላይ እናነባለን። ጌዴዎን ምልክት ጠይቆ የነበረ ሲሆን (መሳ 6:17-18) ያ የጠየቀው ምልክት ሲሰጠው ተገልጦለት የነበረው አካል የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን ተረዳና ወዮልኝ አለ። ነገር ግን ጌዴዎን የተገለጠለት የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን በምን አወቀ? በመሳ 6:11-21 ላይ የእግዚአብሔርን መልአክ "የእግዚአብሔር መልአክ" ብሎ ሲጠራው የነበረው የመሳፍንት መጽሐፍ ጸሐፊ እንጂ ራሱ የእግዚአብሔር መልአክ አይደለም። የእግዚአብሔር መልአክ ጌዴዎንን ሲያነጋግረው "እኔ የእግዚአብሔር መልአክ ነኝ" አላለውም። ታዲያ እንዴት መሥዋዕቱን በእሳት ተቀብሎ ከተሰወረ በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን አወቀ? ጌዴዎን ተገልጦለት የነበረው አካል "እኔ የእግዚአብሔር መልአክ ነኝ" ሳይለው እንኳ የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን ያወቀው ተገልጦለት በነበረበት ሰዓት ከሆነውና ከተከሰተው ነገር የተነሳ ነው። ይህንን እንዴት ማወቅ እንችላለን? ነጥብ በነጥብ እንመልከተው፦ ጌዴዎን ከእርሱ በፊት እግዚአብሔር ለእስራኤል ሕዝብ ያደረገውን ነገር እና ከእርሱ ዘመን በፊት ተጽፎ የነበረውን የእግዚአብሔርን ቃል ያውቅ የነበረ ሰው ነው። ይህንንም ራሱ ከተናገረው ቃል መረዳት እንችላለን፦ "ጌዴዎንም። ጌታዬ ሆይ፥ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ይህ ነገር ሁሉ ለምን ደረሰብን? #አባቶቻችንስ። #እግዚአብሔር ከግብፅ #አውጥቶናል ብለው #ይነግሩን የነበረ ተአምራቱ ወዴት አለ? ወዴት አለ? አሁን ግን እግዚአብሔር ትቶናል፥ በምድያማውያንም እጅ አሳልፎ ሰጥቶናል አለው" (መሳ 6:13) በዚህ ቦታ ላይ ጌዴዎን አባቶቻችን እግዚአብሔር ከግብፅ አውጥቶናል ብለው ይነግሩን የነበረ ተአምራቱ ወዴት አለ ማለቱን እናነባለን። ስለዚህ ከዚህ ንግግሩ አባቶቻቸው በዮሴፍ ዘመን ወደ ግብፅ እንደወረዱ፥ በግብፅም ለረዥም ዘመን እንደኖሩ፥ ከዚያም ዮሴፍን የማያውቅ ንጉሥ በግብፅ ላይ በነገሠ ጊዜ ወደ ባርነት እንደገቡ፥ በባርነትም ለረዥም ዘመን እንደኖሩ፥ በኋላም እግዚአብሔር አምላክ ሙሴን እንደላከውና በተአምራት ከግብፅ እንዳወጣቸው፥ ከሙሴ ሞት በኋላም በምድረበዳ ኢያሱን ልኮ እንዲመራቸው ማድረጉን፥ በኢያሱ መሪነትም ወደ ቃል ኪዳኗ ምድር መግባታቸውን እንደሚያውቅ እንረዳለን። ስለዚህ አምስቱን የኦሪት መጻሕፍትን እና የኢያሱን መጽሐፍ ያውቃል ማለት ነው። እነዚህ ነገሮች በሙሉ የተዘገቡት በእነዚህ መጻሕፍት ነውና። ከዚህ በተጨማሪም እነዚህ መጻሕፍት የተጻፉት ከጌዴዎን ዘመን በፊት ስለሆነ ከተጻፉ በኋላ የመጣው ጌዴዎን ስለ እነርሱ እንደሚያውቅ ጥርጥር የለውም። ይህ ጌዴዎን ተገልጦለት የነበረው የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን እንዲረዳ አስችሎታል። ምክንያቱም የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጦለት በነበረ ሰዓት የተገለጠለት በትር በያዘ ሰው አምሳል ነው (መሳ 6:21) ሲያነጋግረው የነበረው ግን እንደ አምላክ ነው (መሳ 6:14 መሳ 6:16) በአምስቱ የኦሪት መጻሕፍት እና በመጽሐፈ ኢያሱ ላይ በሰው አምሳል ተገልጦ እንደ አምላክ የሚናገረው የእግዚአብሔር መልአክ ነው። ለምሳሌ:- 1) የእግዚአብሔር መልአክ ለአጋር ተገልጦላት ነበር (ዘፍ 16:13) ዘርሽን አበዛለሁ ብሎ እንደ አምላክ ተናግሯታል (ዘፍ 16:10/ዘፍ 13:16) 2) የእግዚአብሔር መልአክ በሰው አምሳል ተገልጦ ያዕቆብን ታግሎታል (ዘፍ 32:24) እግዚአብሔር ተብሎም ተጠርቷል (ዘፍ 32:30) 3) የእግዚአብሔር መልአክ ለበልዓም ሰይፍ በያዘ ሰው አምሳል ተገልጦለት ነበር (ዘኁ 22:23) መንገድህ በፊቴ ጠማማ ነው ብሎ እንደ አምላክ አነጋግሮት ነበር (ዘኁ 22:32/ምሳ 15:9) 4) የእግዚአብሔር መልአክ ለኢያሱ በሰው አምሳል ተገልጦ ነበር (ኢያ 5:13) የቆምህበት መሬት ቅዱስ ነውና ጫማህን አውልቅ ብሎ እንደ አምላክ ተናግሮት ነበር (ኢያ 5:15/ዘጽ 3:5-6) ✍️ ይህን ሁሉ የሚያውቀው ጌዴዎን ይህ በትር በያዘ ሰው አምሳል ተገልጦለት የነበረውና (መሳ 6:21) ልኬሃለሁ (መሳ 6:14/መሳ 2:16) እኔ ከአንተ ጋር ነኝ (መሳ 6:16/ኢያ 1:5) በማለት እንደ አምላክ ሲያነጋግረው የነበረው አካል መሥዋዕቱን ተቀብሎ ሲሰወር ያ ከጥንት ጀምሮ ለአባቶቻቸው በሰው አምሳል ተገልጦ እንደ አምላክ ሲናገር የነበረው የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን አወቀ። ጌዴዎን ለእርሱ ተገልጦ የነበረው የእግዚአብሔር መልአክ "እኔ የእግዚአብሔር መልአክ ነኝ" ሳይለው እንኳን የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን ያወቀው ለዚህ ነው። ይህ የእግዚአብሔር መልአክ በባህርይው መለኮት መሆኑን ከማሳየት ባሻገር ከጥንት ጀምሮ ያለ ምንም መቋረጥ የብሉይ ኪዳን አባቶችን ሲናገርና ለእነርሱም ሲገለጥ የነበረው የብሉይ ኪዳኑ አምላክ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው። ከዚህም ባሻገር ግን ጌዴዎን የተገለጠለት አካል የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን ያወቀበት ተጨማሪ መንገድ አለ። ▶️ ይቀጥላል

Открыть в Telegram
Просмотры5 840+33%к среднему
Пересылки—
Реакции15
Комментарии—
#1579Текст

🚩 የእግዚአብሔር መልአክና ጌዴዎን (ክፍል 5) ባለፈው ክፍል ላይ መለኮት የሆነው የእግዚአብሔር ልጅ በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር መልአክ በመባል ይገለጥ እንደነበር እና በዚህ መንገድ ከተገለጠባቸው አጋጣሚዎች አንዱ የሆነውን የጌዴዎንን ታሪክ ማየት ጀምረን ነበር። ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ለመግለጽ እንደሞከርነው መልአክ የሚለው ቃል በዕብራይስጥ "ማልአኽ/מַלְאַ֥ךְ" በግሪክ ደግሞ "አንጌሎስ/ἄγγελος" ሲሆን ትርጉሙ መልእክተኛ ማለት ነው። የመልእክተኝነት ግብር ያለው የትኛውም አካል መልአክ/መልእክተኛ ተብሎ ይጠራል። የመልእክተኛው ባህርይ ሰዋዊ ይሁን፥ የፍጡራን መናፍስት ይሁን መለኮታዊ ይሁን የሚታወቀው በአውዱ ነው። እንጂ አንድ አካል መልአክ ስለተባለ ብቻ ከፍጡራን መናፍስት አንዱ ነው ማለት አይደለም። የእግዚአብሔር ልጅም መልአክ የተባለው የአባቱ መልእክተኛ ስለነበር እንጂ ፍጡር ስለሆነ አይደለም። እግዚአብሔር ቢፈቅድ ከባለፈው ክፍል በመቀጠል የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ የእግዚአብሔር መልአክ በመባል ለጌዴዎን የተገለጠበትን ክስተት ማየት እንቀጥላለን፦ " #የእግዚአብሔርም_መልአክ። ሥጋውንና የቂጣውን እንጎቻ ወስደህ በዚህ ድንጋይ ላይ አኑር፥ መረቁንም አፍስስ አለው። እንዲሁም አደረገ" (መሳ 6:20) ጌዴዎን ይዞት የመጣው መሥዋዕት ከአድባሩ ዛፍ በታች ለእግዚአብሔር መልአክ ካቀረበ በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ ሥጋውንና የቂጣውን እንጎቻ ወስደህ በዚህ ድንጋይ ላይ አኑር መረቁንም አፍስስ እንዳለውና ጌዴዎንም እንደዚያ እንዳደረገ በቁ.19 ላይ እናነባለን። ባለፉት ክፍሎች ላይ ለማየት እንደሞከርነው በቁ.17-18 ጌዴዎን በአንተ ዘንድ ሞገስ ካገኘሁ የምትናገረኝም አንተ እንደሆንህ ምልክት አሳየኝ ወደ አንተም እስክመለስ ድረስ ቁርባኔንም እስካቀርብልህ ድረስ እባክህ ከዚህ አትላወስ ብሏል። ይህንን ያለው በቁ.16 ላይ በእርግጥ ከአንተ ጋር እሆናለሁ ምድያምንም እንደ አንድ ሰው ትመታለህ ላለው እግዚአብሔር ነው። ይህን ከአቅራቢያው ጠቋሚ (nearest antecedent) እንረዳለን። ስለዚህ በቁ.17-18 ላይ ጌዴዎን ለተናገረው ለዚህ ንግግር እስክትመለስ ድረስ እቆያለሁ በማለት የመለሰለት ይህ በቁ.16 ላይ የተናገረው እግዚአብሔር ነው ማለት ነው። ነገር ግን ማን ነበር ጌዴዎን መሥዋዕቱን ይዞ እስኪመለስ በዚያ ስፍራ የቆየው ወይም የጠበቀው? ጌዴዎን መሥዋዕቱን ይዞ እስኪመለስ ድረስ በዚያ ስፍራ የጠበቀው የእግዚአብሔር መልአክ ነው። በቁ.20 ላይ እንደተገለፀው ጌዴዎን መሥዋዕቱን ይዞ ከተመሰለ በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ ሥጋውንና የቂጣውን እንጎቻ ወስዶ በደንጋዩ ላይ እንዲያኖር፥ መረቁንም እንዲያፈስስ ለጌዴዎን እንደነገረው እናነባለን። ስለዚህ በቁ.18 ላይ እስክትመለስ ድረስ እቆያለሁ ያለው ያ በቁ.16 ላይ የተናገረው እግዚአብሔር በቁ.20 ላይ ጌዴዎን መስዋዕቱን ይዞ እስኪመለስ ድረስ ጠብቆት የነበረው የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን ከዚህ እንረዳለን። የእግዚአብሔር መልአክ በዚህ መልኩ እግዚአብሔር ተብሎ መጠራቱ በባህርይው አምላክ መሆኑን የሚያረጋግጥ ተጨማሪ ማስረጃ ነው። ከዚያም ጌዴዎን የእግዚአብሔር መልአክ እንዳለው መሥዋዕቱን በድንጋዩ ላይ ካኖረ በኋላ እንዲህ ሆነ፦ " #የእግዚአብሔርም_መልአክ በእጁ ያለውን የበትሩን ጫፍ ዘርግቶ ሥጋውንና የቂጣውን እንጎቻ አስነካ፤ #እሳትም ከድንጋዩ ውስጥ ወጥቶ ሥጋውንና የቂጣውን እንጎቻ #በላ። የእግዚአብሔርም መልአክ ከዓይኑ ተሰወረ" (መሳ 6:21) ጌዴዎን የእግዚአብሔር መልአክ እንዳለው ሥጋውን እና የቂጣውን እንጎቻ በድንጋዩ ላይ ካኖረ በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ በእጁ ያለውን የበትሩን ጫፍ ዘርግቶ መሥዋቱን እንዳስነካና እሳትም ከድንጋዩ ወጥቶ ሥጋውንና የቂጣውን እንጎቻ እንደበላ ከቁ.21 እናነባለን። ይህ ብዙ ነጥቦችን የያዘ ክፍል ነው። አንደኛ ከዚህ ቦታ የእግዚአብሔር መልአክ በሰው አምሳል እንደተገለጠ እንረዳለን። ለጌዴዎን ሲገለጥለት በእጁ በትር የያዘ ሰው መስሎ እንደተገለጠለት እንረዳለን። በቁ.12 ላይ "ለእርሱ ተገልጦ" የሚለው ለዚያ ነው። በሰው አምሳል ተገልጦለት ነበርና። ሲቀጥል በቁ.18-19 ላይ እስካቀርብልህ ብሎት ያቀረበለትን መሥዋዕት የእግዚአብሔር መልአክ የተቀበለው በእሳት ነበር። የእግዚአብሔር መልአክ የቀረበለትን መሥዋዕት በእሳት መቀበሉ በባህርይው መለኮት መሆኑን የሚያረጋግጥ እውነታ ነው። ምክንያቱም መሥዋዕትን በእሳት የሚቀበለው እግዚአብሔር ብቻ ነው፦ " #እሳትም ከእግዚአብሔር ዘንድ #ወጣ፥ በመሠዊያውም ላይ የሚቃጠለውን #መሥዋዕት ስቡንም #በላ፤ ሕዝቡም ሁሉ አይተው እልል አሉ፥ በግምባራቸውም ወደቁ" (ዘሌ 9:24) "ዳዊትም በዚያ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ፥ የሚቃጠለውን #መሥዋዕትና የደኅንነቱን #መሥዋዕት_አቀረበ፥ እግዚአብሔርንም ጠራ፤ ከሰማይም ለሚቃጠለው መሥዋዕት በሚሆነው መሠዊያ ላይ #በእሳት መለሰለት" (1ዜና 21:26) "ሰሎሞንም ጸሎቱን በፈጸመ ጊዜ #እሳት ከሰማይ ወርዶ የሚቃጠለውን #መሥዋዕትና ሌላ መሥዋዕቱን #በላ፤ የእግዚአብሔርም ክብር ቤቱን ሞላ" (2ዜና 7:1) "የእግዚአብሔርም #እሳት ወደቀች፥ የሚቃጠለውን #መሥዋዕቱንም እንጨቱንም ድንጋዮቹንም አፈሩንም #በላች፥ በጕድጓዱም ውስጥ ያለውን ውኃ ላሰች" (1ነገ 18:38) "ፀሐይም በገባች ጊዜ ታላቅ ጨለማ ሆነ፤ የምድጃ ጢስና #የእሳት_ነበልባል በዚያ #በተከፈለው መካከል #አለፈ" (ዘፍ 15:17) - በዘፍ 15:17 ላይ ተከፍሎ የነበረውና እሳት ያለፈበት በዘፍ 15:9-10 ላይ አብርሃም በየወገኑ ከፍሎ ያቀረበው መሥዋዕት ነው በቁ.14 እና በቁ.16 ላይ እግዚአብሔር የተባለው የእግዚአብሔር መልአክ በብሉይ ኪዳን ውስጥ እግዚአብሔር መሥዋዕት በሚቀበልበት መንገድ ለእርሱ የቀረበውን መሥዋዕት ተቀብሏል። ባለፉት ክፍሎች ላይ ለመግለጽ እንደሞከርነው ከእግዚአብሔር በቀር ለማንም መሥዋዕት መሠዋት ክልክል ነው (ዘጽ 22:20) የእግዚአብሔር መልአክ ግን መሥዋዕት ተሠውቶለታል (መሳ 6:18-19) መሥዋዕት ተቀባይ ከመሆኑም ባሻገር ከላይ ለመመልከት እንደሞከርነው መሥዋዕቱን የተቀበለው እግዚአብሔር ብቻ በሚቀበልበት መንገድ ነው። ይህ የእግዚአብሔር መልአክ ለእርሱ የቀረበውን መሥዋዕት በእሳት የሚቀበለው እግዚአብሔር መሆኑን በማያሻማ አኳሃን ያረጋግጣል። ጌዴዎንም በቁ.17 ላይ የጠየቀው ምልክት ይህ ነበር። በቁ.14 እና በቁ.16 ላይ ያለው ንግግር አምላክ እንጂ ፍጡር ሊናገረው የሚችለው ንግግር አይደለም። ስለዚህ ለእርሱ የተገለጠው አካል ልክ እንደ ንግግሩ በእርግጥም መለኮት መሆኑን ለማረጋገጥ ምልክትን ጠየቀው። ምልክቱ ደግሞ ያቀረበለትን መሥዋዕት እግዚአብሔር ብቻ በሚቀበለው ልዕለ-ተፈጥሯዊ (supernatural) መንገድ ወይም በእሳት መቀበል ነበር። ይህ ለእርሱ የተገለጠው አካል የቀረበለትን መሥዋዕት አምላክ ብቻ በሚቀበለው መልኩ ከተቀበለው በእርግጥም ልክ እንደ ንግግሩ መለኮት መሆኑ ይረጋገጣል ማለት ነው። ለጌዴዎን የተገለጠው የእግዚአብሔር መልአክም በባህርይው መለኮት በመሆኑ ጌዴዎን ያቀረበለትን መሥዋዕት በእሳት በመቀበል በተጠየቀው ምልክት መሰረት አምላክነቱን አረጋግጧል። ▶️ ይቀጥላል

Открыть в Telegram
Просмотры5 750+31%к среднему
Пересылки—
Реакции15
Комментарии—
#1573Текст

🚩 የእግዚአብሔር መልአክና ጌዴዎን (ክፍል 4) ባለፈው ክፍል ላይ መለኮት የሆነው የእግዚአብሔር ልጅ በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር መልአክ በመባል ይገለጥ እንደነበር እና በዚህ መንገድ ከተገለጠባቸው አጋጣሚዎች አንዱ የሆነውን የጌዴዎንን ታሪክ ማየት ጀምረን ነበር። ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ለመግለጽ እንደሞከርነው መልአክ የሚለው ቃል በዕብራይስጥ "ማልአኽ/מַלְאַ֥ךְ" በግሪክ ደግሞ "አንጌሎስ/ἄγγελος" ሲሆን ትርጉሙ መልእክተኛ ማለት ነው። የመልእክተኝነት ግብር ያለው የትኛውም አካል መልአክ/መልእክተኛ ተብሎ ይጠራል። የመልእክተኛው ባህርይ ሰዋዊ ይሁን፥ የፍጡራን መናፍስት ይሁን መለኮታዊ ይሁን የሚታወቀው በአውዱ ነው። እንጂ አንድ አካል መልአክ ስለተባለ ብቻ ከፍጡራን መናፍስት አንዱ ነው ማለት አይደለም። የእግዚአብሔር ልጅም መልአክ የተባለው የአባቱ መልእክተኛ ስለነበር እንጂ ፍጡር ስለሆነ አይደለም። እግዚአብሔር ቢፈቅድ ከባለፈው ክፍል በመቀጠል የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ የእግዚአብሔር መልአክ በመባል ለጌዴዎን የተገለጠበትን ክስተት ማየት እንቀጥላለን፦ " #ጌዴዎን_ገባ የፍየሉንም ጠቦት የኢፍ መስፈሪያም ዱቄት የቂጣ እንጎቻ #አዘጋጀ፤ ሥጋውን በሌማት አኖረ፥ መረቁንም በምንቸት ውስጥ አደረገ፥ ሁሉንም ይዞ #በአድባሩ_ዛፍ_በታች #አቀረበለት" (መሳ 6:19) በቁ.18 ላይ ጌዴዎን ወደ አንተም እስክመለስ ቁርባኔንም እስካቀርብልህ ድረስ ከዚህ አትላወስ ካለው በኋላ ገብቶ ለመስዋዕት የሚቀርቡትን የፍየል ጠቦት ስጋ፥ የኢፍ መስፈሪያ ዱቄት፥ የቂጣ እንጎቻ አዘጋጅቶ፥ ስጋውን በሌማት አኑሮ፥ መረቁን በምንቸት ውስጥ አድርጎ ከአድባሩ ዛፍ በታች እንዳቀረበለት በዚህ ስፍራ እናነባለን። ጌዴዎን ለመስዋዕት ያዘጋጃቸው ነገሮች በሙሉ ለእግዚአብሔር በመስዋዕትነት የሚቀርቡ ነገሮች ናቸው። የፍየል ስጋ (ዘሌ 4:23) የኢፍ መስፈሪያ ዱቄት (ዘኁ 5:15) የቂጣ እንጎቻ (ዘጽ 29:23-25) በሙሉ በቤተ-መቅደስ ውስጥ ለእግዚአብሔር የሚቀርቡ መስዋዕት ናቸው። ይህ ጌዴዎን ያቀረበው ቁርባን ለመለኮት ብቻ የሚቀርብ የአምልኮ መስዋዕት መሆኑን ያረጋግጣል። ባለፈው ክፍል ላይ ለማየት እንደሞከርነው ጌዴዎን በቁ.18 ላይ እስካቀርብልህ ያለው በቁ.16 ላይ ለተናገረው እግዚአብሔር ነው። ያም እግዚአብሔር ደግሞ በቁ.11-12 ላይ ተገልጦለት እርሱን ማነጋገር የጀመረው የእግዚአብሔር መልአክ ነው። ስለዚህ በቁ.19 ላይ አቀረበለት ሲል ለዚያ በቁ.18 ላይ እስካቀርብልህ ድረስ አትላወስ ላለው የእግዚአብሔር መልአክ ነው። ያም የእግዚአብሔር መልአክ በቁ.16 ላይ እግዚአብሔር ተብሎ ተጠርቷል። የጽሑፉ ተፈጥሯዊ ፍሰት የሚያሳየው ይህንን ነውና። በቁ.19 ላይ "አቀረበለት" ተብሎ የተተረጎመው ቃል ከሁለት የዕብራይስጥ ቃላት የተዋቀረ ነው። የመጀመሪያው ቃል "יָצָא/ያጻ" የሚለው ሲሆን "አወጣ፥ አቀረበ" የሚል ትርጉም ያለው ሲሆን (Strong's H3318) ሁለተኛው ቃል ደግሞ "אֵלָיו/ኤላቭ" የሚለው ሲሆን "ለእርሱ" የሚል ትርጉም አለው (Strong's H413) ስለዚህ የክፍሉ ቀጥተኛ ትርጉም "ለእርሱ አቀረበ፥ ለእርሱ አወጣ" የሚል ነው። ይህ የመስዋዕቱ ተቀባይ እግዚአብሔር ተብሎ የተጠራው የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን በሚገባ ያረጋግጣል። ምክንያቱም ይህ "אֵלָיו/ኤላቭ" ወይም "ለእርሱ" የሚለው ቃል አንድ ተግባር ለማን እንደተደረገ የሚያሳይ ቃል ነው። አንድ ቃል ለአንድ አካል ከተነገረ ወይም አንድ መስዋዕት ለአንድ አካል ከቀረበ "ለእርሱ ተነገረ" ወይም "ለእርሱ ቀረበ" ለማለት ይህ ቃል ጥቅም ላይ ይውላል። ያ ተግባር ለማን እንደተደረገ የሚያመለክት ቃል ነው። ለምሳሌ፦ "ስለ ሕዝቡ የሆነውን የደኅንነት መሥዋዕት በሬውንና አውራውን በግ አረደ የአሮንም ልጆች #ደሙን_አመጡለት" (ዘሌ 9:18) በዚህ ስፍራ ላይ አሮን በሬውንና አውራውን በግ ካረደ በኋላ ልጆቹ ደሙን እንዳመጡለት እናነባለን። "አመጡለት" ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጥ ልክ ቃል መሳ 6:19 ላይ "አቀረበለት" እንደሚለው ቃል ከሁለት የዕብራይስጥ ቃላት የተዋቀረ ነው። የመጀመሪያው ቃል "מְצִאוּ/ማጻኡ" የሚለው ቃል ሲሆን "አመጡ፥ አቀረቡ" ማለት ነው (Strong's H4672) ሁለተኛው ቃል ደግሞ መሳ 6:18 ላይ ያለው "אֵלָיו/ኤላቭ" የሚለው ቃል ሲሆን "ለእርሱ" የሚል ትርጉም አለው (Strong's H413) ክፍሉ በቀጥታ ሲተረጎም "ለእርሱ አመጡ፥ ለእርሱ አቀረቡ" የሚል ነው። ስለዚህ ዘሌ 9:18 ላይ ይህ "אֵלָיו/ኤላቭ" የሚለው ቃል ደሙ ለማን እንደመጣ የሚያሳይ ቃል ነው። ደሙ የቀረበው ለአሮን ነው። ወይም የደሙ ተቀባይ አሮን ነው። "አመጡ" ሳይሆን "አመጡለት" ተብሎ የተተረጎመው ለዚያ ነው። ስለዚህ በመሳ 6:19 ላይም ይህን "אֵלָיו/ኤላቭ" የሚለውን ቃል በማካተት "አቀረበለት" ሲል መስዋዕቱ እግዚአብሔር ተብሎ ለተጠራው የእግዚአብሔር መልአክ መቅረቡን ያሳያል "እግዚአብሔርም ከመገናኛው ድንኳን ውስጥ ሙሴን ጠርቶ እንዲህ ሲል #ተናገረው" (ዘሌ 1:1) በዚህ ስፍራ ላይ እግዚአብሔር አምላክ ሙሴን እንደተናገረው እናነባለን። "ተናገረው" ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጥ ቃል እንዲሁ የሁለት ዕብራይስጥ ቃላት ውጤት ነው። የመጀመሪያው ቃል "יְדַבֵּר/ይድቫር" የሚለው ቃል ሲሆን "ተናገረ" ማለት ነው (Strong's H1696) ሁለተኛው ቃል ደግሞ ሁለተኛው ቃል ደግሞ መሳ 6:18 ላይ ያለው "אֵלָיו/ኤላቭ" የሚለው ቃል ሲሆን "ለእርሱ" የሚል ትርጉም አለው (Strong's H413) ክፍሉ በቀጥታ ሲተረጎም "ለእርሱ ተናገረ" የሚል ነው። ስለዚህ በዘሌ 1:1 ላይ ይህ "אֵלָיו/ኤላቭ" የሚለው ቃል እግዚአብሔር ለማን እንደተናገረ የሚያሳይ ነው። እግዚአብሔር የተናገረው ለሙሴ ነው። የንግግሩ ተደራሲ ሙሴ ነው። "ተናገረ" ሳይሆን "ተናገረው" ተብሎ የተተረጎመው ለዚያ ነው። ስለዚህ በመሳ 6:19 ላይም ይህን "אֵלָיו/ኤላቭ" የሚለውን ቃል በማካተት "አቀረበለት" ሲል መስዋዕቱ እግዚአብሔር ተብሎ ለተጠራው የእግዚአብሔር መልአክ መቅረቡን ያሳያል። ✍️ ከዚህ ባሻገር ግን መስዋዕቱ የቀረበው ለእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን የምናውቅበት መንገድ አለ። በቁ.19 ላይ እንደምናነበው ጌዴዎን መስዋዕቱን ይዞ ያቀረበለት ከአድባሩ ዛፍ በታች ነው። ይህ መስዋዕቱ የቀረበው ለእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን በማያሻማ ሁኔታ የሚያሳይ ተጨማሪ ማስረጃ ነው። ምክንያቱም የእግዚአብሔር መልአክ ለጌዴዎን ሲገለጥ ተቀምጦ የነበረው ከአድባሩ ዛፍ በታች ነበር፦ " #የእግዚአብሔርም_መልአክ መጥቶ በዖፍራ ባለችው ለአቢዔዝራዊው ለኢዮአስ በነበረችው #በአድባሩ_ዛፍ_በታች_ተቀመጠ ልጁም ጌዴዎን ከምድያማውያን ለመሸሸግ በወይን መጥመቂያው ውስጥ ስንዴ ይወቃ ነበር" (መሳ 6:11) የእግዚአብሔር መልአክ ለጌዴዎን ሲገለጥለት የተቀመጠው ከአድባሩ ዛፍ በታች ነበር። ስለዚህ እርሱን ሲያነጋግረው እዚያ ጋር ሆኖ ነበር ማለት ነው። ጌዴዎንም በቁ.18 ላይ ወደ አንተ እስክመለስ ድረስ አትላወስ ሲለው ከአድባሩ ዛፍ ዘወር አትበል ማለቱ ነበር። መስዋዕቱን ይዞ ተመለሶ ሲመጣ ከአድባሩ ዛፍ በታች ያቀረበው ለዚያ ነው። እያቀረበው የነበረው ከአድባሩ ዛፍ በታች ለነበረው የእግዚአብሔር መልአክ ነውና። ይህ የእግዚአብሔር መልአክ መስዋዕት ተቀባይ እንደሆነና ከቁ.14 ጀምሮ ሲያነጋግረው የነበረው እግዚአብሔር መሆኑን ያሳያል። ▶️ ይቀጥላል

Открыть в Telegram
Просмотры6 120+40%к среднему
Пересылки—
Реакции22
Комментарии—
#1568Текст

🚩 የእግዚአብሔር መልአክና ጌዴዎን (ክፍል 3) ባለፈው ክፍል ላይ መለኮት የሆነው የእግዚአብሔር ልጅ በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር መልአክ በመባል ይገለጥ እንደነበር እና በዚህ መንገድ ከተገለጠባቸው አጋጣሚዎች አንዱ የሆነውን የጌዴዎንን ታሪክ ማየት ጀምረን ነበር። ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ለመግለጽ እንደሞከርነው መልአክ የሚለው ቃል በዕብራይስጥ "ማልአኽ/מַלְאַ֥ךְ" በግሪክ ደግሞ "አንጌሎስ/ἄγγελος" ሲሆን ትርጉሙ መልእክተኛ ማለት ነው። የመልእክተኝነት ግብር ያለው የትኛውም አካል መልአክ/መልእክተኛ ተብሎ ይጠራል። የመልእክተኛው ባህርይ ሰዋዊ ይሁን፥ የፍጡራን መናፍስት ይሁን መለኮታዊ ይሁን የሚታወቀው በአውዱ ነው። እንጂ አንድ አካል መልአክ ስለተባለ ብቻ ከፍጡራን መናፍስት አንዱ ነው ማለት አይደለም። የእግዚአብሔር ልጅም መልአክ የተባለው የአባቱ መልእክተኛ ስለነበር እንጂ ፍጡር ስለሆነ አይደለም። እግዚአብሔር ቢፈቅድ ከባለፈው ክፍል በመቀጠል የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ የእግዚአብሔር መልአክ በመባል ለጌዴዎን የተገለጠበትን ክስተት ማየት እንቀጥላለን፦ "ወደ #አንተም_እስክመለስ ድረስ፥ #ቍርባኔንም አምጥቼ #እስካቀርብልህ ድረስ፥ እባክህ፥ ከዚህ #አትላወስ አለው። #እርሱም። እስክትመለስ ድረስ #እቆያለሁ_አለ" (መሳ 6:18) በቁ.16 ላይ እግዚአብሔር የተባለው የእግዚአብሔር መልአክ ለጌዴዎን ከአንተ ጋር እሆናለሁ ምድያምን እንደ አንድ ሰው አድርገህ ትመታለህ ሲለው ጌዴዎን የምትናገረኝ አንተ እንደሆንህ ምልክት አሳየኝ ይለዋል። ከዚያም በቁ.18 ላይ ያ ምልክት ምን እንደሆነ እናነባለን። እርሱም ወደ አንተ እስክመለስ ድረስ ቁርባኔንም አምጥቼ እስካቀርብልህ ድረስ እባክህ ከዚህ አትላወስ ይለዋል። እርሱም እስክትመለስ ድረስ እቆያለሁ ይላል። ይህ በቁ.18 ላይ የምናነበው ቃል የእግዚአብሔር መልአክ እግዚአብሔር መሆኑን በይበልጥ የሚያረጋግጥ ነው። በቁ.18 ላይ ጌዴዎን "ወደ አንተ እስክመለስ ድረስ" ያለው ማንን ነው? ጌዴዎን በቁ.18 ላይ "ወደ አንተ እስክመለስ ድረስ" ያለው በቁ.16 ላይ ሲያነጋግረው የነበረውን እግዚአብሔር ነው። በቁ.16 ላይ እንደምናነበው እግዚአብሔር ከአንተ ጋር እሆናለሁ ምድያምንም እንደ አንድ ሰው ትመታለህ ብሎት ነበር። ስለዚህ ጌዴዎን በቁ.17-18 ላይ የተናገረው ንግግር እንዲህ ብሎ ለተናገረው እግዚአብሔር የሰጠው መልስ ነው። ስለዚህ ወደ አንተ እስክመለስ ድረስ ያለው በቁ.16 ላይ ሲያነጋግረው ለነበረው እግዚአብሔር ነው ማለት ነው። ነገር ግን ማን ነበር ለጌዴዎን ተገልጦለት የነበረው? ማን ነበር ወደ እርሱ መጥቶ የነበረው? በመሳ 6:11-12 እንደምናነበው ለጌዴዎን ተገልጦለት የነበረው የእግዚአብሔር መልአክ ነው። ስለዚህ ጌዴዎን ቁርባኑን ለማምጣት ሄዶ ከተመለሰም ሊመለስ የሚችለው ወደ እግዚአብሔር መልአክ ነው። ምክንያቱም ተገልጦለት የነበረው እርሱ ነውና። ስለዚህ በመሳ 6:18 ላይ "ወደ አንተ እስክመለስ" ሲል ያ ወደ እርሱ ሊመለስ የሚችለው አካል የእግዚአብሔር መልአክ ነው። ይህ ከምንም ነገር በላይ በቁ.16 ላይ እግዚአብሔር የተባለው፥ ጌዴዎንም ወደ አንተ እስክመለስ ያለለት እግዚአብሔር በቁ.11-12 ላይ ለእርሱ ተገልጦለት የነበረው የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን በሚገባ ያረጋግጣል። ✍️ ጌዴዎን በቁ.17 ላይ ምልክት እንዲሰጠው ጠይቋል። ይህም ምልክት በቁ.18 ላይ እንደተገለጸው ቁርባን ነው። በመሳ 6:18 ላይ "ቁርባን" ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጥ ቃል "ሚንኻ/מִנְחָה" ሲሆን (Strong's H4503) ለእግዚአብሔር የሚቀርብን የአምልኮ መሥዋዕት ወይም ቁርባን ያመለክታል። ለምሳሌ፦ " #ቍርባንህም (מִנְחָה/ሚንኻ) በምጣድ የተጋገረ የእህል ቍርባን ቢሆን፥ በዘይት የተለወሰ የመልካም ዱቄት ቂጣ ይሁን" (ዘሌ 2:5) "ለስሙ የሚገባ ክብርን ለእግዚአብሔር አምጡ፤ #ቍርባን (מִנְחָה/ሚንኻ) ያዙ ወደ አደባባዮችም ግቡ" (መዝ 96:8) "እግዚአብሔርን ከመከተል እንድንመለስ፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና #የእህል_ቍርባን (מִנְחָה/ሚንኻ) እንድናሳርግበት፥ የደኅንነትንም መሥዋዕት እንድናቀርብበት ብለን መሠዊያ ሠርተን እንደ ሆነ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ ይበቀለን" (ኢያ 22:23) "በእግዚአብሔር ፊት ያለው የናሱ መሠዊያ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና #የእህሉን_ቁርባን (מִנְחָה/ሚንኻ) የደኅንነቱንም መሥዋዕት ስብ ይይዝ ዘንድ ታናሽ ስለ ነበረ፥ በዚያ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና #የእህሉን_ቍርባን (מִנְחָה/ሚንኻ) የደኅንነቱንም መሥዋዕት ስብ አሳርጎአልና በእግዚአብሔር ቤት ፊት የነበረውን የአደባባዩ መካከል ንጉሡ በዚያ ቀን ቀደሰ" (1ነገ 8:64) ✍️ ስለዚህ ጌዴዎን ለእግዚአብሔር መልአክ ላቅርብልህ ያለው ቁርባን ለእግዚአብሔር የሚቀርብ የአምልኮ መሥዋዕት ነው። በሙሴ ሕግ በግልጽ እንደተቀመጠው ከእግዚአብሔር በቀር ለማንም መሥዋዕት መሠዋት ክልክል ነው (ዘጽ 22:20) ታዲያ እንዴት ጌዴዎን ለእግዚአብሔር መልአክ መሥዋዕት አቀረበ ከተባለ የእግዚአብሔር መልአክ እግዚአብሔር በመሆኑ ነው። የእግዚአብሔር መልአክ መሥዋዕት መቀበሉ መለኮት ለመሆኑ የማይታበል ማስረጃ ነው። በቁ.18 ላይ እንደምናነበው ጌዴዎን ቁርባኔን #እስካቀርብልህ ነው ያለው። በዚህ ቦታ ላይ "..እስካቀርብልህ.." ተብሎ የተተረጎመው ቃል ከሁለት የዕብራይስጥ ቃላት የተዋቀረ ነው። አንደኛው የዕብራይስጥ ቃል "הִנַּחְתִּ֖י/ሃናኽቲ" የሚለው ቃል ሲሆን "እስካኖር" ወይም "እስካሳርፍ" ማለት ነው (Strong's H3240) ሁለተኛው የዕብራይስጥ ቃል ደግሞ "לְפָנֶ֑יךָ/ለፓኔኻ" የሚለው ቃል ሲሆን "በፊትህ" ማለት ነው (Strong's H6440) ስለዚህ ቃሉ በቀጥታ ሲተረጎም "በፊትህ እስካቀርብ" ማለት ነው። ይህ መሥዋዕቱ የቀረበው ለእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን በሚገባ ያረጋግጣል። ምክንያቱም እነዚህ ሁለት ቃላት መሥዋዕት በመሠዋት አውድ ሲመጡ የእግዚአብሔርን መሥዋዕት ተቀባይነት ይገልጻሉና፦ "አሁንም እነሆ፥ አቤቱ፥ አንተ የሰጠኸኝን የምድሪቱን ፍሬ በኵራት #አቅርቤአለሁ። አንተም በአምላክህ በእግዚአብሔር #ፊት_አኑረው፥ በአምላክህም በእግዚአብሔር ፊት ስገድ" (ዘዳ 26:10) በዚህ ቦታ ላይ ለእግዚአብሔር አምላክ ስለሚቀርበው የበኩር ፍሬ መሥዋዕት እናነባለን። መሥዋዕቱን የሚያቀርበው ሰው "..በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት አኑረው.." በሚለው ቃል መሰረት ለእግዚአብሔር መስዋዕቱን ያቀርባል። በዚህ ቦታ ላይ "ፊት" ተብሎ የተተረጎመው ቃል መሳ 6:18 ላይ ያለው "ፓኒ/פָנֶ֑י" የሚለው ቃል ሲሆን (Strong's H6440) "አኑረው" ተብሎ የተተረጎመው ቃል ደግሞ መሳ 6:18 ላይ ያለው "ሃናኽቶ/הִנַּחְתּ֗וֹ" የሚለው ቃል ነው (Strong's H3240) በሁለቱም ቦታዎች ላይ የቃልና የሀሳብ አንድነት አለ። ✍️ ይህ ማለት በዘዳ 26:10 ላይ የእግዚአብሔር መሥዋዕት ተቀባይነት በተገለጸበት በዚያው መንገድ መሳ 6:18 ላይ የእግዚአብሔር መልአክ መሥዋዕት ተቀባይ መሆኑ ተገልጿል ማለት ነው። በቁ.14 እና በቁ.16 ላይ እግዚአብሔር ከመባሉ ባሻገር የእግዚአብሔር መልአክ መሥዋዕት ተቀባይ መሆኑ ተገልጿል። በኦሪቱ ሕግ መሰረት ከእግዚአብሔር በቀር ለማንም መሠዋት ፍጹም ክልክል ነው (ዘጽ 22:20) ስለዚህ ይህ የእግዚአብሔር መልአክ መሥዋዕት የሚቀበለው መለኮት መሆኑን በሚገባ ያረጋግጣል። ▶️ ይቀጥላል

Открыть в Telegram
Просмотры6 390+46%к среднему
Пересылки—
Реакции20
Комментарии—
#1567Текст

🚩 የእግዚአብሔር መልአክና ጌዴዎን (ክፍል 2) ባለፈው ክፍል ላይ መለኮት የሆነው የእግዚአብሔር ልጅ በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር መልአክ በመባል ይገለጥ እንደነበር እና በዚህ መንገድ ከተገለጠባቸው አጋጣሚዎች አንዱ የሆነውን የጌዴዎንን ታሪክ ማየት ጀምረን ነበር። ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ለመግለጽ እንደሞከርነው መልአክ የሚለው ቃል በዕብራይስጥ "ማልአኽ/מַלְאַ֥ךְ" በግሪክ ደግሞ "አንጌሎስ/ἄγγελος" ሲሆን ትርጉሙ መልእክተኛ ማለት ነው። የመልእክተኝነት ግብር ያለው የትኛውም አካል መልአክ/መልእክተኛ ተብሎ ይጠራል። የመልእክተኛው ባህርይ ሰዋዊ ይሁን፥ የፍጡራን መናፍስት ይሁን መለኮታዊ ይሁን የሚታወቀው በአውዱ ነው። እንጂ አንድ አካል መልአክ ስለተባለ ብቻ ከፍጡራን መናፍስት አንዱ ነው ማለት አይደለም። የእግዚአብሔር ልጅም መልአክ የተባለው የአባቱ መልእክተኛ ስለነበር እንጂ ፍጡር ስለሆነ አይደለም። እግዚአብሔር ቢፈቅድ ከባለፈው ክፍል በመቀጠል የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ የእግዚአብሔር መልአክ በመባል ለጌዴዎን የተገለጠበትን ክስተት ማየት እንቀጥላለን፦ " #እርሱም። ጌታ ሆይ፥ እስራኤልን በምን አድናለሁ? ወገኔ #ከምናሴ ነገድ ከሁሉ ይልቅ የተጠቃ ነው፤ እኔም #በአባቴ ቤት የሁሉ ታናሽ ነኝ #አለው" (መሳ 6:15) መሳ 6:14 ላይ እግዚአብሔር ተብሎ የተጠራው የእግዚአብሔር መልአክ ለጌዴዎን በዚህ በጉልበትህ ሂድ እስራኤልንም ከምድያም እጅ አድን እነሆ ልኬሃለሁ ካለው በኋላ ጌዴዎን ጌታ ሆይ እስራኤልን በምን አድናለሁ ወገኔ ከምናሴ ነገድ ሁሉ ይልቅ የተጠቃ ነው በአባቴም ቤት የሁሉ ታናሽ ነኝ ብሎ ይመልስለታል። ባለፈው ክፍል ለመግለጽ እንደሞከርነው ለጌዴዎን ተገልጦ የነበረው (መሳ 6:11-12) ሲያነጋግረውም የነበረው (መሳ 6:12) የእግዚአብሔር መልአክ ነው። እስከ ቁ.15 ድረስ የቀጠለው ንግግር ቁ.12 ላይ የጀመረው ንግግር ነው። ጌዴዎን ከአንድ አካል ጋር እንጂ ከሁለት አካላት ጋር እየተነጋገረ አልነበረም። ስለዚህ ይህንን መልስ የሰጠው ለእግዚአብሔር መልአክ ነበር። ጌዴዎን በቁ.15 ላይ ለተናገረው ንግግር በቁ.16 ላይ የተሰጠውን መልስ እንመለከታለን፦ " #እግዚአብሔርም። በእርግጥ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፥ #ምድያምንም እንደ አንድ #ሰው አድርገህ ትመታለህ #አለው" (መሳ 6:16) በቁ.16 ላይ እንደምናነበው እግዚአብሔር በእርግጥ ከአንተ ጋር እሆናለሁ ምድያምንም እንደ አንድ ሰው አድርገህ ትመታለህ ብሎ ይመልስለታል። በዚህ ክፍል ላይ እንደምናየው ለጌዴዎን ይህን መልስ የሰጠው እግዚአብሔር ነው። በቁ.12 ላይ እርሱን ማናገር የጀመረው የእግዚአብሔር መልአክ ልክ በቁ.14 ላይ እግዚአብሔር እንደተባለው በቁ.16 ላይም እግዚአብሔር ተብሎ ተጠርቷል። የጽሑፉ ተፈጥሯዊ ፍሰት (the natural flow of the text) እንደሚያሳየው በቁ.14 እና በቁ.16 ላይ እግዚአብሔር ተብሎ እየተጠራ ያለው ተናጋሪ በቁ.12 ላይ ጌዴዎንን ማናገር የጀመረው የእግዚአብሔር መልአክ ነው። የእግዚአብሔር መልአክ በባህርይው መለኮት በመሆኑ በቀጥታ እግዚአብሔር ተብሎ ተጠርቷል። ✍️ በእንዲህ አይነቱ የስነ ጽሑፍ ፍሰት አንድን አካል በሌላ ስሙ መጥራት የተለመደ ነው። ልክ የእግዚአብሔር መልአክ በቁ.12 ላይ የእግዚአብሔር መልአክ ተብሎ በቁ.14 እና በቁ.16 ላይ እግዚአብሔር ተብሎ እንደተጠራው ማለት ነው። ለምሳሌ፦ "የዚያን ጊዜም #ናቡከደነፆር በሲድራቅና በሚሳቅ በአብደናጎም ላይ ቍጣ ሞላበት፥ የፊቱም መልክ ተለወጠባቸው፤ እርሱም ተናገረ፥ የእቶንም እሳት ይነድድ ከነበረው ይልቅ ሰባት እጥፍ አድርገው እንዲያነድዱት #አዘዘ" (ዳን 3:19) በዳን 3:19 ላይ የእቶኑ እሳት ቀድሞ ይነድድ ከነበረው ሰባት እጥፍ እንዲነድድ ያዘዘው ናቡከደነፆር እንደሆነ እናነባለን። ነገር ግን በዚያው አውድ ላይ ናቡከደነፆር በሌላኛው መጠሪያው ሲጠራ እንመለከታለን፦ " #የንጉሡም_ትእዛዝ አስቸኳይ ስለሆነ የእቶኑም እሳት እጅግ ስለሚነድድ፥ ሲድራቅንና ሚሳቅን አብደናጎንም የጣሉአቸውን ሰዎች የእሳቱ ወላፈን ገደላቸው" (ዳን 3:22) በዳን 3:22 ላይ እንደምናነበው ደግሞ የእቶኑ እሳት ሰባት እጥፍ ጨምሮ እንዲነድድ ያዘዘው ንጉሱ ነው። ስለዚህ በቁ.22 ላይ ንገሱ ተብሎ እየተጠራ ያለው በቁ.19 ላይ ናቡከደነፆር ተብሎ የተጠራው ሰው ነው ማለት ነው። ስለዚህ በስነ-ጽሑፉ ተፈጥሯዊ ፍሰት (the natural flow of the literature) መሰረት በሁለት ስያሜዎቹ እየተጠራ ያለው አንዱ ሰው ነው። ▶️ በመሳፍንት 6:11-16 የምንመለከተውም ይህንን ነው። በቁ.12 ላይ የእግዚአብሔር መልአክ ተብሎ የተጠራው አካል በቁ.14 እና በቁ.16 ላይ እግዚአብሔር ተብሎ ተጠርቷል። ከላይ ባየነው ምሳሌ ላይ ናቡከደነፆርም ንጉሱም የአንድ አካል መጠሪያ እንደሆነው በመሳፍንት 6 ላይ እግዚአብሔርም የእግዚአብሔርም መልአክ የአንድ አካል መጠሪያ ነው። አንዱ የእግዚአብሔር ልጅ የተጠራባቸው ስያሜዎች ናቸው። በቁ.16 ላይ እግዚአብሔር ተብሎ የተጠራው የእግዚአብሔር መልአክ ለጌዴዎን ከመለሰለት በኋላ ጌዴዎን እንዲህ ይላል፦ " #እርሱም። በአንተ ዘንድ ሞገስ ካገኘሁ፥ #የምትናገረኝም አንተ እንደ ሆንህ #ምልክት አሳየኝ" (መሳ 6:17) በቁ.16 ለጌዴዎን በእርግጥ ከአንተ ጋር እሆናለሁ ምድያምንም እንደ አንድ ሰው አድርገህ ትመታለህ ሲለው ጌዴዎን በፊትህ ሞገስ ካገኘሁ የምትናገረኝ አንተ እንደሆንህ ምልክት አሳየኝ አለው። ከላይ ለማሳየት እንደሞከርነው ከቁ.12 ጀምሮ ያናግረው የነበረው የእግዚአብሔር መልአክ ነው። እዚህ ቁ.17 ላይ ግን የምትናገረኝ አንተ እንደሆንህ የሚለው በቁ.16 ላይ ሲናገረው የነበረውን እግዚአብሔርን ነው። ይህ በእርግጥም ጌዴዎንን ሲያነጋግረው የነበረው እግዚአብሔር ተገልጦለት የነበረው የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን ያረጋግጣል። ከዚያ ባሻገር ግን በቁ.17 ላይ ጌዴዎን የምትናገረኝ አንተ እንደሆንህ ምልክት ስጠኝ ብሏል። ለምን ምልክት እንዲሰጠው ፈለገ? ጌዴዎን ምልክት እንዲሰጠው የፈለገው እያነጋገረው የነበረው አካል ተራ ሰው አለመሆኑን መረዳት ስለጀመረ ነው። ንግግሩን ከቁ.12-13 ሲጀምር ጌዴዎን ከተራ ሰው ጋር የሚነጋገር ነበር የመሰለው። ነገር ግን ንግግሩ በቀጠለ ጊዜ የተገለጠለት አካል እንደሚልከው (ቁ.14) ከእርሱም ጋር እንደሚሆን (ቁ.16) ነገረው። ተራ ሰው እነዚህን ነገሮች ሊናገር አይችልም። ምክንያቱም አዳኝ መስፍኖችን የሚልከው ወይም የሚያስነሳው እግዚአብሔር ነው (መሳ 2:16) ከእስራኤል መሪዎች ጋርም የሚሆነው እግዚአብሔር ነው (ኢያሱ 1:5) ስለዚህ ጌዴዎን እያነጋገረው ያለው አካል ተራ ሰው አለመሆኑን በመጠርጠር ምልክት እንዲሰጠው ጠየቀ። ♦️ በመሳፍንት ዘገባ ውስጥ ለጌዴዎን የተገለጠው አካል እግዚአብሔር መሆኑን በመንፈስ ቅዱስ ጥንሳሴ የነገረን የመሳፍንቱ ጸሐፊ ነው። በሰዓቱ ግን ጌዴዎን እግዚአብሔር እንደተገለጠለት አላወቀም ነበር። ነገር ግን ያ የተገለጠለት አካል ተራ ሰው ሊናገር በማይችለው መንገድ ሲናገር ጌዴዎን ይህ አካል ተራ ሰው አለመሆኑን ጠርጥሮ ምልክትን ጠይቋል። ▶️ ይቀጥላል

Открыть в Telegram
Просмотры6 710+53%к среднему
Пересылки—
Реакции10
Комментарии—
#1566Текст

🚩 የእግዚአብሔር መልአክና ጌዴዎን (ክፍል 1) ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ለመመልከት እንደሞከርነው በብሉይ ኪዳን መለኮት የሆነው የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር መልአክ ተብሎ ይጠራ ነበር፥ በዚያም መንገድ ይገለጥ ነበር። መልአክ የሚለው ቃል በዕብራይስጥ "ማልአኽ/מַלְאַ֥ךְ" በግሪክ ደግሞ "አንጌሎስ/ἄγγελος" ሲሆን ትርጉሙ መልእክተኛ ማለት ነው። የመልእክተኝነት ግብር ያለው የትኛውም አካል መልአክ/መልእክተኛ ተብሎ ይጠራል። የመልእክተኛው ባህርይ ሰዋዊ ይሁን፥ የፍጡራን መናፍስት ይሁን መለኮታዊ ይሁን የሚታወቀው በአውዱ ነው። እንጂ አንድ አካል መልአክ ስለተባለ ብቻ ከፍጡራን መናፍስት አንዱ ነው ማለት አይደለም። የእግዚአብሔር ልጅም መልአክ የተባለው የአባቱ መልእክተኛ ስለነበር እንጂ ፍጡር ስለሆነ አይደለም። ዛሬ እግዚአብሔር ቢፈቅድ የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ በዚህ መንገድ ከተገለጠባቸው አጋጣሚዎች መካከል አንዱን አጋጣሚ ለመመልከት የምንሞክር ይሆናል። እርሱም ለጌዴዎን የተገለጠበት ታሪክ ነው። ክፍሉ እንዲህ ይላል፦ "11 #የእግዚአብሔርም_መልአክ መጥቶ በዖፍራ ባለችው ለአቢዔዝራዊው ለኢዮአስ በነበረችው በአድባሩ ዛፍ በታች ተቀመጠ፤ ልጁም ጌዴዎን ከምድያማውያን ለመሸሸግ በወይን መጥመቂያው ውስጥ ስንዴ ይወቃ ነበር። 12 #የእግዚአብሔርም_መልአክ ለእርሱ #ተገልጦ። አንተ ጽኑዕ ኃያል ሰው፥ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው አለው" (መሳፍንት 6:11-12) በዚህ ስፍራ ላይ ጌዴዎን ከምድያማውያን በመሸሸግ በወይን መጥመቂያ ውስጥ ስንዴ ይወቃ እንደነበር እናነባለን። በጊዜው እስራኤላውያን በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር ስለሰሩ ሰባት ዓመታት በምድያም እጅ አሳልፎ ሰጥቷቸው ነበር (መሳ 6:1) በዚህም ምክንያት የምድያም እጅ ስለጠነከረችባቸው የእስራኤል ልጆች በተራራ ላይ ጉድጓድና ዋሻ ምሽግም ሰርተው ነበር (መሳ 6:2) ይህ የሆነበት ምክንያት እስራኤላውያን ዘር በዘሩ ጊዜ ምድያማውያን፥ አማሌቃውያን በምስራቅ የሚኖሩ ሰዎች ይመጡባቸዋል፥ በእነርሱም ላይ ይሰፍሩባቸዋል እስከ ጋዛም ድረስ የምድሩን ቡቃያ ያጠፉ ነበር፥ ምግብንም ለእስራኤል አይተውም ነበር፥ በግ ወይም በሬ ወይም አሕያ ቢሆን አይተውም (መሳ 6:3-4) ስለዚህ የእስራኤል ልጆች ወደ እግዚአብሔር ጮኹ (መሳ 6:7) የእግዚአብሔር መልአክ ለጌዴዎን የተገለጠው በዚህ ሁኔታ ነው። በቁ.11 ላይ እንደምናነበው የእግዚአብሔር መልአክ የተቀመጠው ከአድባሩ ዛፍ በታች ነበር። ይህ በኋላ ላይ ለሚነሱት ወሳኝ ነጥቦች አስፈላጊ የሆነ መረሳት የሌለበት ነጥብ ነው። ከዚያ በቁ.12 ላይ እንደተገለጸው የእግዚአብሔር መልአክ ለጌዴዎን ተገልጦ ያነጋግረው ዘንድ ይጀምራል። ይህም በኋላ ለሚነሳው ነጥብ እጅግ አስፈላጊ ሀሳብ ነው። የእግዚአብሔር መልአክ ጌዴዎንን "አንተ ጽኑዕ ኃያል ሰው፥ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው" ይለዋል። ስለዚህ ከቁ.12 እንደምንረዳው ጌዴዎንን የሚያናግረው ተናጋሪው የእግዚአብሔር መልአክ ነው። ከዚያም የእግዚአብሔር መልአክ ጌዴዎንን እንደዚህ ሲለው ጌዴዎን የሚከተለውን መልስ ይመልስለታል፦ "ጌዴዎንም። ጌታዬ ሆይ፥ #እግዚአብሔር ከእኛ ጋር #ከሆነ ይህ ነገር ሁሉ ለምን ደረሰብን? አባቶቻችንስ። #እግዚአብሔር ከግብፅ አውጥቶናል ብለው ይነግሩን የነበረ ተአምራቱ ወዴት አለ? ወዴት አለ? አሁን ግን እግዚአብሔር ትቶናል፥ #በምድያማውያንም እጅ አሳልፎ ሰጥቶናል #አለው" (መሳ 6:13) የእግዚአብሔር መልአክ ለጌዴዎን አንተ ጽኑዕ ኃያል ሰው እግዚአብሔር ካንተ ጋር ነው ሲለው ጌዴዎን እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ለምን ይህ ሁሉ መከራ ደረሰብን? አባቶቻችንስ እግዚአብሔር ከግብፅ አውጥቶናል ብለው የነገሩን ተአምራቱ ወዴት አለ? አሁን ግን እግዚአብሔር ትቶናል በምድያማውያን እጅ አሳልፎ ሰጥቶናል ብሎ ይመልስለታል። ♦️ ጌዴዎን በመሳ 6:13 ላይ የመለሰውን መልስ ሲመልስ እየተነጋገረ የነበረው ከተራ ሰው ጋር እንደሆነ ነበር የሚያስበው። እንጂ እስከዚህ ሰዓት ድረስ የተገለጠለት የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን አላወቀም ነበር። ነገር ግን ቀጥለን እንደምንመለከተው ንግግሩ ሲቀጥል ጌዴዎን የተገለጠለት ተራ ሰው እንዳልሆነ መረዳት ይጀመራል። ከዚያም በመሳ 6:13 ላይ ጌዴዎን እንደዛ ከመለሰ በኋላ አስደናቂ ነገር እንመለከታለን፦ " #እግዚአብሔርም ወደ እርሱ #ዘወር ብሎ። በዚህ በጕልበትህ ሂድ፥ እስራኤልንም ከምድያም እጅ አድን፤ እነሆ፥ ልኬሃለሁ #አለው" (መሳ 6:14) ጌዴዎን በቁ.13 ላይ እግዚአብሔር ትቶናል ብሎ ለተናገረው ንግግር በቁ.14 ላይ መልስ ሲሰጠው እናነባለን። እርሱም በዚህ በጉልበትህ ሂድ እስራኤልንም ከምድያም እጅ አድን እነሆ ልኬሃለሁ የሚል ነበር። እስራኤላውያን የተጣሉ እንዳልሆኑ ነገር ግን አሁን ከምድያማውያን እጅ የሚድኑበት ጊዜ እንደደረሰና ለዚህም ተልዕኮ የተመረጠው እርሱ እንደሆነ ተነገረው። ነገር ግን በቁ.14 ላይ ይህን መልስ ለጌዴዎን የሰጠው ማን ነው ስንል እግዚአብሔር ነው! ከላይ ከቁ.12 ጀምሮ ከጌዴዎን ጋር ሲናገር የነበረው የእግዚአብሔር መልአክ ነው። ጌዴዎንም በቁ.13 ላይ የመለሰው ለእግዚአብሔር መልአክ ነው። ነገር ግን በቁ.14 ላይ ከጌዴዎን ጋር ሲነጋገር የነበረው አካል #እግዚአብሔር ወይም ያሕዌ ተብሎ ተጠርቷል። ✍️ በቁ.14 ላይ #እግዚአብሔር ወይም #ያሕዌ ተብሎ የተጠራው የእግዚአብሔር መልአክ ነው! በጽሑፉ ተፈጥሯዊ ፍሰት (The natural flow of the text) እግዚአብሔር ተብሎ እየተጠራ ያለው የእግዚአብሔር መልአክ ነው። ጌዴዎን ከሁለት አካላት ጋር እየተነጋገረ አልነበረም። ከቁ.12-14 ድረስ ሲነጋገር የነበረው ከአንደ አካል ጋር ነበር። ያ ከጌዴዎን ጋር ሲነጋገር የነበረው አካል በቁ.12 ላይ የእግዚአብሔር መልአክ ተብሎ ተጠርቶ በቁ.14 ላይ ግን እግዚአብሔር ተብሎ ተጠርቷል። ምክንያቱም መለኮት የሆነው የእግዚአብሔር ልጅ ነውና። እግዚአብሔር ወይም ያሕዌ መባሉ በባህርይው አምላክ መሆኑን የሚያሳይ ነው። ለዚህ ተጨማሪ ማስረጃ የሚሆነው ደግሞ በመሳ 6:14 ላይ "እግዚአብሔርም ወደ እርሱ ዘወር ብሎ" መባሉ ነው። እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን የሞላ፥ በቦታ የማይወሰን አምላክ ነው (ኤር 23:23-24 መዝ 139:8) ስለዚህ እንዴት ዘወር አለ ሊባልለት ይችላል? ከየት ነው ዘወር ያለው? ወደ የት ነው ዘወር ያለው? ይህ ሊባል የቻለው በዚህ ቦታ እግዚአብሔር እየተባለ ያለው የእግዚአብሔር መልአክ በመሆኑ ነው። በዚህ ቦታ ላይ የእግዚአብሔር መልአክ ለጌዴዎን ተገልጦ ነበር (መሳ 6:12) ሲገለጥም ለጌዴዎን ታይቶታል (መሳ 6:22) የተገለጠውም በሰው አምሳል ነው (መሳ 6:21) ስለዚህ የተገለጠለት በዚህ መልኩ ስለሆነ ወደ እርሱ ዘወር ሊል ይችላል። በሰው አምሳል ስለሆነ የተገለጠው ወደ እርሱ ዘወር አለ ሊባልለት ችሏል። ይህ በመሳ 6:14 ላይ እግዚአብሔር የተባለው መልአኩ ለመሆኑ የማይታበል ተጨማሪ ማስረጃ ነው። በዚህ ቦታ ላይ እግዚአብሔር የተባለው በሰው አምሳል ያልተገለጠው የመልአኩ ላኪ ወይም አብ ቢሆን ኖሮ ዘወር አለ ባልተባለለት ነበር። ወደ እርሱ ሊዞር በሚችልበት የሰው አምሳል አልተገለጠምና። ስለዚህ ወደ እርሱ ዘወር አለ የተባለለት በሰው አምሳል የተገለጠው የእግዚአብሔር መልአክ ወይም ልጁ ነው። ▶️ ይቀጥላል

Открыть в Telegram
Просмотры3 720−15%к среднему
Пересылки—
Реакции21
Комментарии—
#1564Текст

🚩 የዕብራውያን መልእክት ጸሐፊ (ክፍል 27) ባለፉት ተከታታይ ክፍሎች የዕብራውያን መልእክት ጸሐፊ ሐዋሪያው ጳውሎስ ለመሆኑ ከራሱ ከዕብራውያን መልእክት ውስጠ-ጽሑፋዊ (inter-textual) ማስረጃዎችን ማቅረብ ጀምረን ነበር። ሙስሊሞች ሆኑ ሌሎች ከክርስትና ውጪ ያሉ አካላት የዕብራውያን መልእክት ጸሐፊ ስለማይታወቅ መጽሐፉ የመጽሐፍ ቅዱስ አካል መሆን የለበትም፥ የእግዚአብሔርም ቃል ሊሆን አይችልም ብለው ሊሟገቱ ይሞክራሉ። ነገር ግን ባለፉት ክፍሎች ለማሳየት እንደሞከርነው ይህ ፍጹም ስህተት የሆነ አመለካከት ነው። የዕብራውያን መልእክት ጸሐፊ ሐዋሪያው ጳውሎስ ለመሆኑ ከምሁራንና ከቤተክርስቲያን ታሪክ ብዙ ማስረጃዎችን ማምጣት ይቻላል። በተጨማሪም ከራሱ ከዕብራውያን መልእክት ጸሐፊው ራሱ ሐዋሪያው ጳውሎስ መሆኑን የሚያረጋግጡ ማስረጃዎችንም ማቅረብ ይቻላል ▶️ እግዚአብሔር ቢፈቅድ በዚህም ክፍል ላይ ካለፉት ክፍሎች በመቀጠል የዕብራውያኑ ጸሐፊ ራሱ ሐዋሪያው ጳውሎስ መሆኑን የሚያረጋግጡ ተጨማሪ ውስጠ-ጽሑፋዊ (inter-textual) ማስረጃዎችን ማቅረብ እንቀጥላለን፦ 54) አዲስን መሰረት አለመመስረት "ስለዚህ የክርስቶስን ነገር መጀመሪያ የሚናገረውን ቃል ትተን ወደ ፍጻሜ እንሂድ፤ #መሠረትን_ደግመን_አንመሥርት፥ እርሱም ከሞተ ሥራ ንስሐና በእግዚአብሔር እምነት፥ ስለ ጥምቀቶችና እጆችንም ስለ መጫን ስለ ሙታንም ትንሣኤ ስለ ዘላለም ፍርድም ትምህርት ነው" (ዕብ 6:1-2) በዚህ ስፍራ ላይ የዕብራውያን ጸሐፊ አዲስን መሰረት ስላለመመስረት ሲናገር እንመለከታለን። በበፊተኛው ምዕራፍ ላይ የዕብራውያን ጸሐፊ የዕብራውያን ክርስቲያኖችን እንዳልበሰሉ ይነግራቸዋል። በክርስትና ከቆዩበት ጊዜ አንጻር አስተማሪዎች መሆን ሲገባቸው እነርሱ ግን ገና ለወተት ማለትም ስለ እግዚአብሔር ቃል ላለው የመጀመሪያው ትምህርት እንጂ ለጠንካራ ምግብ ወይም ጠለቅ ላለው የነገረ እግዚአብሔር ትምህርት እንዳልደረሱ ይነግራቸዋል (ዕብ 5:12-14) ይህን ካለ በኋላ ነው በቀጣዩ ምዕራፍ ላይ ስለዚህ የክርስቶስን ነገር መጀመሪያ የሚናገረውን ቃል ትተን ወደ ፍጻሜ እንሂድ አዲስ መሰረትም አንመስርት ያለው። ይህ ማለት ስለ ክርስቶስ ማንነት ከመጀመሪያውና ከቀላሉ ትምህርት ተሻግራችሁ ወደ ላቀው ወደ ረቀቀው መረዳት እለፉ ማለት ነው። ሰዎቹ በመንፈሳዊ አረዳዳቸው ለጋ እንደነበሩ በበፊተኛው ምዕራፍ ላይ ስለገለጸ በቀጣዩ ምዕራፍ ላይ ከዚህ ለጋ ከሆነ መንፈሳዊ አረዳድ ወጥታችሁ ወደ ፍጻሜው ማለትም ወደ በለጠውና የበሰሉ ክርስቲያኖች ወዳላቸው መረዳት ኑ ማለት ነው። ነገር ግን ወደ ተሻለው መረዳት ሲመጡ አዲስ መሰረት በመመስረት አይደለም። ማለትም ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን አስመልክቶ ያለውን መሰረታዊውን የክርስትና ትምህርት ትቶ ሌላ ትምህርትን በመፍጠር ወይም በማስተማር አይደለም። የጌታን ማንነት አስመልክቶ በአረዳዳቸው መብሰልና መጨመር ያለባቸው ቀድሞ በተመሰረቱበት መሰረት ላይ ሆነው ነው። የዕብራውያን ጸሐፊ አዲስ መሰረት መመስረት እንደሌለበት መናገሩ ጸሐፊው ሐዋርያው ጳውሎስ ለመሆኑ ውስጠ-ጽሑፋዊ (Inter-Textual) ማስረጃ ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ አዲስ መሰረት መመስረት እንደሌለበት በመልእክቱ ገልጿልና፦ " #ከተመሠረተው_በቀር_ማንም_ሌላ_መሠረት ሊመሠርት #አይችልምና፥ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው" (1ቆሮ 3:11) በዚህ ስፍራ ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ ከተመሠረተው መሠረት በቀር ማንም ሌላ መሠረት ሊመሠርት እንደማይችልና ይህም መሠረት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ ሲናገር እንመለከታለን። በቁ.4 ላይ አንዱ እኔ የጳውሎስ ነኝ ሁለተኛውም እኔ የአጵሎስ ነኝ ቢል ሥጋውያን መሆናችሁ አይደለምን ይላል። ከቁ.1-3 ላይ የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች ለጽኑ መብል ያልደረሱ ወተት ሊጋቱ የሚገባቸው በመንፈሳዊ ደረጃቸው ገና መሆናቸውን ወይም ሥጋውያን መሆናቸውን ከገለጸ በኋላ ይህ ሥጋዊነት ምን እንደሚመስል በቁ.4 ላይ ይናገራል። እርሱም "እኔ የእከሌ ነኝ እኔ የእከሌ ነኝ" ብለው መከፋፈላቸው ነው። ጌታ ኢየሱስን በመከተል ፈንታ ሰውን አይቶ መከፋፈል የሥጋዊነት ምልክት መሆኑን ይገልጻል። ከዚያም በቁ.5 ላይ አጵሎስ ምንድነው? ጳውሎስስ ምንድነው? በእነርሱ እጅ ያመናችሁ አገልጋዮች ናቸው፥ ለእያንዳንዳቸውም ጌታ እንደሰጣቸው እንደሚያገለግሉ ይገልጻል። ከዚያም በቁ.6-7 ላይ እርሱ እንደተከለ አጵሎስ እንዳጠጣ ነገር ግን ያሳደገው እግዚአብሔር እንደነበርና የሚያሳድግ እግዚአብሔር እንጂ የሚተክል ቢሆን ወይም የሚያጠጣ ቢሆን አንዳች አይደለም ይላል። ይቀጥልና በቁ.8 ላይ የሚተክልና የሚያጠጣ አንድ ናቸው ነገር ግን እያንዳንዱ እንደ ራሱ ድካም መጠን የራሱን ደመወዝ ይቀበላል ይላል። ይህ ማለት የሚተክልም የሚያጠጣም ሁለቱም ከእግዚአብሔር የስራቸውን መጠን የሚከፈላቸው አገልጋዮች ናቸው እንጂ የእምነት መሰረት አይደሉም ማለት ነው። ከዚያም በቁ.9 ላይ የእግዚአብሔር እርሻ ናችሁ የእግዚአብሔር ሕንጻ ናችሁ እኛም ከእርሱ ጋር የምንሰራ ነንና ይላል። ከዚያም በቁ.10 ላይ የእግዚአብሔር ጸጋ እንደተሰጠኝ መጠን እንደ ብልሃተኛ የአናጺ አለቃ መሠረትን መሠረትሁ ሌላውም በራሱ ያንጻል። እያንዳንዱ ግን በእርሱ ላይ እንዴት እንዲያንጽ ይጠንቀቅ ይላል። መሠረትን መሰረትሁ ሲል መሰረታዊውን የክርስትና ትምህርት ለእናንተ በሕንጻ ለተመሰላሁት ክርስቲያኖች አስተማርሁ ማለት ነው። ሌላውም በራሱ ያንጻል ማለት በዚያ በተመሰረተው መሰረት ላይ ከፍ ያሉ ተጨማሪ የክርስትና ትምህርቶችን ያስተምራል ማለት ነው። እያንዳንዱ በእርሱ ላይ እንዴት እንዲያንጽ ይጠንቀቅ ማለት ደግሞ ከመሰረቱ ውጪ የሆነን ትምህርት አለማስተማሩን ይጠንቀቅ ማለት ነው። ለዚያ ነው ቀጥሎ በቁ.11 ላይ ከተመሰረተው በቀር ማንም ሌላ መሠረት ሊመሰርት አይችልም እርሱም ክርስቶስ ነው ያለው። አንድ ጊዜ ከተማሩት ነገረ ክርስቶስ ውጪ የሆነን ሌላ ነገረ ክርስቶስ እንደ እምነት መሰረት መስበክ አይቻልም። በ1ቆሮ 3:11 ላይ የምንመለከተው ይህ ሀሳብ በዕብ 6:1-2 ላይ ያለው ራሱ ሀሳብ መሆኑ የሁለቱም መልእክቶች ጸሐፊ ራሱ ሐዋርያው ጳውሎስ ለመሆኑ ውስጠ-ጽሑፋዊ (Inter-Textual) ማስረጃ ነው። ♦️ 1ቆሮንቶስ 3:1-11 እና ዕብራውያን 5:12-14 እና ዕብ 6:1-2 ከፍተኛ ቁርኝት ያላቸው ክፍሎች ናቸው። በሁለቱም ቦታዎች የአማኞች አለመብሰል ተገልጿል (1ቆሮ 3:1-3 ዕብ 5:12-14) አማኞቹ ስላልበሰሉ በወተት ስለተመሰለው የመጀመሪያው የክርስትና ትምህርት ተነግሯል (1ቆሮ 3:2 ዕብ 5:13) ደግሞም አዲስ መሰረት መመስረት እንደሌለበት ተገልጿል (1ቆሮ 3:11 ዕብ 6:1-2) የሁለቱም ክፍሎች መዋቅር (structure) አንድ አይነት መሆኑ የሁለቱም ክፍሎች ጸሐፊ ራሱ ሐዋርያው ጳውሎስ ለመሆኑ የማይታበል ማስረጃ ነው። ▶️ ይቀጥላል

Открыть в Telegram
Просмотры4 640+6%к среднему
Пересылки—
Реакции11
Комментарии—
#1563Текст

🚩 እሬቻ "1 በመካከልህም ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ቢነሣ፥ ምልክትም ተአምራትም ቢሰጥህ፥ 2 እንደ ነገረህም ምልክቱ ተአምራቱም ቢፈጸም፥ እርሱም። ሄደን #የማታውቃቸውን ሌሎች #አማልክት እንከተል #እናምልካቸውም ቢልህ" (ዘዳ 13:1-2) ሰሞኑን እሬቻ የተሰኘው በአል በአዲስ አበባ ሲከበር ነበር። ይህ በአል ሃይማኖታዊ በአል ሲሆን የኦሮሞ ሕዝብ ወንጌልን ሰሞቶ ወደ ክርስትና ከመምጣቱ በፊት የነበረበት ግልጽ ጣዖት አምልኮ ነው። በክርስቶስ ኢየሱስ ወንጌል አማካኝነት የእስራኤልን አምላክ ከማወቁ በፊት የነበረበት ጣዖታዊ ባዕድ አምልኮ ነው የእግዚአብሔር ቃል እንደሚናገረው ከግብፅ ምድር የወጡት እስራኤላውያን ካወቁት አምላክ ከእግዚአብሔር/ከያሕዌ በቀር ሌሎች አማልክትን ማምለክ እግዚአብሔር የሚጸየፈው ጣዖት አምልኮ ነው። በእሬቻ በአል የሚመለከው ዋቃና ሌሎቹ ጣዖታት (አቴቴ፥ ቦርንትቻ ወዘተ...) በሙሉ እስራኤል ያላወቃቸው እርኩሳን ጣዖታት ናቸው (ዘዳ 29:17 1ነገ 11:7) እነዚህን ጣዖታት ማምለክ በጣዖት አምላኪነት ያስጠይቃል፥ የእግዚአብሔርንም ቁጣ በምድር ላይ ያመጣል ✍️ መጽሐፍ ቅዱስ ከእስራኤል አምላክ ከእግዚአብሔር ውጪ የሆኑ አማልክት በሙሉ አጋንንት እንደሆኑ ይናገራል፦ "17 #እግዚአብሔር ላልሆኑ #አጋንንት፥ #ለማያውቋቸውም #አማልክት" (ዘዳ 32:17) "አይደለም፤ ነገር ግን #አሕዛብ የሚሠዉት #ለአጋንንት እንዲሆን እንጂ #ለእግዚአብሔር እንዳይሠዉ እላለሁ፤ ከአጋንንትም ጋር #ማኅበረተኞች #እንድትሆኑ #አልወድም" (1ቆሮ 10:20) ስለዚህ አንድ ሰው በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ወደዚህ በአል ከሄደና ተሳታፊ ከሆነ በአምልኮተ አጋንንት እየተሳተፈ ነው። አጋንንትን እያመለከ ነው። የእግዚአብሔር ቃል "..የአጋንንት ማህበርተኞች እንድትሆኑ አልወድም.." እያለ አንድ ሰው ወደዚህ ባዕድ አምልኮ ሄዶ ከተባበረ የእርኩሳን መናፍስት ማህበርተኛ እየሆነ ነው። እግዚአብሔርን ያልሆኑ ሰይጣናትን በቀጥታ እያመለከ ነው በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያምኑ ክርስቲያኖች ከጣዖታት ጋር #በምንም_አይነት መንገድ ሕብረት ሊኖራቸው አይችልም፦ " #ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም #ከጣዖት ጋር ምን #መጋጠም አለው? እኛ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ #መቅደስ ነንና እንዲሁም እግዚአብሔር ተናገረ እንዲህ ሲል። በእነርሱ እኖራለሁ በመካከላቸውም እመላለሳለሁ፥ አምላካቸውም እሆናለሁ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።" (2ቆሮ 6:16) ➢ ከላይ የተገለጸው አይነት ጣዖት አምልኮ ሁሉ ደግሞ የዘላለምን ሞት እንደሚያስከትል መጽሐፍ ቅዱስ አስረግጦ ይነግረናል፦ "ዳሩ ግን የሚፈሩና የማያምኑ የርኵሳንም የነፍሰ ገዳዮችም የሴሰኛዎችም የአስማተኛዎችም #ጣዖትንም_የሚያመልኩ የሐሰተኛዎችም ሁሉ ዕድላቸው #በዲንና_በእሳት በሚቃጠል ባሕር ነው፤ ይኸውም #ሁለተኛው_ሞት_ነው" (ራዕ 21:8) "ውሻዎችና አስማተኞች ሴሰኛዎችም ነፍሰ ገዳዮችም #ጣዖትንም_የሚያመልኩት ውሸትንም የሚወዱና የሚያደርጉ ሁሉ #በውጭ_አሉ" (ራዕ 22:15) "20 መዳራት፥ #ጣዖትን_ማምለክ፥ ምዋርት፥ ጥል፥ ክርክር፥ ቅንዓት፥ ቁጣ፥ አድመኛነት 21 መለያየት፥ መናፍቅነት፥ ምቀኝነት፥ መግደል፥ ስካር፥ ዘፋኝነት፥ ይህንም የሚመስል ነው። አስቀድሜም እንዳልሁ፥ እንደዚህ ያሉትን የሚያደርጉ #የእግዚአብሔርን መንግሥት #አይወርሱም" (ገላ 5:20-21) "9 ወይስ ዓመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንዳይወርሱ አታውቁምን? አትሳቱ፤ ሴሰኞች ቢሆን ወይም #ጣዖትን_የሚያመልኩ ወይም አመንዝሮች ወይም ቀላጮች ወይም ከወንድ ጋር ዝሙት የሚሠሩ 10 ወይም ሌቦች ወይም ገንዘብን የሚመኙ ወይም ሰካሮች ወይም ተሳዳቢዎች ወይም ነጣቂዎች የእግዚአብሔርን #መንግሥት #አይወርሱም" (1ቆሮ 6:9-10) "ይህን እወቁ፤ አመንዝራም ቢሆን ወይም ርኵስ ወይም የሚመኝ እርሱም #ጣዖትን_የሚያመልክ በክርስቶስና በእግዚአብሔር #መንግሥት ርስት #የለውም" (ኤፌ 5:5) ▶️ የዚህ አስከፊ እርኩሰት ውጤት የዘላለም ሞት በመሆኑ፥ መጽሐፍ ቅዱስ በተደጋጋሚ ከጣዖት አምልኮ እንድንሸሽ አዝዞናል፦ "ልጆች ሆይ፥ #ከጣዖታት ራሳችሁን #ጠብቁ" (1ዮሐ 5:21) "ስለዚህ፥ ወዳጆቼ ሆይ፥ #ጣዖትን ከማምለክ #ሽሹ" (1ቆሮ 10:14) "ሕዝብም ሊበሉ ሊጠጡም ተቀመጡ ሊዘፍኑም ተነሡ ተብሎ እንደ ተጻፈ ከእነርሱ አንዳንዶቹ እንዳደረጉት #ጣዖትን #የምታመልኩ #አትሁኑ" (1ቆሮ 10:7) "ነገር ግን #ከጣዖት ርኵሰትና ከዝሙት ከታነቀም ከደምም #ይርቁ ዘንድ እንድንጽፍላቸው እቈርጣለሁ" (ሐዋ 15:20) "አምነው ስለ ነበሩ አሕዛብ ግን #ለጣዖት ከተሠዋ ከደምም ከታነቀም ከዝሙትም #ነፍሳቸውን #እንዲጠብቁ ፈርደን እኛ ጽፈንላቸዋል" (ሐዋ 21:25) " #ለጣዖት ከተሠዋ፥ ከደምም፥ ከታነቀም፥ ከዝሙትም #ትርቁ ዘንድ ከዚህ ከሚያስፈልገው በቀር ሌላ ሸክም እንዳንጭንባችሁ እኛና መንፈስ ቅዱስ ፈቅደናልና፤ ከዚህም ሁሉ ራሳችሁን ብትጠብቁ በመልካም ትኖራላችሁ። ጤና ይስጣችሁ" (ሐዋ 15:28-29) ▶️ እሬቻ ባህል አይደለም። እሬቻ በባህል ስም የሚካሄድ ጣዖት አምልኮ ነው። በባህልና በሌሎች ሰበቦች ስም እግዚአብሔር በልጁ ወንጌል ብርሃን ካዳነንና ካላቀቀን ጣዖት አምልኮ ጋር ተመልሰን መቆራኘት፥ ተቆራኝተንም በዚህ እርኩሰት ረክሰን ነፍሶቻችንን ማጣት የለብንም! ቃሉ እንደሚለው እግዚአብሔርን #ብቻ እናምልክ! "ሳሙኤልም የእስራኤልን ቤት ሁሉ። በሙሉ ልባችሁ ወደ እግዚአብሔር ከተመለሳችሁ እንግዶችን አማልክትና አስታሮትን ከመካከላችሁ አርቁ፥ ልባችሁንም ወደ #እግዚአብሔር አቅኑ፥ እርሱንም #ብቻ #አምልኩ፤ ከፍልስጥኤማውያንም እጅ ያድናችኋል ብሎ ተናገራቸው" (1ሳሙ 7:3) "ያን ጊዜ ኢየሱስ። ሂድ፥ አንተ ሰይጣን ለጌታህ #ለአምላክህ ስገድ እርሱንም #ብቻ #አምልክ ተብሎ ተጽፎአልና አለው" (ማቴ 4:10) ♦️ በክርስቶስ ስም የእሬቻን ጣዖት አምልኮ #እንቢ በሉት! Say #No to irecha Idol Worship in the name of Christ!

Открыть в Telegram
Просмотры4 050−7%к среднему
Пересылки—
Реакции48
Комментарии—