Кабинет

Посты канала The Christian News

сначала новые

#4846Превью ссылки
Просмотры222−65%к среднему
Пересылки—
Реакции2
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч55
6 ч222
  1. Через 1 час55
  2. Через 6 часов222
  3. Всего сейчас222
#4845Превью ссылки

"ከኢትዮጵያ ቤተክርስቲያናት 2 በመቶ የሚሆኑት እንኳን ሚዲያን በአግባቡ አይጠቀሙም" የሚዲያ ባለሞያ ዘሪሁን ግርማ ዛሬ ላይ ምናልባት አብዛኛው አገልጋዮች እራሳቸውን ከፕልፒት ይልቅ ሚዲያ ላይ እያስተዋወቁ እንደሆነ የሚታዩ ብዙ ምልክቶች አሉ። ይህንን እኔም በግሌ አምናለሁ። ነገር ግን የወንጌላውያን ሚዲያ ባለሞያዎች ማሕበር ፕሬዝደንት እና የሚዲያ ባለሞያ የሆኑት ወንድም ዘሪሁን ግርማ ግን ይህንን ሃሳብ በተቃራኒው ይሞግታል። ከሰሞኑ "ሚዲያ እና የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን" የሚል 2ኛ መጽሀፉን ለንባብ ለማቅረብ እየተዘጋጀ የሚገኘው ወንድም ዘሪሁን ግርማ ከኢቫንጀሊካል ሚዲያ ጋር በነበረው ቆይታ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን (የወንጌላውያን) ሚዲያን 2 በመቶ እንኳን እየተጠቀመችበት አይደለም ይላል። መሪዎች ሊነቁ እና ሚዲያን በትክክለኛው መንገድ ሊጠቀሙ ይገባል የሚለው ወንድም ዘሪሁን አሁን ላይ ምን ያክል ቤተክርስቲያን እና አጥቢያዎች እንዳሉ በማንሳት ከእነዚህ መካከል ምን ያክሉ ውጤታማ እና ትክክለኛ በሆነ መንገድ ሚዲያን ይጠቀማሉ የሚለውን ሃሳብ አንስቶ በመሞገት ቤተክርስቲያን ሚዲያን ዋነኛው የወንጌል ማዳረሻ መንገድ አድርጋ ልትጠቀም ይገባል ይላል። እንደ ወንድም ዘሪሁን ገለጻ ይህ ዋናኛ መንገድ መሆን አለብት እንጂ ብቻኛ መንገድ እንዳልሆነም ይጠቅሳል። በዮሐንስ ግርማ ሙሉ ቃለ መጠይቁን ለመመልከት ሊንኩን ይጠቀሙ። https://www.youtube.com/watch?v=1QXLIbaoR5c

Открыть в Telegram
Просмотры434−31%к среднему
Пересылки—
Реакции5
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
9 ч197
29 ч434
  1. Через 24 часа434
  2. Всего сейчас434
#4844Фото

#ሰበር #ዜና መካነ ኢየሱስ አዲስ ፕሬዝደንት መረጠች። 22ኛው የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ዓብይ ጉባኤ ለሚቀጥሉት አራት ዓመታት ቤተ ክርስቲያኒቱን የሚመሩ መሪዎችን መርጧል። «በፍቅር የጸና መሠረት» (ኤፌሶን 3፥17) በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ 22ኛው ዓብይ ጉባኤ፣ ለሚቀጥሉት አራት ዓመታት ቤተ ክርስቲያኒቱን በታማኝነትና በትሕትና የሚያገለግሉ መሪዎችን በፀሎት መርጧል። በዚሁ መሠረት፦​ 1. ቄስ ዶ/ር ለሊሳ ዳንኤል — የቤተ ክርስቲያኒቱ ፕሬዚዳንት፤​ 2. ቄስ ዶ/ር ታሪኩ ቶሎሳ — የቤተ ክርስቲያኒቱ ምክትል ፕሬዚዳንት፤​ 3. አቶ መላኩ አመኑ — የቤተ ክርስቲያኒቱ ዓቃቤ ንዋይ​ በመሆን ለቀጣዮቹ አራት ዓመታት ቤተ ክርስቲያኒቱን በመሪነት የሚያገለግሉ ይሆናል።​ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ለተመረጡት አዳዲስ መሪዎች መልካም ምኞቷን እየገለጸች ለአገልግሎታቸው ስኬት ትጸልያለች! The Christian News - የክርስቲያን ዜና የክርስቲያን ዜና ለተመረጡ አዳዲስ አመራሮች መልካም የአገልግሎት ዘመን እንዲሆን ይመኛል።

Открыть в Telegram
Просмотры454−28%к среднему
Пересылки—
Реакции12
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
10 ч319
25 ч454
  1. Через 24 часа454
  2. Всего сейчас454
#4843Фото

"ሙስናን መከላከልና መታገል የመንግሥትና የተወሰኑ ተቋማት ተግባር ብቻ አይደለም" መጋቢ ታምራት አበጋዝ የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ጽሀፊ መጋቢ ታምራት አበጋዝ ይህንን ያሉት በዛሬው እለት በይፋ መከበር በጀመረው አለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን ምክንያት በማድረግ ከሃይማኖት አባቶች ጋር በተደረገው ምክክር መድረክ ላይ ነው። የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከአዲስ አበባ ከተማ ስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ጋር በመሆን ከሃይማኖት መሪዎች ጋር የፀረ-ሙስና ቀንን ምክንያት በማድረግ ምክክር አድርገዋል። በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ጽሀፊ መጋቢ ታምራት አበጋዝ ሙስናን መከላከልና መታገል የመንግሥትና የተወሰኑ ተቋማት ተግባር ብቻ ሳይሆን፣ የሁሉም ዜጎች፣ ማለትም የሃይማኖት ተቋማት የሲቪል ማኅበራትና፣ የሙያ ተቋማት በአጠቃላይ የማህበሰረሰብ የጋራ ኃላፊነት ሊሆን ይገባል ብለዋል። መጋቢ ታምራት አበጋዝ አክለው የሃይማኖት ተቋማት የሥርዓተ የአምልኮ ማካሄጃ ማዕከላት ብቻ ሳይሆኑ፣ የሥነ-ምግባርና የሞራል እሴት መገንቢያ፣ ማኅበራዊ ኃላፊነትና መልካም እሴቶች የሚጎለብቱባቸው ተቋማት መሆናቸውን ጠቅሰው ሙስናን ለመከላከል ጠንካራ መንፈሳዊና ሞራላዊ መሠረት የሆኑትን ሃይማኖቶች ሐቀኝነትን፣ ታማኝነትን፣ ፍትሕን፣ ትሕትናን፣ ለሌሎች የመጠንቀቅ ኃላፊነትን አበክረው ሊያስተምሩ እንደሚገባ ተናግረዋል። የአዲስ አበባ ከተማ ስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀማል ረዲ ሙስና የሀገርን ሀብት ከማባከኑም በላይ የሕግ የበላይነትን፣ የፍትሕ ሥርዓትንና የሕዝብን እምነት የሚሸረሽር አደገኛ ወንጀል በመሆኑ የሃይማኖት አባቶች በቁርጠኝነት ሊታገሉት እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።

Открыть в Telegram
Просмотры460−27%к среднему
Пересылки—
Реакции5
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
16 ч410
26 ч460
  1. Через 24 часа460
  2. Всего сейчас460
#4842Фото

GTA 6 የዲጂታል መዝናኛ ወይስ የሥነ ምግባር ፈተና? አንድ ጨዋታ በሰዓታት ውስጥ በቢሊዮን ዶላር ገቢ ሊያስገኝ ይችላል። በዓለም ዙሪያ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችንም ትኩረት ሊስብ ይችላል። ግን አንድ ጥያቄ ላንሳ እነዚህ ጨዋታዎች በወጣቶች አስተሳሰብ፣ ባህሪና የሥነ ምግባር እሴት ላይ ምን ተጽዕኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ? ይህ ጥያቄ በአሁኑ ወቅት ከዓለም አቀፉ የቪዲዮ ጌም ኢንዱስትሪ ትልቁ የውይይት ርዕስ ከሆነው Grand Theft Auto 6 ጋር ተያይዞ ተነስቷል። የብሪታኒያዊው ጋዜጠኛና ተንታኝ Peter Hitchens በኖቬምበር 20 በDaily Mail ላይ ባሳተመው የአስተያየት ጽሑፍ GTA 6ን ከባድ ትችት አቅርቦበታል። Hitchens ጨዋታውን ከሥነ ምግባርና ከክርስቲያናዊ ሥልጣኔ አንጻር በመመልከት፣ በጨዋታው ውስጥ የሚታዩ የወንጀል፣ የጥቃትና የሌሎች አጥፊ ድርጊቶች ይዘቶችን ተችቷል። በዚህም ተነስቶ ጨዋታውን "Electronic Poison" ሲል ገልጾታል፤ የ2,000 ዓመታት የክርስቲያናዊ ሥልጣኔን ያዳክማል የሚል ከባድ ትችትም አቅርቧል። የአሜሪካው ESRB የጨዋታዎች የዕድሜ ምደባ ተቋም GTA 6ን ለ17 ዓመት እና ከዚያ በላይ ብሎ መድቦታል። የምደባው ምክንያቶችም ከባድ ጥቃት፣ ደምና ግፍ፣ ወሲባዊ ይዘት፣ እርቃን፣ ጸያፍ ቋንቋ፣ አደንዛዥ ዕፅና አልኮልን ያካትታሉ። ይህም ወላጆች የልጆቻቸውን የዲጂታል መዝናኛ ምርጫ በጥንቃቄ እንዲከታተሉ የሚያሳስብ ነው። ወጣቶች ሆይ፤ ዛሬ በስልካችንና በኮምፒውተራችን ላይ የምናየውና የምንጫወተው ነገር የመዝናኛ ጉዳይ ብቻ አይደለም። ለማሰብ፣ ለመማርና ለመዝናናት የምናሳልፈው ጊዜ የሕይወታችን አካል ነው። ስለዚህ ራሳችሁን ጠይቁ፤ የምመለከተው ይዘት ምን እያስተማረኝ ነው?

Открыть в Telegram
Просмотры411−35%к среднему
Пересылки—
Реакции9
Комментарии—
#4841Фото

በኬንያ የቤተክርስቲያናት የአምልኮ አገልግሎትን በቀጥታ ማሰራጨት እንዲገደብ የተደረገው ጥረት በሃይማኖት መሪዎች ዘንድ ተቃውሞ አስነሳ። የቤተክርስቲያን መሪዎች እርምጃውን አድሎአዊና በአምልኮ ነፃነት ላይ ጫና የሚፈጥር በማለት ተቃውመዋል። በኬንያ የመረጃ ጥበቃ ኮሚሽነር የነበሩት ኢማኩሌት ካሳይት፣ ቤተክርስቲያናት የምእመናንን ምስልና ድምፅ በቀጥታ ከማሰራጨታቸው ወይም ቪዲዮና ፎቶዎችን በኢንተርኔት ከመልቀቃቸው በፊት ግልጽ ፈቃድ ማግኘት እንዳለባቸው ማሳሰባቸው ውዝግቡን አስነስቷል። የኬንያ የቤተክርስቲያንና ቀሳውስት ማኅበር ሊቀመንበር ኤጲስ ቆጶስ ሁድሰን ንዴዳ፣ ኮሚሽኑ ቤተክርስቲያናትን ብቻ ለምን እንደለየ ጠይቀዋል። ፖለቲከኞችም ሰልፎቻቸውን በቀጥታ እያሰራጩ ሳለ የሃይማኖት ተቋማት ብቻ ላይ ገደብ መጣሉ አድሎአዊ ነው ብለዋል። በተጨማሪም ቤተክርስቲያናት ይህንን መመሪያ ካልተከተሉ እስከ 5 ሚሊዮን የኬንያ ሺሊንግ ቅጣት ሊጣልባቸው እንደሚችል ተገልጿል። የሃይማኖት ባለሙያዎች ማኅበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኤዝቅኤል ሙኤንዶ በበኩላቸው፣ መመሪያው በተለይ ትናንሽ የሃይማኖት ተቋማትን ሊጎዳ እንደሚችል ገልጸዋል። ማኅበሩም በመንግሥት አካልና በሃይማኖት ተቋማት መካከል ውይይት እንዲደረግ ጠይቋል። መፍትሔ ካልተገኘም ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ለማቅረብ እንደሚያስቡ አስታውቋል። ይህ ጉዳይ በዘመናዊው ዓለም የወንጌል ስርጭትን ማስፋፋትና የምእመናንን የግል መብት መጠበቅ እንዴት ሊጣጣሙ ይችላሉ? የሚለውን ትልቅ ጥያቄ አስነስቷል። ለማንኛውም ይህ ነገር መቼም በኢትዮጵያ እንዴት እንደተስፋፋ ግልፅ ነዉ ? ሕጉን እንዴት አያችሁት ኢትዮጵያ ቢመጣ አዋጭ ይመስላችኋል ? ሃሳባችሁን አጋሩን 🙏 በዮሐንስ ግርማ

Открыть в Telegram
Просмотры513−19%к среднему
Пересылки—
Реакции5
Комментарии—
#4840Фото

በኮንጎ የኢቦላ ወረርሽኝን ለመከላከል ክርስቲያን አገልጋዮች የጤና ባለሙያዎችን እየደገፉ ነው። በዲሞክራቲክ ኮንጎ እየተስፋፋ ያለውን የኢቦላ ወረርሽኝ ለመቆጣጠር ክርስቲያን አገልጋዮችና የሃይማኖት መሪዎች በቤት ለቤት የግንዛቤ ሥራ ከጤና ባለሙያዎች ጋር እየተባበሩ እንደሚገኙ ተዘገበ። የReligion News Service እንደዘገበው፣ በአገሪቱ ምሥራቃዊ ክፍል በተለይም በሰሜን ኪቩ ግዛት በቤኒ ከተማ የሚገኙ ክርስቲያን አገልጋዮች ስለ በሽታው ትክክለኛ መረጃ ለማኅበረሰቡ በማድረስ ላይ ናቸው። በአካባቢው የአንግሊካን ቤተክርስቲያን አገልጋይ ፓትሪክ ሎኮምቤ እንደገለጹት፣ አንዳንድ ማኅበረሰቦች በጤና ባለሙያዎች ላይ እምነት በማጣታቸው ወደ ሕክምና ተቋማት ለመሄድ ፈቃደኛ አልነበሩም። በዚህም ምክንያት የእምነት መሪዎች ወደ ማኅበረሰቡ በመግባት ስለ በሽታው ስርጭት፣ መከላከያ ዘዴዎችና የሕክምና አስፈላጊነት ማብራሪያ እየሰጡ ነው። የአንግሊካን የጎማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ማርቲን ጎርደን በበኩላቸው፣ ማኅበረሰቡ የቤተክርስቲያን መሪዎችን ስለሚያምን ትክክለኛ መረጃን በእነርሱ በኩል ማድረስ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል። የዓለም ጤና ድርጅት እ.ኤ.አ. ኖቬምበር 20 ባወጣው መረጃ መሠረት፣ እስከ ኖቬምበር 17 ድረስ በኮንጎ 11,613 የተረጋገጡ የኢቦላ ተጠቂዎችና 5,678 ሞት ተመዝግቧል። ወረርሽኙም በስምንት ክልሎች ወደሚገኙ 68 የጤና ዞኖች መዳረሱን ድርጅቱ ገልጿል። የግጭት ሁኔታዎች፣ የሕዝብ መፈናቀልና የጤና ተቋማት እጥረት የወረርሽኙን ቁጥጥር እያወሳሰቡት መሆኑም ተጠቁሟል። ምንጭ፦ Religion News Service፣ World Health Organization በዮሐንስ ግርማ

Открыть в Telegram
Просмотры542−14%к среднему
Пересылки—
Реакции7
Комментарии—
#4838Фото

"ሚድያ እና የኢትዮጵያ ቤተክስርቲያን" የሚል ርዕስ ያለው አዲሱን መጽሐፉን አስመልክቶ ዛሬ ለሚዲያዎች ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰቷል። በፍሬንድሽፕ ሆቴል በነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ የአዲሱን የመጽሐፉ ይዘትና ዓላማ፣ የምረቃው ቀንና ቦታ እንዲሁም አንባቢዎች መጽሐፉን የሚያገኙበት መንገድ በዝርዝር የተገለጸ ሲሆን በምርቃት መረሃ ግብሩ ቀን ሚዲያን በትክክለኛው መንገድ ጥቅም ላይ ስናውል ለቤተክርስቲያንና ለማኅበረሰብ ሊያበረክተው የሚችለውን አስተዋጽኦ፣ እንዲሁም ያለ ኃላፊነት ሲጠቀሙበት ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት ለውይይት እንደሚያቀርብ ተገልጿል። "ሚዲያ እና የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን" የተሰኘው ይህ አዲስ መጽሀፍ ታሪካዊ ሂደትን እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መመሪያዎችን እንዲሁም ተያያዥ የሕግ ማዕቀፎችን የያዘ እንደሆነ የመጽሀፉ አዘጋጅ ወንድም ዘሪሁን ግርማ በመግለጫው ላይ ተናግሯል። የመጽሀፉን አሁናዊ ጠቀሜታ በተመለክተ ንግግር ያደረገችው የሚዲያ ባለሞያ እና አገልጋይ እህት ትዕግስት እጅጉ በበኩሏ የመጽሀፉ ዋና ዓላማ "የዘርፉን ተሞክሮ ለትውልድ በጽሁፍ ማስተላለፍ" ነው ብላለች። እንደ እህት ትዕግስት ገለጻ ከሆነ በሚዲያ ስራ ላይ የሚገጥሙን ውሳኔዎችን በቡድን ለመመርመር መጽሀፉ ጉልህ ጠቀሜታ ያለው ነው ስትል ገልጻዋለች። የአባቶቻችሁን ታሪክ እንድታውቁ እድል የሚሰጥ መጽሐፍ ነው ያሉት ደግሞ አርቲስት እና አገልጋይ የሆኑት እንዲሁም በሚዲያ ረዥም ዓመት ልምድ ያላቸው አርቲስት ሽዋፈራው ደሳለኝ ናቸው። አንጋፋዎች የሰሩትን እና ያዩትን እንዲያካፍሉ ወጣቶችም ዛሬ ያላቸውን ቴክኖሎጂ እና እውቀት ከቀደመው ተሞክሮ ጋር እንዲያገናኙ መልካም አጋጣሚ የሚፈጥር ነው ያለችው ደግሞ አርቲስት ሀረገወይን አሰፋ ነች። ተጨማሪ ዝርዝር ከፌስቡክ ገጻችን ያንብቡ ! https://web.facebook.com/share/p/1TqY

Открыть в Telegram
Просмотры604−4%к среднему
Пересылки—
Реакции5
Комментарии—
#4837Видео
Просмотры585−7%к среднему
Пересылки—
Реакции3
Комментарии—
#4836Превью ссылки
Просмотры624−1%к среднему
Пересылки—
Реакции5
Комментарии—
#4835Фото
Просмотры1 020+62%к среднему
Пересылки—
Реакции17
Комментарии—
#4834Фото

በፍቅር የጸና መሰረት - መካነ ኢየሱስ 22ኛ ዓብይ ጉባኤ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ 22ኛ አብይ ጉባኤ ማካሄድ ጀመረች። ከ700 በላይ መሪዎች ከመላው ኢትዮጵያና ውጪ አገራት በተሰባሰቡበት ጉባኤ "በፍቅር የጸና መሰረት" በሚል መሪ ቃል እየታካሄደ የሚገኝ ሲሆን ጥሪ የተደረገላቸው የአብያተ ክርስቲያናት መሪዎች እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችን ጨምሮ ከፍተኛ የቤተክርስቲያኒቱ አመራሮች የተገኙ ሲሆን መሪዎች ቤተክርስቲያን ባለፉት ከ100 ዓመታት በላይ በተሻገረው የሁለንተናዊ አገልግሎቷ እውቅና በመስጠት አመስግነዋል። የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝደንት እና የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ተስፋስላሴ ታደሰ በመድረኩ ተገኝተው ጉባኤው ለወንጌል መስፋት ተጨማሪ እቅድ የሚወጣበት እንዲሆን ተመኝተው በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ምክንያት ሀገራችን ተባርካለች ሁላችንንም የሚሰበስበንን ወንጌል ስታደርሱ ቆይታችኋል ይህ እንዲቀጥል መልካም ምኞታቸውን አቅርበዋል። ዛሬ በሀገራችን እና በሌሎች አለም የሚገኙ በርካታ ምሁራንን በማፍራት ሂደት ውስጥ የመካነ ኢየሱስ ቤ/ክ ከፍተኛ ድረሻ ነበራት ያሉት ደግሞ የቀድሞ የፌዴራል የሕግና ፍትሕ ኢንስቲትዩትን ዋና ዳይሬክተር እና በአሁኑ ሰዓት የኦሮሞ መጽሀፍ ቅዱስ ማህበር ፕሬዝደንት ክቡር አምባሳደር አቶ ደግፌ ቡላ ናቸው። ሙሉ ዜናውን ፌስቡክ ላይ ያንብቡት : https://web.facebook.com/share/p/16XqCJGPKpG/

Открыть в Telegram
Просмотры683+8%к среднему
Пересылки—
Реакции5
Комментарии—
#4832Фото

#አዲስ #መረጃ አለን የሀገሪቱ ዋና መውጫና መግቢያ መንገድ ላይ እንደመገኘቷ በእዛጋ ያለፉ ሁሉ፤ በእግርም ሆነ በመኪና ለጉዳይም ሆነ ለወክ በበሯ የመጡ ሁሉ i belong to Jesus (እኔ የኢየሱስ ነኝ) የሚለውን ታፔላ በትልቁ አይተውታል። እግር ጥሏቸውም ሆነ አስበውበት ሊካፈሉ የመጡ ሁሉ ከመደርኩ በሚለቀቀው የእግዚአብሔር ቃል ትምህርት ፣ በወንጌሉ ቃል ድነዋል፣ ተባርከዋል ፣ተፅናንተዋል፣ ተጠቅመዋል ህይወታቸው ተቀይሯል። መሀል ቦሌ የምትገኘው ዮጎ ሲቲ ቤተክርስቲያን። ይህች ከሁለት አስርት አመታት በላይ ቦሌ ላይ የወንጌላውያን አማኞች ምልክት ሆና የቆየች ታላቅ ቤተክርስቲያን አሁን ደግሞ ጌታ ፈቅዶ አካባቢውን የሚመጥን ህንፃ ቤተክርስቲያን ለመስራት ግንባታ በቅርቡ ትጀምራለች። አገልግሎቱም ከህዳር 27 ጀምሮ እዛው ቦሌ ብርሃኔ አደሬ ህንፃ ጀርባ ወዳለው ጉዲና ቱምሳ ማዕከል እንደሚዛወር ተሰምቷል። የቤተክርስቲያኒቷ ስራ ተጀምሮ እስከሚያልቅ በፀሎት ፣ በገንዘብ ፣ በጉልበት ጌታ በሰጠን ነገር ሁሉ በማገዝ እዚህ ቦታ ላይ ታሪካዊ ህንፃ ቤተክርስቲያን ለማቆም መረባረብ ከሁላችን አማኞች ይጠበቃል...

Открыть в Telegram
Просмотры1 110+76%к среднему
Пересылки—
Реакции11
Комментарии—
#4831Фото
Просмотры658+4%к среднему
Пересылки—
Реакции6
Комментарии—
#4830Превью ссылки
Просмотры774+23%к среднему
Пересылки—
Реакции9
Комментарии—
#4829Фото

ከ500 ዓመታት በፊት በ1526 ዓ.ም የመጀመሪያው የአዲስ ኪዳን በስዊድንኛ ታትሞ ለሕዝብ ቀርቦ ነበር። ይህ ታሪካዊ ክስተት መጽሐፍ ቅዱስ በሕዝቡ የሚነገር ቋንቋ እንዲነበብ ያደረገ ትልቅ ለውጥ ነበር። አሁን ይህንን 500ኛ ዓመት ለማክበር የስዊድን መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር NT 2026 የተሰኘ አዲስ የአዲስ ኪዳን ትርጉም አዘጋጅቶ አስተዋውቋል። ትርጉሙ ከጥንታዊው የግሪክ ጽሑፍ በቀጥታ የተዘጋጀ ሲሆን የዘመኑን የቋንቋ አጠቃቀምና የመጽሐፍ ቅዱስ ምርምር ውጤቶችን በማካተት ለዘመናዊ አንባቢዎች ተስማሚ እንዲሆን ተደርጓል። አዲሱ ትርጉም በሴፕቴምበር 24 በጎተንበርግ የመጽሐፍ አውደ ርዕይ ላይ ይፋ ሆኗል። ከዚያም በኖቬምበር 18 የስዊድን ቤተክርስቲያን አጠቃላይ ሲኖዶስ አዲሱ ትርጉም በቤተክርስቲያን አገልግሎቶች እንዲጠቀምበት በአንድነት ወስኗል። በተጨማሪም በመጪው እሑድ ኖቬምበር 29 የመጀመሪያ ቀን በመላው ስዊድን የቤተክርስቲያን አገልግሎት ለሚካፈሉ ሰዎች 200 ሺህ የአዲሱ ትርጉም ቅጂዎች እንዲሰራጭ ታቅዷል። ይህ የ500 ዓመት ታሪካዊ ክብረ በዓል የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም በሕዝብ ቋንቋ ለማድረስ ያለውን አስፈላጊነት የሚያሳይ ሲሆን፣ አዲሱ ትርጉም በስዊድን ያሉ ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስን በአዲስ መንገድ እንዲያነቡና እንዲያጠኑ የሚያበረታታ እርምጃ እንደሆነ ይጠበቃል። ምንጭ Church of Sweden ክርስቲያናዊ የቪዲዬ ዜናዎችን በቪዲዬ ለመመልከት ሊንኩን ይጠቀሙ 🙏🙏 https://www.youtube.com/watch?v=BP5Ys72uBhE

Открыть в Telegram
Просмотры756+20%к среднему
Пересылки—
Реакции7
Комментарии—
#4828Фото

የማንቸስተር ዩናይትድ ደጋፊዎች ለክለባቸው በቤተክርስቲያን ጸሎት አደረጉ። የእግር ኳስ ፍቅር አንዳንድ ጊዜ ከስታዲየም እና ከሜዳ ውጭም ይታያል። በኡጋንዳ የሚገኙ የማንቸስተር ዩናይትድ ደጋፊዎች ለክለባቸው የውጤት ችግር መፍትሔ በጸሎት ለመፈለግ ወደ ቤተክርስቲያን ተሰብስበዋል። የኡጋንዳ የማንቸስተር ዩናይትድ ደጋፊዎች በSt Mary Assumpta Catholic Parish በሚገኘው በRagem የተሰበሰቡ ሲሆን፣ ለክለባቸው የተሻለ ውጤት እንዲመጣ በጸሎት እና በመባ ስነ-ሥርዓት ተሳትፈዋል። ደጋፊዎቹ ይህን የጸሎት ስነ-ሥርዓት ያካሄዱት ማንቸስተር ዩናይትድ በዚህ የውድድር ዘመን እጅግ አስቸጋሪ የውጤት ሁኔታ ውስጥ በመግባቱ ነው። ክለቡ በፕሪሚየር ሊጉ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ከመገኘቱ በተጨማሪ፣ የአሰልጣኝ ለውጥም አድርጓል። ይህም ለደጋፊዎቹ አሳሳቢ ሁኔታ ፈጥሯል። የቤተክርስቲያኑ ካህን ፋዘር ኮልበርት አቾራ በዚህ አጋጣሚ የእግር ኳስ ፍቅር ሰላምን እና አንድነትን ለማሳደግ መጠቀም እንደሚገባ አስተላልፈዋል። ደጋፊዎች የሚደግፉት ቡድን የተለያየ ቢሆንም፣ በሰላም እና በመተባበር መኖር እንደሚገባ ገልጸዋል። በኡጋንዳ የተፈጸመው ይህ ድርጊት የእግር ኳስ፣ እምነት እና የሰዎች አንድነት እንዴት አብረው ሊኖሩ እንደሚችሉ የሚያሳይ አስገራሚ ምሳሌ ነው። በዮሐንስ ግርማ ለማንኛውም ዛሬ እሁድ ነው። የት ቤተክርስቲያን ሄዳችሁ ? ፕሮግራም እንዴት ነበር ? የክርስቲያን ዜናዎችን በቪዲዮ ለመመልክት የዩቲዩብ ሊንኩን ይጠቀሙ Youtube

Открыть в Telegram
Просмотры845+34%к среднему
Пересылки—
Реакции17
Комментарии—
#4827Фото

አብያተ ክርስቲያናት ቀይ ብረሃን ተሸፍነዋል። ይህ የሆነበት ምክንያት የክርስቲያኖች ስደትን ለማሳየት ቤተክርስቲያናትና ታሪካዊ ሕንፃዎች በቀይ ብርሃን ተሸፍነዋል። በዓለም የተለያዩ ከተሞች የሚገኙ ቤተክርስቲያናትና ታሪካዊ ሕንፃዎች የክርስቲያኖችን ስደት ለማሳየት በቀይ ብርሃን እየተደረጉ ነው። ይህ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚካሄደው Red Week ወይም ቀይ ሳምንት ዘመቻ ነው። ዘመቻው በAid to the Church in Need የተባለ የካቶሊክ ድርጅት የሚደገፍ ሲሆን፣ በዓለም የተለያዩ አገራት የሚኖሩ ክርስቲያኖች በሃይማኖታቸው ምክንያት የሚደርስባቸውን ጫና፣ ስደትና የሃይማኖት ነፃነት ጥሰት ለማሳየት ያለመ ነው። በዚህ ዘመቻ የተለያዩ ቤተክርስቲያናት፣ ታሪካዊ ሕንፃዎችና የሕዝብ መስህቦች በቀይ ብርሃን ይበራሉ። ቀይ ቀለም የስደት፣ የመስዋዕትነትና በእምነታቸው ምክንያት ሕይወታቸውን ያጡ ክርስቲያኖችን ለማስታወስ ይጠቀማል። በዚህ ዓመት ከኖቬምበር 18 እስከ 22 ድረስ በተለያዩ አገራት የጸሎት ስብሰባዎች፣ የምስክርነት መርሃ ግብሮችና የማስታወሻ ዝግጅቶች እየተካሄዱ ነው። በብራስልስ የአውሮፓ ፓርላማም የሃይማኖት ነፃነትን እና በእምነታቸው ምክንያት የሚጎዱ ክርስቲያኖችን ለማስታወስ ዝግጅት ተካሂዷል። የዘመቻው ዋና መልዕክት በሃይማኖት ምክንያት የሚፈጸም ግፍ በዓለም ላይ በትኩረት እንዲታይ እና ለተጎዱ ማህበረሰቦች ድጋፍ እንዲጠናከር ነው። በዮሐንስ ግርማ የክርስቲያን ዜናዎችን በቪዲዮ ለመመልክት የዩቲዩብ ሊንኩን ይጠቀሙ https://www.youtube.com/watch?v=BP5Ys72uBhE

Открыть в Telegram
Просмотры799+27%к среднему
Пересылки—
Реакции5
Комментарии—
#4826Фото
Просмотры769+22%к среднему
Пересылки—
Реакции4
Комментарии—