Кабинет

Посты канала ኦርቶዶክሳዊ ወጣትነትና ሥነምግባር

сначала новые

#21881Текст

Переслано из Quality Button Bot

💕ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይ ፈ ል ጋ ሉ ? 🔔 💕 [┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 💕 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 💕 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ [┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 💕 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ💕 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 💕 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 💕 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 💕 ዘማሪ አቤል መክብብ 💕 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 💕ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ💕 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 💕ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ💕 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 💕 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 💕 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 💕 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 💕 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ 🌷👥 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇 🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧

Открыть в Telegram
Просмотры12−98%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
2 ч5
4 ч9
6 ч12
  1. Через 1 час5
  2. Через 6 часов12
  3. Всего сейчас12
#21880Текст
Просмотры12−98%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
2 ч7
4 ч9
7 ч12
  1. Через 6 часов12
  2. Всего сейчас12
#21879Фото
Просмотры21−97%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
2 ч16
4 ч18
7 ч21
  1. Через 6 часов21
  2. Всего сейчас21
#21736Текст
Просмотры1 490+129%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#21557Фото
Просмотры3 790+482%к среднему
Пересылки—
Реакции10
Комментарии—
#20049Текст

✝ በጾም ወራት በጎነትን እንስራ፦ ለወንድማችን ኃይለኢየሱስ የእርዳታ ጥሪ "እኔ የመረጥሁት ጾም ይህ አይደለምን? ... እንጀራህን ለተራበ ትቆርስ ዘንድ፥ ስደተኞቹን ድሆች ወደ ቤትህ ታገባ ዘንድ፥ የተራቆተውንም ብታይ ታለብሰው ዘንድ፥ ከሥጋ ዘመድህ እንዳትሸሸግ አይደለምን?" (ኢሳይያስ 58፥6-7) ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች፣ እንደምን ሰነበታችሁ? የጾም ወራት የጸሎት ብቻ ሳይሆን፣ የተቸገረን ወንድም በማሰብ የምንባረክበት ወቅት ነው። ዛሬ አንድ ትልቅ የበረከት ዕድል ይዘንላችሁ መጥተናል። ወንድማችን ኃይለኢየሱስ ከባድ የጤና ፈተና አጋጥሞት፣ በፈጣሪ ቸርነት ከሦስት ተከታታይ ቀዶ ጥገናዎች በኋላ ለጤና በቅቷል። ነገር ግን የሕክምናው ሂደት የቤተሰቡንና የእርሱን አቅም ሙሉ በሙሉ አሟጥጦታል። ዛሬ ወንድማችን ትምህርቱን ለመቀጠል ዩኒቨርሲቲ ቢገባም፣ ለትምህርት መርጃ የሚሆን (ለኮፒና ለፕሪንት) አቅም አጥቶ ተቸግሯል። በአሁኑ ሰዓት በእጁ ላይ ያለው 100 ብር ብቻ ነው! ቅዱስ መጽሐፍ እንዲህ ይላል፦ "ለድሀ ቸርነትን የሚያደርግ ለእግዚአብሔር ያበድራል፥ ስጦታውንም ይመልስለታል።" (ምሳሌ 19፥17) ወንድማችን በትህትና ሆኖ "50 ብርም ቢሆን ትልቅ ነገር ነው" ብሎናል። እኛ ግን አሥር አሥር ብር ብናዋጣለትስ? ለእኛ 10 ብር ትንሽ ልትሆን ትችላለች፣ ለወንድማችን ግን ትምህርቱን እንዲቀጥልና ከጭንቀቱ እንዲላቀቅ ትልቅ ተስፋ ናት። 🙏 የምንረዳበት መንገድ፦ 🔹 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE)፦ 1000670545788 በዚህ ቅዱስ የጾም ወቅት፣ ስለ ቅድስት ኪዳነምህረት ስንል አቅማችን የፈቀደውን በመለገስና በጸሎት በማሰብ ከጎኑ እንቁም! እግዚአብሔር ለሁላችንም በረከቱን ይስጠን። "እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት።" (ማቴዎስ 25፥40)

Открыть в Telegram
Просмотры23 900×37к среднему
Пересылки—
Реакции55
Комментарии—
#19090Превью ссылки

#ጾመ_ነቢያት እግዚአብሔር አምላካችን ዓለምን ለማዳን ሲል የሰውን ሥጋ መልበሱን፣ ከእናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም ጋር ወደ ግብጽ ግብር መሰደዱን፣ በባሕረ ዮርዳኖስ መጠመቁን፣ በትምህርቱ ብርሃንነት ጨለማውን ዓለም ማብራቱን፣ ለሰው ልጆች ድኅነት ሲል ልዩ ልዩ ዓይነት መከራ መቀበሉን፣ መሰቀሉን፣ መሞቱን፣ ከሙታን ተለይቶ መነሣቱን፣ ማረጉንና ዳግም ለፍርድ የሚመጣ መኾኑን በአጠቃላይ የማዳን ሥራውን በየዘመናቱ የተነሡ ቅዱሳን ነቢያት በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው አስቀደመው በትንቢት ተናግረዋል፡፡ ትንቢቱ ተፈጽሞ ለመመልከትም ‹‹አንሥእ ኃይለከ ፈኑ እዴከ፤ ኃይልህን አንሣ፤ እጅህን ላክ›› እያሉ በጾም በጸሎት ተወስነው አምላክ ሰው ኾኖ ዓለምን የሚያድንበትን ጊዜ በቀናት፣ በሳምንታት፣ በወራትና በዓመታት እያሰሉ ሲጠባበቁ ቆይተዋል፡፡ የእግዚአብሔርን ሰው መኾን ሲጠባበቁ የኖሩት የነቢያት ትንቢትና ጸሎትም በእግዚአብሔር ሰው መኾን ፍጻሜ አግኝቷል፡፡ ይህን ምሥጢር በማሰብ በየዓመቱ ከኅዳር ፲፭ ቀን ጀምሮ እስከ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት ዋይዜማ ድረስ እንድንጾም አባቶቻችን መምህራነ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ሠርተውልናል፡፡ ይህ ጾም፣ ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ሲኾን፣ በስያሜም #ጾመ_ነቢያት (የነቢያት ጾም) እየተባለ ይጠራል፡፡ ወቅቱ ለአዳም የተነገረው የድኅት ተስፋ የተፈጸመበት ስለ ኾነም #ጾመ_አዳም (የአዳም ጾም) ይባላል፡፡ ስለ እግዚአብሔር ሰው መኾን በስፋት ትምህርተ ወንጌል የሚሰጥበት ወቅት በመኾኑም #ጾመ_ስብከት (የስብከት ጾም) የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ የጾሙ መጨረሻ (መፍቻ) በዓለ ልደት በመኾኑ ደግሞ #ጾመ_ልደት (የልደት ጾም) በመባል ይታወቃል፡፡ በተጨማሪም #ጾመ_ሐዋርያት እየተባለ ይጠራል፤ ምክንያቱም ቅዱሳን ሐዋርያት "በዓለ ትንሣኤን ዐቢይ ጾምን ጾመን እናከብረዋለን፤ በዓለ ልደትንስ ምን አድርገን እናከብረዋለን?" በማለት ነቢያት በጾሙበት ማለት ከልደተ ክርስቶስ በፊት ባለው ወቅት ጾመዋልና፡፡ በሌላ አጠራር ይኸው ጾመ ነቢያት #ጾመ_ፊልጶስ (የፊልጶስ ጾም) በመባል ይታወቃል፤ ሐዋርያው ቅዱስ ፊልጶስ በአፍራቅያ እና አውራጃዋ ዅሉ እየተዘዋወረ በጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ወንጌልን በማስተማር፣ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን በማድረግ ብዙዎችን ወደ አሚነ እግዚአብሔር ሲመልስ ቆይቶ ትምህርቱን በማይቀበሉ የአፍራቅያ ሰዎች አማካይነት በሰማዕትነት ዐርፏል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ሥጋውን ሊቀብሩ ሲሉም ተሰወረባቸው፡፡ በዚህ ጊዜ በዓት ዘግተው፣ ሱባዔ ገብተው፣ በጾም በጸሎት ተወስነው የሐዋርያውን ሥጋ ይመልስላቸው ዘንድ እግዚአብሔርን ቢለምኑት ልመናቸውን ተቀብሎ ሱባዔ በያዙ በ፫ኛው ቀን የቅዱስ ፊልጶስን ሥጋ (በድን) መልሶላቸው በክብር አሳርፈውታል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ የሐዋርያውን ሥጋ ካገኙ በኋላ እስከ ጌታችን ልደት ድረስ ጾመዋል፡፡ ስለዚህም ጾመ ነቢያት 'ጾመ ፊልጶስ' እየተባለ ይጠራል፡፡ ከዚሁ ዅሉ ጋርም ወልደ አምላክ ክርስቶስን በግብረ መንፈስ ቅዱስ እንደምትፀንሰው፣ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ካበሠራት በኋላ "ሰማይና ምድር የማይወስኑትን አምላክ ፀንሼ ምን ሠርቼ እወልደዋለሁ?" በማለት ጌታችንን ከመውለዷ አስቀድማ እመቤታችን ጾማዋለችና ይህ ጾም #ጾመ_ማርያም በመባልም ይታወቃል፡፡ በአጠቃላይ በዚህ በጾመ ነቢያት፣ ነቢያትም ሐዋርያትም፣ ቀደምት አባቶቻችንም ጾመው በረከት አግኝተውበታል፡፡ እኛ ምእመናንም የነቢያት፣ የሐዋርያት፣ የጻድቃንና የሰማዕታት አምላክ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ከቅዱሳን ነቢያትና ሐዋርያት በረከት እንዲያሳትፈን በዚህ በጾመ ነቢያት ወቅት በጾም በጸሎት ተወስነን እግዚአብሔርን ልንማጸነው ይገባናል፡፡       ጾሙን ጾመ ሥርየት፤ ጾመ መድኃኒት ያድርግል! ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE  https://t.me/Ortodokstewahido https://t.me/Ortodokstewahido https://t.me/Ortodokstewahido

Открыть в Telegram
Просмотры28 200×43к среднему
Пересылки—
Реакции46
Комментарии—
#19089Текст

🙏 ከአንዱ ወዳጄ🙏 መልክት 🥹 በቅርቡ ከባድ ቀዶ ጥገና ተደርጎለት ነበር። እግዚአብሔር ይመስገን አሁን ደህና ሆኗል፣ ክብር ለመድኃኔዓለም ይሁን! 🥹 ነገር ግን ይህ የጤና መታመም ከፍተኛ የገንዘብ ጫና ፈጥሮበታል። ቤተሰቦቹ ለህክምና ወጪዎች ሲሉ ያለውን ሁሉ አውጥተዋል፣ እሱም ምንም አልያዘም። በአሁኑ ወቅት አካውንቱ ላይ ያለው ገንዘብ 200 ብር ብቻ ነበር። 😢 አሁን ደግሞ ዩኒቨርሲቲ ገብቷል። የመጀመሪያ ሳምንት ለሚያስፈልገው ሰርተፍኬት ፕሪንት ለማድረግ ከነበረችው 200 ብር ላይ አውጥቶ አሁን 100 ብር ብቻ ነው የቀረው። እንደ ማንኛውም ተማሪ ፕሪንት እንኳ ማድረግ አልቻለም። "የሚል ካርድ" ስላልተሰጣቸው ቁርስና ምሳ ሳይበላ ቀርቷል። "ማርያምን ቁርስ እና ምሳ አልበላሁም ነበር" ሲል የደረሰበትን የረሃብ ስሜት ገልጿል። 😥 "ይህ ሁሉ የኃጢአቴ ውጤት ነው፣ እሄ ሲያንሰኝ ነውና ጸልዩልኝ" በማለት የመንፈስ ጭንቀቱንና ትህትናውን አሳይቷል። "ለሰው መድኃኒቱ ሰው ይባል የለ፣ አደራችሁን" በማለት ከእኛ እርዳታን ይፈልጋል። ቢያንስ ለመማሪያ ደብተር የሚሆን ገንዘብ እንኳ ቢገኝለት ትልቅ ነገር ነው። ወንድማችን "ማርያምን 50 ብር ቢሆን ለእኔ ትልቅ ነገር ነው!" ብሏል። የቻልነውን ያህል በጸሎትም ሆነ በገንዘብ እንርዳው። እያንዳንዱ ትንሽ እርዳታ ትልቅ ለውጥ ያመጣለታል። 🙏 የንግድ ባንክ አካውንት ቁጥሩ: 1000670545788 አግዙት፣ መልካምነት ያስከፍላል! -

Открыть в Telegram
Просмотры29 400×45к среднему
Пересылки—
Реакции40
Комментарии—
#18760Превью ссылки
Просмотры14 800×23к среднему
Пересылки—
Реакции11
Комментарии—
#18554Превью ссылки

“ክርስቲያን” ተብለህ መጠራትህ ዋስትና አይኾንህም፤ ዋስትና የሚኾንህ … በመንገድ ዳር ላይ ዘርን የሚዘሩ ሰዎች ምንም የሚያገኙት ጥቅም እንደ ሌለ ኹሉ፥ እኛም ለልጅነታችን የሚገባ’ ምግባር ከሌለን ክርስቲያኖች ተብለን ከመጠራት የምናገኘው በቁዔት የለም፡፡ ይህ እንዴት ይኾናል የምትለኝ ከኾነም የጌታችን ወንድም የተባለው ያዕቆብን ምስክር አድርጌ እነግርሃለሁ፡፡ እርሱ፡- “ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው” ብሎአልና (ያዕ.2፡17)፡፡ ስለዚህ ለእኛ (ለክርስቲያኖች) ምግባር መያዝ ግዴታ ነው፡፡ ምግባር ከሌለን ግን “ክርስቲያን” የሚለው ስም ለእኛ የሚፈይደው ምንም ነገር የለም፡፡ በዚህ ተደነቅህን? እንኪያስ ንገረኝ ! በዓውደ ውጊያ የማይሳተፍ፣ ለሚመግበው ንጉሥም የማይዋጋ ከኾነ አንድ ወታደር ወታደር ተብሎ ቢጠራ ምን ጥቅም አለው? ለንጉሡ ክብር የማይዋጋ ከኾነስ ወታደር ተብሎ ባይጠራ ይሻለዋል፡፡ ይህ ሰው በንጉሡ የሚመገብ ኾኖ እያለ፥ ነገር ግን ንጉሡ በጠላቱ ላይ ድል እንዲያደርግ የማይዋጋ ከኾነ እንዴት ከቅጣት ሊያመልጥ ይችላል? ንጉሡን ምሳሌ አድርጌ ልናገረው የፈለግሁትስ ምንድን ነው? ልለው የፈልገሁት እግዚአብሔር በትንሹ ስለ ገዛ ነፍሳችን እንድንጠነቀቅ (ምግባር መያዝ እንድንችል) ኃይል (ዓቅም) ሰጥቶናል ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ንስሐና ምጽዋት ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE   https://t.me/Ortodokstewahido https://t.me/Ortodokstewahido https://t.me/Ortodokstewahido

Открыть в Telegram
Просмотры19 200×29к среднему
Пересылки—
Реакции25
Комментарии—
#18499Превью ссылки

አዲስ ዓመት ከገቢረ ኀጢአት ሳይወጡ አዲስ ዓመት ሲመጣ መደሰት፣ ብዙ መብልና መጠጥ ማዘጋጀት፣ አዲስ ልብስም መልበስ ጥቅም የለውም፡፡ ነፍሳችን በኀጢአት እየተጨነቀች፣ ነፍሳችን ተርባና ተጠምታ ሳለ፣ የተዳደፈ የኀጢአት ልብስም ተጆቡና ሳለ አዲስ ዓመት ማክበር ለእኛ ምን ጥቅም ይሰጠናል? እንዲህ ከገቢረ ኀጢአት ሳይወጡ አዲስ ዓመትን ማክበር ማለት ለእኔ እንደ ልጆች የዕቃ ዕቃ ጨዋታ ነው፡፡ ክርስቶስ ከዚሁ ሥራ አውጥቶናል፡፡ ከሕፃንነት አዕምሮ ወደ ማወቅ አሸጋግሮናል፡፡ ከምድራውያን ለይቶ ከሰማያውያን ጋር ደባልቆናል፡፡ ስለዚህ “መልካሙን ሥራችሁን ዐይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ” እንደ ተባለ አፍአዊ ሳይኾን መንፈሳዊውን ብርሃን ልናበራ ይገባናል (ማቴ.5፡16)፤ በአዲሱ ዓመት፡፡ ይህም ብርሃን ተስፋ መንግሥተ ሰማያትን የሚያስገኝ ነው፡፡ ወዳጄ ሆይ! ቤቱ ቆሽሾ ሳለ ውጫዊ በሩን ብቻ ለማሽቀርቀር ለምን ትጨነቃለህ? ነፍስህ በኀጢአት ተዳድፋ ሳለ ሥጋህን ብቻ ለማስደሰት ለምን ትሮጣለህ? አስቀድመህ ቤቱን (ነፍስህን) ለማስዋብ አትሽቀዳደምምን? አስቀድመህ ለነፍስህ የምታስብ ከኾነ ከሰው እጅ ሳይኾን ከክርስቶስ እጅ ሹመት ሽልማት ትቀበላለህ፡፡ ኹል ጊዜ “የማደርገው ነገር እግዚአብሔር ይከብርበታልን?” ብለህ አስብ እንጂ እንዲሁ በዘልማድ የምትመላለስ አትኹን ብዬ እመክርኻለሁ፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ሲመክረን፡- “እንግዲህ የምትበሉ ወይም የምትጠጡ ብትኾኑ ወይም ማናቸውም ነገር ብታደርጉ ኹሉን ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት” ያለንም ስለዚሁ ነውና በአዲሱ ዓመት በድርጊቶቻችን ኹሉ እግዚአብሔርን ለማክበር እንዘጋጅ (1ኛ ቆሮ.10፡31)፤ አዲስ ዓመት ማክበር ማለት ይኼ ነውና፡፡ #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ (ሰማዕትነት አያምልጣችሁ መጽሐፍ - #ገብረ_እግዚአብሔር_ኪደ) ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE      https://t.me/Ortodokstewahido https://t.me/Ortodokstewahido https://t.me/Ortodokstewahido

Открыть в Telegram
Просмотры10 300×16к среднему
Пересылки—
Реакции11
Комментарии—
#18480Превью ссылки

#ጳጉሜን የጳጉሜን ወር ዕለተ ምጽአት የሚታሰብበትም ወር ነው በቅድስት ቤተክርስቲያን ካሉት ሁለት የፈቃድ አጽዋማት መካከል አንዱ በዚህ በጳጉሜ ወር የምንጾመው የፈቃድ ጾም ነው፡፡ ጳጉሜን ማለት ጭማሪ ማለት ነው፡፡ ይህም በዓመቱ መጨረሻ ላይ አምስት ወይም ስድስት ቀን በመሆን የምትመጣ ናት፡፡ በአራት ዓመት አንዴ ማለትም በዘመነ ሉቃስ ጳጉሜን ስድስት ቀን ይሆናል፡፡ በዚህም ሐገራችን ኢትዮጵያ የአስራ ሦስት ወራት ጸጋ /Thirteen months of sunshine/ በመባል ትታወቃች ትለያለች፡፡ ጳጉሜን በዘመነ ዮሐንስ መግቢያ በዘመነ ሉቃስ ማብቂያ  ስድስት በምትሆንበት ጊዜ ጾመ ነቢያት /የገና ጾም/ ህዳር 15 ቀን ይገባና ታህሳስ 28 ቀን ጾሙ ተፈቶ የልደት በዓል ይከበራል፡፡ በቅድስት ቤተክርስቲያን ካሉት ሁለት የፈቃድ አጽዋማት መካከል አንዱ በዚህ በጳጉሜን ወር የምንጾመው የፈቃድ ጾም ነው፡፡ ይህም ጾመ ዮዲት በመባል ይታወቃል፡፡ ይህ ግን እንደ አንደኛው የፈቃድ ጾም /ጽጌ ጾም/ በብዙዋኑ ዘንድ የታወቀ አይደለም፡፡ የዮዲት ጾም የሚባለውም እርሷ ስለ ጾመችው ነው፡፡ እዚህ ላይ ዮዲት ተብላ የተጠቀሰችው በቤተክርስቲያን ታሪክ ትምህርት ላይ በጥፋት ሥራዋ በተደጋጋሚ የምትጠቀሰው ዮዲት ጉዲት እንዳልሆነች ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡ ወደ ታሪኩ ስንመለስ የፋርስ ንጉስ ናቡከደነጾር በሠራዊቱ ተመክቶ ሹም ጠላት አጥፋ ድንበር አስፋ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበልህ ያላመነውን እያሳመንህ ና ብሎ ለጦር አበጋዙ ለሆሎፎርኒስ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ ዮዲ 2፥2-7፡፡ እርሱም እንደታዘዘው በኃይላቸው የታመኑ 12ሺህ እግረኞችንና በፈረስ የተቀመጡ 12ሺህ ጦረኞችን እየመራ ዘምቶ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበለ ያላመነውን እያሳመነ ብዙ ሀገሮችን እያጠፋ ሲሔድ ከአይሁድ ከተማ ደረሰ በዚህም ብዙ ጥፋ በመድረሱ የእስራኤል ልጆች አለቀሱ፡፡ ዮዲት ባሏ ሞቶባት ከወንድ ርቃ ንጽሕናዋን ጠብቃ በጾም በቀኖና በሀዘን ተወስና ትኖራለች በተፈጠረው ጥፋት ህዝቡ ላይ ለመጣው መከራ ማቅ ለብሳ በራስዋ ላይ ትብያ ነስንሳ ወደ እግዚአብሔር አለቀሰች፡፡ የፍጥረቱን ጥፋት የማይሻ እግዚአብሔር አምላክም ሕዝቡን የሚያድኑበትን መንገድ ለመጠየቅ ሱባኤ በገባች በሦስተኛው ቀን ገለፀላት፡፡ ዮዲ 8፥2፡፡ ከዚህ በኋላ ጠላታቸውን በዮዲት ምክንያት እስራኤላውያን እስከ ዮርዳኖስ እየተከተሉ አጥፍተዋቸዋል፡፡ ዮዲት ጠላቷን ለማጥፋት የቻለችው በጾምና በጸሎት ከእግዚአብሔር አምላክ ኃይል አግኝታ ነው፡፡ ስለዚህ ምዕመናን ጥንተ ጠላታችን ሰይጣንን ፈቃደ ሥጋን ለማሸነፍ በጾም ከፈጣሪያችን ኃይልን መጎናጸፍ አለብን ብለው ጳጉሜን በፈቃድ ይጾማሉ፡፡ የጳጉሜን ወር ዕለተ ምጽአት የሚታሰብበትም ወር ነው፡፡ ይህም ጳጉሜ የዓመታት መሸጋገሪያ ጨለማው የክረምት ወቅት ወደ ማብቂያው የምናልፍባት እንደሆነች ሁሉ ምጽአትም ከጊዜያዊው ወደ ዘላለማዊ ከምድራዊ ወደ ሰማያዊ ከዚህ ዓለም ወደ ወዲያኛው መሸጋገሪያ ነውና ነው፡፡ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇    https://t.me/Ortodokstewahido https://t.me/Ortodokstewahido https://t.me/Ortodokstewahido

Открыть в Telegram
Просмотры9 440×14к среднему
Пересылки—
Реакции11
Комментарии—
#18366Превью ссылки

#ነሐሴ_16 #ዕርገተ_ማርያም ነሐሴ ዐሥራ ስድስት በዚህች ቀን አምላክን የወለደች የእመቤታችን ድንግል ማርያም ሥጋዋ ወደ ሰማይ ያረገበት መታሰቢያዋ ሆነ። ከዕረፍቷም በኋላ ከእርሳቸው ስለመለየቷ ሐዋርያት ፈጽሞ እያዘኑ ነበር። ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ተገለጠላቸው እርሷን በሥጋ ያዩ ዘንድ እንዳላቸውም ተስፋ ሰጣቸው። ወንጌላዊ ዮሐንስም እስያ በሚባል አገር እያስተማረ ሳለ በነሐሴ ወር ዐሥራ ስድስተኛ ቀን ተድላ ደስታ ወደአለባት ገነት በመንፈስ ቅዱስ ተነጠቀ። የክብር ባለቤት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን የእመቤታችን ማርያም ሥጋዋ ካለበት ከዕፀ ሕይወት ሥር ተቀምጦ አየው። የንጽሕት እናቱንም ሥጋ ታወጣ ዘንድ ምድርን እንዲጠሩዋት ሰባቱን የመላእክት አለቆች አዘዛቸው። እነርሱም የንጽሕት እናቱን ሥጋ ታወጪ ዘንድ እግዚአብሔር አዞሻል አሏት። ያን ጊዜም ከዕፀ ሕይወት በታች ካለ መቃብር የእመቤታችን ማርያም ሥጋዋ ወጣ። የክብር ባለቤት ጌታችንም እንዲህ እያለ አረጋጋት የተወደድሽ የወለድሽኝ እናቴ ሆይ ዘላለማዊ ወደ ሆነ መንግሥተ ሰማያት አሳርግሽ ዘንድ ነዪ። ያን ጊዜም በገነት ያሉ ዕፀዋት ሁሉም አዘነበሉ መላእክት የመላእክት አለቆች ጻድቃን ሰማዕታትም እየሰገዱላትና ፈጽሞ እያመሰገኗት አሳረጓት። አባቷ ዳዊትም ንግሥት እመቤታችን ወርቀ ዘቦ ለብሳ ደርባ ደራርባ በቀኝህ ትቀመጣለች እያለ በበገና አመሰገናት። በኪሩቤል ሠረገላ ተቀምጣ ከዐረገች በኋላ በልጁዋና በፈጣሪዋ ቀኝ በታላቅ ክብር ተቀመጠች። ወንጌላዊ ዮሐንስም ከእርሷ በረከትን ተቀብሎ ሰግዶላት ተመልሶ ከሰማይ ወረደ ሐዋርያትን ተሰብስበው ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋ ፈጽሞ ሲያዝኑና ሲተክዙ አገኛቸው። እርሱም እንደ አየ እንደ ሰማ ሥጋዋንም በታላቅ ክብር በምስጋና እንደ አሳረጓት ነገራቸው። ሐዋርያትም በሰሙ ጊዜ ዮሐንስ እንዳየና እንደሰማ ባለማየታቸውና ባለመስማታቸው እጅግ አዘኑ። ከዚህም በኋላ እያዘኑ ሳሉ እነሆ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገለጠላቸውና የፍቅር አንድነት ልጆች ሰላም ይሁንላችሁ ስለ እናቴ ማርያም ሥጋ ለምን ታዝናላችሁ። እነሆ እኔ እርሷን በሥጋ ላሳያችሁ ልባችሁም ደስ ሊለው ይገባዋል አላቸው ይህንንም ብሎ ከእርሳትው ዘንድ ወደ ሰማያት ዐረገ። ሐዋርያትም ዓመት ሙሉ ቆዩ የነሐሴም ወር በባተ ቀን ለሐዋርያት ዮሐንስ እንዲህ አላቸው አምላክን የወለደች የእመቤታችንን ሥጋዋን ለማየት የተዘጋጀን አድርጎ ያሰየን ዘንድ ኑ ይህን ሁለት ሱባዔ በመጾም የክብር ባለቤት ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን እንለምነው በልጅዋ በወዳጅዋ ቀኝ ተቀምጣ አይተን በእርሷ ደስ እንዲለን። በዚያን ጊዜም ዮሐንስ እንዳላቸው በጾም በጸሎት ሱባዔ ያዙ የነሐሴ ወር እንደ ዛሬ ዐሥራ ስድስተኛ ቀን በሆነ ጊዜ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉንም ሐዋርያት ወደ ሰማይ አወጣቸው። በታላቅ ክብር በተወደደ ልጅዋ ቀኝ ተቀምጣ ከሥጋዋ ተዋሕዳ ተነሥታ እመቤታችን ማርያምን አዩዋት። እጆቿንም ዘርግታ የከበሩ ሐዋርያትን እያንዳንዳቸውን ባረከቻቸው በልባቸውም እጅግ ደስ አላቸው። የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በከበረ ሥጋውና ደሙ ላይ ሠራዒ ካህን ሆነ። እስጢፋኖስም አዘጋጀ ዮሐንስም በመፍራት ቁሙ አለ። ሁሉም ሐዋርያት በመሠዊያው ዙሪያ ቆሙ በዚያን ጊዜ ከቶ እንደርሱ ሆኖ የማያውቅ ታላቅ ደስታ ሆነ። ጌታችንም የቅዳሴውን ሥርዓት በፈጸመ ጊዜ ሥጋውንና ደሙን አቀበላቸው ። ከዚያም በኪሩቤልና በሱራፌል ሠረገላ ተቀምጣ በምታርግ ጊዜ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናቱ እመቤታችን ማርያምን እንዲህ ብሎ ተናገራት። በዚች ቀን የሆነ የዕርገትሽን መታሰቢያ በዓለም ውስጥ እንዲሰብኩ ልጆችሽ ሐዋርያትን እዘዣቸው። መታሰቢያሽን የሚያደርገውን ሁሉ ተጠብቆም በዚች ቀን ቅዱስ ቁርባንን የሚቀበለውን ኃጢአቱን እደመስስለታለሁ። የእሳትን ሥቃይ ከቶ አያያትም መታሰቢያሽን ለሚያደርግ ሁሉ በዚች ቀን ለድኆች በስምሽ ለሚመጸውት ቸርነቴ ትገናኘዋለች ይህም ሥጋሽ ወደ ሰማይ ያረገበት ነው። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ክብር ይግባውና ጌታችንን እንዲህ አለችው ልጄ ሆይ እነሆ በዐይኖቻቸው አዩ በጆሮቻቸውም ሰሙ በእጆቻቸውም ያዙ ሌሎችም ታላላቅ ደንቆች ሥራዎችን አዩ። እመቤታችንም ይህን ስትናገር ጌታችን ሰላምታ ሰጥቷቸው በታላቅ ደስታ ወደ ደብረ ዘይት ተመለሱ። የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ በፍጹም ደስታ መታሰቢያዋን እናደርግ ዘንድ ይገባናል እርሷ ስለእኛ ወደ ተወደደ ልጅዋ ሁልጊዜ ትማልዳለችና። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ይማረን። በረከቷም ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ከአባ ማትያስ ከሁሉም ሊቃነ ጳጳሳትና ኤጲስቆጶሳት ጋራ ሐዋርያት ከሰበሰቧት ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች ከሁላችን ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን። (#ስንክሳር_ዘወርኀ_ነሐሴ) ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE  https://t.me/Ortodokstewahido https://t.me/Ortodokstewahido https://t.me/Ortodokstewahido

Открыть в Telegram
Просмотры10 300×16к среднему
Пересылки—
Реакции16
Комментарии—
#18355Превью ссылки

#ቡሄ፣ #ጅራፍ_ማስጮህ፣ #ችቦ_ማብራትና #ሙልሙል_ዳቦ ሃይማኖታዊ ምስጢራቸው ምንድነው? ደብረ ታቦር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያዕቆብን፣ ዮሐንስንና ጴጥሮስን ይዞ ወደ ታቦር ተራራ ከወሰዳቸው በኋላ በዚያ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበትና ሙሴና ኤልያስን ጠርቶ የህያዋንና የሙታን አምላክነቱን ያሳየበት ከዘጠኙ የጌታ ዓበይት በዓለት ውስጥ አንዱ ነው። ቤተክርስቲያናችንም የተለያዩ ስርዓቶችን በመፈፀም አክብራው ታልፋለች፡፡ በደብረ ታቦር በዓል የሚፈጸሙ (#ቡሄ፣ #ጅራፍ ማስጮህ፣ #ችቦ ማብራትና #ሙልሙል_ዳቦ) ትውፊታዊ የሃይማኖት ሥርዓቶች ምሳሌዎች ምን እንደሆነ እናያለን፡፡ #ቡሄ ቡሄ ማለት ብራ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ማለት ነው፡፡ ከስሙ ትርጉም እንደምንረዳው ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት በዓል ስለሆነ ብራ፣ ብርሃን ደማቅ የሚል ፍቺ ያለው ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ አንድም ቡሄ ማለት ወቅቱ የክረምት ጨለማ አልፎ የብርሃን ወቅት ስለሚመጣ ሰማይም ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት የመሸጋገሪያ ወቀት ስለሆነ ብራ ተብሏል፡፡ "ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት እንዲሉ" አንድም ቡሄ ቡኮ /ሊጥ/ ማለት ነው፡፡ በዚህ በዓል ቡኮ ተቦክቶ ዳቦ/ሙልሙል/ ተጋርሮ የሚታደልበት በዓል ስለሆነ ይህ ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ #ሙልሙል_ዳቦ ሙልሙል ዳቦ አመጣጡ ጌታችን ብርሃናዊ መለኮቱን በገለጠበት በዚህ ዕለት በደብረ-ታቦር አካባቢ የነበሩ ህፃናት እረኞች ቀኑ የመሸ ስላልመሰላቸው /ጌታችን በብርሃን አካባቢውን ሞልቶት ስለነበረ/ በዛው ሆነው ከብትና በጎቻቸውን እየጠበቁ ሲቆዩባቸው የሰዓቱን መግፋት የተመለከቱ ወላጆች በችቦ ብርሃን ተጠቅመው ለልጆቻቸው የሚቀመስ ሙልሙል ዳቦ ይዘው ወዳሉበት መምጣታቸውን ያሳያልና ታሪኩን እየዘከርን በዓሉን እናከብራለን፡፡ አንድም እንደ ሐዋርያት የምስራች ሲነግሩን ወንጌል ሊሰብኩልን በየደጃፋችን መጥተው "ቢሄ በሉ" የሚሉትን ታዳጊዎችን ይበሉት ዘንድ ይሰጣቸዋል ይህም መጽሐፋዊ ነው ጌታችን ደቀ መዛሙርቱን በደረሳችቡት ሁሉ ተመገቡ /ማቴ 10፥12/ ብሏልና ህፃናቱም የጌታን በዓል ሊያበስሩ ሲመጡ ዳቦ መስጠት ልማዳዊ ብቻ ሳይሆን ህፃናቱም የደቀመዛሙርት ምሳሌ ናቸው፡፡ መዝሙራቸው ደግሞ የምስራች ወንጌል ይዘው የመምጣታቸው ምሳሌ ነው፡፡ ሐዋሪያት በገቡበት ሀገር ሁሉ አስተምረው አጥምቀው የፀጋ ልጅነትን አሰጥተው እንደሚቆዩ ሁሉ ልጆችም ዘምረው አመስግነው መርቀው ውለዱ ክበዱ የመንግሥተ ሰማያት ወራሾች ያድርጋችሁ ብለው አመስገነው ይሄዳሉና በሐዋሪያት ህፃናቱ ይመሰላሉ፡፡ #ችቦ_ማብራት ችቦ የጌታችንን ብርሃነ መለኮት መገለጥን የሚያመለክት ነው፡፡ ጌታችን በደብረ ታቦር መለኮቱን ሲገልጥ ብርሃን አካባቢውን ሞልቶት ነበርና ያንን በዘመናችን ለመግለጥ የበዓሉ ዋዜማ ማታ ችቦ አብርተን አምላካችንን እናመሰግናለን፡፡ አንድም ደግሞ የችቦ ታሪክ ከላይ እንደገለፅነው የእረኞቹ ወላጆች ይዘውት የመጡት ብርሃን ነው፡፡ #የጅራፍ_ምሳሌነት በደብረ ታቦር በዓል በትውፊታዊ መልኩ የሚታየው ሚስጥር በእየሩሳሌም ስለሚሆነው የጌታችን ሞቱ ምሳሌ ነው፡፡ በዚህ በዓል ጅራፍ መገመዱ እና ማጮሁ ሁለት አይነት ምሳሌ አለው፡፡ #የመጀመሪያው ጌታችን በዕለተ አርብ የደረሰበትን ግርፋትና ህማም እናስብበታለን፣ #ሁለተኛው ደግሞ ድምፁን ስንሰማ የባህሪ አባቱን የአብን የምስክርነት ቃልና በግርማው ሲገለጥ የተሰማውን ነጎድጓድ ያስታውሰናል፡፡ የጅራፍን ትውፊታዊ ውርስ መጽሐፋዊ ትምህርቱንና ምስጢሩን ከትውልድ ጠብቆ ማስተላለፉ ተገቢ ነው፡፡ በአጠቃላይ በዓለ ደብረ ታቦር ከነዚህ ምስጢር ካላቸው ትምህርቶችና ትርጓሜያቱ ከትውልድ ወደ ትውልድ በቅብብል እንደመጣልን እኛም ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ሳይለቅ ማስተላለፍ ይጠበቅብናል፡፡ የዚህ ነገር ባለ ድርሻ አካላት ደግሞ ወጣቶችና ወላጆች ናቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜ በቡሄ ጨዋታ የሚሰሙ ግጥሞች ስድብ ፊዝና ሳቅ ይታይባቸዋል ተጫዋቾቹም ከሰጡን እንመርቃለን ካልሰጡን እንራገማለን አይነት መልዕክት ያስተላልፋሉ። የሚብሰው አሳባቢ ነገሩ ደግሞ ኃይማኖታዊ ስርዓቱን ወደ ገንዘብ ማግኛ መቀየሩ ነው፡፡ ስለሆነም ይህን ነገር በተለይ የነገ የሀገር ተረካቢና የቤተክርስቲያን ተተኪ የሆኑት ወጣቶች ማስተካከል ይኖርባቸዋል፡፡ ወላጆችም ሕፃናት በየደጃፋችን ላይ በዓሉን ሊያበስሩ ሲመጡ አስደንግጦ ከማባረር በሚገባው መልኩ አስተምረን መርቀን ማስተናገድ ይጠበቅብናል ባህሉም እንዳይተው የበኩላችንን አደረግን ማለት ነው። ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን (ምንጭ - ጽሐፈ ታሪክ ወግሥ ገጽ 307 በመምህር አፈወርቅ ተክሌ ) ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE https://t.me/Ortodokstewahido https://t.me/Ortodokstewahido https://t.me/Ortodokstewahido

Открыть в Telegram
Просмотры8 450×13к среднему
Пересылки—
Реакции10
Комментарии—
#18341Превью ссылки

#ደብረ_ታቦር ነሐሴ ዐሥራ ሦስት በዚች ቀን ክብር ይግባውና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታላቅና ክቡር በዓል ነው። በዚች ቀን መድኃኒታችን ሦስቱን ደቀ መዛሙርቶቹን ጴጥሮስን፣ ያዕቆብንና ዮሐንስን ይዞ ወደ ታቦር ተራራ ላይ አወጣቸው። መልኩም በፊታቸው ተለወጠ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ሆነ። ስለ እነርሱም ጌታችን የሰው ልጅ በጌትነቱ ሲመጣ እስከሚያዩት ድረስ በዚህ ከቆሙት መካከል ሞትን የማይቀምሱት አሉ አለ። ሰዎች ሁሉ እርሱ ለሙሴ ጌታውና ከሞት ያስነሣው እንደሆነ ለኤልያስም ፈጣሪው እንደሆነና ካሳረገበትም ያወረደው እርሱ እንደሆነ ያውቁ ዘንድ እነሆ ከጌታ ከኢየሱስ ጋራ እየተነጋገሩ ሙሴና ኤልያስ ወደርሱ መጡ። ስለዚህም ጴጥሮስ ጌታችንን እንዲህ አለው አቤቱ በዚህ ትኖር ዘንድ ትወዳለህን ሦስት ሰቀላዎችንም አንድ ላንተ፣ አንድ ለሙሴ፣ አንድ ለኤልያስ እንሠራ ዘንድ። በዚህም ቃል የደካማነትና የትሕትና ምልክት አለበት። ደካማነት የተባለ ጴጥሮስ ጌታችን ከሰማይ የወረደበትን ሥራ ትቶ በተራራ ላይ ይኖር ዘንድና ራሱን የሚሠውርበትን ቤት ይሠራለት ዘንድ የተናገረው ነው። ትሕትና ያልነውም ጴጥሮስ ለራሱና ለባልንጀሮቹ ሐዋርያት ቤት ይሠራ ዘንድ ስለ አላሰበ ነው። ራሱንና ባልንጀሮቹ ሐዋርያትን እንደ ባሮች ነቢያትን ደግሞ እንደ ጌቶች አድርጎ አስቧልና። ሰለ ሐዋርያትም የእውቀት ማነስ አታድንቅ በዚያን ጊዜ ፍጹማን አልሆኑምና። እንዲህም በሚልበት ጊዜ ጌታችን በሰው እጅ የተሠራ ማደሪያን የማይሻ መሆኑን ለጴጥሮስ ያሳየው ዘንድ እነሆ ደመና ጋረዳቸው። የጌታችንን ጌትነቱን የሚገልጽ በሐዋርያትም ልቡና እምነትን የሚያጸና እንዲህ የሚል ቃል ከደመና ውስጥ መጣ። ይህ የምወደው በእርሱ ደስ የሚለኝ ልጄ ይህ ነው እርሱንም ስሙት። ሙሴና ኤልያስም ከእርሱ ጋራ ሲነጋገሩ ተሰሙ ስለ ርሱ መምጣት የተናገሩትን ትንቢታቸውንም በቸርነቱ አረጋገጠ። ወደ ተራራ ላይ በመውጣቱም ነቢያትና ሐዋርያት ደስ አላቸው። ሁለተኛም የአብን ቃል በሰሙ ጊዜ ከእነርሱ ሥውር የነበረ የወልድ ዋሕድን በእውነት ሰው መሆን በዚያን ጊዜ ተረዱ ያን ጊዜ የጌትነቱ ክብር ተገልጦአልና። ሐዋርያትም ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው የሆነ እርሱ ሙሴን ከመቃብር ያስነሣው ኤልያስንም ያሳረገው አውርዶም ያመጣው እርሱ እንደሆነ አወቁ። ከእርሱ በቀር ማንም ማን የሙሴን መቃብር የሚያውቅ የለምና ከዐሳረገው ከእርሱ በቀር ማንም ማን ኤልያስ ያለበትን የሚያውቅ የለምና። በሰማይና በምድር ሥልጣን ካለው ከሁሉ ጌታ በቀር ሙታንን አድኖ ሊአስነሣቸው ማንም አይችልም። ደብረ ታቦርም የቤተ ክርስቲያን አምሳል ሆነች ከብሉይና ከሐዲስ በውስጧ ሰብስባለችና። የአብንም ቃል በሰሙ ጊዜ በግምባራቸው ፍግም ብለው በምድር ላይ ወደቁ እንደ ሙታንም ሆኑ። ከዓለም አስቀድሞ ከእርሱ ጋራ በህልውና እንዳለ ለልጁ አብ ምስክርን ሆነ ወዲያውኑ ሙሴ ወደ መቃብሩ ኤልያስም ወደ ቦታው ተመለሱ። ሐዋርያትንም በአነቃቸው ጊዜ ከብቻው ጌታችን በቀር ማንንም አላገኙም። ከባሕርያችን የተዋሐደና ሥጋችንን የለበሰ ፍጹም አምላክ እንደሆነ በዚህ ሐዋርያት አስተማሩ። እንግዲህ እናስተውል ሰው ካልሆነ ቅዱስ ገብርኤል እመቤታቸንን ድንግል ማርያምን በአበሠራት ጊዜ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋራ ነው እንዴት አላት። አምላክ ካልሆነስ ለመንግሥቱ ፍጻሜ የለውም እንዴት አላት። ሰው ካልሆነ በበረት እንዴት አስተኙት። አምላክስ ካልሆነ መላእክት ከሰማይ ወርደው ለእግዚአብሔር በሰማያት ምስጋና በምድርም ሰላም ለሰውም ግዕዛኑ ሊሰጠው እያሉ እንዴት አመሰገኑ። ሰው ካልሆነ ዮሐንስ በውኃ እንዴት አጠመቀው አምላክስ ካልሆነ አልዓዛርን ከመቃብር እንዴት ሊያስነሣው ቻለ። ይህ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው እንድ ልጅ አካላዊ ቃል እግዚአብሔር እርሱ ያለ መለወጥ ያለ መለየት አንድ አካል አንድ ባሕርይ በመሆን ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው እንደሆነ እናምንበታለን። እርሱም ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ ሁል ጊዜ አንድ ህላዌ ነው ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን። (ስንክሳር ዘወርኀ ነሐሴ) ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE  https://t.me/Ortodokstewahido https://t.me/Ortodokstewahido https://t.me/Ortodokstewahido

Открыть в Telegram
Просмотры7 970×12к среднему
Пересылки—
Реакции9
Комментарии—
#18223Превью ссылки

ቂም የነፍስ የጨለማ መጋረጃዋ ነው። ይኸውም ለክፉ ክፉ መመለስን ከመውደድ የሚመጣ በቀል ነው። ከተበቀለ በኋላ ግን በጸጸት ጅራፍ ይገረፋል። ቂምስ ምን ትመስላለች ትለኝ እንደሆነ የእናታቸውን ማኅፀን የሚበሉ የትሎችን ልጆች ትመስላለች ብየ እመልስልሃለሁ። የልብ ቂም በቀልን ያወርሳል፤ በቀልም አጥንትን ይሰብራል። የልቡና ቂም በጎ ሥነ ምግባራትን ሁሉ ያጠፋቸዋል። ቂም በእውነት እግረ ነፍስን እንደወደደች እንዳትራመድ የሚገታ የሚጎዳ ማሰሪያ ነው። ቂም ለእግዚአብሔር የሚገባውን ሁሉ ከማድረግ እንድናቋርጥ ያደርጋል። ቂም የዚህን ዓለም ሐሳብ በመፈለግ በጠማማ ጎዳና እንዲቆሙ ያደርጋል፤ የልብ ፍላጎት በቂም ገመድ ታስሯልና። ጁባን የለበሰ ቦርቦርቴን የደፋ ሰው የተወረወረ ጦር የተነቀነቀ ዘገር የሠረረ ቀስት እንደማያገኘው እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰውንም ቂም ወይም በቀል አያገኘውም። ቂም በልቡናው ያደረበት ሰው ከበቀል አይርቅም፤ ከዓለምም መራቅ መመነን አይቻለውም። እርሱ በቂም ሆኖ ሌሎችን የሚገሥጽ ራሱንም ንጹሕ እንደሆነ የሚያስብ የተናቀ ወራዳ ነው። ዓለምን የናቃት ሰው ዘወትር ደስተኛ ነው፤ ቂምና የልብ ፍትወት ከጸና ዘንድ ግን ወደ አፍቅሮ ንዋይ ይወስዳል። ጥሪት ቁሪትን ገንዘብን የሚወድ ሰው ግን ፈጽሞ ደስ ይለዋል። በምንም በምን ስለ እርሱ አይጨነቅም። የጠቢብ ሰው መታሰብ በሁሉ ዘንድ ያማረ የተወደደ ነው፤ ቂምና የልብ ፍትወት ግን ደካማ ነው። ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE    https://t.me/Ortodokstewahido https://t.me/Ortodokstewahido https://t.me/Ortodokstewahido

Открыть в Telegram
Просмотры8 630×13к среднему
Пересылки—
Реакции15
Комментарии—
#18186Превью ссылки

ቁሉቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም በምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ከአዲስ አበባ በስተምሥራቅ 461 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት በሜታ ወረዳ የሚገኝ ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ በዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዮዲት ጉዲት ተነሥታ አብያተ ክርስቲያናትን ስትመዘብር፣ ክርስቲኖችን ስትገድልና መጻሕፍትን ስትቆነጻጽል ንጉሥ አንበሳ ውድም በአክሱምና በአካባቢዋ የነበሩ ታቦታትንና ንዋያተ ቅድሳትን በመያዝ ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ወደ ዝዋይ መጣ፡፡ ከ40 ዓመታት ስደት በኋላ አንበሳ ውድም ወደ አክሱም ሲመለስና የንዋያተ ቅድሳት ቆጠራ ሲደረግ ታቦተ ቅዱስ ገብርኤል በዝዋይ መቅረቱ ታወቀ፡፡ አባ ሌዊ የተባሉ አባት ታቦቱን ለማምጣት ከንጉሡ አስፈቅደው ወደ ዝዋይ መጡ፡፡ አባ ሌዊ ከ7 ቀን ሱባዔ በኋላ ታቦተ ቅዱስ ገብርኤልን ይዘው ወደ አክሱም ሲጓዙ ቅዱስ ገብርኤል ተገልጦ “እኔ ወደማሳይህ ቦታ ታቦቱን ይዘህ ሂድ” አላቸው፡፡ አባ ሌዊም ታቦቱን ይዘው ተከተሉት፡፡ በመጨረሻም ቁሉቢ ደረሱ፡፡ ለአባ ሌዊም የተፈቀደላቸው ቦታ ይህ መሆኑን ታቦቱም በኋላ ዘመን ለሕዝቡ ድንቅ ሥራ እንደሚሠራ ቅዱስ ገብርኤል ነግሯቸው ተሠወረ፡፡ አባ ሌዊ በቦታው ለ130 ዓመታት ያህል አገልግለው በንጉሥ ግርማ ሥዩም ዘመነ መንግሥት ታኅሣሥ 14 ቀን ዐርፈዋል፡፡ ግራኝ አሕመድ ኢትዮጵያን ሲወር ብዙ ካህናት ከሰሜን ኢትዮጵያ (ታቦታትንና ንዋያተ ቅድሳትን ይዘው ሲጓዙ ቁሉቢ ደረሱ፡፡ መልአከ ገነት መብረቁ፣ መምህር የማነ አብ፣ አባ ተከሥተ ሥሉስ የተባሉ ካህናት ከተነጠፈ ድንጋይ ላይ የተጻፈ ነገር ያገኛሉ፡፡ ጽሑፉም ታቦተ ቅዱስ ገብርኤል በስውር መቀመጡን፣ ልዩ ልዩ ተአምራት እንደሚፈጸምበት፣ ወደ ፊት ታላቅ ቤተ መቅደስ እንደሚሠራበት፣ እንዴት አባ ሌዊ ታቦቱን ወደዚህ ቦታ እንዳመጡት የሚገልጽ ነበር፡፡ እነርሱም ይህን ታሪክ ይዘውት በነበረው በመጽሐፈ ቀሌምንጦስ ኅዳግ ላይ ጻፉት፡፡ ወደ ደሴተ ዝዋይ ሲደርሱም መጽሐፉን በዚያ አኖሩት፡፡ ልዑል ራስ መኮንን ከዝዋይ ደሴት መጽሐፈ ቀሌምንጦስን አስመጥተው ሲያነቡ የቁሉቢ ገብርኤልን ታሪክ በማግኘታቸው የቅዱስ ገብርኤልን ቤተ ክርስቲያን ለማነጽ ተነሡ፡፡ ልዑል ራስ መኮንን በአካባቢው የአየር ንብረት ተማርከው በሥፍራው ቤት ሠርተው ነበር፡፡ ልዑል ራስ መኮንን ቁሉቢ ገብርኤልን ከመትከላቸው በፊት ቦታው የአካባቢው ጎሳዎች የግጭት መናኸሪያ ነበር፡፡ ሰላምን በአካባቢው ከመሠረትህ በቦታው በስምህ ቤተ ክርስቲያን እሠራልሃለሁ ብለው እንደተሳሉ ይነገራል፡፡ የተሳሉት በመፈጸሙ የቅዱስ ገብርኤል ታቦት የት እንዳለ ሲያፈላልጉ ቡልጋ ውስጥ ከአዠጉጉ ካህናተ ሰማይ ጋር አባ ዱባለ የተባሉ ካህን ያስቀመጡት ታቦተ ቅዱስ ገብርኤል መኖሩ ተነገራቸው፡፡ ልዑል መኮንን ለአባ ዱባለ መልእክት ስለላኩባቸው ከሐረር በተላኩት ካህናት አማካኝነት የቅዱስ ገብርኤልን ታቦት ላኩ፡፡ ልዑል ራስ መኮንንም ከነሠራዊታቸው ሸንኮራ ድረስ ሔደው ታቦቱን በመቀበል የካቲት 20 ቀን 1884 ዓ.ም ታቦቱ ቁሉቢ ገባ፡፡ የመቃኞው ሥራ በ1883 ዓ.ም ተጀምሮ ፍጻሜ አግኝቶ ቅዳሴ ቤቱ የተከበረው ሐምሌ 19 ቀን 1884 ዓ.ም ነው፡፡ በዚህ ዕለት የዋናው ቤተ ክርስቲያን ሕንፃ ሥራ የመሠረቱ ድንጋይ ተጥሎ ታኅሣሥ 19 ቀን 1888 ዓ.ም የቤተ ክርስቲያኑ ሥራ ተፈጽሞ በአቡነ ማቴዎስ ተባረከ፡፡ ቦታውን ከባላባቶች የገዙት በአርባ የቁም ከብት ነው፡፡ በመጀመሪያ ሲተከል በገጠር ቤተ ክርስቲያን ሥሪት ሲሆን በኋላ ግን በስእለት ሰማዒነቱ በመላ ኢትዮጵያ እየታወቀ ስለመጣ ደብር ሆኗል፡፡ ምንጭ፡- የቤተ ክርስቲያን መረጃዎች https://t.me/Ortodokstewahido https://t.me/Ortodokstewahido https://t.me/Ortodokstewahido

Открыть в Telegram
Просмотры7 170×11к среднему
Пересылки—
Реакции11
Комментарии—
#18164Превью ссылки

Seenaa gabaabaa Kawaala Qulqulluu Gabri’eel Qullubbii Kawaalli/gadaamiin Qulqulluu Gabr’eel Qullubbii godina Harargee Bahaa Magaalaa Qullubbii keessatti argama. Finfinnee irra fageenyi gadaamichaa kara bahaatti kiilo meetira 461. Akka seenaan gara garaa ibsanitti jaarraa saglaffaa keessa bara mootittii Yoodiit Gudit manneen kiristaanaa gubaa fi balleessaa turtetti luboonni Taabota naannoo Aksum jiran hunda gara hora Danbalitti(Ziwaay) qabatanii baqatan. Taabota gara hora danbal dhufan keeysa tokko Taabota Gabri’eel Qullubbiiti. Sana boodas deebisanii gara Aksumitti fudhachuu yemmuu barbaadan monoksee aabbaa Lewii jedhamutti tti “lakki gara Aksum osoo hin taane iddoon ani sitti agarsiisutti Taabota kana geessi” kan jedhu sagalee ergamaa Gabri’eel dhagahee,monoksichi gara Qullubbii geessee, ajaa’ibni gara garaa Taabota kanaan akka raawwatamu itti hime. Aabbaa Lewiinis iddoon Waaqayyo Taabota kanaaf filate Qullubbii ta’uu isaa erga baranii booda hanga guyyaa boqonnaa isaanitti achumatti tajaajilaniiru. Jaarraa 16ffaa keessa bara Giraagn Ahimad kiristaanota ajjeesaa, kitaabota kiristaanaa gubaa, kiristaanaa balleessaa, manneen kiristaanaa diigaa kiristaanota balleessuuf ka’etti lubootni Taabota baatanii baqachaa osuma jiran naannoo Qullubbii yemmuu gahan barreeffama dhakaa irratti waa’ee Taabotni qulqulluu Gabr’eelii dhoksaadhaan naannoo sana jiraachuu isaa ibsu argan. Barreeffamichis Taabotichi akkamitti akka dhufe, ajaa’iba inni raawwatuufii raajii gara fuula duratti naannoo sanatti bataskanni guddaan ijaarramee namootni kadhannaa itti godhan,wanti kadhatanis battalatti dhagahamuuf kan ibsu ture. Isaanis seenaa kana kitaaba Qalamnxoos harkaa qaban miila jalatti irratti barreessanii, kitaabicha irratti barreessan sana gara hora Danbal fidan. Bulchaa Harar ka turan Raas Makonnin W/Mikaa’el Guddisaa, seenaa kana kitaabicha fichisiisanii erga dubbisaanii hubatanii booda bataskaana achitti ijaaruf hawwan. Sana booda Taabotichi suni eessatti akka argamu gaafachutti yemmuu ka’an naannoo Ittisaa Takle Hayimaanotitti akka jiru bira gahamee taaboticha achii fidanii gara Qullubbiitti geessan. Taabotichi garasitti dhufuun isaa bara 1879- 1884 dunkaana keessa erga taa’ee booda bara 1884 bataskaanni itti ijaaramee phaaphaasi biyya Gibxiitii dhufan Abbaa Maatewoosin eebbifamee tajaajila jalqabee hanga bara 1954 tajaajila osoo kennu ture. Booda kadhannaan namoota taabota kana duratti taasifamu battalumatti dhageettii argachuun isaa waan dhagahameef biyyattii keessatti battalumatti beekkamuutti ka’e. Gamoon amma jirus akka haaratti bara 1957 hojjetamee xumurame. Namootni amantaan isaanii illee Ortodoksii hin taane kadhannaan isaan Taabota sana duratti godhan ni dhagahama, wareega hedduus galchaa jiru, dhugaa bahaas jiru. Waaqayyo bara kanatti ajaa’iba akkanaa kana biyya keenya keessatti akka agarruu fi dhageenyu kan nu taasise maqaan Isaa ol ol kan jedhe fi kan galateeffame haa tahu. Ajaa’iba dirree Qullubbiitti raawwatu barreessanii xumuruuf dheeradha,raawwatama jiras si’achi.Namootni qaaman dhaqanii osoo ilaalanii baay’ee gaaridha. Haa ta’u malee ayyaana kanaan walqabatee namoonni dhimma waa’ee hojii afuurawaa of keessa hin qabne waan akka sirbaa, nyaataa dhugaatii, machii fi dhimma foon garagaraaf garasitti imalan baay’achaa dhufuun isaanii baldhinaan ni dhagahama. Hojiin akkasii ammoo jibbamaa ta’uu hubatanii laphee qulqulluudhaan iddoo sanarraa sugaargatanii deebi’uutu dansa’a. “DHIIFAMNI WAAQAYYO BARA BARAAF; DHEEKKAMSI ISAA AMMOO GUYYAA TOKKO” akka jedhu kitaabni,Waaqayyo arjaadha jedhanii cubbuu irratti iddo qulqullaa’aa ta’ettu cubbuu biraa dabaluun qurxama fida.` Sugni, fi araarsumman hangafa ergamoota Qulqulluu Gabr’eelii, nu waliin yaa ta’u. (Seenaa Maddeen gara garaa irraa argame) https://t.me/Ortodokstewahido https://t.me/Ortodokstewahido https://t.me/Ortodokstewahido

Открыть в Telegram
Просмотры6 730×10к среднему
Пересылки—
Реакции13
Комментарии—
#18102Превью ссылки

“አንተ የምትተኛ ንቃ ከሙታንም ተነሣ ክርስቶስም ያበራልሃል" / ኤፌ 5÷14/ ወዳጆቼ ብዙዎቻችን ስልክ ስናወራ ሳንቲሜ ቆጠረ እንጂ ዕድሜዬ ቆጠረ አንልም ከዕድሜው ይልቅ ለሳንቲም ዋጋ እንሰጣለን። በስልክ ከወዳጆቻችን ጋር የምናወራውን ያክል እንኳ ከፈጣሪያችን ጋር ማውራት ሸክም ሆኖብናል። በመንፈሳዊ ህይወት ላይ ለውጥ ለማምጣት በፕሮግራም ሳይሆን በእግዚአብሔር ፈቃድ ነው መኋዝ ያለብን።  ነገ እጀምራለው ነገ ይህን አደርጋለው እያልን ቆጠሮ ብንሰጥ ትርፉ መሰላቸት ነው ማድረግ ያለብንን ዛሬ አሁኑን እንጀምረው። የእግዚአብሔር ፈቃዱም አሁኑኑ እንድንድን ነው። ነቢያት ስላልመጣው ዘመን ያውቁ ነበር ፤ እኛ ግን የምንኖርበት ዘመን ምንነት እንኳ ተሰውሮብናል። ሐዋርያት ሄደው ዓለምን ዞረው ይሰብኩ ነበር ፣ እኛ ግን በተመቻቸ ቦታ መጥታችሁ ተሰበኩ እንላለን። ሰማዕታት ለክርስቶስ ፍቅር ሞቱ ፣ እኛ ግን ለጥቅማችን ፣ ለምኞታችን ፣ ለኃጢያታችን እንሞታለን። ጻድቃን የዚህን ዓለምን ጣዕም ንቀው መነኑ ፣ እኛ ግን ዓለም መራራ ሆናብንም እንኳ ደግመን ደጋግመን እንፈልጋታለን። ቅዱሳን አባቶቻችን ከሕግ አልፈው በትሩፋት ኖሩ ፣ እኛ ልጆቻቸው ግን የታዘዝነውን እንኳ መፈጸም ተስኖናል። ደናግል መነኮሳት የክርስቶስ ሙሽሮች ሆኑ ፣ እኛ ግን በአንድ ሃይማኖታችን ጸንተን ክርስቶስን መከተል (ማምለክ) አቅቶናል። ሊቃውንት አባቶቻችን አህያ እንኳ የማትሸከመውን መጽሐፍ በቃላቸው አጠኑ ፣ እኛ ግን አንድ ጥቅስ ለማጥናት ያዙኝ ልቀቁኝ እንላለን። ጌታ ሆይ እባክህን እኛን እንቅልፋሞቹን ከእንቅፋችን አንቃን ! ለተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE  https://t.me/Ortodokstewahido https://t.me/Ortodokstewahido https://t.me/Ortodokstewahido

Открыть в Telegram
Просмотры7 090×11к среднему
Пересылки—
Реакции21
Комментарии—