አሁን እኔ ሰው ነኝ🥹 በእኔ ክፉ በደል በልጅሽ አስፈርጂ ስበደል ሳጠፋ በኃጢያት ወድቄ ለከንቱዋ ዓለም ልቤን አስገዝቼ ቀን በቀን ስበድል በእርኩሰት ወድቄ አሁን እኔ ሰው ነኝ ንገሪኝ እናቴ የከፈለልኝ የመስቁን ዋጋ አንቺ ያዘንሽበት ሲገረፍ ሲመታ የኔን እመም ታሞ እሱ ሲንገላታ አምርረሽ አለቀሽ ልጅሽን ስታዪ ስቃዩን እያየሽ ልጄ ልጄ ስትዩ እና እኔ ሰው ነኝ ይህን ሁሉ ትቼ ኃጢያቴን እያየ ያለፈኝ በአንቺ ነው ወድቄ እንዳልቀር ሁሌ ስትለምኚ እኔ ግን ከንቱ ነኝ ክፋት የከበበኝ ትላንትን ረስቼ ዛሬም የምረክስ ውለታውን ትቼ ዛሬም የምካሰስ ደግሞ አይገርምሽም ስራዬን ስታዩው መበደሉ ሳያንስ ኃጢያት መስራቱ ትቢተኛው ልቤ ሳይጸልይ ይተኛል አንቺ እሩሩነሽ መቼም አጨክኚም ያ ደጉ ልጅሽም ስራዬን እያየ ዛሬም ያኖረኛል ዝምታው ሳስብ ውስጤን ይጨንቀኛል🥹🥹 Enate16✍ 📢በየቀኑ ኦርቶዶክሳዊ ሥነ-ጹህፎች ለማግኘት ቻናላችንን ይ🀄️ላ🀄️ሉ 👇👇 💚 @orthodoxawi_gtm 💚 💛 @orthodoxawi_gtm 💛 ❤️ @orthodoxawi_gtm ❤️ ይ🀄️ላ🀄️ሉ👆👆🤍
Открыть в TelegramПосты канала ✟ ኦርቶዶክሳዊ ሥነ-ጹህፎች ✟
ኪዳነ ምህረት ❤️🩹🤍 እንዴት ብዬ ልምጣ እንዴት ላዋይሽ በየትኛው ቃላት በምንስ ላስረዳሽ የኔ ኪዳነ ምህረት የኔ የጭንቄ ደራሽ ከሀዘኔ ፈዋሽ የእንባዬም አባሽ እመ አምላክ ሆይ ድንግል ዛሬኮ ከበደኝ በሀዘን ተዋጥኩኝ እናቴ ጨነቀኝ ምነው ጨከንሽብኝ ምነው አልራራም አልሽ 🥺🥺 ምነው ስጮህ ሳለቅስ እንዴትስ አስቻለሽ 🥹😥 አልቀርም መጣለሁ ሁሌም ከደጅሽ እናቴ እያልኩኝ ስንቱን ላዋይሽ ዛሬ ግን ተሳነኝ ማውራትም ከበደኝ ሁሉም ግራ ሆነ ሕይወት ጠመመብኝ አንቺ የአምላኬ እናት አንቺ ደጓ እናቴ ያኔም አንቺ ነበርሽ ፅናት በረከቴ ...ዛሬም አለሽ አይደል ..ዛሬም አለሽ አይደል እማ ልጠብቅሽ ሁሉም ከኔ ሲርቅ እናቴ ልበልሽ ሲከብደኝ ሲጨንቀኝ መጥቼ ላዋይሽ እናቴ ልለምን ወድቄ ከእግሮችሽ ፊትሽ ወደ አምላኬ ይዙር ወደ ልጅሽ እባክሽ አሰጪኝ ምህረትን በእጆችሽ አውቃለሁ ሲጨንቀኝ እንደማያስችልሽ 🥺🥰🙏 ናርዶስ ✍✍ 📢በየቀኑ ኦርቶዶክሳዊ ሥነ-ጹህፎች ለማግኘት ቻናላችንን ይ🀄️ላ🀄️ሉ 👇👇 💚 @orthodoxawi_gtm 💚 💛 @orthodoxawi_gtm 💛 ❤️ @orthodoxawi_gtm ❤️ ይ🀄️ላ🀄️ሉ👆👆🤍
Открыть в Telegramየሰማዩን ምስክር ጨለማን ሰባሪ_ብርሃን ወጥቶብሻል ሞትን የሚገድል_ትንሳኤን ወልደሻል ንጽሕ መሶበ ወርቅ_ ድንግል ተብለሻል ለከበረው ክብርሽ_ስግደት ይገባሻል። የሰማዩ ምስክር_ የታየው በራማ በምድራዊው ገነት_ እነሆ ተሰማ የመልአኩን በስራት_ኤልሳቤጥ ስትደግመው በሆዷ ያለው ጽንስ_ ደስታ አዘለለው መጥምቀ መለኮት_ክብሩ ከፍ ያለ ነው። ለኛ ስለሰጠች _ የሕይወት እንጀራን ሁሌም ለዘለአለም_ እንወዳታለን የምስራቋ ደጃፍ_የወለደች ፀሐይ የኤልሳዕ ማሰሮ_ የበረከት ሲሳይ። የፍቅር የሰላም _ የምሕረት መገኛ የምንመካብሽ _ ነይ ነይ ወደ እኛ ኖርዶስ ቀሲመታት_ በጎ መዓዛ ነሽ የአማኑኤል ማደሪያ_ የለም የሚመስልሽ። ጌታዬ ከሰጠኝ_ እናቴ እልሻለው የመንገድ ስንቄ ነሽ_ እመካብሻለው ለጠየኩሽ ሁሉ _ መልስ የምትሰጪኝ እንዳልነዋወጥ_ በዐለቱ ትከይኝ። በመከራ ጊዜ _ መሸሸጊያ ሆኖን የመከራን ባሕር_ በፍቅሩ አሻግሮን እንደበደላችን_ ሳያጠፋን ጌታ አቆመን በደጁ_ ሞልቶን በእልልታ። ከኛ የበረታችሁ _ አስቡን በጸሎት በስጋ ፈተና _ እንዳይገለን ምቾች በሄድንበት ሁሉ_ እንዲገጥመን ሰላም ፍፃሜአችን እንዲያምር_አማልጅን ማርያም። የተሰቀለውን _በገና አውርዱ መሰንቆ ክራሩን_ ከበሮ አሰናዱ መቆሚያ ጽናጽል_ ይታደል ለሁሉም በያሬድ ውብ ዜማ_በሚያስረሳ ዓለም ተነሱ እንዘምር_ ለመድኃኒዓለም። እንዲህ እናምናለን_ እንታመናለን በተበተንበት በባዕዱ ምድር_ እንመሰክራለን የሥላሴን ጥበብ_ ትውልድ እንዲረዳ ይምጣና ይመገብ_ ከእናቱ ጓዳ ኋላ ለጥያቄ _እነዳይሆን እንግዳ ትጉኃን በዝማሬው ጣዕም_ተሞልተን ደስታ በተዋሕዶነቷም _ ነፍሳችን ተጽናንታ በቃሉ ምስክር _ ቀርቦልን ማዕድ በወልድ እናት ምልጃ _በሕይወት መንገድ ከቅድስት ምድራችን _በመጡት በደጀ ሰላሙ አለን_ ተሰብስበን። በመረዋ ድምጹ_ በሚስረቀረቀው ሲሰማ አርነት_ተሰፋን በሚሰብከው የአባቶችን ምክር_ትዕዛዝ በሚያከብረው በረጋው አንደበት_ ከቴድሮስ ሰማነው ኪዳነምሕረት_ በእቅፏ ታኑረው። ከዕርስታችን ወተን_ ብንኖርም በእሩቅ መተላለፋችን_ በስሙ እንዲፋቅ ክብር ሞገስ ሆነን_ ስራው የሚያስደንቅ። ሀይማኖት ከምግባር_የነፃነት በፍታ የሚያስተምር ፍቅር_ ጠዋትና ማታ የወንጌል አርበኛ_ የሚያስር የሚፈታ ደጀንን ሸለመን_ የሰራዊት ጌታ። ለዘመኑ ሕመም_ መድኃኒት ያመርታል የነፍስ ዶክተር ነው _ትውልድ ይፈውሳል ብሉይን ከሐዲስ _ እያመሳጠረ ስንቱን ሐሰተኛ_ ከቤት አባረረ። በጠላት ተከቦ_ ሲደፈር ተራራው እንደ ተመረጡት_ በእውነት አብበው ወንጌልን ተጫምቶ_ በብዕር ይሻገራል በለበሰው ሞገስ_ ሁሉን ያስደምማል _ 📢በየቀኑ ኦርቶዶክሳዊ ሥነ-ጹህፎች ለማግኘት ቻናላችንን ይ🀄️ላ🀄️ሉ 👇👇 💚 @orthodoxawi_gtm 💚 💛 @orthodoxawi_gtm 💛 ❤️ @orthodoxawi_gtm ❤️ ይ🀄️ላ🀄️ሉ👆👆🤍
Открыть в Telegramከነጠላው ጀርባ በደልን የማታይ አንተ ደጉ ጌታ ታየኛለህ መቼስ ሁልግዜም ሳጠፋ ፅድቅ የለኝ ለአፍታ ጊዜያዊ ሰው ሆንኩኝ ከሁሉም ክልስ ጥዋት አመስግኜክ ማታ የምረክስ ቤትህን ሁል ግዜ ልቤ ይናፍቃል ቀን በቀን ብመጣም ስራዬ ሸሽቶካል 🖤🖤 ስንቱን ጉድ ሸፈነው ያ ውብ ነጠላዬ ከደጅህ መጣለሁ በእርሱ ተከልዬ በምን ልሸፋፈን በምን ውስጥ ልከለል እንጃታየው ጉዴን ለኔ በደል ካሳ ቅጣቴስ ምን ይሆን??? ❤️🩹❤️🩹 ማረኝ ከትመርምረኝ ስራዬ ብዙ ነው በቸርነት ጎብኘኝ በደሌን አትየው ተራራ እንደመውጣት፣ዳገት እንደመግፋት እንደ ሰማይ ርቀት፣እንደ መንገድ ርዝመት እንደ ከባድ ስቃይ፣በአይን እንደማይታይ ካንተ ለመጠጋት ውስጤ ባይታበይ እንደ ጨረቃ ውበት፣እንደ ኮከብ ድምቀት እንደ የጥዋት ፀሀይ፣በፍቅር እንደምትታይ እዋብ እደምቅ ነበር በቤተ መቅደስህ በንፁህ ልቦና ሁሌ ምመላለስ አሁንም አልረፈደም ጌታዬ መልሰኝ ፀሎቴ እንደ ግብዝ አባቴ አይሁንብኝ ከነጠላው ጀርባ ከውጪ ለሚያየኝ ለአምላኳ ተገዢ ፍፁም አገልጋይ ነኝ። 😢😢 ላንተ ግን ግልፅነው ይታይሀል ሁሉም ማንነት ምንነት የሚቀርህ የለም ግና ምን አረከኝ ምን አረክ አምላኬ በድዬ ስመጣ ሳለቅስ ተንበርክኬ መቼ አባረርከኝ ከደጅህ አውጥተህ አላንቋሸሽከኝም ልጅነቴን ነስተህ ልጄ ሆይ ልጄ ሆይ ነይ ግቢ ከቤትሽ ብለህ ስትጠራኝ ልጀዘጅነትን ንቄ ባርያ ሆንኩኝ ርካሽ ባርያ ሆንኩኝ ዕድፍ የሀጥያት ምርኮኛ እረፍት የሌለው ሰው የሆነ ቀማኛ ይሁዳ ግን እንዴት ጌታን ለአይሁድ ሰጠው በመሳም ለይቶ አሳልፎ ሸጠው... 🤔😑 ብዬ ምገረመው ሁሌ ምደነቀው እኔም ቀማኛ ነኝ ሠራቂ ከአምላኳ የርሱን ግዜ ሰርቃ ሌላ ምታንኳኳ ይሁዳ ጌታዬን ለሠላሳ ዲናር አሳልፎ ሠጠው አለሁ አይደል እኔ ደግሜ ደግሜ በነፃ ምሸጠው 🥹🥹 ያን የሚያህል አምላክ ያን የሚያህል ጌታ አሁንስ መቼ ተወኝ በደሌ ሲፀና ትግስቱ በረታ ሐዋርያው ጴጥሮስ ሶስት ግዜ ቢክድህ አለሁ አይደል እኔ በአፌ እየደሰኮርኩ ተግባሬ ማይመስልህ ዶሮ ሳይጮህ ገና አላውቀውም ቢልህ በንሠኃ ታጥቦ ተመለሰ ቤትህ 🤍🤍🤍 እኔንም መልሰኝ ቅን ልቦናን ስጠኝ ከሀዲዋ ልጅህ አልቻልኩም ደከመኝ ማረኝ አትመርምረኝ በደሌን አትየው በቸርነት ጎብኘኝ!!!! 🥺🥺🥺🙏 ናርዶስ ✍✍ 📢በየቀኑ ኦርቶዶክሳዊ ሥነ-ጹህፎች ለማግኘት ቻናላችንን ይ🀄️ላ🀄️ሉ 👇👇 💚 @orthodoxawi_gtm 💚 💛 @orthodoxawi_gtm 💛 ❤️ @orthodoxawi_gtm ❤️ ይ🀄️ላ🀄️ሉ👆👆🤍
Открыть в Telegramልባም ሴት🧕 ልባም ሴት አድርገኝ የሆነች መልካም ለሰው ሳይሆን ላንተ የምትደክም ልባም ሴት ልሁን አምላኬ እኔስ በአለም ታልዬ አልኑር አሁንስ። ያቺን በጎ ሴት ያቺን አገልጋይ በመልካም ምግባሯ ሁሌ የምትታይ። አኑረኝ በመቅደስህ ልኑር በቤትህ ወዳንተ መልስኝ እንዳገለግልህ። የታወኩኝ ነኝ በአለሙ መሄጃ ያጣሁኝ አለም ከብዳብኝ አንተን የጠራሁኝ። ልባም ሴት ልሁን ታዛዥ እንስት ልባም ሴት ልሁን እግዚአብሔር የምትኮራባት። አልሁን ከንቱ የታለለች በብልጭልጭ አልሁን እኔ ለአለም የምትታጭ። ፈሪሀ እግዚአብሔር ያላት እርሱን የምፈራ አድርገኝ አባቴ ለሰው የምትራራ። ነኝና ተጠቂ በአለም በምድሩ ቀላቅልኝ አምላኬ አንተ ካከበሩ መሆን እፈልጋለሁ ልባም ሴት መሆን እፈልጋላሁ ያላት የልብ ውበት። ነኝ ከዘፈኑ ነኝ ከአለሙ መሀል ከንቱ ነኝ አምላኬ የማልገለፅ በቃል ልባም ሴት ልሁን አሁን ግን ይበቃል ሳይተካከል አሁንም እድሜዬ አልቋል። አይደለሁም ጀግና አይደለሁም ብርቱ የለም በአለም ላይ እንደኔ አይነቱ። አስተካክለኝና ልመለስ በቤትህ ልባም ሴት ሁኜ እኔስ ላገልግልህ። ለነፍሴ አልሆንኩ ደግሞም ለስጋዬ ከምኑም ሳልሆን ልቤ ተሰቃዬ። ሁሉም አለፊ ነው ዛሬ ያለኝ ሁሉ ያለኝ የመሰለኝ አንድ ቀን ይጠፋሉ የአበበልኝ ሁሉ ይጠወልጋሉ። ልባም ሴት አድርገኝና ልመረቅ አባቴ ጥሩ ስራ ሰርቼ እንድትቆም ከፊቴ። ልቧሟን ሴት መሆን እኔስ እሻለሁ ደግሞም መድሀኒቴ አሁንም እቀጥላለሁ ያቺን ቀን እንደማይ ተሰፋ አደርጋለሁ። ✍Nave(Mekdi)🦋 📢በየቀኑ ኦርቶዶክሳዊ ሥነ-ጹህፎች ለማግኘት ቻናላችንን ይ🀄️ላ🀄️ሉ 👇👇 💚 @orthodoxawi_gtm 💚 💛 @orthodoxawi_gtm 💛 ❤️ @orthodoxawi_gtm ❤️ ይ🀄️ላ🀄️ሉ👆👆🤍
Открыть в Telegramቅዱስ ሚካኤል ❤️🩹 . . . ሕይወቴ ሽንቁር ሲበዛዉ እንደ ሬት ጣዕም ቢመረኝ፤ ስምህን ነዉ የምጠራዉ ያላንተ ወዳጅ ማን አለኝ፤ ስጓዝ ብደነቃቀፍ እንቅፋት እግሬን ቢመታዉ፤ ከአምላክህ እያማለድክ ምርቅዝ ቁስሌን ፈወስከዉ፤ ወዳጄ ያልኩት ርቆ ብቻዬን መቆም ሲያቅተኝ፤ በዛ በጭንቅ ቀኔ ለአፍታም አልተለየኸኝ፤ የመላአክት አለቃ ሚካኤል ቅዱሱ፤ የወርቅ ሀመልማል መብረቅ ነዉ ቀሚሱ፤ የመላእክት አለቃ ሚካኤል ንጉሡ፤ ከመላእክት ሁሉ ከፍ ያለ ሞገሱ፤ የአምላክ ባለሟል ሚካኤል ኃያሉ፤ ምሕረት ይለምናል ለአዳም ልጅ በሙሉ፤ ተፋጥኖ ይደርሳል ለሚጠሩት ሁሉ። ...................................................... [ ዔደን ታደሰ ]
Открыть в Telegram#ኅዳር_12_ቀን ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የታላቁን ገናናው መልአክ የቅዱስ ሚካኤል በዓልን ስለ አራት ምክንያት በታላቅ ድምቀት ታከብረዋለች፡፡ የመጀመሪያው ሳጥናኤል ከእግዚአብሔር የተሰጠውን ክብር ትቶ አምላክነትን በትዕቢቱ በመሻቱ ምክንያት ከሥልጣኑ ተገፍፎ ወደ ምድር ተጥሎ በቦታውም ቅዱስ ሚካኤል የተሾመበትን ዕለትን አስባ በታላቅ ድምቀት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታከብረዋለች ፡፡ ሁለተኛው እስራኤላውያን በግብፅ በባርነት ቀንበር ተይዘው በስቃይ መከራ ፀንቶባቸው ሲኖሩ ሳለ ዕንባቸው መንበረ ጸባዖት ደርሶ እግዚአብሔር ሊቀ ነቢያት ሙሴን አሥነስቶ ባሕረ ኤርትራን ከፍሎ ካሻገራቸው በኋላ በሲና በርሐ ለዐርባ ዘመናት ሲጓዙ ቀን በደመና ሌሊቱን በብርሃን እየመራ ያደረሳቸው ቅዱስ ሚካኤል በመሆኑ ይሄንን ዕለት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስባ በታላቅ ድምቀት ታከብረዋለች ፡፡ ሦስተኛው ዱራታዎስንና ሚስቱ ቴዎብስታ የቅዱስ ሚካኤል የበዓሉን መታሰቢያ ያደርጉ ነበር ነገር ግን ለበዓሉ መታሰቢያ የሚያደርጉበትን እስኪያጡ ድረስ በቸገራቸው ጊዜ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በታላቅ መኮንን አምሳል ተገልጾ የታደገበትን ዕለት ቅድስት ቤተ ክርስቲያ በታላቅ ድምቀት ታከብረዋለች ። አራተኛው እስራኤላውያን የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግረው ወደ ተስፋይቱ ምድር ከገቡ በኋላ የኢያሪኮን ከተማ ለመውረስ በተዘጋጁበት ወቅት ቅዱስ ሚካኤል የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ ይዞ ለኢያሱ ወልደ ነዌ በሰው አምሳል በተገለጠ ጊዜ ኢያሱ “ ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ? ” አለው ፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም “ እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ነኝ አሁንም ወደ አንተ መጥቻለሁ ” አለ ኢያሱም ወደ ምድር በግንባሩ ተደፍቶ ሰገደ እግዚአብሔር የቅዱስ ሚካኤልን ክብር ገልጧል፡፡ ( ኢያ. 5፥13-14 ) ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን በየዓመቱ እነዚህን በዓላት በማሰብ ኅዳር 12 ቀን በታልቅ ድምቀት ታከብረዋለች፡፡ ከመላእክት አለቃ ከቅዱስ ሚካኤል ከበዓሉ በረከት ረድኤት ይክፈለን፤ ጥበቃውና አማላጅነቱ አይለየን አሜን ፡፡
Открыть в Telegramቅሩበ እግዚአብሔር መጋቢ ብሉይ ህዝበ እስራኤልን በፅቅ የመራ የድሆች አባት ለምስኪናኑ ቀድሞ 'ሚራራ ታሪክ ቀያሪው የሞት ደብዳቤን በህይወት የሻረ የባህራን ወዳጅ ስሙ የከበረ የአፎሚያ አባት የዳንኤል ደራሽ ደጉ ሚካኤል እልፍ እንባን አባሽ ..........ቅሩበ እግዚአብሔር..... የነፀብራቅ ዝናር በወገቡ ታጥቆ ልጆቹን የሚያድን ከዳቢሎስ ነጥቆ በእሳታዊ አክናፍ ቀድሞ እየጋረደ ሐሩሩ በረሃ ቀዝቅዞ በረደ ከተስፋይቱ ምድር እየመራ አገባን ፍቅርህ ነው ሚካኤል ዛሬ የሚያስነባን ኤርትራን ከፍለኸው በደረቅ አልፈናል ከሙሴ ጋር ሆነን ጥልቁን ተሻግረናል በአለቱም ውሃ ነብሳችን 'ረክቷል ያወረድከው መና እጅጉን በርክቷል በህይወታችን ውስጥ በእያንዳንዱ ቅፅበት እኮ የቱ ጋር ነው አንተ የሌለህበት አሳድገኸናል በፍቅርህ አቀማጥለህ የታመነብህን መች ታውቃለህ ጥለህ የእመቤቴ ወዳጅ የልኡል ባለሟል በእንባ የነገርንህ የጠየቅንህ ሰምሯል ✍ Ayni✍
Открыть в Telegramይድረስ ለሊቀ ፡ መላእክት ፡ ቅዱስ ፡ ሚካኤል #በዚህች_ቀን_ያውም_ለአንተ_ክብር #ተጻፈ፦ ከአንዱ ፡ ልጅህ ፡ ወልደ ፡ ገብርኤል ) ፧ ታውቀኝ ፡ የለ ~ የሰዓታቱን ፡ ደውል ~ ፍጹም ፡ ሳልታገስ ፣ ገስግሼ ፡ ነበር ~ ለሊቱን ፡ ሳልፈራ ~ ከመቅደሱ ፡ ምድረስ ፤ ፧ ስጋዬን ፡ ለማሰብ ~ ለአፍታ ፡ እንኳ ፡ ሳ'ልሰንፍ ፣ ልቤ ፡ እየቸኮለ ~ ለቅኔው ፡ ስሰለፍ ፤ ፧ #እንዲህ_እንደዛሬው ~ ከአልጋዬ ፡ ሳልውድቅ ~ ደዌ ፡ ሳይጠናብኝ ፣ በወደድኩት ፡ አካል ~ ፍቅርን ፡ በማለቴ ~ ጥላቻ ፡ ሳይቀጣኝ ፤ ፧ ደዌ ፡ ደንድኖ ~ ጤናዬ ፡ ሲከዳኝ ፣ ከአልጋዬ ፡ እያማጥኩ ~ ቅዳሴው ፡ 'ሚሰማኝ ፤ ፧ መንፈሴ ፡ ታመመ ~ እሾህ ፡ ወጋው ፡ እግሬን ፣ ደፍሬ ፡ እንዳልመጣ ~ አሰለለው ፡ አቅሜን ፤ ፧ ናርዶስ ፡ ሰውነቴ ~ ጠረኑ ፡ ከረፋ ፣ ጊዜ ፡ እምነትን ፡ ሲሽር ~ የማምነውን ፡ ሳጣ ~ የሚያምነኝም ፡ ጠፋ ፤ ፧ #እንኳን_ላሳደከኝ ~ ከደጅህ ፡ ተጥዬ ~ ያለ'እናት ፡ ያለ'አባት ፣ እኔ ፡ አውቀው ፡ የለምውይ ~ #ሚካኤል ፡ ለሚልህ ~ ስታድል ፡ ምህረት ፤ ፧ #ለምን ? ከ'አልጋ ፡ ተውከኝ ~ ነገድ ፡ እንደሌለው ~ እንደ ፡ ከዳተኛ ፣ ያለ'አንዳች ፡ ጠያቂ ~ ነሳህኝ ፡ መጽናኛ ፤ ፧ #ለምንድን_ዝም_አልከኝ ~ ነፍሴ ፡ ቅኔ ፡ ልትዘርፍ ~ ቀንህን ፡ ስናፍቅ ፣ ምስጋናን ፡ ልሰዋ ~ የጌታ ፡ ቀን ፡ ብዬ ~ በጉጉት ፡ ስጠብቅ ፤ ፧ #እንዴት_ችላ_አልከኝ ~ ዘምር ፡ ዘምር ፡ ሲለኝ ~ ልቤን ፡ ዜማ ፡ ሞልቶት ፣ ለክብርህ ፡ የቆመ ~ ዝናህን ፡ ሊናገር ~ ሕዝብ ፡ በሞላበት ፤ ፧ #እንደምን_አራቀኝ ~ ደዌ ፡ በእኔ ፡ ጠንቶ ~ ለፍቅር ፡ ብተጋ ፣ ምህረትህ ፡ ሳጣ ~ እሞታለው ፡ ብዬ ~ ለምን ፡ ነፍሴ ፡ ሰጋ ፤ ፧ #እኔ_እውቅህ_የለ ~ እንኳን ፡ ልቡ ፡ አዝኖ ~ ቃላት ፡ እያማጣ ~ ማረኝ ፡ ላለህ ፡ ቀርቶ ፣ እንባ ፡ እያዘነበ ~ ከመቅደሱ ፡ ደፍ ፡ ላይ ~ በፍቅር ፡ ተደፍቶ ፤ : ትደርስለት ፡ የለ ~ ከአፉ ፡ ቃል ፡ ሳይወጣ ~ ከልቦናው ፡ ፈጥነህ ፣ ክንፍህን ፡ እያማታህ ~ እንባውን ፡ አብስህ ~ የምታማልደው ፡ ከአምላክህ ፤ ፧ #ታዲያ_ለምንድን_ዝም_አለከኝ ~ ተራዬ ፡ ነው ፡ ብዬ ~ አልጋዬን ፡ ልሸከም ፣ ምልጃህን ፡ ታምኜ ~ ከጨለማ ፡ እልፍኜ ~ ተግቼ ፡ ስጠብቅ ~ አንተም ፡ አልመጣህም ፤ ፧ #እናም_በእኔ_በኩል °°°°°°°°°°°°°°°°°°° ፧ #ዛሬ ፡ በክብርህ ፡ ቀን ~ መቅደስህን ፡ ልሳለም ~ ፍቅርህ ፡ ግድ ፡ ቢለኝ ፣ በማፍቅረ ፡ የዛለው ~ ስጋዬ ፡ አቅም ፡ አጣ ~ የጥንቱን ፡ አስበህ ፡ እንዳትቀየመኝ ፤ ፧ #ሚካኤል_አባቴ !! እኔ ፡ አልመጣም ፡ ዛሬ ~ ጉብዝናዬ ፡ ረግፏል ፣ ያሳደከው ፡ ልጅ ~ ከወገን ፡ ርቆ ~ ብቻውን ፡ ቁጭ ፡ ብሏል ፤ ፧ " መኑ ፡ ካመከ" ፡ ዜማ ~ በሩቅ ፡ እየሰማው ~ ደጅህን ፡ ብናፍቅ ፣ መምጣት ፡ ቢሳነኝ ፡ ነው ~ በጨለማው ፡ ስፍራ ~ ከአልጋዬ ፡ ተኝቼ ~ አንተን ~ 'ምጠብቅ ፤ ፧ ፧ #ና_ና_ና_ሚካኤል_ና_ና ~ አዝኛለሁና ፡ በ'አንተ ፡ ልጽናና ፤ ፧ ድምጽ ፡ በሌለው ~ እልልታ ፡ ታጅቤ ~ በናፍቆት ~ ስጠራህ ፣ በእንባ ፡ ተጠምቄ ~ ስዘምርልህ ፣ ና ፡ ሚካኤል ፡ ና ~ ድረስልኝ ፡ ፈጥነህ ፤ ፧ ለአምላኬ ፡ ቃሌን ~ እንድታደርስልኝ ፣ ልጅህ ፡ ነኝ ፡ አባቴ ~ ፈጥነህ ፡ ቅረበኝ ፤ ፧ #ናፍቆቱ_ጠናብኝ ~ የደጀ ፡ ሰላሙ ~ የአባቶች ፡ ምርቃት ፣ የእናቶች ፡ ሽርጉድ ~ ትህትና ፡ የሞላበት ፤ ፧ የሕጻናት ፡ ዝማሬ ~ የሰንበት ፡ ተማሪው ~ ያሬዳዊ ፡ ዜማ ፣ ከአውደ ፡ ምህረቱ ~ በእልልታ ፡ ታጅቦ ~ ጭብጨባው ፡ ሲሰማ ፤ ፧ #እንደምን_ልቻለው ~ ይህን ፡ ሁሉ ፡ ስርዓት ~ መቅደሱን ፡ ርቄ ፣ #እስከመች ፡ ልኖር ፡ ነው ? ከጨለማው ፡ እልፍኝ ~ እንዲህ ፡ ተደብቄ ፤ : #ና_ና_ሚካኤል_ና_ና ነጠላውን ፡ ባለብስ ~ እግሬ ፡ ጸንቶ ፡ ባይቆም ፣ ከትንሿ ፡ አልጋዬ ~ በደዌ ፡ ብወድቅም ፣ ዝክርህ ፡ ለማሰብ ~ በጭራሽ ፡ አልደክምም ፤ ና ና ና ና #ሚካኤል_ና_ና ረዳት ፡ የሌለኝ ~ ብቸኛ ፡ ነኝና ና ና ና ና እግሬ ፡ እስኪጸና ~ መንፈሴ ፡ ጠንከሮ ~ አልጋዬን ፡ እስካዝል ፣ ከአምላክህ ፡ ማልደህ ~ ጥላቻን ፡ አርቄ ~ መልክህን ፡ እስክመስል ፤ ና ና ና ና #ሚካኤል_ና_ና ፣ አዝኛለውና ፡ በአንተ ፡ ልጽናና ፤ ፧ ፧ ፧ #ሚካኤል_አባቴ_በምህርት_ቅረበኝ !!! : ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ 📢በየቀኑ ኦርቶዶክሳዊ ሥነ-ጹህፎች ለማግኘት ቻናላችንን ይ🀄️ላ🀄️ሉ 👇👇 💚 @orthodoxawi_gtm 💚 💛 @orthodoxawi_gtm 💛 ❤️ @orthodoxawi_gtm ❤️ ይ🀄️ላ🀄️ሉ👆👆🤍
Открыть в Telegramየማይሰለቸኝ ወዳጄ ሚካኤል* ብሩቱ ሀያል ክንፉ ሰፊ እሰመ አምላክ ብርቱ ወዳጅ እረኛ ነው ለወዳጁ ጠዋት ማታ ክንደ ብርቱ ይው መጣሁ ከደጅህ ሰር ልማጸንህ ልለምንህ ዘውትር ብመጣ ከደጀ ሰላምህ ዘውትር ባደርሰም ውዴሴ ከአወደ ምህረትህ እመላለሳለሁ ከቤተ መቅተሰህ ኪዳን ላድርሰ እመላለሳለሁ ከቤተ መቅደሰህ ቅዳሴን ላሰቀድሰ እመላለሳለሁ በፀበልህ ድኜ ምሰክር ልሆንህ እመጣለሁ ደግሞ ማታ ተመልሼ የቀኑን ውሎየን ላዋይህ በእንባየ ታጅቤ እመጣለሁ ደግሞ ሲከፍኝ ሲከፍኝ አተም አሰለቸኝ እመጣለሁ ደግሞ ወዳጅ ሲጠፍብኝ ወዳጅ እንድሆነኝ ይሄው ዛሬም መጥቻለሁ አንተም አሰለቸኝ @orthodoxawi_gtm ባልታደለውም ልክ እንደ ወንድሜ ባልታደለውም ልክ እንደ እኅቴ ባልቦርቅ ከደጅህ በህፃንነቴ ባላድግ ከቤትህ እንደወንድሞቼ አንተ እንደሁ አሰለች ባልዘምር በቤትህ በደጅህ አድጌ ባልቋደሰውም አጋፔን አብሬ አንተ እንደው አሰለች ዘምሬ ዘምሬ ከቤተህ ርቅህ ቅዳሴው ኪዳኑ በዛብኝ እያልኩኝ ሰርቅ ከርሜ አንተ እንው አሰለች ከደጅህ መራቅን ሰንት ጊዜ ሸፈትኩ ፆም ፀሎት ሰግደቱ በዛብኝ እያልኩኝ ሰዓት ሰርቂያለሁ ድርሳንህ ሲነበብ ተምህርህ ሲነበብ ቁሜ ሰምቻለሁ ብዙ ልጆች አሉት ተብሎ ሲዘመር አብሬ ዘምሬ በዛው ቀርቻለሁ የሞቴን ደብዳቤ ተቀዶልኝ ሳለ ምስክር ሳልሆን በዛው ቀርቻለሁ በሰጠህኝ መክሊት ሳላገለግል ዘመናት ቢያልፎኝም ከደጅህ ሰላም አላሰቀረህኝም ከፉት ወድቄ አደራ ያልኩህን አላሰቀረህብኝም ለአለም ሰሮጥ አብርህ ትርጣለህ ተሰፍ ሰቆርጥብህ የተሰፍ ቃልህ ትመግበኛል ሞቴን ለቆፈረው መቃብር ደፈነሀል ሲርበኝ ሲጠማኝ መናን መግብሀል ሀዘኔን አፅናንተህ ዛሬ መጥቻለሁ አፅናኙ ሚካኤል ተራዳኝ ብያለሁ በል ልሳኔን ሙላው ምሰክር ልሆን ከቤትህ ቁሚያለሁ በእናቴ እቅፍሁኜ የመጣሁት ልጅህ ዛሬም መጥቻለሁ ወዳጄ ወዳጄ ልልህ እወዳለሁ አፅናኜ አአፅናኜ ሚካኤል ልልህ እወዳለሁ @orthodoxawi_gtm አንተ እንደው አሰለች ዛሬም መጥቻለሁ ያን ሁሉን ሀጢያቴ በክንፍህ ሸፍነህ ከሰው እኩል አርገህ ታቆማለህደግሞ በአውደ ምህረትህ እኔሰ ይገርመኛል የሚካኤል ሰራ እኔሰ ይደንቀኛል ቅዱሱ ወዳጄ ተራራላይ ያለው ሚካኤል አባቴ ከመንበርህ በራፍ ቁጭብየ በድፍረት መቼ ተፀየፈከኝ ሚካኤል በእውነት ቃላት እያጣሁኝ ያደረክልኝ መመሰከርአቃተኝ ኮልታፍ ብሆንም ሀጢያት ያጎደፈው አማላጅህ መሆንህ መቼም አልክደውም መላኩ ሚካኤል ገናና ነው ሰምህ ይርቃ ዲያብሎሰ ሰምህ ሳወድሰ አንተን ተገድፌ ተናንት አልፌዛሬን አይቻለሁ ክንደ ብርቱ ሀያል ወዳጅ ለትውልዱ ደግሞ እመጣለሁ እግዚአብሔር ቢፈቅድ የዝቋላው አባት ክብሩን ልመሰክር ዳግም እመጣለሁ ሰማእቷ አርሴማ ያረከችልኝ ዘናዋን ልናገር አልቀርም እመጣለሁ ጥበብ ቅኔ የሞላኝ ክርሰቶሰ ልመሰክር ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን !! ✍ ተፃፍ ያህዌህ ንሲ ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ 📢በየቀኑ ኦርቶዶክሳዊ ሥነ-ጹህፎች ለማግኘት ቻናላችንን ይ🀄️ላ🀄️ሉ 👇👇 💚 @orthodoxawi_gtm 💚 💛 @orthodoxawi_gtm 💛 ❤️ @orthodoxawi_gtm ❤️ ይ🀄️ላ🀄️ሉ👆👆🤍
Открыть в Telegramየቅዱስ ሚካኤል ግጥም(ሥነ-ጹህፍ) አሸን መሰናክል በጫንቃዬ አዝዬ መቆም እስኪከብደኝ በፈተና ዝዬ እየዳኹኩ በጉልበት - ስቆም ምስልህ ፊት ሚካኤል አባቴ ተልጦ ይረግፋል የውድቀቴ ቅርፊት በጸሎቴ መሀል የሀሰትን መና ሽቅብ አንጠልጥሎ ሰቅሎ ከደመና "ይብቃህ ዳዊት መድገም - ተው ውዳሴ ማርያም ምስጋና፣ መሻትህ - ደርሷል ከአርያም ተመልከት ወደ ላይ - አንጋጥጥ በጥብቅ አየህ በረከትክን አንተን ሲጠብቅ" እያለ ይጮኻል - ከንቱ ወናፍ ላንቃ ከመች ጀምሮ ነው ጸሎት የሚቋረጥ ምስጋናስ ሚበቃ? እንጃ ግራ ገባኝ አለማወቅ ጎዳኝ ሚካኤል ረዳቴ - ዞርኩኝ ወደ ምስልህ አሳቼን አየኹት ሲንፈራገጥ ከእግርህ በስምህ ልዘክር - ካለኝ ላይ ቀንሼ በደስታ እያበራኹ ከደጅህ ደርሼ ስከፍት ሞሰቤን እጄን እያነቀ በአዛኝ ከንፈሩ የፌዝ እየሳቀ የኑሮን ውድነት እየዘረዘረ "ገነት ለገባ ነፍስ - ጸድቆ ለበረረ ገንዘብ የሚያባክን ምጽዋት ምን ሊበጅ? ከሞት አያነቃ ህይወት አያደረጅ" ይለኛል አስሬ እየዘጋ መንገድ ከመቼ ወዲህ ነው ምጽዋት ተለግሶ ውድቀት የሚታጨድ? እንጃ ግራ ገባኝ አለማወቅ ጎዳኝ ሚካኤል አጋዤ ምስልህን ስታቀፍ ጠላቴን አየሁት ከመኖር ሲቀረፍ ክብርህ ያልገባቸው ምልጃህን ሊያጎድፉ ጥቅስ እያጣቀሱ ቃል ሲለፈልፉ ላስረዳቸው ስጥር ገድልህን አንብቤ እንድትገልጥላቸው ስጽልይ በልቤ የኔን እየተው ሊጫኑኝ በጩኸት አፋቸው ደጋግሞ በውድቀት ሲከፈት መዳረቅን ሽሽት ስሄድ ጥያቼው እየተዘባበቱ በጉድፍ ቃላቸው መክሰሬን ሲገልጹ አንተን በማክበሬ የፌዝ ሳቅ አንግቤ - ሳያቸው ዞሬ "ሂድና በላቸው ጥርሳቸውን አርግፍ እንዴት ዝም ትላለህ - ክብሬ ሲጎድፍ" የሚል ቁጣ ትዕዛዝ - ገባ ወደ ዕዝኔ መቼ ይሆን ደግሞ ስላንተ መምታትን የተማርኩት እኔ? እንጃ ግራ ገባኝ አለማወቅ ጎዳኝ አልመስልህ አለኝ እውን ያንተ ቃል ለስምህ መሞት እንጂ - መግደል ያጸድቃል? ሚካኤል አዳኜ አወጣኹ ምስልህን - ኪሴ ውስጥ መዝዤ አነቀኝ አንዳች ኃይል - ቀረኹኝ ፈዝዤ ባጣ መታገያ አቅም - ወረደ እንባዬ ብቻ ግን ደስ አለኝ - አልሳትኩም ተታልዬ ልጅህን የማትተው በፈተና ቃርሚያ አዳንከኝ ሚካኤል ልክ እንደ አፎሚያ አሸን መሰናክል በጫንቃዬ አዝዬ መቆም እስኪከብደኝ በፈተና ዝዬ እየዳኹኩ በጉልበት - ስቆም ምስልህ ፊት ሚካኤል አባቴ ተልጦ ይረግፋል የውድቀቴ ቅርፊት ✍#ኤልዳን ➮ኦርቶዶክሳዊ ሥነ-ጹህፎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይ🀄️ላ🀄️ሉ 👇👇 💚 @orthodoxawi_gtm 💚 💛@orthodoxawi_gtm💛 ❤️@orthodoxawi_gtm ❤️
Открыть в Telegramጎጆ ቀለስኩልህ ሚካኤል🧎➡️💒 በአውላላ ሜዳ በጠራራ ፀሐይ ከአስፓልቱ አጠገብ ስኖር ጎዳና ላይ የበጋውን ንፋስ በዙሪያዬ ከቦኝ እንደ ዥዋዥዌ ወዲያ ሲወስደኝ፡፡ ...................ወዲህ ሲመልሰኝ ዝናቡ በተራው ጉዴን ተመልክቶ ...................ጉድፌን አፅድቶ ይወደኝ ይመስል ልብሴን ያጥብልኛል ጎጆዬን አፈራርሶ በብርድ ይገርፈኛል፡፡ ከዚህ የባሰ ግን ሰዉ ነው 'ሚገርመኝ በነጋ በጠባ መተንፈሻ ያሳጣኝ፡፡ ስለተናገርኩኝ ማጣት መከፋቴ የእውነት ስለኖርኩኝ ውሸትን ጠልቼ አፋቸውን ሞልተው እብድ ነው ይሉኛል አንዳንዴ ሲያሻቸውም ድሃ ነው ይሉኛል፡፡ የሆነው ሆነና ቅር አላለኝም አጣሁኝ ብዬም አላማረርኩም ጌታ እንዳስተማረኝ ለበጎ ነው ብዬ የማይቻል የለም እኖራለህ ችዬ፡፡ ይሄውልህ ግን ሚካኤል ሆይ... የሰው ልጅ ሲሸሸኝ ማንነቴን አይቶ ሰላምታ ሲነፍገኝ ኑሮዬን ተመልክቶ አንተ ግን አንተ ነህ የአምላክ መልእክተኛ ሁሌ 'ምትጠብቀኝ መቼም የማተኛ፡፡ ምንም ሳይገድብህ ከቤቴ ገብተሀል ድሃዋን ጎጆዬ በፍቅር ጎብኝተሀል፡፡ እናም ሚካኤል ሆይ.... ከኔ እንዳትርቅ ስለሳሳሁልህ በንፁህ ልቤ ውስጥም ጎጆ ቀለስኩልህ፡፡ ✍ ✍ በሰመረ ፍስሃ ✨ ➷ኦርቶዶክሳዊ ሥነ-ጹህፎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይ🀄️ላ🀄️ሉ 👇👇 @orthodoxawi_gtm 💚 @orthodoxawi_gtm 💛 @orthodoxawi_gtm ❤️
Открыть в Telegramአሻግረን ባህሩን ! ለነፃነት ያልነዉ፣ የግብፅ ህልም እንጀራ ፣ ባርነት ሆኖብን፤ የሸጥነዉም ዮሴፍ፣ በሕሊና ወንበር ፣ እየፈረደብን፤ በባዕድ ሀገር በዝተን ፣ የበረከት ፈንታዉ ፣ ጥሎን ከሥጋቱ፥ የወለድነዉን ልጅ ፣ መልሰን ከጭቃዉ ፣ ረግጦ መጫወቱ፥ ያኘክነዉም ጮማ ፣ ከጥርሳችን ሳይወርድ ፣ የመርገም ሞት ጠርቶ፥ የመኖር ህግ ሲጎድል፣ በሞት ተጠግቶ…ሞትን ተመክቶ፤ ከአስሩ መቅሰፍት፣ ቸነፈር ረሃቡ ፣ ተዓምር ድንቃ ድንቁ፤ አንድ አማኝን አጥተዉ ፣ በኩረ ሞት እስኪደርስ፣ ድንጋን ላይ ሲወድቁ፤ የምፅዓት ምልክት፣ በበሮቹ መቃን፣ ቢቀባ በበግ ደም፤ የግብፃዉያን ዓይን- የጡቡን ግንብ እንጂ ፣ ይህን ማየት አይወድም። የተፈራዉ ደርሷል፣ ሞት ገብቷል በየቤት ፣ ሀገር ተሸብራል፤ የመቅሰፍት ወላፈን ፣ መጥቶ ሲጥል እንጂ፣ ሲሄድ ተሰዉሯል፤ ለእምነት የሚሆን ፣ የበግ ደም ያለበት ፣ የእምነት ፍሪዳ፥ አንሶ ዋይታ ሆኗል፣ በፈረኦን ቤትም ፣ በእስራኤልም ጓዳ፤ ለነፃነት ብለን ፣ ሌሊት የተጓዝነዉ፣ ሌሊቱ ረዝሞብን፥ ከቀመስነዉ መና ፣ የለመድነዉ ሽንኩርት ፣ ያምናዉ አይሎብን፥ የጨረቃዉ ድምቀት፣ የኮከቡ ምሪት ፣ የሌሊቱ መንገድ፥ አንተ ካላበራህ ፣ ለመቆም አይሆንም፣ እንኳንስ ለመሄድ፤ የጪንጫ ላይ ወሃ፣ አይፈልቅም ያለ አንተ ፣ ለጥማችን አይሆን፤ የበረሃ ልብሳችን ፣ ለቀን አይበረክት፣ አያረካ ለዓይን፤ የገመጥነዉ ሥጋ ፣ ከጉሮሮ ሳይወርድ ፣ ሆኖብን ሞት ጠሪ፤ በሄድንበት ጉዞ፣ ያለ ሩኅሩኅ መልአክ ፣ ያለ መንገድ መሪ። ከፊታችን ቆሟል ፣ የኤርትራ ባህር ፣ ግንብ ሆኖ በመፍሰስ፤ ከኋላችን መጥቷል ፣ የፈረኦን ሠራዊት ፣ ጦር ሰብቆ በፈረስ፤ ከሁለቱም በፊት ፣ ከሙሴ በትር ጋር ፣ ሚካኤል ሆይ ድረስ። በጦርም በባህርም ፣ የኢትዮጵያ ድንኳን፣ አይተህ መሸበሩን፤ ልንሰጥም ነዉና፣ መልአከ ምህረት ሆይ ፣ አሻግረን ባህሩን። ኢትዮጵያ ሆይ ትንሳኤሽን ያሳየኝ !🙏🏻 ➷ኦርቶዶክሳዊ ሥነ-ጹህፎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይ🀄️ላ🀄️ሉ 👇👇 💚 @orthodoxawi_gtm 💚 💛@orthodoxawi_gtm💛 ❤️@orthodoxawi_gtm ❤️
Открыть в Telegramሕይወትና እጣፈንታ ሕይወት እጣፈንታ እጣፈንታም ሕይወት አይኖርም ማንም ሰው በራሱ ፍላጎት ሕይወት እኮ ቅኔ ምኗም ማይታወቅ ልክ ሲደርሱባት አቅጣጫዋን ምትስት ግራ የገባው ድንብርብር አለም በዚ ልድፈን ሲባል በዛ የሚጎድል ሕይወት ፈተና ናት እልፍኝ ትልቅ ገደል ያወቀባት አውቆ ድልድይ ሚሰራባትበድልድዩም ሁሌ ሚመላለስባት ላላወቀው ደሞ ሕይወት መስጠሚያው ከጥፋት ገደል ውስጥ ከታ ምታስቀረው አቤቱ ጌታ ሆይ ማስተዋሉን ስጠን ገብተን ምንወጣበት መሄጃው በር ጠፋን አዳምን ልጄ ሆይ ብለህ እንደፈለከው ቃልህን አክብረህ ደምህን እንዳፈሰስከው ዛሬም ናልን በለን ከወዴት ናችሁ በቀኝ ወይስ ግራ በየት ነው ውሎአችሁ ብለህ አፈላልገን ከቤትህ ውስጥ ሆነን ጠፍተናል ልጆችህ ላንተ ምን ይሳናል ሁሉን ለሚቻልህ ክብርና ምስጋና አቤቱ ይድረስህ 🙏🙏🙏 ናርዶስ ✍✍
Открыть в Telegramአትፍረዱ🙏 ትዕግስቱን ስጠኝ የምልፍበትን ለበጎ ነው ብዬ የምኖርበትን🤦♀ ነውና ነገሩ ያላሰብነው የሚታስብበት እውነት የተናገር ፍፁም የማይወደድበት አቅም ስጠኝ ችይ የማልፍበት። አይቶ እንዳላዬ የሚያልፍ ልብ ስጠኝ ሰው ከእኔስ ከፍቷል ጌታዬ አበርታኝ። ምንም ቢከፋኝ አባቴ አንተ አለህ አንተማ እንደሰው መቺ ትሆናለህ አምንሀለሁ ደግሞም ዛሬም ታሳልፈኛለህ። እንቅፋቴ በዝቷል ሁሉም ይመታኛል ሀጥያቴን እያሰቡ ሰው ይፈርዱብኛል እኔማ እላለሁኝ እግዜር ይምረኛል። ይሁን እስኪ🥹 ሀጥያት ስሰራ እንጂ ንስሀ ስገባ አላዩኝም አወጥተው ጣሉኝ እንድ ከጠላቴ አላስጣሉኝም። ፈረዱብኝ በእኔ ፈረዱብኝ በልጅህ መድሀኒያለም አንሳኝ መገፋቴን አይተህ ምላሽ ባልሰጣቸው ደጋግመው ወቀሱኝ ሀጥያተኛ ናት ብለው ከዳር አቆሙኝ። ሀጥያቴን አይተዋል በደሌን ሰምተዋል ንስሀ መግባቴን ግን መቺ ጠይቀዋል ከእኔ የፈረዱት በእነሱ እንደሚደርስ እረስተዋል🙏 ይገርመኛል እንደው አምላኬ ሁሉም ብቻ ስለምታሳልፋኝ አሁንም ዘላለም። ዝም ብላቸው በዳይ እኔ ሆንኩኝ ሚካኤልን አባቴ ሰዎች ፈረዱብኝ🥺 ሌላ ምንም አልል ትዕግስቱን ስጠኝ። አንተ ታስችላለህ ዳግም ትሰራለህ ሀጥያተኛ ናት ብለህ መቺ ትተወኛለህ እንደሰው አይደለህ ይቅር ትለኛለህ። ቢከፋኝ፣ብወድቅም፣ ሰው ባይኖረኝም አንተ ሰላለህኝ መቼም ተስፋ አልቆርጥም😊 ብቻ እግዚያብሔር ትዕግስቱን ስጠኝ ከዚህ በላይ ምንም ፀሎት የለኝ አላወቁም ስፈርድባቸው እኔም እንደተፈረደብኝ በሰው ላይ የወቀስኩት እንደደረሰብኝ አሁን ላይ ተምሬ መፍረድ እንዳቆምኩኝ። ነገ ምን እንደሚያመጣ አታውቁምና አትፍረዱ መፈረድ አሁንም አለና። ብቻ ግን ይከብዳል በጣም ያስከፋል በሰው ላይ መፍረድ በእራስ ያስፈርዳል። ''ሰዎች ፈረዱብኝ አንተ ግን አዳንከኝ(2) ጌታዬ ሆይ ተመስገንልኝ አምላኬ ሆይ ተመስገንልኝ ሌላ ምን ቃል አለኝ''🥹 አትፍረዱ አትፍረዱ አትፍረዱ🥺🙏 ✍Nave(Mekdi)🦋 📢በየቀኑ ኦርቶዶክሳዊ አስተማሪና እውነተኛ ታሪኮችን ፣ ሥነ-ጹህፎችን ፣ ለማግኘት ቻናላችንን ይ🀄️ላ🀄️ሉ 👇👇 @orthodoxawi_gtm @orthodoxawi_gtm @orthodoxawi_gtm ይ🀄️ላ🀄️ሉ👆👆
Открыть в Telegramምስጢራዊ አደራ ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችሁ ጋር ይሁን የእግዚአብሔር ቤተሰቦች🙏 እንደምታውቁት #ምስጢራዊ_አደራ_የተሰኘው_ድንቅ_መንፈሳዊ_ልቦለድ ክፍል 18 ላይ እንደተቋረጠ ነው። የተቋረጠበት ምክንያት ደራሲው ማለትም ደራሲ መልካሙ ስሜነህ እንደነገረን.... በተለያዩ Social ሚዲያዎች... Tiktok, Telegram, YouTube, Facebook ላይ ብዙ ሰዎች Copy እያደረጉ የኔንም ስም ትተው ስለሚለቁ እና በ Audio እና በ Video አቀናብረው ካለኔ እውቅና እና ፍቃድ የኔንም ስም ትተው ስለሚለቁት ነው በማለት ገልፆልናል። እናም በነዚህ ምክንያቶች የእርሱ የ Social ሚዲያዎች ቻናል ላይ መልቀቁን አቋርጦታል። ከዚህ ቀደም ፖስት ላይ👇 https://t.me/orthodoxawi_gtm/2163 እዳሳወቅናችሁ ድርሰቱን በመጽሐፍ መልኩ ለማዘጋጀት አስቧል። ያለን መረጃ ይኸ ነው ቤተሰብ። ወስብሐት ለእግዚአብሔር። ✍ Owner ✍ @YOHANNES_2421
Открыть в Telegram#ዳግሞ_አትበድይ_ክፍል_አራት_የመጨረሻው_ክፍል ….....… ውስጤ ሲቆርጥልኝ ከቅዱስ ራጉኤል ቤተ ክርስቲያን ቅጽር ግቢ ሳልወጣ የንስሐ አባት ለማግኘት ዓይኖቼን አዟዟርኩ። እግዚአብሔር መንገዴን አቅንቶት ኖሮ ፊታቸው ላይ የገርነትና የርኅራኄ ብርሃን የሚበራባቸውን አንድ አረጋዊ መነኩሴ አባት አገኘሁ። ተንቀጠቀጥኩ የእርኩሰት ሸክሜ በመነኩሴው ፊት እንዳልንቀሳቀስ አስሮኝ የነበሩ ቢሆንም በጥቁር ነጠላዬ ዕንባዬን እየጠረግኩ ሂጄ እግራቸው ስር ተደፋሁ። "አባቴ… እባክዎትን ያድኑኝ እኔ የኃጢአት ባሕር ያሰመጠኝ ረክሼ የኖርኩ ዕድሜዬን በዝሙት ያሳለፍኩ ሴት ነኝ" አልኳቸው ድምፄ በስቅስቅታ እየተቋረጠ። እኒህ አባት ግን አልገፈተሩኝም አልኮነኑኝም ይልቁኑ በሰፊው የክህነት ካባቸው ሸፍነው እንደ አባት አጽናንተው አስነሱኝ። ወደ ተረጋጋ ስፍራ ወስደውም የውስጤን ማዕበል ሁሉ በጥሞና አዳመጡኝ ሕይወቴን ስብራቴን ከእናት ከአባቴ ቤት መጥፋቴንና በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ያሳለፍኩትን ገሃነማዊ ሕይወት ዘርዝሬ ነገርኳቸው። ሁሉንም ሰምተው ሲያበቁ መጽሐፍ ቅዱስን ገልጠው ድምፃቸውን ዝቅ አድርገው መከሩኝ በተለይም በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያለውን "የጠፋው ልጅ" ታሪክ ሲያነቡልኝ፣ ውስጤ አዲስ ተስፋ መዝራት ጀመረ። """"""ልጄ ሆይ፣ ያ የጠፋው ልጅ የአባቱን ገንዘብ በዝሙትና በምናምንቴ ሕይወት አጥፍቶ በመጨረሻ እሪያዎች ከሚበሉት ቆሻሻ ምግብ ሊበላ በተመኘ ጊዜ ነበር የአባቱ ቤት ትዝ ያለው ። 'ከአባቴ ቤት እጀግ ብዙ እህል አለ እኔ ግን እዚህ በራብ እጠፋለሁ ተነሥቼም ወደ አባቴ እሄዳለሁ' አለ። አስቦም አልቀረ ወደ አባቱ ቤት ሄደ ገናም ሩቅ ሳለ አባቱ አየውና አዘነለት እየሮጠም አንገቱን አቅፎ ሳመው።" ብለው ነገሩኝ "አንቺም ዛሬ ወደ ልብሽ ተመለስሽ እግዚአብሔር አምላክ ንስሃሽን ተቀብሎሻል ስለዚህ #ዳግም_አትበድይ! አሁንም ሳታመነቺ ወደ አባትሽ ቤት ተመለሺ እግዚአብሔር መንገዱን ይከፍትልሻል" በማለት በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል አጽናንተውኝ የንስሐ ቀኖና ሰጥተውኝ በጸሎት አሰናበቱኝ። ከአዲስ አበባ ወደ ባሕር ዳር የሚወስደውን አውቶቢስ ስሳፈር ልቤ በፍርሃትና በጭንቀት ይወራጭ ነበር። "እንዴት አድርጌ አባቴ ፊት እቆማለሁ? እናቴስ ስታየኝ ምን ትለኝ ይሆን? ጎረቤትስ እንዴት ያየኛል?" የሚሉ ጥያቄዎች በአእምሮዬ ነግሠውብኝ ነበር። ባሕር ዳር ደርሼ ወደ ልጅነት ቤቴ አካባቢ ስቃረብ እግሮቼ ሊታዘዙኝ አልቻሉም እየተንገደገድኩ በዕንባ በተሸፈኑ ዓይኖቼ የቤታችንን በር አንኳኳሁ። በሩን የከፈተችው እናቴ ነበረች ለአፍታ አተኩራ አየችኝ የኑሮ መከራና የሳንባ ምች ህመም ያከሳውን ያጎሰቆለውን ፊቴን ስታስተውል ጩኸቷኝ ለቀቀች። "ልጄ! የጠፋችው ልጄ" እያለች እቅፍ አደረገችኝ የክፍል መጋረጃውን ሰንጥቆ የወጣው አባቴም እኔን ሲያየኝ መቆም አቃተው። በጉልበቴ ተደፍቼ "አባቴ… በሰማይም በአንተም ፊት በደልኩ ከእንግዲህ ልጅህ ልባል አይገባኝም" ብዬ ይቅርታ ለመጠየቅ ስንሰቀሰቅ አባቴ ግን አላስጨረሰኝም። በፍቅር አንሥቶ አቀፈኝ የአባቴ ዕንባ በትከሻዬ ላይ ሲፈስ ተሰማኝ። አባቴ ወዲያውኑ ነበር ዘመዶቹን ሁሉ የጠራቸው። "ይህች ልጄ ሞታ ነበር ሕያው ሆናለች ጠፍታም ነበር ተገኝታለችና ደስ ይበላችሁ!" በማለት ትልቅ ድግስ ደገሰ። ዘመድ አዝማድ የሰንበት ትምህርት ቤት ጓደኞቼ ሁሉ መጥተው በፍቅር ተቀበሉኝ ማንም የት ነሽ ምን ሆንሽ አላለኝም በፍቅር ማዕበል ውስጥ ዋኘሁ። ዛሬ ያ መጥፎና ጨለማ ጊዜ አልፏል ያንን የኃጢአትና የውርደት ዘመን ጨርሼ ረሳሁት ወደ አባቴ ቤት ወደ ቤተ ክርስቲያኔ ተመልሼ ሙሉ ሰላምና ደስታ አግኝቻለሁ። አሁን እኔ አዲስ ፍጥረት ነኝ በአምላኬ ቸርነት በንስሐ አባቴ ምክርና በወላጆቼ ፍቅር ታጥቤ ካለፈው የሴተኛ አዳሪነት ሕይወት ወጥቼ አዲስ ሕይወት መኖር ጀምሬያለሁ። #ተፈጸመ እግዚአብሔር አምላክ ሁላችንንም ከጠፋንበት ወደ ቤቱ መልሶ ለንስሃ ሞት ያብቃን። 📢በየቀኑ ኦርቶዶክሳዊ አስተማሪና እውነተኛ ታሪኮችን ፣ ሥነ-ጹህፎችን ፣ ለማግኘት ቻናላችንን ይ🀄️ላ🀄️ሉ 👇👇 @orthodoxawi_gtm @orthodoxawi_gtm @orthodoxawi_gtm ይ🀄️ላ🀄️ሉ👆👆
Открыть в Telegram#ዳግሞ_አትበድይ_ክፍል_ሦስት(➌) ……..አንድ ቀን እንደልማዴ መርካቶ አመዴ ገበያ ፊት ለፊት ገባ ብሎ ከሚገኘው ወንዶችን እያፈራረክሁ ዝሙት ከምፈጽምባት የኃጢያት ምሽጌ ከሆነች አልጋየ ላይ በዕለተ ሰንበት በሌሊት ተነስቼ በእርኩሰት የጠቆረውን ማንነቴን በነጠላ ሸፍኜ ወደ ቅዱስ ራጉኤል ቤተ ክርስቲያን ገሰገስኩ። እግዚአብሔር ያደለው ወንዱም ሴቱም የቅዳሴውን ተሰጥኦ እየመለሰ ሲያስቀድስ ከሩቅ ይሰማል ። እኔም ወደ ቤተ ክርስቲያኑ በር ስደርስ ጉልበቴ እየተንቀጠቀጠም ቢሆን ተሳለምኩ ከፊት ለፊቴ ያለውን መስቀል ለማየት ድፍረት አጣሁ። ዞር ብየ ከግንቡ ስር ባዶ ቦታ ፈልጌ ቆምኩ ራሴን ለማረጋጋት ብሞክርም ኃጢያቴ ከፊቴ ድቅን እያለ ዐይኖቼ የዕንባ ጎርፍ ማውረዳቸውን ቀጠሉ ። አምላኬ ሆይ መቼ ነው ከዚህ የምትገላግለኝ ? "የመዳን ቀን አሁን ነው" ይል የለም መጽሐፍ ቅዱስ እባክህ ይብቃኝ ዳግም ወደ ጥፋቴ እንዳልመለስ እርዳኝ እያልኩ አነባለሁ። የዝሙት ሥራ መረረኝ ጥዋት እና ማታ ጸሎት የሚደርስበት እንግዳ የሚስተናገድበት የአባቴን ቤት እናፍቃለሁ። ግን እንዴት አድርጌ ልሂድ ? የሰማያዊ አባቴን ክብር ያዋረድኩ እሱም ከውስጡ አውጥቶ የጠፋኝ ከሙታን የተቆጠርኩ እንዴት ፊቱ ልቁም ? ልቦናየ ……"ሂጂ ጥፊ ጻድቅ በሞላበት ከተማ ምን ትሰሪያለሽ ? አንቺ እኮ ለብዙዎች በዝሙት መውደቅ ምክንያት የሆንሽ ነሽ ሂጂ ብረሪ እንጂ " ይለኛል። እግሬ ደግሞ ተሳሰረ ዕንባየ ያለ ከልካይ ይፈሳል ወንጌል ተነበበ ከወንጌል በኋላ ለአጭር ደቂቃ እርፍ ብለን የተነበበውን ወንጌል መሠረት አድርገው የዕለተ መምህር ማስተማራቸውን ቀጠሉ ። ቃል በቃል መግለጽ ባልችልም አይሁድ "ዝሙት ስትሰራ አግኝተናታል " ብለው በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት ያቆሟትና ፍርድ እዲሰጣት ስለጠየቁባት ሴት ነበር። " ሙሴ በዝሙት ምክንያት የተገኘችውን በድንጋይ ተወግራ ትሙት ብሏል አንተስ ምን ትላለህ ? ብለው ጠየቁት። እሱም ወደ መሬት ጎንበስ ብሎ በጣቱ ጻፈና "ከእናንተ መካከል ኃጢኣት የሌለበት ቢኖር በድንጋይ ወግሮ ይግደላት" አላቸው። በእያንዳንዳቸውም ግንባር ላይ በደላቸው ተነበበባቸው ያኔ ሁሉም ሹልክ ሹልክ እያለ ሄዱ ። ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ወደ ሴትዮዋ እየተመለከተ አንቺ ሴት ከሳሾችሽ የት አሉ ?" ሲል ጠየቃት። እሷም "ጌታየ እኔ አላውቅም" ስትል መለሰች እኔም አልፈርድብሽም "#ዳግመኛ_አትበድይ ! በማለት አሰናበታት" ታሪኩ ይህ ነበር ከሞላ ጎደል። በአእምሮየ ተቀርጾ የቀረው " #ዳግም_አትበድይ " የሚለው ነው ። እናም ውስጤ እንዲቆርጥ ታገልኩ ዳግም ወደ ዝሙት እንዳልመለስ አይኖቼን ወደ ሰማይ አቅንቼ አምላኬን ከልቤ ተማጸንኩ። በዝሙት ምክንያት የተያዘችውን ሴት አስብኳት እኔ ግን ይብቃኝ መረረኝ ! አምላኬን ይቅርታ መጠየቅ አለብኝ ከእኔም አይፈርድብኝም እሱ ቸር ይቅር ባይ አምላክ ነው እያልኩ ከራሴ ጋር ሙጉት ገጠምኩ። ውስጤ ሲቆርጥልኝ ……… 👉 የመጨረሻው ክፍል 4⃣ ይቀጥላል......✍💔 📢በየቀኑ ኦርቶዶክሳዊ አስተማሪና እውነተኛ ታሪኮችን ፣ ሥነ-ጹህፎችን ፣ ለማግኘት ቻናላችንን ይ🀄️ላ🀄️ሉ 👇👇 @orthodoxawi_gtm @orthodoxawi_gtm @orthodoxawi_gtm ይ🀄️ላ🀄️ሉ👆👆
Открыть в Telegram