Посты канала Nuradis🥀(ኑርአዲስ)🥀منهج السلف
መልካም ለዋለልህ ሰው,,,,👇 ================== مَنْ صَنَعَ إِلَيْكُمْ مَعْرُوفًا فَكَافِئوه، فَإِنْ لَمْ تَجِدُوا مَا تُكَافِئُونَهُ فَادْعُوا لَهُ حَتَّى تَرَوْا أَنَّكُمْ قَدْ كَافَأْتُمُوهُ (رواه أبو داود والترمذي) ማንኛውም ሰው መልካም (ውለታ) ላደረገላችሁ (ምላሽ ስጡና) ካሳ አድርጉለት፤ ካላገኛችሁም (የምትከፍሉት ነገር ከሌላችሁ) ካሳ አድርጋችሁለታል እስከምትገመቱት ድረስ (በላቀ ሁኔታ) እሱኑ በመጥራት (በዱዓ) ምልሱለት። 👇👇👇👇👇 Https://t.me/Nuradis53 •════•••🌺🍃•••════•
Открыть в Telegramእስኪ ራሳችንን በሚዛን ላይ እናስቀምጥ! ⚖️ ✅ለዱንያ ጉዳይ ስንል በጣም እንደክማለን፣ እንለፋለን። ደክሞንም እንኳ የግድ የሚያስፈልገን ነገር ካለ ተገድደንም ቢሆን እንሰራለን። የገንዘብ ወይም የጥቅም ነገር ከሆነ ሌሊቱን 9 ሰዓት ተነስተን እንወጣለን፣ እንሰራለን፤ ለዓለማዊ ትምህርትም ካለ መሰልቸት እናጠናለን፣ እንለፋለን። ➡️የአኺራ ጉዳይ ሲመጣ ግን ታሪኩ ይቀየራል... ትንሽ ድካም ሲሰማን "ደክሞኛል" ብለን በዛው ራሳችንን እናሳርፋለን (እናደክማለን)። 👉የሱብሂ ሶላት፦ ለስራ ወይም ለጥቅም ሌሊት መነሳት የሚችል ሰው፣ ሱብሂን በወቅቱ ለመስገድ ሲሆን ይከብደዋል፣ ያመልጠዋል። 👉የጀመዐ ሶላት፦ የገቢ ምንጭ ወይም ስራ ቢሆን ድካምን ችሎ ከሀገር እንኳን ይወጣል። መስጊድ ሄዶ ጀመዐ ለመስገድ ሲሆን ግን ድካም ያስቆመዋል። 👉ዲናዊ ትምህርት እና ዳዕዋ፦ ለዓለማዊ ትምህርት የሚሰጠው ትኩረትና ጥረት፣ ለዲን እውቀት (ደርስ) ወይም ለዳዕዋ ሲሆን ይጎድላል፤ "ጊዜ የለኝም'' ወይም ደክሞኛል ይበዛል። እስኪ ራሳችንን እንፈትሽ ድካማችን እና ጥረታችን የትኛው ላይ ነው እየበዛ ያለው❓ ለዱንያ ወይስ ለአኺራ❓ አሏህ ለዲናችን እና ለአኺራችን የምንተጋ፣ ድካም የማይበግረን ያድርገን! 👇👇👇👇👇 Https://t.me/Nuradis53 Https://t.me/Nuradis53 •════•••🌺🍃•••════•
Открыть в Telegram♻️የአህባሾች ምላሽ ምን ይሆን❓❗️ 👉እኛ አሏህ ከአርሽ በላይ ነው ስንል፣ ጌታችን በቁርአኑ በበርካታ ቦታዎች የነገረንን እና መልክተኛው (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) በሐዲሶቻቸው ያረጋገጡትን እውነት ይዘን ነው። ➡️አህባሾችስ ለዚህ ምን ምላሽ ይኖራቸዋል? 👉በዱንያ ላይ "አሏህ ከአርሽ በላይ ነው" ያለውን አካል እንደ ሙጀሲም (አካላዊ መልክ አለው ባይ) ፈርጀው፣ ስንቱን ከእስልምና ውጪ አድርገው ነበር። ነገር ግን ነገ በትንሳኤው ዕለት የፍልስፍና ክርክር ሁሉ ያበቃል፤ እውነቱ በግልጽ ይወጣል። 👉ጌታችን አሏህ በእለተ ትንሣኤ ስለዚህ ጉዳይ ሲጠይቀን የሚኖረን ምላሽ ምን ይሆን? በዛን ዕለት ፍልስፍና ሳይሆን ቁርአንና ሐዲስ ይናገራሉ። 👌ለማንኛውም ነገ በጌታችን ፊት ለሚሰጠው ምላሽ ዛሬውኑ በሰከነና ከቁርአንና ከሐዲስ ጋር በተጣጣመ መልኩ በቂ ዝግጅት ማድረግ ይገባል። 👇👇👇👇👇👇👇 Https://t.me/Nuradis53 Https://t.me/Nuradis53 •════•••🌺🍃•••════•
Открыть в Telegramትዕቢት እና ሰዎችን መናቅን አስመልክቶ የተላለፉ የቁርአን አንቀጾችና የሐዲስ መልእክቶች,,,,, ولا تمش في الأرض مرحا إنك لن تخرق الأرض ولن تبلغ الجبال طولا [الإسراء: 37] በምድርም ላይ በትዕቢት (እየተንቀባረርክ) አትሂድ፤ አንተ ምድርን ፈጽሞ አትሰነጥቅምና፤ ተራራዎችንም ቁመትን አትደርስምና። إن الله لا يحب من كان مختالا فخورا [النساء: 36] አላህ ኩሩ የሆነን፣ ተመጻዳቂን ሁሉ አይወድም። ➡️ራስን በራስ ማጽደቅ እና መመጻደቅ የተከለከለ ነው። فلا تزكوا أنفسكم هو أعلم بمن اتقى [النجم: 32] ነፍሶቻችሁንም አታጥሩ (ንፁህና ከፍ ያልነን አትበሉ)፤ እርሱ አላህን ፈሪ ማን እንደሆነ ዐዋቂ ነው። ➡️እኛ ከሌላው እንበልጣለን ማለት የኢብሊስ (የሸይጧን) ባህሪ ነው። قال أنا خير مني خلقتني من نار وخلقته من طين [الأعراف: 12] (ኢብሊስ) “እኔ ከእርሱ እበልጣለሁ፤ ከእሳት ፈጠርከኝ፤ እርሱን ግን ከጭቃ ፈጠርከው” አለ። ➡️የብናኝ ያህል ኩራት ያለበት ጀነት ያስከለክላል። (ኩራት ማለት ሰዎችን መናቅ ነው) قال رسول الله صلى الله عليه وسلم: لا يدخل الجنة من كان في قلبه مثقال ذرة من كبر. قال رجل: إن الرجل يحب أن يكون ثوبه حسنا ونعله حسنة؟ قال: إن الله جميل يحب الجمال، الكبر بطر الحق، وغمط الناس. [رواه مسلم] የአላህ መልዕክተኛ (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፦ በልቡ ውስጥ የብናኝ ያህል ኩራት (ትዕቢት) ያለበት ሰው ጀነት አይገባም። አንድ ሰውም ሰውዬው ልብሱ ውብ እንዲሆን፣ ጫማው ውብ እንዲሆን ይወዳል (ይህ ኩራት ነውን?) ሲል ጠየቀ፤ እሳቸውም፦ አላህ ውብ ነው ውበትን ይወዳል፤ ኩራት ማለት እውነትን አለመቀበል እና ሰዎችን መናቅ (ዝቅ አድርጎ ማየት) ነው አሉ። ➡️ሰዎችን በንቀት መመልከት ለክፋት በቂ ነው። قال رسول الله صلى الله عليه وسلم: بحسب امرئ من الشر أن يحقر أخاه المسلم. [رواه مسلم] የአላህ መልዕክተኛ (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) አንድ ሰው ሙስሊም ወንድሙን መናቁ ለእርሱ (ለጥፋትና ለክፋት) በቂው ነው ብለዋል። ➡️በትዕቢት ራሱን ከፍ አድርጎ በመመጻደቅ ሲሄድ የነበረ ሰው ቅጣት قال رسول الله صلى الله عليه وسلم: بينما رجل يمشي في حلة تعجبه نفسه، مرجل جمته، إذ خسف الله به، فهو يتجلجل إلى يوم القيامة. [متفق عليه] የአላህ መልዕክተኛ (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፦ አንድ ሰው በልብሱ ተውቦ፣ ፀጉሩን አበጥሮ በራሱ እየተደነቀና እየተመጻደቀ ሲሄድ አላህ መሬትን አዘዛትና አሰመጠችው፤ እርሱ እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ ወደ መሬት ውስጥ እየሰመጠ ይቆያል። التكبر على الناس واحتقارهم مذموم في الشرع، وهو من صفات إبليس، وقد حرمه الله ورسوله. ሰዎችን መናቅና በእነሱ ላይ እውነት ሲመጣ ትክክል መሆኑን እያወቁ በንቀት አለመቀበል በሸሪዓ የተወገዘ ነው፤ የኢብሊስም ባህሪ ነው፤ አላህና መልዕክተኛውም ክልክል አድርገውታል። Https://t.me/Nuradis53 Https://t.me/Nuradis53 •════•••🌺🍃•••════•
Открыть в Telegramዒልም,,,,,, ዒልም የሌለው ሰው እንደ ጨለማ ቤት ነው፤ ቤቱ ትልቅ ቢሆንም ብርሃን ከሌለው ውበቱ አይታይም። ሀብት ሲወጣ ይቀንሳል፤ እውቀት ግን ሲሰጥ....... ዓሊይ ኢብን አቢ ጧሊብ በአንድ ምክራቸው ውስጥ እንዲህ የሚል መከሩት ለكميل بن زياد الْعِلْمُ خَيْرٌ مِنَ الْمَالِ، الْعِلْمُ يَحْرُسُكَ وَأَنْتَ تَحْرُسُ الْمَالَ، وَالْمَالُ تَنْقُصُهُ النفَقَةُ، وَالْعِلْمُ يَزْكُوا عَلَى الإِنْفَاقِ እውቀት ከሀብት ይበልጣል። እውቀት ይጠብቅሃል፤ አንተ ግን ሀብትን ትጠብቃለህ። ሀብት ሲወጣ ይቀንሳል፤ እውቀት ግን ሲሰጥ (ለሌሎች ሲካፈል) እያደገ ይሄዳል። «الْعِلْمُ حَارِسُ الْعِلْمِ، وَالْمَالُ تَحْرُسُهُ» (እውቀት ባለቤቱን ይጠብቃል፥ ሀብት ግን አንተ እንድትጠብቀው ይጠይቃል። 👇👇👇👇👇 Https://t.me/Nuradis53 Https://t.me/Nuradis53 •════•••🌺🍃•••════•
Открыть в Telegram➡️የተውሂድ ባለቤቶች ክብር‼️ =================== የአሏህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል። አንድ ሙስሊም የሆነ ሰው ሞቶ በአሏህ ላይ ቅንጣት ያክል የማያጋሩ አርባ (የተውሂድ ባለቤቶች) በጀናዛው ላይ አይሰግዱበትም፦ አሏህ ሸፈአቸው (ሽምግልናቸው) የተቀበላቸው ቢሆን እንጂ። 📘(ሙስሊም ዘግቦታል።) @Nuradis53
Открыть в Telegramإن الله وملا ئكته يصلون على النبي ياأيها الذين آمنو صلوا عليه وسلمو تسليمًا "አላህና መላእክቱ በነብዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ ፤ እናንተ ያመናችሁ ሆይ !በርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ ፤ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ ።አል-አህዛብ اللهم صل على محمد وعلى آل محمد كما صليت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد، اللهم بارك على محمد وعلى آل محمد كما باركت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد وسلم تسليما كثيرا. Https://t.me/Nuradis53 Https://t.me/Nuradis53 •════•••🌺🍃•••════•
Открыть в Telegram✅የሱና ሶላትን ላይ ለምንዘናጋ ! قال الإمام ابن باز اﻹﻛﺜﺎﺭ ﻣﻦ ﺻﻼﺓ اﻟﻨﺎﻓﻠﺔ فيه ﺧﻴﺮ ﻛﺜﻴﺮ ﻳُﺠﺒِﺮُ اﻟﻠﻪ ﺑﻪ ﻧﻘﺺ ﺻﻼﺓ اﻟﻔﺮﺽ ﻣﻊ اﻷﺟﻮﺭ اﻟﻌﻈﻴﻤﺔ. ♻️ ኢብኑ ባዝ (رحمه الله) ከፈርድ ውጪ የሆኑ የሱና ሶላቶችን ማብዛት ያለውን ጥቅም ሲናገሩ እንዲህ ብለዋል።⤵️ ➡️በውስጡ ብዙ ኸይር ይዟል ➡️የውመል ቂያማ ከፈርድ ሶላት የጎደለውንም ይጠግናል ➡️ተጨማሪ ብዙ የሆነ ምንዳ ከመኖሩም ጋር 📚- مجموع فتاواه ٣٢٦/١٠
Открыть в Telegramነቢዩ ሙሐመድ (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ስለ ኡሁድ (ኡሁድ) ተራራ ያላቸውን ፍቅር እና ክብር በሚገልጹ በርካታ ሶሒሕ ሐዲሶች ላይ ተናግረዋል። ከእነዚህም መካከል ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፦ أُحُدٌ جَبَلٌ يُحِبُّنَا وَنُحِبُّهُ (رواه البخاري ومسلم) ኡሁድ እኛን የሚወድ፣ እኛም የምንወደው ተራራ ነው። عن أنس بن مالك رضي الله عنه : أن النبي صلى الله عليه وسلم صعد أُحُدًا وأبو بكر وعمر وعثمان، فرجف بهم، فقال: اثبت أحد، فإنما عليك نبي وصديق وشهيدان رواه البخاري والترمذي وغيرهما አነስ ባወሩትና ኢማሙ ቡኻሪ በዘገቡት ሐዲስ የአሏህ መልእክተኛ ከአቡ በከር ከዑመርና ዑስማን ጋር ሆነው በኡሁድ ተራራ ላይ ወጡ, ተራራውም ተንቀጠቀጠ ። ነብዩም እንዲህ አሉ፦ ኡሑድ ሆይ እርጋ ! ባንተ ላይ ነብይ ፣ እውነተኛና (አቡ በከር) ሁለት ሸሂዶች ( ዑመርና ዑስማን) ናቸው ያሉት አሉ ። በሌላ ዘገባ ላይም ደግሞ ነቢዩ እሁድ ተራራን ከጀነት ተራራዎች አንዱ ተራራ ነው። በማለት ገልፀውታል። أُحُدٌ جَبَلٌ مِنْ جِبَالِ الْجَنَّةِ Https://t.me/Nuradis53 •════•••🌺🍃•••════•
Открыть в Telegram➡️አንዳንዴ አሏህ በኛ ላይ ሀራም ባላደረገው ነገር እና እንዳንሰራው ባልከለከለን በሆነ ነገር ለምን እራሳችንን እናስቸግራለን ? 👉መስለሀ እና መፍሰዳ አይተን የሆኑ ነገሮችን ልንተው እንችል ይሆናል ነገር ግን ሁሉም ከልክ በላይ መለጠጥ ዲን የሚመስለን ደግሞ ተሳስተናል። 👉በነገራችን ላይ ሁሉም ነገር ደግሞ በማግራራት ብቻ ዲን የሚመስለንም ይሄም ስህተት ነው። 👌ዲነል ኢስላም በማስረጃ የተመሰረተ እያንዳንዱ ማድርግ ያለብን እና የሌሉብን ነገሮች ግልፅ በሆነና በማያሻማ መልኩ በቁርአን እና በሐዲስ ሰፍሮልናል እሱን ለመረዳት አሏህ ያግራልን። والله أعلم @Nuradis53
Открыть в Telegram