Кабинет

Посты канала ኑ በብርሃኑ እንመላለስ

сначала новые

#15623Текст

Переслано из ΦΩΣ (light)

የሙስሊም አቃቢያን በአዲስ ኪዳን ጥንታዊ እደክታባት ውስጥ ከ400 ሺ በላይ የጽሁፍ ልዩነቶች አሉ ብለው በብዛት ሲናገሩ መስማት የተለመደ ነው። እነዚም ልዩነት ብለው የሚጠቅሷቸው ከ99 % በላይ በትርጉም ላይ ልዩነት የማያመጡ እንደሆነ እና እነዚህ በውሸት አምላካቸውን ማግነን የሚፈልጉ አቃቢያን የማያነቡ ክርስቲያኖችን ለማስደንገጥ የሚያደርጉት ተራ ሙከራ ብቻ እንደሆነ ከዚህ በፊት ተመልክተናንል። እናም እነርሱ የሚጠቅሱትን የጽሁፍ ልዩነቶች በተመሳሳይ መንገድ በቁርአን እደክታባት ውስጥ መመልከት እንችላለን። ለምሳሌ በ አረበኛ ቋንቋ ውስጥ ረጅም አናባቢ የሚባሉት አሊፍ ያ እና ዋው በጥንታዊ እደክታባት ውስጥ ያሉትን ልዩነቶች እንመልከት፦ አሊፍን የሚያካትቱ ልዩነቶች በቀደምት የእጅ ጽሑፎች ውስጥ በብዛት የሚገኙ ልዩነቶች ናቸው። Medial alif missing አሊፍን መሃል ላይ ያላካተቱባቸው ሱራ 14:35 ላይ قال qāla በጥንታዊ የ ቁርአን እደ ክታባት መሃል ላይ ያለችውን አሊፍ የማያካትቱ አሉ(قل)። ከነዚህም እደ ክታባት ውስጥ ISTANBUL, 01-28.1, BL Or. 2165, BNF 326a, BNF 328a የተሰኙ እደክታባት ይሄንን ረጅም አናባቢ አሌፍን አያካትቱም። በተመሳሳይ እዚው ሱራ 14:35 ላይ لاصنام አላስናም እዚሁ ላይ በተመሳሳይ ጥንታዊ የቁርአን እደክታባት middle form አሌፍን ሳያካትቱ የሚገኙ እደ ክታባት አሉ። ከነዚህ ውስጥ Istanbul, Topkapi, 01-28.1, 01-29.1, 01-20.x, BL Or. 2165, BNF 325a, 326a, 328a, 330a, 331, 332, 333c, 334c, 370a. እነዚህ ጥንታዊ እደክታባት ይሄንን ክፍል ላይ በተመሳሳይ የአሌፍ ልዩነት አለ።

Открыть в Telegram
Просмотры38−77%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#15622Текст

Переслано из ልባም ሴት 😍

ተወዳጄ እህቴ ሆይ 👋 የዛሬ ዲያቆን የነገው ካህን አጋርሽን ተጠንቀቂለት 🕊️። 🙏ያለጊዜ በዝሙት ወጥመድ ወድቆ ክብርት ከሆነች ከማዕረገ ቅስና እንዳይቀር ተጠንቀቂለት ። 🙏ስትገናኙ እንደሚገባ መጠን ልክ ለብሰሽ ተገኝ 👗 ። የተጋለጠ አካልሽን አይቶ በፆረ ዝሙት እንዳይወጋብሽ ተጠንቀቂለት ። 🙏ከልክ ባለፈ የሰላምታ መተቃቀፍ መቀራረብ አንድኛችሁ ለአንድኛችሁ ምክኒያተ ድቀት እንዳትሆኑ ተጠንቀቂለት ። 🙏የጌታን ደም በፅዋህ የያዙ እጆቹ 🍷 ፣ በቤተመቅደሱ በንፅህና የተመላለሱ እጆቹ ፣ ቃለ እግዚአብሔርን ላደመጡ ጆሮዎቹ ፣ ህገ እግዚአብሔር ላወጀው ልሳኑ ፣ ለአገልግሎት ለሚተጋው አካሉ ፤ ስለቤተመቅደስ አገልግሎት ለሚወጣው ለሚወርደው ህሊናው ተጠንቀቂለት 🙏 ። 🙏ስለአንቺ በማሰብ እግዚአብሔር እንዳይረሳ አግዢው ። 🙏ባንቺ ምክኒያት ከአገልግሎት እንዳይሰንፍ አበርቺው ⏰ ። 🙏ለከበረች ለክህነት ማዕረግ እንዲበቃ አይዞህ በይው ። 🙏ከእግዚአብሔር የተቀበልሽው ስጦታሽ ነውና እንደሚገባው መጠን አክብሪው ✨ ። 🙏በአንቺ ምክኒያት ዘለላ እንባ እንዳያፈስ አንቺ በእርሱ ደስታን እንጂ ሐዘንን እንዳታይ ተጠንቀቂ ። ......ዲያቆናት እጮኛ ያላችሁ ሴቶች ሆይ እንደሚገባ መጠን ልክ ተጠንቀቁላቸው ። @አላትዮን

Открыть в Telegram
Просмотры46−72%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#15621Текст
Просмотры63−62%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#15618Текст

Переслано из ΦΩΣ (light)

የቀጠለ የሐዲስ ኪዳን ፀሐፊያን ብቁ እና የሰለጠኑ ነበሩ በቅርብ ጊዜ የተደረጉ ጥናቶች ያሳያሉ የጥንታዊ ክርስቲያናዊ እደ ክታባት ውበት እንደተጠበቀ ሆኖ ጽሑፎቹን የገለበጡት ሰዎች (ጸሐፊዎች) ስለነበራቸው ሥልጠና እና ብቃት ማስረጃዎቹ ምን ይጠቁማሉ? ለሚሉ ጥናቶች እንደ እድል ሆኖ ለዚህ ​​ጥያቄ በእርግጠኝነት መልስ መስጠት ችለዋል። ለዚህ እንደ ምክንያት የሚቀርበው የሥራቸውን ጥራት ለመረዳት እስካሁን ከተገኙት እጅግ ጥንታዊ እደ ክታባት መካከል አንዳንዶቹን መመልከት ብቻ በቂ ነው። እንዲያውም ብዙ ምሁራን በቅርቡ የጥንታዊ ክርስቲያናዊ ጸሐፊዎችን የሥልጠና ደረጃ እና ችሎታ ለማወቅ ትናትና አድርገዋል። በአጭሩ ያገኙት ውጤት እንደሚያሳየው አብዛኛዎቹ ጥንታዊ ክርስቲያናዊ እደክታባት የተዘጋጁት በሰለጠኑ እና ብቃት ባላቸው ባለሙያዎች እንጂ በጋለ ስሜት ብቻ በሚንቀሳቀሱ ጀማሪ ፀሐፊዎች (ሙያዊ ሥልጠና በሌላቸው ሰዎች) አይደለም የሚል። የ Guardians of Letters ፀሐፊ Kim Haines-Eitzen በመፅሐፏ ላይ: "ስለ ጥንታዊ የክርስትና ፓፒረስ ጽሑፎቻችን የሚገርመው ነገር ሁሉም የስነ-ጽሑፋዊ እና የመዝገብ አያያዝ ዘይቤዎች ተጽዕኖ የሚታይባቸው መሆናቸው ነው፤ እንዲሁም ሁሉም በተሞክሮ እና በክህሎት ደረጃ ረገድ መካከለኛ ቦታ ላይ የሚገኙ ይመስላሉ። እነዚህን ቅጂዎች ያዘጋጁት ጸሐፍት፣ ከፊል-ተያያዥ(ቅጥልጥል ፅሁፍ) (semicursive) የጽሕፈት ዘይቤ ትምህርትን ያካተተ ትምህርት የወሰዱ፣ ሙያተኞችም ሆኑ ሙያተኞች ያልሆኑ ነበሩ፣ የተለያዩ ተግባራትን የሚያከናውኑ ጸሐፍት (multifunctional scribes) ከሚለው መግለጫ ጋር በደንብ ይጣጣማሉ።" በማለት በመፅሐፏ ላይ ገልፃለች:: ሌላ በቅርብ ጊዜ የተደረገ ጥናትም ተመሳሳይ መደምደሚያ ላይ ደርሷል። እ.ኤ.አ. በ2016 አላን ሙግሪጅ (Alan Mugridge) Copying Early Christian Texts: A Study of Scribal Practice በተሰኘ መፅሐፉ ላይ የጥንታዊ ክርስቲያን ፓፒሪ አካላዊ ቅርፅን በተመለከተ ሰፊ ትንታኔ አሳትሟል፣ እርሱም የእደ ክታባቱን እንደ የፅሁፍ ውበት ፣ የፃፉባቸውን እቃዎች ፣ የፅሁፎቹን ልኬቶች፣ መስመር በመስመር ፊደላት መፃፍ ፣ ሥርዓተ-ነጥብ፣ ወሳኝ ምልክቶች እና የመሳሰሉትን ባህሪያት በመመልከት እሱም በተመሳሳይ አብዛኛዎቹ የጥንት ክርስቲያን ፀሐፊዎች ብቁ ገልባጮች እንደነበሩ ወደ መደምደሚያው ደርሷል፡- “አብዛኛው የክርስቲያን ፓፒሪዎች በሰለጠኑ ጸሐፊዎች የተገለበጡ መሆናቸው ግልጽ ይመስላል።" ለዚህ ማስረጃ የሚሆነንን አንድ ምሁራዊ ጥናት እንመልከት ለምሳሌ P45 ተብሎ የሚጠራውን እደ ክታብ እንመልከት ፤ ይህ በሦስተኛው መቶ ዘመን የተጻፈ codex የ ወንጌላትንና የሐዋርያት ሥራን የያዘ የፓፒረስ ቅጂ ነው። ከመጀመሪያው ከነበሩት ወደ 220 ገደማ ቅጠሎች (ወይም 440 ገጾች)፣ በአሁኑ ጊዜ የተረፉት 30 ቅጠሎች (ወይም በሁለቱም በኩል ሲቆጠር 60 ገጾች) ብቻ ናቸው። ይህንን የእጅ ጽሑፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ያዘጋጀው ምሁር ስለ አጻጻፉ ሲገልጽ እንዲህ ይላል፦ “መጽሐፉ በሙሉ የተጻፈው በትንሽ እና በጣም ግልጽ በሆነ የእጅ ጽሑፍ ነው። አጻጻፉ እጅግ ትክክለኛ ነው፤ ምንም እንኳን ለየት ያለ የጌጣጌጥ ስልት (calligraphy) ባይኖረውም፣ ብቃት ባለው ጸሐፊ የተከናወነ ሥራ ነው።” P45፣ እንደ ጀማሪ ፀሐፊ ሰው የተዘበራረቀ ጽሑፍ ሳይሆን፣ በዘዴ የተካነ እና ልምድ ያለው ጸሐፊ ያከናወነውን ሥራ የተሰራ መሆኑን ይጠቁማል። ሌላም ምሳሌ እንመልከት በሦስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተጻፈውና የጳውሎስን መልእክቶች የያዘው P46 ከተሰኘው እደክታብ ሰማንያ ስድስት ቅጠሎች (ወይም 172 ገጾች) ተርፈዋል። የዚህን ጽሑፍ አጥኚ በውስጡ ያለውን የእጅ ጽሑፍ ከላይ ከተጠቀሰው ከP45 ጋር ሲያወዳድረው እንዲህ ይላል፦ "በዚህ ፓፒረስ ላይ ያለው ጽሑፍ፣ ወንጌላትንና የሐዋርያትን ሥራ ከያዘው ከቼስተር ቢቲ (Chester Beatty) ፓፒረስ [P45] በእጅጉ የተለየ ነው። ይህ ጽሑፍ ይበልጥ ጥበባዊ (calligraphic) መልክ ያለው ሲሆን፣ ፊደላቱ ትልልቅ፣ ነጻ እና ተመሳሳይ ፍሰትን የሚከተል አጻጻፍ ያላቸው፣ እንዲሁም የተወሰነ ውበትና ቅጥ የተላበሱ ናቸው። ፊደላቱ ቀጥ ያሉና አራት ማዕዘን ቅርጽ ያላቸው ሲሆን፣ በፊደላቱ መካከልም ሆነ በረድፎቹ መካከል በቂ ክፍተት ተትቶላቸዋል። . . . በአጠቃላይ ሲታይ፣ የፊደላቱ አጻጻፍ ዘይቤ ቀደምትነት ያለው እና በጥሩ የሮማውያን አጻጻፍ መልክ የተዋቀረ ነው ማለት ይቻላል።" በማለት ይሄ እደ ክታብ በተማረ ፀሐፊ መዘጋጀቱን ይገልፃል ይህ ብቻ ሳይሆን ለሉቃስ ወንጌል እና የዮሐንስ ወንጌል ትልቅ ማስረጃ ተደርጎ የሚታየው P75 ተመሳሳይ መስፈርትን እንደሚያሟላ ባለሙያዎች ይገልፃሉ:: ታዲያ እነዚህ እደ ክታባት በጣም በተማሩ ፀሐፊያን እንደተዘጋጁ ሁሉ በደንብ ባልተማሩ እና በቸልተኛ ፀሐፊያን የተዘጋጁ እደክታባት እንዳሉም ማስተዋል ይገባል ::

Открыть в Telegram
Просмотры157−5%к среднему
Пересылки—
Реакции1
Комментарии—
#15617Текст

Переслано из ΦΩΣ (light)

ሰሞኑን እደክታባት infallible ናቸው የሚል ሃሳብ የሚያነሱ ሰዎች ለዚ አንድ ማስረጃ አድርገው የሚያቀርቡት አንዱ ጥንታዊ የክርስቲያን ፀሐፊያን (copy አድራጊዎች) በዚህ ሙያ ላይ በደንብ የሰለጠኑ አልነበሩም እና ለእምነታቸው ካላቸው ጥልቅ ፍቅር የተነሳ ነዉ copy የሚያደርጉት በመሆኑም መፅሐፍ ቅዱስ fallible ነዉ የሚል ሃሳብን ሲያቀርቡ ተመለከትኩ:: እንደ እውነቱ ከሆነ መፅሐፍ ቅዱስ infallible ነዉ ሲሉን ምን እያሉን እንደሆነ ግልፅ ቢያደርጉልን መልካም ነዉ ነገር ግን ጥንታዊ ፀሐፊያን የሚሳሳቱ ስለነበሩ እና ጥንታዊ manuscribts (እደክታባት) ላይ የፅሁፍ ልዩነቶች ስላሉ አሁን በእጃችን ላይ ያለው መፅሐፍ ቅዱስ fallible ነዉ ማለት ስህተት ነዉ:: ምክንያቱም 100% በስህተት የተሞላ እና 100% ትክክል የሆነ እደክታባት ስለሌሉን ይህንን ልንለይ አንችልም በዛው ልክ እነዚህ እደክታባት በ 1 ግለሰብ እና በ 1 ቦታ የተፃፉ ባለመሆናቸው ሁሉም እደክታባት ተመሳሳይ ስህተት አለባቸው ማለት አስቸጋሪ ስለሆነ:: ሲቀጥል የመፅሐፍ ቅዱስን infallibility የምንወስነው መፅሐፍ ቅዱስ እደክታባት ላይ ባሉ ጥቃቅን ልዩነቶች ነዉ ወይ? የሚለው ጥያቄም consider መደረግ ያለበት ይመስለኛል:: ለአሁን ግን የጥንታዊ ፀሐፊዎች ቅጂ አዘጋጆች የተማሩ ነበሩ ወይስ ማንበብ እና መፃፍ ብቻ የሚችሉ? የሚለውን እንመልከት ይሄንን ጥያቄ ከብዙ ሰዎች መስማት የተለመደ ነዉ ብዙ scholars በዚ ሃሳብ ለሁለት ተከፍለው ይከራከራሉ አንዳንዶቹ እንደ Bart Erhman አይነቶቹ "እስካሁን የተመለከትናቸው የቅጂ አሠራሮች በዋናነት የሚያተኩሩት በክርስትና የመጀመሪያዎቹ ሦስት ክፍለ ዘመናት ላይ ነው። በዚያ ወቅት፣ የክርስቲያናዊ ጽሑፎችን የሚገለብጡ ሰዎች አብዛኛዎቹ ለዚህ ሥራ የሰለጠኑ ባለሙያዎች አልነበሩም፤ ይልቁንም ማንበብና መጻፍ የሚችሉ፣ በተለያዩ ጉባኤዎች ውስጥ የሚገኙ ክርስቲያኖች ነበሩ። እነዚህ ሰዎች በትርፍ ጊዜያቸው የማኅበረሰቡን ጽሑፎች እንዲገለብጡ ይጠየቁ ነበር። ይህንን ሥራ ለመሥራት ከፍተኛ ሥልጠና ስላልነበራቸው፣ እንደ ባለሙያ ጸሐፍት ስህተት የመሥራት ዕድላቸው ሰፊ ነበር።" በማለት ማንበብ እና መፃፍ የሚችሉ ብቻ ሲሆኑ ለሃይማኖታቸው ካላቸው ቀናኢነት የተነሳ copy ያደርጉ እንደነበር ሲገልፁ ሌሎች ደግሞ አንዳንድ ምሁራን ስለ መጀመሪያዎቹ ጸሐፊዎች ፍጹም ተቃራኒውን ይናገራሉ። እነዚህን ምሁራን በማንበብ የሚሰማው ስሜት አብዛኛዎቹ የጥንት ክርስቲያን ገልባጮች በተቃራኒው በእውነቱ ሙያዊ ጥንቃቄ የተሞላባቸው እና በደንብ የሰለጠኑ ነበሩ እና በጽሑፉ ላይ ምንም አይነት ለውጥ ከማድረግ በትጋት ይቆጠቡ ነበር። ልክ እንደ አይሁዳውያን አቻዎቻቸው ሁሉ፣ ልክ እንደ ብሉይ ኪዳን የዕብራይስጥ ጽሑፍን በጥንካሬ እና በጥቂቱ ዝርዝር ውስጥ በአክብሮት እና በትኩረት ይገለብጡ እንደነበር ሁሉ ብዙ የጥንት ክርስቲያን ገልባጮችም ጽሑፉ የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ በማመን አስተላልፈዋል። ከሁሉም በላይ፣ የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች ራሳቸው አይሁዳውያን ነበሩ፣ እና የአዲስ ኪዳን መጻሕፍትን ልክ እንደ ብሉይ ኪዳን መጻሕፍት በጥንቃቄ መገልበጣቸው ተፈጥሯዊ ይሆናል። ይቀጥላል

Открыть в Telegram
Просмотры137−17%к среднему
Пересылки—
Реакции1
Комментарии—
#15616Текст

Переслано из ΦΩΣ (light)

F.F. Bruce The New Testament Documents are they reliable? በሚል መጽሃፉ ላይ የሐዲስ ኪዳን ጸሃፊያን ተአማኝነት ላይ ጥያቄ የሚያነሱ ላይ አንድ የምወደትን ሙግት ያነሳል ፤ ከገጽ 12 ጀምሮ እንዲህ የሚል ሃሳብን ያነሳል: “ሐዲስ ኪዳን ጽሁፎች ላይ ያሉን ማስረጃዎች ከጥንታዊ ጽሁፎች (classic writing) በላይ ናቸው። እነዚህ ጥንታዊ ጽሁፎች [ተአማኝነት] ላይ ማንም ጥያቄ አያነሳባቸውም፤ የሐዲስ ኪዳን ጽሁፎች አላማዊ ጽሁፎች ቢሆኑ ኖሮ ማንም ጥያቄ አያነሳባቸውም ነበር። የታሪክ ተመራማሪዎች ከነገረ መለኮት ምሁራን በላይ የሐዲስ ኪዳን መዛግብት ላይ እምነት መጣላቸው በጣም የሚስብ ነገር ነው። (ለዚህም እንደ ምክንያት የሚያቀርበው የታሪክ ተመራማሪዎች አላማዊ መጽሃፍንም ቅዱሳት መጽሃፍትንም የሚያዩበት መንገድ ተመሳሳይ መሆኑ ነው። ሌሎች የነገረ መለኮት ምሁራን ግን ቅዱሳት መጽሃፍት ላይ ጥርጣሬን ያነሳሉ።) ከሀዲስ ኪዳን መጽሐፎቻችን ጋር በእኩል ጊዜ የተጻፉ ጥንታዊ መጽሃፍቶችን ስናነጻጽር ለሀዲስ ኪዳን የሚቀርበው ማስረጃ ዐጅግ ጠንካራ ነው። ለሐዲስ ኪዳን ያለን ማስረጃ ከሌሎች ጥንታዊ ጽሁፎች ጋር ብናነጻጽረው የሀዲስ ኪዳን ጽሁፎች ምን ያህል ከፍተኛ እንደሆኑ እንረዳለን። ለምሳሌ የቄሳር የጋሊክ ጦርነት (Gallic War) ከ 58_50 ቅድመ ልደተ ክርስቶስ የተጻፈ ነው እና በርካታ ቅጂዎች ቢኖሩትም ከእነዚህ ውስጥ ጥሩ ሁኔታ ላይ የሚገኙት 9 ወይ 10 ብቻ ናቸው። በጣም ጥንታዊ የሆነው እደክታብ ከቄሳር ከ900 ዓመት በኋላ የተጻፈ ነው። ከ 142 የሊቪ (Livy) የሮም ታሪክ የተሰኙ መጽሃፍት (ከ59 ቅ/ል/ክ_17 ዓ.ም የተጻፉ) የተረፉት 35 ብቻ ናቸው። ከእነዚህ ውስጥ እኛ 20ውን ነው የምናቃቸው ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ እንዱ ብቻ ነው በ 4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተጻፈው። ታሲተስ (100ዓ.ም) ከጻፋቸው 14 History of Tacitus መጽሃፍት ውስጥ 4ቱ ብቻ ናቸው የተረፉት ከ16 annals ከተሰኘው ስራው 10ሩ ብቻ ናቸው የተረፉት አሁን በእጃችን ላይ ያሉት እነዚህ ታላቅ ስራ ሁለት እደክታባት ላይ ብቻ የተመሰረቱ ናቸው። እንዱ ከ ዘጠነኛው አንዱ ከ አስራአንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተገኙ ናቸው። ከ 460_400 ቅ/ል/ክ የኖረው ቱሲዲደስ (Thucydidus) The History of Thucydidus እኛ ጋር የደረሱት 8 እደክታባት ብቻ ናቸው ፤ ከእነዚህም ውስጥ በጣም የሚባለው ከ 900 ዓ.ም የተገኘ ነው። በተመሳሳይ ይህ ለሄሮደተስ (Herodotus) (488-428 ቅ/ል/ክ) ያገለግላል። እናም የትኞቹም ጥንታዊ ተመራማሪዎች ከመጀመሪያዎቹ (original) ጽሁፎች ከ 1300 ዓመት በኋላ ዘግይተው የተጻፉ ዕደ ክታባት ቢሆኑም የሄሮደርተስንም ሆነ የቱሲዲደስን ስራዎች አይጠራጠሩም።” ይህንን ሃሳብ ስንጠቀልለው አሁን ላይ ማንም የእስተማማኝነት ጥያቄ የማያነሳባቸው የጥንታዊ ጸሃፊያን ጽሁፎቻቸው እኛ ጋር የደረሱት ወይ ጸሃፊዎቹ ካለፉ ከብዙ ዘመን በኋላ የተጻፉት ናቸው ወይም ደሞ ለማመሳከሪያነት እንኳን የተገኙ ሁለት ወይ ሶስት ቁርጥራጭ ጽሁፎችን ነው። ወደ ሐዲስ ኪዳን ስንመጣ ከሁለተኛው መቶ ክፍለ ዘመን 12 እደክታባት ከሶስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን 64 እደክታባት ከአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከ48 በላይ እደክታባት በአጠቃላይ ከ 5700 በላይ ጥንታዊ የግሪክ እደክታባት በእጃችን ላይ ማስረጃዎች ኖረውን እነዚያ ጥንታዊ የታሪክ መጽሀፎች ላይ ጥያቄ ሳይነሳ የሀዲስ ኪዳን ተአማኝነቱ ላይ ጥያቄ መነሳቱ ሳገርማል።

Открыть в Telegram
Просмотры140−15%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#15615Фото

የመድኃኔዓለም ዓመታዊ ክብረ በዓል ስለምን ጥቅምት ፳፯ ይከበራል❓❓❓ ጥቅምት ፳፯ ቀን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሥርዓት መሠረት የመድኃኔዓለም (የኢየሱስ ክርስቶስ) ዓመታዊ የ«ጥንተ ስቅለት» መታሰቢያ በዓል ሆኖ በደማቁ ይከበራል። ይህ በዓል በጥቅምት ፳፯ ቀን እንዲከበር የተደረገበት ዋና ዋና ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው፦ ፩./ የበዓል መዛወር (የለውጥ በዓል)፦ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ለማዳን በቀራንዮ መስቀል ላይ የተሰቀለውና ደሙን ያፈሰሰው መጋቢት ፳፯ ቀን ነው። ነገር ግን ይህ ቀን አብዛኛውን ጊዜ በዐቢይ ጾም (በሁዳዴ ጾም) ወቅት ይውላል። በዐቢይ ጾም ወቅት ደግሞ የሐዘንና የጸሎት እንጂ ከበሮ የሚመታበት፣ እልልታና የደስታ ዝማሬ የሚሰማበት የንግሥ በዓል ማክበር በቤተክርስቲያን ሥርዓት አይፈቀድም። ስለዚህ ምእመናን የበዓሉን በረከት በደስታና በምስጋና እንዲያከብሩት አባቶች ሊቃውንት መጋቢት ፳፯ የሚውለውን የጥንተ ስቅለት በዓል ወደ ጥቅምት ፳፯ ቀን አዙረው እንዲከበር ሥርዓት ሠርተዋል። ፪./ የማዳን ሥራውን ለማሰብ፦ በዚህ ዕለት ክርስቶስ ስለ ሰው ልጆች ፍቅር ሲል የተቀበላቸው ዐሥራ ሦስቱ ሕማማተ መስቀል፣ መከራውና በሞቱ ሞትን ሽሮ ዓለምን ነጻ ማውጣቱ በሰፊው ይታሰባል። ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን አሜን።

Открыть в Telegram
Просмотры866+426%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#15614Текст

Переслано из ΦΩΣ (light)

ዛሬ ከ textual criticism ርዕስ ወጣ ልበል እና አንድ ያስገረመኝን ልፃፍ ይሄ ዜና ትንሽ የቆየ ቢሆንም የነገሮች መገጣጠም ስላስገረመኝ ላጋራችሁ ዜናው የአምና ሲሆን pope Leo 14ኛ እና Patriarch Bartholomew 1ኛ 1700ኛውን የኒቂያ ጉባኤ ለመዘከር ፀሎተ ሃይማኖትን በጋራ አድርሰዋል የሚል ነዉ:: እና ሁለቱ ቤተእምነቶች የሚለያዩበት ዋና አንቀፅ ያለበትን የኒቂያ ጉባኤ የሃይማኖት መግለጫ በጋራ ሲሉት መንፈስ ቅዱስ ከአብ ብቻ ነዉ የሚሰርፀው የሚለውን አንቀፅ ካቶሊኮች እና ከወልድም ይሰርፃል ስለሚሉ እንዴት እንዳረጉት ባላቅም ይሄንን ሳነብ የ leo የሚባል Pope የካቶሊክ ቤተክርስቲያንን ሲመራ የሆነ ነገር መፈጠሩ አስገረመኝ:: በ 451 ዓ. ም Oriental orthodox እና catholic ሲለያዩ የመለያየታቸው ዋነኛ ምክንያት የነበረው pope Leo 3ኛ ነዉ:: በሌላ አገላለፅ በ pope Leo 3ኛ ጊዜ የorthodox እና የcatholic መለያየት ሆነ:: በ 1054 የ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን እና የ ምስራቅ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ረጅም ዘመን ከቆየ የውስጥ ችግራቸው በሁላ የመጨረሻውን መለያየት ያደረጉት በ ካቶሊኩ Pope Leo 9ኛ እና በምስራቅ ኦርቶዶክስ Patriarch Michael I Cerularius መካከል ነበር አሁንም ሌላ ትልቅ ልዩነት ሲፈጠር የነበረው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን መሪ pope Leo የሚባል ነዉ:: በ 16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የፕሮቴስታንት እንቅስቃሴ ሲነሳ እና ማርቲን ሉተር ከ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ወቶ የራሱን ድርጅት በሚያቋቁምበት ወቅት የካቶሊክ ፖፕ የነበረው Pope Leo 10ኛ ይባላል:: እንግዲ እንደምታዩት በክርስትና ትልልቅ ቤተእምነቶች ሲከፋፈሉ የምዕራቡን ቤተእምነት ይመራ የነበረው Pope ስሙ Leo ይባላል:: ከዚህ በተጨማሪ በ 7ኛው መቶ ክፍለ ዘመን iconoclast controversy ወይም ቅዱሳት ስእላትን የሚቃወሙ ሲነሱ በወቅቱ የነበረው የባዛንታይን ንጉሥ Leo ሳልሳዊ ይባል ነበር:: ይሄ ነገር ተራ ግጥምጥሞሽ ወይስ ከስሙ ጀርባ ሌላ ታሪክ አለው የሚለው እያስገረመኝ አሁን ያሉት Pope Leo 14ኛ ይሄንን ታሪክ እንደሚቀይሩት ተስፋ አደርጋለው::

Открыть в Telegram
Просмотры121−26%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#15613Текст
Просмотры97−41%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#15612Текст

የቀጠለ ከላይ እንዳየነው ይሄንን ክፍል አልያዙም ተብሎ ከሚታመንባቸው እደክታባት P69 እና P75 ባይገኝም ከነሱ እድሜ እኩል ያለው GA 0171 የተሰኘ እደክታብ ይሄንን መያዙን አይተናል አሁን ውጫዊ ማስረጃ ብለው ምሁራን የሚጠቅሱትን እንመልከት በ 2ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከተነሱ አባቶች ይህንን ጥቅስ የሚያውቁት በመጀመሪያ ሰማእቱ ዮስጢኖስን (Justin Martyr) በ 155 ዓ.ም አካባቢ ፅፎታል ተብሎ የሚታመነው dialogue with trypho መፅሐፍ ላይ እንዲህ የሚል ፅሁፍ እናገኛለን "በሐዋርያቱ እና እርሱን በተከተሉ ደቀመዛሙርቱ በተዘጋጁ ፅሁፎች ውስጥ እርሱ አባት ሆይ ከተቻለ ይህች ፅዋ ከኔ ትለፍ ብሎ ሲፀልይ ላቡ እንደ ደም ጠብታ ወደ መሬት ይወርድ ነበር ተብሎ ተፅፏል::" በማለት dialogue 103:8 ላይ ከሉቃስ 22:43-44 ወስዶ ፅፏል ታዲያ justine martyr ሁለተኛ መቶ ክፍለ ዘመን ላይ ያለ leluqas ወንጌል የቀረበ እንደመሆኑ የእሱን ፅሁፍ እንደምስክርነት መውሰድ እንችላለን:: ሌላ በዚሁ ክፍለ ዘመን እንደኖረ የሚታመነው ሔረኒዎስን እንመልከት againest heresis በተሰኘ መፅሐፉ 3.22.2 ላይ የክርስቶስን ሰውነት የሚክዱትን እንዲ በማለት ይናገራል "እንደ ደም ጠብታዎች ያሉ ብዙ የላብ ጠብታዎችን አላበ::" በማለት ከ ሉቃስ 22:43-44 ያለውን ቃል ወስዶ ለነዚሁ የክርስቶስ ፍፁም ሰውነትን የሚክዱትን ያስተምርበታል:: በሁለተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የኖሩትን የ ሁለት አባቶች ምስክርነት ከተመለከትን ቀጥሎ ባለው ክፍለ ዘመን ማለትም በ ሶስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተነሱ አብቶችም እንዲሁ ከዚህ ክፍል ወስደው ፅፈዋል ለምሳሌ :- አቡሊዲስ (Hipolytus the rome) ይህንን ክፍል ያውቅ እንደነበር ፅሁፎቹን ተመልክተን መገመት እንችላለን Againest Noetus በተሰኘ ስራው (220ዓ.ም) ላይ ክርስቶስ መከራ መቀበልን እና መበርታት እንዳስፈለገው ፅፏል:: ይህ መበርታት የሚለው በዚሁ በሉቃስ ወንጌል ላይ የሚያበረታው መልአክ ታየው ከሚለው ክፍል የተወሰደ ነዉ:: ከላይ ያነሳናቸውን እስከ 3ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበሩ አባቶች በቀጥታ ቃሉን ተጠቅመው የፃፉትን እንደተመለከትነው ሁሉ ሌሎች አባቶች ቃሉን በቀጥታ ወስደው ባይፅፉም ነገር ግን ይሄንን ታሪክ ከሌላ ታሪክ ጋር በማዛመድ ወይም allusion ፅፈውበታል እነዚህም ይሄ ክፍል በትንታውቷ ቤተክርስቲያን እንደሚታወቅ ማስረጃ ነዉ ከ 4ኛው መቶ ክፍለ ዘምን በሁአላ በተነሱ አባቶች ውስጥ ይሄ ክፍል በስፋት የሚታወቅ ሲሆን በነ አትናቴዎስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ ጎርጎርዮስ ዘኢንዝናዙ ዮሐንስ አፈወርቅ ኤፍሬም እና ሌሎች አባቶች ውስጥ በስፋት የተገለፀ ክፍል ነዉ:: ይሄንን ክፍል ከላይ እንዳነሳሁት ከ ኢ አማንያን የሚመጣ ፌዝ በመፍራት በክርስትና አማኞች ዘንድ እንደተቀነሰ የሚያሳዩ ነገሮችን ስንመለከት ክርስትና ላይ በመቀለድ ከሚታወቁ ኢ አማንያን መካከል የሆኑት ሴልሰስ ፖርፊሪ ጁሊያን የመሳሰሉት የክርስትና መፅሃፍትን በማንበብ ተራ ክስ ብቻ ሳይሆን ክርስቲያኖች በሚያምኑት እምነት ላይ ያፌዙ ነበር:: ለምሳሌ ሴልሰስ ይህንን የጌቴሰማኔ ፀሎትን በማንሳት ኢየሱስ ክርስቶስ በሞት ፊት የሞራል ድፍረት አልነበረውም በማለት ያፌዝ ነበር:: ፖርፊሪም ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት ለማምለጥ ፀሎት አድርጕል ብሎ ይከሳል:: እንደው ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ቢሆን ኖሮ አፅናኝ መልአክ አያስፈልገውም ነበር እያለ ይሳለቃል:: ከእነርሱ ሌላ ሄሮክለስ የተባለ ሰው Friend of Truth በተሰኘ ስራው ላይ ኢየሱስ ክርስቶስን ከ አፖሎንየስ ጋር እያነፃፀረ የአፖሎንየስን የበላይነት ለማሳየት ይሞክራል:: በዚሁ መፅሐፉ ላይ አንድ ሰው ለሞት እንዴት መዘጋጀት አለበት የሚለውን እንደዋና መከራከሪያ ያነሳል:: ታዲያ በወቅቱ የነበሩ ክርስቲያኖች እንዴት መመለስ እንዳለባቸው ባለማወቅ እነዚህን መሰል ትችቶች ፍራቻ የሉቃስ ወንጌልን በሚገለብጡበት ጊዜ ሳያካትቱ ቀርተዋል እንጂ ከላይ ያነሳናቸው ማስረጃዎች ይህ ክፍል በሉቃስ እንደተፃፈ እንድናምን የሚያረግ ነዉ:: ነገር ግን እግዚአብሔር ቃሉን አልጠበቀም የሚል መከራከሪያ በእንደዚህ አይነት ጥቅሶች ላይ ቢነሳ እንደውን እንደዚህ አይነት ጥቅሶችን ስንመለከት ፈጣሪ ቃሉን ጠብቆ ለትውልድ ማስተላለፉን እንረዳለን ምክንያቱም ይሄ ጥቅስ አንዳንዶች እንደሚሉት ተቆርጦ ተወግዶ እንደነበር እና በዛው የቀረ ቢሆን ኖሮ ወይም ደግሞ እንደነሳላህ አይነቶቹ እንደሚያነሱት በሁአላ ዘመን የተጨመረ ቢሆን እውነትም ፈጣሪ ቃሉን አልጠበቀም ይባላል ነበር ግን ፈጣሪ ቃሉን እንፈጠበቀ የምንረዳበት አንዱ መንገድ ይህ ክፍል ተቆርጦ ሳይቀር እግዚአብሔር ለትውልድ እንዲተላለፍ ማድረጉ ነዉ ::

Открыть в Telegram
Просмотры234+42%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#15611Текст

Переслано из ΦΩΣ (light)

ሳላህ ሰምአቱ ብራና ብሎ ባዘጋጀው መፅሐፉ ላይ ከሚያነሳቸው ጥያቄዎች አንዱ ይሄኛው በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 22:43-44 ያለው ጥቅስ የደብረ ዘይቱ ፀሎት ጭማሪ በሚል ከገፅ 67 ጀምሮ በ ጥንታውያን እደ ክታባት ውስጥ አይገኝም በ ፀረ ዶሴቲካውያን (anti docetism) ወይም ዶሴቲካውያንን ለመቃወም የተጨመረ ክፍል ነዉ በማለት ያነሳል :: የዚህ መፅሐፍ ፀሐፊ የሚያነሳቸውን ክሶች ካየው በሁአላ ፀሐፊው ምን ሊፅፍ እንደፈለገ ያወቀው አልመሰለኝም:: ይሄንን ጥቅስ ዶሴቲክ እምነት ተከታዮችን ለመርታት ተጨምሯል ከሚል የክርስቶስን ድካም ስለሚያሳይ ተቀንሷል ብሎ ቢፅፍ ለሱ ትልቅ መከራከሪያ የሆነው ነበር:: ነገር ግን የነ Bart Erhman ን ፅሁፍ እንደወረደ ስለሚገለብጥ በምን መልኩ መከራከር እንዳለበትም አልተረዳም:: በርግጥ ይህ ክፍል እሱ በሚያነሳቸው እደክታባት ላይ አይገኙም እናም ይሄንን ፅሁፍ ይዘው የሚገኙትን እደክታባትም አንስቷል ያም ቢሆን ግን የፀሐፊው ሃሳብ ግን ተጨምሯል ለሚለው ያደላ ነዉ :: እንደ አጠቃላይ ስንመለከተውም መፅሐፍ ቅዱስ አልተጠበቀም ወይም የፈጣሪ ቃል አደለም የሚለውን እንዴት አድርጎ መሞገት እንዳለበትም እንዳልገባው ከተረዳውበት አንዱ ሃሳብ ይሄ ነዉ :: እርሱ እዚህ ክፍል ላይ ያነሳውን አጠር አርጎ ለመመለስ እንሞክር ይሄንን የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 22 :43-44 ያለውን ጥቅስ የተጨመረ ሳይሆን እንደውን አንዳንዶች እንደሚሉት ከ2ኛው መ/ክ/ዘ አጋማሽ በሁላ እና ከ 3ኛው መ/ክ/ዘ መጨረሻ በፊት ባሉት ጊዜያት ውስጥ የተቀነሰ እንደሆነ ይናገራሉ:: ለዚህም እንደምክንያት የሚያቀርቡት: የጥንት ክርስቲያኖች ይሄ ክፍል በእቅበተ እምነት ላይ ፈታኝ ሆኖ አግኝተውታል የሚል ነዉ እናም እምነታቸውን ከመጠበቅ (apologetics reason) አንፃር አስወግደውት ይሆናል ክፍሉ ኢየሱስ ክርስቶስን ደካማ አድርጎ ስለሚያሳይ በወቅቱ ከ ኢ አማኞች የሚመጣባቸውን ፌዝ እና ጥያቄ በመፍራት እና ለ ፀረ ክርስትና ክርክር ወሳኝ አድርገው ስለምጠቀሙት ይሄንን ክፍል ማስወገድ እንደ ትልቅ ችግር ፈቺነት ወስደውት ይሆናል የሚል ግምትን ያስቀምጣሉ:: ይህንን ክፍል ከ አንድ ወገን ብቻ ተመልክቶ የተጨመረ (interpolation) ነዉ ማለት አስቸጋሪ ነዉ ይህንን ክፍል ያላካተቱ እደክታባት እንዳሉ ሁሉ ያካተቱም አሉ:: ለምሳሌ:- ሳላህ እንደገለፀው P75 እና እነ ኮዴክስ ቫቲካነስ የመሳሰሉት እደክታባት ይሄንን ክፍል አይዙም ነገር ግን ኮደክስ ሳይናቲከስን ጨምሮ ቀደምት ከሚባሉት እደክታባት መካከል GA 0171 ይህንን ክፍል ይዞ ይገኛል:: (ይህንን እደክታብ አንዳንዶች ወደ 200 ዓ.ም አካባቢ የተፃፈ ነዉ ብለው ሃሳብ ያነሳሉ) ታዲያ እንደዚ በጥንታውያን እደክታባት ላይ የሚገኝ ከሆነ ይህንን ክፍል ተጨምሮ ቢሆን በእነዚህ እደክታባት ላይ ባልተገኘ ነበር :: Textual criticism ስናጠና ፅሁፎችን የምንገመግምበት አንደኛው መንገድ external evidence ነዉ ይህም ጥንታውያን አባቶች ምን ብለዋል የሚለውን እንገመግማለን:: ይቀጥላል..

Открыть в Telegram
Просмотры89−46%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#15610Текст
Просмотры95−42%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#15609Текст

ሐዋርያት የቃል ትምህርትን በሚያስተላልፉበት ጊዜ ምን ያህል ትክክል ነበሩ ብለው ጥያቄ ለሚያነሱ ሲመልስ "በጥንታዊ አይሁዳውያን ዘንድ በቃል ማስታወስ (memorize ማድረግ) ምን ያህል የተስፋፋ እና የተለመደ ነገር እንደሆነ ማየት ይቻላል በአይሁዳውያን ትውፊት የመምህራንን ቃላት ቃል በቃል መያዝ ወይም ማስታወስ የተለመደ ነገር እና ተፈጥሯዊ ነገር ነዉ:: ሂላል የተባሉ ታዋቂ ሰው የተናገሩት አንድ አባባል በባብሎናውያን ታልሙድ ላይ እንዲህ ሲል ሰፍሮ ይገኛል 'ትምህርቱን አንድ መቶ ጊዜ የሚደግም ሰው አንድ መቶ አንድ ጊዜ ከሚደግም ሰው ጋር ሊወዳደር አይችልም'":: ልክ በእኛ ሀገር በአብነት ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች የመምህራኑን ትምህርት በቃል እንደምይዙት ሁሉ በአይሁዳውያን ዘንድ የመምህራኑን ትምህርት በቃል ሸምድዶ መያዝ የተለመደ ነገር ስለሆነ ሐዋርያቱም በአይሁድ ባህል እንደማደጋቸው የጌታችንን ትምህርት በቃል ሸምድዶ ለመያዝ የሚቸገሩ አይሆኑም:: አንዳንዶች እንደሚገልፁት የኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርቶች ብዙውን ጊዜ በቅኔ መልክ ወይም በቀላሉ ሊታወስ በሚችል መልኩ የሚገለፅ ነበሩ:: R. Riesner የጌታችንን ትምህርት ሲገልፁ " የኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርት 80% የሚሆነው በቅኔያዊ መልክ የቀረበ ነዉ:: ከዚህም ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዛሙርቱ ከእርሱ እንዲማሩ ይጠብቅ እንደነበር መረዳት እንችላለን:: ይህ የቃል ትምህርትም ቶሎ እንዲታወስ ይረዳል::" ሌላው ሐዋርያቱ የቃል ትምህርቱም እንደማይረሱ ማስረጃ የሚሆንነን ሲገልፁ "ምናልባትም ከኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዛሙርት አንዳንዶች እርሱ በሚያስተምርበት ወቅት ማስታወሻ ይይዙ ይሆናል:: ምንም እንኳን ማስረጃ ማቅረብ ባይቻልም ነገር ግን ይህን ከማድረግ የሚያግዳቸው ነገር አይኖርም::" በማለት በቃል ከመሸደዳቸውም በዘለለ ማስታወሻ ሊይዙ እንደሚችሉ ግምታዊ ሃሳባቸውን አስቀርተዋል ለዚህም በጥንት ጊዜ የታላላቅ ሰዎች ታሪካቸውን በደቀመዛሙርቶቻቸው ይፃፍ ስለነበር እና ማስታወሻ መያዝም የተለመደ ስለሆነ ሐዋርያትም ይሄንን ላለማድረጋቸው ማረጋገጫ አይኖርም::

Открыть в Telegram
Просмотры220+34%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#15608Текст

የወንጌላትን እውነተኝነት እና የሐዋርያትን የማስታውስ አቅም በተመለከተ ብዙ ጊዜ ጥያቄዎች የሚያነሱ አሉ:: አንዳንድ ሰዎች ኢየሱስ ክርስቶስ ካረገበት ጊዜ አንስቶ ወንጌላት እስከተፃፉበት ባሉት አስርት አመታት ውስጥ ለምን ያህል ጊዜ መዘግየት ተፈጠረ? እንዲሁም በእነዚህ ጊዜያት ምን ተፈጠረ ብለው ይጠይቃሉ::ይህንን ጥያቄ እነ ዳንኤል ዋሌስ ሲመልሱ እንዲህ ይላሉ "እዚህ ጋር ማስተዋል ያለብን የሐዋርያት የመጀመሪያ አላማዎች ውስጥ ቅድሚያ የሚሰጠው ነገር ወንጌልን በቃል መመስከር ነበር:: እነሱም የእግዚአብሔር ቃል በቻሉት ፍጥነት ለዓለም ሁሉ ለማድረስ ይተጉ ነበር::" ይህ ማለት የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ሐዋርያትና መሪዎች ወንጌልን በቃል በማሰራጨት ላይ ያተኩሩ ነበር:: በዚህ ወቅት በፅሁፍ የተዘጋጀ ወንጌል ስለመኖሩ ማሰብ አያስፈልጋቸውም ነበር:: ቤተክርስቲያን በተመሰረተችባቸው የመጀመሪያዎቹ ጥቂት አመታት ወንጌል በመላው የሮም ግዛት ውስጥ በፍጥነት በመሰራጨቱ ሐዋርያት በቃል ትምህርታቸው ላይ ምን ያህል ስኬታማ እንደነበሩ የሚያሳይ ምስክር ነዉ:: ሌላም ተመሳሳይ ጥያቄ ሐዋርያት የቃል ስብከት ጊዜ የተፃፉ ወንጌላት ትክክለኝነታቸውን ማስረጃ መሆን ይችላል ወይ የሚለውን ጥያቄ ሲመልሱ:- "ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰበከው የመጀመሪያው ስብከት በሁአለኛው ዘመን የተለወጠ ቢሆን ኖሮ የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች ስለ ለውጦቹ ይቃወሙ ነበር:: እንደውም አዲስ እና እንግዳ ወይ የተሻሻለ የክርስትና ትምህርትን ለመቃወም ከቤተክርስቲያን ውጪ ያሉ ሰዎችን ሃሳብ መጠበቅ አያስፈልገውም ነበር:: አማኞች በራሱ ይሄንን ይቃወሙ ስለነበር:: ወንጌል ከኢየሩሳሌም ወጥቶ በፍጥነት በመሰራጨቱ ሐዋርያት እንኳን መልክቱን ለመቀየር ምንም አይነት አጋጣሚ አያገኙም ነበር::" አንዳንዶች ደግሞ ሐዋርያት ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ባላቸው ከፍተኛ እምነት የተነሳ ትምህርቱን ቀይረውት ይሆናል ወይም ደግሞ የአንዳንድ ደቀመዛሙርቱ ትውስታቸው ዳካማ ሆኖ ትምህርቱን ቀይረውታል ብለው ለሚጠይቁት ሲመልሱ: " ይህ የሚሆንበት ምንም እድል አይኖርም ምክንያቱም ሐዋርያት የክርስቶስን ትምህርት ረስተዋል ብለን መናገር የምንችለው ካረገ እስከ ጰራቅሊጦስ ባለው ጊዜ ውስጥ ነዉ ከዛ በሁአል ባሉት ጊዜ ውስጥ ደግሞ ሊረሱት አይችሉም ምክንያቱም ከ ጰራቅሊጦስ በሁአላ አንዴ ማስተማር ስለጀመሩ ነዉ ይህንን ትምህርት ደግሞ ሁልጊዜ (ቀን በቀን) በመደጋገም ስለሚያስተምሩት የሚረሱበት ምክንያት አይኖርም:: ከ እርገቱ እስከ ጰራቅሊጦስ ባሉት 10 ቀናት ውስጥ ደግሞ ረስተውታል ማለት አስቸጋሪ ነዉ ::"

Открыть в Telegram
Просмотры211+28%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#15607Текст
Просмотры88−47%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#15606Текст

ሞቶ ያላረፈው ጳጳስ በ896 ዓ. ም. ላይ 111ኛው የሮማው ጳጳስ (ፖፕ) የነበረው ፎርሞሰስ ሞተ። በመንበሩ ላይ የተተካው እስጢፋኖስ 6ኛ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ (ምናልባት በዐለም ታሪክም) ያልተለመደ ነገር ፈጸመ። ምን ነበር? ከፎርሞሰስ ቀጥሎ 112ኛው የሮማው ጳጳስ (ፖፕ) ሆኖ የተሾመው እስጢፋኖስ 6ኛ ከእርሱ በፊት በሮም መንበር ላይ (ከ891-96 ዓ. ም.) ጳጳስ (ፖፕ) የነበረውን ፎርሞሰስን አስከሬኑን ከተቀበረበት አስቆፍሮ ካስወጣ በኋላ፣ በመበስበስ ላይ የነበረውን ሰውነቱን የጵጵስና ልብስ አስለብሶ በመንበረ ጵጵስና ላይ አስቀምጦ በቤተ ክርስቲያን ጉባኤ ፊት ለልዩ ልዩ ክሶች መልስ እንዲሰጥ ለፍርድ አቀረበው። ከሞተ በኋላ አስከሬኑ ለፍርድ ለቀረበው ተከሳሽ ፖፕ ፎርሞሰስ መልስ ይሰጥለት ዘንድ አንድ ዲያቆን ተመደበለት። በሟቹ ፖፕ ፎርሞሰስ ላይ የቀረቡበት ክሶች - ፈጽሟቸዋል የተባሉ ቀኖናዊ ጥሰቶች፣ በቤተ ክርስቲያን ጳጳስነቱ ሊሠራቸው ሲገባ ያልሠራቸው፣ በተቃራኒው ደግሞ ማድረግ ያልነበረበት ግን ያደረጋቸው ተግባሮች የተባሉና መሰል ሌሎች ክሶችም ነበሩ። በመጨረሻም ፖፕ ፎርሞሰስ በቀረቡበት ክሶች ጥፋተኛ ሆኖ ተገኝቷል በመባሉ አስከሬኑ ጥፋተኛ ተብሎ ተፈረደበት። ስለዚህም ልብሰ ጵጵስናው ተገፈፈ፣ ሦስቱ የቀኝ እጆቹ ጣቶቹ እንዲቆረጡ ተደረጉ፣ በመጨረሻም ከመበስበስ የተረፈው ሰውነቱ በሮም በሚገኘው የቲበር ወንዝ ውስጥ እንዲጣል ተደረገ። ይህ ውሳኔ በራሱ በፖፕ ስቴፈን 6ኛ ላይም ያስከተላቸው መዘዞች አሉ። በዚህ ታሪካዊ ኩነት ላይ በቀኝም በግራም የሚነገሩ ብዙ ሐተታዎች አሉ። ቀኝም ሆነ ግራ የሌለው ክስተት ግን ፖፕ ፎርሞሰስ በቤተ ክርስቲያን ላይ ፈጽሟቸዋል በተባሉት ወንጀሎችና ግድየለሽነቶች ምክንያት ከሞተ በኋላም እንኳ አስከሬኑ ከፍርድና ከመጎሳቆል ነጻ ሊሆን አለመቻሉ ነው። እርሱ ብቻ የሚያውቀው በእግዚአብሔር ዘንድ ያለው እውነተኛውና ዘለዓለማዊው የሰማይ ፍርድ እንዳለ ሆኖ፣ በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚፈጸም ቸልተኝነትም ሆነ ነውረኛነት በዚህ ዐለምም ቢሆን በሕይወተ ሥጋ እያሉ ብቻ ሳይሆን ከሞቱ በኋላም እንኳ ዕረፍት ሊነሣና በሰላም ላያስቀብር የሚችል መሆኑን ግን በተግባር ያሳየ ማስጠንቀቂያ ሆኖ አልፏል። Yaregal Abegaz Kebede

Открыть в Telegram
Просмотры272+65%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#15605Текст

Переслано из ΦΩΣ (light)

"በእርግጥ በ እደ ክታባት ውስጥ ከሚገኙት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የፅሁፍ ልዩነቶች (textual variant) መካከል አብዛኞቹ ፍፁም ትርጉም የለሽ ዋጋ ቢስ እና ምንም አይነት ትክክልኛ ፋይዳ የሌላቸው ናቸው:: እነዚህን ልዩነቶች የሚያሳዩት አንድ ነገር ቢኖር ፅሁፍ ገልባጮች እንደኛ እኛ ሁሉ የፊደል አፃፃፍ ስህተት ሊሰሩ ወይም ትኩረታቸውን ጠብቀው መስራት ሊሳናቸው እንደሚችል ብቻ ነዉ ::" ይህንን ፅሁፍ በሚገርም ሁኔት የ Bart D. Erhman Misqouting Jesus የተሰኘው መፅሐፉ ውስጥ ያለ ነዉ (እርግጥ ይህ ፕሮፌሰር ክርስትና ላይ ተደጋጋሚ ትችትን በመስጠት ቢታወቅም አንዳንድ ጊዜ ግን የዚ አይነት ሃሳቦችን እንደምስክርነት ወስዶ ማሳየት ይቻላል):: ፕሮፌሰር Bart በእስላም ወገኖቻችን በተደጋጋሚ የሚጠቀስ ሲሆን ሳላህ ሰምአቱ ብራና መፅሐፍ ላይ ወደ 11 ጊዜ ከሱ መፅሀፎች ጠቅሰው የመፅሐፍ ቅዱስን መበረዝ ሃሳባቸውን አጠንክሮበታል:: ታዲያ ይሄንን ፅሁፍ ሌላ የክርስቲያን textual criticism ባለሙያ ተናግሮት ቢሆን ምንም ላያስገርም ይችላል ሌላው ቢቀር ለራሱ አድልቶ ነዉ በሚል ሊታለፍ ይችላል ነገር ግን sceptic ከሆነ አንድ ምሁር ይሄንን መስማት የመፅሐፍ ቅዱስ የእደክታባት የፅሁፍ ልዩነት እውነትም ያን ያህል ለውጥ የሚያመጣ አደለም ብለን እንድንወስድ ይረዳናል:: ፕሮፌሰሩ በዚ ብቻ አያበቃም በሌላ ቦታም "ፀሐፊዎቹ ያደረጕቸውን ለውጦች ቢያንስ ሆን ተብለው የተደረጉ (intentional) ቢሆኑ ኑሮ ያለጥርጥር መፅሐፉ ላይ ለውጥ ይታይ ነበር ነገር ግን ይህ የተከሰተው ምናልባትም ከእነሱ በፊት የነበሩት አዘጋጆች በስህተት የፅሁፉን ቃላት ቀይረዋቸዋል ብለው ፀሐፊዎቹ ስላመኑ ብቻ ሊሆን ይችላል:: በአብዛኛው አላማቸው ግን ትውፊቱን መለወጥ ሳይሆን መጠበቅ ነበር::" በማለት ከዚ በፊት የተመለከትነው ፀሐፊዎች ሆን ብለው ቃላትን ሊለውጡ ይችላሉ የሚለውን ሃሳብ እራሱ በመጥፎ ጎኑ ሳይሆን በምን ምክንያት ሊከሰት እንደሚችል ምልከታውን አስቀምጧል:: ጣድያ ሰምአቱ ብራና ላይ ከ 11 ጊዜ በላይ የጠቀሰው ይህ ፕሮፌሰር ይህንን ሃሳቡን ግን በመፅሐፉ ላይ ሳይጠቅሰው አልፏል ሳላህ የባርት ኤርማን መፅሐፍ ሙሉውን አላነበበው እንደሆነ ባላቅም:: እናም በተደጋጋሚ እንዳልኩት textual criticism ጥናት ለእስልምና የሚጠቅም ሳይሆን ምንም ወገንተኝነትን ሳናሳይ የምናጠናው ከሆነ የመፅሐፍ ቅዱስን እውነተኝነት ያረጋግጥልናል::

Открыть в Telegram
Просмотры132−20%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#15604Текст

Переслано из ΦΩΣ (light)

የማርቆስ ወንጌል ረጅሙ አስተላለቅ መደምደሚያ እስካሁን ያየናቸውን በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚገኙትን ጥንታውያን ከ 1 እስከ 4 መቶ ክፍለ ዘመን የነእደክታባት እና የቤተክርስቲያን አባቶች ምስክርነትን ይዘን እውነትም የ ማርቆስ ወንጌል ረጅሙ አስተላለቅ ከ ቁጥር 9 እስከ 20 ድረስ ያለው ታማኝ እንደነበሩ እና በማርቆስ እንደተፃፉ መረዳት ያችላል:: ከዚህም ተነስተን ይሄንን ማለት እንችላለን :- 1. በቂ አስተማማኝነት ያላቸው ማስረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ የማርቆስ ወንጌል ምዕራፍ 16 ቁጥር 9 እስከ 20 ያሉት ክፍሎች፣ በሮም, በታናሿ አዥያ, በፍልስጤም, በሶርያ, በግብፅ, በቁስጥንጥንያ, በሰሜን አፍሪካ, በጎል እና በብሪታንያ በሚገኙት የመጀመሪያዎቹ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ እንደ ወንጌሉ አካል ተቀባይነት አግኝተው ነበር። እስከ 350 ዓ.ም. አካባቢ ድረስ፣ የማርቆስ ወንጌል ምዕራፍ 16 ቁጥር 9-20 በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አልተካተቱም ነበር ብለው የሚያመለክቱት ቦታዎች ግብፅ እና ቂሣርያ (ከግብፅ የመጡ የእጅ ጽሑፎች በቤተ መጻሕፍቱ ውስጥ ይገኙበት የነበረ ቦታ) ብቻ ናቸው። 2. ማርቆስ ጽሑፉን በምዕራፍ 16 ቁጥር 8 መጨረሻ ላይ እንዲያቆም አላሰበም ነበር ብሎ ለማመን በቂ ምክንያቶች አሉ። ማርቆስ ጽሑፉን ሆን ብሎ በምዕራፍ 16 ቁጥር 8 መጨረሻ ላይ አቆመው የሚለው አመለካከት ምክንያታዊ አይደለም። የማርቆስ ወንጌል ምዕራፍ 16ቁጥር 8 ላይ የሚያበቃ ከሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት ከተነሳ በሁአላ ከደቀመዛሙርቱ ጋር የተገናኘበትን እውነተኛ ክፍተት ላናይ ነዉ ማለት ነዉ :: ጌታችን በዚሁ ወንጌል ላይ ለደወመዛሙርቱ 3 ጊዜ ከሞት እንደሚነሳ ነግሯቸዋል:: ታዲያ ጌታችን ስለ ራሱ ትንሣኤ 3 ጊዜ ከተነበየ በሁአላ ይህን ሲፈፀም አለማየት ትንቢቱን በራሱ ሙሉ ሊያደርግልን አይችልም የማርቆስ ወንጌል ፀሐፍም በተደጋጋሚ ይሄንን ትንቢት ፅፎንል ከትንሳኤው በሁአላ ያለውን ወሳኝ ክፍል በእንጥልጥል ይተወዋል ማለት አይቻልም በመሆኑም እነዚህ የመጨረሻዎች 12 ቁጥሮች በዚሁ በማርቆስ ወንጌል ፀሐፊ መፃፉን እናውቃለን:: 3. በኔሮ ዘመነ መንግሥት ማርቆስ በሮም ስለነበረው አገልግሎት እና በአሌክሳንድሪያ ስለተፈጸመው ሰማዕትነቱ የሚናገሩት ትውፊቶች የማርቆስ ወንጌል ዝግጅት በድንገት ለምን እንደተቋረጠ የሚያብራራ ታሪካዊ ሁኔታን ያሳያሉ። 4. ከ300 ዓ.ም. በፊት የነበሩ ምንም ዓይነት ውጫዊ ማስረጃዎች፣ የማርቆስ ወንጌል ምዕራፍ 16 ቁጥር 9 እስከ 20 በወንጌሉ ውስጥ አልነበሩም ብለው አያመለክቱም። 5. የማርቆስ ወንጌል ምዕራፍ 16 ቁጥር 9 እስከ 20 ያሉት ክፍሎች፣ በማርቆስ የተጻፉ አለመሆናቸውን ለማሳየት እንደ ማስረጃ የቀረቡት የጽሑፍ ዘይቤ ልዩነቶች፣ እጅግ አናሳ ናቸው:: ወይም ደግሞ ማርቆስ እነዚህን ክፍሎች ወንጌሉን ከመጻፉ በፊት እንደ ገለልተኛ ጽሑፍ አድርጎ ጽፏቸው ከሆነ፣ ይህ የሚያሳየው ክፍሎቹ የተጻፉት ከምዕራፍ 16 ቁጥር 8 ቀጥለው የሚመጡ ማጠቃለያዎች ሆነው እንዳልሆነ ብቻ ነው፤ እንጂ ማርቆስ ራሱ እንዳልጻፋቸው የሚያሳይ አይደለም። 6. በአሌክሳንድሪያ የነበሩት የመጀመሪያዎቹ የጽሑፍ ቅጂዎች ውስጥ፣ የማርቆስ ወንጌል ምዕራፍ 16 ቁጥር 9 እስከ 20 የጠፉበትን ሁኔታ ሊያስረዱ የሚችሉ በርካታ ምክንያታዊ አጋጣሚዎች አሉ። 7.የማርቆስ ወንጌልን እንደ “የጴጥሮስ ትውስታ" (Memoirs of Peter) አድርጎ የመመልከት ጠንካራ ዝንባሌ በመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች ዘንድ እንደነበር የሚያሳዩ ማስረጃዎች አሉ። የማርቆስ ወንጌል ምዕራፍ 16 ቁጥሮች 9 እስከ 20፣ ከጴጥሮስ ትውስታዎች (Memoirs) የተለየ እና በማርቆስ ቀደም ብሎ የተጻፈ ጽሑፍ ተደርጎ ቢታሰብ ኖሮ፣ ይህ ሁኔታ በግብፅ የነበሩ ጥንቁቅ ቅጂ አዘጋጆች (copyists) በሁለተኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ በግብፅ ይገኙ በነበሩ የእጅ ጽሑፎች (codices) ውስጥ እነዚህን ቁጥሮች እንዲያስወግዱ ምክንያት ሊሆን ይችል ነበር። ስለዚህ፣ የማርቆስ ወንጌል ምዕራፍ 16 ቁጥሮች 9 እስከ 20፣ ወንጌሉ ለመጀመሪያ ጊዜ ለቤተክርስቲያን አገልግሎት ከመሰራጨቱ በፊትም እንኳ የማርቆስ ወንጌል አካል ነበሩ ብለን መደምደም ያስችለናል። በመሆኑም የማርቆስ ወንጌል ምዕራፍ 16 ቁጥሮች 9 እስከ 20 በማርቆስ ወንጌል ቀኖናዊ ጽሑፍ ውስጥ የሚገኙ መሆናቸው ሊሰመርበት ይገባል። በ 5 ክፍል ያቀረብነው የማርቆስ ወንጌል አስተላለቅን ከተመለከትን በቀጣይ የtextual criticism ጥናታችንም ይቀጥላል::

Открыть в Telegram
Просмотры118−28%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—