Кабинет

Посты канала 🌺 ለስኬታማ ቤተሰብ 🌺

сначала новые

#806Фото
Просмотры182−41%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#805Фото
Просмотры201−35%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#804Фото
Просмотры352+14%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#803Текст
Просмотры560+82%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#802Фото

Переслано из ኢብኑ መስኡድ ኢስላሚክ ሴንተር – አዲስ አበባ ibnu Mas'oud islamic center

የተጣሉ ሰዎችን ማስታረቅ አላህ እንዲህ ብሏል “ ከውይይታቸው በምጽዋት ወይም በበጎ ስራ ወይም በሰዎች መካከል በማስታረቅ ከሚያዙ ሰዎች ውይይት በስተቀር በብዙው ውስጥ ደግነገር የለበትም ይሄንንም ( የተባለውን ) የአሏህን ውዴታ ለመፈለግ የሚሰራ ሰው ታላቅ ምንዳን እንሰጠዋለን ” ኒሳዕ 114 የተጣሉ ሰዎችን ማስታረቅ አጅሩ ከፍተኛ ነው:: ነቢያችን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል " ከጾም ከሶላት ከሶደቃ በደረጃ የሚበልጥን ነገር ልንገራችሁ እንዴ ? እነርሱም አዎ፣ እንዴታ! አሉ ፣ እርሳቸውም " ሰዎችን ማስታረቅነው " አሉ በሰዎች መሀል ማስታረቅ የነቢያት አንዱ ስራ ነበር:: ነቢያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ረዥም ርቀት ተጉዘዉ ሰዎችን ያስታርቁ ነበር ። አንድ ጊዜ ሰዎች እርስ በእርስ እየተገዳደሉ መሆናቸዉን መረጃ ደረሳቸዉ ከዚያም ለሰሃባዎቻቸዉ ተነሱ እንሂድ እና እናስታርቃቸዉ አሉ። ነገር ግን አስታራቂ ሰዉ አገናዛቢ ፣ ጥበበኛ እና ንቁ መሆን ይገባዋል። እነዚህን ቁልፍ ችሎታዎችን ሳይላበስ በሰዎች መሀል ለማስታረቅ ዘው ብሎ የገባ ሰው ግን ይበልጥ ችግሩን ከማባባስ ውጭ የሚያስገኘው ጥቅም የለም :: በሰዎች መሀከል ማስታረቅ አሳሳቢ እና ትልቅ ስራ መሆኑን ከሚያመለክቱ ነገሮች አንዱ ሸሪዐ ዉሸትን ለሚያስታርቅ ሰው መፍቀዱ ነዉ::https://www.tiktok.com/@ibnu.masoud.islam?_r=1&_t=ZS-99tey35SEBW

Открыть в Telegram
Просмотры423+37%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#801Фото

Переслано из ኢብኑ መስኡድ ኢስላሚክ ሴንተር – አዲስ አበባ ibnu Mas'oud islamic center

📣 بشرى سارة للطالبات مجالس علمية متميزة للنساء ✔️ تنبيه:- الدعوة خاصة بالنساء. يسرُّ مركز ابن مسعود الإسلامي أن يدعو الأخوات الكريمات لحضور مجالس علمية وتربوية متميزة، تقدمها الأستاذة الفاضلة أم ليلى من المملكة العربية السعودية، وذلك وفق البرنامج الآتي: 📖  أولًا: شرح رسالة «معالم التوحيد» الدرس الأول: أهمية التوحيد وخصائصه وأنواعه. الدرس الثاني: تحقيق التوحيد، ونواقضه ونواقصه. الدرس الثالث: مصدر التوحيد وفوائده وثماره. 📖 ثانيًا: دروس ومحاضرات متنوعة - سنن قلَّ العمل بها. - دور المرأة في الإصلاح وحماية المجتمع. - التوبة وأهميتها في حياة المسلم. 📅 التاريخ: يومي الاثنين والثلثاء، ٢٦-٢٧ أكتوبر ٢٠٢٦م ⏳ وقت المحاضرة: العاشرة صباحا (الساعة الرابعة صباحا بالتوقيت المحلي) 📍 المكان: معهد دار الحديث بمركز ابن مسعود الإسلامي – حي ١٨، أديس أبابا نسأل الله أن يجعل هذه المجالس مباركة نافعة، وأن يرزقنا جميعًا العلم النافع والعمل الصالح. مركز ابن مسعود الإسلامي ____ 🕌 ibnu Masoud islamic Center t.me/merkezuna

Открыть в Telegram
Просмотры455+48%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#800Фото
Просмотры1 220+296%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#798Фото
Просмотры1 100+257%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#797Фото
Просмотры914+197%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#796Фото
Просмотры704+128%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#795Текст

Переслано из የኡስታዝ ኢልያስ አሕመድ የትምህርት መድረክ (official)

🌙 የጎዳና ኢፍጣር🌙 =============== 🖌 በኢልያስ አሕመድ በቅድሚያ ይህን ፕሮግራም ለማሰናዳት በቅንነት የሚለፉ ግለሰቦችና ድርጅቶችን አላህ የኒያቸውን እንዲሰጣቸው እንለምናለን፤ ከዚህ በታች ያለው አጭር ፅሑፍ የልፋታቸው መሰረት የተስተካከለ እንዲሆን ታስቦ በተቆርቋሪነት የተከተበ ነው።               ››››› ‹‹‹‹‹ በህብረት ማፍጠር ሁለት አይነት አፈፃፀሞች ሊኖሩት ይችላል፦ 1ኛ/ ለማፍጠር መሰባሰቡን ዋና ኢላማ ሳያደርጉ በተወሰኑ አጋጣሚዎች በህብረት ማፍጠር ሲሆን ይህም እንደማይወገዝ ግልፅ ነው። ለምሳሌ፦ ለሰላት ወደ መስጂድ የመጣውን ስብስብ ወይም ድሆችን በአንድ ቦታ ለማስፈጠር የሚኖረው መሰባብሰብ ተቃውሞ ሊነሳበት አይችልም። ዘመድና ጓደኛን ጠርቶ በጋራ ማፍጠርም እንደተራ ግብዣ ሊታይ ይችላል። ፆመኛን ማስፈጠርን አስመልክቶ የተወራውን ምንዳ ለማግኘት ከታሰበ ደግሞ እንደ እሳቤው የተወደደ ሊሆን ይችላል። ብዙ ዑለማዎች የፈቀዱትም በዚህኛው ምድብ የሚካተተውን ነው። 2ኛው/ ለኢፍጣር መሰባሰቡ ራሱ እንደ ዋና ግብ ታልሞና ይህንንም በሚያሳብቁ ተግባራት ታጅቦ በስፋት የሚተገበር አፈፃፀም ሲሆን ይህ የቢድዓ መገለጫን ሊላበስ ይችላል። በሀገራችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተለመደው የጎዳና ኢፍጣር ይህንን ይዘት እንደተላበሰ ከሚያሳዩ ምልክቶች መካከል፦ 👉 እንደ በዓላት የሚጠበቅ ህዝባዊ ኩነት መሆኑ፣ (Grand Iftar 1, 2 እየተባለ ዘንድሮ 4ኛው ላይ ደርሰናል!) 👉 ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የበድር ዘመቻ የተካሄደበት የረመዳን 17ኛው እለት ለዚህ አመታዊ መሰባሰቢያ እንዲሆን በተደጋጋሚ መመረጡ፣ 👉 ሰዎች በነቂስ ወጥተው እንዲታደሙ ሰፊ ጥሪ መደረጉ፣ 👉 በታዳሚያን ብዛት ከሌሎች አገራት ጋር ፉክክር ውስጥ የተገባበት መሆኑ፣ እና ሌሎች አባሪ ሂደቶች ሊጠቀሱ ይችላሉ። የነዚህ ሂደቶች ስብስብ ተግባሩን ራሱን የቻለ አዲስ የሙስሊሞች ይፋዊ ምልክት (ሺዓር) እያደረገው ነው። 📌 ታላቁ ኢማም #ኢብኑ_ተይሚያህ በዲን ውስጥ ስለሚጨመሩ የፈጠራ በዓላት በሚያብራሩበት አውድ ስለ በዓላት ምንነት ሲያስረዱ የሚከተለውን ይላሉ፦ «“ዒድ” (በዓል) በተለመደ መልኩ ለሚደጋገም ሁሉን አቀፍ መሰባሰብ የሚሰጥ ስያሜ ሲሆን በየአመቱ፣ በየሳምንቱ፣ በየወሩ ወይም በተመሳሳይ ሁኔታ (በውስን ቀናት) የሚመላለስ ነው። በዓል የተወሰኑ ነገሮችን አቅፎ ይይዛል፤ ከነሱ መካከል፦ እንደ ዒድ አል-ፊጥር እና እንደ ጁሙዓ የሚመላለስ ቀን፣ (በቀኑ) መሰባሰብ፣ ይህን ተከትለው የሚመጡ አምልኳዊ ወይም ልማዳዊ ተግባራት ይገኛሉ። በዓል በውስን ቦታ የተገደበ ሊሆን ይችላል፤ ያልተገደበም ሊሆን ይችላል፤ እነዚህ ነገሮች ሁሉ (በነጠላ) ዒድ ሊሰኙ ይችላሉ.... “ዒድ” የሚለው ቃል ለእለቱና በውስጡ ላለው ተግባር ጥምረት የሚሰጥ ስም ሊሆን ይችላል፤ ይህም አብዛኛው (አጠቃቀሙ) ነው።» [“ኢቅቲዷኡ’ሲራጢ’ል’ሙስተቂም” (1/496 – 497)] 📌 በሌላ ቦታም እንዲህ ብለዋል፦ «ከተደነገጉት መሰባሰቦች ውጪ ሳምንታት፣ ወራት፣ ወይም አመታት በተደጋገሙ ቁጥር የሚደጋገም  መሰባብሰብን በቋሚነት መያዝ ለአምስቱ ሰላቶች፣ ለጁሙዓ፣ ለሁለቱ ዒዶችና ለሐጅ ከመሰባብሰብ ጋር ይመሳሰላል፤ ፈጠራና አዲስ ተግባር ማለት ይህ ነው!)) [“ኢቅቲዷኡ’ሲራጢ’ል’ሙስተቂም” (2/140)] 📌 አለፍ ብለውም እንዲህ ይላሉ፦ «ከነዚህ (ከተደነገጉት) መሰባሰቦች ባሻገር የሚለመድ ተጨማሪ መሰባሰብ ከተጀመረ አላህ ከደነገገውና ካፀደቀው ፈለግ ጋር የሚመሳሰል ይሆናል …. - ለብቻው የሆነ ግለሰብ ወይም ውስን ስብስቦች አንዳንዴ ከሚሰሩት በተለየ መልኩ!)) [“ኢቅቲዷኡ’ሲራጢ’ል’ሙስተቂም” (2/144)] ይህ ማብራሪያ ሰዎች በየውስን ጊዜ በታወቀ ቀጠሮ የሚፈፅሙት ህዝባዊ ስብስብ እንደ በዓል ባይታቀድ እንኳ በዓላዊ ይዘትን እንደሚላበስ ያሳያል። አንድ ነገር በጥቅሉ የሚፈቀድ፣ ብሎም የሚደነገግ ከመሆኑ ጋር በአፈፃፀሙ ረገድ የሚኖሩ ተጓዳኝ ነገሮች ብይኑ እንዲቀየር ሊያደርጉ ይችላሉ። 📌 ታዋቂው ዓሊም #ኢብኑ_ደቂቅ_አል_ዒድ አንዳንድ ሸሪዓዊ አፈፃፀሞችን ለመተግበር በደካማ የሐዲሥ ዘገባ ላይ ስለመመርኮዝ የሚነሳውን ውዝግብ አስመልክቶ እንዲህ ይላሉ፦ «የ“መውዱዕ” (የተቀነባበረ የውሸት ሐዲሥ) ክልል ውስጥ ያልገባ ደዒፍ (ደካማ) ከሆነ በዲን ላይ አዲስ ይፋዊ ምልክት “ሺዓር” የሚፈጥር ከሆነ ይከለከላል፤ ካልሆነ ደግሞ ምልከታ የሚቸረው ይሆናል...» [“ኢሕካሙ’ል-አሕካም” (1/501)] 👉 አንድን ተግባር እንደ “ሺዓር” ከሚያስቆጥሩት የአፈፃፀም ሂደቶች መካከል ሰዎች ተጠራርተው የሚሰባሰቡበት ኩነት መሆኑ ነው፤ በተለይ እንደ ዒድ ሰላት በጎዳና/በአደባባይ ላይ የሚተገበር ከሆነ! ይህን የሚያብራራ አንድ ምሳሌ እንጥቀስ፦ ሰዎች በተሰባሰቡበት አጋጣሚ አንዳንዴ ዱዓ ማድረግ የሚቻል ከመሆኑ ጋር ይህን በህብረት ለመፈፀም መጠራራትን ብዙ የኢስላም ሊቃውንት አይደግፉም። 📌 #አል_ኢማም_አሕመድ እንዲህ ተብለው ተጠየቁ፦ «ሰዎች ተሰባስበው አላህን መለመናቸውና እጃቸውንም ማንሳታቸው ይጠላል?» እርሳቸውም፦ «مَا أَكْرَهُهُ لِلْإِخْوَانِ إذَا لَمْ يَجْتَمِعُوا عَلَى عَمْدٍ إلَّا أَنْ يَكْثُرُوا» = «ሆን ብለው ካልተሰባሰቡ ለ(ዲን) ወንድማማቾች አልጠላውም – ካልበዙ በስተቀር!» 📌 #አል_ኢማም_ኢስሓቅ ኢብኑ ራሀወይህ ሲጠየቁም ተመሳሳይ መልስ ሰጥተዋል። «ካልበዙ በስተቀር» ሲሉ ልማድ በማድረግ እስካልተበራከቱ ድረስ ማለታቸው እንደሆነ ጠያቂው (ኢስሓቅ ኢብኑ መንሱር) ተናግረዋል! [“መሳኢሉ’ል-ኢማሚ አሕመድ ወኢስሓቅ” (9/4879)፣ “ኢቅቲዷኡ’ሲራጢ’ል’ሙስተቂም” (2/140)]፣ “አል-ኣዳብ አሽ-ሸርዒይ-ያህ” ሊ’ብኒ ሙፍሊሕ (2/103)] 👉 ስለሆነም ነገሩ ከዚህ በላይ ሳያድግ መግታቱ አስፈላጊ ነው። ይህ ከዚህ በፊት የተስተዋሉ የአፈፃፀም ግድፈቶችን ከግምት ሳናስገባ የምንደርስበት መደምደሚያ ሲሆን፤ ያለ በቂ ምክንያት መንገድ መዘጋጋት፣ አግባብ ያልሆነ የወንድና የሴት መቀላቀል፣ የሴቶች ምስል በሚዲያ የሚሰራጭበት ቀረፃ፣ ሴቶች በምሽት መንገላታታቸው፣ በሙዚቃ መሳሪያ የታጀበ "ነሺዳ"፣ የምግብ ብክነት እና መሰል ጥፋቶች የሚታከሉበት ከሆነ ደግሞ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ይሆናል። አዎን! ፕሮግራሙ ከዚህ በፊት ሞራላዊ ጥቅምን አስገኝቶ ሊሆን ይችላል፤  ነገር ግን በውስጡ ከላይ የጠቆምነውን አመዛኝ ጉዳት ማካተቱ ለመታቀብ በቂ እንደሆነ አስባለሁ። አላህ ይበልጥ አዋቂ ነው። ረመዳን 15/1445 ____ @ustazilyas

Открыть в Telegram
Просмотры801+160%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#794Фото
Просмотры837+172%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#793Фото
Просмотры862+180%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#789Фото
Просмотры893+190%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#788Фото
Просмотры849+176%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—