Кабинет

Посты канала የአረብ ገንዳ መስጂድ ወጣቶች

сначала новые

#5982Текст
Просмотры10−96%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#5981Текст

Переслано из Islam Mindset

ቁርዓን ሲያፀዳህ ማጣት ፈተና መሆኑን አብዘሀኛው ሰው ዕውቀቱ ቢኖረውም በትግዕስት የሚያልፉት ጥቂቶች ናቸው። ምክንያቱም ትግዕት የጊዜ አቀበት ነው።አቀበቱን መውጣት የሚችለው ደግሞ የኢማን ነዳጅ ብቻ ያለው ነው።በተቃራኒው ማግኘት ፈተና መሆኑን የሚረዱት ሰዎች በጣም ጥቂቶች ናቸው። ኧረ እንዳውም አላህ የወደዳቸው የሚመስላቸው ሰዎች አሁን አሁን ተበራክተዋል። ለዛም ነው አላህ ያዘነለት ሲቀር ያገኘው ሀብት ከሱ የሚርቀው አይመስለውም። አስተማማኝ ደረጃ ላይ የደረሰ ይመስለዋል። አላህ የሰጠው ሳይሆን በዕውቀቱ እና በብልሃቱ ያገኘው ይመስለዋል። ስንቶች ከሱ በላይ ዕውቀት ኖሯቸው ብልሃት ኖሯቸው እንዳላገኙት አያስተነትንም።በልቡ ቁርዓን የጠቀሰውን ቃሩን ያላትን ንግግር የአስተሳሰቡ መሰረት አድርጎት ያርፈዋል። ማግኘት የሚያከብደ፣ ሰውዬው ምን ያህል የነፍስያ (የእጅ ፍሬን) እንዳለው የሚፈተንበት መንገድ መሆኑ ነው። ምክንያቱም መንገዱ ቁልቁል እና በቀላሉ የሚያንደረድር ነው። የነፍስያ የእጅ ፍሬን ደግሞ "ተዝኪያ" ይባላል። ...ማለትም ቁርዓን " ወዩዘኪሒም.." ብሎ የጠቀሰው ሙዕሚኖችን ከነፍስያ ቆሻሻ የሚያጠራ መፅሃፍ ነው። በብዛት የቁርዓን ጓደኛ ስትሆን ቁርዓን በዱንያ ላይ የሚሰጥህ ትልቁ ሽልማት ነው። ሰውዬው እዚህ ደረጃ ላይ ሳይደርስ ገንዘብ ከተሰጠው የነፍስያ የእጅ ፍሬኑ አስተማማኝ አይደለም። ቅድሚያ መስጠት የሚገባውን ጉዳይ ተራ ያደርገዋል። ለዛም ነው በብዛት ገንዘብ ያላቸው ሰዎች የመጀመሪያው ሶፍ ላይ የማናገኛቸው! ... ለዛም ነው ዘካን እንደ ሰደቃ ሲያደርጉት የምንመለከታቸው ...ለዛም ነው ረመዳንን የኢባዳ ወር ሳይሆን የምግብ ወር እንደሆነ ሊያሳዩን የሚሞክሩት...! ባጠቃላይ ልክ ያልሆነውን ሚዛን ልክ እንደሆነ በገንዘባቸው ሊያስረዱን ይሞክራሉ። ምክንያቱም ቁርዓንን ትተውታል።ግዜ አይሰጡትም፣ የሚለውንም አያስተነትኑም፣ የሚያዛቸውን እንኳን ሊተገብሩ ይቅር እና ዝግጁም አይደሉም። በነሱ አስተሳሰብ ሌላ ከፍ ያለ ሀሳብ ላይ ናቸው። አላህ ያዘነለት ሲቀር...አላህ በቁርዓኑም እንዳለው:- وَقَالَ الرَّسُولُ يَا رَبِّ إِنَّ قَوْمِي اتَّخَذُوا هَٰذَا الْقُرْآنَ مَهْجُورًا መልክተኛውም «ጌታዬ ሆይ! ሕዝቦቼ ይህንን ቁርኣን የተተወ ነገር አድርገው ያዙት» አለ፡፡... አላህ በቁርዓኑ ያፀዳው ሰው ለሁሉም ነገር ብቁ ሰዉ ነው። ምክንያቱም ምንም ያህል ዕውቀት እና ብልሃት ቢኖረውም በዱንያ ሲኖር አላህ እንዴት እንደሚሰራ በጥልቀት ይረዳል....! በዕውቀቱ እና በብልሃቱ ሳይሆን ሰበቡን የሰጠውን ጌታ ሁሌም ያስቀድማል። ሁሉም ነገር ከአላህ መሆኑን ይመሰክራል፣ ነፍሱም የብልሃቱ እና የዕውቀቱ ባለቤት እንዳልሆነች ያሳምናታል። #viralpost #like #engagement #share

Открыть в Telegram
Просмотры247−11%к среднему
Пересылки—
Реакции2
Комментарии—
#5979Текст
Просмотры712+155%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#5976Текст

Переслано из Islam Mindset

የሆነ ግዜ ላይ ትንሽ በሚባሉ ነገሮች የደስታ ጣራ ላይ ትደርስ ነበር። አሁን ደግሞ ብዙ ነገሮችን አላህ ሰጥቶህ በፊት ከምትደሰተው አንፃር እንኳን ትንሽ ልትደሰት ቀርቶ ጭንቀቱ እና ጥበቱ ቢጠፋልህ ትመኛለህ። ቆም ብለህ አስበኸው ታውቃለህ?! ... ብዙ ነገሮችን አላህ ሰጥቶህ አለመደሰትህ አይደለም ያንተ ጥፋት ... ጥፋቱ ቆም ብለህ "ለምን አልተደሰትኩም?" ብለህ አለመጠየቅህ ነው! ፈጣሪያችን አላህም ሱ.ወ የሚያወራው ይሄንን ጉዳይ ነው... ቃሩንን ከዚያ ከቆሸሸ ዉዳቂ በግ እና ፍየል ጠባቂነት አውጥቶት እስካሁን በሰው ልጆች ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ የሀብት ማማ ላይ ሲያስቀምጠው አላህ ሱ.ወ በዚች ተራ ዱንያ ሁሉንም ነገር ቻይ መሆኑን በቃሩን ሲያስረዳህ በተቃራኒው ደግሞ የሰውን የእኔን እና ያንተን ባህሪ መልሶ በቃሩን ንግግር ያስተምረናል። "አላህ በአንተ ላይ መልካም እንደዋለል ሁሉ መልካምነት ለሚሹ መልካም ዋልላቸው" ሲባል ቃሩንም "እኔ ኮ ያመጣሁት በማውቀው እውቀት ተራቅቄ እና ተጠብቤ ነው!" ብሎ መመለሱን ቁርዓን አስቀምጦልሃል። ምንም ነገር ሳይኖርህ በዛ የደስታ ጥግ ሆነህ አሁን ብዙ ነገር አላህ ሱ.ወ ሲሰጥህ ለምንድን ነው ደስታህ የራቀው?! ያውም እንደቃሩን ቁልፉ ብቻ ጠንካራ በሚባሉ ሰዎች የሚሸከሙት ሀብት አልሰጠህ ደስታህ የተነጠቀው ?! ...ችግሩ እዚህ ላይ ነው የሚጀምረው, አለኝ የምትለው ነገር ሁሉ ከሚዛኑ ውጪ መመዘን ስትጀምር ምናልባች በግዜያዊ ሊያስደስትህ ይችላል። ግን እጥፍ ድርብ ሆኖ በህይወት እስካለህ ድረስ ጭንቀት ይሆናል። ወደ ሚዛኑ እስክትመልሰው ድረስ! በገንዘብ አልኩህ እንጂ እንደ ገንዘብ ሁሉ ሁሉም ነገር አላህ ያስቀመጠለት የተመጠነ ሚዛን አለው። እንዳትገረም ጤንነት ራሱ የራሱ አላህ ሱ.ወ ያስቀመጠለት ሚዛን አለው። አላህ ሱ.ወ ባስቀመጠው መልኩ የፈቀደልህን ስትበላ፣ ስትጠጣ እና ስትለብስ ብቻ ነው ጤናማ ነህ ምትባለው! ሰዎች የፈበረኩት ሚዛን(ልኬት) ስትከተል ደስታህ እንደ ጉም ተኖ ይጠፋል። ከዚያም የነገሮች ውስብስብነት እየጨመሩ ስለሚመጡ አላህ ሱ.ወ ያስቀመጠውን ሚዛን ከጀርባህ ታደርገው እና ፍሬ በሌለው አስተሳሰብ ታጭቀህ አንተ ያደራጀኸውን መሃይምነትህን እንደ እውቀት መመልከት ትጀምራለህ። ምክንያቱም ብዙሃኑ የሚለውን ስለምታስተጋባ! ከዚያም ለነገሮች ባርያ ሆነህ ታርፈዋለህ። ይሄንን ጉዳይ ነው አላህ ሱ.ወ የሚናገረው " አላህ ነቢዩን ﷺ አስጠንቅቆ እንዲህ አለ፦ " በምድር ላይ ያሉት ብዙዎቹ ሰዎች ከቅን መንገድ ርቀዋል። አንተ እነሱን ብትከተል፣ ከአላህ መንገድ ያስቱሃል።" · ከዚያም አላህ እንዲህ አለ፦ "እነሱ ከግምት በስተቀር ሌላ አይከተሉም፤ እነሱ የሚሠሩትም መገመትና መቀስቀስ ነው።" ሰላማችሁ ይብዛልኝ ቅኑን መንገድ ለተከተለ ሁሉ🤲 #follow #engagement #like

Открыть в Telegram
Просмотры671+141%к среднему
Пересылки—
Реакции1
Комментарии—
#5975Текст

Переслано из Islam Mindset

ምናልባች በድንገት እገሌ ሞተ ስትባል ያስደነግጠሃል! ...ያስደነግጣልም!!!😓 በተለይ ደግሞ ታዳጊ ከሆነ፣ በተለይ ወጣት ከሆነ! አሁን አሁን እማ ህይወታችን ሁሉ ቧልት የበዛበት ስለሆነ በሶሻል ሚዲያ አንድ ታላቅ ሼኽ ሞት ከመባል ይልቅ በእንትና #podcast ሲያጫውተን የነበረው ሞተ ብንባል በጣም ያሳዝነናል!...ይሄ ምንም የምንደባብቀው ጉዳይ አይደለም! ምክንያቱም ዉድ ጊዜያችን ለሳቅ እና ለቧልት ስለሰጠነው ።ይሄ አይደለም ከባዱ የኛ ውድቀት... ከባዱ የኛ ውድቀት ሳይኮሎጂካሊ እኛ ያ ወጣት አልያም ታዳጊ እንደደረሰበት እንሆናለን ብለን ቅንጣት ታክል እንኳን አለመሰማቱ ምን ያህል ከአላህ እንደራቅን ብቸኛ ማሳያው ነው። ጥቅጥቅ ባለ የልብ ጨለማ ውስጥ እየኖርን ግን ደግሞ እዚህ ግባ በማይባል ተራ ምክንያት መኖርን እንሻለን፣ እንጓጓለን! ያንኑ የተለመደውን ልብን በሚያጨልም ስራ ለመሰማራት! ምሳሌ የሚሆኑ ባለ ታሪክ አባቶቻችን ፀሃይ ወታ ስትጠልቅ ደስታቸው ወደር የለውም ነበር።ምክንያቱም የሶላተለይል ግዜ ስለደረሱ...በሶላት እና በዚክር ለማንጋት ዘንድ አላህ ዕድል ስለሰጣቸው!...አሁን የኔን እና ያንተን ሆኔታ እንዳው ዝም ነው!...መላዒካን ማድከም ነው ብናወራው!...የሪዝቅን ጉዳይ መቼም ቀድሞውኑ ፅፎት እንጂ በኛ ስራ ብቻ ቢሆን ኖሮ ሁላችንም በራሃብ እንሞት ነበር። ግን አላህ ሱ.ወ እንደሱ አላደረገውም! የበፊቶቹ በኢባዳ ጠልቀው አላህን ራህመት ቢሹም ይርበተበቱ ነበር" ይምረኝ ይሆን!" እያሉ, እኛ ደግሞ ያለ ኢባዳ በልበ ሙሉነት(በኮንፊደንስ) በአላህ ራህመት ነው ምንኖረው ስንል እንስተዋላለን። ስለሞት ሲታሰብ አንድ ነገር አስባለሁ። ሞት ከባድ የሚያደርገው የሞት ህመምን መቅመስ አይደለም!..ምክንያቱም አላህ ሁሉም ነፍስ ሞትን ቀማሽ ናት። ሞትን የሚያከብደው ነገር " ማች በሚሞትበት ቅፅበት የጀነት አልያም የጀሃነብ መሆኑን ማወቁ ነው።" ስንቶቻችሁ ይሄንን አስተውላችኋል።ለዛ ነው የሞተ ሰው የስራ መዝገቡ ተዘግቷል የሚባለው! አላህ አንድን ባርያ የሚረዳው የተሻለ የሚያደርገው በህይወት ሳለ ነው። ለዛ ነው ጊዜ ህይወት ነው የሚባለው አላህ ም ሱ.ወ በቁርዓን ላይ ሱረቱ - አል-ረዕድ ቁጥር 11 «እነሆ አላህ በአንድ ሕዝብ ያለውን ሁኔታ እስከሚቀይሩ ድረስ አይለውጠውም።» ያለው ማለትም አላህ አንድን ሕዝብ ከጸጋ ወደ መከራ፣ ወይም ከክብር ወደ ውርደት አይለውጥም — እስከሚለወጡ ድረስ። ይህ ለውጥ የሚጀምረው ከልብ ነው፤ ከነፍስ፣ ከድርጊት እና ከሀሳብ። አየህ ቤተሰብህ፣ ወንድምህ ፣ አልያም ጓደኛህ ወይም የምታደንቀው ምንም ይሆን ምን ሲሞት አዝነህ አልቅሰህ ግን በፊት ያለህበት መጥፎ ቦታ ላይ ካለህ አላህ በህይወት እያለህ አይረዳህም። የዚህም ትንሿ ምክንያት በምላስህ እንኳን ለትንሽ ግዜ አላህን ለማስታወስ አልጣርክም። ለዚህም ነው ረሱል ሰ.ዐ.ወ ( ያ አላህን የሚያስታውስ እና ያ አላህን የማያስታውስ ልክ በህይወት እንዳለ እና በህይወት እንደሌለ ነው የልዩነት ምሳሌያቸው!) ያሉት .... ሳይለቀስባቸው ከሞቱት ውስጥ አላህ አያድርገን...! ረጅም እድሜ ኖረው ኸይር ስራቸው ከበዛላቸው ውስጥ አላህ ያድርገን🤲 #followformore #ShareThisPost

Открыть в Telegram
Просмотры557+100%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#5974Текст

Переслано из Islam Mindset

በረካ ይሻልሃል ወይስ በአዕምሮህ ውስጥ ያስቀመጥከው የቁጥር ብዛት አብዘሀኛው ሰው ብዛትን ይመርጣል! ምክንያቱም ብዛት የሚታይ መሆኑ እና በቀላሉ ማመዛዘን ስለሚቻል! በዚህ ደግሞ ካፊሩም ሙሰሊሙም አንድ ነው። በረካን ለመረዳት እና ለማወቅ ግን በልብህ ውስጥ የኢማን ብርሃን ያስፈለገዋል። ካልሆነ ሁሌ እንደሌለህ ይሰማሃል። ሁሌ ዝቅ እንዳልክ ታስባለህ እውነቱ ግን ከዚህ በተቃራኒ መሆኑን ማወቅ የምትችለው ተደቡር ስታደርግ ብቻ ነው። ያኔ ወደራስህ መለስ ብለህ ወደአላህ ስትዞር እናም ከብዙ ተውበት እና መዋደቅ በኋላ ትንሽዬ የኢማን ብርሃን በልብህ ሲቸርህ በረካ የሚለውን በተግባር ትመለከተዋለህ። በምሳሌ እንኳን ብመስልልህ የውሻን ህይወት ተመልከት ሲዋለድ እንኳን ብዙ ነው። ቢያንስ አንዲት ሴት ውሻ በአንድ ግዜ ከ6 ቡችሎች በላይ ትወልዳለች። ነገር ግን ስንቶቹ ያድጋሉ?! ስንቶቹስ ይሞታሉ?! አላህ ይወቀው። ነገር ግን እንደመወለዳቸው ብዛት ሁሉም ቢያድጉ ከእኛ ከሰዎች በላይ ይበዙ ነበር። ግን አይደሉም...ያደጉትን እንኳን ብትመለከት ጥቂት ናቸው። ለሰው ልጆች እንኳን ጠቀሙ ቢባል ጥበቃ ብቻ ነው ስራቸው። ቤት መጠበቅ አልያም የቤት እንስሳዎችን መጠበቅ...አለቀ! ይሄ ብቻ ነው። በሌላ በኩል የበግን አልያም የፍየልን መሰል እንስሳዎችን ተመልከት ሲወለዱ እንኳን 1 ወይም 2 ቢበዛ ሶስት ነው። ነገር ግን ከውሾች ጋር ስታነፃፅራቸው ብዛት አላቸው። ጥቅማቸውም ሰፊ ነው። ስጋቸው ይበላል፣ ቆዳቸው ለአልባሳት ይጠቅማል፣ ፁጉራቸው ሳይቀር ለሰዎች ይጠቅማል። አየህ በረካ የሚለው ትርጉም እዚህ ላይ ይመጣል። ከላይ የጠቀስኩልህ እንሰሳቶች በአኗኗል ዘይቤያቸው እንኳን ይለያያሉ። ውሻ ለሊቱን ሙሉ ሲጮህ አድሮ ፈጅር ላይ ይተኛል። የበጎች እና ፍየሎች መሰል እንሰሳቶች ቀኑን ሙሉ ሳያርፉ ለሊት ይተኛሉ ። በረካ በቀላሉ ሲተረጎም ይሄንን ይመስላል። አላህ አንድን ሙስሊም ባርያውን ሲወደው በሁሉም ነገር በረካ ያደርግለታል። ልብ በል በቁጥር ያበዛለታል ሳይሆን ጥቅሙን ያበዛለታል...በግዜው፣ በቤተሰቡ፣ በገንዘቡ፣ በጓደኞቹ፣በዘመዶቹ፣ በሌሎቹም ነገሮች...ለዚህ ይመስላል ለረሱል ሰ.ዐ.ወ በላጭ ሰው ማነው ተብለው ሲጠየቁ " በላጩ ሰው ለሰዎች ጠቃሚ የሆነ ሰው ነው። " ብለው የመለሱት ...አላህ በረካ ይስጠን! የተሰጠንም በረካ የምናቅ የምንረዳም አላህ ያድርገን🤲 👉 #follow እና #like እያደረጋችሁ!

Открыть в Telegram
Просмотры602+116%к среднему
Пересылки—
Реакции2
Комментарии—
#5973Текст
Просмотры625+124%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#5972Текст

Переслано из Islam Mindset

አንተ ከየትኛዎቹ ውስጥ ነህ? የእውነት በአላህ ላይ ተስፋ አለህን?! አንዳንዶች እንደዚህ አይነት ጥያቄ ሲጠየቁ "ያለ አላህ ራህመት እንዴት ልንሆን ነው ታዲያ!" ይላሉ. ልክ ናቸው ያለ አላህ ራህመት ካልሆነ አንዲትም ፍጡር በምድር አትንቀሳቀስም ነበር። ግን ኮ ጥያቄውን በደንብ ያጤነው ሰው ምላሹ ስለራሱ ይሆናል። የአላህ ራህመት የአላህ በጎ ስራ ነው... "አንተ እንደ አላህ ባርያ በተግባርህ እንዴት ነው ተስፋ እያደረክ ያለኸው ነው?" ዋናው ጥያቄ...! 👉 አላህ ያዘዘህ ቦታ ላይ ከተገኘህ አንተ በአላህ ላይ በሙሉ ተስፋ ላይ ነህ..ተስፋ ከቆረጡትም አለመሆንህን ልነግርህ እወዳለሁ። ... 👉 አላህ ያዘዘህ ቦታ ላይ ግን ካልተገኘህ ምንም አይነት ምክንያት ብታቀርብ ተስፋ ከቆረጡት ውስጥ መሆንህ ላበስርህ እወዳለሁ!..... [ ۞ قُلْ يَا عِبَادِيَ الَّذِينَ أَسْرَفُوا عَلَىٰ أَنفُسِهِمْ لَا تَقْنَطُوا مِن رَّحْمَةِ اللَّهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ يَغْفِرُ الذُّنُوبَ جَمِيعًا ۚ إِنَّهُ هُوَ الْغَفُورُ الرَّحِيمُ ] سورة الزمر (آية 53) በላቸው «እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፡፡ አላህ ኃጢኣቶችን በመላ ይምራልና፡፡ እነሆ እርሱ መሓሪው አዛኙ ነውና፡፡ ......አንተ ከየትኛዎቹ ውስጥ ነህ???!.. ምክንያቱም ተስፋ በልብ, በዕምነት እና በተግባር ይገለፃልና....

Открыть в Telegram
Просмотры1 010+262%к среднему
Пересылки—
Реакции1
Комментарии—
#5970Текст
Просмотры906+225%к среднему
Пересылки—
Реакции2
Комментарии—
#5969Текст
Просмотры1 060+280%к среднему
Пересылки—
Реакции5
Комментарии—
#5968Текст
Просмотры1 140+309%к среднему
Пересылки—
Реакции3
Комментарии—
#5966Текст
Просмотры1 030+269%к среднему
Пересылки—
Реакции2
Комментарии—
#5963Текст
Просмотры747+168%к среднему
Пересылки—
Реакции1
Комментарии—