Посты канала ✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽
Переслано из ✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽
THE GLIMPSE OF HELLFIRE 🔥 (የጀሀነም እሳት እይታ) ~ "የጀሀነም እሳት እይታ" በሚል የቀረበ አጭር ዳዕዋ ~ ከጀሀነም እሳት አላህ ይጠብቀን ! #SHARE_The_خير
Открыть в TelegramПереслано из ✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽
.🗓️「 የጁምዓ ዕለት 」✨. 📏📏📏📏📏📏📏📏 ✅:በጁምዓ ዕለት የሚሰሩ ሱና ስራዎች 1⃣. ከፍተኛ ምንዳ ለማግኘት በግዜ ወደ ጁምዓ መስጂድ መሄድ። 🟧አቡ ሑረይራ ባስተላለፉት ሀዲስ ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል ፦ ⬅️የጁምዓ ሰላት ገላውን ታጥቦ በመጀመሪያው ሰዓት የተጓዘ ግመል እንዳቀረበ ነው ፣ በሁለተኛው ሰዓት የተጓዘ ከብት እንዳቀረበ ነው ፣ በሶተኛው ሰዓት የተጓዘ ቀንዳማ በግ እንዳቀረበ ነው ፣ በአራተኛው ሰዓት የተጓዘ ዶሮ እንዳቀረበ ነው ፤ በአምስተኛው ሰዓት የሄደ እንቁላል እንዳቀረበ ነው ፤ ኢማሙ ሚንበር ላይ ሲወጣ መላእክት ኹጥባ ለማድመጥ ይቀመጣሉ➡️ 🔘ቡኻሪ እና ሙስሊም 🔘 2⃣.ገላን መታጠብ 👆:ከላይ ባሳለፍነው ሀዲስ ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል ⬅️የጁምዓን ዕለት ገላውን ታጥቦ ….➡️ በየሳምነት ጁምዓ ገላ መታጠብ #ሱና ሲሆን በተለይ የሠውነት ጠረን ባለበት ሰው ይበረታል፡፡ 🔗:አንዳንድ ዑለማዎች ⬅️ጁምዓን ዕለት መታጠብ እያንዳንዱ አቅመ አዳም የደረሰ ሰው ላይ ግዴታ ነው➡️(ቡኻሪ ሙስሊም) የሚለውን ሀዲስ መሰረት በማድረግ በጁምዓ ገላ ትጥበት ግዴታ (ዋጂብ) ነው ይላሉ፡፡ 3⃣.ከልብሶቹ ጥሩውን መልበስ ➡️ኢብን ዑመር ባስተላለፉት ሀዲስ ‹‹ዑመር ኢብን ኸጣብ መስጂድ በር ላይ ከሰይራዕ የመጣ ካባ ተመልክተው ⬅️የአላህ መልዕክተኛ ሆይ ይህንን ካባ ገዝተው ለጁመዐና እንግዶች ሲመጡ ቢለብሱት?➡️ አል ቡኻሪ ይህንን ሀዲስ በጁምዓ ዕለት ጥሩን ልብስ መልበስ ሱና ስለ መሆኑ መረጃ አድርገው የተጠቀሙበት ሲሆን አልሃፊዝ ኢብን ሀጀር መረጃ ሊሆን የቻለው ነብዩ (ﷺ) የዑመርን ሀሳብ ባለመቃወም ስለተቀበሉት እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ 4⃣.በነብዩ (ﷺ) ላይ ሰላትና ሰላም ከሌላው ቀን በበለጠ መልኩ ማስፈን ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል ⬅️በጁምዓ ዕለት በይበልጥ እኔ ላይ ሰላት አውርዱ➡️[አቡዳውድ ነሳኢይ] 5⃣.የጁምዓ ሱብሂ ሰላት ላይ በመጀመሪያው ረከዓ ሱረቱ ሰጅዳህ በሁለተኛው ሱረቱል ኢንሳን ማንበብ የነብዩ (ﷺ) ተደጋጋሚ ተግባር ስለነበር ሱና ነው፡፡ በቀኑ ክፍለ ጊዜ ደግሞ ሱረቱል ከህፍን ማንበብ፡፡ [ቡኻሪ] 🟠ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ‹‹በጁምዓ ዕለት ሱረቱል ከህፍን ያነበበ ዕለተ ቂያማ ከእግሩ እስከ ሰማይ ጫፍ የሚያበራ ብርሐን ይኖረዋል፡፡ እንዲሁም ከዕለቱ ጁምዓ እስከ ቀጣዩ ጁምዓ የሚፈፀም ኃጢአት ይማርለታል››[ሃኪም 2/368] 6⃣.መስጂድ ገብቶ ከመቀመጡ በፊት ሁለት ረከዓ መስገድ። ➡️ ነብዩ (ﷺ) ያዘዙት [ቡኻሪ 93ዐ] ተግባር ሲሆን ኢማሙ ኹጥባ ላይ ከሆነ ግን ሰላቱን ቀልጠፍ አድርጎ መስገድ አለበት። 7⃣. ጁምዓ ዱዓ ይበልጥ ተቀባይነት ያለው ወቅት በመሆኑ ዱዓ ማብዛት። 🟠ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ⬅️በጁምዓ ዕለት አንድ ሰው እየሰገደ ሊገጥመው የሚችል ልዩ ሰዓት አለ፡፡ በዚያ ሰዓት አንድ ሰው አላህን አንድ ነገር ቢጠይቅ ወዲያው ይሰጠዋል፡፡➡️[ቡኻሪ እና ሙስሊም] ┊ ┊ ┊ ┊ ┊ ┊ ┊ ✿ ┊ ┊ ❀ 📚 ┊ ✿ 📌 ❀ ✨ ╠═══ •『 ﷽ 』• ═══╣ ┣𝐆RP• @Muslim_group2 ┣━━━━╗ ❤️ ╔━━━━⎙ ┣CHL• @Muslimchannel2 ╠════•❁🎐❁•═════╣ 🌐 #SHARE_The_خير
Открыть в TelegramПереслано из ✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽
🗺「 ኢሬቻ 」🗓️ ▭▬▭▬▭▬▭▬ ❗️:"ኢሬቻ ባህል እንጂ ሃይማኖት አይደለም" የሚሉ ሙስሊሞችን ማየት በጣም ልብ የሚያደማ ነው። ተመልከቱ ለዛፉ ሲሰግዱ! ተመልከቱ የሚሰሩትን። ሙስሊሙ ወንድሜ ሆይ! የብሄር አጀንዳ አቅልህን አስ፞ቶ ጀሀነም እንዳይከትህ ተጠንቀቅ። አላህን ፍራ!! መስቀልን የምንቃወመው የአማራ ስለሆነ አይደለም። የኩፍር በአል ስለሆነ እንጂ። ኢሬቻ የኦሮሞ ስለሆነ በተለየ አይን አናየውም። የኩፍር ቡላና ዳለቻ የለውም። ሁሉም ኩፍር ነው። ሁሉም የጣኦት አምልኮ ነው። ሁሉም ተውሒድን በጥብቅ ከሚያስተምረው ኢስላም ጋር ፈፅሞ የሚፃረር ነው። ሁለቱም ከኢስላም ጠርጎ የሚያስወጣ የለየት ክህደት ነው። ዛሬ የብሄር አጀንዳ እራሱን የቻለ ጣኦት ሆኗል። ሰዎች ለብሄር ሲሉ ካፊርን ይወዳሉ። ሙስሊምን ይጠላሉ። ለብሄር ሲሉ ለመስቀል፣ ለኢሬቻ ወግነው ይሟገታሉ። የኩፍር በአል ያከብራሉ። የሚያሳፍረው ሸይኾችና ዱዓቶች ጭምር በዘረኝነት መለከፋቸው ነው። እስኪ የመስጂድ ኢማም ሆኖ፣ ጥምጣም ጠምጥሞ የኦርቶዶክስ ሰልፍ የሚያደምቅ፣ በዘራቸው የተነሳ ሙስሊም ትግሬዎችን ጭምር የሚያጥላላ፣ ለኢሬቻ "የእንኳን አደረሳችሁ" መልእክት የሚያስተላልፍን ልክፍተኛ አስቡ። ዘረኝነት አደዛዥ እፅ ነው። በዚህ በሽታ የተለከፈ ሰው እይታው ቁንፅል ነው። አርቆ ማሰብ አይችልም። ይህንን ሀሺሽ፣ ይህንን ጣኦት አጥብቀን ካልተዋጋነው ብዙ ነገር ያሳጣናል። © ibnu Munewer ┊ ┊ ┊ ┊ ┊ ┊ ┊ ✿ ┊ ┊ ❀ 📚 ┊ ✿ 📌 ❀ ✨ ╠═══ •『 ﷽ 』• ═══╣ ┣𝐆RP• @Muslim_group2 ┣━━━━╗ ❤️ ╔━━━━⎙ ┣CHL• @Muslimchannel2 ╠════•❁🎐❁•═════╣ 🌐 #SHARE_The_خير🔺
Открыть в Telegram📮ለበጎ ነው📮 📯አላህ ﷻ በኛ መጎዳት የሚጠቅመው ምንም ነገር የለም። ጉዳት መስሎ የታየን ጥቅም ሊሆን ይችላል። በርግጥም እውነት ተጎድቻለው ብለህ የምታስብ ከሆነ ብሶትህን ወደ ላይ አቤት በል። ወደ መሬትና ወደጎን ሳይሆን ወደ ሰማይ ተመልከት። አቤቱታህን በእንባ ፈርምበትና ማመልከቻህን ሰማይ ቤት አስገባ። ኑሮ ከከበደህ፤ ነገር መሰመር አልይዝ ካለህ፣ በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ሆነህ አላህን ﷻ አወድስ። አመስጋኝ እንጂ አጉሮምራሚ ድምፆች በሰማይ ቤት አይወደዱም። ከአጭርም ይሁን ከረጅም ጊዜ ዱዐእ በኋላ የሚላክልህን መልስ ምንም ቢሆን በፀጋና በውዴታ ተቀበል።📬 ──────⊱◈◈◈⊰────── 💡 @Muslimchannel2 💡 @Muslimchannel2 💡 @Muslimchannel2 #join_our_channel_
Открыть в Telegram🍃 "እንተዛዘን "🍃 🔶ጥሩ ለሰራ፣ በጎ ነገረ ላበረከተና መክሮ ላስተካከለ ሰው በድብቅ ይሁን በይፋ ዱዐዕ የማያደርግ ሰው እሱ ምቀኛ ነው። 🔷ለሰው የተወሰነ ውለታ ውሎ መልሱን ያውም በበለጠና በተሻለ ሁኔታ ከጓደኛው የሚጠብቅ ሰው ጓደኛ ሳይሆን ጉደኛ የሆነ አትራፊ ነጋዴ ነው። 🔶ባልሰራንና በሌለን ነገር የሚያሞካሸን ሰው ካለን አንዱን ሊወስድብን ሳይሆን አይቀርም። 🔷በዲን ውስጥ ለሚሰራው ማንኛውም መልካም ስራ ክፍያው ከአላህ ትቶ ከሰው የሚጠብቅና ካልተከፈለው በቀር ሞራሉ የማይነሳሳ ሰው ከሸይጧንም ቢከፈለው ያገለግላል ። 🔶ጠንክሮ የማይሰራና ባገኘውም ብኩን የሆነ ሰው ድህነት ለሱ ቅርብ ነው። 🔷ስራችን አስደስቶት "አላህ ይጨምርልህ ያቆይብህ" ከማለት ይልቅ "አድናቂህ ነኝ" እያለ የሙገሳ ቃላቶችን የሚደረድርልን ሰው እያሰራን ሳይሆን ስራችንን እያበላሸብን ነው። 🔶ታላቁ ሶሃባ አብዱላህ ኢብን መስዑድ ከአንድ መጅሊስ ሲነሱ ሰዎች ታላቅነታቸውን ስለሚያውቁ ተከተሏቸው። እርሳቸውም በመተናነስ መልክ እንዲህ አሏቸው። "ሰዎች ሆይ! አትከተሉኝ ወይ እኔ እጠፋለሁ ወይ እናንተ ትጠፋላቹህ።" ──────⊱◈◈◈⊰────── 🔖 @Muslimchannel2 🔖 @Muslimchannel2 🔖 @Muslimchannel2 #join_our_channel_👏🏻
Открыть в Telegram