ልክ እንደማትበራ ልክ እንደማትሰራ ልክ እንደማትሰውር ነፍሱ የወጣ በድን ልክ እንማታድን አድርገው ሲነግሩኝ አምኜ …. ቀረብኳት ለመድኳት ወደድኳት ከዛ ግን ፦ እንግዳ ተዓምር በመደዳ አስማት በየአፍታው ፈውስ በየቡድን እሩቡን ስትፈውስ ግማሹን ስታድን እውር ስታበራ ሰው ቀርፃ ስትሰራ ስቃይ ስትወረውር ጅማት ስትደውር ፈትላ ስታሳምን ህይወት ስትሸምን እያየው ቀረብኳት ልክ እንደኔው ቢጤ ያልለመደ መጤ ልክ እንደማትመራኝ ልክ እንደማትሰራኝ ልክ እንደማትወስደኝ መጥታ ስታውደኝ አቅርባ ስታቅፈኝ ስጋዬ ቀፈፈኝ ህይወቴ ቀፈፈኝ እናታቸውና ምንድን ማጣጣል ምንድነው ማሳነስ መሬት ላይ መነስነስ የገዳምን እጣን መዓዛ እንዳላጣን ፈውስ እንዳላጣን የሰው ሰው ማጣጣል አሁን ከየት ይመጣል ሌላ ተዓምረኛ በግ እና እረኛ በቀን ሜዳ ምትውል ከእኩያ ግብግብ በሌት ተደብቃ ህይወት የምትመግብ ቀትር እንደማንም ጥርሷን የማትከድን በሌት በአይን ብቻ ህይወት የምታድን እሷን ነው እንግዲህ ተዋወቃት ያሉኝ ልቤን ሊያስበሉኝ ልክ እንደማትበራ ልክ እንማትሰራ ነፍስ የወጣ በድን ልክ እንደማታድን እንደኔ እንደሆነች ህይወት ግራ የገባት ዘፈን የሚያባባት ኮከብ የምትቆጥር ገብስ የምታበጥር ዝምብሎ ዝምብሎ ተስፋ አገኝ ብሎ እንደሚኖር ተልባ ግማሹን በሃሳብ ቀሪውን ባንቀልባ ተሸክሞ እንዳለ አንድ ዘለስተኛ እረቦት የሚበላ ደክሞት የሚተኛ የኔው ቢጤ አድርገው እርሷን ነግረው ላኩኝ ይኸው ዛሬ ገና በድፍረቴ ሳኩኝ ላይ ላዩን ስቀልድ ስቃ እየፈካው እንደማያቃጥል መዳፏን ስነካው አኔው ተቃጥዬ እኔው እየረካው ስትምረኝ ሰታቅፈኝ ደርሶ እየቀፈፈኝ የኔ ሰውነቴ ከርሷ ሲነፃፀር እርሷ ዉሃ ሆና እኔ እድፍ ዘር በትኩረት ስትሰማኝ ልክ እንደ ጅል አማኝ እንደምመጥናት እንደማትበዛብኝ እየተምታታብኝ እሰይ ቆየሁ ከርሷ ሲመግበኝ ጥርሷ ሲመግበኝ አይኗ ሙሉ አለሜ ሆና እንደኔ ደስተኛ ፤ በዓለም አይገኝም ልብ ግን የለኝም !። @mikiyas_feyisa
Открыть в Telegram
ሚኪያስ ፈይሣ
ግጥም ወግ ሀሳቦች ልቦለዶች 🤝 @mika145
Новые посты
እልፍ አእላፍ ከአንድ አይበልጥም ባህር ሙላት ጥም አይቆርጥም የስኬት ጫፍ አይጣፍጥም። ከተራው ላይ ቀልብህን ጣል እንዳይከፋው ሆድህ ባሻው ከመንገዱ ከጉዞው’ንጂ ጣዕም የለም ከመድረሻው!። ከህልምህ ጋር አብረህ አትክነፍ ደመና☁️ነው የሚናድ ቃል፤ ሞተህ ሞተህ ስትደርስበት ካንተ እኩል ፍቅርህ ያልቃል!። በ’ነገ’ ላይ ቤት አትስራ❌ ህልምህ ዛሬን እስኪከድን መዳረሻው ሙት አካል ነው🪦 ህይወት ኖሮት እንኳን ሊያድን። ደክመህ ዝራ፤ ሰብል አትጠብቅ ነፍስ ያጠግባል ማይበቅል እርሻ በመሃል ቆይ በመሃል ሳቅ በመሃል ኑር ህይወት የለም መጨረሻ❗️። @Mikiyas_feyisa
Открыть в Telegramየፀሀይ ስለት-ልጅ፦ አብረቅራቂ ኮከብ አበ ነፍስ አባቷ፥ ከጥጥ የተሰራ መላ ሰውነቷ። ከጥርሷ ታይታ እኩል ነፀብራቅ ሚከተል፤ ከ’ሳትና ከወርቅ ደምስሯ ሚፈተል!። ሲነኩት የሚሰርግ ወዲያ ሚያስገበግብ ወዲህ የሚያሳሳ፥ በጣት ማይነሳ፦ ምላስ የማይቀምሰው፥ ግማሽ ማር ፣ግማሽ ሰው! ስዕብናዋ ሙሉ ፍቅር የተለበጠ ብልጣብልጥነቷ እፍኝ ያልበለጠ ውጫዊ ህይወቷ በፈገግታ እንጂ በአልማዝ ያላጌጠ፦ የከናፍሯ ወዝ ከገነት የቀዱት፤ ፀጉሯን ብትለቀው ደረሰው ማይከነዱት፦ የጥርሷ ድርዳሮ የእምነበረድ ችምችም፥ እኔ እንደማፈቅራት አልተፈቀረችም!። @mikiyas_feyisa
Открыть в Telegram“ብርሃን!” “ብርሃን!” የታለሽ ንግስቴ ፈሰሰ አካላቴ ደከመ ገላዬ፦ አረ በማምዬ! ድምፅ ሳያሰማ ወረሰኝ ጨለማ። እባክሽን አውጪኝ ለኔም እድል ስጪኝ አንቺ ነሽ ህይወቴ አንቺ ነሽ ንግስቴ አትራቂኝ እሺ ሺህ አመት ንገሺ። ፦፦፦፦፦ “ሰላም ሆይ!” “ሰላም ሆይ!” አንቺ ወረቀ ጉንጉን አንቺ የ’ንቁ ኒሻን ፤ እንደምን ከርመሻል? ያንቺ ስልጣን መብለጥ ያንቺን ሀይል መሻል፦ ተረዳሁኝ አሁን ብርሃን ጥላኝ ስትሄድ ሲወርሰኝ ድቅድቁ፤ ቢመሽም ይኖራል ሰላም ነው ትልቁ። አንቺ ነሽ ንግስቴ አንቸ ነሽ ህይወቴ አትራቂኝ እሺ ሺህ አመት ንገሺ!። ፦፦፦፦፦ “ፍቅር ሆይ!” “ፍቅር ሆይ!” የታለሽ ሰው አጣው ብቻዬን ተቀጣው ሁሉም በሰልፍ ሄደ ጊዜም ተቀጠፈ፥ ሰላም አያገኝም ብዙ ኖሮ ኖሮ ሰው ያላተረፈ። ተረዳሁኝ አሁን ሰላም ሆኜ ስኖር ባዶነት አጠቃኝ፥ ሁሉም ጥንቅር ይበል ያለ ፍቅር በቃኝ። አንቺ ነሽ ንግስቴ አንቸ ነሽ ህይወቴ አትራቂኝ እሺ ሺህ አመት ንገሺ። ፦፦፦፦፦ … አረ አሁንስ በቃኝ አረ ተቃጠልኩኝ፥ ህልም አልባ ነበርኩኝ! ጊዜያዊ ነበርኩኝ! ይኸው ብሼ ብሼ ባዶነቴ ሰፋ፥ እባክሽን “ተስፋ!” በፈጠረሽ ማሪኝ ልከተልሽ ጥሪኝ ሰው በሰው ቢከበብ የሚሻው ባይቀርም ፤ ያለ ተስፋ አይኖርም!። ተረዳሁኝ አሁኝ ካገኘውት ሰው ጋር ስለይ እያለኝ ቅር፥ ለካ አይበቃም ፍቅር። አንቺ ነሽ ንግስቴ አንቸ ነሽ ህይወቴ አትራቂኝ እሺ ሺህ አመት ንገሺ። ፦፦፦፦ … ወይ የሰው መሳሳት ወይ የሰው መጃጃል፥ አልገርምም እኔ ጃል? ስንቱን ደጅ ጠናሁ ስንቱን ተማፀንኩኝ ስንቱ እግር ወደኩኝ መቼ ሽሬ ዳንኩኝ? አሁንም ግርግር አሁንም አበሳ፦ አፉ በለኝሳ፥ ያላንተ ዋለልኩኝ ካለም ጋር በዋይታ፦ አንተ ጋር ፀጥታ! አንተ ጋር ዝምታ! አንተ ጋር ባዶ ቃል መተኛት ይበቃል። ደርሶኛል ገና አሁን የጥበብ ዳር ቅምሻው፥ የትም ዞረው ዞረው አንተ ነህ መድረሻው!። ሞት ነህ መጨረሻው!። የትም ጥረው ግረው አንተ ነህ ፍፃሜ፦ ይኸው ነበር አቅሜ? ልክ እንደምረታህ ልክ እንደማትሰብረኝ ህይወት ስትመክረኝ ስትደልለኝ በቃል እርሷን እየሰማው፦ ፍቅር ስል፣ ሰላም ስል ስብርብር እራሴን ይበልጥ እያደማው፤ በጨለማ መሃል ብርሃን አገኝ ብዬ … ተስፋ ሳቀጣጥል፥ አንዱን እያነሳው አንደኛውን ስጥል፦ ደስታ ስል ሰላም ስል ፍቅር ስል … ስቆስል፦ በረሃ ውቅያኖስ ላይ ለብቻ እየዋፕው፥ ሸሽቼህ ፣ ሸሽቼህ አንተው ጋር ተገፕው። አንተ ግን ደግ ነህ ባዶ ተስፋ አሰጥም፥ በሚጨልም ብርሃን አታንቆጠቁጥም። እዉነታ! ዝምታ! እርጋታ ነው ገድልህ፦ ከቅዠት ሰልፍ አውጪ ከህልም አለም አዳኝ፥ .. እባክህ አደራ አንተም እንዳትከዳኝ!። @mikiyas_feyisa
Открыть в Telegramንፅህት ነሽ ተዋህዶ ፀኣዳ ነሽ ተዋህዶ ከእንቁ ከወርቅ የነጠርሽ ውብ የሰማያት ግዝፈ ነገድ ሀጣኖችን ወደጌታ ምታደርሺ ፈጣን መንገድ። ፀኣዳ ነሽ ተዋህዶ ወለላ ነሽ ተዋህዶ ከማር ወተት ምጣፍጪ እንደ ስንዴ ምትራቢ ፤ በዉበት ላይ ሌላ ውበት በጣ’ም ላይ ጣ’ም ምትደርቢ። ንፅህት ነሽ ተዋህዶ ፀኣዳ ነሽ ተዋህዶ የተከበርሽ ንፁህ ድንኳን ወልድ ያቀናሽ ገል ቀልሶ የደም ጥሎሽ የተሸለምሽ የዘመን ጥልም ሽረት ምሶ፦ ንፅህት ነሽ ተዋህዶ ከነኣን ነሽ ተዋህዶ የመድረሻ መጠጊያ ቅጥር ለደከመው ጥላ ዋርካ የእቅፍሽ ምቾት ሰላም ነፍስ ድረስ የሚነካ ውበትሽ ልብ የሚነጥቅ ብርሃንሽ ምድር የመላ በሺህ ዘመን ተፈትነሽ ምታበሪ ንፁህ ገላ፦ ንፅህት ነሽ ተዋህዶ ፀኣዳ ነሽ ተዋህዶ ለልጁነት ስሰናዳ ከጌታ ጋር የተገኘሽ: በለሊቱ ለመስጋና ተብታባ አፌን ዜማ የቃኘሽ ከጨቅላነት ጣፋጭ እንቅልፍ ለማህሌት የጠራሺኝ ህማማቱን ግርፋቱን ትንሳኤውን ያሳየሺኝ ለህይወቴ ቅርፅ የሰራሽ ለምግባሬ ልክ ያበጀሽ ቆምኩኝ ስልም አንደ ማገር ለመደገፍ ያላረጀሽ። ከሰማያት ሰማይ በላይ የትዕግስትሽ ስፋት ጥልቀት ተግሳፅ ቁጣሽ የስስት ቅብ ንጭንጭሽ የእናት ጭንቀት ሁሌም ቀርበሽ የምታጥቢ አካላቴን በንፁህ ውሀ ፈሰስ አርገሽ ምታነፂ እድፍ ልቤን በንስሃ ላለማወቅ መዳፈሬ ማትቆጪ ማትይ እምቢኝ ትቼሽ ሄጄ ብመጣ እንኳን ልጄ ብለሽ ምታስገቢኝ። ንፅህት ነሽ ተዋህዶ ፀኣዳ ነሽ ተዋህዶ እንስፍስፍ ነሽ ወላድ ምስኪን የርዕዮት እምነት ልስን ከልጅነት እስከ እልፈት ያወኩብሽ ክርስቶስን መሸሸጊያ ሁነኛ ቅጥር የስጋዬም ሰላም ቦታ ይኸዉ እያልሽኝ ያቀረብሺኝ ገፍተሽ ገፍተሸ ወደጌታ። ንፅህት ነሽ ተዋህዶ ፀኣዳ ነሽ ተዋህዶ ከጌታሽ እጅ የወረስሽው አይቶ መግዛት ስቦ ማዳን ደረቅ ልቡን ለምለም ማድረግ ፍቅር አጥቶ የተጎዳን። ንፅህት ነሽ ተዋህዶ አርያም ነሽ ተዋህዶ የሱራፌል ልዩ ግርማን የኪሩብን ሀያል ስልጣን ወስደሽ አብን ያሸፈትሽው በቅዳሴሽ ልዩ እጣን አስተምሮሽ ቀጥተኛ ምሶሶሽም ግርፋቱ፥ ስግው ቃሉ እግዚአብሄር ወልድ የቆምሽበነት መሰረቱ ጉልላትሽ የእርሱ መስቀል እንደ ታምር ሚታይ ሽቅብ ውጪሽ ውስጥሽ ጌታ ተኮር ሙሉ ገላሽ ክርስቶስ ቅብ። ንፅህት ነሽ ተዋህዶ ከነኣን ነሽ ተዋህዶ ቅዱስ ጼጥሮስ አለት ሆኖ ጌታ ቅጥሩን ያቆመብሽ የሃጣኑንም የፃድቃኑም ክፍል ቅጥር የሌለብሽ። ንፅህት ነሽ ተዋህዶ ከነኣን ነሽ ተዋህዶ ጋለሞታ ብለው ቢያልፉሸ ዘሟች ብለው ቢያፌዙብሽ ከአንደበትሽ ምን ይወጣል? ህይወት የሆነ አምላክ ይዞ ከማን ጋራ ይማገጣል? ከሎሌው ጋር? ከባሪያው ጋር? ከእናቱ ጋር? ማን ይኖራል? ማን ይሆናል? የህይወትሽ ካስማ ማገር የይሁንታሽ ጉልበት ተገኝ?፤ በርሱ የሌለ በሌላ ዘንድ ምን ፈልገሽ ምን ልታገኝ?። የጠላት ጦር መድረሻ ግብ የማምለጫ ካርታ ቅጂ ከቅዱሳን የተዋወቅሽ በክርስቶስ በኩል እንጂ፦ ከማን ጋራ ማግጠሻል? ከማን ጋራ ወስልተሻል? ወለላይቱ ተዋህዶ የኛ ዘመን ፈሪሳዊ መቼ እንደዚው ይለቅሻል?። መግቢያ መንገድ ያግኝ እንጂ ፍርዱ ክሱ የት ይቀራል? ለማሪያም ልጅ ላንቺም አምላክ አስገድዶ ይጨምራል። አየሽ አደይ አየሽ እመይ ንፅህት ቅድስት ፥ ወለላይቱ እንኳን ተስፋሽ ጌታ ሆኖ፦ የቆምሽበት መሰረቱ፦ ለእቶን ፍቅርሽ ቅጥፈት ሆኖ የተኳለው ድርብ እዳሽ ፥ ጡት አጥብተሽ ያሳደግሺው በልቶ ጠግቦ እየከዳሽ ፦ እንስፍስፍሽ ማይቀየር መሬት ሆድሽ ህመም ወልዶ ፤ ማንም በፍቅር የማይበልጥሽ ፀዓዳ ነሽ ተዋህዶ። ህልውናሽ ጤዛ ሆኖ ግርማሽ በዓለም ተበትኖ እንደ ገረድ ሲተፉብሽ አንገት ደፍተሽ ብትጎጂ ፤ ከነድርሳን ከነዜማሽ ለክርስቶስ ማታረጂ። ፀዓዳ ነሽ ሁሌም አዲስ ለጠላት ሀይል ነገም ሰርዶ ማንም ቢሆን መንታ ምላስ እንደ ወዳጅ ቀርቦሽ ክዶ፦ በንህፅናሽ ማህፀን ውስጥ በአፍ መንታ ቢያገላግል ፥ እንደ ማርያም ፀዓዳ ነሽ ቅድመም ፣ ድህረም ሁሌም ፣ ድንግል። @mikiyas_feyisa
Открыть в Telegram.. “ጥበብ” ጠራቺኝ “ና ልጄ” አለቺኝ ሄድኩኝ: አቀፈቺኝ በስሱ ሳመቺኝ ከዛን …..ገረፈቺኝ። ደም በጠጣ ጅራፍ ባልተገራ ድንበር፤ አጥንቴ ላይ እንኳን እስኪወጣ ሰንበር። አላገቺኝ ጥፊ ስቃይ በገፍ ጠጣው፥ ሲዖል ሙሉ መስኳን ተመልክቼ ወጣው። ከዛን … ለቀቀቺኝ ምንም እንዳልሰራ ግፍ እንዳላወቀ፥ እየሮጥኩኝ ሆድኩኝ አጥንቴ እየሳቀ። ሚገርመው አታፍርም ደግማ ትጣራለች ልክ እንደ ወዳጅ ሰው፥ የነካኝን እንጃ የለም ማስታውሰው። ብቻ ትዝ ይለኛል በሰመመን ስጓዝ ስታቅፈኝ፣ ስትመኝ፣ ከዛ ጎኔን ሲያመኝ፥ ከዛ ሌላ ጥፊ ከዛ ሌላ እሳት አይ የኔ መሳሳት አይ የኔ መበደል፥ ሳይበቃኝ አልቀረም ወጣሁኝ ከገደል። ከዛ ሸሸው በሽምጥ ድጋሚ እንዳጠራኝ እንዳልሄድ በምርኮ መች ይቀርልኛል ጠራቺኝ ሄድኩ እኮ። ድጋሚ በእሳት ድጋሚ በነደል፤ አይ የኔ መገፋት አይ የኔ መበደል፤ ቀዳቺኝ እንደ ዉሃ ቀዳኋት እንደ ገል፤ የስቃይ ምጥ አለፍኩ ልጅ ለመገላገል። ልጅ ማለት ግን ጥበብ ትንሽዬ ውበት ትንሽዬ ጣዕም ማንም ያልቀመሳት፤ ምትነድ እንደ እሳት ምታምር እንደ ጣይ፥ …. ሃይ! ልቀቂኝ በቃ አሁን ልመለስ ወደ አለም፥ ልጄን ሰታኝ ወጣው ለገስኳት ለዓለም። ሁሉም ተሻማባት የጠገባት የለም። ሁሉም በቋፍ ቀረ ጣ’ሟን የቀመሰው፥ ምትሃት ታምር ናት ግማሽ ቃል ግማሽ ሰው። ዓለም ወደደልኝ ዓለም አበደልኝ ሌላም ፈለገና ሰደደኝ ከገደል፥ አይ የኔ መገፋት አይ የኔ መበደል፦ እድለ ቢስ ስንዴ ዘረ ጥሩ ብቃይ በተራዬ ጠራው ጥበብን ለስቃይ። ተሰቃየው ወለድኩ ከዛ ሰጠው ለዓለም፤ አሁንምጠሃይ ቅብ በድጋሚ ለምለም። ሁሉም ሰው ወደዳት አጣው ተቃዋሚ፤ ከዛን ወደ ገደል ጣሉኝ በድጋሚ። ትጠራኝ ነበረ አሁን ግና አኔ፤ እስኪያንገፈግፋት እስኪለምጥ ጎኔ። ተጋምደን ስንቀምም ስናስረክብ ለዓለም፥ በቃ ሚለን ጠፋ ሆነን ዘለዓለም። አንድ ሁለት ሶስት አለ ቀን ተተካ በቀን፥ አሷ በፍስሃ እኔ በሰቀቀን፦ የፍቅርን ዳር ድንበር ስሌት ስተማምን፥ ህዝብ እየጎረፈ ጥበቤን ሲለምን። ከባዶ ዓለም ላይ ጣዕም እያበጀው፤ ስታገል አድጌ ስታገል አረጀው። . . … እናንተ ግን ተዉ, እንደኔ አትሁኑ ህይወት አታጉድሉ፥ ጥበብ ስትጠራቹ አቤት አትበሉ። …… እሳት ነው : ትርፋቹ ስቃይ ነው : ትርፋቹ፦ ድምፅ የምታሳምር ልታስወልዳቹ። አስወልዳ ለዓለም ዓለም ወደ ገደል፤ ከዛ ስቃይ ብቻ ሁልጊዜ መበደል። ባካቹ ሰው ሁኑ ጥቂት ልብ አትጡ ጥበብ ስትጠራቹ እንዳልሰማ እሩጡ። @mikiyas_feyisa
Открыть в Telegramስፅፍ ያመኛል ጭንቅ ይለኛል ቢሆንም አለው ህይወት ፅፋለው። ደም ቢወጣኝም ግርድፍ ትንፋሼ እየተነነ ፤ የሰው ነፍስ አለ በእኔ መፃፍ ላይ የተወሰነ። ስፅፍ ያመኛል አየር ያጥረኛል ባልፅፍ፣ ብከስም አትተነፍስም። መኖር አለባት መፃፍ አለብኝ ቀለም ሲያልቀኝ ነው የምትሞትብኝ። ሲፅፏት ውለው የልብ አትደርስም ሲያነቧት ውለው አትሰለችም ፤ ልብወለድ ብትሆን ማንነት አላት ባዶ አይደለችም። አንበርክካለች ስንቱን በፍቅር ፅሁፍ ናት ብለው ቢያነቧት ንቀው፤ ፍፁም ሰዉ ልጅ ናት ስጋ ብቻ ነው ጎድሏት የሚያውቀው። እንደ ሌጣ አካል ስትወላገድ ባትገኝ የትም ፤ ቀድሞም ኗሪ ነች ገለጥኳት እንጂ አልፈጠርኳትም። እጣ ህኖባት ኑሮ ሆኖባት ጅምር ህይወቷን በእዉነት ልታርም ፤ እሺ ምን ላድርግ እንደ እድል ሆኖ ካልፃፍኩ አትኖርም። ከፃፍኩኝ ደግሞ . . . ልቤን ያመኛል ፥ . . ምን ይሻለኛል?። ..ኤኤኤኤኤጭ አርፌ ልፃፍ ዝምበሉኝ በቃ ፤ የሷም እድሜዋ የእኔም ድርሰቴ እስከሚያበቃ ፤ እስካሻት ትሳቅ ደም እንባ ላልቅስ፦ አኑሪይት ልሙት ከሞትኩ ይልቅስ። @mikiyas_feyisa
Открыть в Telegramመኖር በቂ አይደለም፦ ያንሰዋል ሰዋሰው ይጎለዋል ቅኔ ፤ አንቺ አለሺኝ አይደል ምናገባኝ እኔ?። መሞት በቂ አይደለም ያንሰዋል ምንነት ይጎለዋል ፍቺ ፤ እኔ አለውሽ አይደል ምን አገባሽ አንቺ?። @mikiyas_feyisa
Открыть в Telegramእርግብ ነበረች ምታምር ድሮ ስትበር ስትማርክ ክንፏ ተሰብሮ እመሬት ስታርፍ ብትደሰትም ያሰበችው ፍቅር አልጠበቃትም። እርግብ ነበረች ምትማርክ ሽቶ ሁሉን ስታውድ ጠረኗ ጠፍቶ ከክንፎቿ ላይ ሲጎል መዓዛ ካቀፋት በላይ የጠላት በዛ። እርግብ ነበረች ምታምር በጣም ስትስቅ ስትስብ ወዳጅ ባታጣም ሀዘን አድቅቋት ስታወጣ እምባ ያጀባት ሁሉ እያያት ገባ። እርግብ ነበረች የምታሳዝን ላየቺው ሁሉ ላባ ምትመዝን ላቀፋት ሁሉ ፍቅር ምትመዝን ውበት ጣዕሟ ህይወት ሚያስቀጥል፤ ሚገጥማት ግና ወጦ የሚጥል። @mikiyas_feyisa
Открыть в Telegram፦፦፦ እንድፅፍለት የጠየቀኝን ሰው ባላስታውሰውም፥ ይሄን ግጥም በችኮላ ነበር የፃፍኩት። ሀረብ ሀገር ስትኳትን ኖራ ብዙ ነገር አሳልፋ፣ ደጋግማ እመብርሃን ላይ እምባዋን አፍስሳ በስተመጨረሻም በሀገሯ የምትወደዉን ሰው በክብር ስጋ ወደሙን አብራ ተቀብላ ያገባችን ሴት ነበር የሚያትተው። ሁለቱም ብዙ ነገር አሳልፈው ነበር ለዚህ የበቁት። ግጥሙ ለቤተ ክርስቲያን ሰርግ ነበር ሊቀርብ የተፈለገው። እኔ በቀኑ ሳልከው ቀርቼ ይሁን በሌላ ምክንያት አልቀረበም ነበር። ዛሬ saved message ውስጥ ሳገኘው ነው ላጋራቹ ያሰብኩት። ተጋበዙልኝ👇🏼 ፦፦፦፦፦፦ ፦፦፦፦፦፦ እምዬ እንደምን አደርሽ እነሆኝ ማለዳ ውዳሴ ዳገቱን በድል አለፈች ቀን በቀን ምትኳትን ነፍሴ የጭንቁ ዘመን አበቃ የቅዠት ህልሜ ተፈታ ላከብርሽ እደጅሽ ቆምኩኝ ሰው ሆኜ ባንቺ ውለታ እያለች እምባ ብትከፍል አኳላም ልቧም በሙሉ፤ ስምሽን እያከበረ ያኔ ግን ሰው ሀገር ሆና ያለችሽ ምንድን ነበረ? "ድንግል ሆይ ልቤን አደራ አልነግርሽ ስለምታውቂኝ ቀንበቀን ብርታት አድዪኝ ለክብር እስክታበቂኝ እምዬ እረፍት የለኝም አይጠፋሽ የጎን ህመሜ ባርኪልኝ በየመንገዱ መና አይቅር ልፋት ድካሜ" ብላ ይሆን ወይንስ ሌላ? "ብቻ አውጪኝ አሳርፊኝ ልሳም,ልስገድ ልደር ደጅሽ ብዙ ሰራው ደግሞ ልኑር ይበቃኛል በአንድ ልጅሽ ተልባ አይደለው መወሰን ላይ ጨከን አርጊኝ ድፍረት ስጪኝ ልውጣ በቃ እፎይ ብዬ እጄን ይዘሽ አስቆርጪኝ" ብላ ነበር ምትፀልየው? ሰርክ እንደሰው በማይገኝ እደጅሽ ላይ በፍቅር ወድቃ እንደዛሬ ብርሃን ከቧት ለክብሯ ሳትበቃ የውጥኗ ሁሉ ሳይሰምር ቅዠት ሆኖ ምትመኘው ሞገስ ለብሶ የቤቷን ራስ መንበሩ ፊት ሳታገኘው ምንድን ነበር ፀሎታቸው? ከላያቸው ሳይነሳ የየግሉ ጭንቀት ሰፈፍ የፍቅርን ሸማ ለብሰው ብቸኝነት ሳይገፈፍ ምንድን ነበር ውጥናቸው? እሩጫቸው የሁለት አለም እርሱ ይክበር ይሄም አልፏል ከዚህ ኋላ ሁለት የለም። ድንግል ብሎ ለተደፋ ላለቀሰ ፡ ወድቆ ደጇ ቤቱን ሞገስ ትሞላለች እመብርሃን ከነልጇ ደስታ ይሁን በሰርግ ቀን ከቶ አናዝንም ለማን ጥቅም? ድንግል ማርያም ባለችበት እንኳን ፍቅር ወይን አያልቅም። ያስተምራል በሰው በኩል ቅዱስ ቃሉ በገለጠው መድሃኒአለም ሰውን ሲወድ ሰው ነው ሁሌም የሚሰጠው። @mikiyas_feyisa @mikiyas_feyisa
Открыть в TelegramСвязи
Похожие каналы
ግጥም የልብ ድምፅ@yenegitiem21Искусство2,2 тыс.
🕯️የህላዌ ብዕር✍️@poem_hiweИскусство1,26 тыс.
الشاعر / بندر عبدالمحسن النمري@bander_alnamryИскусство2,28 тыс.
Уличная поэзия@matvey_matyushkinИскусство2,28 тыс.
Flinsyatina™️@flins2000Искусство2,28 тыс.
Поленово@polenovomuseumИскусство2,27 тыс.
УВАЖАЕМЫЙ СРАМЕР@yungsramerИскусство2,27 тыс.
алешаааа@thealeshaartИскусство2,27 тыс.
