Кабинет

ተዋሕዶን እንወቅ።

አቡነ ዘበሰማያት ይትቀደስ ስምከ ሥረይ ለነ ኲሎ አበሳነ ኢታብአነ ውስተ መንሱት እግዚኦ አድኅነነ እምዕለት እኪት ወባልሐነ ውስተ መንሡት። ✝በከመ ምሕረትከ አምላክነ ወአኮ በከመ አበሳነ✝ የየእለቱን ስንክሳር፥ ውዳሴ ማርያም፥ ጸሎተ አርጋኖን፥ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮችን፥ የጻድቃንና የሰማዕታትን ገድል፥ የተለያዩ መንፈሳዊ ጥያቄዎችን፥ የድሮ እና አዳዲስ መዝሙራትን የሚያገኙበት ቻናል ነው። ይቀላቀሉን።

Юзернейм
@letsknowtheeotc
Подписчики2 393
Просмотров на пост, 7 дн.187−44,7% к пред. 7 дн.
ERR7,81 %за 7 дней

Средние просмотры поста по дням

По дню публикации

Показать таблицей
ДатаПросмотров на пост
12 нояб. 2026 г.470
14 нояб. 2026 г.434
15 нояб. 2026 г.506
17 нояб. 2026 г.399
18 нояб. 2026 г.376
19 нояб. 2026 г.337
20 нояб. 2026 г.316
21 нояб. 2026 г.333
22 нояб. 2026 г.290
23 нояб. 2026 г.276
24 нояб. 2026 г.252
25 нояб. 2026 г.210
26 нояб. 2026 г.184
27 нояб. 2026 г.171
28 нояб. 2026 г.162
29 нояб. 2026 г.79

Самые просматриваемые за месяц

  1. Просмотры506
    Пересылки—
    Реакции2
    Комментарии—
  2. ✝️ ቁስቋም [ ኅዳር 6 ] ኅዳር 6 ቀን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተወደደ ልጇን አዝላ ወደ ግብጽ የተሰደደችበት ስደት የተፈጸበት ቀን ነው ። ደብረ ቁስቋም በደቡብ ግብፅ የሚገኝ ተራራ ነው ። ደብረ ቁስቋም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲሁም ቅዱስ ዮሴፍና ቅድስት ሰሎሜን ይዛ ከስደት ሲመለሱ ያረፋበት ቦታ ነው ። እመቤታችን ከተወደደ ልጇ ጋር በደብረ ቁስቋም ገብተው ካገኛቸው ድካም ባረፉበት በዚሁ ቀን የጌታ መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ታይቶ "የሕፃኑን ነፍስ የፈለጉት ሞተዋልና ተነሣ ፥ ሕፃኑን እናቱንም ይዘህ ወደ እስራኤል አገር ኺድ"ብሎታል ። /ማቴ 2፥19-20/ በነገረውም መሰረት እናቱንና ሕፃኑን ይዞ ተመልሷል ። ከግብጽ ሲመለሱም ጌታችን በእመቤታችን ጀረባ ላይ ሆኖ ድውያንን በፈወሱ ጣቶቹ ወደ ኢትዮጵያ ይጠቁም ያመለክት ነበር፤ እመቤታችንም "ልጄ ሆይ ለምንድነው ጣትህን የምታመለክተው?" ብትለው "ያቺ የተባረከች አገር ናት እኔን የሚያመልኩ አንቺን የሚማልዱ በፍቅርሽ የነደዱ ቅዱሳን መነኮሳት የሚፈልቁባት አገር ናት፤ ያንቺ ዘመዶች ሰቅለው ይገድሉኛል በዚህች አገር ያሉ ግን ሳይዩኝ ያመኑኛል፤ አስራት ሀገርሽ ትሁን" ብሎ ሰጥቷታል ። በኪደተ እግራቸውም ጣና ሐይቅን፣ ዋልድባንና ሌሎችንም ቦታዎች ዞረው እንደባረኩ ድርሳነ ዑራኤልና ተአምረ ማርያም ላይ በስፋት ተጽፏል ። "የዓለም ፡ ሁሉ ፡ እመቤት ፡ ሆይ ፡ ልመናችንን ፡ ትሰሚ ፡ ዘንድ ፣ ከኀዘናችንም ፡ ታረጋጊን ፡ ዘንድ ፡ ወደኛ ፡ ነይ ፡፡" JOIN @Applied_CHRISTIANITY

    Фото
    Просмотры474
    Пересылки—
    Реакции5
    Комментарии—
  3. Просмотры470
    Пересылки—
    Реакции5
    Комментарии—
  4. Просмотры399
    Пересылки—
    Реакции—
    Комментарии—

Новые посты

#8670Фото
Просмотры167−45%к среднему
Пересылки—
Реакции4
Комментарии—
#8669Текст

Переслано из ተግባራዊ ክርስትና

✝️ ከኅዳር 20 እስከ ቀጣይ ሳምንት ኅዳር 26 ተከብረው የሚውሉ ክብረ በዓላት ፦ " የቅዱሳንን ታሪክ እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል ።" /አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ/" 🔔 ኅዳር 20 ቀን #እሑድ 📖 ቅዱስ አባት አንያኖስ አረፈ እርሱም ለመወንጌላዊ ማርቆስ ሁለተኛ የሆነ የእስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳስ ነው ። 📖 የሠራዊት አለቃ የነበረው የሰማዕት የቅዱስ ቴዎድሮስ ቤተ ክርስቲያን የከበረችበት ነው ። 🔔 ኅዳር 21 ቀን #ሰኞ 📖 አክሱም ጽዮን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ጽላት የገባችበት የበዓልዋ መታሰቢያ ነው ። 📖 ከሮሜ ሀገር የሆነ ተዓምራትን የሚያደርግ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዐረፈ ። 📖 የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ አባ ቶዝሞስ ዐረፈ እርሱም ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሃምሳ አራተኛ ነው ። 📖 የእስሙናይን አገር ሰማዕት እልፍዮስ ፣ ዘኬዎስ ፣ ሮማንስ ፣ ዮሐንስ ፣ ቶማስ ፣ ፊቅጦር ፣ ይስሐቅ መታሰቢያቸው ነው ። 📖 የብርሌ የብርጭቆ ሠሪዎች ልጅ የሆነ ከአስዮጥ ሀገር ቅዱስ አባት አባ ዮሐንስ ዐረፈ ። 📖 ጫብሬ ከምትባል ከአገረ ድልበት ዲቦራ ዐረፈች ዜናዋም በገድሏ መጽሐፍ ተጽፎ ይገኛል ። 🔔 ኅዳር ቀን 22 #ማግሰኞ 📖 ቅዱሳን ቆዝሞስና ድምያኖስ ወንድሞቻቸውም አንቲቆስ ፣ ዮንዲኖስ ፣ አብራንዮስ በሰማዕትነት ዐረፉ ። 📖 ሁለት መቶ ስልሳ ሁለት ዘጠኝ ወንዶችና አርባ ዘጠኝ ሴቶች የቅዱስ ቆዝሞስ ማኅበር የሆኑና ቀሌምንጦስ በሰማዕትነት ዐረፉ ። 🔔 ኅዳር 23 ቀን #ረቡዕ 📖 የመቶ አለቃ የነበረ ጻድቅ ቆርኔሌዎስ ዐረፈ ። 📖 የስሙ ትርጓሜ የእግዚአብሔር አገልጋይ የሆነ የነቢይ አብድዩ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው ። 🔔 ኅዳር 24 ቀን #ሐሙስ 📖 በእግዚአብሔር ዙፋን ዙሪያ የሚኖሩ የሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ የበዓላቸው መታሰቢያ ነው ። 📖 የናግራን አገር ቄስ የከበረ አዝቂር የሐሚር ንጉሥ ስራብሄል በነገሠበት ወራት ከእርሱ ጋር ካሉ አርባ ስምንት ሰዎች ጋር በሰማዕትነት ዐረፈ ። 📖 የቀላትው ፣ የጋይዮስ ፣ የቃርዮስ ፣ ጽኑ መስተጋድል የሆነ የመልካም ስም አጠራር ዜና ያለው የዲዮስቆሮስ መታሰቢያቸው ነው ። 📖 ፃን ከሚባል ሀገር የሆነ ዮሴፍ ዐረፈ ። 🔔ኅዳር 25 ቀን #አርብ 📖 የስሙ ትርጎሜ መርቆሬዎስ የሆነ ፒሉፓዴር በሰማዕትነት ዐረፈ ። 📖 የአቃርዮስና የሮማን መታሰቢያቸው ነው ። 🔔 ኅዳር 26 ቀን #ቅዳሜ 📖 ቅዱስ ቢሳርያኖስ ሚስቱ ኪልቂያና እኅቱ ታቱስብያ በሰማዕትነት ዐረፉ ። 📖 ቅዱሳን የደሴት ሰንሲላ ኤጲስ ቆጶስ ጎርጎሬዮስና የሐይቅ ኢየሱስ ሞዐ መታሰቢያቸው ነው ። 📖 የሀገረ ናግራን ሰማዕታትና የአባታቸውም የቅዱስ ኂሩት መታሰቢያቸው ነው ። 📖 የከበረና የተመሰገነ ንጹሕም የሆነ ኢትዮጵያዊ አባታችን አቡነ ሀብተ ማርያም ዕረፍታቸው ነው ። 📖 የጌልዮስ ፣ የምክዋስና የናርልዮስ መታሰቢያቸው ነው ። " ክርስትና የሚጀምረው ከተግባር እንጂ ከወሬ አይደለም ። ሕይወታችን በጥቅስ ተገንዞ በጥቅስ የተቀበረ ፣ ከሕይወትና ከሥራ የተለየ እንዲሆን አንፍቀድለት ። " / ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ /  JOIN @Applied_CHRISTIANITY

Открыть в Telegram
Просмотры157−48%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#8668Фото
Просмотры171−43%к среднему
Пересылки—
Реакции2
Комментарии—
#8665Фото
Просмотры184−39%к среднему
Пересылки—
Реакции5
Комментарии—
#8664Фото
Просмотры210−31%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#8662Текст

Переслано из ተግባራዊ ክርስትና

✝️ ካየሁት እና ከሰማሁት ላካፍላችሁ ! ❖ ክፍል 2 "... ሳሙና ለመግዛት ወደ ሱቅ ወጥቼ ሳለ ሁለት ወንድሞች ከሱቁ አጠገብ ተቀምጠው አንድ ጉዳይ አንስተው ይነጋገራሉ ። ጉዳዩ ስለ ገንዘብ ነበር ። አንዱ ወንድም "የነካሁት ወረቀት ሁሉ ወደ ገንዘብ ቢቀየር ኖሮ ቁጭ ብዬ ሕይወቴን በሰላም እኖር ነበር ።" ብሎ ሲናገር አንድ ጊዜ አንብቤው የነበረው አጭር ታሪክ (ወግ) ትዝ አለኝና ለእናንተ እንዲህ አጋራኋችሁ ፦ አንድ ጎልማሳ ሰው እለት እለት ወደ ቤተክርስቲያን እየሄደ እግዚአብሔርን ወርቅ ስጠኝ እያለ ይለምነዋል በዚህ ተግባሩም ሰነበተ ። እግዚአብሔርም ተገልጾ ምን እንዳደርግልህ ትወዳለህ ይለዋል ። ሰውየውም የምነካው ሁሉ ወርቅ ይሁንልኝ ይለዋል ። እግዚአብሔርም እንዳልክ ይሁንልህ ብሎ ከፊቱ ይሰወራል ። በዚህ የተደሰተው ሰውዬ መንገድ ላይ ያገኘውን ነገር ሁሉ ወርቅ እያደረገ ለባለቤቱ እስኪነግራት እየተቻኮለ በፍጥነት ወደ ቤቱ ገሰገሰ ። እቤቱም እንደደረሰ ባለቤቱን ጠርቶ "የእኔ ውድ አይው እያለ የቤቱን እቃ በሙሉ እየነካ ወርቅ አደረገው ። ባለቤቱም በመደሰት ምግብ ታቀርባለች እሱ ግን ገና ምግቡን ሲነካው ወርቅ በመሆኑ እሷ እያጎረሰችው መመገብ ጀመሩ እሱም ወደ መጥገቡ ሲደርስ "በቃኝ የእኔ ውድ ይላታል" እሷም "እንዴ በዛሬ ቀን ያልተበላ መች ሊበላ ነው" እያለች በላይ በላይ ስታጎርሰው "ውይ በቃኝ" ብሎ እጇን ሲይዛት ወርቅ ሆነች በዚህ ነገር ደንግጦ ራሱን ሲይዝ ወርቅ ሆኖ አረፈው ይባላል ። ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ "የምትለምኑትን አታውቁም !" /ማቴ 20÷22/ ያለው ይህን አይነት ልመና ነው ። እኛ ክርስቲያኖች አስቀድመን ጽድቁን እና መንግሥቱን ነው ልንሻ ሚያስፈልገን ሌላው ትርፍ ነው ። በአንድ ቀን 1 ሚልየን ብር ብናገኝና ከሦስት ቀን በኋላ እንደምንሞት ቢነገረን ምን ሊጠቅመን ይችላል ። ለዚህም ነው መጽሐፈ መክብብ ምዕራፍ 2 ቁጥር 18 ላይ "ከእኔ በኋላ ለሚመጣው ሰው እተወዋለሁና ከፀሐይ በታች የደከምሁበትን ሁሉ ጠላሁት ።" ሲል የተናገረው ። #ኅዳር 15 ቀን 2019 ዓ.ም JOIN @Applied_CHRISTIANITY

Открыть в Telegram
Просмотры252−17%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#8661Фото

Переслано из ተግባራዊ ክርስትና

📖 ተዋስኦተ ቀሲስ አባ ጳውሊ ምስለ ሰይጣን (ሰይጣን በአባ ጳውሊ ተገዝቶ ሳለ ያወጣው ምሥጢር ) ✝️ ከዚህ እውነተኛ ታሪክ (ከቅዱስ አባ ጳውሊ ገድል) የምንማረው ምንድር ነው ? ለሚለው በጥቂቱ ፦ 1, ሰይጣን ከሰዎች በአንዱ አድሮ በኃጢአት ለመጣል አጋዥ የሚሆነው ምን እንደሆነ ። 2, ዓለማውያን ሰዎችን እንዴት እንደሚፈትናቸው ። 3, ሰዎች የሚነግራቸውን ውሸት እንዴት አምነው እንደሚቀበሉት ። 4, መልኩን መለወጥ እንደሚችልና የማያውቀውን ምስጢር ማስመሰል እንደሚችል ። 5, ሰዎችን በማሳቱ ምን እንደሚጠቀም ። 6, ገሃነም የሚባል ቦታ እንዳለ ። 7, ለሰው በምትሀት የሚታየው በምን አምሳል እንደሆነ ። 8, ሰዎች አምላካቸውን እንዲክዱ የሚያደርገው በምን መንገድ እንደሆነ ። 9, ሥጋው የደከመን ሽማግሌ በምን እንደሚፈትነው ። 10, በገዳም ከሚኖሩ መነኮሳት ጋር እንዴት እንደሚዋጋና እንዴት እንደሚያሸንፉት ። 11, ከአዳም ልጆች የሚፈራቸው እና የማይፈራቸው መኖራቸውን ። 12, ምንም ያልበደሉትን ሰዎች ለምንድን እንደ ሚፈትናቸውና ... ሌሎችም ይገኙበታል ። #ምንጭ ፦ ሐይቅ ቅዱስ እስጢፋኖስ ገዳም ከግእዝ ወደ አማርኛ ያሳተመው መጽሐፍ ፣ ዜና አበው ግእዝ በግእዝ መጽሐፍ ፣ ፍኖተ ቅዱሳን ዘተዋሕዶ 📖 ንባብ ለመንፈሳዊ ሕይወት ! "" ሰላም ፡ ለአባ ፡ ጳውሊ ፤ ዘንጉሥ ፡ ወዓሊ ፤ ገዳማዊ ፡ ዘበአማን ፡ ኅሩይ ፤ ርዕሶሙ ፡ ለፈላስያን ፡ እለ ፡ በገዳም ፡፡ "" #ትርጉም ፦ በበረሃ ላሉ ባሕታውያን (መናንያን) አለቃቸው ፤ በእውነት የተመረጠ ገዳማዊ ፤ የንጉሥ ሎሌ ለኾነ ለአባ ጳውሊ ሰላምታ ይገባል ፡፡ JOIN @Applied_CHRISTIANITY

Открыть в Telegram
Просмотры276−9%к среднему
Пересылки—
Реакции3
Комментарии—
#8660Текст

Переслано из ተግባራዊ ክርስትና

📖 ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የታሪክ ክፍል " አንጥረኞችንና ይህን የመሰለውን ሥራ የሚሠሩትንም ሁሉ ሰብስቦ እንዲህ አላቸው ፤ ”እናንተ ሰዎች ሆይ ! ጥቅም የምናገኘው በዚህ ሥራችን እንደ ሆነ እናንተ ታውቃላችሁ..." ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በትምህርቱ እንዲሁም በተሰጠው የፈውስ ጸጋ በሕዝቡ ዘንድ የታወቀ ሆነ ። በዚህ ምክንያት ብር ሠሪ የሆነ ዲሜጥሮስ የሚባል ሰው በጳውሎስ ላይ ተነሳበት ። ይህ ዲሜጥሮስ የተባለ ሰው የጣኦታትን ቤተ መቅደስ ምስሎች በብር አስጊጦ የሚሰራ ነበር ። በዚያህ የክርስቶስ አምላክነት በመሰበኩ ብዙዎች ጦዖታትን ትተው በኢየሱስ ክርስቶስ ያምኑ ነበር ። በዚህ መሀል ይህ ዲሜጥሮስ ተነስቶ ፦" አንጥረኞችንና ይህን የመሰለውን ሥራ የሚሠሩትንም ሁሉ ሰብስቦ እንዲህ አላቸው ፤ ”እናንተ ሰዎች ሆይ ! ጥቅም የምናገኘው በዚህ ሥራችን እንደ ሆነ እናንተ ታውቃላችሁ ይህ ጳውሎስ ኤፌሶንን ብቻ ሳይሆን መላውን እስያ አሳተ ፣ ብዙ ሕዝብንም መለሰ በሰው እጅ የሚሰሩትንም ሁሉ አማልክት አይደሉም አላቸው ። አነርሱም ለጣኦታት በሚሰሩት ምስል ብዙ ገንዘብ ያተርፉ ነበርና ተቆጡ ። ምን ጊዜም ቢሆን ሃይማኖትን እና ሥራን ፣ ነፍስን እና ሥጋን ከፊታችን በማስቀመጥ ብልጫ የሚይዘው የቱ እንደሆነ ለያይተን ማዋቅ አለብን ። እነዚህ ሰዎች ከሞት በኋላ መንግሥተ ሰማያት ሊያገባቸው የሚችለውን እውነተኛ ሃይማኖት ችላ ብለው በዚህ ዓለም ጣኦት እያመለኩ ፣ እየበሉና እየጠጡ በመኖር እግዚአብሔርን መካድ አስበልጠዋል ። ደግሞም ኃጢአት እየሰራን የምናገኘው ገንዘብ ለእኛም ሆነ ለእግዚአብሔር አይጠቅምምና ልንጠነቀቅ ይገባል ። ቅዱስ ጳውሎስ እነዚህን ሰዎች ጣዖት አታምልኩ እንጂ ሥራ አትሥሩ አላላቸውም ፣ ቢያውቁበት ኖሮ ለጣኦት የሚሰሩትን ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በማድረግ በነፍስም በሥጋም ያተርፉ ነበር ። ዛሬም ቢሆን የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ያልተገቡ መልካም ያልሆኑ ሥራዎች ሲሰሩ ስትመለከት በመቃወሟ የልማት ጠል ናት ስትባል ትኖራለች ። .... እናንተስ ምን ትላላችሁ ? 🕊 መልካም ዕለተ ሰንበት ! JOIN @Applied_CHRISTIANITY

Открыть в Telegram
Просмотры290−4%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#8659Текст

Переслано из ተግባራዊ ክርስትና

✝️ ከኅዳር 12 እስከ ቀጣይ ሳምንት ኅዳር 19 ተከብረው የሚውሉ ክብረ በዓላት ፦ " የቅዱሳንን ታሪክ እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል ።" /አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ/" 🔔 ኅዳር 12 ቀን #ቅዳሜ 📖 ለሰው ወገን የሚያዝንና የሚራራ በእግዚአብሔር ጌትነት ዙፋን ፊት ሁል ጊዜ በመቆም ለፍጥረቱ ሁሉ የሚማልድ የመልአክት አለቃ በሰማያትም ለሚኖሩ ኃይሎች ሁሉ አለቃቸው ለሆነ ለቅዱስ ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው ። 📖 የመጥምቁ ዮሐንስ ራስ በደብረ ማህው የታየቼበት ነው ። 📖 የኢትዮጵያ ንጉሥ የጻድቁ በእደ ማርያም የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው ። 📖 ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ስልሳ ሦስተኛ የሆነ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ አባት ፊላታዎስ ዐረፈ ። 🔔 ኀዳር 13 ቀን #እሑድ 📖 የአእላፋት መላዕክትን የበዓላቸው መታሰቢያ እናደርግ ዘንድ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አዘዙን ። 📖 ዐሥራ ሦስት ወንበዴዎች ስለ እርሱ በእርሱ ሃይማኖት ከዓለም የተለዩ የከበረ ባለ ጸጋ አስክናፍር ዐረፈ ። 📖 የሀገረ እድና ኤጲስ ቆጶስ የከበረ አባ ጢሞቲዎስ ዐረፈ ። 📖 ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ስልሳ አራተኛ የሆነ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳስ ቅዱሳ አባ ዘካርያስ ዐረፈ ። 🔔 ኅዳር 14 ቀን #ሰኞ 📖 የሀገረ ጠራኪያ ኤጲስ ቆጶስ ቅዱስ አባ መርትያኖስ ዐረፈ ። 📖 ለፋርስ ንጉሥ ተአማር ያደረገ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የአባ ዳንኤል መታሰቢያ ነው ። 📖 የሱራስጦስ ፣ የእንድራዎስ ፣ የመብሪኖስ ፣ የራጢና የይስጥና ደግሞሞ የጋርሴስ ፣ የበጥላን ፣ የደብረ ቢዘኑም የሃይማኖት መምህር የአባ ዮሐንስ መታሰቢያቸው ነው ። 📖 በደብረ ቀልሞን የተሰራች ቤተ ክርስቲያንም የከበረችበት ነው ። 🔔 ኅዳር 15 ቀን #ማግሰኞ 📖 በዚህች ቀን የስሙ ትርጉም ቡሩክና የታመነ ቅዱስ ሚናስ በሰማዕትነት ዐረፈ ። 📖 ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ስልሳ አንደኛ የእስክንድርያው ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ አባት ሁለተኛው ሚናስ ዐረፈ ። 📖 የስብከት ጌና (ገና) ጾም መጀመሪያ ነው ፤ ይህም ክብር ይግባውና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለተወለደበት በግብጽ የሚኖሩ ያዕቆባውያን ክርስቲያኖች የሠሩት ሥርዓት ነው ። 🔔 ኅዳር 16 ቀን #ረቡዕ 📖 የከበረና የተመሰገነ የገዳማዊ አቡርፍር ከምስር ከተማ ውጭ የተሠራች ቤተ ክርስቲያኑ የከበረችበት ነው ። 📖 ለአባቶች አርባ ስምንተኛ የሆነ የእስክንድርያ ሀገረ ሊቀ ጳጳስ አባ ዮሐንስ ዐረፈ ። 📖 ቅዱስ ኪስጦስ በመኮንን በመክሲሞስ እጅ በሰማዕትነት ዐረፈ ። 📖 በሮሜ አገር በከሀዲ መኮንን በእስክንድርያ እጅ ቅድስት ጣጡስ በሰማዕትነት ዐረፈች ። 📖 የመነኰስ አባ ዳንኤልና የንጉሥ አኖሬዎስ የዕረፍታቸው መታሰቢያ ነው ። 📖 በሐይቅ ዳር እንደ ጽጌሬዳ መዓዛው የሚጥም የፊቅጦር መታሰቢያው ነው ። 🔔 ኅዳር 17 ቀን #ሐሙስ 📖 ታላቅ ክቡር የሆነ የዓለሙ ሁሉ መምህር የቁስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳስ የዮሐንስ አፈ ወርቅ ሥጋው የፈለሰበት ነው ። 📖 የቡሩክ አብርሃምና የሚስቱ የሐሪክ መታሰቢያቸው ነው ። ዳግመኛም የወጺፍ ጻድቃን መታሰቢያቸው ነው ። 📖 ዳግመኛም ለማስተማር የተጠራ የአበመኔቱ የአባ ሲኖዳ መታሰቢያው ነው ። 🔔 ኅዳር 18 ቀን #አርብ 📖 ቅዱሳን ደናግል አጥራስና ዮና በሰማዕትነት ዐረፉ ። 📖 ከዐሥራ ሁለቱ ቅዱሳን ሐዋርያት አባቶቻችን አንዱ ቅዱስ ፊልጶስ ሐዋርያ በሰማዕትነት ያረፈበት መታሰቢያ ነው ። 📖 ቅዱስ ኤላውትሮስና እናቱ አንትያ በሰማዕትነት ዐረፉ ። 📖 ዳግመኛም የየዋህ አትናቴዎስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው ። 🔔 ኅዳር 19 ቀን #ቅዳሜ 📖 ሩጻፋ በሚባል አገር የሰማዕት ሰርጊስ ቤተ ክርስቲያን የከበረችበት ነው ። 📖 የሮም ፣ የአፍርንጊ ፣ የሶርያ ፣ የአርማንያ ፣ ክርስቲያን ከግብጽ ፣ ከኢትዮጵያና ከናባ በቀር የስብከት ጌና (ገና) ጾምን የሚጀምሩበት ነው ። 📖 ጌቶቻችን ከሆኑ ከዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት የአንዱ የቅዱስ በርተሎሜዎስም መታሰቢያው ነው ። 📖 ቅዱስ ቴዎፍሎስ ከሚስቱ ጰጥሪቃ ፣ ከአምስት ወር ልጇም ከደማሊስ  ጋር በሰማዕትነት ዐረፉ ። " ክርስትና የሚጀምረው ከተግባር እንጂ ከወሬ አይደለም ። ሕይወታችን በጥቅስ ተገንዞ በጥቅስ የተቀበረ ፣ ከሕይወትና ከሥራ የተለየ እንዲሆን አንፍቀድለት ። " / ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ /  JOIN @Applied_CHRISTIANITY

Открыть в Telegram
Просмотры333+10%к среднему
Пересылки—
Реакции1
Комментарии—

Все посты