የሕጻናት አመጋገብ (ከ6 እስከ 8 ወር) (ሊንክ፦ ሕጻናት ምግብ ለመጀመር ዝግጁ ሲሆኑ በምን ይታወቃል?) (ሊንክ፦ የሕጻናት አመጋገብ እስከ 6 ወር ዕድሜ) በቀን ምን ያህል እና እንዴት መመገብ ያስፈልጋል? 👉🏾 በዚህ ጊዜም የሕጻናት ዋና ምግብ የጡት ወተት (ካልተቻለ ደግሞ የሕጻናት ወተት/ “ፎርሙላ) ቢሆንም፣ ጠጣር ምግብ መጀመር አለባቸው። 👉🏾 ልጅሽ በመጀመሪያ ሙከራ አልበላ ካለች፣ ጥቂት ቀናት ቆይተሽ ደግመሽ ሞክሪ። 👉🏾 ምግብ ሲጀምር ቅይጥ ነገሮችን ከመመገብ ይልቅ፣ በአንድ ዓይነት ነገር መጀመር ይሞከራል። እንዲህ ማድረጉ ምናልባት ልጅሽ አለርጂ ይኖርባት እንደሁ በቀላሉ ለመለየት ያስችላል። 👉🏾 መጀመሪያ ሰሞን በትንሹ (ከአንድ ወይ ሁለት የሻይ ማንኪያ ያልበለጠ) ምግብ መጀመር ይመከራል። 👉🏾 ቀስ በቀስ መጠኑን ወደ አንድ ወይ ሁለት የሾርባ ማንኪያ ከፍ ማድረግ፣ ምግቡንም እየቀየጡ መሄድ ይቻላል። 👉🏾 ሕጻናት ምግብ ይበልጥ እየለመዱ ሲሄዱ፣ ዓይነቱን እያበዙ እና በቀን ለበርካታ ጊዜ እየመገቡ መሄድ ይቻላል። 👉🏾 አዲስ ምግብ ሲያስጀምሩ ሁልጊዜም በትንሽ መጠን (በአንድ ወይም ሁለት የሻይ ማንኪያ) መጀመር ይመከራል፤ ይህም ልጅሽ አዲሱን ጣዕም እንድትላመድ ያግዛታል። 👉🏾 ሕጻናት እስከ 8 ወር ዕድሜያቸው በአብዛኛው አንድ ወይ ሁለት ጊዜ ብቻ በቀን ሊበሉ ይችላሉ። ከምን ምግቦች መጀመር ይሻላል? 👉🏾 የደቀቀ ፍራፍሬ (በተለይ ሙዝ እና አቮካዶ) 👉🏾 የደቀቀ እና የበሰለ አትክልት 👉🏾 የላመ እና በደንብ የበሰለ ሥጋ 👉🏾 የእህል ገንፎ #አራስ #አራስ_ልጅ #ሕጻን #አመጋገብ #6_ወር #7_ወር #8_ወር #አንደኛ_ዓመት Telegram፦ t.me/LeLijeInc Facebook፦ facebook.com/LeLijeInc Instagram፦ instagram.com/LeLijeInc Tiktok፦ tiktok.com/@LeLijeInc LinkedIn፦ linkedin.com/company/LeLijeInc 🌐 LeLije.com #ለልጄ © LeLije Inc
Открыть в Telegram
ለልጄ - LeLije
t.me/LeLijeChat facebook.com/LeLijeInc ለመልእክት: @LeLijeDM እርግዝና፣ ወሊድ እና ልጅ አስተዳደግ ላይ ከመረጃ ማዕከላችን የተሟላ መረጃ ያግኙ! 👉 በነጻ 👉 አስተማማኝ መረጃ 👉 ለጥያቄዎ መልስ የሚያገኙበት 👉 በተከታታይ እርግዝና እና ልጅ አስተዳደግን የሚከታተሉበት 👉 ማራኪ ሆኖ የቀረበ www.LeLije.com
Средние просмотры поста по дням
По дню публикации
Показать таблицей
| Дата | Просмотров на пост |
|---|---|
| 8 нояб. 2026 г. | 393 |
| 9 нояб. 2026 г. | 372 |
| 10 нояб. 2026 г. | 354 |
| 11 нояб. 2026 г. | 358 |
| 12 нояб. 2026 г. | 361 |
| 13 нояб. 2026 г. | 336 |
| 14 нояб. 2026 г. | 320 |
| 15 нояб. 2026 г. | 310 |
| 16 нояб. 2026 г. | 310 |
| 17 нояб. 2026 г. | 316 |
| 18 нояб. 2026 г. | 283 |
| 19 нояб. 2026 г. | 281 |
| 20 нояб. 2026 г. | 291 |
| 21 нояб. 2026 г. | 237 |
| 22 нояб. 2026 г. | 220 |
| 23 нояб. 2026 г. | 223 |
| 24 нояб. 2026 г. | 202 |
| 25 нояб. 2026 г. | 175 |
| 26 нояб. 2026 г. | 165 |
| 27 нояб. 2026 г. | 104 |
| 28 нояб. 2026 г. | 76 |
Самые просматриваемые за месяц
- 01Просмотры393Пересылки—Реакции—Комментарии—
- 02Просмотры372Пересылки—Реакции2Комментарии—
- 03Просмотры361Пересылки—Реакции1Комментарии—
- 04Просмотры358Пересылки—Реакции1Комментарии—
Новые посты
ለወሊድ ወደ ጤና ተቋም ስሄድ ምን ልያዝ? እርግዝናሽ 36 ወይ 37 ሳምንት ከሆነው በኋላ፣ ድንገት ወደ ጤና ተቋም መሄድ ቢኖርብሽ የሚከተሉትን ይዞ ለመሄድ አዘጋጅቶ መቆየት ይመከራል፦ 👉🏾 መታወቂያ 👉🏾 ምቹ ልብስና ጫማ (ከወለድሽ በኋላ ለመልበስ የሚመችሽ ለቀቅ ያለ ፒጃማ፣ ምቹ የሆነ “ታይት”፣ ካልሲ፣ ሰፋ የሚልሽ ጫማ (እግርሽ ሊያብጥ ስለሚችል)፣ ሻሽ 👉🏾 የመኝታ ጋወን 👉🏾 ጋቢ/ፎጣ 👉🏾 የሚመችሽ ትራስ 👉🏾 የጥርስ ብሩሽና ሳሙና፣ የሚስማማሽ ቅባት/ክሬም/ቫዝሊን፣ ቻፕስቲክ እና የመሳሰሉት 👉🏾 ስልክ እና ቻርጀር (እንዲሁም ለፎቶ/ቪዲዮ በቂ የሆነ “ሜሞሪ”) 👉🏾 የወር አበባ መጠበቂያ “ፓድ” (ከወሊድ በኋላ ለሚኖር ማንኛውም ከማኅጸን የሚወጣ ፈሳሽ) 👉🏾 የአዋቂ ዳይፐር (ለማንኛውም) 👉🏾 ለማንኛውም ሌላ ጉዳይ እየወሰድሽ ያለሽው ማቋረጥ የሌለብሽ መድኃኒት ካለ 👉🏾 ጥሬ ገንዘብ ወይም “የኤቲኤም” ካርድ (በጥንቃቄ የሚያዝ፣ አብሮ ያለ ሰው ቢይዘው የሚሻል) ለመጪው ሕጻን፦ 👉🏾 የአራስ ዳይፐር እና መጥረጊያ “ዋይፕ” 👉🏾 ጡጦ (ለማንኛውም - በተለይ በኦፕራሲዮን የምትወልጂ ከሆነ) 👉🏾 የአራስ ሕጻን ልብስ (ለማልበስ የማያስቸግር) 👉🏾 መጠቅለያ እና መታቀፊያ የምትወልጂበት ተቋም የሚያቀርበው ተጨማሪ ነገር ይኖር ከሆነ ቀድሞ በማጣራት (ለምሳሌ ዳይፐር እና ዋይፕ የሚያቀርብ ከሆነ) አንዳንድ ነገሮችን መያዝ ላያስፈልግሽ ይችላል። ምን ቀረ? ምን ይጨመር? አስተያይት መስጫው ላይ በማከል ያሳውቁን👇🏾 #እርግዝና #ወሊድ #ጤና_ተቋም Telegram፦ t.me/LeLijeInc Facebook፦ facebook.com/LeLijeInc Instagram፦ instagram.com/LeLijeInc Tiktok፦ tiktok.com/@LeLijeInc LinkedIn፦ linkedin.com/company/LeLijeInc 🌐 LeLije.com #ለልጄ © LeLije Inc
Открыть в Telegramሕጻናት ምግብ ለመጀመር ዝግጁ ሲሆኑ በምን ይታወቃል? ሕጻናት 6 ወር እስኪሞላቸው ድረስ የሚመከረው የጡት ወተት ብቻ እንዲጠቡ (ካልተቻለም የሕጻናት ወተት/ፎርሙላ እንዲጠቡ) ነው። (ሊንክ፦ የሕጻናት አመጋገብ እስከ 6 ወር ዕድሜ) ሕጻናት 6 ወር ከሞላቸው በኋላ ግን የሚያስፈልጓቸውን ከጡት ወተት የሚያስፈልጓቸውን ንጥረ ነገሮች ሁሉ አያገኙም። የጡት ወተት በተለይ እስከ አንድ ዓመት ዕድሜ አንዱ ወሳኝ የምግባቸው አካል ሆኖ ቢቀጥልም፣ በ6 ወር ዕድሜ ተጨማሪ ምግብ መጀመር ይኖርባቸዋል። አንዳንድ ሕጻናት ገና 6 ወር ሳይሞላቸው ምግብ ለመጀመር ዝግጁ ሊሆኑ ይችላሉ፤ ሆኖም የቱንም ያህል ቢቀድም ከ4 ወር በፊት ጠጣር ምግብ መጀመር የለባቸውም። ሕጻናት ጠጣር ምግብ ለመጀመር ዝግጁ ሲሆኑ በሚከተሉት ይታወቃል፦ 👉🏾 ራሳቸውን (ጭንቅላታቸውን) በራሳቸው መደገፍ ይችላሉ 👉🏾 የሕጻናት ወንበር ላይ ወይም በድጋፍ መቀመጥ ይችላሉ 👉🏾 ጉልህ የሆነ የክብደት ጭማሪ ያሳያሉ (ሲወለዱ ከነበረው እጥፍ ይመዝናሉ)፤ ቢያንስ 6 ኪሎ ይሆናሉ 👉🏾 ማንኪያ እንደጎረሱ አፋቸውን መግጠም ይችላሉ 👉🏾 የጎረሱትን ምግብ ወደ አፋቸው ውስጠኛ ክፍል መግፋት ይችላሉ ሕጻናት ምግብ ሲጀምሩ በምን ያህል መጠን እና በምን ዓይነት ምግብ ማስጀመር ይሻላል የሚለው ላይ እንመለሳለን። #አራስ #አራስ_ልጅ #ሕጻን #አመጋገብ #6_ወር #አንደኛ_ዓመት Telegram፦ t.me/LeLijeInc Facebook፦ facebook.com/LeLijeInc Instagram፦ instagram.com/LeLijeInc Tiktok፦ tiktok.com/@LeLijeInc LinkedIn፦ linkedin.com/company/LeLijeInc 🌐 LeLije.com #ለልጄ © LeLije Inc
Открыть в Telegramእርግዝና እና የፎሊክ አሲድ አወሳሰድ በእርግዝና ጊዜ ልጅሽ በጤና እንዲያድግ ፎሊክ አሲድ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። የፎሊክ አሲድ እንክብል መውሰድሽ በልጅሽ ላይ የነርቭ ቱቦ ችግር የመከሰት አደጋን ይቀንሳል። (ሊንክ፦ ፎሊክ አሲድ ምንድን ነው? ከምን ከምን ይገኛል?) (ሊንክ፦ ፎሊክ አሲድ ምን ይጠቅማል?) (ሊንክ፦ ፎሊክ አሲድ እና ስፒና ቢፊዳ) ፎሊክ አሲድ ምን ያህልና ከመቼ ጀምሮ መውሰድ አለብኝ? 👉🏾 ለማርገዝ ከመሞከርሽ በፊት (12 ሳምንት ድረስ ቀደም ብለሽ) ጀምሮ፣ አርግዘሽ 12 ሳምንት እስኪሆንሽ ድረስ ፎሊክ አሲድ መውሰድ አለብሽ። (እንደውም የመውለጃ ዕድሜ ላይ የደረሱ ሴቶች ሁሉ ፎሊክ አሲድ እንዲወስዱ ይመከራል) 👉🏾 በዚህ ጊዜ በየቀኑ አንድ 400 ማይክሮ ግራም የፎሊክ አሲድ እንክብል መውሰድ አለብሽ። 👉🏾 ፎሊክ አሲድ ያለ ሐኪም ማዘዣ ከመድሃኒት ቤት መግዛት ይቻላል። 👉🏾 ከፎሊክ አሲድ እንክብሎች በተጨማሪ ፎሌት የሚገኝባቸው እንደ አትክልት፣ ብርቱካን፣ አቮካዶ፣ ጥራጥሬ ያሉ ምግቦችን ተመገቢ። (ሊንክ፦ ፎሊክ አሲድ ከምን ከምን ይገኛል?) ፎሊክ አሲድ መውሰድ የሚያስከትለው አደጋ አለ? በአጠቃላይ የፎሊክ አሲድ በትክክለኛ መጠን መውሰዱ አደጋ አያስከትልም፤ ሰውነታችን ከሚያስፈልገው በላይ የሆነ ፎሊክ አሲድን በሽንት ያስወግዳል። ፎሊክ አሲድ የመውሰድ የጎንዮሽ ምልክቶችና አለርጂ አንዳንድ ሰዎች የሚከተሉት አነስተኛ የጎንዮሽ ምልክቶች ሊያጋጥሟቸው ይችላሉ፦ 👉🏾 የአፍ መምረር 👉🏾 ማቅለሽለሽ 👉🏾 የምግብ ፍላጎት ማጣት 👉🏾 ግራ የመጋባት ወይም የብስጭት ስሜት 👉🏾 የእንቅልፍ መዛባት ፎሊክ አሲድ መውሰድ ስትጀምሪ የሚከትሉት የአለርጂ ምልክቶች ከታዩብሽ ወደ ሐኪም መሄድ ይኖርብሻል፦ 👉🏾 ቆዳ ላይ ሽፍ ማለት 👉🏾 ማሳከክ 👉🏾 የቆዳ መቆጣት/መቅላት 👉🏾 ሲተነፍሱ መቸገር Telegram፦ t.me/LeLijeInc Facebook፦ facebook.com/LeLijeInc Instagram፦ instagram.com/LeLijeInc Tiktok፦ tiktok.com/@LeLijeInc LinkedIn፦ linkedin.com/company/LeLijeInc 🌐 LeLije.com #ለልጄ © LeLije Inc
Открыть в Telegramየሕጻናት አመጋገብ እስከ 6 ወር ዕድሜ 👉🏾 እስከ 6 ወር ዕድሜያቸው ድረስ ጨቅላ ሕጻናት ከመጥባታቸው ውጪ ምግብ መጀመር አይስፈልጋቸውም። 👉🏾 በዚህ ጊዜ የጡት ወተት ብቻ (ካልተቻለ የሕጻናት ወተት ወይም ፎርሙላ) መመገብ አለባቸው ። 👉🏾 የሕጻናት አንጀት እና ጨጓራ ገና በዕድገት ላይ ስለሆነ ጠጣር ምግብን ለመፍጨት ገና ዝግጁ አይደለም። ሕጻናት ለምግብ ዝግጁ የሚሆኑት መቼ ነው፤ እንዴትስ ይታወቃል የሚለው ላይ እንመለሳለን። #አራስ #አራስ_ልጅ #ሕጻን #አመጋገብ #6_ወር #አንደኛ_ዓመት Telegram፦ t.me/LeLijeInc Facebook፦ facebook.com/LeLijeInc Instagram፦ instagram.com/LeLijeInc Tiktok፦ tiktok.com/@LeLijeInc LinkedIn፦ linkedin.com/company/LeLijeInc 🌐 LeLije.com #ለልጄ © LeLije Inc
Открыть в Telegramፎሊክ አሲድ እና ስፒና ቢፊዳ ስፒና ቢፊዳ ምንድን ነው? (ሊንክ፦ እርግዝና እና ፎሊክ አሲድ - ፎሊክ አሲድ ምንድን ነው? ከምን ከምን ይገኛል?) (ሊንክ፦ እርግዝና እና ፎሊክ አሲድ - ፎሊክ አሲድ ምን ይጠቅማል?) ስፒና ቢፊዳ ሕጻናት የጀርባ አጥንታቸው (ሰረሰርን የሚይዘው) እና ሰረሰራቸው በሚገባ ሳያድግ ሲቀር የሚከሰት ከውልደት ጀምሮ የሚያጋጥም ችግር ነው። ስፒና ቢፊዳን የሚያስከተለው መነሻ ምን እንደሆነ ሙሉ በሙሉ ባይታወቅም፣ ከዘረ መል ውርስ (ለምሳሌ የቤተሰብ የነርቭ ቱቦ አለመዳበር የኋላ ታሪክ) እና አካባቢያዊ ነገሮች (ለምሳሌ የፎሌት እጥረት) ድምር ውጤት ጋር ይያያዛል። የስፒና ቢፊዳ ምልክቶች ምንድን ናቸው? የስፒና ቢፊዳ ዓይነቶች፣ ምልክቶች እና ደረጃው ከሰው ሰው ይለያያል። እንዲያም ሆኖ፣ በአጠቃላይ የስፒና ቢፊዳ ምልክቶች የሚከተሉትን ይመስላሉ፦ 👉🏾 የታችኛው የሰውነት ክፍል እግርን ጨምሮ የሚከሰት ሽባነት (paralysis) እና ተያይዞ ለመራመድ መቸገር ወይም አለመቻል 👉🏾 ሽንትን/ሰገራን መቆጣጠር አለመቻል 👉🏾 የጀርባ አጥንት ቅርጽ መዛባት እና የ S ቅርጽ መያዝ 👉🏾 ሲተነፍሱ፣ ሲውጡ፣ ዓይኖችን ሲያንቀሳቅሱ መቸገር 👉🏾 አንድን ነገር ለመማር/ለመልመድ መቸገር ስፒና ቢፊዳ ኖሯቸው የሚወለዱ ሕጻናት በአብዛኛው “ሃይድሮ ሴፋለስ” (hydrocephalus) የተባለ (ጥሬ የላቲን ትርጉሙ “አንጎል ውስጥ ያለ ውሃ” ማለት የሆነ) ሁኔታ ይኖራቸዋል። ይህ ሁኔታ ፈሳሽ ከአንጎል እንዳይወጣ በመዝጋት የሕጻናቱ የጭንቅላት መጠን ከተገቢው በላይ እየጨመረ እንዲሄድ ያደርጋል። እንዲህ ያለ ሁኔታ ሲከሰት በቀዶ ሕክምና ፈሳሽ ከአንጎል ወጥቶ የሚፈስበት ቱቦ በመሥራት ማስተካከያ ይደረጋል። አብዛኛውን ጊዜ የእርግዝና 18ኛ ሳምንት አካባቢ በሚደረግ የአልትራሳውንድ ምርመራ ስፒና ቢፊዳ መኖር አለመኖሩ መጣራት ይችላል። ፎሊክ አሲድ መውሰዱ አንዱ ወሳኝ የሆነበት ምክንያት ስፒና ቢፊዳ የመከሰት ዕድሉን ለመቀነስ ነው። ገና ለማርገዝ ስታስቢ ጀምሮ ፎሊክ አሲድ መውሰድሽ፣ እንዲሁም ፎሌት የሚገኝባቸው ምግቦች መመገብሽ ስፒና ቢፊዳን ይከላከላል። ምን ያህል ፎሊክ አሲድ መውሰድ ያስፈልጋል፤ እንዲሁም የጎንዮሽ ጉዳት ይኖረው ይሆን ወይ የሚለው ላይ እንመለሳለን። #እርግዝና #መጸነስ #ጤና #ፎሊክ_አሲድ #ፎሌት #ቫይታሚን #ስፒና_ቢፊዳ Telegram፦ t.me/LeLijeInc Facebook፦ facebook.com/LeLijeInc Instagram፦ instagram.com/LeLijeInc Tiktok፦ tiktok.com/@LeLijeInc LinkedIn፦ linkedin.com/company/LeLijeInc 🌐 LeLije.com #ለልጄ © LeLije Inc
Открыть в Telegramልጆችን ማድነቅ እና በቂ ትኩረት መስጠት በራስ የመተማመን ስሜታቸውን ይገነባል፤ ለራሳቸው የሚሰጡት ዋጋ ከፍ እንዲልም ያደርጋል። ልጆችን በማድነቅ ስለራሳቸው ቀና የሆነ አስተሳሰብ እንዲኖራቸው ማስለመጃ አንድ ሁነኛ መንገድ ነው። እንዲሁም ጥሩ ነገሮችን ማድረግ እንዲቀጥሉ ማበረታቻም ነው። ልጆቻችንን ስናደንቅ ጥሩ ነገር ሲያከናውኑ ለራሳቸው እውቅና እንዲሰጡ እንዲሁም በራሳቸው ማንነት እንዲኮሩ ማስለመድ ነው። ልጆችን በየዕድሜያቸው ለሚያደርጓቸው ልዩ ልዩ ነገሮች ልናደንቃቸው እንችላለን። ሕጻናትን ያልናቸውን ነገር ስላደረጉ፣ መጫወቻቸውን ወይም የያዙትን ነገር ለሌላ ልጅ ስላጋሩ ወዘተ ልናደንቃቸው እንችላለን። ዕድሜያቸው ከፍ ሲል ራሳቸውን ችለው ስለሚያደርጓቸው ነገሮች ልናደንቃቸው እንችላለን። በአስራዎቹ ዕድሜ የሚገኙ ልጆችን ትምህርታቸውን በአግባቡ ስለያዙ እና የቤት ሥራቸውን ያለ እኛ ማሳሰቢያ ስለሠሩ ልናደንቃቸው እንችላለን። #ሕጻን #ልጅ #እድገት #አስተዳደግ #ወላጅነት #አድናቆት #ማድነቅ #በራስ_መተማመን Telegram፦ t.me/LeLijeInc Facebook፦ facebook.com/LeLijeInc Instagram፦ instagram.com/LeLijeInc Tiktok፦ tiktok.com/@LeLijeInc LinkedIn፦ linkedin.com/company/LeLijeInc 🌐 LeLije.com #ለልጄ © LeLije Inc
Открыть в Telegramእርግዝና እና ፎሊክ አሲድ ፎሊክ አሲድ ምን ይጠቅማል? (ሊንክ፦ እርግዝና እና ፎሊክ አሲድ - ፎሊክ አሲድ ምንድን ነው? ከምን ከምን ይገኛል?) ፎሊክ አሲድ ለሁሉም ሰው የአካል እድገት እና መዳበር አስፈላጊ ቢሆንም፣ ለነፍሰ ጡር እናቶች ደግሞ ይበልጥ ወሳኝ ነው። 👉🏾 ሰውነትሽ የልጅሽን ዘረ መል (DNA) ለመሥራት የሚጠቀመው ፎሊክ አሲድን ነው። 👉🏾 እንዲሁም የልጅሽ የነርቭ ሥርዓት እና የነርቭ ቱቦ በአግባቡ እንዲዳብር ፎሊክ አሲድ ያስፈልጋል። የነርቭ ቱቦ (neural tube) በጽንስ ጊዜ ቀድመው ከሚዳብሩ የአካል ክፍሎች አንዱ ሲሆን፣ ቆየት ብሎ አንጎል እና ሰረሰር እንዲሁም እነዚህን ክፍሎች የሚከቡ አጥንቶች የሚሆን ነው። የነርቭ ቱቦ የሚዳብረው በእርግዝና ከ4 እስከ 6 ሳምንት ጊዜ ውስጥ ነው። የነርቭ ቱቦ ላይ የሚኖር እንከን ልዩ ልዩ የአካል ጉዳት ሊያስከትል ይችላል፤ እነዚህም ሽንት እና ሰገራ መቆጣጠር አለመቻል (ካደጉ በኋላም)፣ እንዲሁም የእግር ሽባነት ያካትታሉ። አንዳንዴ መዘዙ የከፋ ሲሆን ደግሞ “ስፒና ቢፊዳ” (spina bifida) የሚባለውን የነርቭ ቱቦ ችግር ሊፈጠር ይችላል። የስፒና ቢፊዳ ምንነት እና የፎሊክ አሲድ ተጨማሪ ነጥቦች ላይ እንመለሳለን። #እርግዝና #መጸነስ #ጤና #ፎሊክ_አሲድ #ፎሌት #ቫይታሚን Telegram፦ t.me/LeLijeInc Facebook፦ facebook.com/LeLijeInc Instagram፦ instagram.com/LeLijeInc Tiktok፦ tiktok.com/@LeLijeInc LinkedIn፦ linkedin.com/company/LeLijeInc 🌐 LeLije.com #ለልጄ © LeLije Inc
Открыть в Telegramየሕጻናት የወሊድ ክብደትን የሚወስኑ ነገሮች (ሊንክ፦ የሕጻናት የመጀመሪያ ዓመት የሰውነት ክብደት) አዲስ የሚወለዱ ሕጻናት ክብደት በሚከተሉት ነገሮች ሊወሰን ይችላል፦ 👉🏾 የዘረ መል ውርስ የወላጆች የሰውነት ክብደት የሚወለዱት ሕጻናት ክብደት ጋር ተያያዥነት ሊኖረው ይችላል። 👉🏾 የእርግዝና ጊዜ ርዝመት ከሚጠበቀው መውለጃ ቀን ቀድመው የሚወለዱ ሕጻናት በአብዛኛው ክብደታቸው አነስ ይላል፤ ቆይተው የሚወለዱት ደግሞ ይጨምራል። 👉🏾 የእርግዝና ጊዜ አመጋገብ በእርግዝና ጊዜ ጤናማ አመጋገብን መከተል ልጅሽ በማኅጸን ውስጥ ሳለች እና ከዚያም በኋላ ጤናማ እድገት እንዲኖራት ያግዛል። 👉🏾 የእርግዝና ጊዜ የኑሮ ዘዬ ሲጋራ ማጤስ፣ አልኮል መጠጣትና የመሳሰሉ ነገሮች ሌሎች ብዙ ችግሮች ከማስከተል ሌላ ሕጻናት ቀጭጨው እንዲወለዱ ያደርጋሉ። 👉🏾 የሕጻናት ጾታ በትንሹም ቢሆን ወንዶች ከሴቶች ሕጻናት ከፍ ያለ ክብደት ኖሯቸው ይወለዳሉ። 👉🏾 እናት በእርግዝና ጊዜ የነበራት ጤና ይዞታ እንደ ስኳር ሕመም፣ የልብ ሕመም፣ የደም ግፊት፣ ከፍተኛ የሰውነት ክብደት የመሳሰሉ የእናቲቱ ሁኔታዎች የሚወለደው ሕጻን ክብደት ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ። 👉🏾 በአንድ ጊዜ የተጸነሱ ሕጻናት ቁጥር መንታ ወይም ከዚያ በላይ የተረገዙ ከሆነ ማኅጸን ውስጥ ቦታ ስለሚጋሩ ክብደታቸው የቀነሰ ይሆናል። 👉🏾 የውልደት ቅደም ተከተል የበኩር ልጆች ቀጥለው ከሚወለዱ ልጆች በአብዛኛው ክብደታቸው ያነሰ ይሆናል። 👉🏾 የሕጻኑ ጤና ሕጻናት ሲወለዱ ያሉበት የጤና ይዞታ (ከጽንስ ጊዜ ጀምሮ ያለ የጤና እክል ካለ) ክብደታቸው ላይ ተጽዕኖ ይኖረዋል። #አራስ #አራስ_ልጅ #ሕጻን #እድገት #ክብደት Telegram፦ t.me/LeLijeInc Facebook፦ facebook.com/LeLijeInc Instagram፦ instagram.com/LeLijeInc Tiktok፦ tiktok.com/@LeLijeInc LinkedIn፦ linkedin.com/company/LeLijeInc 🌐 LeLije.com #ለልጄ © LeLije Inc
Открыть в Telegramእርግዝና እና ፎሊክ አሲድ እርግዝና ገና ሲታሰብ ጀምሮ አንዱ መወሰድ ያለበት ወሳኝ ንጥረ ነገር ፎሊክ አሲድ ነው። ፎሊክ አሲድ እና ሌሎች ወሳኝ ንጥረ ነገሮችን ጽንስ ከመፈጠሩ በፊትም ሆነ በእርግዝና ጊዜ መውሰድ እጅጉን አስፈላጊ ነው። የፎሊክ አሲድ እንክብሎች ለመጸነስ እየሞከሩ ላሉ ሴቶችም ሆነ ለነፍሰ ጡሮች እንዲወስዱ የሚመከር ነው። ፎሊክ አሲድ ምንድን ነው? ፎሊክ አሲድ “ፎሌት” የሚባለው ቫይታሚን ቢ 9 ሰው ሠራሽ ምርት ነው። ፎሌት ወይም ቫይታሚን ቢ 9 በተፈጥሮ የሚከተሉት ምግቦች ውስጥ ይገኛል፦ 👉🏾 አረንጓዴ ቅጠላማ አትክልት (ጎመን፣ ጥቅል ጎመን፣ ቆስጣ የመሳሰሉ) 👉🏾 ብርቱካን፣ መንደሪን እና ሎሚ 👉🏾 ጥራጥሬ 👉🏾 ለውዝ ከእርግዝና ጊዜ ውጪ ላሉት ጊዜያት ከምግብ የሚገኘው ፎሌት በአብዛኛው በቂ ነው። ሆኖም ፎሌት ምግብ ሲበስል በቀላሉ ሊጠፋ ይችላል። ለማርገዝ እየሞከሩ ላሉ ሴቶች እና ለነፍሰ ጡሮች በተጨማሪ ፎሊክ አሲድ መውሰድ ይኖርባቸዋል። ፎሊክ አሲድ ስላለው ጠቀሜታ እና ሳይወሰድ ሲቀር ሊከተል ስለሚችለው ችግር እንዲሁም ተያያዥ ጉዳዮች ላይ እንመለሳለን። #እርግዝና #መጸነስ #ጤና #ፎሊክ_አሲድ #ፎሌት #ቫይታሚን Telegram፦ t.me/LeLijeInc Facebook፦ facebook.com/LeLijeInc Instagram፦ instagram.com/LeLijeInc Tiktok፦ tiktok.com/@LeLijeInc LinkedIn፦ linkedin.com/company/LeLijeInc 🌐 LeLije.com #ለልጄ © LeLije Inc
Открыть в TelegramСвязи
Похожие каналы
busy mommin’@bookssforkidsСемья и дети1,42 тыс.
Надежда Голендерова. Развитие ребенка с рождения@earlydevelopmentСемья и дети1,42 тыс.
Rummammy@rummammyСемья и дети1,43 тыс.
👸عالم المراءة والطفل👶@naomaatСемья и дети1,42 тыс.
КрутОтец@krutotetsСемья и дети1,43 тыс.
KidsUp • Ваш гид по детскому развитию@kidsup_communityСемья и дети1,43 тыс.
Детский центр «Улей»@detskiy_centr_uleyСемья и дети1,41 тыс.
✌️Теперь мамский блог•Grippulya•Настя@grippulyaaСемья и дети1,41 тыс.