Посты канала #KALTUBE
የፓሪስ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩት ዣን ማሪ ሊውስቲዤ (Jean- Marie Lustiger) ደጋግመው የሚያወሱት አንድ ታሪክ ነበራቸው። አንድ ጊዜ ሦስት ወጣት ወንዶች በአካባቢያቸው ወደ ነበረው ቄስ ይሄዱና ለመናዘዝ እንደሚፈልጉ ይናገራሉ፤ ዓላማቸው በቄሱ ላይ የመቀለድ ብቻ ነበር። ከዚያም ወደ ኑዛዜ ክፍሉ ገብተው ክፉ ክፉ ኀጢአቶችን ለቄሱ ከተናዘዙ በኋላ ምክርም ተግሣጽም ሳይቀበሉ ሮጠው ይወጣሉ። ቄሱ የልጆቹ ዓላማ ገብቷቸዋል። ሁለቱ ልጆች ያሰቡትን ፈጽመው ሮጠው ከወጡ በኋላ የሦስተኛው ተራ ደረሰ። ልጁ አይሁዳዊ ነው። እርሱም ካህኑ ወደሚገኙበት ገብቶ “ኀጢአቱን” ተናዘዘ፤ እርሳቸውም ኀጢአቱን በሚመለከት ምን ማድረግ እንዳለበት መመሪያ ሰጡት። የተሰቀለውን ኢየሱስን ወደሚያሳየው በቤተ ክርስቲያኒቱ አንድ ጥግ ላይ የሚገኝ ምስል ተጠግቶ፣ “ይህን ሁሉ ያደረግኸው ለእኔ ነው፤ እኔ ግን ጕዳዬ አይደለም” በማለት ሦስቴ እንዲናገር አዘዙት። ልጅየው ይህንኑ ሊያደርግ ወጥቶ ሄደ። ይህ ለእርሱ የጨዋታው አካል ነው። ቀና ብሎ ወደ ኢየሱስ የስቅለት ምስል እየተመለከተ፣ “ይህን ያደረግኸው ለእኔ ነው፤ እኔ ግን ጕዳዬ አይደለም” በማለት አንዴ ተናገረ። ደገመው። ከዚያም ሦስተኛ ለመናገር ሞከረ፤ አልቻለም። እያለቀሰ የቤተ ክርስቲያኒቱን ግቢ ለቅቆ ወጣ። “ይህን ታሪክ ያወቅሁት” ይላሉ ጳጳሱ ሲናገሩ፣ “ያ ወጣት እኔ ስለ ነበርሁ ነው።” እናም የተለወጠው ወጣት፣ ማለትም ሊውስቲዤ ሕይወታቸው ተለውጦ እስከ ዕለተ ሞታቸው ድረስ ጌታን ሲያገለግሉ ኖሩ። ወደ መስቀሉ፣ ወደዚያ የውርደትና የፍቅር ስፍራ የሄደ ሁሉ ይለወጣል። የተሰቀለው ያድናልና። 📖 የተሰቀለው ✍ ጳውሎስ ፈቃዱ
Открыть в Telegramድነት ለፍጹማን የተዘጋጀ ሽልማት ሳይሆን በእምነት ለሚቀበሉት የእግዚአብሔር ጸጋ ነው። “የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል።” — ሮሜ 10፡13 አንዳንድ ጊዜ ልባችን በስህተት፣ በጸጸትና በሕይወት ድካም ይሞላል፤ ራሳችንን እንኳን ይቅር ማለት የሚያቅተን ጊዜ ይኖራል። ነገር ግን በዚያ ሁሉ መካከል አንድ የማይለወጥ እውነት አለ፤ እግዚአብሔር አሁንም ይወደናል! ለእርሱ ለመቅረብ ፍጹም መሆን፣ ስህተት አልባ መሆን ወይም ሁሉን በራሳችን መፍታት አያስፈልገንም። የተሰበረ ልብ ይዘን፣ እንባችንን ይዘን፣ የማንነታችንን ድካም ይዘን ወደ እርሱ መምጣት እንችላለን። እርሱ ከእኛ ርቆ የሚጠብቅ አምላክ ሳይሆን ወደ እርሱ የሚመጣውን በፍቅር የሚቀበል አባት ነው። ምንም ያህል ብንርቅ፣ ዛሬም ወደ እርሱ የምንመለስበት መንገድ አለ፤ የእርሱ ፍቅር ከስህተታችን የበለጠ ነው፣ ጸጋውም ከድካማችን የሚበልጥ ነው። ጸሎት አባቴ ሆይ፣ በውስጤ ያለውን ሕመም፣ ጸጸትና የተሰበረ ስሜት አንተ ታውቃለህ። ሰው ሊረዳኝ ባይችልም አንተ ልቤን ትረዳለህ። የደከመውን ልቤን አድስ፣ የጠፋውን ተስፋዬን መልስልኝ፣ በፊትህም አዲስ ሰው አድርገኝ። አሜን። Follow GCME SLM on: Facebook|Telegram|Ask on
Открыть в Telegramተስፋ — የነፍስ መልህቅ “ተስፋችን ማዕበሉ መቆሙ አይደለም፤ ማዕበሉ ቢነሳም መልህቃችን በእግዚአብሔር መጽናቱ ነው።” ተስፋ ማለት ነገሮች እንደምንፈልገው ሲሄዱ ብቻ የምንይዘው እምነት አይደለም፤ ሁኔታዎች ሲለወጡ፣ መንገዶች ሲጨልሙና መልሶች ሲዘገዩም በእግዚአብሔር ታማኝነት ላይ በጽናት መቆም ነው። መርከብ በማዕበል መካከል እንዳትንገዳገድ መልህቅ እንደሚያጸናት፣ ተስፋችንም በሕይወት ማዕበሎች መካከል እንዳንናወጥ ያጸናናል። ምክንያቱም ተስፋችን በሰው ቃል፣ በዓለም ሁኔታ ወይም በራሳችን አቅም ላይ ሳይሆን በማይለወጠው በእግዚአብሔር ታማኝነት ላይ የተመሠረተ ነው። ስለዚህ ዛሬ የምናየው ሁኔታ ምንም ይሁን ልባችን በፍርሃት እንዳይናወጥ፣ በተስፋው ላይ ጸንተን እንቁም። 🙏 ጸሎት ጌታ ሆይ፣ ተስፋዬ በሁኔታዎች ላይ ሳይሆን በአንተ ላይ እንዲመሠረት እርዳኝ። በመከራ ጊዜ እንዳልደክም፣ በመጠበቅ ጊዜ ተስፋ እንዳልቆርጥና በቃልህ እንድጸና እምነቴን አጽና። አንተ ታማኝ እንደሆንክ እያስታወስከኝ በሰላምህ ልቤን ጠብቅ። አሜን! Follow GCME SLM on: Facebook|Telegram|Ask on
Открыть в Telegramደቀ መዝሙር ከመምህሩ አይበልጥም (ማቴ. 10፥24-25)፡፡ ይህ አባባል ታዲያ መከራንስ አይመለከትም? ጌታችን ወደዚህ ምድር ሲመጣ መከራን ከተቀበለ፣ አማኞች በምድር ከምንም ዐይነት መከራ ነጻ ናቸው ብሎ መናገር እንዴት ይቻላል? የኢየሱስን መከራ ብቻ መተረኩ በቂ ይሆናል? የእኛስ የመከራ ተሞክሮ? በፍሬድሪክ ቡችነር ዕይታ፣ አንድ አገልጋይ የሚናገራቸው ሁለት ታሪኮች ይኖሩታል፤ አንዱ የኢየሱስ ሲሆን፣ ሌላኛው የራሱ ታሪክ ነው፡፡ 📖 የብርሃን አንጓዎች ✍ ጳውሎስ ፍቃዱ
Открыть в Telegramነፃነት ማለት ኃጢአትን የማድረጊያ የፈቃድ ወረቀት ማለት አይደለም። ማድረግ የምንፈልገውን ነገር በሙሉ የማድረግ ፈቃድ እጅግ የከፋ ባርነት ነው። «ነፃነት» ማለት በክርስቶስ ልሆን የምችለውን ሁሉ መሆን ማለት ነው። ፈቃድ ግዞት ሲሆን ነፃነት ግን ምሉዕነት ነው። 📖 በብስለት ማደግ ✍ በዋረን ደብልዩ
Открыть в Telegramየአዲስ ኪዳን መነፅር መጽሐፍ የምረቃ ስነስርዓት ሙሉ ፕሮግራም ተለቋል። https://youtu.be/o3h67A8iqGs?si=AEODuw2bhVVHDdcw
Открыть в Telegramለሁሉም ነገር ጊዜ እየሰጠን ለነፍሳችን ሕይወት ለሆነው ለእግዚአብሔር ግን ጊዜ እየቆጠብን እንዳንሆን እንጠንቀቅ። በየዕለቱ በሕይወት ሩጫ፣ በብዙ ሐሳቦችና በማያቋርጡ ጉዳዮች መካከል ስንዋከብ ከእግዚአብሔር ጋር የምናሳልፈውን ጊዜ ቀስ በቀስ ልናጣው እንችላለን። የዛሬ ጉዳይ ነገ ይተካል፣ የዛሬ ጭንቀት በሌላ ሐሳብ ይቀየራል፤ ነገር ግን ነፍሳችን የምታርፍበት የእግዚአብሔር ቃል አይተካም። ስለዚህ የእምነት ጉዞአችን በስሜት የሚጀምርና በድካም የሚቋረጥ ሳይሆን በየቀኑ ወደ እርሱ በመቅረብ የሚጸና መሆን አለበት። መዝሙረኛው፣ «ቃልህ ለእግሬ መብራት፣ ለመንገዴም ብርሃን ነው» እንዳለ (መዝሙር 119፥105)፣ ቃሉ በጨለማ ውስጥ ይመራናል፣ በድካም ጊዜ ያበረታናል፣ በጥርጣሬ መካከልም እምነታችንን ያጸናል። ዛሬ ከሁሉ ነገር ትንሽ ራሳችንን ለይተን፣ ዙረታችንን አቁመን ፊታችንን ወደ እርሱ እናዙር፤ ምክንያቱም እርሱን መፈለግ የአንድ ቀን ልምምድ ሳይሆን የዘላለም ሕይወት መሠረት ነው። ጸሎት: የሰማይ አባታችን ሆይ፣ በየዕለቱ በሚያጋጥሙን ብዙ ነገሮች መካከል አንተን እንዳንረሳ እርዳን። ልባችን በቃልህ እንዲጸና፣ ነፍሳችንም በፊትህ እረፍት እንዲያገኝ አድርግ። የጀመርነውን የእምነት ጉዞ በታማኝነት እንድንቀጥል፣ በድካም ጊዜ እንድንበረታና በሁሉም ወቅት አንተን ከሁሉ በላይ እንድንፈልግ ጸጋህን አብዛልን። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሜን! Follow GCME SLM on: Facebook|Telegram|Ask on
Открыть в Telegramለእግዚአብሔር መኖር ማለት ሁሉን መተው ሳይሆን፣ ያለንን ሁሉ ለእርሱ ክብር መጠቀም ነው። ብዙ ጊዜ ሕይወታችንን የምናሳልፈው የራሳችንን ሕልም ለማሳካት፣ ስኬታማ ለመሆንና የምንመኘውን ለማግኘት ስንሮጥ ነው። ነገር ግን ከዚህ ሁሉ በላይ አንድ ጥያቄ ልንጠይቅ ይገባል፤ እግዚአብሔር በሕይወቴ ምን ሊያደርግ ይፈልጋል? ሕይወታችን ለራሳችን ብቻ አይደለም፤ እግዚአብሔር ለእኛ ዓላማ አለው። ይህ ዓላማ ሁልጊዜ ታላቅ መድረክ ላይ መቆም ወይም ታላቅ ነገር ማድረግ አይደለም፤ በየዕለቱ በምንኖረው ሕይወት፣ በምናሳየው ፍቅር፣ በምንረዳቸው ሰዎችና በምናደርገው አገልግሎት ክርስቶስን ማሳየትም ነው። ስለዚህ ሕይወታችንን ለእርሱ ስንሰጥ እያጣን አይደለም፤ እውነተኛውን የሕይወት ትርጉም እያገኘን ነው። የምንሠራው፣ የምንናገረውና የምንኖረው ሁሉ ለእርሱ ክብር ይሁን። ጸሎት አምላኬ ሆይ፣ ሕይወቴን ለራሴ ብቻ እንዳልኖር እርዳኝ። የራሴን ፍላጎት ከፈቃድህ በላይ እንዳላደርግ፣ ያንተን ዓላማ እንድረዳና በምኖረው ሕይወት ሁሉ አንተን እንዳከብር አስተምረኝ። ሕይወቴ ለአንተ ክብርና ለመንግሥትህ ሥራ የተሰጠ ይሁን። አሜን! ❤️ Follow GCME SLM on: Facebook|Telegram|Ask on
Открыть в Telegramየአዲስ ኪዳን መነጽር መጽሐፍ ይፋዊ ምርቃት በአዲስ አበባ። https://youtu.be/fRz8kayogBs?si=7SoInKTlVG-dfDvp
Открыть в Telegramእግዚአብሔርን መስማት ማለት ሁልጊዜ አዲስ ድምፅ መጠበቅ አይደለም፤ በቃሉ የገለጠልንን እውነት ማወቅና በእርሱ መሠረት መኖር ነው። በየቀኑ በአእምሯችን ውስጥ ብዙ ድምፆች ይሰማሉ፤ የፍርሃት፣ የጥርጣሬ፣ የስራ ብዙ ሐሳቦች ይመላለሳሉ ። አንዳንድ ጊዜ አንድ ነገር ለማድረግ በልባችን ጠንካራ ፍላጎት ሲኖረን፣ “ይህ እግዚአብሔር የሚመራኝ መንገድ ይሆን?” ብለን እንጠይቃለን። ሁሌም በውስጣችን የሚመጣ ሐሳብ የእግዚአብሔር ድምፅ አይደለም። ስለዚህ እንደ ክርስቲያን ስሜታችንን ብቻ ሳይሆን ሐሳባችንንም በቃሉ መመዘን አለብን። መጽሐፍ ቅዱስ በ1ኛ ዮሐንስ 4፥1 “መናፍስትን ሁሉ አትመኑ፥ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ ሆኑ መናፍስትን ፈትኑ” ይለናል። ማለትም የምናስበው ነገር ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ይስማማል? ወደ ፍቅር፣ ወደ ይቅርታ፣ ወደ እውነትና ወደ ቅድስና ይመራናል? ብለን መጠየቅ አለብን። በተጨማሪም በጸሎት መፈለግ፣ በቃሉ ውስጥ መቆየትና መንፈሳዊ ብስለት ካላቸው አማኞች ምክር መስማት ያስፈልገናል። ወዳጆች ሆይ፣ በዚህ ዘመን የራሳችንን ፍላጎት ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር ማምታታት ቀላል ነው። ነገር ግን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመለየት የሚረዳን ዋናው መንገድ ከእርሱ ጋር ያለንን ግንኙነት ማጠናከር ነው። ዛሬ ራሳችንን እንጠይቅ፤ እኔ የራሴን ምኞት እየተከተልኩ ነው ወይስ እግዚአብሔር በቃሉ የሚያሳየኝን መንገድ እየተከተልኩ ነው? ሁልጊዜ ለመስማት ከመፈለጋችን በፊት ለመታዘዝ የተዘጋጀ ልብ ይኑረን። ጸሎት: ጌታ ሆይ፣ ሐሳቤንና ልቤን በቃልህ እንድመረምር እርዳኝ። የራሴን ፍላጎት ከፈቃድህ እንዳላምታታ፣ ድምፅህን በቃልህ እንድለይና በእውነትህ እንድመላለስ ጥበብን ስጠኝ። አሜን። Follow GCME SLM on: Facebook|Telegram|Ask on
Открыть в Telegramየሚገራርሙ ደጋግ ልቦችን እያየን ነው እግዚአብሔር በብዙ ይባርካቹ ! የካሌቤን እናትና ትናናሾቹ አሁንም የኛ እርዳታ ያሻቸዋል! 🏦1000622386511 Birtukan Aragaw Nigatu @christian_mezmur⭐️
Открыть в Telegramሪቫይቫል ሚቲንግ REVIVAL MEETING ቀጥታ በቴሌግራም ላይቭ !! ፀሎት እና ቃል! አገልጋዮች :-- መሳይ አለማየሁ (ነቢይ) ኢዮስያስ አዴቶ (ነቢይ) 👉ዛሬ ማክሰኞ ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ!! 👇Share💐ShareShare💐 @KALTUBE @KALTUBE @KALTUBE
Открыть в Telegramእግዚአብሔር ታጋሾች ሊያደርገን ይፈልጋል። ምክንያቱም ለሌሎች በረከቶች ሁሉ ቁልፍ ትዕግሥት ስለሆነ ነው። ትዕግሥትን መማር የማይችል ትንሽ ልጅ ሌሎች ነገሮችን ለመማር አይችልም። አንድ አማኝ እግዚአብሔርን መጠበቅ ሲማር እግዚአብሔር ታላላቅ ነገሮችን ሊያደርግለት ይችላል። 📖 በብስለት ማደግ ✍ ዋረን ደብልዩ ዌርዝቢ
Открыть в Telegram