#እንጸልይ? 🕊️ 💬 የዘላለም አባቴ ሆይ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ ሕያውና ጽኑ ቃልህን ስለሰጠኸኝ አመሰግንሃለሁ። ጌታ ሆይ፣ ቃልህን ሰምቶ ብቻ አድናቆት ከመስጠት እና ከመዘከር መንገድ አሁን ሕይወቴን አድንልኝ ፥ ጽኑ ባልሆነው እና በሚለዋወጠው አሸዋ ላይም ቤቴን እንድገነባ ለራሴ ፈቃድ አትተወኝ ፣ ጌታ ሆይ ሁሌ ጥበበኛ እንድሆንልና ልቤን እና የዕለትተዕለት ህይወቴን በእውነትህ ላይ እንድመሠርት በጸጋህ እርዳኝ ። ጌታ ሆይ፣ ቃልህን በጆሮዬ እንድሰማ ብቻ ሳይሆን በእምነት እንድቀበለውና በዕለት ተዕለት ልምምዴ ውስጥ እንድተገብረው ዘንድ አስችለኝ። ዝናቡ ሲዘንብ፣ ጎርፍ ሲወርድ፣ የፈተናና የጥርጣሬ ነፋስ በሕይወቴ ላይ ሲመጣ፣ እንዳልናወጥ እና እንዳልጠፋ በቃልህ ደግፈኝ። አባት ሆይ ፤ ቤቴን ፣ አእምሮዬንና ከፊት ለፊቴ ያለውን ዘመኔን ሁሉ በማይነቃነቀው ዓለት በክርስቶስ ላይ አኑርልኝ። በታዛዥነት እንድመላለስ ኃይልህን ጨምርልኝ። ፣ በብርታትህ ተደግፌ፣ በእያንዳንዱ አስቸጋሪ ቀናት ጸንቼ እንድቆም አድርገኝ ። በኢየሱስ ስም ጸልያለው ፣ አሜን። ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ “እንግዲህ ይህን ቃሌን ሰምቶ በተግባር የሚያውል፣ ቤቱን በዐለት ላይ የሠራን ብልኅ ሰው ይመስላል። ዶፍ ወረደ፤ ጎርፍም ጎረፈ፤ ነፋስም ነፈሰ፤ ያን ቤት መታው፤ በዐለትም ላይ ስለ ተመሠረተ አልወደቀም።” (ማቴ 7፥24-25 አመት) 🕊️ Join©️@hymnsofmes
Открыть в TelegramПосты канала ማዳኑን አውሩ | ᴘʀᴏᴄʟᴀɪᴍ ʜɪꜱ ꜱᴀʟᴠᴀᴛɪᴏɴ
💬 ከእግዚአብሔር ጋር የምናደርገውን የዕለት ተዕለት ጉዞ ችላ ስንል፣ ኢየሱስ ያዳነንን ነገር እና በህይወት የመኖራችንን ትርጉም እና ምክንያት ሙሉ በሙሉ እንረሳለን፣ በስተመጨረሻም በመንፈሳዊ ዕውር እንሆናለን። የሚያስደንቀው ነገር ፤ ቸልተኝነት በአንድ ጀምበር እምብዛም አይከሰትም። ይህ የሚሆነው የዕለት ተዕለት ጭንቀቶች፣ የገንዘብ እና የግል ፍላጎቶች ፥ ከልክ ያለፈ ምድራዊነት ፤ ለእግዚአብሔር ያለንን ትኩረት ቀስ በቀስ ሲያደናቅፉ ነው። 💬 እንፀልይ? የሰማይ አምላክ ሆይ ጌታ ኢየሱስን በትኩረት መከተል ፥ በጸሎት እና አምልኮ በየዕለቱ ከኢየሱስ ጋር የግል ግንኙነት በማድረግ እና ቅዱሱን ወንጌል በምርጫዎቼ ፣ በድርጊቶቼ በሁሉ ነገሮች ላይ ባለኝ ግንኙነት መተግበር እንድንችል ፀጋህ ይርዳኝ። አሜን። 🙏 —————————————————— ዕብ 2 2፤ በመላእክት የተነገረው ቃል ጽኑ ከሆነ፥ መተላለፍና አለመታዘዝም ሁሉ የጽድቅን ብድራት ከተቀበለ፥ እኛስ እንዲህ ያለውን ታላቅ መዳን ቸል ብንለው፥ እንዴት እናመልጣለን? 3፤ ይህ በጌታ በመጀመሪያ የተነገረ ነበርና፥ የሰሙትም ለእኛ አጸኑት፥ 🕊️ Join©️@hymnsofmes
Открыть в Telegram#እንጸልይ🙏 💬 የሰማይ አባቴ ሆይ፣ በሕይወት ጉዞዬ ውስጥ ስራመድ ብቻዬን እንደማትተወኝ ቃል ስለገባህልኝ አመሰግናለሁ። ጭንቀት፣ ጥርጣሬ እና አድካሚ ፍርሃት ልቤን ለመሙላት ሲሞክሩ፣ አንተ ከእኔ ጋር እንዳለህ የሚያስታውሰኝን ድምፅህን ፥ እና መንፈስ ቅዱስን እንድሰማ እርዳኝ። ጌታ ሆይ፣ ኃይልህን ከማየት ይልቅ ችግሮቼን በማየቴ ይቅር በለኝ። አንተ አምላኬ ነህ፣ አንተ በእኔ ላይ አትደክምም ደግሞ ተስፋ አትቆርጥም። አምላኬ ሆይ ድካም እና ተስፋ መቁረጥ በሚሰማኝ ቦታ ሁሉ አበርታኝ ፣ ዛሬ በህይወቴ ላይ በሚያጋጥሙኝ ልዩ ልዩ ተግዳሮቶች ሁሉ እርዳኝ እና በጽድቅ ቀኝ እጅህ ደግፈኝ። ጭንቀቴን በጥልቅ ሰላምህ እና ዕረፍትህ ይተካ፣ደግሞም እምነቴ በቃልህ ጸንቶ እንዲቆም አድርገኝ። በኢየሱስ ስም እጸልያለሁ፣ አሜን። “እኔ ከአንተ ጋራ ነኝና አትፍራ፤ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ። አበረታሃለሁ፤ እረዳሃለሁ፤ በጽድቄም ቀኝ እጄ ደግፌ እይዝሃለሁ።” (ኢሳ 41፥10 አመት) 💬 Join @hymnsofmes
Открыть в Telegram🌼መልካም ዐዲስ ዓመት ቤተሰቦች🌼 ይህ የተቀበልነው ዐዲሱ ዓመት እግዚአብሔር እጆቻችንን፣ ቤቶቻችንን እና የሥራ ቦታዎቻችንን የጸጋውና የእርቅ ምሽጎች አድርጎ ይጠቀምባቸው። ብርሃናችን በሌሎች ሰዎች ፊት የበራ ይሁን! አሜን🙏 2ኛ ቆሮ 5 20፤ እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ ስለ ክርስቶስ መልክተኞች ነን፤ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን። @hymnsofmes #ማዳኑንአውሩ
Открыть в TelegramПереслано из Fan's Pulpit
"...በግል ጸሎታችን ውስጥ ጎልጎታን የሚያስታውስ ምስጋና ከጠፋ፣ በምንሰማው ስብከት ውስጥ የመስቀሉ ማዕከላዊነት ከቀረ፣ በጌታ ራት ወቅት የመስቀሉ ትዝታ እንደ አማራጭ ከታየ፣ የጎልጎታው ክስተት፣ በርሱም የተከናወነው አስደናቂ ነገር በጥቂቱም ቢሆን ከእይታችን ከተሰወረ፣ ያን ጊዜ የቅድስና ሕይወት ከእኛ መጥፋቱ አይቀሬ ይሆናል።" ስቱአርት ኦሊዮት "እነሆ ወንጌሉ: የሮሜ መልእክት ማብራሪያ በቀላል አቀራረብ፣ ትርጉም በፋኑኤል ብርሃነ (ዐዲስ ዐበባ፣ ጎስፕል ፎከስ ሚኒስትሪ፣ 2018 ዓ.ም) ገጽ 73። መጽሐፉ ሣር ቤቴ ኤግስት ሕንጻ 4ኛ ፎቅ ላይ ይገኛል።
Открыть в Telegramእግዚአብሔር አምላክ ምንም አይጎድልበትም፤ ነገር ግን በየዕለቱ በግንኙነታችን ውስጥ እርሱን ስንከተለው በፍፁም ነፍሳችን ፥ ልባችን እና ኃይላችን እንድንከተለው ይጠይቃል ? ይህ ፀሎቴ ነው ፤ ዳዊትም በመዝሙር በመዝሙር 139 አምላኩን #አቤቱ_መርምረኝ በማለት ልቡን እና መንገዱን ለአምላኩ በፀሎት ሲያዝገዛ እንመለከታለን። እናንተም በማዳመጥ እንድትፅናኑ በማለዳ አበረታታቹሃለው። ዋና መዝሙር ጌታ ያውቃል እና ብሩክታዊት። https://youtu.be/udd4g7N0Qy0?si=tWMmFvm3rvP1KXf5
Открыть в Telegram𝗦𝗲𝗹𝗮𝗺 𝗗𝗲𝗮𝗿 𝗔𝗹𝗹, 𝗢𝗽𝗲𝗻 𝘆𝗼𝘂𝗿 𝗵𝗲𝗮𝗿𝘁 𝗮𝗻𝗱 𝘁𝗮𝗸𝗲 𝘁𝗶𝗺𝗲 𝘁𝗼 𝘄𝗮𝘁𝗰𝗵 𝘁𝗵𝗶𝘀 𝗽𝗼𝘄𝗲𝗿𝗳𝘂𝗹 𝗺𝗲𝘀𝘀𝗮𝗴𝗲. 𝗠𝗮𝘆 𝗚𝗼𝗱 𝘁𝗼𝘂𝗰𝗵 𝘆𝗼𝘂𝗿 𝗹𝗶𝗳𝗲 𝘁𝗵𝗿𝗼𝘂𝗴𝗵 𝘁𝗵𝗶𝘀 𝘄𝗼𝗿𝗱! 𝗔𝗺𝗲𝗻. ♥️🙏
Открыть в Telegram#እንፀልይ🙏 እግዚአብሔር አባት ሆይ፣ እኔ ስለ እኔ ከማውቀው በላይ አንተ ታውቀኛለህ። ልቤን እንድትመረምርና የሚያስጨንቁኝን ሀሳቦቼን እንድትለይልኝ ልቤን ከፍቼ እጋብዝሃለሁ። ከአንተ ጋር እስመጨረሻው ለመራመድ የሚያደናቅፉኝን ማንኛውንም የተደበቁ ስውር በደሎችን ፣ ሐጢያቶችን እና የጨለማ ሃሳቦችን በሙሉ በፀጋህ አስወግድልኝ። ይቅርታህ በህይወቴ ስለበዛ አመሰግንሃለው ። በዘላለም ሕይወት መንገድ ላይ በፅድቅ እና በቅድስና ምራኝ። በኢየሱስ ስም እፀልያለሁ ፣ አሜን !! ——————————————————— መዝሙረ ዳዊት 139 23፤ አቤቱ፥ መርምረኝ ልቤንም እወቅ፤ ፍተነኝ መንገዴንም እወቅ፤ 24፤ በደልንም በእኔ ውስጥ ብታገኝ እይ፤ የዘላለምንም መንገድ ምራኝ። @hymnsofmes
Открыть в Telegramመዝ 119 103፤ ቃልህ ለጕሮሮዬ ጣፋጭ ነው፤ ከማርና ከወለላ ይልቅ ለአፌ ጣፈጠኝ። —————————————————— #እንፀልይ 🙏 አምላኬ ሆይ ፥ ውብ ስጦታህ ስለሆነው ስለ ቃልህ ተመስገን ፣ ይህም ደግም ለነፍሴ እንደ ቋሚ መልሕቅና ምቹ መጠጊያ ሆኖ ስለሚያገለግለኝ አመሰግንሃለው። መጽሐፍ ቅዱስህን በእውነት እንደ ሕያው እንጀራ እና እንደ ዕለት ተዕለት የሕይወቴ መማሪያ መጽሐፍ አድርጌ እንቆጥረው ጸጋህን ፣ ማስተዋልን ና ጥበብን ጨምርልኝ። ጌታ ሆይ፣ እባክህ ቃልህ በፍፁም ልቤና ሃሳብ እንድወደው እንድኖረውም ዛሬ መንፈሳዊ ስሜቶቼን አነቃቃ። ውስጣዊ ፍላጎቶቼን እንድታድስልኝ እጸልያለሁ፤ እያጋጠመኝ ያለውን ማንኛውንም መንፈሳዊ ድርቀት ወይም ቃልህን ለማንበብ ያለ መሰልቸት እንድትፈውስልኝ ፤ ጸጋህን አፍስስልኝ ። ስለሰማህኝ አመሰግናለሁ ! በኢየሱስ ስም እፀልያለሁ ፥ አሜን! ©️@hymnsofmes
Открыть в Telegram#እንፀልይ 🙏 ጌታ ሆይ፣ ዛሬ ወደ አንተ እንዲህ ብዬ እፀልያለሁ ፥ ቃልህን አንብቤ ፥ ትምህርቶችህን ሰምቼ ብቼ ራሴን የማስት ሳይሆን ፤ ተግባራዊም ለማድረግ የምችልበትን አቅም እንድትሰጠኝ ዘንድ ጸጋህን እለምንሃለሁ። ቃልህን በተግባር ሳላደርግ ሰሚ እና ተናጋሪ ብቻ የሚያደርገኝን ማንኛውንም መንፈሳዊ ስንፍና ወይም ዝለት ከእኔ አስወግድ። ስሜቶቼን፣ እምነቶቼን እና ድርጊቶቼን ሁሉ ከፈቃድህ ጋር በትክክል እንዲስማሙ ቀይር። በምሠራው ስራ ሁሉ አንተን አከብርህ ዘንድ ሕይወቴን በፀጋህ አፅናው ። ስለሰማህኝ አመሰግንሀለሁ ! አሜን! ©️@hymnsofmes
Открыть в Telegram