Кабинет

Посты канала ወኔ እና ቅኔ -(ፈይሠል አሚን)

сначала новые

#3947Фото
Просмотры680−30%к среднему
Пересылки—
Реакции52
Комментарии—
#3944Текст

በመጨረሻም የመጨረሻ መጽሐፌ ቅዳሜ ገበያ ላይ ይውላል! ሰዎች መልካም ቢኾን፣ተንኮልን ባይመርጡ ይኽ መጽሐፍ የዛሬ ሁለት ዓመት ገበያ ላይ ይወጣ ነበር። መንገዱ ተስፋ ቢያስቆርጥም፣ ተንኮል እንደ ቄጤማ ቢጎዘጎዝበትም፣ ብዙ አልቅሼ፣ ብዙ አጥቼ በመጨረሻም ተሳክቷል።ቅዳሜ ገበያ ላይ ይውላል! በመጀመሪያ “ፍቅር ከደመና” የተሠኘች ትንሽዬ የግጥም ስብስብ፣ አስከትዬ “ኢንጅነሩን ማን ገደላቸው?” የተባለ የአጫጭር ታሪኮች አሳትሜ ራሴን ማሳደግ እንዳለብኝ አምኜ ከህትመት ርቄ ነበር። በዚህ መሐል ነው አንድ ባለሃብት አንድ መድረክ ላይ ወግ አቅርቤ ስወርድ “መጽሐፍ ብታሳትም” የሚል ሐሳብ ያቀረበልኝ። ለጊዜው አቅም እንደሌለኝ ስነግረው “አንተ ጨርስ እንጂ እኔ አሳትምልሃለሁ” ያለኝ። በዚህ ምክንያት ያሉኝን ሥራዎች አሰናድቼ ወደ ባለሃብቱ ስሔድ ግን ሥራዬን ዐይቶ ከመወሰን ይልቅ ዙሪያዬ ያሉ ሰዎችን ስለ መጽሐፌ መጠየቅን ነበር የመረጠው። ዙሪያዬ ያሉ ሰዎች ጥሩ ነገር አልነገሩትም። በቆንጆ ቃላት፣ በትህትና ተሞልተው እንዳይታተም አደረጉ። “መጽሐፉ ፖለቲካ ነው!” ብለው ለእሱ ያሰቡ አስመስለው አከሸፉት። ይኽን በቅርብ ነው የሰማሁት። Guess what? ተስፋ አልቆረጥኩም። ተንኮል ይፈጥናል እንጂ አይቀድምም፣ ምቀኝነት ይነሳል እንጂ አይደርስም። ክፋት ይመራል እንጂ አያሸንፍም። ይኼን ሁሉ ያለፈው ሰንባች ቅዳሜ ገበያ ላይ ይውላል። ብዙ ዕዳ ውስጥ ወድቄ፣ የብዙ ሰው ገንዘብ ኖሮብኝም ቢኾን እዚህ አድርሼዋለሁ። ከዚህ በኋላ የማሳተም ፍላጎትም ኾነ አቅም እስካይኖረኝ ድረስ ቢያደርገኝም….አልሃምዱሊላህ እዚህ ደርሷል። በማስተዋወቅ እና በመግዛት አግዙኝ። እንደምትወዱት እልፍ ፐርሰንት እርግጠኛ ነኝ። ቀድማችሁ የገዛችሁ ወዳጆች ከቅዳሜ ጀምሮ በአክብሮት አስረክባችኋለሁ፣ልዩ ምስጋናዬም ይድረሳችሁ!

Открыть в Telegram
Просмотры1 100+13%к среднему
Пересылки—
Реакции43
Комментарии—
#3943Текст
Просмотры2 620+170%к среднему
Пересылки—
Реакции54
Комментарии—
#3942Текст
Просмотры3 780+290%к среднему
Пересылки—
Реакции57
Комментарии—
#3941Текст
Просмотры4 370+351%к среднему
Пересылки—
Реакции75
Комментарии—
#3939Текст
Просмотры5 140+430%к среднему
Пересылки—
Реакции96
Комментарии—
#3938Текст

መስከረምን እወዳታለሁ! (8) #ፈይሠል_አሚን (በዓመት አንድ ቀን ብቻ የሚነበበው ተከታታይ ታሪክ እነሆ ስምንተኛ ዓመቱ wow!😮) . ይህን ስናገር ዛሬ ሰዎች እንደሚገምቱት ልቤ አይደነግጥም። እንደቀድሞም አይሰበርም። አሁን ልቤ ብዙ ነገር አይገርመውም። መስከረምን ያክል እኩል እሣት፣እኩል በረዶ የገጠመው በምን ይገረማል? የሰው ልጅ በየዓመቱ አዲስ ዓመት ሲመጣ አዲስ ሕይወት እጀምራለሁ ይላል። እኔ ግን የጀመርኩት ሕይወት አዲስ አልሆነም። እኔ በአንድ ጉዳይ ስባክን መስከረም ደረሰ።ዓመት ተቀየረ።የጠፉት ወፎች ተመለሱ፣ የከሰሙ ግንዶች እንቡጥ ፀነሱ። አልተቀየርኩም።መስከረም ግን ተቀየረች። “ምን ያህል ነው የምትጠብቀው?” ይሉኛል. . . እኔ ዝም ስል ልቤ ይመልሳል:- “እስከ መቼ እንደሚጠብቅ አላውቅም፤ ግን የሚጠብቀው ሰው እስከሌለ ድረስ ይመስለኛል” ይላል። ዝም እላለሁ።ልቤ አንዳንዴ ከአፌ ይልቅ እውነት እንደሚናገር ስለማውቅ። ⸻ አምና መስከረም ጠብቶ በአስራ ሁለተኛው ቀን የውዷ መስከረም ሠርግ ተደገሰ። መስከረም 12 ድረስ የነበሩትን ቀናት ተከፋፍሎ እንደተቀመጡ የዶሮ ብልት ቆጠርኳቸው። አንድ። ሁለት። ሦስት። አስራ አንድ። አስራ ሁለት። እሷ ልትዳር ነው።እኔም ልቤን ልቀብር ነው።ሠርግ እና ቀብር አንድ ቀን ላይ መዋል እንደሚችሉና አንዱ ከቁብም እንደማይቆጠር ተረዳሁ። ልዩነቱ በአንዱ ላይ ሰዎች ነጭ ጋቢ ለከጥሎሽ ጋር ይሠጣሉ፣ በሌላው ላይ ጋቢ ለብሰው ያዝናሉ። ወደ ሠርጉ ስሄድ አንድ ሰው “ለሙሽራዋ ምን ይዘህ መጣህ?” አለኝ።(ይኼ ሰላይ!) “ምንም።” “እንዴ? በባዶ እጅ?” “በባዶ እጅ አይደለም። የአሥራ ሁለት ዓመት ፍቅር ይዣለሁ።” * መስከረም ወደ አዳራሹ ገባች።የሠርግ ልብስ ለብሳ።ፊቷ ላይ ደስታ ነበር።እኔ ግን ፊቷን እያየሁ በውስጤ አንዲት ልጅ ታየችኝ። የልጅነቴ መስከረም።በጎዳና ላይ ከእኔ ጋር የምትሮጠው።የእኔን እንጀራ ከእኔ ጋር የምትካፈለው።እኔ ስወድቅ የምትስቅብኝ። እሷ ስትወድቅ ግን የማለቅስላት። ያች መስከረም ከዚህች መስከረም ጋር ተመሳሳይ ፊት ነበራት።ግን ተመሳሳይ ልብ አልነበራትም። ምናልባት ሰው እያደገ ሲሄድ ፊቱ በመስታወት ይታያል፤ ልቡ ግን…..ይጠፋል? እኔንጃ! ⸻ ሙሽራው መጣ።አምሮበታል።ጥሩ ልብስ ነበረው። ጥሩ መኪና እንዳለው በሰፈሩ ተወርቷል።ጎበዝ ነጋዴ ነውም ተብሏል።ሰዎች ሁሉ “እድለኛ ልጅ ነው” አሉ። እኔ ግን አንድ ነገር አሰብኩ።እድለኛ ማለት ሁሉን ያገኘ ሰው ነው? ወይስ ያገኘውን ማጣት የማይፈራ ሰው? መልሱን አላገኘሁም። ከመፈላሰፍ በፊት ሆድ መሙላግ ይቀድማል ብዬ ሔጄ ቡፌ አነሣሁ። ⸻ ሠርጉ እየተጠናቀቀ ነበር። መስከረም ከሙሽራው ጎን ቆማ ፎቶ ትነሳ ነበር። እኔ ግን በርቀት ቆሜ ዐየኋት። እና በዚያኅ ቅጽበት ብዙ ነገሮች በሕሊናዬ እየተጨረፉ ማለፍ ጀመሩ። አባቷን፣የበዓል በጎች፣ ያ ሐሰተኛው ፓይለት፣ሕመሟ፣ አልጋዋ፣ ኬኩ. . .ያም የአምስት ብር ሥዕል ይዞ የመጣውን ልጅ ሳይቀር አሰብኩ። ድንገት እንባዬ ከዓይኔ አምልጦ ወደ ጉንጬ ፈሰሰ። ማንም ሳያየኝ በፍጥነት እንባዬን ጠርጌ ወደ ሙሽሮቹ እያየሂ ፈገግ አልኩ። “ምንድነው ያስለቀሰህ?” የሚል የሴት ድምጽ ሰማሁ። ዞር ብዬ ሳያት ልቤ ደነገጠ። ጠይም ቆንጆ ሴት ወይን ይዛ ቆማለች። ውበቷን ከማድነቅ ይልቅ ማልቀሴን መካድ መረጥኩ። እሷ ግን ክህደቴ አልገረማትም። “አንተ ስላላየኸኝ እንጂ ሳለቅስ ብታየኝ እክድ ነበር” ብላ ሳግ ተናነቃት። “ይኼ ከሃዲ!” አለች ሙሽራዋን እያየች። የኔን ህመም የተሸከመ ሰው ያገኘሁ መሰለኝ። ሁለት ከሃዲዎች ሲጋቡ እንባ እያፈሰሱ የቀሩ ሁለት ነፍሶች ተገናኙ። እኔ እና ጠይሟ ቆንጆ። ምንም ዐይነት የታሪክ ማብራሪያ ሳልጠይቅ እጄ ዘርግቼ “ፋሲካ እባላለሁ!” እጄን ሠድጄ: መልሳ እጇን ዘርግታ “መስከረም እባላለሁ” አለች በፈገግታ። ድንግጥ አልኩ። ደግሞ ሌላ መስከረም? ድንጋጤዬ ግራ አጋብቷት “ምነው?” አለች። የሙሽሪቷን ስም አልሰማችም መሰለኝ። የዓመት ሰው ይበለን! ለክፍል 9 ያድርሰን! . @huluezih @huluezih

Открыть в Telegram
Просмотры4 810+396%к среднему
Пересылки—
Реакции79
Комментарии—
#3936Текст
Просмотры4 380+352%к среднему
Пересылки—
Реакции88
Комментарии—
#3935Текст
Просмотры7 520+675%к среднему
Пересылки—
Реакции92
Комментарии—
#3933Текст
Просмотры7 740+698%к среднему
Пересылки—
Реакции89
Комментарии—
#3930Текст

ቀጣይ ዓመት ራሴ ላነበው ለራሴ የጻፍኩት (ማንም እንዳያነበው!) . ዕጣ-ፈንታ ዕድሜ ሠጥቶህ ይኽን እንድታነብ ከፈቀደልህ፣ እንደ ለኸድ የጨለመውንና የጠበበውን መንገድ ማለፍህን እንደማትረሳ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ተስፋ መቁረጥ ጥርሱን አግጥጦ የገፋህን ቅጽበት፣ ቀናት ሁሉ በማይገለጥ ሰንኮፍ ተጋርደው አልነጋ ሲሉ፤በአኬልዳማ ተደልድለው መራመጃ የነፈጉህ መንገዶች፤ አቅም ባጣም በሹክሹክታ ‹‹ያልፋሉ!›› ስልህ ከመጣህበት በላይ የምትደርስበትን ጸዳል ጉብታ በከሲታ ተስፋ ውስጥ. . .ተስፋ አድርጌ ነው፡፡ የዛሬ ዓመት በዚህ ሰዓት ደክሞህ ነበር፡፡ ዕጣ-ፋንታ ጨክኖብህ በሕይወትህ ረግጠህ የማታውቃቸው አዚማም ሥፍራዎች ላይ ቆመሃል፡፡ ፖሊስ ጣቢያ፣ ፍርድ ቤት፣ ወጌሻ ቤት፣ ሐኪም ቤት…ሰው ፊት ሌሎችም፡፡አፈር ልሰህ ወደ ሕልምህ እንዲያቀናህ ያበቀልከውን ፍሬ ሌባ ያለ ኀፍረት ወስዶብሃል፡፡ ድፍረትና ጭስን ተመስለህ በመርፌ ቀዳዳ እንደምትወጣ ፍርሃት በዋጠው ለሆሳስ ነግሬህ ነበር፣ አላሳፈርከኝም…ዛሬ እዚህ ደርሰሃል፡፡ የዛሬ ዓመት በዚህ ሰዓት ዓለም ተገልብጦብህ ነበር፡፡በደም፣ በሥጋ በመንፈስ የተዛመዱህ ጀርባቸውን እንጂ ፊት አልሠጡህም፡፡የኋላ ታሪክህንና የሚደርስልህ ነገህን ረስተው በቆምክበት ሥፍራ መዝነው አቅልለውሃል፡፡ ይጎትቱኛል ያልካቸው መዳፎች ገፍተው ወደ መቀመቅ እንድትወርድ በይነውብሃል፡፡ ፍርሃት ባደበዘዘው ለሆሳስ ነግሬህ ነበር…..‹‹ያልፋል!›› ብዬ፡፡ የዛሬ ዓመት በዚህ ሰዓት…..ደርሶብህ የማያውቀው የመተት ፍላጻ ተወርውሮ ቤትህ ገብቶ ገርበብ ያለ በርህን ዘግቶ፣ ክፍት መስኮትህን ደፍኖ ከሁሉ አራርቆህ፣ የጨበጥከውን ነጥቆ፣ የጎረስከውን አስተፍቶህ ብዙ ቀናትና ወራት ሳይነጉልህ…በድቅድቅ ውስጥ ማንም ሳያይህ ከራስህ ጋር ስትታገል፣ ባልተዘጋጀ ትከሻ ላይ ሲህር ሌላ ሸክም ኾኖ ሲያጎብጥህ፤ ከገጠመህ ይልቅ የሚመጣውን ተዓምር አስቤ ፍርሃት ባደበዘዘው ለሆሳስ ‹‹አይዞህ! ይኽም ያልፋል!›› ብዬህ ነበር፡፡(ይኸው! አለፍከው አይደል?) ‹‹ንገረኝ!›› ሲሉህ እንዴት እንደምትገልፀው ተቸግረህ፣ የምትወደውን ብዕር ጨለማ ውስጥ ጥለህ መናገር ከብዶህ….በዝምታ ከዝምታ ጋር ታግለሃል፡፡ የምትተነፍስበትን ብዕር እንጂ ፈገግታህን እና ጨዋታህን አልጣልክም፡፡ያንኳኳሃቸው በሮች ወቅታቸው ስላልደረሰ እንጂ መከፈታቸው እንደ ቂያማ የማይቀር ቀጠሮ መኾኑን ከሕመሞችህ ልቀው ባይሰ´ሙህም ነግሬህ ነበር፣አላመንከኝም ነበር፡፡ ዛሬ እዚህ ስለደረስክ እኮራብሃለሁ፡፡ ሦስት ነገር አትርሳ….ትንሽ ሻማ ይዘው ጨለማህ ድረስ መጥተው ብርሃናቸውን ያካፈሉህን፣ የተፈጠረው ሳይገባህ፣ የተናገርከው ሳይገባቸው ጆሮ የሠጡህን! ደግሞም ችለው ያልቻሉትን፣ መንገድ መጠቆም ሲችሉ መንገድህን የዘጉትን፣ ጥሩ ቃል እንኳ እንደ መስቀል ወፍ የራቃቸውን፡፡ ሦስተኛ. . .ማን እንደኾንክ አትርሳ፡፡ አሁን ያለህበት ብሩህ ቀን ሲያዘናጋህ ይኽን ጽሑፍ አንብብ፡፡ያለ መሣሪያ ጦርነት ውስጥ ገብተህ የወጣህ፣ ያለ ምሽግ ከፈንጂ ጋር የተጋፈጥክ፣ ራስህን አጥተህ ራስህን ያገኘህ ልበ-ብረት ነህ፡፡ እኮራብሃለሁ! . @huluezih

Открыть в Telegram
Просмотры12 600×13к среднему
Пересылки—
Реакции86
Комментарии—