Кабинет

Посты канала Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

сначала новые

#13029Фото
Просмотры5 110−67%к среднему
Пересылки—
Реакции37
Комментарии—
#13026Фото
Просмотры13 100−16%к среднему
Пересылки—
Реакции40
Комментарии—
#13025Фото
Просмотры13 500−13%к среднему
Пересылки—
Реакции37
Комментарии—
#13024Видео
Просмотры12 900−17%к среднему
Пересылки—
Реакции16
Комментарии—
#13023Текст

• የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለቆጣቢዎች ዕጣ ካወጣ አራት ዓመታት አልፈዋል • በኢትዮጵያ ቤተሰቦች እስከ 70 በመቶ ገቢያቸውን ለቤት ኪራይ እንደሚያወጡ ተገለጸ • 100 ቢሊዮን ብር ካፒታል ያለው የሞርጌጅ ባንክ ለማቋቋም ዝግጅት ተጀምሯል (ዘ-ሐበሻ ዜና) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጋራ መኖሪያ ቤቶች ልማት መርሐ ግብር ተመዝግበው ለሁለት አሥርት ዓመታት ገደማ ሲቆጥቡ የቆዩ ዜጎች፣ የቤት ዕጣ መውጣቱ ለረጅም ጊዜ መቋረጡን ተከትሎ ከፍተኛ ብስጭት ውስጥ መግባታቸውንና ተስፋ እየቆረጡ መሆናቸውን ገለጹ። እ.ኤ.አ. በ2005 በ20/80 መርሐ ግብር ሲመዘገብ የ25 ዓመት ወጣት የነበረው ስዩም፣ ዛሬ በ45 ዓመቱ ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባት ቢሆንም አሁንም በኪራይ ቤት እየተቸገረ መሆኑንና «በሕይወት ዘመኔ ቤት አገኛለሁ የሚል እምነት አጥቻለሁ» ሲል ለካፒታል ጋዜጣ ተናግሯል። በተመሳሳይ እ.ኤ.አ. በ2013 በ40/60 ተመዝግባ ሳዑዲ ዓረቢያ በመሥራት 800 ሺሕ ብር የቆጠበችው ዓይናለም፣ ገንዘቧ በባንክ ታስሮ እስካሁን ቤት ባለማግኘቷ በንግድ ሥራ ባላዋለችው ቁጭት እንደተሰማት ገልጻለች። ብስጭቱ እየበረታ መምጣቱን ተከትሎ በ20/80 እና 40/60 የተመዘገቡ ቆጣቢዎች የባንክ ደብተሮቻቸውን በማኅበራዊ ሚዲያ በማጋራት የቤት ዕጣ እንዲወጣ የሚጠይቅ ዘመቻ ጀምረዋል። የዘመቻው አስተባባሪዎች፣ ከተማ አስተዳደሩ ለአራት ዓመታት ያህል ይፋዊ ዕጣ እንዳላወጣና አዳዲስ የተገነቡ ቤቶችም በኮሪደርና በወንዝ ዳርቻ ልማት ለተነሱ ነዋሪዎች መሰጠታቸውን በቅሬታ አንስተዋል። አስተዳደሩ ለመጨረሻ ጊዜ ዕጣ ያወጣው እ.ኤ.አ. ኖቬምበር 15 ቀን 2022 በ14ኛው ዙር 25,733 ቤቶችን ሲያስተላልፍ ነበር። የአቡክለመሲስ ሪል ስቴት አማካሪ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚና ሲቪል መሐንዲስ ደሳለኝ ከበደ፣ በኢትዮጵያ ቤተሰቦች እስከ 70 በመቶ ገቢያቸውን ለቤት ኪራይ እንደሚያወጡ ገልጸው፣ ይህም 40 በመቶ ከሆነው የአለመቻል መለኪያ በእጅጉ የላቀ መሆኑን አስጠንቅቀዋል። በአዲስ አበባ ከ100 ሺሕ በላይ ቤቶች እየተገነቡ ቢሆንም አብዛኞቹ መካከለኛና ከፍተኛ ገቢ ያላቸውን ያነጣጠሩ መሆናቸውን የጠቀሱት ባለሙያው፣ የባንኮች ከ18 እስከ 25 በመቶ የሚደርስ የብድር ወለድና የ70/30 የመሬት አቅርቦት አሠራር የቤት ዋጋን ከአቅም በላይ እንዳደረጉት አመልክተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቅርቡ በአዲስ አበባ የቤት ልማት ግንባታዎችን ሲጎበኙ፣ መንግሥት በአምስት ዓመታት ውስጥ 1.5 ሚሊዮን ቤቶችን ለመገንባት የገባውን ቃል ለመፈጸም ቀን ከሌሊት እየሠራ መሆኑን ቢገልጹም፣ ለነባር ቆጣቢዎች ዕጣ መቼ እንደሚወጣ ግን በግልጽ አልጠቀሱም። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የቤት ፋይናንስ አቅርቦትን ለማስፋት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክና ዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) የ200 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍን ያካተተ ስምምነት በመፈራረም፣ 100 ቢሊዮን ብር ካፒታል ያለው የሞርጌጅ ባንክ ለማቋቋም ዝግጅት መጀመሩ ታውቋል።

Открыть в Telegram
Просмотры14 800−5%к среднему
Пересылки—
Реакции94
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
53 ч14 400
66 ч14 800
  1. Всего сейчас14 800
#13022Фото
Просмотры13 700−12%к среднему
Пересылки—
Реакции19
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
53 ч13 100
66 ч13 700
  1. Всего сейчас13 700
#13019Фото

የመምህራን የማህበር ቤቶች ግንባታን ለማፋጠን እየተሰራ ነው የመምህራን የማህበር ቤቶች ግንባታ የመስክ ምልከታ ትላንት ተካሄደ፡፡ በምልከታው የየካአባኦዶ ፤ የአራብሳ ሳይት አንድ ፤ የአራብሳ ሳይት አምስት እና የአራብሳ ሰፈራ ሳይት የግንባታ እንቅስቃሴ ማየት ተችሏል፡፡ በ7 ሳይት ከተደራጁት 68 የመምህራን የቤት ግንባታ ማህበራት ውስጥ አብዛኞቹ ወደ ስራ የገቡ ሲሆን  አማካሪው የአዲስ አበባ ዲዛይን እና ግንባታ ስራዎች ማማከር ድርጅት ነው ፡፡ ከተማ አስተዳደሩ በልዩ ትኩረት ወደ መምህራን የቤት ልማት ስራ መግባቱን እና ተግባሩም ታላቅ ሀገራዊ ኃላፊነት በመሆኑ በፍጥነትና በጥራት በተለወጠ የስራ ባህል ስራውን ከግብ ለማድረስ መስራት ይገባል ሲሉ ዶክተር ኢንጂነር መኮንን ጥበቡ የቢሮው ምክትል ቢሮ ኃላፊ በምልከታው ወቅት ተናግረዋል፡፡ ቢሮው ስራዎችን በበላይነት የሚቆጣጠር ፣ የሚከታተል እና የሚደገፍ ሲሆን  ቤቶቹ በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቁ የሚያስችል ሙያዊ አቅጣጫ ሰጥተዋል ፡፡ የከተማ አስተዳደሩ መምህራንን የቤት ባለቤት ለማድረግ ባመቻቸው መሰረት መምህራን በቤት ልማት ማህበር ተደራጅተው ወደ ቤት ግንባታ ስራ መግባታቸው ይታወቃል፡፡   በጉብኝቱ ዶክተር ኢንጅነር መኮንን ጥበቡ የቢሮው ምክትል ቢሮ ኃላፊን ጨምሮ የእዲስ አበባ ዲዛይን እና ግንባታ ስራዎች ማማከር ድርጅት ሙያተኞች እና ስራ ተቋራጮች ተገኝተዋል፡፡ የቤቶች ልማትና አስተዳደር

Открыть в Telegram
Просмотры17 300+11%к среднему
Пересылки—
Реакции71
Комментарии—
#13018Фото

በተሰረዙ ቦታዎች ላይ ለጨረታ ሰነድ ግዥ የተፈፀው ክፍያ በሌላ ፕሎት ለመወዳደር ያገለግላል፡፡ የጨረታ ኮሚቴ አስተባባሪ ህዳር12/2019 (መልአ) **** የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በ9ኛው ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ በተለያያ ምክንያት ከጨረታው በተሰረዙ ሶስት ቦታዎች ላይ ተጫራቾች ለጨረታ ሰነድ ግዥ የፈፀሙት ክፍያ፣ በሌላ ፕሎት ላይ ለመወዳደር መጠቀም እንደሚችሉ አስታወቋል። የቢሮው የጨረታ ኮሚቴ አስተባባሪ አቶ ክብሮም አሰፋ እንደገለጹት፤ በ9ኛው ዙር የሊዝ ጨረታ ለውድድር ቀርበው ከነበሩ ቦታዎች ሶስት ቦታዎች ከጨረታው ውጭ እንዲሆኑ ተደርጓል። በዚህም ምክንያት በእነዚህ ቦታዎች ላይ ለመወዳደር የጨረታ ሰነድ የገዙ ተጫራቾች ለጨረታ ሰነድ ግዥ ያወጡት ወጪ እንዳይባክን በዛው ሰነድ በለሌሎች ቦታዎች ላይ መወዳደር እንደሚችሉ ተናግረዋል ። የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የጨረታ ሂደቱን ግልጽና ቀልጣፋ ከማድረግ ባለፈ ተደራሽ ለማድረግ ከህዳር 14 /2019 ዓ/ም ጀምሮ ለ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ማራዘሙን ያሳታወሱት አቶ ክብሮም፣ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ የህብረተሰብ ክፍሎች ይህንኑ አውቀው እስከ ህዳር 18/2019 ከቀኑ 9፡00 ድረስ ብቻ ሰነዱን ገዝተው በመሙላት እንዲወዳሩ ጥሪ አቅርበዋል። በጨረታው የመጨረሻ ቀን ኦርጅናል ሲፒኦ ብቻ በፖስታ በማሸግ በፖስታው ላይ የሚወዳደሩበት ቦታ የጨረታ ቁጥርና የቦታ ኮድ በመፃፍ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡

Открыть в Telegram
Просмотры15 300−1%к среднему
Пересылки—
Реакции15
Комментарии—
#13017Текст

ኅዳር 11 2019 የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፍሊንትስቶንስ ኢንጂነሪንግ አፓርትመንቶች ተሽጠው ለ87 ባለመብቶች እንዲከፈል አዘዘ፡፡ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፍትሐ ብሔር ምድብ ችሎት፣ ፍሊንትስቶንስ ኢንጂነሪንግ አክሲዮን ማህበር ለ87 ባለመብቶች ያለበትን ዕዳ ለመክፈል፣ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 የሚገኙ ቤቶቹ በጨረታ ተሽጠው ገንዘቡ ለባለመብቶቹ እንዲከፈል ውሳኔ አስተላልፏል። ትዕዛዙን የተሰጠው ትናንት ህዳር 10 ቀን 2019 ዓ.ም በዋለው ችሎት ነው። ትዕዛዙ የተላለፈው የግልግል ዳኞች ሰኔ 1 ቀን 2016 ዓ.ም የሰጡትን ውሳኔ ለማስፈፀም ነው። ችሎቱ ውሳኔው በሚፈለገው መንገድ እንዲፈፀም አዟል። የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐምሌ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ባቀረበው ሪፖርት፣ ቤቶቹ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 በይዞታ ቁጥር 10/69/1/6/43191/00 ላይ በሚገነባ አፓርትመንት ውስጥ እንደሚገኙ አረጋግጧል። አፓርትመንቱ በኩባንያው ስም እንደተመዘገበ መረጋገጡንም በፍርድ ቤቱ ሰነድ ላይ ሰፍሯል። በዚህ መሠረት ችሎቱ ፣ ግንባታቸው 80 በመቶና ከዚያ በላይ የደረሱ ቤቶች ዕዳውን ለመሸፈን በቂ ከሆኑ እነሱ ብቻ እንዲሸጡ አዟል። በቂ ካልሆኑ ደግሞ ከዚያ በታች የግንባታ ደረጃ ላይ ያሉትም ዕዳውን ለመሸፈን በሚበቃ መጠን በጨረታ እንዲሸጡ ወስኗል። ከሽያጩ ለባለመብቶች የተወሰነው ገንዘብ ከተቀነሰ በኋላ የሚቀረው ካለ ለኩባንያው እንዲመለስ ተብሏል። ፍሊንትስቶንስ በሁለት አመት ከ6 ወር ቤቶችን አጠናቅቄ አስረክባለሁ ብሎ ከደንበኞቹ ጋር ውል ቢገባም በውሉ መሰረት ሰርቶ ቤቶቹን አለማስረከቡ ደንበኞቹ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት አንዲወስዱት አድርጓቸዋል፡፡ በዚህ መሰረት ከሳሾች በወቅቱ በነበረው የገበያ ዋጋ ማለትም በካሬ 99 ሺህ ብር ተሰልቶ ይሰጠን ሱሉም ለፍርድ ቤቱ አቤት ብለዋል። የግልግል ዳኝነቱ በወቅቱ ኩባንያው ውሉን አለማክበሩን አረጋግጧል። ነገር ግን ከሳሾች እንዲከፈላቸው ባመለከቱት ሳይሆን በካሬ 24 ሺህ ብር አስቦ እንዲሰጣቸው በፍሊንስቶንስ ኢንጅነሪንግ አ.ማ ላይ መፍረዱን ከፍርድ ቤቱ ውሳኔ ተመልክተናል። በውሳኔው ቅር የተሰኙት ከሳሾች ይግባኝ በማለት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቀርበው ጉዳዩን አስረድተዋል። ፍርድ ቤቱም ጉዳዩን መርምሮ የስር ፍርድ ቤቱን ውሳኔ እንዳፀናው መዘገባችን ይታወሳል። ከሶስት አመት በላይ በፈጀው ክርክር ህዳር 10/2019 ዓ/ም በዋለው ችሎት ቤቶቹ በሀራጅ ተሽጠው ለባለመብቶች እንዲከፈል ችሎቱ የአፈፃፀም ትዕዛዝ ሰጥቷል። ያልተፈፀመ ነገር ካለ መዝገቡ ለጊዜው ተዘግቶ ወደ መዝገብ ቤት እንዲመለስ ማለቱን ከፍርድ ቤቱ የትዕዛዝ ሰነድ ማየት ችለናል። ገዛ ጌታሁን

Открыть в Telegram
Просмотры18 300+18%к среднему
Пересылки—
Реакции53
Комментарии—
#13016Фото

በአዲስ አበባ የቁጠባና ብድር ማህበራት የብድር አሰጣጥ ላይ ክፍተቶች መኖራቸው ተገለጸ በአዲስ አበባ በሺህ የሚቆጠሩ የቁጠባና ብድር ማህበራት ቢኖሩም፣ ተቋማቱን ለመከታተልና ለመቆጣጠር የሚያስችል በቂ የሰው ኃይልና አደረጃጀት እንደሌለ ተገለጸ። የአዲስ አበባ ህብረት ስራ ኮሚሽን የልማት ፋይናንስ ዳይሬክተቶት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ተስፋዬ ይልማ እንደገለፁት በተለይም በብድር አሰጣጥና ስርጭት ላይ የአሰራር ክፍተቶች እንዳሉ ጠቁመዋል። እንደ አቶ ተስፋዬ እንዳነሱት ከ1 ሺህ በላይ የቁጠባ ማህበራትን በጥቂት ባለሙያዎች መቆጣጠር ፈተና ሆኗል። የአዲስ አበባ ህብረት ስራ ኮሚሽን እንዳስታወቀው፣ ባለፈው በጀት ዓመት በቁጠባ ማህበራት ብቻ 7.4 ቢሊዮን ብር ብድር ተሰራጭቷል። ይህን ትልቅ የገንዘብ እንቅስቃሴ በአግባቡ ለመምራት የማህበራቱን መዋቅር፣ አደረጃጀትና የቁጥጥር ስርዓት ማጠናከር እንደሚያስፈልግም ተጠቁሟል። በተጨማሪም የወለድ ምጣኔው አባላት ከሚችሉት ክፍያ በላይ መሆን የማህበራቱን ዘላቂነት ሊጎዳ እንደሚችል ተገልጿል።   ቁምነገር አየለ   ኀዳር 11 ቀን 2019 ዓ.ም

Открыть в Telegram
Просмотры16 600+7%к среднему
Пересылки—
Реакции24
Комментарии—
#13015Фото

9ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ለተጨማሪ 5 የስራ ቀናት ተራዘመ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ 9ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ የሰነድ ግዥ ለተጨማሪ 5 የስራ ቀናት ማራዘሙን ይፋ አደረጓል። በመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የጨረታ ኮሚቴ አስተባባሪ አቶ ክብሮም አሰፋ ፣ በዚህ ዙር ለተለያየ ልማት የተዘጋጁ 127 ቦታዎች ለጨረታ መቅረባቸውን አስታውሰው፣ ተጫራቾች ሰነዶቻቸውን አሟልተው ማቅረብ እንዲችሉና ሰፊ የመወዳደር እድል እንዲያገኙ ታስቦ ከህዳር 14 /2019 እስከ ህዳር 18/2019 ዓ.ም ለተጨማሪ 5 የስራ ቀናት የሰነድ ሽያጭ መራዘሙን ተናግረዋል ፡፡ በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ አልሚዎች የጨረታ ሰነዱን ከተቋሙ ድረገጽ https://addislandfarm.gov.et በተራዘሙት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ ቀኑ 9 ሰዓት ብቻ በመግዛት በዚህ ከእጅ ንክኪ መሉ ለሙሉ በተላቀቀው ጨረታ እንዲሳተፉ ጥሪ ያቀረቡት የጨረታ ኮሚቴ አስተባባሪው ከዚህ በታች የተገለጹ የቦታ ኮዶች ከጨረታ የተሰረዙ መሆናቸውን ተናግረዋል። 1ኛ የጨረታ ቁጥር ጉ/ክ/ከ/04/09 የቦታ ኮድ LPP-GU01000280 ክ/ከተማ ጉለሌ ወረዳ 01 2ኛ የጨረታ ቁጥር አ/ክ/ከ/01/09 የቦታ ኮድ LPP-AR05000272 ክ/ከተማ አራዳ ወረዳ 05 3ኛየጨረታ ቁጥር አ/ክ/ከ/02/09 የቦታ ኮድ LPP-AR06000277 ክ/ከተማ አራዳ ወረዳ 06 የሲፒኦ ማስረከቢያውም ህዳር 18/2019 ዓ.ም ለም ሆቴል አካባቢ በሚገኘው የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 የጨረታ ኮሚቴ አባላት ፣ የሚዲያ ተቋማትና የፀጥታ አካላት በተገኙበት እንደሚከናወንም ከኮሚቴው የተገኘ መረጃ ያሳያል፡፡

Открыть в Telegram
Просмотры17 500+13%к среднему
Пересылки—
Реакции32
Комментарии—
#13013Фото
Просмотры18 900+22%к среднему
Пересылки—
Реакции29
Комментарии—
#13010Текст
Просмотры24 400+57%к среднему
Пересылки—
Реакции50
Комментарии—