🎧*መባዘን አይደለም መዋል ከአንተ ጋራ* *ሰለ እላዩ ምክርህ ነፍሴ ስታዋራህ* ሰብሰብ ብሏል ቀኔ አልተዝረከረከም* *ማይወሰድ ዕድል ከዚህ በላይ የለም*🎧 ተስፋበኢየሱስ Channel 🔆 @HopeOfJesusChannel 🔆
Открыть в TelegramПосты канала ተስፋ በኢየሱስ Channel
. *የእግዚአብሔር ጥበቃ* *በልዑል መጠጊያ የሚኖር ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ሥር ያድራል። እግዚአብሔርን፣ መጠጊያዬ፣ ምሽጌ፣የምታመንብህ አምላኬ” እለዋለሁ።* *እርሱ ከአዳኝ ወጥመድ፣ ከአሰቃቂ ቸነፈር ያድንሃልና። በላባዎቹ ይጋርድሃል፤ በክንፎቹ ሥር መሸሸጊያ ታገኛለህ፤ ታማኝነቱ ጋሻና መከታ ይሆንሃል። የሌሊትን አስደንጋጭነት፣በቀን የሚወረወረውንም ፍላጻ አትፈራም፤ በጨለማ የሚያደባ ቸነፈር በቀትር ረፍራፊውም አያሠጋህም። በአጠገብህ ሺህ፣ በቀኝህም አሥር ሺህ ይወድቃል፤ ወደ አንተ ግን አይቀርብም።* *የክፉዎችንም መቀጣት ታያለህ እግዚአብሔርን መሸሸጊያ፣ ልዑልንም መጠጊያህ አድርገኸዋልና። በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ፣ መላእክቱን ስለ አንተ ያዛቸዋልና። እግርህ ከድንጋይ ጋር እንዳይጋጭ፣ በእጆቻቸው ወደ ላይ ያነሡሃል። በአንበሳና በእፉኝት ላይ ትጫማለህ፤ ደቦሉን አንበሳና ዘንዶውን ትረግጣለህ።* *“ወዶኛልና እታደገዋለሁ፤ ስሜን አውቆአልና እከልለዋለሁ። ይጠራኛል፤ እመልስለታለሁ፤ በመከራው ጊዜ ከእርሱ ጋር እሆናለሁ፤ አድነዋለሁ፤ አከብረዋለሁ። ረጅም ዕድሜን አጠግበዋለሁ፤ማዳኔንም አሳየዋለሁ።”* 📖መዝሙር 91÷1-16📖 ተስፋበኢየሱስ Channel 🔆 @HopeOfJesusChannel 🔆
Открыть в Telegram*እስከ ዛሬ ከአንተ ጋር ኖሬ* 🎧 *ተጉዣለሁ ብዙ አብሬ*🚶➡️... *አንዱ ሲሄድ አንዱ ሲመጣ*🏃♀➡️🧍🏃♂ * አትለወጥ አንተ ግን ጌታ*❤️ *ጠቆር አይል ፊትህ አይቀየር* 😠 *አትዘጋ የምህረትን በር* 🫸😧 *እረ ስንቱ ጭንቁን እረስቶ እፎይ ብሏል በአንተ ላይ ታምኖ*.....🧎🧎♀➡️😇 ተስፋበኢየሱስ Channel 🔆 @HopeOfJesusChannel 🔆
Открыть в Telegramበውስጣችን የሚኖረው መንፈስ ቅዱስ ከማንኛውም አካል በላይ የተሻለ ያውቀናል። ሕይወት በሚከብድበትና በሚያምበት ጊዜም በተጎዳንበትና በታመምንበት ስፍራ ሁሉ መጽናናትንና ፈውስን የማምጣት ኃይል አለው። *የርኅራኄ አባት፣ የመጽናናትም ሁሉ አምላክ የሆነው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ።* *እኛ ራሳችን ከእግዚአብሔር በተቀበልነው መጽናናት፣ በመከራ ያሉትን ማጽናናት እንድንችል፣ እርሱ በመከራችን ሁሉ ያጽናናናል።* 📖2ቆሮንቶስ 1÷3-4📖 ተስፋበኢየሱስ Channel 🔆 @HopeOfJesusChannel 🔆
Открыть в Telegram*አዕምሮ ፍቃድና ስሜት* *እንድያስተምረው የጌታን ልብ ማን አውቆት ነው እኛ ግን የክርስቶስ ልብ አለን፡፡* 📖 1 ቆሮ 2÷16📖 ኢየሱስን ወደ ልባችን እንዲመጣ ስንጋብዘው መንፈስ ቅዱስ በእኛ ውስጥ መኖሪያ ያደርጋል፡፡ ከዚያ የልባችን ዙፋን ውስጥ የሕይወታችን ማዕከል መንፈስ ቅዱስ ነፍሳችንን ማጥራት ይጀመራል፡፡ (አእምሮአችነን፣ ፈቃዳችንንና ስሜቶቻችንን)፡፡ አእምሮአችን ምን እንደምናስብ ይነግረናል ነገር ግን እግዚአብሔር የሚያስባውን አይደለም መንፈስ ቅዱስ በሕይወታችን የምሰራው ያንን ለመለወጥ ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ሀሳብ ጋር ተስማምተን ለማሰብ እንድንችል መማር አለብን እንዴት እግዚአብሔር ሃሣቡን የምፈፅምበት ዕቃ (መሣሪያ) መሆን እንችላለን? አሮጌ ሃሣቦች ከእኛ መጽዳት (መታደስ) አለባቸው አዳዲስ ሃሣቦች የእግዚአብሔር ሃሣቦች የእኛ የሃሣብ ክፍሎች መሆን አለባቸው፡፡ የእኛ ስሜት ምንና እንዴት እንደተሰማን ይነግሩናል፡፡ በመዝ 7÷9 "ልብንና ኵላሊትን የምትመረምር ጻድቅ አምላክ ሆይ የክፉዎችን ዐመፅ አጥፋ ጻድቁን ግን አጽና።" መሠረት እግዚአብሔር ስሜታችንን ይፈትናል ደግሞም ይመረምራ፡፡ እርሱ ከእኛ ጋር የምሰራው እኛ በሰውኛ ስሜት እስካልተነዳን ብቻና በመንፈሱ ስንሆን ነው፡፡ የእኛ ፍቃድ የእግዚአብሔርን ፍቃድ ሳይሆን እኛ የምንፈልገውን ይነግረናል ፈቃድ ስሜትን እንዲሁም ሃሳብን ይቆጣጠራል፡፡ ትክክለኛውን ነገር ልንሰራበት እንጠቀምበታለን፡፡ ነፃ ፈቃድ አለን እግዚአብሔርም ደግሞ ምንም ነገር እንድናደርግ አያስገድደንም እራሱ ለእኛ መልካም መሆኑን ወደሚያውቅ ነገር በመንፈሱ ይመራናል፡፡ ነገር ግን የመጨረሻው ውሳኔ ለማድረግ የእኛ ፈንታ ነው፡፡ ይህ ደግሞ አዕምሯችን በእግዚአብሔር ቃል ከተሞላ የምንወስነውን የታወቀ ነው ነፃ ፍቃዳችንን ተጠቅመን እግዚአብሔር ሁልጊዜ በቋሚነት ከእኛ ጋር በስምምነት ላይ የተመሠረተ የእርሱ ፈቃድ እንዲሆን ይፈልጋል የእኛ ፈቃድን ብቻውን አይደለም፡፡ እነዚህ ሦስቱ የሕይወታችን ክፍሎች፡- አእምሮ፣ ፈቃድና ስሜት ከኢየሱስ ክርስቶስ አመራር ሥራና ከመንፈስ ቅዱስ ሥር እየገቡ ሲመጡ እንደ አማኝ በመንፈሳዊ ብስለታችን እያደግን እንመጣለን፡፡ እንዲሁም በየጊዜው እየተለዋወጠ አየተሰማን እንዳለው ስሜታች ሳይሆን እንደ እግዚአብሔር ቃል ለመኖር እና ነገሮች ለማድረግ ሀይል እያገኘን እንመጣለን (ከሙዳችን በላይ እንሆናለን) *የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡- ስሜቶችህን አንተው በመቆጣጠር መግዛት ትችላለህ፡፡* ተስፋበኢየሱስ Channel 🔆 @HopeOfJesusChannel 🔆
Открыть в Telegram*ጌታ ኢየሱስ በቂ ነው ለሰማዩም ለምድሩም ኢየሱስ በቂ ነው* ••••••••••••••••••••••••••••••••• ነገር ግን ክርስቶስ ሁሉም ነው፤ በሁሉም ነው። ••••••••••••••••••••••••••••••••• 📖ቆላስይስ 3:11📖 ተስፋበኢየሱስ Channel 🔆 @HopeOfJesusChannel 🔆
Открыть в Telegram🎧*አንተ ማጣት ነው ብቸኝነት መፀለይ🧎 ማቆም ነው ድርቀት* *መንፈስህን መተው ነው ክስረት ዉሎ ማደር አንተ በሌለህበት*🧎♀🎧 *ቃልህን📖 መርሳት ነው ጎዶሎነት ሳይሰሙ መውጣት መውጣት ነው ዙረት*🎧 *ያለ ድምፅህ ማውራት ነው ቅዠት ዉሎ ማደር አንተ በሌለህበት**📖 መኖር አልችልም ያላንተ ያላንተ እፈራለሁ ሁሉም ጭልምልም ያለ ነው ተስፋበኢየሱስ Channel 🔆 @HopeOfJesusChannel 🔆
Открыть в Telegramበእሳት መጥራት በቀንና በሌሊትም ይሄዱ ዘንድ መንገድ ሊያሳያቸው ቀን በደመና አምድ ሊያበራላቸውም ሌሊት በእሳት ዓምድ እግዚአብሔር በፊታቸው ሄደ፡፡ 📖ዘፀአት 13÷21📖 መጽሐፍ ቅዱስ ስለተለያዩ የእግዚአብሔር እሳት እንዴት በተለያዩ የሕይወት ጉዳዮቻችን እንደሚሠራ በተለያዩ የመጽሐፍ ክፍሎች ይዘረዝራል፡፡ የተሻለውን የእግዚአብሔርን ነገር ብንፈልግ የእግዚአብሔርን በእሳት የማጥራት ሕይወት ለመኖር ፈቃደኛ መሆን አለብን፡፡ በውስጣችን ወርቅ (ጥሩ የሆነ ነገር) በውስጥ ሕይወታችን አለን፡፡ ነገር ግን ያልተጣሩና ሊወገዱ የሚገቡ ነገሮችም አብሮ አሉን፡፡ እያንዳንዱ ሰው በእግዚአብሔር መልካምነት መደሰት ይፈልጋል፡፡ ነገር ግን ጥቂቶች ብቻ በእሳቱ በተከታታይ ለመሠራት ጉጉት አለው፡፡ የእግዚአብሔር እሳት በሕይወትህ ሲመጣ ለውጥን የሚያመጣ ነበልባል እንደሆነ ሁልጊዜ አስታውስ እሳቱ ከሕይወታችን ሙሉ በሙሉ እንዲወጣ አያደርግም፡፡ እንዲሁም ደግሞ እሳቱ እንዲያጠፋንም አያደርግም እርሱ ከምንችለው በላይ እሳቱ እንዲያይልብንም አያደርግም፡፡ በሕይወታችን ሁሌ አንዳንድ ጊዜ አስቸጋሪ የሚመስሉና ሌላ ጊዜ ደግሞ ቀላል የሚመስሉ ገጠመኞች ይፈራረቁብናል፡፡ ጳውሎስ ይህንን ጊዜያት ሲገልጽ በሁሉም እራሱን ለማስለመድና ከሁለቱ በአንዱ ለመደሰት የምችልበት እንደተማረ ይናገራል፡፡ የእግዚአብሔር ጥበብ ፍጹም እንደሆነና ሁሉን ነገር ለመልካም እንደሚሆን ተምሮአል፡፡ እኛም ልክ እንደ እርሱ ምርጫችንን ማድረግ እንችላለን፡፡ የእግዚአብሔርን እሳት መቋቋማችን በእኛ ሕይወት እንዳይነድ ከማድረግ መከልከል አንችልም፡፡ እሳቱ እንዲጠፋ ከመቃወም ይልቅ እሳቱ ከእግዚአብሔር እንደሆነ ከተረዳን በሕይወታችን አይሎ ስራውን ሰርቶ እንዲያልፍ ወይም ያንን ጊዜ መቋቋም እንድትችሉ እግዚአብሔር ፀጋ እንዲሰጣችሁ መፀለይ ብቻ ነው፡፡ የእግዚአብሔር እሳት የሚመጣው ጥቅም የሌለውን ነገር ከሕይወታችን ለማቃጠልና ለእኛ መልካም መስሎ የታየን ነገር ግን እግዚአብሔር ያልወደደብንን ነገር ከእኛ ለማስወገድ ነው እንዲሁም እርሱን አልታዘዝ ስንለው ከፈጠረን አላማ ውጪ ለመኖር ስንሞክር እኛን በዚያ መንገድ ወደ ፈጠረን አላማ ለመምራት ይጠቀምበታል። በዚያ ጊዜ ቃሉ ላይ ቆዩ መልስ አገኛለሁ ብላችሁ ሌሎች አማራጮች ፍለጋ አትዙሩ እሳቱ ከእግዚአብሔር ስለሆነ ከእግዚአብሔር ቃል ውጪ ሚፈውሳችሁና መልስ የሚሰጣችሁ የለም። የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡- በምታልፍባቸው ነገሮች ውስጥ ከነገሮቹ መሸሽ የለብህም ልትፈራቸውም አይገባህም፡፡ ተስፋበኢየሱስ Channel 🔆 @HopeOfJesusChannel 🔆
Открыть в Telegram🎧ዝም ስትል ጊዜ ስታጠፋ ድምጽህን ያሰብኩት በመሉ እንዳልነበር ሲሆን ቀኑ ሲጨላልም ፈርቼ ሁኔታውን መልዕክት ልኬ ነበር ትመጣ ይሆን የሚል🎧 ጠብቅሀለሁ ጌታ ባስቀመጥከኝ ቦታ በመጠበቂያዬ ላይ ዳግም እስክትመጣ🙌 ድምፅህን አሰማኝ ልቤ እንዲፀናና ግን አንተ ዝም ካልከኝ እፈራለሁና...🥺🧎♂ ተስፋበኢየሱስ Channel 🔆 @HopeOfJesusChannel 🔆
Открыть в Telegram“ሥጋ ለባሽ ሁሉ እንደ ሣር ነው ክብሩም ሁሉ እንደ ሜዳ አበባ ነው። ሣሩ ይጠወልጋል፤ አበባውም ይረግፋል የጌታ ቃል ግን ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።” 📖 1ኛ ጴጥሮስ 1÷24-25📖 ተስፋበኢየሱስ Channel 🔆 @HopeOfJesusChannel 🔆
Открыть в Telegram*በዮሐንስ 6:63 ላይ ኢየሱስ የተናገራቸው ቃላት መንፈስና ሕይወት እንደሆኑ ይናገራል። መጽሐፍ ቅዱስን ስናነብና ስናጠና እግዚአብሔር ማንነታችንን በ እውነት ይለውጣል እሱን የመሰል ፍላጎትና ችሎታንም ይሰጠናል። በአጭሩ የእግዚአብሔር ቃል እውነት ነው፤ ነጻ የሚያወጣንም እውነት ነው!* *መንፈስ ሕይወትን ይሰጣል፤ ሥጋ ግን ምንም አይጠቅምም። እኔ የነገርኋችሁ ቃል መንፈስም ሕይወትም ነው* 📖 ዮሐንስ ወንጌል 6÷63📖 ተስፋበኢየሱስ Channel 🔆 @HopeOfJesusChannel 🔆
Открыть в Telegramጌታን ለማገልገል በመንፈስ የጋላችሁ ሁኑ እንጂ ከዚህ ትጋት ወደ ኋላ አትበሉ። በተስፋ ደስተኞች ሁኑ፤ በመከራ ታገሡ፤ በጸሎት ጽኑ። 📖ሮሜ 12÷11-12📖 ተስፋበኢየሱስ Channel 🔆 @HopeOfJesusChannel 🔆
Открыть в Telegram🎧በፊትህ እስክጥለው የእኔ ነበር በትሩ ፍቃዴን ማድረግያ ያልታየኝ አቅሙ... 🎧ከምርኩዜ ማያልፍ ማይዘልቅ ከማገቻ በእጄ የከረመ ድጋፍ መወጣጫ...🎧 ያን ዕለት ገብቶኛል ትኩረቴን ስትስበው በሚነድ ቁጥቋጦ እግሬን ስታፈጥነው.. 🎧የሰጠኸኝን መልሼ ብጥል ከእግሮችህ ስራ እንደምትሰራብኝ በአንተ እጅ እንዲያምር አውቄያለሁ.... *እንካ ጊዜዬን ተጠቀምበት በልብህ እንዳለ አከናውንበት እንካ ያለኝን ወርቅና ብር እኔ ጋራ ሆኖ ጓዳ እንዳይቀር*🙌 ተስፋበኢየሱስ Channel 🔆 @HopeOfJesusChannel 🔆
Открыть в Telegram🎧አልደግ አንተ ላይ እራሴን አልቻል አጓግል ነው ሁሉም ያላንተ መች ያምራል መጠበቅያ አጥሬ መሰንበቻዬ ነህ ልኑር እንደፈዘዝኩ አይኔ አንተ እያለ 🎧 ጉዳዬ አንተ መናፈቄ መምጣትህ ጉጉቴ አይኔ እስከሚያይህ *ሁሌ ሁሌ ሁሌ ሁሌ...አንተን ብቻ እስከ እድሜዬ መቋጫ..🙌* ተስፋበኢየሱስ Channel 🔆 @HopeOfJesusChannel 🔆
Открыть в Telegram*የእግዚአብሔር የማንጠሪያ እሳት ለእድገታችሁ እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ ታውቃላችሁ? ስለዚህ አስቸጋሪ የሕይወት ምዕራፎችን ወይም ፈተናዎችን አትጠሉዋቸው ምክንያቱም እግዚአብሔር እነዚህን ጊዜያት ለ አዲስ ነገር እናንተን ለማሳደግ ይጠቀምባቸዋል።* *ወንድሞቼ ሆይ፤ ልዩ ልዩ መከራ ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት* *ምክንያቱም የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንደሚያስገኝ ታውቃላችሁ ምንም የማይጐድላችሁ ፍጹማንና ምሉኣን እንድትሆኑ ትዕግሥት ሥራውን ይፈጽም።* 📖 ያዕቆብ 1÷2-4📖 ተስፋበኢየሱስ Channel 🔆 @HopeOfJesusChannel 🔆
Открыть в Telegram*በእግዚአብሔር ስትተማመኑ ምንም እንኳን የምትፈልጉትን ነገር ባይሰጣችሁም ከምትፈልጉት የተሻለ ነገርን ይሰጣችኋል።* * ሁልጊዜ ትክክል የሆነን ነገር ለማድረግ ያ ነገር እናንተ የምትወዱት ነገር ብቻ መሆን የለበትም። ትክክል ስለሆነና እግዚአብሔርን ስለምትወዱት ብቻ አድርጉት።* ተስፋበኢየሱስ Channel 🔆 @HopeOfJesusChannel 🔆
Открыть в Telegramአትታበይ.... *ይህን ያህል በመታበይ አትናገሩ እንዲህ ያለውም የእብሪት ቃል ከአፋችሁ አይውጣ እግዚአብሔር አምላክ ዐዋቂ ነውና ሥራም ሁሉ በእርሱ ይመዘናል።* *የኀያላን ቀስቶች ተሰባብረዋል ደካሞች ግን በኀይል ታጥቀዋል። ጠግበው የነበሩ ለእንጀራ ሲሉ ተገዙ ተርበው የነበሩ ግን እንጀራ ጠገቡ መካኒቱ ሰባት ልጆች ወልዳለች ብዙ ወንዶች ልጆች ወልዳ የነበረችው ግን መከነች።* *እግዚአብሔር ይገድላል ያድናልም ወደ መቃብር ያወርዳል ያወጣልም። እግዚአብሔር ያደኸያል ያበለጽጋልም* * ያዋርዳል ከፍ ከፍም ያደርጋል እርሱ ድኻውን ከትቢያ ያነሣል ምስኪኑንም ከጒድፍ ከፍ ከፍ ያደርጋል ከመኳንንቱ ጋር ያስቀምጣቸዋል የክብር ዙፋንም ያወርሳቸዋል።* *የምድር መሠረቶች የእግዚአብሔር ናቸውና ዓለምን በእነርሱ ላይ አድርጎአል እርሱ የቅዱሳኑን እግር ይጠብቃል ክፉዎች ግን በጨለማ ውስጥ ይጣላሉ* *ሰው በኀይሉ ድል አያደርግም፤ ከእግዚአብሔር ጋር የሚጣሉ ይደቃሉ እርሱ ከሰማይ ያንጐደጒድባቸዋል እግዚአብሔር እስከ ምድር ዳርቻ ይፈርዳል።* 📖 1ኛ ሳሙኤል 2÷3-10📖 ተስፋበኢየሱስ Channel 🔆 @HopeOfJesusChannel 🔆
Открыть в Telegram🎧አንተን ችላ ያሉ ፀጋ ሲርቃቸው አይቻለሁ ጌታ ቀን ሲመሽባቸው እስከ አሁን ያለፍኩት ሸለቆ ተራራ ምን ይውጠኝ ነበር ባልሆን ከአንተ ጋራ 🎧 *እንዳልበድልህ ጠብቀኝ* 🙌 *እንዳላሳዝንህ ጠበቀኝ *🧎♀ *እኔ ከአንተ ሌላ ማንም የለኝም*🧎 ተስፋበኢየሱስ Channel 🔆 @HopeOfJesusChannel 🔆
Открыть в Telegram*ሰዎች ለገዦችና ለባለ ሥልጣናት እንዲገዙ፣ እንዲታዘዙና መልካም የሆነውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ እንዲሆኑ አሳስባቸው።* *እንዲሁም በማንም ላይ ክፉ እንዳይናገሩ፣ ሰላማውያን እንዲሆኑ፣ ለሰዎችም ሁሉ ከልብ የመነጨ ትሕትና እንዲያሳዩ አስገንዝባቸው።* *ቀደም ሲል እኛ ራሳችን ማስተዋል የጐደለን፣ የማንታዘዝ፣ የተታለልን፣ ለተለያየ ምኞትና ምቾት ባሪያ ሆነን የተገዛን ነበርን፤ እየተጣላንና እርስ በርስ እየተጠላላን በክፋትና በምቀኝነት እንኖር ነበር።* *ነገር ግን የአዳኛችን የእግዚአብሔር ቸርነትና ፍቅር በተገለጠ ጊዜ፣ስላደረግነው የጽድቅ ሥራ ሳይሆን፣ ከምሕረቱ የተነሣ አዳነን።* 📖 ቲቶ 3÷1-5📖 ተስፋበኢየሱስ Channel 🔆 @HopeOfJesusChannel 🔆
Открыть в Telegram