Кабинет

Посты канала Hakim

сначала новые

#45239Фото

አንዳንዴ በሙያ አከባቢ የምንቸገርባቸውን ማህበረሰቡ ያውቅ ዘንድ በዚህ እናጋራ አንድ የ30አመት ወጣት ጋራዥ አከባቢ ሲሰራ እጁ ላይ ተቆርጦ ደ**ም እየፈሰሰው በ10 ደቂቃ ውስጥ ሆስፒታል ደረሰ። ወዲያውኑ እንደደረሰም ድንገተኛ ክፍል ያሉ ባለሙያዎች የመጀመሪያ እርዳታ አደረጉለት። ደሙ ሊቆም ስላልቻለ የሚመለከተው የቀዶ ህክምና ባለሙያ ተጠራ። የቀዶ ህክምና ባለሙያውም በፍጥነት ኦፕሬሽን ክፍል ገብቶ የሚደማው መሥተካከል አለበት ብሎ ወሰነ። ወጣቱም የኦፕራሲዮኑ ጥቅምና ጉዳት ተነግሮት ለኦፕራሲዮኑ መፍቀዱን ፈርም ተባላ። እሱ ግን "ባለቤቴና ወንድሜ ሳይመጡ አልፈርምም" አለ። የቀዶ ህክምና ባለሙያውም በቆዬ ቁጥር የወጣቱ ህይወት አደጋ ውስጥ መውደቁ አሳሰበው። በዚህ ደግሞ ያለ ፍቃዱ ምንም ማድረግ አይችልም። እናንተ ብትሆኑ ምን ታደርጋላችሁ? በእውኑ ማህበረሰቡ በእንደዚህ መሠል ጉዳዮች ያለው እይታ ምን ይመስላል? የወጣቱ ህይወት ሆስፒታል ውስጥ በዚህ ሁኔታ ቢያልፍ ተጠያቂው ማነው? ዶ/ር መዝገቡ ቦጋለ: የቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት @HakimEthio

Открыть в Telegram
Просмотры2 580−42%к среднему
Пересылки—
Реакции26
Комментарии—
#45235Фото

የሽንት ፊኛ ጤናን እንዴት እንጠብቅ? ፊኛ ከኩላሊታችን የሚመጣውን ሽንት በጊዜያዊነት የሚያከማችና በምቹ ጊዜ ከሰውነታችን እንዲወጣ የሚያግዝ አስፈላጊ የሰውነታችን አካል ነው። የፊኛችን ጤና ሲታወክ በሥራችን ፣ በእንቅልፋችን ፣ በማኅበራዊ ኑሯችንና በሕይወታችን ጥራት ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ከባድ ነው። ታዲያ ፊኛችንን ጤናማ ለማድረግ ምን ማድረግ አለብን? አንደኛ፦ በቂ ውሃ መጠጣት። በቀን በአማካይ 1.5–2 ሊትር ፈሳሽ መጠጣት ለብዙ ጤናማ አዋቂዎች ጥሩ መነሻ ነው። ነገር ግን የአየር ሁኔታ፣ የአካል እንቅስቃሴና የጤና ሁኔታ የሚያስፈልገንን ውሃ መጠን ይቀይራሉ። ውሃን በቀን ውስጥ በተከፋፈለ መንገድ ይጠጡ፤ ሽንት እንዳይመጣ ብለው ውሃ አይቀንሱ። ሁለተኛ፦ ትክክለኛ የሽንት መሽናት ልምድ ማዳበር። በቀን በአማካይ በየ3–4 ሰዓቱ መሽናት ይልመዱ። ሽንትን ለረጅም ጊዜ መያዝም ሆነ ያለ ምክንያት ቶሎ ቶሎ ሽንት ቤት መሄድ አይመከርም። ሽንት ሲሸኑም ሳይጣደፉ ዘና ብለው ፊኛዎ እንዲወጣ ያድርጉ። ሶስተኛ፦ የምንመገበውንና የምንጠጣውን መቆጣጠር። ቡና፣ ሻይ፣ ኢነርጂ ድሪንክና አልኮል የሽንት ፍጥነትንና የፊኛ መቆጣጠር ችግርን ሊያባብሱ ይችላሉ። በተለይ ችግሩ ካለብዎ መጠናቸውን ይቀንሱ። አራተኛ፦ የሆድ ድርቀትን መከላከል። አትክልት፣ ፍራፍሬ፣ ባቄላና ሌሎች ፋይበር ያላቸውን ምግቦች ይመገቡ። የሆድ ድርቀት በፊኛና በዳሌ ወለል ጡንቻዎች ላይ ጫና ሊፈጥር ይችላል። አምስተኛ፦ የዳሌ ወለል ጡንቻዎችን ማጠናከር። እነዚህ ጡንቻዎች ፊኛን፣ ማህፀንንና አንጀትን ይደግፋሉ። በትክክል የሚደረጉ የኬግል ልምምዶች የሽንት መፍሰስን ለመከላከልና ለማከም ይረዳሉ። ስድስተኛ፦ ሲጋራ ማጨስን ማቆም። ሲጋራ ማጨስ ለፊኛ ካንሰር ከፍተኛ የአደጋ ምክንያት ነው። ስለዚህ ማጨስን ሙሉ በሙሉ ማቆም አስፈላጊ ነው። ሰባተኛ፦ የአደጋ ምልክቶችን ማወቅ። በሽንት ውስጥ ደም ማየት፣ ሽንት ሲሸኑ ቃጠሎና ህመም መሰማት፣ ቶሎ ቶሎ ሽንት መምጣት፣ የሽንት መፍሰስና ሽንት መውጣት አለመቻል ችላ ሊባሉ አይገባም። በተለይ ሽንት ፈጽሞ መውጣት ካልቻሉ፣ ወይም ትኩሳትና የወገብ ህመም አብረው ካሉ አስቸኳይ ህክምና ይፈልጉ። በሽንት ውስጥ ደም ካዩም ሳይዘገዩ ምርመራ ያድርጉ። ውድ ወገኖቼ፣ የሽንት መፍሰስ፣ ቶሎ ቶሎ ሽንት መምጣትና ሽንትን መቆጣጠር አለመቻል የእድሜ ወይም የወሊድ የተፈጥሮ ውጤት ብቻ አይደሉም። ብዙዎቹ ችግሮች በትክክለኛ ምርመራና ህክምና የሚስተካከሉ ናቸው። የሽንት ፊኛዎን ጤና ይጠብቁ ፤ ችግር ካለ ግን ወደ ህክምና ይሂዱ:: References 1. International Urogynecological Association (IUGA). Bladder Health Awareness Month: Bladder Health. IUGA Patient Information Series; 2022. 2. American Urological Association (AUA), Society of Urodynamics, Female Pelvic Medicine and Urogenital Reconstruction (SUFU). The AUA/SUFU guideline on the diagnosis and treatment of idiopathic overactive bladder. 2024. 3. European Association of Urology (EAU). EAU Guidelines on Non-neurogenic Female Lower Urinary Tract Symptoms. 2025. ዶ/ር ፍኖት የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት የሴቶች ሽንት ፊኛና ዳሌወለል ቀዶህክምና ሰብ ስፔሻሊስት ለበለጠ መረጃ 0934601360 @HakimEthio

Открыть в Telegram
Просмотры3 340−25%к среднему
Пересылки—
Реакции28
Комментарии—
#45234Фото

The Hidden Cost of Cheap Healthcare in Ethiopia: Who Really Pays the Price? Affordable healthcare is essential. No one should be denied medical attention because of their financial circumstances. Ethiopia's efforts to provide subsidized and free healthcare deserve recognition. However, I believe we need to ask an important question: Can we sustainably deliver quality healthcare when the amount patients contribute is far below the actual cost of providing the service? Healthcare is not free to provide. Hospitals need qualified professionals, adequate staff compensation, essential medicines, laboratory reagents, diagnostic equipment and functioning infrastructure. All require sustainable financing. When patient contributions are minimal and government funding cannot adequately fill the gap, the consequences become visible: long waiting times, medicine shortages, limited investigations, overcrowded hospitals and increasingly dissatisfied healthcare professionals. But perhaps the most concerning consequence is what happens next. Patients are gradually pushed from underfunded public hospitals into the private healthcare sector. A patient who initially seeks affordable treatment in a government hospital may end up paying several times more in a private facility simply because medicines, investigations or timely services are unavailable in the public system. This creates an unfortunate paradox: healthcare that appears cheap at the public hospital entrance may eventually become extremely expensive for the patient. Moreover, when patients have limited alternatives, they become vulnerable to excessive charges, unnecessary investigations and other forms of financial exploitation in some parts of the private sector. I believe we need to rethink healthcare financing in Ethiopia. Rather than focusing exclusively on making healthcare cheaper, we should focus on making it financially sustainable while protecting access for the poor and vulnerable. Those who can afford it could contribute a reasonable amount toward the actual cost of services, supported by stronger health insurance mechanisms, transparent pricing and appropriate exemptions for disadvantaged populations. Government should remain a major financier and guarantor of equitable access, but it cannot indefinitely carry the entire financial burden of an expanding health system. Sometimes, making healthcare artificially cheap does not eliminate the cost. It simply transfers that cost to patients in a much more expensive way. Dr. Mengisteab Kassahun Assistant Professor of Internal Medicine Salale University @HakimEthio

Открыть в Telegram
Просмотры3 670−17%к среднему
Пересылки—
Реакции17
Комментарии—
#45233Фото

"ዶክትር መድሀኒት አታዝልኝም?" ይህ ቃል በጣም የተለመደ ነው። ኧረ እኛ ሀኪሞችን ልባችንን ቀጥ ከሚያደርጉት የታካሚ ንግግር አንዱ ነው። በተለይ ሳል፣ የላይኛው መተንፈሻ፣ የጉሮሮ ህመም፣ ተቅማጥ ህመም የገጠሟቸው ሰዎች ይችን ቃል ያዘወትሯታል። ይህ ዝም ብሎ የመጣ አይደለም። በራሱ ለሚጠፋ የቫይራል ህመም ጸረ ባክቴሪያ መድሀኒት (antibiotic) ይሰራል ከሚል እሳቤ ነው። ዳሩ ግን ዛሬ ላይ ትክክለኛ የባክቴሪያ ህመም ሳይኖር የታዘዘ መድሀኒት ነገ የቁርጥ ቀን ሲመጣ በቀላል አሞክሳሲልን መዳን የነበረብህን ህመም እንዳይሻልህ ያደርጋል። ወዳጀ፣ ሰውነትህ ብቻውን አይደለም። አብረዉት ብዙ ቢሊዩን ባክቴሪያዎች በአፍህ፣ በአፍንጫህ፣ በቆዳህ፣ በውስጠ አንጀት ክፍል፣ ኧረ እንዲያውም በሳንባህ ውስጥ ይኖራሉ። ....አንዳንዶችም ሌላ ባዕድ ባክቴሪያ ሲገባ ይደመስሱታል። አንተ ግን ህመምህ ሳይረጋገጥ በራስህም ሆነ በሀኪምህ "አለመንጠቅቅ" የወሰድከው ጸረ ባክቴሪያ መድሀኒት እነዚህ በሰላም ግዜ አትንካኝ አልነካህም ብለው የነበሩ ባክቴሪያዎች መድሀኒቱን እንዴት መሸወድ እንዳለባቸው ይማራሉ። ያኔ በአንድም በሌላ ምክንያት እነዚህ ባክቴሪያዎች ወደ ደምህ ስር ሲገቡ ጸባያቸው ይለወጣል። ሰውነትህንም ያጠቃሉ። በቀላሉ ባሉ መድሀኒቶች ለማከም ያስቸግራሉ። ሲከፋም እስከ ሞትም ያደርሳሉ። የሚያሳዝነው ግን እነዚህ ችግር ያስተማራቸው ባክቴሪያዎች አንተ ላይ ብቻ አያበቁም። በማህበረሰቡ ይስፋፋሉ። በአሁኑ ግዜ ብቻ በአለም ላይ ከ6 ኢንፌክሽን ከያዘቸው ሰዎች ውስጥ አንዱ መድሀኒት የተላመደ ባክቴሪያ ነው። በየአመቱ እስከ 4.7 ሚሊየን ሚደርሱትም ህይወታቸው ያልፋል። ችግሩን አስከፊ የሚያደርገው ደግሞ የጤና ባለሙያ ለዚህ አስተዋጾ ማድረጉ ነው። በተለይ የግል ህክምናው። አሁን አሁንም "ceftriaxone" ለ3 ቀን ሳይታዘዝለት የሚሸኝ ታካሚ ማግኘት አስቸጋሪ ሆኖል... ታካሚውም መርፌ አዘዝሎኝ ይላል... ኧረ መርፌ ጥሩ ነው ይላል። ያ ጠይቂ ጎረቤቱ... እውነታው ግን ይህ የባክቴሪያ በሽታ ሳይኖር የታዘዘው መድሀኒት የነገ ሆስፒታል ገብተህ ድህነህ የመውጣት እድልህን እያጠበበው ነው። ዶ/ር አብርሃም ተስፋሁን: የውስጥ ደዌ ሬዝዳንት @HakimEthio

Открыть в Telegram
Просмотры4 4500%к среднему
Пересылки—
Реакции54
Комментарии—
#45232Фото

የሀዘን መግለጫ በደቡብ ወሎ ዞን ጤና መምሪያ መቅደላ ወረዳ የመቅደላ ሆስፒታል የተቀናጀ የድንገተኛ ቀዶ ህክምና ባለሞያ (IESO) የነበሩት አቶ አንዷለም አዛናው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። አቶ አንዷለም አዛናው አቤ ሚያዝያ 1974 ዓ.ም ከአባታቸው አቶ አዛናው አቤና ከእናታቸው ወ/ሮ አስካበች አራጋው በደቡብ ወሎ ዞን፣ ቦረና ወረዳ፣ መካነ ሰላም ከተማ፣ በቆርኪ ሚካኤል 08 ቀበሌ የተወለዱ ሲሆን በሕይወታቸው የትምህርትንና የሙያን አስፈላጊነት በመገንዘብ በትጋት ተምረው የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከወሎ ዩኒቨርሲቲ፣ የሁለተኛ ዲግሪያቸውን (Master's Degree) ደግሞ ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አግኝተዋል። ትዳር መሥርተው ከባለቤታቸው ወ/ሮ ወሰን አባቡ ጋር ሦስት ወንድ ልጆችን አፍርተዋል። በሙያ አገልግሎታቸው ወቅት በተለያዩ የጤና ተቋማት በተለያዩ ኃላፊነቶች አገልግለዋል። ከእነዚህም፦ • በማሻ ጤና ጣቢያ በባለሙያነትና በኃላፊነት አገልግለዋል። • በሰሜን ሸዋ ዞን ሞላሌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በባለሙያነት ሠርተዋል። • በአቅስታ ጠቅላላ ሆስፒታል በድንገተኛና በተቀናጀ የቀዶ ሕክምና ባለሙያነት አገልግለዋል። • ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ በመቅደላ ወረዳ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በተቀናጀ የድንገተኛ ቀዶ ጥገና ባለሙያነት አገልግለዋል። በአቶ አንዷለም አዛናው ህልፈተ ህይወት የተሰማንን ሀዘን እየገለፅን ለቤተሰቦቹ እና ለሞያ አጋሮቹ መፅናናትን እንመኛለን። Source: ደቡብ ወሎ ዞን ጤና መምሪያ @HakimEthio

Открыть в Telegram
Просмотры5 060+14%к среднему
Пересылки—
Реакции24
Комментарии—
#45231Фото

To: Oromia Regional Health Bureau Subject: Request for Facilitation of an Institutional Referral Linkage for Holeta Primary Hospital and a tertiary hospital I hope this message finds you well. My name is Dr. Bilisuma Gutu, a General Practitioner (GP) currently working at Holeta Primary Hospital. I am writing to respectfully bring to your attention an important concern regarding the referral linkage of our hospital with higher-level health facilities. Previously, Holeta Primary Hospital had an established referral linkage with St. Paul's Hospital Millennium Medical College (SPHMMC), which played an important role in facilitating access to specialized medical services for patients requiring advanced investigations, specialist consultations, and comprehensive management beyond the capacity of our facility. Unfortunately, it has now been approximately five months since our previous referral arrangement became inactive. During this period, no alternative tertiary or higher-level referral facility has been officially assigned to our hospital. Consequently, we are facing considerable challenges in ensuring timely and appropriate referral services for patients who require specialized care. This situation is a significant concern, particularly for patients with complicated medical and surgical conditions, critical cases requiring advanced interventions, and those whose management exceeds the diagnostic and treatment capacity of our institution. The absence of a clearly established referral pathway may contribute to delays in accessing appropriate care and could adversely affect patient outcomes. In view of these challenges, I would like to kindly request your support and intervention in facilitating the establishment of a formal referral linkage between yikatit/ BLH and Holeta Primary Hospital as an alternative referral arrangement. Establishing this linkage would greatly contribute to: - Ensuring timely referral and continuity of patient care. - Improving access to specialized consultations and advanced diagnostic services. - Strengthening collaboration and coordination between the two health institutions. - Reducing unnecessary delays in the management of complicated and emergency cases. - Improving the overall quality and effectiveness of healthcare services provided to our community. We strongly believe that your support and coordination would be instrumental in addressing this longstanding challenge and establishing a sustainable referral arrangement. We would highly appreciate your kind consideration and any assistance you can provide toward resolving this matter. Thank you very much for your time, understanding, and continued commitment to strengthening healthcare services. Kind regards, Dr. Bilisuma Gutu: General Practitioner Holeta Primary Hospital @HakimEthio

Открыть в Telegram
Просмотры5 240+18%к среднему
Пересылки—
Реакции22
Комментарии—
#45230Фото

ለኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች የቀረበ ጥሪ በኢትዮጵያ የጤናው ዘርፍ ውስጥ እየታየ ያለው አንድ አሳሳቢ ሁኔታ የሁሉንም የጤና ባለሙያዎች ትኩረት ጥልቅ ምልከታና የጋራ ኃላፊነት የሚጠይቅ ጉዳይ ሆኖ አግኝቻለሁ:: ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተለያዩ የጤና ባለሙያዎች እርስ በርሳቸው በአደባባይ ሲወነጃጀሉ የሙያ ብቃታቸውንና ሥነ-ምግባራቸውን ሲያጠራጥሩ የሌሎችን ሙያዊ ክብር ሲያጎድፉና አንዱ ሙያ ሌላውን ሲያንቋሽሽ መመልከት እየተለመደ መጥቷል። ምንም እንኳን ሙያዊ ትችት አለመግባባትና ተጠያቂነት የጤና አገልግሎትን ጥራት ለማሻሻል አስፈላጊ ቢሆኑም እነዚህን የምንገልጽበትና የምንፈታበትን ትክክለኛ መንገድ ማግኘት እጅግ አስፈላጊ ነው። ልንረዳው የተገባ መሠረታዊ እውነታ ቢኖር የአንዳችንን ሙያዊ ክብር በአደባባይ ዝቅ ስናደርግ በጊዜ ሂደት ሕዝቡ በሁላችንም ላይ ያለው እምነት እንዲሸረሸር ምክንያት እየሆንን ነው:: ይህ በንድፈ ሐሳብ ደረጃ ብቻ ያለ ስጋት አይደለም። በዓለም የተለያዩ አገራት ያጋጠሙ ተሞክሮዎች የሙያዊ ግጭቶችና የሙያ ዝና መጎዳት በሕዝብ እምነት ላይ ምን ያህል አሳሳቢ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ እንደሚችሉ በግልጥ አሳይተዋል። 1. ደቡብ ኮሪያ - ደቡብ ኮሪያ በ2020 እና በ2024 በሐኪሞችና በመንግሥት መካከል ከፍተኛ የሙያዊ አለመግባባቶችና ግጭቶች አጋጥመዋታል። - በ2026 በ Journal of Korean Medical Science ላይ የታተመ ጥናት እነዚህ ግጭቶች በሐኪሞች ላይ ባለው የሕዝብ እምነት ላይ ያሳደሩትን ተጽዕኖ መርምሯል። - በተለይም ከ2024ቱ ረጅም ግጭት በኋላ በሐኪሞች ላይ ያለው የሕዝብ እምነት በንጽጽር ቡድኖች ላይ ከታየው ለውጥ በተጨማሪ በ7.45 በመቶ ነጥብ የቀነሰ መሆኑን ጥናቱ ገልጿል። 2. ቻይና - በ2021 በBMC Health Services Research ላይ የታተመ ጥናት በቻይና ከ10 ክልሎች የተውጣጡ 842 ሐኪሞችን በማካተት በሐኪሞች ሙያዊ ዝና ላይ የደረሰውን ጉዳት መርምሯል። - ጥናቱ ከተሳታፊዎቹ 83 በመቶ ያህሉ የሙያ ዝናቸው እንደተጎዳ እንደተሰማቸው አሳይቷል። በተጨማሪም በብዙዎቹ ላይ የሥራ ድካም፣ ጭንቀትና ሥራቸውን የመልቀቅ ፍላጎት መኖሩን ገልጿል። 3. በ21 አገራት የተደረገ ጥናት - በ2025 በ International Journal of Public Health ላይ የታተመ ጥናት ከ21 አገራት የተውጣጡ ከ621,000 በላይ ሰዎችን መረጃ በመተንተን በጤና ባለሙያዎች ላይ ባለ እምነትና የጤና አገልግሎት ፍለጋ መካከል ግንኙነት መኖሩን አሳይቷል። - በባለሙያዎች የሚያምኑ ሰዎች የሕክምና እርዳታ ፍለጋን የማዘግየት ዕድላቸው ያነሰ መሆኑን ጥናቱ ያመለክታል። ይህም ለእኛ አንድ አስፈላጊ ጥያቄ ያነሳል፦ ሕዝባችን በጤና ባለሙያዎች ላይ ያለውን እምነት ማጣት ከጀመረ ምን ይከሰታል? እምነት ሲቀንስ የጤና አገልግሎት ፍለጋም ሊጎዳ ይችላል:: በሀገራችን ኢትዮጵያ በጅማ ዩኒቨርሲቲ ሜዲካል ሴንተር በተኙ 404 ታካሚዎች ላይ ተደረጎ በ2023 ይፋ በሆነ ጥናት ከተሳታፊዎቹ 38 በመቶ ያህሉ በጤና አገልግሎት ሰጪዎቻቸው ላይ ዝቅተኛ እምነት እንደነበራቸው አመልክቷል። ይህ ጥናት ዝቅተኛው የእምነት ደረጃ በሙያዎች መካከል ባለ ግጭት የተከሰተ መሆኑን አያረጋግጥም። ሆኖም በአገራችን የሕዝብ እምነት ለመጠበቅና ለማሻሻል ትልቅ ትኩረት እንደሚያስፈልግ ያስገነዝበናል። በመሆኑም ሕዝቡ ሁልጊዜ በግለሰብ ደረጃ የተፈጸመን ጥፋት የተለያዩ የጤና ሙያዎችንና ተቋማዊ አለመግባባቶችን ለይቶ ላያይ ይችላል። የጤና ባለሙያዎች እርስ በርሳቸው ሲወነጃጀሉ የአንዱ ሙያ ብቃት በሌላው ሲናቅና በአደባባይ የጥላቻ መልዕክቶች ሲሰራጩ ሕዝቡ በጠቅላላው የጤና ሥርዓቱ ላይ እምነቱን ሊያጣ ይችላል። ይህም እምነት ሲጎድል • ታካሚዎች ትክክለኛና ሕጋዊ የሆኑ ሙያዊ ምክሮችን መጠራጠር • ሕክምና ፍለጋን ማዘግየት • በታዘዘው ሕክምና ላይ ያለው ታዛዥነት መቀነስ • በጤና ተቋማትና በሙያ ማኅበራት ላይ ያለው እምነት መዳከም • በሁሉም የጤና ባለሙያዎች ላይ የሕዝብ ጥርጣሬ መጨመር • የባለሙያዎች የሥራ ሞራልና የትብብር መንፈስ መዳከም እና የመሳሰሉ አደጋዎችን ማስከተሉ እርግጥ ነው:: ሳጠቃልለው በዚህ ስሁት አካሄድ የምንጎዳው የጤና ባለሙያው ብቻ ሳይሆን የህክምና ተገልጋዩ እና ስንኩሉ የጤና ስርዓታችንም ነው:: ሐኪም ፣ ነርስ ፣ ፋርማሲስት ፣ አዋላጅ ፣ ጤና መኮንን ፣ የላቦራቶሪ ባለሙያ ፣ የሕዝብ ጤና አጠባበቅ ባለሙያ ወይም የሌላ የጤና ሙያ ባለቤት ብንሆንም፣ የጋራ ኃላፊነት አለብን። የሙያ ወሰናችን የሥልጠና ደረጃችንና አስተያየታችን ሊለያይ ይችላል። ሆኖም የመጨረሻ ኃላፊነታችን አንድ ነው:: የምናገለግለውን ሕዝብ ጤና ክብርና እምነት መጠበቅ! የሕዝብ እምነት ከሁላችንም ላይ እስኪጠፋ ድረስ መጠበቅ የለብንም:: ዛሬ በምንፈጽማቸው ድርጊቶች የነገውን የሕዝብ እምነት እየገነባን ወይም እያፈረስን መሆናችንን ልንገነዘብ ይገባል። የሙያ ልዩነታችን ሕዝቡ በጤና አገልግሎት ላይ እምነቱን የሚያጣበት ምክንያት ፈጽሞ መሆን የለበትም! የሙያ ጥላቻን በገንቢ ውይይት፣ የአደባባይ ውንጀላን በተቋማዊ ተጠያቂነት፣ የሙያ ፉክክርን በትብብር የምንተካበት ጊዜ አሁን ነው። References 1. South Korea – Physician–government conflict and public trust (2026) 2. China – Damage to physicians' professional reputation (2021) 3. Trust in health professionals and access to healthcare (2025) 4. Ethiopia – Patient trust in healthcare providers in Jimma (2023) Dr. Habtamu Solomon Internal Medicine Resident Hawassa University @HakimEthio

Открыть в Telegram
Просмотры5 760+30%к среднему
Пересылки—
Реакции65
Комментарии—
#45229Фото

Antimicrobial Resistance (AMR) is one of the greatest global public health challenges of our time. It occurs when bacteria, viruses, fungi, and parasites develop the ability to resist medicines designed to eliminate them, making infections increasingly difficult to treat. As a pharmacist, I believe that raising awareness and promoting the responsible use of medicines are essential steps towards protecting our communities and future generations. WHY SHOULD WE BE CONCERNED? Misuse and overuse of antibiotics and other antimicrobial medicines can accelerate antimicrobial resistance. This can lead to: Treatment failure. Longer hospital stays. Increased healthcare costs. More severe infections. Increased risk of disability and death. HOW CAN WE PREVENT ANTIMICROBIAL RESISTANCE? Never use antibiotics without a valid prescription from an authorized healthcare professional. Never use antibiotics to treat common colds or flu caused by viruses. Always follow the prescribed dose, frequency and duration of treatment. Never share antibiotics with other people. Never reuse leftover antibiotics. Avoid unnecessary use of antimicrobial medicines in humans and animals. Maintain proper hand hygiene and sanitation. Get recommended vaccinations to prevent infections. Support responsible medicine dispensing and prescribing practices. A MESSAGE TO HEALTHCARE PROFESSIONALS Doctors, pharmacists, nurses, laboratory professionals, veterinarians and other healthcare workers have a shared responsibility to promote antimicrobial stewardship. As pharmacists, we must ensure rational medicine use, educate patients, discourage self-medication and contribute to the fight against antimicrobial resistance. MY CALL TO ACTION Antibiotics are precious medicines, not ordinary drugs. Their effectiveness must be protected today so that future generations can benefit from them. Remember: The misuse of antibiotics today may lead to untreatable infections tomorrow. Let's work together to protect human health, animal health and our environment. ONE HEALTH, ONE ACTION: PREVENT AMR NOW! Pharmacist Duceysane Ugas Husen Aden Clinical Pharmacy | Rational Drug Use | Public Health Awareness AMR Awareness Campaign 2026 @HakimEthio

Открыть в Telegram
Просмотры5 010+13%к среднему
Пересылки—
Реакции14
Комментарии—
#45228Фото
Просмотры4 530+2%к среднему
Пересылки—
Реакции12
Комментарии—
#45227Фото

🚨 ANTIMICROBIAL RESISTANCE (AMR): A SILENT CRISIS THAT THREATENS OUR FUTURE Antimicrobial Resistance (AMR) is one of the greatest public health threats of our time. It threatens human health, food security, economic development, and our environment. When microorganisms become resistant to antimicrobial medicines, infections that were once easily treatable can become difficult, expensive, and sometimes impossible to cure. ⚠️ THE IMPACT OF AMR IS ENORMOUS: 🔴 Infections become harder to treat and control. 🔴 Treatment costs increase, placing additional financial burdens on patients and healthcare systems. 🔴 Hospital stays become longer, increasing pressure on healthcare facilities. 🔴 The risk of complications, disability, and death increases. 🔴 Routine medical procedures, surgeries, and cancer treatments become more dangerous. 🔴 Food security, livestock production, and economic development are threatened. ⚠️ WHAT CONTRIBUTES TO AMR? • Unnecessary and inappropriate use of antibiotics. • Overuse and misuse of antimicrobial medicines. • Self-medication and incomplete treatment. • Poor infection prevention and control practices. • Inadequate Water, Sanitation, and Hygiene (WASH) services. • Limited access to quality diagnostics. • Improper use of antimicrobials in humans, animals, and agriculture. • Environmental contamination from antimicrobial waste. ✅ HOW CAN WE FIGHT AMR? • Prevent infections through proper hygiene and infection prevention. • Use antibiotics and other antimicrobials responsibly and only when indicated. • Strengthen antimicrobial stewardship programs in healthcare facilities. • Expand access to vaccines, diagnostics, and effective treatment. • Improve Water, Sanitation, and Hygiene (WASH) services. • Promote awareness among healthcare professionals, communities, and the public. • Reduce environmental pollution caused by antimicrobial misuse. 🌍 AMR IS EVERYONE'S RESPONSIBILITY! Antimicrobial resistance is not just a healthcare problem. It is a threat to public health, food security, environmental sustainability, and global development. The medicines we misuse today may no longer work when we need them tomorrow. 🤝 Let us act together to prevent infections, use antimicrobials responsibly, and preserve these lifesaving medicines for future generations. 🔵 NO ACTION TODAY, NO EFFECTIVE TREATMENT TOMORROW. 💊 Protect antimicrobials. 🛡️ Prevent infections. 🌍 Preserve our future. #StopAMR #AntimicrobialResistance #PatientSafety #PublicHealth #OneHealth #HealthForAll #AMRAwareness ✍️ By Mohammed Wabe: pharmacist, MPH @HakimEthio

Открыть в Telegram
Просмотры3 980−10%к среднему
Пересылки—
Реакции6
Комментарии—
#45221Фото
Просмотры4 840+9%к среднему
Пересылки—
Реакции8
Комментарии—
#45220Фото

🌍 WORLD ANTIMICROBIAL RESISTANCE AWARENESS WEEK 2026 Theme: Act Now: Protect Our Present, Secure Our Future Antimicrobial Resistance (AMR) is one of the major global public health threats. It occurs when microorganisms such as bacteria, viruses, fungi, and parasites develop resistance to medicines designed to treat them. As a result, infections become more difficult to treat, increasing treatment costs, complications, and the risk of death. As healthcare professionals and members of the community at Muke Turi Hospital, we all have an important responsibility to prevent and control antimicrobial resistance. 1. Role of Prescribers/Hakim Prescribers play a critical role in ensuring the rational use of antimicrobial medicines. - Prescribe antibiotics only when clinically indicated. - Follow national treatment guidelines and hospital protocols. - Select the appropriate antimicrobial, dose, route, and duration. - Request appropriate laboratory investigations and culture tests when indicated. - Review treatment according to laboratory results and clinical response. - Avoid unnecessary prescriptions and inappropriate use of broad-spectrum antibiotics. - Educate patients about the importance of taking medicines correctly. 2. Role of Pharmacists/dispensers Pharmacists/dispensers are essential in promoting the responsible use of antimicrobial medicines. - Dispense antimicrobials according to valid prescriptions and applicable regulations. - Verify the correct medicine, dose, frequency, and duration. - Counsel patients on the proper use of antibiotics. - Discourage self-medication and the sharing of antibiotics. - Avoid dispensing antibiotics without appropriate prescriptions. - Monitor antimicrobial use and identify potential misuse. - Participate in antimicrobial stewardship activities and provide feedback to prescribers. - Promote proper storage and disposal of antimicrobial medicines. 3. Role of the Community 👨‍👩‍👧‍👦 Every community member has a responsibility to protect the effectiveness of antimicrobial medicines. - Never use antibiotics without a healthcare professional's prescription. - Do not demand antibiotics for common colds, flu, or other viral infections. - Take antimicrobial medicines exactly as prescribed. - Never share leftover antibiotics with others or use someone else's medicines. - Do not keep leftover antibiotics for future illnesses. - Maintain proper hand hygiene and sanitation. - Get recommended vaccinations. - Seek appropriate healthcare advice when sick. 4. Our Commitment at Muke Turi Hospital At Muke Turi Hospital, let us strengthen teamwork among prescribers, pharmacists, nurses, laboratory professionals, and the community to promote rational antimicrobial use. Remember: - Prescribers: Prescribe responsibly. - Pharmacists/dispensers: Dispense appropriately. - Healthcare professionals: Prevent infections and promote patient safety. - Community: Use antimicrobials responsibly. TOGETHER, WE CAN FIGHT ANTIMICROBIAL RESISTANCE! Antimicrobials are precious resources. Protect their effectiveness today to save lives tomorrow. #WorldAMRWeek2026 #AntimicrobialResistance #AMRAwareness #AntibioticStewardship #RationalDrugUse #MukeTuriHospital Muke Turi Hospital:- Together Against Antimicrobial Resistance! Prepared by: Pharmacist Berhanu Dejene Muke Turi Hospital @HakimEthio

Открыть в Telegram
Просмотры4 860+9%к среднему
Пересылки—
Реакции12
Комментарии—