Кабинет

Посты канала ሀበሻ 🇪🇹

сначала новые

#11162Текст
Просмотры626−31%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#11161Текст
Просмотры1 150+27%к среднему
Пересылки—
Реакции1
Комментарии—
#11156Текст

"ሴት ልጅ ፈፅሞ የማትረሳው ወንድ" (አሌክስ አብርሃም) ብዙ ወንዶች "ሴት የመጀመሪያዋን ወንድ በህይወት ዘመኗ ሁሉ አትረሳም የሚል ያረጀ ያፈጀ ነገር ሰምተው የመጀመሪያ ለመሆን ሲጋደሉ ይታያሉ!(ሲጋደሉ ይገባችኋል) ወንድ መቸስ ለጅል ድርጊቱ ሁሉ ሐውልት እንዲቆምለት የሚፈልግ ፍጡር ነው። እስኪ አሁን ላለመረሳት እንትን 😁 የሆነ ሆኖ ዛሬ የገረመኝንና ይሄን አመለካከት ውሃ የሚያስበላ ነገር አነበብኩ፤ ከአራት ሺ በላይ ሴቶች ከመላው አለም ጠይቂያለሁ ይላል ፀሐፊው ፤ እና ሴቶች ፈፅሞ የማይረሷቸው ወንዶች ብሎ አንደኛ ደረጃ ላይ ያስቀመጠው ምን ቢሆን ጥሩ ነው? (ምን አይነት ስክራፓጯሯሟሷ የሆነ ፆታ እንደሆነኮ) "አብሯቸው በዝናብ ውስጥ የሮጠ ወንድ ፈፅሞ አይረሱም " ይላል። ከምር ገርሞኛል። ካስቀመጠው ምክንያት አንዱ The "Us Against the World" Feeling ይለዋል። ስንፈስረው ሲዘንብ ሁሉም ሰው እየሮጠ ይጠለል የለ? በቃ እኔና አንች ሁነን ዓለም የሚፈራውን አድቬንቸር ተጋፈጥነው፣ አንች ጋር ከሆንኩ ምንም አልፈራም እንደማለት ነው ለሴቷ። ለወንዱ ደግሞ ሜካፔ ታጥቦ ፀጉሬ ተንጨባሮ ክብሬ ምናምኔ ከሚል ፍርሃት በላይ አብሬህ የትም እገባለሁ የሚል መልእክት ይፈጥርበታል። ዙሮ ዙሮ ወንዱ ዝናቡ ሲቆም ይረሰዋል ሴቷ ግን ለዘመናት በዘነበ ባጉረመረመ በጠረረ ሰዓት ሁሉ በዝናብ የቀጨመ ፀጉሯን እያከከች ታስታውሰዋለች ይላል። (እንግዲህ የሮጣችሁ መስክሩ) እኔኮ አንዲት የሰፈሬ ልጅ በተገናኘን ቁጥር ህፃናት ሁነን የሩፋኤል ዝናብ ውስጥ የቦረቅነውን ስታነሳ ማስታወሷ ይገርመኝ ነበር! እስከአሁን በዝናብ ውስጥ ሲሮጡ የተነሱትን ፎቶ የለጠፉ ፍቅረኞች አልገጠሙኝም። አላችሁ? ሞክሩት የባዝ ሩም ፎቶ ሰልችቶናል¡ የሆነ ሆኖ አሁን ሁለት ጠቃሚ ሀሳብ አለኝ ... 1. ከአሁን በኋላ ከእህቶች ጋር ራት የመብላት ዕድል ከገጠመኝ የአየር ትንብያ ቀድሜ አይቸ ነው ቀጠሮ የምይዘው፤ ዶፍ በሚወርድበት ቀን ሐምሌ 23 ወይም ነሐሴ 19 ምናምን ! ወይ በዝናብ ሩጦ ዘላለም መታወስ ነው አልያም "አባቴ በዚህ በዝናብማ አንሄድም እዚሁ እንደር?" የሚል አማራጭ ነው። እሽ አንች ቅደሚ ወደሩማችን እማየ፣ አንተ ቅደም አባየ ... የተባረከ ጥናት! 2. ሰርጎች በዝናብ ቀን አውላላ ሜዳ ላይ ቢደገሱ ፍች የሚቀንስ አይመስላችሁም? በዝናብ ውስጥ ከሮጡ ሲጋቡ አይረሳሱም፣ መንጨባረሩንም ከቀን አንድ ጀምሮ ይለምዱታል😁 ማሳሰቢያ ፦ ሴትን ልጅ ካለፍላጎቷ ዝናብ ውስጥ መጎተት የዝናብ ውስጥ ፆታዊ ጥቃት ነው!!

Открыть в Telegram
Просмотры3 390+276%к среднему
Пересылки—
Реакции4
Комментарии—
#11154Текст
Просмотры3 100+244%к среднему
Пересылки—
Реакции5
Комментарии—
#11153Текст

ሰው ሲሸነፍ ማሸነፍ ምንድነው?            የምኞት አዝመራ የደስታ መከር፤           የታጨደ ጣጣ የተወቃ ችግር፤           የሞተ መከራ፤ የሚነድ እሳት ነው ተዳፍኖ የበራ። እያደር ጠፊ ነው፤ እያደር ቀሪ ነው ሲቆይ ይሰለቻል፤           ዋጋው ይቀነሳል። ሁልጊዜ በማግኘት፤ ዘወትር በማሸነፍ ዘወትር በመመከት፤            በመግዛት በመቅጣት፤ ደስታ አይገኝም። ሌላ ይፈልጋል የሰው ልብ አይጠግብም። ለጥቅሙ የሚያስብ የተስገበገበ፤ መንገዱን የማያቅ ግቡ የጠበበ፤                ስስታም ይሆናል ለፍቶ  ጥሮ ግሮ ሲያጋጥመው ዕድል። ዕረፍት አያገኝም። ሲያስብ፣ ሲያጠነጥን፣ ሲታትር፤ ሲደክም፤ አንዱን በመጨረስ መጥኖ ሌላውን፤ ያንን በመሰልቸት ሲጀምር አዲሱን፤ ያቅበዘብዘዋል፤                ትዕግሥት ይነሳዋል። ትንሽ መሰናክል እሾህ መንገዱ ላይ፤ የኑሮ ሕመም ነው የሕይቱ ሥቃይ። ያገባዋል እልክ ደሙን አስቆጥቶ፤ ንዴቱን አምጥቶ። ይተዋል ይሉኝታን ከግቡ ለመድረስ ወዲያ ወዲህ ብሎ ኃይሉን እስኪጨርስ። በመሸነፍም ነው፤ ሰው ደስታ ያለው።          በመተው በመርሳት፤ በመልቀቅ በማጣት፤          በመሸሽ በመፍራት። ወደፊት ከመሔድ አውቆ በማፈግፈግ፤ ከማሰብ ለብዙ ጥቂት በመፈለግ፤ በማነስ ከማደግ። በመጣል ከማንሣት፤ በመስጠት ከመውሰድ፤ በማልቀስ ከመሣቅ በመቅረት ከመሔድ፤               ከመውጣታት በመውረድ። ከመልበስ መታረዝ፤ ከማምለጥ በመያዝ። ክብርን ለመጠበቅ ደፍሮ ከመናገር፤ አንገት በማቀርቀር። በመዋረድና በችግር ተጎድቶ፤ በመውደቅ ተገፍቶ፤ በመናቅ ተጠልቶ፤ በሐዘን፤ በድካም፤ በሕመም፤ ባርምሞ፤ አግኝቶ በመስከር በመሻር ተሹሞ፤ ያውቃል ማ መሆኑን፤                    ይረዳል  አቅሙን። የሕይወት ለውጥ ነው ያለ በኑሮ ላይ፤ እንደ ቀን፤ እንደ ሌት፤ እንደ መሬት ሰማይ፤ እንደ ውሀ እንደሳት እንደ ልቅሶ ሣቅ፤ እንደርጥብ ደረቅ፤ ሁሉም ተለውጦ አንጻሩን ይይዛል፤ የሚሮጠው ጊዜ ጥቂት ይታገሣል። ሰዓቱ ይቆማል፤          ደቂቃው ይተኛል። ይሸፈናል ወሩ፤           ይታሰራል ቀኑ፤           ቀስ ይላል ዘመኑ። © ገብረክርስቶስ ደስታ ሁሌም ማንበብ!

Открыть в Telegram
Просмотры5 290+486%к среднему
Пересылки—
Реакции5
Комментарии—
#11150Текст
Просмотры7 640+747%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#11149Текст

የልቅ ወሲብ ፊልሞች ሱስ ፖርኖግራፊ የግሪክ ቃል ሲሆን ፖርኒ «Porni» በኢንግሊዘኛዉ ፕሮስቲቲዩት «Prostitute ወይንም ሴተኛ አዳሪ የሚል ፍቺ ሲኖረዉ ግራፌይን (Graphein) በእንገሊዘኛዉ (To write) ወይንም መፃፍ የሚል ፍቺ ይይዛል፡፡ በግርድፉ ስለ ሴተኛ አዳሪዎች የተጻፈና የተተረከ ወሲብ ቀስቃሽ ጽሁፍ ወይንም ምስል ማለት ነዉ፡፡ እኚሁ ወሲብ ቀስቃሸ ምስሎች በተለያዩ አረኪዎሎጂስቶች በሜሶፖታሚያ እና አከባቢዉ (ኢራን እና አከባቢዉ ማለት ነዉ) በሱሜሪያዉያን ዘመን እንዲሁም በ መካከለኛዉ አሶራዉያን ህዝቦች ቅሪተ ቅርሶች እንደተገኘ ይነገራል፡፡ ይህንንም አረኪዮሎጂስቶች ቬኑስ ፊጉርስ ( Venus Figurines) ይሉታል ፡፡ እንዲሁም ይህዉ ወሲብ ቀስቃሽ ምስሎች በጥንት ግጻዉያን በዴር መዲና (Deir-el-Medina) (5500 ዓ.ዓለም ተቀርጾም እንደነበር አርኪዮሎጂስቶች ይናገራሉ፡፡ ህንዶች ካማ ሱትራ ሚለዉን ወሲብ ቀስቃሽ ምስል ህትመት ከ 4 ኛዉ ክፍለ ዘመን ጀምሮ በተለያዩ ቅርጻ ቅርጾች ላይ ከመቅረጽ አልፈዉ እንደ መጽፋፍ ጭምር በማዘጋጀት ስንፈተ ወሲብን ለማከም፣ የተዛባ የትዳር ህይወትን ለማስተካከል፣ የፍቅር አጋርን ለማማለል እና ለመምረጥ፣ ብሎም በወሲብ ዉስጥ ያለዉን ጥቅም ለማስተማር ይጠቀሙት እንደነበር ይናገራሉ፡፡ በፈረንሳይ የ ፖርኖግራፊ አብዮት በ600 በ ኢንላይትመንት ዘመን ( ከ748-49) የህትመት ሚዲያዉን መስፋፋት ተከትሎ እንደ ጀመረ ይነገራል፡፡ በዚሁ ሀገር ጆን ክሌላንድ የተባለ ደራሲ እና ጸሃፊ ፋኒ ሂል ( Funny Hill ) ተብሎ የተሰየመዉን ወሲብ ቀስቃሽ ልብወለድ በማቅረብ ይጠቀሳል፡፡ በኋላም ይህ ፉኒ ሂል የተሰኘ የፈረንሳይ ፖስት ካርድ ተብሎ ይሸጥ እንደነበር ይነገራል፡፡ በጃፓን በ6ኛዉ ክፈለ-ዘመን የወሲብ ቀስቃሽ ምስል ኢሮቲክ ዉደ ቡሎክ (Erotic wood block) ተብሎ እንደ ታተመ ተሪክ ያስረዳል፡፡ የፖርኖግራፊ ታሪካዊ አጀማመር በተያዩ ሀገራ ያለዉን እዉነታ እንገነዘባለን፡፡ ይህ የፖርኖግራፊ አብዮት በየሀገሩ እንዲህ እንዲህ እያለ እየተስፋፋ በ837እንደ አዉሮፓዉያን አቆጣጠር ንግስት ቪክቶርያ ወደ ስልጣን ሲመጡ በለንደን ከተማ ከ5ዐ በላይ የልቅ ወሲብ ቀስቃሽ ምስሎች (ፖርኖግራፊ) ሱቆች እንደነበሩ ይነገራል፡፡ በ9ኛዉ ክፍለዘመን የተንቀሳቃሽ ምስሎች ለመላዉ አለም ሲተዋወቅ በዚያዉ የልቅ ወሲብ ፊልሞች አለማችንን ማጥለቅለቅ እንደጀመር በዘርፉ ጥናት ያደረጉ ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡ ባጠቃላይ በእሩቅ ምስራቅ እና በመካከለኛዉ ምስራቅ የሚገኙ ሜሶፖታማዉያን፣ ሱሜርያዉያን እና ግብጾች እና ህንዶችን ጨምሮ አረኪዮሎጂስቶች እንደሚናገሩት ይህን ወሲብ ቀስቃሽ ምስል እና እርቃን የሆኑ ፎቶዎች እና ስእሎችን በመጠቀም በስንፈተ ወሲብ የተጠቃን ግለሰብ የሚያክሙበት ጥበብ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ ይህን እርዳታ እና ህክምና የሚያደርጉበት ምክንያት በአከባቢዉ በርካታ ሰዎች የሚከተሉት እምነት ለተመስጦ ወይንም ለሜዲቴሽን ትልቅ ትርጉም እና ዋጋ ስለሚሰጡ፣ ስሜትን ማለትም ወሲባዊ ስሜትን መጫን እና ማጥፋት ለፈጣሪ እንደ መቀደስ ተደርጎ ስለሚወሰድና የእምነቱ ዋናዉና መሰረታዊ ቀነኖ በመሆኑ ከዚህም የተነሳ ቅድስናቸዉም ስለሚጨምር ፣ ነፍስ እና መንፈሳቸዉ ለፈጣሪ ስለምትለይ፣ በፈጣሪ ዘንድ ጽድቅም ተደርጎ ስለሚቆጠርላቸዉ ምናልባት ለወደፊት ትዳር መመስረት የሚፈልግ ሰዉ በ ስንፈተ ወሲብ የመጠቃት እድል ይኖረዋል ብለዉ በማመናቸዉ ይህን የፖርኖግራፊክ ቴራፒ (ህክምና) አድርገዉ እንዳዘጋጁት ይናገራሉ፡፡ ከዚህ የተነሳ በወቅቱ የነበሩ የዚህ ስራ ባለሙያዎች እንዲህ አይነቱን ችግር ለመቅረፍ የሚሰጡት ህክምና እና እርዳታ የጎልማሶችን የዎሲብ ባህሪ ለማነቃቃት የተለያዩ ስእሎችን በመሳል በተለይም ወሲብ ቀስቃሽ ምስሎችን እንዲመለከቱ በማድረግ እርዳታ እና ህክምና መስጠት ከብዙ ሺ አመታት በፊት ጀምሮ የተለመደ እንደሆነ የፖርኖግራፊ ምስሎች ታካዊ አመጣጥ ያስረዳል። ልቅ የወሲብ ፊልሞች (Pornography)- ተብሎ የሚጠራዉ ከድህረገጽ እና ከፊልም ኢንዱስተሪዉ ማደግ ጋር ተያይዞ አሁን መላዉን አለም እያወከ፣ እያሳመመ፣ አእምሮን እያበሰበሰ እና ትዉልድን እያጨነገፈ ያለ ገዳይ የ2ኛዉ ክፍለዘመን ድምጽ አልባ አዉዳሚ ጦርነት እና የጦር መሳርያ ነዉ፡፡ ፖርኖግራፊ የዚህ ትዉልድ ፈተና እና አጨንጋፊ ገዳይ መርዝ ነዉ፡፡ በአሜሪካን ሆሊዉድ፣ በህንድ በቦሊዉድ፣ በናይጄሪያ ናሊዉድ የፊልም ኢንዱስተሪያቸዉ ዉስጥ ከፍተኛ ክፍያ እየተከፈላቸዉ ይህንን አስጸያፊ ፊልም የሰሩ መልከ መለካ ሞዴል አርቲስቶች ብዙ ገንዘብ ቢያገኙም ስለተበላሸዉ ህይወታቸዉና ማንነታቸዉ የሰጡትን ምስክርነት የዚህን ገዳይ አደገኛ መርዛማ ፊልም መዘዝን መረዳት ይቻላል፡፡ ሰዎች በተለይም ወጣቶች ለምን በዚህ አደገኛ ፊልም ሱስ ይጠመዳሉ? ለምንስ ከገቡበት መላቀቅ ያቅታቸዋል? የሚያስከትለዉ ችግርስ ምንና ምንድነዉ? መዉጫ መንገዱ እና እርዳታ እንዴት ማግኘት ይቻላል የሚሉ ሃሳቦችን በዚህ ርእስ ስር እናያለን፡፡ ከላይ ለመመልከት እንደሞከርነዉ ፖርኖግራፊ ወሲብ ቀስቃሽ ፍልሞች ብቻ ማለት አይደለም፤ ወሲብን ሊቃሰቅሱ የሚችሉ እርቃን ፎቶ ግራፎች፣ ጽሁፎች፣ በድምጽ የሚተላለፉ ንግግሮች፣ ዳንሶች እና እስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ያካትታል፡፡ ይህን ትዉልድን በአደገኛ ሁኔታ እየፈጀ ያለዉ የፖርኖግራፊ ዳራ ይህ እንደሆነ ይነገራል፡፡ የሆነ ሆኖ ይህ በዚያ ዘመን የተጀመረዉ ልቅ የወሲብ ቀስቃሽ ምስል አሁን አድጎ በማህበራዊ ድህረገጽ የእያንዳንዱን ሰዉ ጓዳ እያወከ፣ ትዉልድ እያበላሸ፣ ከትምህርት፣ ከስራ እና ከእድገት ሀገሪቷን ወደኋላ እያስቀረ፣ ከልጅ እሰከ አዋቂ የሚገኝን ትዉልድ አእምሮ እያበላሸ ይገኛል፡፡ ባጠቃላይ ፖርኖግራፊ የዚህ የ2ኛዉ ክፍለዘመን ትዉልድ አጨንጋፊ እና ገዳይ መርዝ ሆኗል፡፡ ስለ ፖርኖግራፊ አሁን ብዙ ማዉራት ሳይሆን ትዉልዳችንን እንዴት እንታደግ በሚል ብዙ መነጋገር እና እርምጃ መዉሰድ የሚገባን ሰዓት ላይ እንገኛለን፡፡ እያንዳንዱ ቤተሰብ አሁን ለራሱ እና ለልጁ ብሎም ለትዉልድ ስነ አእምሮ እና መንፈሳዊ ጤና ይህንን አደገኛ ጦርነት ለመፋለም መነሳት ይገባዋል፡፡ ጌዜዉ ሳይረፍድ እና ሳይሄድብን በፖርኖግራፊ ላይ መዝመት አሁን ነዉ፡፡ Bini Girmachew

Открыть в Telegram
Просмотры8 980+895%к среднему
Пересылки—
Реакции7
Комментарии—
#11147Фото

ልክ እንደችግሩ ይሄንንም ተሻምታችሁ ሸር አድርጉት! ይሄው እንግዲህ ሜዳው! የግድ ሰው ካለመነ አንረዳም ካላልን በስተቀር ይሄ ሰው የማንንም እርዳታ ሳይሆን የስራውን ውጤት ያገኝ ዘንድ ይህን እናድርግ ... በቅርቡ ተቸገረ ብለን ስንቀባበለው የነበረው ደራሲ ሀብታሙ አለባቸው እነዚህ የፃፋቸው መፅሐፍት ባለመሸጣቸው መጋዘን ውስጥ ተቆልፎባቸው የተገኙ ናቸው። ያሉት መፅሐፎች ብዛትና የአንዱን ዋጋ ከጋዜጠኛ ወሰንሰገድ ገብረኪዳን ፅሁፍ ላይ ኮፒ አድርጌ እንዲህ በአጭሩ አስቀምጨዋለሁ። እስቲ ሁላችንም ቢያንስ አንድ መፅሐፍ በመግዛት በቀናት ውስጥ እንጨርሳቸው። ከአገር ውጭ የሆንን ደግሞ እንደተለመደው! የገዛችሁ ፎቶ ተነስታችሁ ብትልኩልኝ በደስታ ፖስት አደርገዋለሁ! መፅሐፎቹ ሸልፋችን ላይ መገኘታቸው ለእኛም ትልቅ ሐብት ናቸው!! 👉 የሱፍ አበባ 384 መጽሐፍ ተገኝቷል ....የአንዱ ዋጋ 580 ብር 👉ጉልጥምት ኢትዮጵያ 378 ፍሬ.......580ብር 👉 አውሮራ 44 ፍሬ......400 ብር 👉አስኳላ 264ፍሬ.......450 ብር 👉 ታላቁ ተቃርኖ 700ፍሬ....700 ብር 👉 የቄሳር እምባ 1178 ፍሬ .....450ብር የምትገዙበትን ቦታና ሁኔታ ለማወቅ ወሰንሰገድ ገብረኪዳንን ፃፉለት። ሙሉውን የወሰንሰገድ ፅሁፍ ለማንበብ ኮሜንት ላይ ሊንኩን አስቀምጫለሁ።

Открыть в Telegram
Просмотры6 280+596%к среднему
Пересылки—
Реакции5
Комментарии—
#11146Текст

ወቅታዊ መረጃ፡ ስለ እህታችን ናዝራዊት አበራ አዲስ ተስፋ ሰጪ ዜናዎች በቻይና በእስር ላይ ስለምትገኘው ኢትዮጵያዊት ናዝራዊት አበራ ወቅታዊ ሁኔታ ከቅርብ ቤተሰቦቿ የተገኘ አዲስ መረጃ ደርሶናል። ናዝራዊት ካለችበት አስቸጋሪ ሁኔታ አንፃር አሁንም ብርቱ ሆና እንደሚገኝ ተገልጿል። ቀደም ሲል ተከስሶባት የነበረው የሞት ቅጣት በይግባኝ ወደ እድሜ ልክ እስራት መቀየሩ የሚታወስ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ደግሞ ቅጣቱን ይበልጥ ለማቃለል ሌላ የይግባኝ ጥያቄ ቀርቦ በሂደት ላይ ይገኛል። ይህም ለቤተሰቦቿ ትልቅ ተስፋ ሆኗል። ናዝራዊት በእስር ላይ ቢሆንም ጊዜዋን በከንቱ እያሳለፈች አይደለም፦ * ባላት የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታ ለሌሎች እስረኞች ትምህርት እየሰጠች ትገኛለች (በእስረኞች ዘንድም እጅግ ተወዳጅ ናት)። * በቻይንኛ ቋንቋ የመጀመሪያ ዲግሪዋን የያዘች ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በርካታ የቻይንኛ መጻሕፍትን በማንበብ እውቀቷን እያዳበረች ትገኛለች። ከዚህ ቀደም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጉዳዩን በቅርበት ሲከታተሉት የቆዩ ሲሆን፣ ከቻይና ባለስልጣናት ጋርም በተደጋጋሚ ተወያይተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለቤተሰቦቿ ስልክ በመደወል ድጋፋቸውን መግለጻቸውም ተጠቁሟል። በቅርቡም እህቶቿ እና ፓይለት የሆነው ወንድሟ ወደ ቻይና በመጓዝ በአካል አይተዋት ተመልሰዋል። አንዳንድ በማህበራዊ ሚዲያ የሚዘዋወሩ ያልተረጋገጡ መረጃዎች በቤተሰቧ ላይ ከፍተኛ ድንጋጤ እየፈጠሩ ይገኛሉ። ቀናቶች ቀሯት የሞት ፍርድ የሚባል ነገር የለም እባካችሁ ቤተሰብ አታስጨንቁ ፈጣሪ መጨረሻውን ያሳምርላት፤ በሰላም ወደ ሀገሯ የምትመለስበትን መንገድ ያቅናላት! 🙏🙏🙏 Via Tina 🌴🌴🌴

Открыть в Telegram
Просмотры5 620+523%к среднему
Пересылки—
Реакции2
Комментарии—
#11145Текст
Просмотры4 440+392%к среднему
Пересылки—
Реакции6
Комментарии—
#11144Превью ссылки
Просмотры4 090+353%к среднему
Пересылки—
Реакции1
Комментарии—
#11143Текст

ሐሜት ግን በጣም ነው የሚደብረው! ባለፈው ሰርግ ተጠራን፤ ጥሬ ከብስል በገፍ ቀርቦ እየተበላ እየተጠጣ ዲጀው ሙሽሮቹ አጠገብ ካለው መድረክ ላይ ያቀውጠዋል። "እጃችሁን ወደላይ " ይላል፤ ለምን ወይ በአንድ ፊቱ አትብሉ አይለንም? ምግብ አቅርቦ የምን እጅ ወደላይ ነው?! ሙዚቃው በጣም ከመጮኹ ብዛት ከሙሽራዋ ፊት ላይ የሆነ ነገር ርግፍ ርግፍ ሲል አይቻለሁ፣ ሜካፕ መሠለኝ። ሚዜዋ የግንበኞች መለሰኛ ጣውላና ማንኪያ ይዛ የረገፈውን ከአገጯ ስር እየዛቀች መልሳ ትለስናታለች፤ (አውቃለሁ ግነት እንደሚመስላችሁ ... ያየሁትን ነው የፃፍኩት) እኔም እጀ ቫይብሬት እያደረገ ሁለት ጊዜ አፌን ስቸዋለሁ። ዘፈን በመድፍ ታጅቦ ነበር የሚመስለው። ድምፁ የሙሽሮቹን ጆሮ የሆነ ነገር አድርጎት ነው መሰል በኋላ ጠጋ ብየ "እንኳን ደስ ያላችሁ፣ ጋብቻችሁ የአብርሃም የሳራ ..." ስል ሁለቱም በአንድ ላይ "እ?" አሉኝ። "መ ል ካ ም ጋ ብ ቻ" "መልካሙ ተበጀ? ክፈትለት ዲጀ ...(እንዴት ነው ወደፊት የሚኗኗሩት?!) በመሀል ዲጀው ምን አንደነካው እንጃ ሙዚቃውን ፀጥ ሲያደርገው አንድ ስልል ያለ የወንድ ድምፅ ከሰርገኛው መሀል "ሙሽራዋ አታምርም! " ሲል ተሰማ። ሁላችንም ደነገጥን። ጎን ለጎን ተቀምጠው የሚያሙ ወንዶች ናቸው፣ ድንገት ሙዚቃው ሲቋረጥ በፊት በሚያወሩበት ድምፅ ያምባረቁት! ዞሬ አየኋቸው ...ሰሃናቸው ላይ ጎጆ ቤት የሚያክል ምግብ ቆልለው እያቀራሰሙ ነው የሚያሙት! ወንድነትማ እየተመናመነች ነው ጓዶች! ዋናው እንኳን ጆሮየ ሰላም ሆነ!

Открыть в Telegram
Просмотры4 110+355%к среднему
Пересылки—
Реакции2
Комментарии—