😯 #ምን_ተሰማ 😯 በተጠባቂው ጨዋታ ማንቸስተር ዩናይትድ ላይ ግብ ያስቆጠረው የሊቨርፑሉ ሶቦስዝላይ በጨዋታው የለበሰው ማሊያ መነጋገሪያ ሆኗል ድንቁ አማካይ ዶሚኒክ ሶቦስዝላይ ሊቨርፑል ማንቸስተር ዩናይትድን 4ለ0 ባሸነፈበት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ላይ ስህተት የነበረበት ማሊያ ለብሶ የተጫወተ መሆኑ ግርምት ፈጥሯል። ከትናንት በስትያ እሁድ በአንፊልድ በተደረገው ጨዋታ ሶቦስዝላይ ረጅም እጅጌ ያለውን የሊቨርፑል ማሊያ ለብሶ በ10ኛው ደቂቃ የመጀመሪያውን ጎል ሲያስቆጥር በቅርብ ካሜራ ምስሎች እንደታየው በማሊያው የታችኛው የቀኝ ክፍል ላይ የሚገኘው ነጭ እና ብርማ የትጥቅ አቅራቢው "Authentic" ባጅ ተገልብጦ (አርማው ወደ ታች ተቀምጦ) ተለጥፎ ታይቷል። በጨዋታ ቀን የስም ወይም የስፖንሰር ጽሑፍ ስህተቶች አልፎ አልፎ ቢከሰቱም እንደዚህ ያለ በፋብሪካ ደረጃ የተፈጠረ የተገለበጠ ኦሪጅናል ባጅ በፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ላይ መታየቱ በጣም ያልተለመደ ስህተት ነው። ከዚህ በተጨማሪ ከጨዋታው ማሊያ ጋር በተያያዘ ሊቨርፑል በዚህ ጨዋታ ከተለመደው የስታንዳርድ ቻርተርድ ስፖንሰር ምስል ውጪ ሴት ልጆች በስፖርት እንዲበረታቱ ለመደገፍ የሚያግዝ "Play On" የሚል ልዩ የማሊያ የፊት ለፊት አርማ ለብሶ የነበረ ሲሆን በጨዋታው የተለበሱትና የተፈረመባቸው ማሊያዎች የኤልኤፍሲ ፋውንዴሽን በጎ አድራጎት ድርጅትን ለመደገፍ ለጨረታ እንደሚቀርቡ ተገልጿል። @goferesportswear
Открыть в TelegramДинамика просмотровСкрыть динамику
Рост просмотров
Часов после публикации
Показать таблицей
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 2 ч | 172 |
| 4 ч | 238 |
- Через 6 часов238
- Всего сейчас238