Кабинет

Посты канала ገድለ ቅዱሳን ዘእለታት

сначала новые

#13976Превью ссылки
Просмотры27−70%к среднему
Пересылки—
Реакции1
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
1 ч19
4 ч27
  1. Через 1 час19
  2. Всего сейчас27
#13974Фото
Просмотры22−75%к среднему
Пересылки—
Реакции1
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
1 ч16
4 ч22
  1. Через 1 час16
  2. Всего сейчас22
#13973Текст

✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞ ✞✞✞ እንኩዋን ለኃያል ሰማዕት "ማር ቴዎድሮስ" እና "ቅዱስ አንያኖስ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞ +"+ ቅዱስ ቴዎድሮስ ማር ሰማዕት +"+ =>በቤተ ክርስቲያን የሰማዕታት አለቅነት ከተሰጣቸው ሰማዕታት አንዱ የሆነው ማር ቴዎድሮስ የተወለደው በምድረ አንጾኪያ (ሶርያ) በ3ኛው መቶ ክ/ዘ ነው:: አባቱ ዮሐንስ በትውልድ ግብጻዊ የሆነ ክርስቲያን ነው:: እናቱ ግን አስቸጋሪና ጣዖት አምላኪ ሶርያዊት ነበረች:: +ባልና ሚስት አብረው ሲኖሩ ሚስት ባሏ ክርስቲያን መሆኑን አታውቅም ነበር:: ቴዎድሮስ (የእግዚአብሔር ስጦታ ማለት ነው) በተወለደ ጊዜ ግን ጠብ ተነሳ:: እሱ ክርስትና ለማስነሳት: ሚስት ደግሞ ወደ ጣዖት ቤት ለመውሰድ ተጋጩ:: ሚስት ወገኖቿ ባለስልጣኖች ናቸውና ልጁን ቀምታ ባሏን ዮሐንስን ወደ ግብፅ አሳደደችው:: +ዮሐንስ በስደት ባለበት ሃገር ስለ ልጁ ፈጽሞ ይጸልይ: ያለቅስም ገባ:: እግዚአብሔር ደግሞ ልመናውን ሰማ:: ማር ቴዎድሮስ ወጣት በሆነ ጊዜ ማንም ሳይጠራው ወደ ቤተ ክርስቲያን ሔዶ ተማረ: ተጠመቀ:: ዕለት ዕለትም ጾምና ጸሎትን ከምጽዋት ጋር ያበዛ: ድንግልናውን ለመጠበቅ ይተጋ ነበር:: +በዛው ልክ ደግሞ ገና በ20 ዓመቱ በጉልበቱ ኃያል: በውበቱም ደመ ግቡ: በጠባዩም ገራገር ነበርና ተወዳጅ ነበር:: ነገሥታቱም የአንጾኪያ የጦር ሠራዊት አለቃ አድርገው ሾሙት:: እነሆ እስከ ዛሬ "የሠራዊት አለቃ" ተብሎ ይጠራል:: +ማር ቴዎድሮስ በተሳተፈባቸው ጦርነቶች ሁሉ ተሸንፎ አያውቅም:: ይልቁኑ የነገሥታቱን (የጠላት) ልጆች በመማረክ ነው የሚታወቀው:: እንዲያውም አንድ ጊዜ ከአሕዛብ ጋር በተደረገ ጦርነት ብቻውን አሸንፏቸዋል:: +የፋርስ ሰዎች ሊዋጉ ሲመጡ መልአክ ከሰማይ ወርዶ ሰይፍ ሰጠው:: ፋርሶችን "በከንቱ ከምትጠፉ ወደ ሃገራችሁ ተመለሱ" አላቸው:: እነርሱ ግን ተሳለቁበት:: ከፈረሱ ወርዶ ወደ ምስራቅ ዙሮ ጸልዮ በመስቀል አማተበ:: በመካከላቸው ገብቶም በመልአኩ ሰይፍ ለወሬ ነጋሪ ሳያስቀር አጠፋቸው:: +አንድ ቀን ወደ አንድ ከተማ ቢገባ ዘንዶ ሲመለክ አገኘ:: ይባስ ብሎ የአንዲት ክርስቲያን ልጆችን ለመስዋዕትነት ሲያቀርበቧቸው ተመለከተ:: በስመ ሥላሴ አማትቦ: በፈረሱ ላይም ተቀምጦ ዘንዶውን በጦር ገደለው:: የዘንዶውም ርዝመት 24 ክንድ ነበር:: +ከነገር ሁሉ በሁዋላ ቅዱስ ቴዎድሮስ ስለ አባቱ ወሬ ሰምቶ: ካለበት ሥፍራ አፈላልጎ አግኝቶ ደስ አሰኘው:: እስኪያርፍ አብሮት ቆይቶ: ቀብሮት ወደ አንጾኪያ ሲመለስ ግን የሚያሳዝን ነገር ጠበቀው:: +ክርስቶስ ተክዶ: ጣዖት ቁሞ: አብያተ ክርስቲያናት ተቃጥለው: የክርስቲያኖች ደም ፈሶ: ከተማዋ በግፍ ተሞልታ ተመለከተ:: እርሱም በዚያች ሰዓት መወሰን ነበረበትና አደረገው:: የሁሉ ሠራዊት አለቃ ቢሆንም የክብር ልብሱን አውልቆ: ባጭር ታጥቆ በንጉሡ ዲዮቅልጢያኖስ ፊት ቆመ:: +ማር ቴዎድሮስ በአደባባይ እንዲህ ተናገረ:- "አንሰ አመልኮ ለክርስቶስ ንጉሠ ስብሐት በኩሉ ልብየ: ወእሠውዕ ሎቱ - እኔስ የክብር ባለቤት ክርስቶስን በፍጹም ልቤ አመልከዋለሁ: ለእርሱም ብቻ እሠዋለሁ::" ንጉሡ በቁጣ መሬት ላይ ጥለው እንዲደበድቡት አዘዘ:: ወታደሮቹ ደሙ እስኪንጠፈጠፍ ገረፉት:: +በብዙ መክፈልተ ኩነኔ አሰቃይተው በእሳት አቃጠሉት:: እርሱ ግን በጸሎቱ እሳቱን ውሃ አደረገው:: ወታደሮቹ እርሱን በብዙ አሰቃዩ:: እርሱ ግን በእግዚአብሔር ኃይል ጸና: ታገሠ:: +በመጨረሻም ጌታችን በግርማ ወርዶ "ወዳጄ ቴዎድሮስ ስምህን የጠራ: መታሠቢያህን ያደረገ: ገድልህን (ዜናህን) የጻፈ: ያጻፈ: ያነበበ: ገዝቶ በቤቱ ውስጥ ያኖረውን ሁሉ እምርልሃለሁ" አለው:: +በስሙም ረድኤት እንደሚደረግ ነግሮት ዐረገ:: ወታደሮቹም በዚህ ቀን አንገቱን ሰይፈው የክብር አክሊልን ተቀብሏል:: እጅግ ብዙ ሺህ ሰዎችም አብረውት ተሰይፈዋል:: +"+ ቅዱስ አንያኖስ ዘግብጽ +"+ =>ይህ ቅዱስ አባት ውለታው ከፍ ያለ ነውና በምድረ ግብጽ እጅግ ይከበራል:: በተለይ ክርስትናን ከሐዋርያት ተቀብሎ ለምዕመናን ያስረከበ አባት በመሆኑ ልዩ ቦታ ይሰጠዋል:: ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:- +ወንጌላዊው ሐዋርያ ቅዱስ ማርቆስ በሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ዼጥሮስ ተመድቦ: በፈቃደ እግዚአብሔር ወንጌልን ይሰብክ ዘንድ በ50ዎቹ ዓ/ም አካባቢ ወደ ምድረ ግብጽ ወረደ:: +እስክንድርያ ከተማ በሜዲትራኒያን ባሕር ዳርቻ እንደ መኖሯም መጀመሪያ ወደ እርሷ ደረሰ:: ልክ ወደ ከተማ ሲገባ ገና አንደበቱ ለወንጌል ሳይከፈት እንቅፋት መትቶት ጫማው ተበጠሰ:: ያን ሁሉ በርሃ የቻለች ጫማ በእንቅፋት በመበጠሷ እያዘነ ወደ ጫማ ሰፊ ዘንድ ደርሶ "ሥራልኝ?" ይለዋል:: +ይህ ጫማ ሰፊ አንያኖስ (አንያኑ) ይባላል:: ጣዖት አምላኪ: ግን ደግሞ ቅንና ገር የሆነ ሰው ነበር:: "እሺ" ብሎ ሲሰፋለት መሳፈቻው (መስፊያው) ስቶ መሐል እጣቱን ስለ ወጋው "ኢታስታኦስ (አታኦስ)" ብሎ ጮኸ:: ትርጉሙም "አንድ አምላክ" ማለት ነበር:: +ይህንን የሰማው ቅዱስ ማርቆስ ቀና ብሎ "ጌታየ ሆይ! ጐዳናየን ስላቀናህልኝ አመሰግንሃለሁ!" ብሎ: ምራቁን እትፍ ብሎ በጭቃ የአንያኖስን እጅ ቀባው:: +ወዲያውም ደሙ ቁሞ: ቁስሉም ድኖ እንደ ነበረው ሆነ:: በዚህ ተአምር ድንጋጤም: ደስታም ቢሰማው "ማነህ አንተ?" ሲል ቅዱሱን ጠየቀው:: ወንጌላዊውም መልሶ "እኔ የክርስቶስ ሐዋርያ ነኝ" አለው:: +አንያኖስም "እባክህ ወደ ቤቴ እንሒድ" ብሎ ሐዋርያውን ጋበዘው:: እቤት ሲደርሱም ከሚስቱና ከልጆቹ ጋር አስተናግደውት የሕይወትን ቃል ለመኑት:: ቅዱስ ማርቆስም ከስነ ፍጥረት እስከ ጌታችን የማዳን ሥራ አስተምሯቸው አመኑ:: አጥምቆ ሥጋውን ደሙን አቀበላቸው:: +ይህቺው የቅዱስ አንያኖስ ቤትም በምድረ ግብጽ የመጀመሪያዋ ጉባኤ ቤትና ቤተ ክርስቲያን ሆነች:: ቅዱሱ ሐዋርያ በ60 ዓ/ም አካባቢ በቅዱስ አንያኑ ቤት ሆኖ በርካቶችን አሳመነ:: በሰማዕትነት ከማረፉ በፊትም ቅዱስ አንያኖስን የምድረ ግብጽ ሁሉ ሊቀ ዻዻሳት (ፓትርያርክ) አድርጐ ሾመው:: +ቅዱስ አንያኖስም ለ12 ዓመታት የክርስቶስን መንጋ እያበዛ ተጋደለ:: ከሐዋርያው የተቀበለውን ንጹሕ ዘር ዘራ:: የድኅነት የምሥራቹንም አዳረሰ:: ይሔው ይህ መልካም ተክል ዛሬም ድረስ ሳይጠወልግ አለ:: +የአሁኑ ፓትርያርክ አቡነ ታውድሮስም ከቅዱስ ማርቆስ 118ኛ ሲሆኑ ከቅዱስ አንያኖስ 117ኛ ናቸው:: ቅዱሱ ለእኛ ኢትዮዽያውያንም የክህነት አባታችን ነው:: ይህች ቀንም ዕለተ ዕረፍቱ ናት:: =>አምላከ ቅዱሳን ክፉውን አርቆ ከበጐው ዘመን ያድርሰን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን:: =>ኅዳር 20 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ማር ቴዎድሮስ ኃያል ሰማዕት 2.ቅዱስ አንያኖስ (አንያኑ) =>ወርኀዊ በዓላት 1..ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር 2.ቅዱስ አክሎግ ቀሲስ 3.ቅዱስ አፄ ካሌብ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮዽያ) 4.አባ አሞንዮስ ዘሃገረ ቶና 5.ቅድስት ሳድዥ የዋሒት =>+"+ በጐንም ለማድረግ ብትቀኑ የሚያስጨንቃችሁ ማን ነው? ነገር ግን ስለ ጽድቅ እንኩዋ መከራን ብትቀበሉ ብጹዓን ናችሁ:: ማስፈራራታቸውንም አትፍሩ: አትናወጡም:: ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስን በልባችሁ ቀድሱት:: +"+ (1ዼጥ. 3:13) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

Открыть в Telegram
Просмотры24−73%к среднему
Пересылки—
Реакции1
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
1 ч17
4 ч24
  1. Через 1 час17
  2. Всего сейчас24
#13972Видео
Просмотры63−29%к среднему
Пересылки—
Реакции2
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
1 ч23
4 ч42
10 ч63
  1. Через 1 час23
  2. Всего сейчас63
#13971Превью ссылки

+++#ከላይ_የሚመጣ_ፈተና#+++ (Temptation From Above) አረጋዊው አባ ቀልዮጳ በክርስትና ሕይወት ስንኖር ከስምንት አቅጣጫ ፈተና ሊመጣብን ይችላል ይላሉ። ሌሎቹን ትቼ አንዷንም ከፍዬ አጭር ነገር ላቀርብ ወደድኹ። ከስምንቱ ዝርዝር ውስጥ አንዱ ከላይ የሚመጣ ፈተና (Temptation from above) የምንለው ነው። ይህ የፈተና ዓይነት በውስጡ ኹለት ክፍል አለው። አንደኛው በአጭሩ ከአቅም በላይ መጋደልን ማዕከል ያደረገ ነው። በአንዴ ፍጹማን የሚያደርጉትን ለማድረግ መሞከር፣ በአንዴ ብዙ ዓመት እንደ ተጋደሉ ቅዱሳን ተጋድሎ ካልተጋደልኹ ማለት፣ ወይም በሕማም ውስጥ ኾነው ሳለ ለረጅም ጊዜ ካልጾምኩ፣ ገና ከዓለም የመጡ ኾነው ሳለ እንደ አባ እንጦንስ ካልጸለይኹ ... የማለት ፈተና ነው። መንፈሳዊነት የማይቋረጥ ዕድገት እንጄ በአንዴ ከኹሉ ተደርሶ የሚያልቅ ጉዳይ አይደለም። ...! ኹለተኛው መንፈሳዊ ብስለትንና ዕድገትን ያላገናዘበ የቅዱሳት መጻሕፍት መረዳት ፍላጎት ወይም ከአቅም በላይ የኾነ የመንፈስ ቅዱስን ምሥጢር ወይም ጠቅለል ሲል የእግዚአብሔርን ምሥጢር የመመርመርና የመረዳት ፍላጎት ፈተና ነው። ቅዱሳን በቅድስና ከእግዚአብሔር ዘንድ ተገልጦላቸው የተረዱትን የመንፈስ ቅዱስ ምሥጢር እንዲሁ መንፈሳዊ ዕድገት ላይ ሳይደርሱ በጥልቀት የመረዳትና የማስረዳት ፍላጎት ፈተና ነው። ያለ አቅም እንደ ቄርሎስ፣ እንደ አትናቴዎስ፣ እንደ ሄሬኔዎስ ራስን አድርጎ የማሰብ ወይም የማሳሰብ ፈተና ነው። ጥልቅ የኾነውን የእግዚአብሔርን ምሥጢር በራስ የመረዳት መጠን የማድረግና የማስረዳት ፈተና ከላይ የሚመጣ ፈተና ነው። እንግዲህ ይህን ዘመን በእርጋታ ካየነው በአብዛኛው በኔ ዕድሜና ከኔም አነስ ያልን ጀማሪዎች በጣም የመራቀቅ፣ የራስን መረዳት ያለቀለት አድርጎ የማሰብ፣ በአጭር ንባብ ብዙ የመናገር፣ ረጋ ብሎ ሕይወቱ ያላቸውን ከማማከር ይልቅ በለብ ለብ ንባብ የተገኘችን ዕውቀት እንደ ልዩ መረዳት አድርጎ በማሳሰብ ራስን የማግነን ወይም ራስን የማስወደድ ፍላጎት ያለብን ይመስለኛል። ከባድ ፈተና ላይ ነን። በአንዴ ከላይ ያሉትን ታላላቅ አባቶች ለመምከር፣ ለማረም፣ በኔ መረዳት በኩል እለፉ ብሎ ለመለካት፣ እንደኔ ተቀባይነት የላችሁም የሚል የሚመስል reaction የማሳየት እጅግ ፈተና ውስጥ ነን። ፍጹም የማንሰማና የምንቸኩል፣ ቶሎ ቶሎ እያልን ረቂቁን ምሥጢረ እግዚአብሔር አእምሯዊ ብቻ አድርገን በመፈላሰፍ አጀንዳ የመኾን ... ፈተናችን ጥልቅ ነው። የኾነች ንባብ ካገኘን አንረጋጋም፣ አንመረምርም፣ አናብሰለስልም፣ በአግባቡ ጊዜ ወስደን ለመረዳት አንሞክርም ይልቁን ወዲያው ማጯጯህና በማይኾን አገላለጽ መግለጽ ልማድ እየኾነብን ይመስላል። ትንሽ ንባብ ይዘን ወዲያው መካሪ ዘካሪ፣ የክርስትና አስተማሪ ለመኾን እንጥራለን። በተለይ ይህ ሚዲያ ማንንም እንዳንፈራ፣ ውስጣችን ጻፍ ያለንን እንዲሁ ዝም ብሎ የመጻፍ ፍላጎት ላይ አድርሶናል። ሌላው ቀርቶ አንዳንዴ የምንጽፈውና የምንናገረው ስለ እግዚአብሔር መኾኑን እንኳን ልብ የምንል አይመስልም። በኹሉም ዐዋቂ የመምሰል አደገኛ ፈተና ውስጥ ከመኾናችን የተነሣ፣ በአጭር ዕድሜያችን በመገለጥ እናግኝ ወይስ በምን እንጃ! ነገረ ሃይማኖትን፣ ታሪክን፣ ፍልስፍናን፣ ሳይንስን፣ ... ኹሉንም ነገር ካላብራራው፣ ካልተነተንኩ፣ በኹሉም አለኹኝ ማለት ጀምረናል። በኹሉም ረገድ የበዛ ተራቃቂነት፣ ከመጠን ያለፈ መርማሪነት፣ ከመጠን ያለፈ አመክንዮአዊነት፣ እጅግ ጠርጣሪነት፣ ... ይታይብናል። እንግዲህ በጊዜ ብንስተካከል አይሻልምን? እግዚአብሔር ከክፉ ፈተና በቸርነቱ ይጠብቀን። https://t.me/gedlekdusan

Открыть в Telegram
Просмотры67−25%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
3 ч44
8 ч67
  1. Через 6 часов67
  2. Всего сейчас67
#13970Текст
Просмотры65−27%к среднему
Пересылки—
Реакции5
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
2 ч33
8 ч65
  1. Всего сейчас65
#13969Фото
Просмотры65−27%к среднему
Пересылки—
Реакции2
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
2 ч32
8 ч65
  1. Всего сейчас65
#13967Фото
Просмотры93+5%к среднему
Пересылки—
Реакции3
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
11 ч57
26 ч93
  1. Через 24 часа93
  2. Всего сейчас93
#13966Превью ссылки

✞✞✞✝ እንኳን ለቅዱሳን ሰማዕታት ሰርጊስ ወቴዎፍሎስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ✞✞✞✝ ✞✞✞✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ✞✞✞✝ ✞✞✞✝ ቅዱሳን ባኮስ ወሰርጊስ ✞✞✞✝ ሰማዕትነት በክርስትና ለሃይማኖት የሚከፈል የመጨረሻው ዋጋ (መስዋዕትነት) ነው:: ሰው ለፈጣሪው ሰውነቱን ሊያስገዛ: ሃብት ንብረቱን ሊሰጥ ይችላል:: ከስጦታ በላይ ታላቅ ስጦታ ግን ራስን አሳልፎ መስጠት ነው:: ራስን መስጠት በትዳርም ሆነ በምናኔ ውስጥ ይቻላል:: የመጨረሻ ደረጃው ግን ሰማዕትነት ነው:: "አማን መነኑ ሰማዕት ጣዕማ ለዝ ዓለም: ወተዓገሡ ሞተ መሪረ በእንተ መንግስተ ሰማያት" እንዳለው ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ሰማዕትነት ማለት መራራውን ሞት ስለ ፍቅረ እግዚአብሔር ሲሉ መታገስ ነው:: እርሱ ቅሉ መድኃኒታችን ክርስቶስ የሰማይና የምድር ጌታ ሲሆን ኃፍረተ መስቀልን ታግሦ ሙቶልን የለ! በዓለም ያሉ ብዙ እምነቶች ስለ መግደል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ያስተምራሉ:: ክርስትና ግን መሞትን እንጂ መግደልን የሚመለከት ሕግ የለውም:: እርሱ ባለቤቱ "ጠላቶቻችሁን ውደዱ:: የሚረግሟችሁን መርቁ:: ስለሚያሳድዷችሁ ጸልዩ::" ብሎናልና:: (ማቴ. 5:44) ነገር ግን ዕለት ዕለት ራሳችንን በሃይማኖትና በምግባር ካልኮተኮትነው ክርስትና በአንድ ጀምበር ፍጹም የሚኮንበት እምነት አይደለምና በፈተና መውደቅ ይመጣል:: በተለይ የዘመኑ ክርስቲያን ወጣቶች ልናስተውል ይገባናል:: የቀደሙ ወጣት ሰማዕታት ዜና የሚነገረን እንድንጸና ነውና:: እስኪ ለዛሬ ደግሞ በአጭሩ የቅዱሳን ባኮስና ሰርጊስን ዜና እንካፈል:: እነዚህ ቅዱሳን የዘመነ ሰማዕታት ፍሬዎች ናቸው:: ባኮስ እና ሰርጊስ (ሰርግዮስ) ከልጅነት ጀምሮ ባልንጀሮች ናቸው:: በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን በሮም ግዛት ሥር መክስምያኖስና ዲዮቅልጢያኖስ እስከ ነገሡበት ዘመን ድረስ በአንጻሩም ቢሆን ሰላም ነበር:: ታዲያ በዚህ የሰላም ጊዜ ሁለቱ ቅዱሳን ሥራ አልፈቱም:: ጾምን: ጸሎትንና በጐ ምግባራትን ሁሉ ይከተሉ ነበር:: ለመከራ ዘመን ስንቅ የሚሆነን በሰላሙ ዘመን የተያዘ ስንቅ ነውና:: በዚያው አንጻር ደግሞ ሠርቶ መብላት ይገባልና ሥራ ሲፈልጉ መክስምያኖስ ሠራዊት መሰብሰብ ጀመረ:: እነርሱም ከሠራዊቱ ዘንድ ተቆጥረው የምድራዊ ንጉሥ ጭፍሮች ሆኑ:: በእርግጥ በዘመናችን ለክርስትና አይመቹም ከሚባልላቸው ሥራዎች አንዱ ውትድርና ነው:: ነገር ግን ብዙ ቅዱሳንን ስትመለከቷቸው ሙያቸው ይሔው ነበር:: ቅዱሳን ባኮስና ሰርጊስ ጊዜው የሰላምም ይሁን የጦርነት ይጾማሉ:: ይጸልያሉ:: ይመጸውታሉ:: እንዲህ እንዲህ እያሉም ዘመናት አለፉ:: ከቆይታ በኋላ ግን ሰይጣን ያደረበት ንጉሡ መክስምያኖስ ጣዖት አመለከ:: አዋጅም አውጥቶ ክርስቲያኖችን ያሰቃይ: ይገድልም ያዘ:: ቅዱሳኑ ይህንን ሲሰሙ አዘኑ:: ቁጭ ብለውም ተወያዩ:: በልባቸው ፍቅረ ክርስቶስ ይነድ ነበርና ወጣትነታቸው: መልካቸው: ተወዳጅነታቸው ሁሉ ሊያታልላቸው አልቻለም:: እንደ አንድ ልብ መካሪ: እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ስለ ሃይማኖት ሊሰው ወሰኑ:: በማግስቱም ንጉሡ ወደ ሾመው የቅርብ አለቃቸው ቀረቡና "የምንነግርህ ነገር አለን" አሉት:: "እሺ" ሲላቸው በወገባቸው ያለውን የክብር መታጠቂያና የክብር ልብሳቸውን በፊቱ ወረወሩለትና "እኛ የክርስቶስ ጭፍሮች ነንና ከዚህ በኋላ ላንተ: ለጣዖት አምላኪው አንታዘዝም" አሉት:: መኮንኑ ነዶታልና አስገረፋቸው: አሳሰራቸው:: በረሃብና በጥም: በብዙ መክፈልተ ኩነኔም አሰቃያቸው:: እነርሱ ግን ጽኑዓን ነበሩና አልቻሏቸውም:: ጥቅምት 4 ቀን በሆነ ጊዜ ግን ሁለቱን ለያዩዋቸው:: ቅዱስ ባኮስን ለብቻው ወስደው ትልቅ ድንጋይ በአንገቱ ላይ አሠሩበትና ባሕር ውስጥ አሰጠሙት:: ነፍሱም ከስጋው ስትለይ ባሕር ወደ ዳር አስወጣችው:: በአካባቢውም "ባባ" እና "ማማ" የሚባሉ ባሕታውያን ነበሩና እግዚአብሔር እንዲገንዙት አዘዛቸው:: ሲሔዱም ቅዱስ ሥጋውን አንበሳና ተኩላ ሲጠብቁት አግኝተው: በታላቅ ዝማሬ ገንዘው: በራሳቸው ተሸክመው ወስደው: በበዓታቸው ውስጥ ቀበሩት:: ቅዱስ ሰርጊስን ደግሞ ለ6 ቀናት ካሠሩት በኋላ እጁንና እግሩን በእንጨት ላይ ቸንክረው: በእንስሳት ጭራ ላይ አስረው ሲጐትቱት ውለዋል:: አንገቱን በሰየፉት ጊዜም አንዲት ወጣት ደሙን ተቀብላ በረከትን አግኝታለች:: የመከራ ዘመን ካለፈ በኋላም ለቅዱሳኑ ቤተ ክርስቲያን ታንጾ በዚህች ቀን ተቀድሷል: ተአምራትም ታይተዋል:: ✞✞✞✝ ቅዱስ ቴዎፍሎስና ቤተሰቡ ✞✞✞✝ ቅዱስ ቴዎፍሎስ በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን በሮም ግዛት ሥር ይኖር የነበረ ጽኑዕ ክርስቲያን ነው:: እግዚአብሔር ሲያድለው ደግሞ ጸንታ የምታጸና: በርትታ የምታበረታ ሚስትን ሰጠው:: ስሟም ጰጥሪቃ ይባላል:: በክርስትናዋና በፈጣሪዋ ፍቅር ላይ ይሉኝታና ድርድርን የማታውቅ ብርቱ ሴት ናት:: ሁለቱ ተጋብተው በሕጉና በሥርዓቱ ሲኖሩ እግዚአብሔር በረድኤት ጐበኛቸውና ቅድስት ጰጥሪቃ ጸነሰች:: በወለደችውም ጊዜ "ደማሊስ" ስትል በሃገራቸው ልሳን ስም አወጣችለት:: ልክ ግን ከአራስነት አልጋዋ በተነሳችበት ወራት ያ የመከራ ዘመን (ዘመነ ሰማዕታት) ድንገት ደረሰ:: እሷም አካሏ አልጸናም: ልጇም ገና 5 ወሩ ነው:: ባሏ ቅዱስ ቴዎፍሎስ ደግሞ በጨካኙ ንጉሥ እጅ መውደቁን (መታሠሩን) ሰማች:: ይኼ እጅግ ከባድ ፈተና ቢመስልም እርሷ ግን ልጇን አዝላ ወደ እሥር ቤት ሔደች:: ባሏንም "ወንድሜ! እኔና ልጅህን በክርስቶስ ዘንድ ስለምታገኘን ጽና:: ክብርህን እንዳትተው" አለችው:: እርሱም ደስ ብሎት ብዙ መከራን ተቀበለ:: ግርፋቱ: እሳቱ ስለቱ ሁሉ ሲያልፍበት በተአምራቱ አሕዛብን ማረከ:: ቅዱስ መልአክም ከሰማይ ወርዶ ማርና ወተትን መገበው:: ከዚያም በዚህ ቀን ለአንበሳ ተሰጠ:: አንበሳውም ለቅዱሱ ሰግዶ: እግሩንም ስሞ: አንገቱን ተጭኖ ገደለው:: ወዲያው ሚስቱ ቅድስት ጰጥሪቃ ተይዛ እርሷም ከነ ልጇ ለአንበሳ ተሰጠች:: በዚህ ጊዜ የ5 ወር ሕጻን ቅዱስ ደማሊስ አፉን ከፍቶ "እኔስ በሥላሴ አምናለሁና አንበሳን አልፈራም" ሲል እየሳቀ ጮኸ:: ወዲያውም እናትና ልጅን አንበሳው ገደላቸው:: ቅዱሱ ቤተሰብም ለክብር በቃ:: ††† አምላከ ሰማዕታት ጽንዐታቸውን: ትእግስታቸውንም ያድለን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን:: ††† ኅዳር 19 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ ሰርጊስ ሰማዕት 2.ቅዱስ ቴዎፍሎስ ሰማዕት 3.ቅዱሳን ጰጥሪቃና ደማሊስ (የቅዱሱ ሚስትና ልጅ) 4.ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ (ልደቱ) ††† ወርሐዊ በዓላት 1.ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት 2.ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት 3.አቡነ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ 4.አቡነ ስነ ኢየሱስ 5.አቡነ ዮሴፍ ብርሃነ ዓለም 6.ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ ††† "እግዚአብሔር ለኛ የሰማዕትነትን ሥራ ይሰጠን ዘንድ ቅዱሳን ስለሚሆኑ ሰማዕታት እንማልዳለን::" ††† (ሥርዓተ ቅዳሴ ቁ. ፸፫) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> ከኢ/ኦ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ የተገኙ የእለቱ የቅዱሳን(የጻድቃን) አባቶቻችን እና የቅዱሳን(የጻድቃን) እናቶቻችን ጽድቅ እና ገድላት ይነገርበታል። በመሀልም ጠቃሚና አስተማሪ ነው የምንላቸውን ታሪኮች ወደእናንተ የምናቀርብ ይሆናል። https://telegram.me/gedlekdusan

Открыть в Telegram
Просмотры93+5%к среднему
Пересылки—
Реакции3
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
11 ч56
26 ч93
  1. Через 24 часа93
  2. Всего сейчас93
#13965Превью ссылки
Просмотры890%к среднему
Пересылки—
Реакции3
Комментарии—
#13963Фото

እሰይ ነጋ🌅 ✨🤍 መንጋቱ አይቀርም እና ነጋ ሳይሆን ማለት ያለብን ማታ ስተኛ ጠዋት 🌅 እንድነሳ ያረሳኝ አምላክ ፤ ከቀን ላይ ቀን ፤ ከእድሜ ላይ እድሜ የጨመረልኝ ፤ በምህረቱ እና በቸርነቱ ያረሳኝ ፤የንስሃ እድሜን ፤ የማመስገኛ ዘመንን የጨመርክልን አምላኬ እግዚአብሔር ሆይ ተመስገንልኝ እንበል። እግዚአብሔር ይመስገን የንስሃ እድሜን የጨመረልን ቅዱስ ጳውሎስ ደሞ እንዲ ይለናል 🥰🙏🤲 11 ከእንቅልፍ የምትነሡበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ፤ ካመንንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቦአልና። 12 ሌሊቱ አልፎአል፥ ቀኑም ቀርቦአል። እንግዲህ የጨለማውን ሥራ አውጥተን የብርሃንን ጋሻ ጦር እንልበስ። 13 በቀን እንደምንሆን በአገባብ እንመላለስ፤ በዘፈንና በስካር አይሁን፥ በዝሙትና በመዳራት አይሁን፥ በክርክርና በቅናት አይሁን፤ 14 ነገር ግን ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት፤ ምኞቱንም እንዲፈጽም ለሥጋ አታስቡ። ወደ ሮሜ ሰዎች 13:11-14 መልካም ቀን ፤ መልካም ዕለተ አርብ ይሁንልን🙏🙏🙏

Открыть в Telegram
Просмотры87−2%к среднему
Пересылки—
Реакции5
Комментарии—
#13960Превью ссылки

ሕዝቡን ሰብስቦ በአንዲት ልጁ አጥራስስና በወዳጇ ዮና ላይ በእሳት እንዲሞቱ ፈረደባቸው:: እሳቱ ብዙ እጥፍ ነዶ ሕዝቡ ሲያለቅስላቸው 2ቱ ደናግል እርስ በርስ ተቃቅፈው ተሳሳሙ:: እየጸለዩም ወደ እሳቱ ተወረወሩ:: በዚያም ለፈጣሪያቸው ነፍሳቸውን ሰጡ:: እሳቱ ግን ልብሳቸውን እንኩዋ አላቀነበረውም:: =>አምላከ ቅዱሳን ስለ ወዳጆቹ ሲል ቸርነቱን: ምሕረቱን ይላክልን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን:: =>ኅዳር 18 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ (ከ12ቱ) 2.ቅዱስ ኤላውትሮስና እናቱ እንትያ (ሰማዕታት) 3.ቅዱሳት ደናግል አጥራስስ ወዮና (ሰማዕታት) 4.ቅዱስ አትናቴዎስ የዋሕ =>ወርሐዊ በዓላት 1.አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ረባን 2.አቡነ አኖሬዎስ ዓቢይ 3.ማር ያዕቆብ ግብጻዊ 4.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት) =>+"+ እኔንስ ብታውቁኝ አባቴን ደግሞ ባወቃችሁ ነበር:: ከአሁንም ጀምራችሁ ታውቁታላችሁ:: አይታችሁትማል አለው:: ፊልዾስ:- 'ጌታ ሆይ! አብን አሳየንና ይበቃናል' አለው:: ጌታ ኢየሱስም አለው:- 'አንተ ፊልዾስ! ይህን ያህል ዘመን ከእናንተ ጋር ስኖር አታውቀኝምን? እኔን ያየ አብን አይቷል:: እንዴትስ አንተ አብን አሳየን ትላለህ? እኔ በአብ እንዳለሁ: አብም በእኔ እንዳለ አመታምንምን? +"+ (ዮሐ.14:7) ✞✞✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞✞✞ ከኢ/ኦ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ የተገኙ የእለቱ የቅዱሳን(የጻድቃን) አባቶቻችን እና የቅዱሳን(የጻድቃን) እናቶቻችን ጽድቅ እና ገድላት ይነገርበታል። በመሀልም ጠቃሚና አስተማሪ ነው የምንላቸውን ታሪኮች ወደእናንተ የምናቀርብ ይሆናል። https://telegram.me/gedlekdusan

Открыть в Telegram
Просмотры79−11%к среднему
Пересылки—
Реакции3
Комментарии—
#13959Текст

✞✞✞✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞✝ ✞✞✞✝ እንኩዋን ለቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ ለቅዱስ ኤላውትሮስ እና ለደናግል አጥራስስ ወዮና ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞✝ ✞✞✞✝ ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ✞✞✞✝ =>እንደ አባቶቻችን ትርጉም 'ፊልዾስ' ማለት 'መፍቀሬ አኃው ወንድሞችን የሚወድ' ማለት ሲሆን ከ12ቱ ቅዱሳን ሐዋርያት አንዱ ነው:: (ማቴ. 10:3) በዚህ ስም የሚጠራ ሐዋርያ ከ72ቱ አርድእት ውስጥ ነበር:: እርሱም ጃንደረባውን ባኮስን ያጠመቀው ነው:: አንዳንዴ የ2ቱ ታሪክ ሲቀላቀል እንሰማለን:: ለሁሉም ይህኛው ቅዱስ ፊልዾስ ቁጥሩ ከ12ቱ ሐዋርያት ሆኖ ምሑራነ ኦሪት ከሚባሉትም አንዱ ነበር:: በወቅቱ ገማልያል የሚሉት ክቡርና ምሑረ ኦሪት በርካታ ምሑራነ ኦሪትን አፍርቶ ነበር:: እንደ ምሳሌም ቅዱሳኑን "ዻውሎስን: ኒቆዲሞስን: ናትናኤልን: እስጢፋኖስንና የዛሬውን ሐዋርያ ቅዱስ ፊልዾስን" መጥቀስ እንችላለን:: ቅዱስ ፊልዾስ ነገዱ ከእሥራኤል ሲሆን ተወልዶ ያደገው በቤተ ሳይዳ ነው:: ኦሪትን ተምሮ በመንገድ ዳር ቁጭ ብሎ 'መሲሕ ቀረ' እያለ ሲተክዝ ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እርሱ ደረሰ:: ትክ ብሎ አይቶት "ተከተለኝ" አለው:: (ዮሐ. 1:44) ቅዱስ ፊልዾስም ያለ ማመንታት: ሁሉን ትቶ በመንኖ ጥሪት ተከተለው:: በዚህ ዓይነት ጥሪ መድኃኒታችን ቅዱስ ማቴዎስንም ጠርቶታል:: (ማቴ. 9:9) ቅዱስ ፊልዾስ ጌታን ከተከተለ በሁዋላ ሥራ አልፈታም:: ወዲያውኑ ሒዶ ለናትናኤል (ቀናተኛው ስምዖን) ሰበከለት እንጂ:: "ሙሴ በኦሪት: ነቢያትም የተነበዩለትን መሲሕን አግኝቸዋለሁ" አለው:: ይሕ አነጋገሩም ምሑረ ኦሪት እንደ ነበር በእርግጥ ያሳያል:: (ዮሐ. 1:46) ቅዱስ ናትናኤልም ምሑር ነውና "ከናዝሬት ደግ እንዴት ይወጣል?" ቢለው ቅዱስ ፊልዾስም መልሶ "ነዐ ትርአይ-ታይ ዘንድ ና" አለው:: ናትናኤልም ሒዶ በጌታ አመነ:: ቅዱስ ፊልዾስ አገልጋይ እንደ መሆኑ መጠን በዮሐንስ ወንጌል ተደጋግሞ ስሙ ተጠቅሷል:: በተለይ ደግሞ ጌታ የ5 ገበያ ሕዝብን አበርክቶ ሲመግብ አስቀድሞ ጥያቄ ቀርቦለት ነበር:: እርሱ ግን "ጌታ ሆይ! የ200 ዲናር እንጀራ ብንገዛም አንዘልቀውም" ብሎ ነበር:: በሁዋላ ግን የጌታን ድንቅ ተአምር ተመለከተ:: (ዮሐ. 6:5) በተለይ ደግሞ በሐዋርያት አበው መካከል ለጌታ እንደ እንደራሴ ሆኖ ያገለግል እንደ ነበርም ተጠቅሷል:: ሰዎች ጌታን ማግኘት ሲፈልጉ እሱና እንድርያስን ያናግሩ ነበር:: (ዮሐ. 12:20) አንድ ጊዜ ግን እስካሁን ሊቃውንትን የምታስደምም ጥያቄ ጠይቆ ነበር:: አጠያየቁ ደግሞ ፍጹም የዋሕ እንደ ሆነ ያሳያል:: ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ባሕርይ አባቱ አብ እየነገራቸው ሳለ ቅዱስ ፊልዾስ ከመካከል ተነስቶ "እግዚኦ አርእነሁ ለአብ ወየአክለነ": ልክ ወልድን በዐይኑ እንዳየ ሁሉ አብን ሊያይ ቸኩሎ "አቤቱ ስለ አብ የሰማነው ይበቃልና አሳየን" ብሎታል:: (ዮሐ. 14:8) ጌታችን ግን "ዘርእየ ኪያየ ርዕዮ ለአብ-እኔን ያየ አብን አይቷል" (ዮሐ.14:9) ብሎ ምሥጢረ ባሕርዩን: አንድነቱን ሦስትነቱን አስረድቶታል:: ቅዱስ ፊልዾስም ጌታን እስከ ሕማሙ አገልግሎ: ቅድስት ትንሳኤውን አይቶ: ለ40 ቀናት መጽሐፈ ኪዳንን: ትምሕርተ ኅቡዓትን ተምሮ: ቅዱስ መንፈሱን ከ72 ልሳን ጋር ነስቶ ለስብከተ ወንጌል ወጥቷል:: ቅዱሳን ሐዋርያት ዓለምን በእጣ ሲካፈሉ ለእርሱ አፍራቅያ (አፍሪካ) ደርሳዋለች:: ስለዚህም በምድረ አፍሪካ ወንጌልን ከሰበኩ ሐዋርያት አንዱ ነው:: በአፍራቅያና በቀድሞው የኃምስቱ አሕጉር ግዛት ድንቅ ድንቅ ተአምራትን አድርጐ ብዙዎችን ወደ መንጋው (ወደ ክርስትና በረት) ቀላቀለ:: ለበርካታ ዓመታትም በተለያዩ የዓለም ክፍሎች እየተዘዋወረ ወንጌልን ሲሰብክ: ብርሃነ ክርስቶስን ሲያበራ: ነፍሳትንም ሲማርክ ቆየ:: ገድለ ሐዋርያት እንደሚለው የቅዱስ ፊልዾስ ፍጻሜው በሰማዕትነት እንደ ሆነ ቢታወቅም የትኛው ሃገር ውስጥ እንደ ሆነ መለየት አልተቻለም:: ዜናው ግን እንዲህ ነው:- በአንዲት ሃገር ውስጥ ገብቶ ሰበከ:: ብዙዎችንም አሳመነ:: ያላመኑት ግን ይዘው አሰቃዩት: ገረፉት:: "በክርስቶስ እመኑ እባካችሁ!" እያለ እየለመናቸው ዘቅዝቀው ሰቅለው ገደሉት:: ከዚያም በእሳት እናቃጥላለን ሲሉ ቅዱስ መልአክ ከእጃቸው ነጥቆ ወደ ኢየሩሳሌም ወሰደው:: በዚህ የደነገጡት ገዳዮቹ ለ3 ቀናት ጾሙ: ተማለሉ:: በዚህ ምክንያት የቅዱሱ ሥጋ ተመልሶላቸው: ገንዘው ቀብረውት በክርስቶስ አምነዋል:: ✞✞✞✝ ቅዱስ ኤላውትሮስ ሰማዕት ✞✞✞✝ =>ቅዱሱ ሰማዕትና ቅድስት እናቱ (እንትያ ትባላለች) የዘመነ ሰማዕታት ፍሬዎች ናቸው:: ቅድስት እንትያ መልካም እናት ናትና ቅዱስ ኤላውትሮስን በሃይማኖት በሥርዓት አሳደገችው:: በ17 ዓመቱ ዲቁናን ተሾመ:: በ18 ዓመቱ ቅስና: በ20 ዓመቱ ደግሞ ዽዽስናን ተሾመ:: ያን ጊዜ ሃገራቸው ሮም የግፍ ቦታ ነበረችና የቅዱሱ ዜና ሕይወት: ብርሃንነቱ: ስብከቱ: ንጹሕ ሕይወቱ በሃገረ ገዢው ዘንድ ተሰማ:: አንዱን መኮንን ጠርቶ "ሒድ አምጣው" አለው:: መኮንኑ ሲደርስ ቅዱስ ኤላውትሮስ እየሰበከ ነበርና በጣዕመ ስብከቱ ተማርኮ ከነ ተከታዮቹ አምኖ በዚያው ቀረ:: አገረ ገዢውም ሌላ መኮንን ልኮ አስመጣውና ቅዱሱን "ለምን የተሰቀለውን ታመልካለህ?" አለው:: ቅዱሱም መልሶ "ማስተዋል የተሳነህ! ቢገባህ ኑሮ የተቀለው እኮ ለእኔና ለአንተ ነው" አለው:: ሞት ተፈርዶበት ቅዱሱን ብዙ አሰቃይተው እሥር ቤት ሲጥሉት ርግብ መጥታ መገበችው:: እግሩን ቸንክረው በመንገድ ላይ ሲጐትቱት መልአክ ወርዶ ፈታው:: ወደ በርሃም ወሰደው:: ከጊዜያት በሁዋላ እንደ ገና ይዘው አምጥተው: ብዙ አሰቃይተው በዚህች ዕለት: ከእናቱ ቅድስት እንትያ ጋር በጦር እየወጉ ገድለዋቸዋል:: ሊቃውንትም የሰማዕታቱንና የሐዋርያውን ተጋድሎ እያደነቁ እንዲህ ጸልየዋል:- "ሰላም ለፊልዾስ ጽዑረ አባል በመቅሰፍት: ወለኤላውትሮስ ርጉዝ በብልኃ ኩናት: ምስለ እንትያ እባእ ኀበ ተርኅወ ገነት: ያሩጸኒ መዓዛሆሙ ወጼናሆሙ ዕፍረት: ለዝ ሐዋርያ ወለዝ ሰማዕት::" (አርኬ) ✞✞✞✝ ደናግል አጥራስስ ወዮና ✞✞✞✝ =>እሊህ ቡሩካት ሴት ወጣቶችም ምድራቸው ሮም ናት:: ቅድስት አጥራስስ የንጉሥ ልጅ ስትሆን ቅድስት ዮና ደግሞ የታላላቆች ልጅ ናት:: 2ቱ ቅዱሳት አንስት አይተዋወቁም ነበር:: ዮና ገና በልጅነቷ ክርስትናን አጥንታለች:: አጥራስስ ግን አባቷ ጣዖት አምላኪ በመሆኑ ቤት ሠርቶ: በወርቅ አንቆጥቁጦ ጣዖቶችን እንድታመልክ: ሰውም እንዳታይ አደረጋት:: እርሷ ግን ጣዖቱ እንደ ማይረባ ተመራምራ አውቃ ጣለችው:: "የማላውቅህ እውነተኛው አምላክ ተገለጽልኝ?" ስትልም ጸለየች:: ያን ጊዜ ቅዱስ መልአክ "ዮና የምትባል ሴት ታስተምርሽ" ስላላት አስፈልጋ አስመጣቻት:: ቅድስት ዮናም ክርስትናን ከጥንቱ ጀምራ አስተማረቻት:: 2ቱ ቅዱሳት አብረው እየዋሉ: አብረው እያደሩ በጾምና በጸሎት ቢጠመዱ ድንግል ማርያም እመቤታችን ተገለጠችላቸው:: ከልጇ ዘንድ አቅርባም አስባረከቻቸው:: ይህ ሁሉ ሲሆን የቅድስት አጥራስስ አባት ንጉሡ በሃገር አልነበረም:: ሲመለስ ግን የሆነውን ሁሉ አወቀ::

Открыть в Telegram
Просмотры78−12%к среднему
Пересылки—
Реакции4
Комментарии—
#13956Текст
Просмотры138+55%к среднему
Пересылки—
Реакции6
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
47 ч129
66 ч138
  1. Всего сейчас138
#13954Фото
Просмотры145+63%к среднему
Пересылки—
Реакции9
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
57 ч139
66 ч145
  1. Всего сейчас145
#13948Фото
Просмотры126+42%к среднему
Пересылки—
Реакции2
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
59 ч123
68 ч126
  1. Всего сейчас126
#13943Превью ссылки

በዚህ ስታዝን ይባስ ብሎ ጠዳ ላይ የአቡነ ስምዓን (ዻዻሱን) ልብስ ግዳይ ይዞ ቀረበ:: እርሷም ልቧ ቆረጠ:: ፈጣሪ 3ቱን ልጆቿን አከታትሎ ወሰደ:: ደስ ብሏት ጠፍታ ሳጋ (ዛሬ ገዳሟ ያለበት) ገባች:: ቀጥላም መነኮሰች:: ከዚህ በሁዋላ እየዞረች መናፍቃን ስታሳፍር: ሕዝቡን ስታጸና ዓመታት አለፉ:: በሷ ስብከትም ብዙ መነኮሳትና ምዕመናን ሰማዕት ሆኑ:: እሷም በየገዳማቱ ተንከራተተች:: በደዌ ተሰቃየች:: በንጉሡ ተይዛ 2 ጊዜ ወደ በርሃ ተሰደደች:: ፋሲል ነግሶ: ሃይማኖት ተመልሶ ሃገር ሲረጋጋ ወደ ምጽሊ: ከዚያም ወደ መንዞ መጥታ ገዳም መሥርታ: መናንያንን ሰብስባ: ስታጽናና ኑራለች:: በተወለደች በ50 ዓመቷም በ1630ዎቹ መጨረሻ አካባቢ ዐርፋ ተቀብራለች:: የተጋድሎ ዘመኗም 26 ዓመታት ናቸው:: ቅድስት ወለተ ዼጥሮስ ሰማዕትም ጻድቅም ናት:: ††† የጥቡዓን አምላክ የሊቁን ምሥጢር: የቅድስቷን መጨከን: ከበረከታቸውም ይክፈለን:: ††† ኅዳር 17 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ (ፍልሠቱ) 2.ቅድስት ወለተ ዼጥሮስ ኢትዮዽያዊት 3.አባ ሲኖዳ (ዘደብረ ጽሙና - ጐጃም) 4.ጻድቃን እለ ወጺፍ 5.ቅዱሳን አብርሃምና ሐሪክ 6.ቅድስት ወለተ ዻውሎስና ወለተ ክርስቶስ ††† ወርኀዊ በዓላት 1.እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት 2.ያዕቆብ ሐዋርያ 3.መክሲሞስና ዱማቴዎስ 4.አባ ገሪማ 5.አባ ዸላሞን 6.አባ ለትጹን 7.ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ††† "በድካምና በጥረት: ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት: በራብና በጥም: ብዙ ጊዜም በመጦም: በብርድና በራቁትነት ነበርሁ . . . የቀረውን ነገር ሳልቆጥር ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው::" ††† (2ቆሮ. 11:23) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> ከኢ/ኦ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ የተገኙ የእለቱ የቅዱሳን(የጻድቃን) አባቶቻችን እና የቅዱሳን(የጻድቃን) እናቶቻችን ጽድቅ እና ገድላት ይነገርበታል። በመሀልም ጠቃሚና አስተማሪ ነው የምንላቸውን ታሪኮች ወደእናንተ የምናቀርብ ይሆናል። https://telegram.me/gedlekdusan

Открыть в Telegram
Просмотры121+36%к среднему
Пересылки—
Реакции3
Комментарии—
#13942Текст

✞✞✞✝እንኳን ለዓለም ሁሉ መምሕር ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ እና ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ✞✞✞✝ ✞✞✞✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ✞✞✞✝ ለቤተ ክርስቲያን የብርሃን ምሰሶ ስለሆነላት ስለ ታላቁ ሐዋርያዊ ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ምን እላለሁ? ምንስ እናገራለሁ? እንደ እኔ ያለ ኃጥእ: ለባሴ ሥጋና ገባሬ ንስሃ ስለሱ ሊናገር አይቻለውምና:: አባቶቻችን እንደ ነገሩን ስለ አፈ ወርቅ ለመናገር አፈ ወርቅ መሆን ያስፈልጋል:: እስኪ በቅዱሱ አባት ምልጃ ጥቂት ልሞክር:: ††† ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ማን ነው? ነገዱ ከሶርያ: የተወለደው በ347 ዓ/ም በእስክንድርያ ሲሆን አባቱ አስፋኒዶስ እናቱ ደግሞ አትናስያ ይባላሉ:: እነርሱ ደግ ቢሆኑ ይህንን እንቁ ልጅ እግዚአብሔር ሰጣቸው:: ዮሐንስ ለክርስቲያን እንደሚገባ በትምሕርትና በጥበብ አደገ:: ገና በሕጻንነቱ ወደ ግሪክ ሔዶ የዘመኑን ሳይንስ (ፍልስፍና) ከአፉ እስከ ገደፉ ተምሮ ተመልሷል:: ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅን ለየት ከሚያደርጉት ነገሮችም አንዱ ይሔው ነው:: በዘመናዊም ሆነ በመንፈሳዊ ትምሕርት ይህ ቀረህ የማይሉት ሊቅ የሆነው ገና በ15 ዓመቱ ነበር:: በ2 ወገን የተሳለ ሰይፍ በመሆኑ ስንኩዋን በሕይወተ ሥጋ እያለ ዛሬም ለንፉቃን ትልቅ የራስ ምታት ነው:: ቅዱሱ ገና በ16 ዓመቱ ሃብት: ንብረት: ውበት: ክብርና እውቀት የሞላለት ቢሆንም ያለውን ሁሉ ለነዳያን ሰጥቶ መጻሕፍትን ብቻ ሰብስቦ ከባልንጀራው ቅዱስ ባስልዮስ ጋር በርሃ ገባ:: ሰውነቱን በጾምና በጸሎት እየቀጣ በበርሃ ሲኖር ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስና ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ዼጥሮስ ወደ እርሱ መጡ:: ሊቀ ሐዋርያት የመንግስተ ሰማያትን መክፈቻ ስልጣን ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌሉን ሰጥተው ተሰወሩት:: ከዚህች እለት በሁዋላ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ባሕረ ምስጢራት ሆነ:: ብሉይ ከሐዲስ: ከኦሪት ዘፍጥረት እስከ ራዕየ ዮሐንስ ድረስ በአንድምታ ትርጉዋሜ ተነተናቸው:: በተለይ ሐዲስ ኪዳንን እየመላለሰ አመሰጠረው:: ቅዱስ ሕሊናው ሳይታክት: ንጹሕ እጆቹ ሳይዝሉ የጻፋቸው ድርሳናት: መልዕክታትና ትርጉዋሜያት ቢቆጠሩ አሥር ሺህ ሞሉ:: በእውነት ለዚህ አንክሮ ይገባል! የሚገርመው ይህን ሁሉ ሲሰራ እድሜው ገና ለጋ: ማዕርጉም ዲቁና ነበር:: ከዚህ በሁዋላ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ቅስና ተሹሞ በስብከተ ወንጌል ብዙ ቦታዎችን አዳረሰ:: በቅድስናው ወደውታልና የቁስጥንጥንያ ፓትርያርክ አድርገው ሾሙት:: አፈ ወርቅ ሲናገርም ሆነ ሲያስተምር እንኩዋን የሚያወራ ኮሽ የሚል የለም:: ከጣዕመ ትምሕርቱ የተነሳ ሕዝቡ በተደሞ ይሰሙት ነበር:: ሲያስተምር ምድራዊው ሰው ይቅርና ልዑላኑ መላእክት ተሰብስበው ያደንቁት ነበር:: አንዴም እመቤታችን በሕዝብ መካከል አፈ ወርቅ ብላ ጠርታዋለች:: ለዛም ነው አፈ ወርቅ የሚባለው:: ቅዱሱ በሥልጣነ ቃሉ መልዐከ ሞትን ገስፆ 10 ዓመት አቁሞታል:: ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ለሰው ፊት አያደላም:: በርሱ ዘንድ ንጉሥና ደሃ ነዳይ እኩል ነው:: ለሞት ያበቃውም ይሔው ነበር:: ምክንያቱም የወቅቱ ንግስት አውዶክስያ ያንዲት ድሃ መበለትን መሬት ቀምታ አልመልስም በማለቷ መክሮ አወገዛት:: እርሷ ግን ከኃጥአንና መናፍቃን ጋር መክራ 2 ጊዜ አጋዘችው:: በተሰደደበት ሃገር ፍሬ አፍርቶ: አስተምሮና አሳምኖ በ407 ዓ/ም አርፏል:: ቤተ ክርስቲያንና ምእመናን ሳይጠግቡት እንደናፈቁት በ60 ዓመቱ አጡት:: በወቅቱ ታላቅ ሐዘንና ለቅሶ ተደረገ:: አንድ ቀን የዘመኑ ደግ ንጉሥ አርቃድዮስ ግብር አገባ:: (ግብዣ አዘጋጀ) በዚያች ሌሊት ደግሞ ቅዱሱ ሊቅ ታጥቆ ሲጸልይ ሳለ: አባ ማርዳሪ የሚባል ጻድቅ ደግሞ 12ቱ ሊቃነ መላእክት (እነ ቅዱስ ሚካኤል) ከሰማይ በግርማ ሲወርዱ ተመለከተ:: ደንግጦ "ወዴት ናችሁ ጌቶቼ" ቢላቸው "ቁስጥንጥንያ: ወደ ዮሐንስ አፈ ወርቅ እንሔዳለን:: እርሱ እመቤታችንን እንደሚያመሰግናት ጌታ ነግሮናልና" አሉት:: "እባካችሁ እኔም የአፈ ወርቅ ምስጋናው እንዲገለጥልኝ መርቁኝ" አላቸው:: ሊቃነ መላእክቱም መርቀውት ጐዳናቸውን ቀጠሉ:: በማግስቱ በቤተ መንግስት ውስጥ ሊቃውንቱ: መሳፍንቱ: ዻዻሳቱ: ሕዝቡ ሁሉ ተሰብስበው ከድግሱ በሉ:: ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ግን በመንበሩ ተቀምጦ ነበር እንጂ አልበላም:: ድግሱ ሲጠናቀቅ ንጉሡ አርቃድዮስ ሊቁን "ጥያቄ አለኝ" ብሎ በጉባኤ መካከል ጠየቀው:: "ምነው ወንጌላዊ ማቴዎስ 'ኢያዕመራ ዮሴፍ እስከ አመ ወለደት ወለደ ዘበኩራ - የበኩር ልጇን እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም' ማለቱ (ማቴ. 1:25) ስለ ምን ነው?" ቢለው ቅዱሱ ተነስቶ: በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ ይተረጉምለት ጀመር:: "ድንግል ማርያም ንጹሕ ብርሌን ትመስላለች:: ብርሌ የተለያየ ቀለም ያለው ፈሳሽ ቢያስገቡበት ቀለሙ አብሮ ይቀያየራል:: እመቤታችንም ጌታን ጸንሳለችና ሕብረ መለኮቱ ሲለዋወጥ መልኩዋ አብሮ ሲለዋወጥ እያየ ዮሴፍ ይደነግጥ ነበር:: 'እርሷ ማን ናት? በማሕጸኗ ያለውስ ማን ነው?' እያለ ይጨነቅ ነበር:: ጌታን ከወለደች በሁዋላ ግን አንድ ሕብረ መልክ ሆናለችና:: አስቀድሞ ማን እንደ ነበረች አላወቀም:: አሁን ግን እርሷም ወላዲተ አምላክ: ልጇም አምላክ ዘበአማን መሆኗን አወቀ ማለት ነው" እያለ ሲተረጉም ሰምተው ሁሉም ሲያደንቁ: በዚያ የነበረች ስዕለ አድኅኖ "አፈ ወርቅ! ልሳነ ወርቅ! አፈ በረከት!" ስትል ተናገረች:: ያን ጊዜ አርቃድዮስ የወርቅ ልሳን በሊቁና በስዕሏ ላይ አደረገ:: አፈ ወርቅ ግን ባጭር ታጥቆ "እሰግድ ለኪ! እሰግድ ለኪ! ወእዌድሰኪ . . ." ብሎ ዛሬ በተአምረ ማርያም የምናውቀውን ምስጋና ሰተት አድርጐ አደረሰላት:: ይህንን ምስጋናም ሊቃነ መላእክቱ ሰምተው እያደነቁ ወደ ሰማይ ወጥተዋል:: ሊቁ ባረፈ በ35 ዓመቱ በትንሹ ቴዎዶስዮስ ዘመን: በዚህ ቀን ሥጋው ፈልሷል:: ወደ ቁስጥንጥንያ ሲደርስም ከናፍቆት የተነሳ ታላቅ ዝማሬና እንባ ተደርጉዋል:: አፈ ወርቅም ቀና ብሎ ሕዝቡን ባርኩዋል:: ††† ቅዱሱ ሲጠራ እንዲሕ ነው:- =>ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ =>አፈ በረከት =>አፈ መዐር (ማር) =>አፈ ሶከር (ስኩዋር) =>አፈ አፈው (ሽቱ) =>ልሳነ ወርቅ =>የዓለም ሁሉ መምሕር =>ርዕሰ ሊቃውንት =>ዓምደ ብርሃን (የብርሃን ምሰሶ) =>ሐዲስ ዳንኤል =>ሊቀ ዻዻሳት ዘበርትዕ (እውነተኛው) =>መምሕር ወመገስጽ ዘኢያደሉ ለገጽ =>ጥዑመ ቃል - - - ✞✞✞✝ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ ኢትዮጵያዊት ✞✞✞✝ ቆራጧ እናታችን ቅድስት ወለተ ዼጥሮስ ለእኛ ለኢትዮዽያውያን የተዋሕዶ አማኞች ሞገሳችን ናት:: እጅግ የሚደነቅ መንፈሳዊ አርበኝነትን በካቶሊኮች ላይ አሳይታለችና:: ቅድስት ወለተ ዼጥሮስ የተወለደችው በ16ኛው መቶ ክ/ዘመን በምሥራቅ ኢትዮዽያ ዳውሮ አካባቢ ነው:: ወላጆቿ ባሕር አሰግድና ክርስቶስ ዕበያ ይባላሉ:: ክርስትናን በሚገባ አጥንታ አድጋ: በወላጆቿ ፈቃድ በሥርዓቱ ባል አገባች:: ግን ወዲያው አፄ ያዕቆብ ገደሉባት:: ወላጆቿም ግድ ብለው ስዕለ ክርስቶስ የተባለ የሱስንዮስን የጦር መሪ አጋቧት:: እስከ 24 ዓመቷም ልጆችን ወለደች:: በዚህ ሁሉ ጊዜ የጾምና የጸሎት ሰው ነበረች:: አፄ ሱስንዮስ ተዋሕዶን ክዶ ካቶሊክ በሆነ ጊዜ ባሏ ወደ ንጉሡ እምነት ገባ::

Открыть в Telegram
Просмотры108+21%к среднему
Пересылки—
Реакции3
Комментарии—
#13941Превью ссылки
Просмотры124+39%к среднему
Пересылки—
Реакции4
Комментарии—