Динамика просмотровСкрыть динамику
Рост просмотров
Часов после публикации
Показать таблицей
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 3 ч | 223 |
| 5 ч | 236 |
| 7 ч | 240 |
- Через 6 часов236
- Всего сейчас240
Часов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 3 ч | 223 |
| 5 ч | 236 |
| 7 ч | 240 |
Часов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 5 ч | 242 |
| 8 ч | 276 |
Часов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 5 ч | 245 |
| 8 ч | 278 |
Часов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 5 ч | 238 |
| 8 ч | 269 |
Часов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 5 ч | 233 |
| 8 ч | 261 |
Часов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 5 ч | 237 |
| 8 ч | 265 |
Часов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 5 ч | 237 |
| 8 ч | 264 |
Часов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 3 ч | 153 |
| 26 ч | 512 |
Часов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 10 ч | 227 |
| 28 ч | 459 |
Часов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 17 ч | 402 |
| 24 ч | 463 |
Часов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 32 ч | 528 |
| 66 ч | 692 |
Часов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 58 ч | 645 |
| 71 ч | 673 |
እንድታውቁት ጾመ ነቢያት ማክሰኞ ኅዳር 15/ 2019 ዓ.ም (Nov. 24/2026 GC) ይጀምራል። የቅዱሳን አምላክ የጾሙን በሰላም አስፈጽሞ ለብርሃነ ልደቱ በሠላም ያድርሰን! ለሀገራችን ሰላሙን፣ ፍቅሩን፣ አንድነቱን ይስጥልን! አሜን! #ፍሬ_ሃይማኖት_ሚዲያ ይህ ብ/ዓ/ጴ/ወጳ/ቤ/ክ ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተከፈቱ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ናቸው። ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በማጋራት አብረውን ያገልግሉ። የቴሌግራም ቻናል https://t.me/FrehaymanotSS የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@frehaymanotss?si=0evYyW4fI__UEEmO የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@fre.haymanot?_r=1&_t=ZS-9ALhPVxYyqD የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/share/1EytjinVgm/
Открыть в Telegramኅዳር ፲፫ እልፍ አእላፋት መላእክት እግዚአብሔር ቅዱሳን መላእክትን ሲፈጥራቸው በነገድ መቶ (100) በክፍለ ነገድ አሥር (10) አድርጓቸዋል። አቀማመጣቸውንም በ3 ሰማያትና በ10 ከተሞች (ዓለማት) አድርጎል። መላእክት ያሉባቸው ከተሞች ከታች ወደ ላይ "ኤረር ፥ ራማና ኢዮር" ይባላሉ። አሥሩ ክፍለ ነገድ ደግሞ ከነ አለቆቻቸው ይህንን ይመስላሉ፦ ፩. አጋዕዝት (የቀድሞ አለቃቸው ሳጥናኤል አሁን የተረፉት በቅዱስ ሚካኤል ሥር ናቸው) ፪. ኪሩቤል (አለቃቸው ኪሩብ) ፫. ሱራፌል (አለቃቸው ሱራፊ) ፬. ኃይላት (አለቃቸው ሚካኤል) ፭. አርባብ (አለቃቸው ገብርኤል) ፮. መናብርት(አለቃቸው ሩፋኤል) ፯. ሥልጣናት (አለቃቸው ሱርያል) ፰. መኳንንት (አለቃቸው ሰዳካኤል) ፱. ሊቃናት (አለቃቸው ሰላታኤል) ፲. መላእክት(አለቃቸው አናንኤል) ናቸው። ከእነዚህም ፣ አጋዕዝት ፣ ኪሩቤል ፣ ሱራፌልና ኃይላት መኖሪያቸው በኢዮር (በ3ኛው ሰማይ) ነው። አርባብ ፤ መናብርትና ሥልጣናት ቤታቸው ራማ (2ኛው ሰማይ) ነው። መኳንንት፣ ሊቃናትና፣ መላእክት ደግሞ የሚኖሩት በኤረር (በ1ኛው) ሰማይ ነው። መላእክት ተፈጥሯቸው እምኀበ አልቦ ኀበቦ ነው። አይራቡም ፥ አይጠሙም ፥ አይዋለዱም ፥ አይሞቱም። ተፈጥሯቸውም ረቂቅ ነው። ተግባራቸውም ዘወትር "ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ" እያሉ ፈጣሪያቸውን ማመስገን ነው። ምግባቸውም ይሄው ነው። ዕረፍት ብሎ ነገርን አያውቁም። "አኮቴቶሙ ዕረፍቶሙ ፥ ወዕረፍቶሙ አኮቴቶሙ" እንዲል። በተጨማሪም መልአክ ማለት ተላላኪ (አገልጋይ) ነውና ከፈጣሪ ወደ ሰው ልጆች ለምሕረትም ለመዓትም ይላካሉ። ምሕረትን ያወርዳሉ ልመናን ያሳርጋሉ ቅጡ ሲባሉም ይቀጣሉ ሥነ ፍጥረት (አራቱ ወቅቶች) እንዳይዛቡ ይጠብቃሉ። ዘወትርም ስለ ሰው ልጆች ይማልዳሉ (ዘካ. 1:12) ምሥጢርን ይገልጣሉ (ዳን. 9:21)ይረዳሉ (ኢያ. 5:13) እንዳንሰናከል ይጠብቃሉ (መዝ. 90:11) ያድናሉ (መዝ. 33:7)ስግደት ይገባቸዋል (መሳ. 13:20, ኢያ. 5:13, ራዕ. 22:8) በፍርድ ቀንም ኃጥአንን ከጻድቃን ይለያሉ (ማቴ. 25:31) በአጠቃላይ ለሰው ልጆች ሕይወትና ድኅነት ሲባል ከፈጣሪያቸው የተሰጣቸውን ትዕዛዝ ሲጠብቁና ፈቃዱን ሲፈጽሙ ይኖራሉ። እልፍ አእላፋት ይህ ዕለት በሊቃውንት አንደበት "እልፍ አእላፋት" እየተባለ ይጠራል። በሃይማኖት ፥ በተልእኮትና በምስጋና የሚኖሩ 99ኙ ነገደ መላእክት በአንድ ላይ የሚከብሩበት ቀን ነው። ኅዳር 13 ቀን ዓመታዊ በዓላቸው ነው በየወሩ ደግሞ በ13 ወርሐዊ በዓላቸው መሆኑን ያሳያልና ዘወትር ልናስባቸው ይገባል። ቅዱስ መጽሐፍ ቅዱሳን መላእክትን በስምና በማዕረግ እንደሚነግረን ሁሉ በማኅበር (በትዕይንት) አገልግሎታቸውም ይነግረናል:: ለምሳሌ:- ያዕቆብ በረዥም መሰላል ሲወጡና ሲወርዱ ተመልክቷል (ዘፍ. 28:12)። ኤልሳዕ ለግያዝ አሳይቶታል (2ነገ. 6:17)።ዳንኤል ተመልክቷል (ዳን. 7:10)።በልደት ጊዜ በዝማሬ መገለጣቸውን ቅዱስ ሉቃስ ጽፏል(ሉቃ. 2:13) ዮሐንስ በራዕዩ አይቷቸዋል (ራዕይ.5:11) ከዚህም በላይ በብዙ የመጻሕፍት ክፍል ተጠቅሰዋል። ቅዱሳን መላእክተ ብርሃን መንፈሳውያን ፥ ሰባሕያን ፥ መዘምራን ፥ መተንብላን (አማላጆች) ተብለውም ይጠራሉና ያስቡን ዘንድ ልናስባቸው ይገባል:: #ፍሬ_ሃይማኖት_ሚዲያ
Открыть в Telegramእስራኤልን ከግብጽ ባርነት እየመራ ያወጣበት ይህም የሆነው ያዕቆብ በረሃብ 70 ኹኖ ወደ ግብፅ ከወረደ በኋላ ከ215 ዓመታት (አብርሃም ወደ ግብፅ በተሰደደ ከ430 ዓመታት) በኋላ፤ የዮሴፍን ዝና ያልሰማ፥ ዮሴፍን የማያውቅ ፈርዖን በግብፅ ነገሠ፡፡ እስራኤል ከእኛ ይልቅ በዝተዋል ጠላቶቻችን ቢነሱብን ከጣለቶቻችን ጋር ተደርበው ያጠፉናል በማለት አገዛዝ አጸናባቸው፥ ፍርድ አጓደለባቸው፡፡ የእስራኤል ሴቶች ልጅ ሲወልዱ ወንድ ከሆነ እንዲገደል በማድረግ መከራ አጸናባቸው፡፡ ለ215 ዓመታት በግብፅ በባርነት ከቆዩ በኋላ ከዕብራውያን ወገን የሆነችው ራሔል ጭቃ እያቦካች ምጥ በያዛት ጊዜ ከሥራዋ እንዲያሳርፏት ጠየቀች፤ ግብጻውያን ግን የሕፃናቱ ደም ጡቡን ያጠነክራል ርገጭ አሏት፡፡ ከማሕፀኗ የወጡ ሁለት መንትያ ልጆቿን እያየች ከጭቃ ጋር ረገጠች፤ ራሔልም መሪር ልቅሶን አለቀሰች፤ ስለ ልጆቿም መጽናናትን እንቢ አለች፡፡ የእስራኤል ንጉሥ ሆይ የሆነብንን እይ ስትል ራሷን ይዛ ታለቅስ ጀመር ፥ እንባዋንም ወደ ሰማይ ንጉሥ ወደ እግዚአብሔር ረጨች፡፡ የራሔል እንባዋ የሕዝበ እስራኤልን ሁሉ ጩኸት ፥ እሮሮ ይዛ ቅድመ እግዚአብሔር ደረሰች፡፡ “. . . ራሔል ስለ ልጆቿ አለቀሰች የሉምና ስለ ልጆቿ መጽናናት እንቢ አለች” /ኤር 31፥5፤ ማቴ 2፥17/ እንዲል፡፡ ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን አስነሣና፤ በሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል መሪነት፤ 10 ተአምራትን በምድረ ግብፅ በ11ኛ ተዓምር ደግሞ በኅዳር 12 (ፈርዖንን ከነሠራዊቱ በኤርትራ ባሕር አስጥሞ) ወደ ተስፋይቱ ምድረ መራቸው፡፡ ባሕረ ኤርትራን እስራኤላውያን እንደተሻገሩም የእስራኤል ልጆች የሙሴ የአሮን እኅት ማርያም ከበሮ እየመታች ‹‹ንሴብሖ ለእግዚአብሔር ስቡሐ ዘተሰብሐ ፤ እግዚአብሔር ተዋጊ ነው ስሙም እግዚአብሔር ነው እያሉ፡፡›› ጠላታቸውን የመታላቸውን ፥ እነሱንም በተአምራቱ ያሻገራቸውን ፥ ከጠላታቸው እጅ ያዳናቸውን እግዚአብሔርን አመሰገኑ፡፡ ከዚህ በኋላ መጋቤ ብሉይ ቅዱስ ሚካኤል እየመራቸው ፥ መና ከሰማይ እያወረደላቸው ፥ ውሃ ከጭንጫ እያፈለቀላቸው ፥ ቀኑን በደመና ፥ ሌቱን በብርሃን መርቷቸው አርባ ዘመን ተጕዘው የቃል ኪዳን አገራቸው ምድረ ርስት ከነዓንን (የዛሬዋ ኢየሩሳሌምን) ወርሰዋል፡፡ /ዘጸ. 15/ ከሙሴ በኋላ እስራኤልን የመራው ነቢዩ ኢያሱም እስራኤልን በሚመራበት ጊዜ ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል እስራኤልን ይረዳቸው ነበር፡፡ ከጠላቶቻቸው ጋር ሲዋጉም ሰልፉን ይመራ የነበረው ቅዱስ ሚካኤል ነበር፡፡ ለምሳሌ እስራኤላውያን ከኢያሪኮ አጠገብ በነበሩበት ጊዜ ቅዱስ ሚካኤል ተገልጦ ኢያሱን አነጋግሮታል፡፡ ኢያሱ በኢያሪኮ አጠገብ ሳለ ቀና ብሎ ሲመለከት የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ አንድ ሰው ከፊቱ ቆሞ አየ፤ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ “ከእኛ ወገን ነህ ወይስ ከጠላቶቻችን?” ሲል ጠየቀው፡፡ እርሱም “አይደለሁም ነገር ግን የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ በመሆኔ መጥቻለሁ” ብሎታል /ኢያሱ 5፥13-15/፡፡ ይህ የተመዘዘ ሰይፍ ይዞ ከኢያሱ ፊት ለፊት የቆመው መልአክ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል (እንዲሁም መልአኩ ቅዱስ ራጕኤል) ነው፡፡ ይህን ለአብነት አነሣን እጅ እስራኤል በሚበድሉበት ጊዜ ሁሉ ወደ እግዚአብሔር የሚማልድላቸው ይህ ታላቅ መልአክ መጋቤ ብሉይ ቅ/ሚካኤል ነበር፤ እግዚአብሔር አምላክ በእደ መልአኩ ይጠብቀን፤ ከበዓሉ ረድኤት ፥ በረከት ይክፈለን፤ አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡ #ፍሬ_ሃይማኖት_ሚዲያ
Открыть в Telegramኅዳር ፲፪ ቅዱስ ሚካኤል በእልፍ አእላፍ መላእክት ላይ የተሾመበትና እስራኤልን የመራበት ክብረ በዓል ነው፡፡ በዓለ ሢመቱ ሚካኤል ማለት ማን እንደ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ከሌሎች መላእክት ጋር በዕለተ እሑድ ካለመኖር ወደ መኖር የተፈጠረ ሲሆን፤ እርሱም መጀመሪያ ከ100 ነገደ መላእክት የ10ሩ ነገደ መላእክት (የኃይላት) አለቃቸው ነበር፤ በተጨማሪም ከሳጥናኤል ውድቀት በኋላ የኃይላት አለቅነቱን እንደያዘ የአጋዕዝትን ነገድም (ሳጥናኤል/ሰማልያል/) ይመራቸው የነበሩትን 10 ነገዶችም በአለቅነት ደርቦ አለቃ ሆኗል፤ እንዲሁም በዛሬው ዕለት ለመቶውም (99ኙም) ነገደ መላእክት (ለእልፍ አእላፋት መላእክት) አለቃቸውም ቅዱስ ሚካኤል ሆኖ የተሾመበት ዕለት ነው፡፡ ልዑል ውእቱ ልዑለ መንበር ያሰኘውም ይኸው ነው፡፡ ቅ/ሚካኤል ለሰው ልጆች ምሕረትን ከኅዳር 12 (ከበዓለ ሢመቱ) ጀምሮ እስከ ኅዳር 13 (የአእላፍ መላእክት) በዓል ድረስ ከአምላኩ ለፍጥረታት ሁሉ ምሕረትን የሚለምንበት ዕለታት ናቸው፡፡ #ፍሬ_ሃይማኖት_ሚዲያ
Открыть в Telegram