Кабинет

Посты канала እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net

сначала новые

#1195Текст

ነገር ግን የሳቱ ይመስለኛል። እነዚህ ሰዎች የጠቀሱት የአል ዐዚም ኣባዲ “ዐውኑ ’ል መዕቡዲ” መጽሐፍ የሱነኑ አቢ ዳውደን መጽሐፍ የሚያብራራ ነው። በቅጽ ስምንት እነርሱ የጠቀሱት ማብራሪያ ከቶ አይገኝም። ምናልባት በተለያዩ ኅትመቶች ውስጥ የቅጽ ለውጥ ይኖራል ብለን ስላሰብን ስለ ትዃኑ የጠቀሱት ልክ ይኾናል ብለን እናስባለን። ዳሩ ግን በዐውኑ ’ል መዕቡዲ ላይ አል ዐዚም ኣባዲ የጠቀሰውን ማንሣት ሳይኖርብን አይቀርም፡— أنها كانت تفلي): في القاموس: فلى رأسه بحثه عن القمل) “(ትቀምል (ትለቅም) ነበር)፡— በአል ቃሙስ (አል ቃሙሱ ’ል ሙሒጢ)፡— ራሱን ቀመለ፥ ቅማልን ሻ (ፈለገ)።” ከዚህ በፊት “ፈላ” የተሠኘውን የዐረብኛ ቃል አስመልክተን በኡስታዝ ወሒድ ላይ የጻፍነውን ጽሑፍ አንባቢዎች መለስ ብለው ያነብቡ ዘንድ እንመክራለን። እንግዲህ አል ዐዚም ኣባዲ መዝገበ ቃላት ጠቅሶ ይህን ብሏል። ኡስታዞቹ ይህን ማስረጃ አላዩምን? እነርሱ ስንኳ ሳይቀሩ ያመኑበትን እውነት ኡስታዞቹ ስለ ምን ይክዳሉ? ሌሎች ነፍሳት መኖራቸውን ስለ ነገረን ደስተኞች ነን፥ ነገር ግን ቅማል አይደለም ማለት ትክክል እንዳልኾነ እናውቃለን። ሌሎችም እልፍ ስሕተቶች ታጭቀውበታል። ባስፈለገ ጊዜ እንጽፍባቸዋለን። ከ Namrud R. Teferi የፌስቡክ ገጽ የተወሰደ

Открыть в Telegram
Просмотры1 360−14%к среднему
Пересылки—
Реакции24
Комментарии—
#1194Текст

ስለዚህ የሐዲሱም ኾነ የቍርኣኑ አገላለጽ ሞትን የሚያመለክት እንጂ ሌላ አይደለም። አንድ ሰው የቍርአኑ አገላለጽ እንዲህ ነው ቢል ትክክል እንጂ አላዋቂ አይባልምና። በዚሁ መጽሐፍም የሙሐመድ የሐዲሱ አፈታት በቁሙ አንዳይፈታ ይናገራል። ሙሐመድ ይህን አባባል መጠቀሙም ግርምትን ያጭራል። ቍርኣኑን በቃሉ ያስታውስ ከነበረ፥ ከቍርአኑ ጋራ የሚመሳሰለውን ይህን አባባል የሞት ጣር ይዞት ሳለ መጠቀሙ አንዳች ነገር የሚነግረን ይመስላል፤ ምናልባትም የራሱን ነቢይነት አጠያያቂ ኾኖ ሳያገኘው አልቀረም። አል ራዚ የሐዲሱን አባባል ሲያስገነዝብ “አሟሟቱ አብሀሩ እንደ ተቈረጠበት ሰው ያለ ነው” ማለቱም ለዚህ ይመስላል። ብዙ ሰዎች በማይገለገሉበት እንዲህ ባለ አነጋገር መናገሩ ከቍርኣኑ ጥቅስ ጋራ የተቈራኘ ቢኾን ነው። 3. ኡስታዞቹ አል አብሀር “በዠርባ አጥንት ውስጥ የሚያልፍ ነርቭ/A vein in the back” ብለው የተናገሩትም ታላቅ ቅጥፈት ነው። Vein ነርቭ ማለት አይደለምና፤ የሙሐመድን ሕመም የነርቭ ሕመም እንደ ኾነ ለማስመሰል ሞክረዋል። Vein የደም ሥር ነው። ኡስታዙ “የነቢዩ (ﷺ) የልብ ደም ሥር የተቈረጠ ሳይሆን (አል ወቲን፤ ሱራ 69 ፥ 46) ፥ በመርዙ ምክንያት የተሰማቸው የነርቭ ሕመም (አል አብሀር) ነው፤ ሞታቸውም የተፈጥሮ ፍጻሜ እንጂ “የሐሰተኝነት ቅጣት” አይደለም” ብለዋል። ይህ ትክክል አይደለም፤ የነርቭ ሕመም አይደለም። አል አብሀርና አል ወቲን ኹለቱም የደም ሥሮች ናቸው። የሱና ድረ ገጽ ስንኳ አል አብሀርን በማያሻማ እንግሊዝኛ “aorta” ይለዋል። በዘመናዊ ዐረብኛ ስንኳ አብሀር “aorta” ተብሎ ይተረጐማል። ኡስታዞቹ የልብ ሕመም መኾኑን መቀበል አልፈለጉም፥ አለያ ደግሞ ዐረብኛ በቅጡ አያውቁም። በውኑ የሙሐመድ ንግግር ከቍርኣኑ ጋራ መተባበሩ ያስደነግጣል፤ በዚህ ምክንያት ኡስታዞቹ የሙሐመድን ሕመም ከነርቭ ሕመም ጋራ ቢያቈራኙ የሚደንቅ አይደለም። እንኪያስ አል አብሀር ምን ማለት ይኾን? የዐረቡ ዓለም ሊቃውንት አብሀር የተሠኘውን ቃል በተለያየ መንገድ ተገንዝበውታል። በዝርዝር ካብጠረጠሩት የዐረብ ሊቃውንት መካከል ኢብን አል አሲር አንዱ ነው። ይህ ሰው “አል ኒሃየቱ ፊይ ገሪቢ ’ል ሐዲሲ ወል አሰሪ” የተባለ መዝገበ ቃላት ያዘጋጀ ሊቅ ነው። አብዛኞቹ የርሱን አፈታት ተጠቅመዋል። ርሱ እንዲህ ይላል፡— الأبهر عرق في الظهر ، وهما أبهران. وقيل هما الأكحلان اللذان في الذراعين. وقيل هو عرق مستبطن القلب فإذا انقطع لم تبق معه حياة. وقيل الأبهر عرق منشؤه من الرأس ويمتد إلى القدم ، وله شرايين تتصل بأكثر الأطراف والبدن ، فالذي في الرأس منه يسمى النأمة ، ومنه قولهم: أسكت الله نأمته أي أماته ، ويمتد إلى الحلق فيسمى فيه الوريد ، ويمتد إلى الصدر فيسمى الأبهر ، ويمتد إلى الظهر فيسمى الوتين ، والفؤاد معلق به ، ويمتد إلى الفخذ فيسمى النسا ، ويمتد إلى الساق فيسمى الصافن ትርጕሙም ይህ ነው፡— “አል አብሀሩ የዠርባ ሥር ነው። እነርሱም ኹለቱ አብሀሮች ናቸው። እነርሱም በክንድ ላይ ያሉ አክሐሎች (የክንድ የደም ሥሮች) ናቸው ይሏል። ርሱም (አል አብሀሩ) በልብ የተከለለ ሥር (የደም ሥር) ነው ይሏል። የተቈረጠም እንደኹ ሕይወት አልቀጠለም። አል አብሀሩ መነሻው ከራስ በኩል የኾነ ሥር ነው፤ ወደ እግርም ይዘረጋል ይሏል። ለርሱም ከብዙ ጫፎችና (ጥንፎችና) ከሰውነት ጋራ የሚገናኙ መትረቦች አሉት። በራስ በኩል ያለው አል ነእመቱ ይባላል (ተብሎ ይሰየማል) ። ከዚህም ነው አባባላቸው (የመጣው)፡— “አስከተ አላሁ ነእመተሁ” (አላህ ነእመቱን ጸጥ ያድርገው) ፤ ይኸውም “ያሙተው” (ይግደለው ማለት ነው) ። ወደ ጕረሮም ይዘረጋል፤ በርሱም ዘንድ አል ወሪይዱ ይባላል። ወደ ደረትም ይዘረጋል፤ አል አብሀሩ ይባላል። ወደ ዠርባም ይዘረጋል፤ አል ወቲኑ ይባላል፤ ልብም በርሱ ላይ የተንጠለጠለ ነው። ወደ ጭንም ይዘረጋል፤ አል ነሳኡ ይባላል። ወደ ባትም ይዘረጋል፤ አል ሳፊኑ ይባላል።” በሥራው የተደነቀ የዐረቡ ሊቅ ኢብን መንዙር ደግሞ የአል አብሀርን ምንነት ሲያስገነዝብ እንዲህ ይላል፡— والأبهر: عرق في الظهر ، يقال هو الوريد في العنق ، وبعضهم يجعله عرقا مستبطن الصلب “አል አብሀሩ፡— በዠርባ ያለ ሥር። ርሱም ባንገት ያለው ወሪድ (አል ወሪዱ) ነው ይባላል፤ አንዳንዶች በሰረሰር የተከለከለ ሥር (የደም ሥር) ያደርጉታል።” والأبهر: عرق إذا انقطع مات صاحبه ؛ وهما أبهران يخرجان من القلب ثم يتشعب منهما سائر الشرايين “አል አብሀሩ፡— ሥር፤ የተቈረጠ እንደ ኾነ ባለቤቱ ይሞታል። ከልብ የሚወጡ ኹለት አብሀሮች ናቸው፤ ቀጥሎ ቀሪዎቹ መትረቦች ከርሱ ይሠርጻሉ።” (መትረብ በተለምዶ “የደም ቧንቧ” የምንለው ነው) قال أبو عبيد: الأبهر عرق مستبطن في الصلب والقلب متصل به فإذا انقطع لم تكن معه حياة “አል ዑበይድ አለ፡— አል አብሀሩ በሰረሰር ውስጥ ያለ የተከለለ ሥር ነው። በተቈረጠም ጊዜ በዚያ ሕይወት አይኾንም።” በዃላም ከላይ የተተረጐመውን የኢብን አሲርን አፈታት በአል አብሀሩ ሥር አስፍሯል። የመናዊው የታሪክ ሊቅና የፊቅህ ሰው የነበረው ዑመር አል ጀዕዲ (አል ጀዕዲ) “ጠበቃቱ ፉቀሃኢ አል የመኒ” በተባለ መጽሐፉ ይህን ጽፏል፡— “አል አብሀሩ፡— በሰውነት ውስጥ ያለ ሥር፤ ለርሱም በአባል (በአካል) ኹሉ ስም አለው፤ በእጅ አል አክሐሉ፥ በእግር አል አንጀሉ፥ በሆድ አል ወቲኑ፥ በደረት አል ኒያጡ...።” እነዚህ ኡስታዞች እፎይ የተባለው ሰው አል አብሀሩና አል ወቲኑ የተባሉትን ስያሜዎች መለየት የማይችል ሰው እንደ ኾነ ይነግሩናል። ነገር ግን ራሳቸው አል አብሀሩና አል ወቲኑ ምን እንደ ኾኑ አያውቁም። አል አብሀሩ የተባለውን ቃል “ነርቭ” ማለታቸውም በዚህ የተነሣ ነውና። እነርሱ ይቅሩና የዐረቡ ዓለም ሊቃውንት ስንኳ በእነዚህ ቃሎች የተለያየ አስተሳሰብ ኖሯቸዋል። የየመኑ ሊቅ አል ወቲን በሆድ አካባቢ ያለ ነው ይላል። ኢብን አሲር ደግሞ በዠርባ በኩል ያለ ይለዋል። አል አብሀሩም ከራስ ዠምሮ እስከ እግር የሚዘልቅ ሥር እንደ ኾነ፥ የተለያዩ ስሞችም እንዳሉት ነግሮናል። ዳግመኛም በደረት በኩል ያለው ሥር አል አብሀሩ እንዲባል ጽፏል። እንኪያስ አል አብሀር ከልብ ጋራ የተቈራኘ ሥር መኾኑን ልብ ይሏል። በዠርባም ይኹን በደረት፥ ከልብ ጋራ የተቈራኘ በመኾኑ፥ ይህ ሥር ቢበጠስ ሕይወት እንዳይቀጥል እነዚህ የዐረብ ሊቃውንት ተናግረዋል። ኡስታዞቹ ምላሽ ይኾነናል ብለው ወዳሰፈሩት ወደ ሌላኛው ጽሑፍ እግረ መንገዴን ልኺድ። ኡስታዞቹ ዘይነብ ሙሐመድን አልቀመለችም ሲሉ እንዲህ ጽፈዋል፡— “በአቡ ዳውድ (3080) ላይ ዘይነብ የለቀመችው ከነቢዩ ጸጉር ላይ “ቅማል” ሳይኾን “በቀን” (بقّا) ፥ ትዃን ወይም ትናንሽ በራሪ ነፍሳት) መኾኑንና ይህም የኾነው በጊዜው የነበረው ቤታቸው ከዘንባባ ቅጠል (ጣሪያ) በመሠራቱ ምክንያት ነፍሳት ከጣሪያው ላይ ስለሚረግፉባቸው መኾኑን ጸሓፊው ኾነ ብሎ አጣሞታል (ዐውኑ ’ል መዕቡዲ፤ 8/292)።

Открыть в Telegram
Просмотры1 140−28%к среднему
Пересылки—
Реакции6
Комментарии—
#1193Текст

የሕያ ኢብኑ ኑሕና አቡ ዩስራ የሚባሉ ኡስታዝ ቢጤዎች ለእፎይ ምላሽ ሰጥተናል በማለት የጻፉትን መጽሐፍ አንድ ወዳጄ አጋራኝ። መጽሐፉን አነበብኹ። ነገር ግን እነዚህ ኡስታዞች ከእፎይ ያልተሻሉ እንደ ኾኑ ለወር ያኽል ተግተው ለፍተው የጻፉትን መጽሐፍ አንብቤ አስተዋልኹ። እነዚህ ኡስታዞች መልስ ይኾኑናል ብለው ከጻፏቸው ምላሾች መካከል አንዳንዶቹ የሚያሥቁ ይመስላሉ። ስለ ሙሐመድ አሟሟት የጻፉት ይደንቃል። የሚያነብ ሰው የለም ብለው ነውን? እንኪያስ ለዛሬ በሙሐመድ አሟሟት ላይ ያነሡትን ምላሽ እንተች ዘንድ ይገባል። ኡስታዞቹ እንዲህ ይላሉ፡— “ሀ. ጸሓፊው ኹለት የተለያዩ ዐውዶች ያላቸውን ቃላት ኾነ ብሎ አምታትቷል። ነቢዩ (ﷺ) “የደም ሥሬ የተቆረጠ ያኽል ይሰማኛል” ማለታቸው፥ በዐረብኛ ቋንቋ ዘይቤያዊ አገላለጽ ከፍተኛ የኾነ የሕመም ስሜትን ለመግለጽ የሚነገር ቃል ነው። (ልክ በዐማርኛ “አንዠቴ ተቆረጠ” ወይም “ዐጥንቴን ሰበረው” ብለን ስሜትን እንደምንገልጸው ማለት ነው) ። በቍርኣን ላይ የተገለጸው “ወቲን” ግን ዘይቤያዊ ሕመም ሳይኾን፣ አላህ ሐሰተኛን ነቢይ በቅጽበት አጥፍቶ መልእክቱን እንዳያስተላልፍ የሚያደርግበት ቀጥተኛ እና ቅጽበታዊ መለኮታዊ ርምጃ ነው። የልብ ደም ሥር (Aorta) ቃል በቃል ከተቈረጠ፥ ሰውየው በሴኮንዶች ውስጥ ይሞታል እንጂ ለዓመታት አይቈይም። ለ. ሱራ 69 ፥ 44-46 የተዋቀረው በቅድመ ኹኔታ (Conditional “If” Clause) ነው፡— “በእኛ ላይ ከፊል ቃላትን በቀጠፈ ኖሮ በኀይል በያዝነው ነበር፤ ከዚያም የልቡን ሥር በቈረጥን ነበር።” ይህ የሰዋሰው ሕግ የሚያሳየው፥ ውሸት (መቅጠፍ) ቢፈጸም ኖሮ ወዲያውኑ መበጠስ ይከሠት ነበር። የዚህ ቅጣት ዋና ዓላማ የሐሰት መልእክት ለሕዝብ እንዳይደርስ በቅጽበት ማስቆም ነው። ነቢዩ ግን መልእክቱን ሙሉ በሙሉ አድርሰዋል።” ቀጥሎም እፎይ የተባለውን ሰው እየተቹ ይህን ጽፈዋል፡— “እዚህ ላይ ጸሓፊው የፈጸመው አሥቂኝ የቋንቋና የትርጉም ሸፍጥ፡— 1. በሱረቱ ’ል ሓቀቲ (69 ፥ 46) ላይ የተጠቀሰው የዐረብኛ ቃል “አል ወቲን” (الوتين) — ከልብ ወደ አካል ደም የሚረጭ ዋናው የደም ቧንቧ/Aorta ሲሆን፣ ነቢዩ (ﷺ) ከአራት ዓመት በዃላ ባመማቸው ጊዜ ሕመሙን ለመግለጽ የተጠቀሙት ቃል ግን “አል አብሀር” (الابهر) — በዠርባ አጥንት ውስጥ የሚያልፍ ነርቭ/A vein in the back ነው (ፈትሑ ’ል ባሪ፤ ቅጽ 8፤ ገጽ 131) ። ኹለቱ ቃላት አካላዊ ቦታቸውም ሆነ ትርጉማቸው ፈጽሞ የተለያዩ ናቸው። 2. ነቢዩ (ﷺ) ይህንን ቃል የተጠቀሙት “መርዙ ዛሬ ቈረጠኝ/ገደለኝ” ለማለት ሳይሆን የመርዙን ሕመም ጽናት በዘይቤ ለመግለጽ ነው፤ አላህም በዚያ መርዝ ምክንያት ሸሂድነትን (የሰማዕትነትን ክብር) ሊያጎናጽፋቸው በመጨረሻው ሕመማቸው ላይ የመርዙን ስሜት ቀሰቀሰባቸው (ሸርሑ ’ል ነወዊዪ፤ ቅጽ 14፤ ገጽ 171) ። ጸሓፊው ግን የቃላቱን ልዩነት ኾነ ብሎ በመደባለቅ አንባቢን አታሏል።...” በሌላም ቦታ ይህን ጽፈው ይገኛሉ፡— “የነቢዩ (ﷺ) የልብ ደም ሥር የተቈረጠ ሳይሆን (አል ወቲን፤ ሱራ 69 ፥ 46) ፥ በመርዙ ምክንያት የተሰማቸው የነርቭ ሕመም (አል አብሀር) ነው፤ ሞታቸውም የተፈጥሮ ፍጻሜ እንጂ “የሐሰተኝነት ቅጣት” አይደለም።” (ገጽ 167፥ 150ና 176፤ ጽሑፉ የፊደልና የአጻጻፍ ዕርማት ተደርጎበታል) አንባቢ ሆይ፥ አል አብሀርና አል ወቲን የሚባሉ ስሞችን በሰማኽ ጊዜ ግር አይበልኽ። ኹለቱም የደም ሥሮች ናቸው። እነዚህ ስያሜዎች በዱሮ ዐረብኛ አል አብሀሩና አል ወቲኑ ይባላሉ። እነዚህ ኡስታዞች ለእፎይ መልስ በሚል ባዘጋጁት በዚህ መጽሐፍ ውስጥ፥ የሙሐመድን አሟሟት በተመለከተ የሠሯቸው ስሕተቶች እነዚህን ይመስላሉ፡— 1. በሐዲሱ የተጠቀሰው አል አብሀር (አል አብሀሩ) ከቍርኣኑ አል ወቲን (አል ወቲኑ) ጋራ ፈጽሞ የተለያየ እንደ ኾነ አበክረው ገልጸዋል። ይኸውም አል አብሀር በዐማርኛ “አንዠቴ ተቆረጠ” እንደምንለው ያለ አባባል እንጂ ሌላ እንዳይደለ ተናግረዋል። በጀ። ሙሐመድ በመሞቻው ሰዓት ላይ ሳለ የተናገረውን መመልከት ያሻልና፡— يا عائشة ما أزال أجد ألم الطعام الذي أكلت بخيبر، فهذا أوان وجدت انقطاع أبهري من ذلك السم (ሰሒሑ ’ል ቡኃሪዪ) ትርጕሙም ይህ ነው፡— “(ነቢዩ ሰላላሁ ዐለይሂ ወሰለም በሕመሙ በሚሞትበት ጊዜ እንዲህ ይል ነበር)፡— ዓኢሻ ሆይ፥ በኸይበር ሳለኹ የበላኹትን፥ የምግቡን ደዌ የማላስቀረው ኾኖ ይሰማኛል። በዚህም ጊዜ ከዚያ መርዝ (የተነሣ) የደም ሥሬ ሲቈረጥ ተሰማኝ።” ሰው እየሞተ ሳለ በዘይቤ ከተናገረ፥ የሕመሙን ክብደትና እውነተኛ ስሜት እየተናገረ ነው። ሙሐመድ “በዚህም ጊዜ የልብ ሥሬ (መትኔ) ሲቈረጥ ይሰማኛል” ብሏል። ለሰው ልጅ ሲታመም የሚናገርበት የንግግር ምሳሌ አለው። ታዲያ ይህ ሕመም በተመረዘ ምግብ የተከሠተ እንደ ኾነ በሐዲሱ የተጻፈ ነው። “ከዚያ መርዝ የተነሣ...” ፥ “በዚህም ጊዜ...” ማለቱን ይመለከቷል። እንኪያስ የተመረዘው ምግብ የልቡን ሥር ቈርጦታል ብንል ትክክል ይኾናል። ምክንያቱም “ከመርዙ የተነሣ የደም ሥሬ ሲቈረጥ ተሰማኝ” ብሏልና። ሙሐመድ ታሞ ሳለ ይህን ተናገረ፤ እንዲያው በደፈናው የተሰማውን ተናገረ እንጂ በቁሙ የልብ ሥሬ ተቈረጠ እያለ ላይኾን ይችላል። የሕመሙ ስሜት ግን የደም ሥርን የመቍረጥ ዐይነት ነው ብንል ማጋነን አይኾንም። 2. ኡስታዞቹ “በቍርኣን ላይ የተገለጸው “ወቲን” ግን ዘይቤያዊ ሕመም ሳይኾን፥ አላህ ሐሰተኛን ነቢይ በቅጽበት አጥፍቶ መልእክቱን እንዳያስተላልፍ የሚያደርግበት ቀጥተኛ እና ቅጽበታዊ መለኮታዊ ርምጃ ነው። የልብ ደም ሥር (Aorta) ቃል በቃል ከተቈረጠ፥ ሰውየው በሴኮንዶች ውስጥ ይሞታል እንጂ ለዓመታት አይቈይም” ብለዋል። ኡስታዞቹ ከላይ አል አብሀርን የንግግር ዘይቤ ነው ብለው ሲያበቁ፥ አል ወቲን ግን የንግግር ዘይቤ ያይደለ ቀጥተኛ አነጋገር እንደ ኾነ ጽፈዋል። ነገር ግን ሙሐመድ “የልቤ ዥማት ሲቈረጥ ይሰማኛል” ባለበት ቅጽበት ያኔ በኸይበር ሳለ የጐረሰው ምግብ ዐይሎበት የልቡን ሥር በሚበጥስ መልኩ እንደ ተሰማው የሐዲሱ ጥቅስ ያስገነዝባል። ይህ አባባል በአላህ መቀጣቱን የሚያመለክት አይደለም። ምክንያቱም እኛ በሙሐመድና በቍርኣን የተጻፈውን የምንቀበል ሕዝብ አይደለንም፤ ቍርኣን ከእኛ በዃላ ዘግይቶ የመጣ ደኃራዊ ነውና። ኤሎሂምን እንጂ አላህን አናመልክም፤ የቍርኣንን ምስክርነት አንሻም። የአባቶቻችን አምላክ ለሙሐመድ ተገልጦ አናግሮታል አንልምና። ዳሩ ግን የአሟሟቱ ነገር ከቍርኣኑ ጥቅስ ጋር የተመሳሰለ መኾኑ ያስገርማል። የልቡ የደም ሥር ተቈርጧልና። ይኸውም ሙሐመድ የቍርኣኑን ቃል ደግሞ እየተናገረ ያለ ይመስላል። ቍርኣን የሙሐመድ ቃል ነው የሚባልበት አንዱ ምክንያት ይህ ሳይኾን አይቀርም። አል ራዚ በጻፈው “መፋቲሑ አል ገይቢ” የተሠኘ የተፍሲር መጽሐፍ ውስጥ ሱረቱ ’ል ሐቀቲ (ቍርኣን 69 44-46) በቁሙ እንደማይፈታ ኢብን ቁተይባ እንደ ተናገረ ጠቅሶ ጽፏል፡— قال ابن قتيبة: ولم يرد أنا نقطعه بعينه بل المراد أنه لو كذب لأمتناه “ኢብን ቁተይባ አለ፡— “ዕሰባው “ቢዋሽ እናስሞተው (እንገድለው) ነበር” የሚል እንጂ “ራሱኑ (ወቲኑን) እንቈርጠዋለን” ብሎ የሚያሳስብ አይደለም።”

Открыть в Telegram
Просмотры1 230−22%к среднему
Пересылки—
Реакции8
Комментарии—
#1192Превью ссылки
Просмотры2 610+65%к среднему
Пересылки—
Реакции29
Комментарии—
#1190Текст
Просмотры7 220+356%к среднему
Пересылки—
Реакции37
Комментарии—
#1189Текст
Просмотры6 490+309%к среднему
Пересылки—
Реакции46
Комментарии—
#1188Текст

Переслано из ደቂቀ አትናቴዎስ አማርኛ

መሲሓዊ ትንቢት እና ኢብኑ ተይሚያ የራሳቸውን እምነት የሚጻረር ቢሆንም እንኳ የክርስትና አስተምህሮን ከተቃወመላቸው ከይሖዋ ምስክሮች አንስቶ እስከ ሥዝም ሰብአዊ ምሁራን ሙግቶች ድረስ የሚቃርሙትና የሚያግበሰብሱት ሙስሊም ዐቃቤያነ እምነት አሁን ደግሞ “ከብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ውስጥ ኢየሱስ ክርስቶስ አንድም ትንቢት አልፈጸመም” በማለት መሞገት ጀምረዋል። ይህ ዓይነቱ የሙግት መስመር በታሪክ ውስጥ የአይሁድ ሊቃውንት በክርስቲያኖች ላይ የሚያቀርቡት ዋና መከራከሪያ ሲሆን ትክክለኛ ባይሆንም እንኳ ክርስቲያኖች እንደ ማስረጃ ለሚያቀርቧቸው ጥቅሶች አጸፋዊ ምላሽ እና ተለዋጭ ትርጉም ሲሰጡ ኖረዋል። ዘግይተውም ቢሆን በመሲሓዊ ትንቢቶች ላይ የአይሁድ ሊቃውንት የሚያቀርቡትን ሙግት እንዲሁም አጸፋዊ ምላሽ ማንበብ የጀመሩት ተንባላት እነዚያ ያረጁ እና ያፈጁ እንዲሁም በተደጋጋሚ የተረ’ቱ ሙግቶችን እንደ በቀቀን በመደገም ላይ ይገኛሉ። ሆኖም ዐቃቢያኑ ከአይሁድ ሊቃውንት በቃረሙት ሙግት በእስልምና ውስጥ ትልቅ ቦታ ከሚሰጣቸው ሊቃውንት ጋር እየተቃረኑ እንደሆነ የሚያውቁ አይመስልም። ስለሆነም በዚህ አጭር መጣጥፍ ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ “አል-ጀዋብ አስ-ሰሒሕ” በተሰኘ ሥራው በብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ውስጥ ሙስሊሞች እና ክርስቲያኖች የሚስማሙባቸው በአይሁድ ግን ተቃውሞ የሚቀርብባቸው የክርስቶስን መሲሕነት የሚያሳዩ መሲሓዊ ትንቢቶች መኖራቸውን ስለመግለጹ በአጭሩ የምንጽፍ ይሆናል - መልካም ቆይታ ! ኢብኑ ተይሚያ “አል-ጀዋብ አስ-ሰሒሕ” በተሰኘ መጽሐፉ የቀደሙ ነቢያት የሙሐመድን መምጣት መተንበያቸውን ያነሳና ፣ ይህ ሊታውቅ የሚችልባቸው አምስት መንገዶች ያሰፈረ ሲሆን አራተኛውን መንገድ በሚያብራራበት ስፍራ በቀደሙ መጻሕፍት ስለ ሙሐመድ የተነገሩ ትንቢቶች ስለ ክርስቶስ እንደ ተነገሩት ዓይነት መሆናቸውን እንዲህ በማለት ይገልጻል :-  “ብዙ ሊቃውንት ነቢይነቱን የሚደግፉ ብዙ ትንቢቶችን ከመጽሐፋቸው የተለያዩ ቦታዎች ማውጣት ችለዋል። ረጅም የሆነ ጥቅል ራሱ አዘጋጅተዋል። ከእነዚህ መጻሕፍት የተወሰዱ እነዚህ ትንቢቶች የክርስቶስን (ሰላም በእርሱ ላይ ይሁን) መምጣት እንደሚተነብዩት ያሉ ናቸው።” [1] አክሎም በቀደሙት መጻሕፍት ስለ ሙሐመድ እና ኢየሱስ ክርስቶስ የተነገሩ ትንቢቶች መሐከል ያለው መመሳሰል ምን ዓይነት እንደሆነ ሲያብራራ ፣ አይሁድ በትንቢት ቃላቶቹ ይስማሙና ይመጣ ዘንድ ስለሚጠበቀው ነቢይ አያወሩም በማለት በትርጉማቸው ላይ ማፈንገጣቸው እንደሆነ ተናግሯል። “አይሁድ በየትንቢት ቃላቶቹ ይስማማሉ ይሁን እንጂ በተለየ መልኩ ይተረጉሟቸዋል። መምጣቱ የተተነበየው ኢየሱስ ክርስቶስ ሳይሆን ሌላ አካል ነው ብለው ይናገራሉ። ... ስለ አንድ የሚጠበቅ ነቢይ አያወሩም በማለት የትንቢቶቹን ትርጉም ይበርዛሉ።... አይሁድ ስለ ክርስቶስ መምጣት የሚገልጹ ሁሉንም ምልክቶች ያጣምማሉ። እንደ ሙስሊሞች እና ክርስቲያኖች ከሆነ ይህ ስለ ክርስቶስ መምጣት የተነገሩ ትንቢቶችን ሐሰት አያደርግም። ይልቁንም አንቀጾቹ መምጣቱን እንደሚያመለክቱ እና የአይሁድን ጥመት እንደሚያፈርሱ ያሳያል። ” [2] ልብ በሉ ! “እንደ ሙስሊሞች እና ክርስቲያኖች ከሆነ ይህ ስለ ክርስቶስ መምጣት የተነገሩ ትንቢቶችን ሐሰት አያደርግም። ይልቁንም አንቀጾቹ መምጣቱን እንደሚያመለክቱ እና የአይሁድን ጥመት እንደሚያፈርሱ ያሳያል።” ማለቱ ኢብኑ ተይሚያ በአይሁድ መጽሐፍ ውስጥ - ይኸውም ብሉይ ኪዳን ነው - ስለ ሙሐመድ መምጣት የሚናገሩ ትንቢቶች እንዳሉ ሁሉ ፣ ስለ ክርስቶስ መምጣትም የሚገልጹ ትንቢቶችም አሉ ብሎ እንደሚያምን ያመለክታል። ይህ ማለት ግን ኢብኑ ተይሚያ ክርስቲያኖች ስለ ክርስቶስ የተነገሩ ትንቢቶች ናቸው ብለው በሚያቀርቧቸው ጥቅሶች ሁሉ ይስማማል ማለት አይደለም ፣ ይህም በመጽሐፉ ውስጥ ክርስቲያኖች ስለ ክርስቶስ የተነገሩ ናቸው የሚሏቸውን ጥቅሶች ለሙሐመድ በማዋሉ መገንዘብ ይቻላል። ሆኖም ያለምንም ጥርጥር ተበርዟል ብሎ በሚያምነው የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ውስጥ እንኳ አይሁድ ሊያስተባብሉ የማይቻላቸው ፣ ሙስሊሞች እና ክርስቲያኖች ደግሞ ስለ ክርስቶስ መምጣት የተነገሩ እንደሆኑ የሚረዷቸው አያሌ ትንቢቶች እንዳሉ ማመኑን ልብ ይለዋል።             አሜን ጌታ ኢየሱስ ሆይ ና !             ✍   ዲ/ን ዘአትናቴዎስ 1). Answering those who Altered the Religion Of Jesus Christ By Shaikhul-Islam Ibn Taimiyah , pp. 327-328 2). Ibid

Открыть в Telegram
Просмотры7 400+367%к среднему
Пересылки—
Реакции53
Комментарии—
#1187Текст
Просмотры5 870+270%к среднему
Пересылки—
Реакции58
Комментарии—
#1181Фото

አሕመዲን ጀበል የኢትዮዽያ ሕዝበ ሙስሊም ቆጠራ ተጭበርብሯል ብሎ እያለቃቀሰ ነው። ምን ዓይነት ጥናት ሠርቶ ይሆን? በ1999 ዓ.ም በተካሄደው የኢትዮጵያ የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ከአጠቃላይ ግምት ውስጥ ወደ 2 ሚሊዮን የሚሆን ሕዝብ ቁጥር 'እንደጠፋ' እና ከቆጠራው ውጭ እንደ ተደረገ የተነገረው የአማራ ክርስቲያንም በዚህ ልክ አልጮኸም። በወቅቱ የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ወ/ሮ ሳሚያ ዘካሪያ እንደ ነበሩ የሚታወስ ነው። በራሳቸው ሰው የተመራ ቆጣሪ ኤጀንሲ ለዚያውም ይህን ያሕል ከሞላ ጎደል ክርስቲያን የሆነ ሕዝብ የት እንደ ገባ እንደማይታወቅ በድፍረት አስታውቆ ሳለ ሙስሊሙ እንደ ተጭበረበረ መናገር አሳፋሪ ነው። ወሓቢዝም ምንም ዓይነት ሐፍረትና ይሉኝታ የማያውቅ ጭፍንና ጨለምተኛ ንፅረተ ዓለም ነው። ኃላፊነት የሚሰማው መንግሥት በሀገሪቱ ካለ ይህንን ግለሰብ መርዘኛ ምላሱን እንዲሰበብ እንዲያደርግልን እንጠይቃለን። ይህ ካልሆነ ግን የኢትዮዽያ ሕዝብ ሳይቆጠር ለዘላለም ሊቀር ነው። ከተቆጠረም እንዲህ ያሉ ማሰብያቸው የተናጋ ግለሰቦች ከፍተኛ ሁከት ሊፈጥሩ ይችላሉ። በሕግ አምላክ!

Открыть в Telegram
Просмотры10 700+575%к среднему
Пересылки—
Реакции98
Комментарии—
#1180Фото

ChatGPT ተጠቅማ እስልምና እውነት መሆኑን ለማረጋገጥ የምትሞክረዋን አውስትራሊያዊት ፈረንጅ አወቃችኋት? ሊሊ ጄይ ትባላለች። "ሀይ ቻት ጂፒቲ ከእስልምናና ከከርስትና የቱ ነው እውነት?" ብላ ትጠይቃለች። ማሽኑም "ያለ ምንም ጥርጥር እስልምና!" ብሎ ይመልስላታል። እንደዚያ ብሎ እንዲመልስ አስቀድማ ነግራው ነው ቪድዮ የምትቀዳው። እንዲህ ያሉ ቪድዮዎችዋን ሙስሊሞች በሚሊዮኖች እየተቀባበሉ በኢንተርኔቱ ዓለም ታዋቂ ሆና ነበር። ሴትዮዋ ቅንጡ ኑሮ የምትኖር ሲሆን "ሊሊ ጄይ ፋውንዴሽን" የተሰኘ በአፍሪካና በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ የተራቡ ህፃናትን እንደሚመግብ የሚናገር የእርዳታ ድርጅት ትመራለች። ድርጅቱ ከሙስሊሞች ዘንድ ብዙ ገንዘብ የሚላክለት ሲሆን በየ ጊዜውም እነዚህ ህፃናት እርዳታ ሲቀበሉ የሚያሳዩ ቪድዮዎችን ትለቃለች። ምን እንደ ተከሰተ ገምቱ? አብዛኞቹ የምትለቃቸው ቪድዮዎች በቻት ጂፒቲ የተቀናበሩ እንጂ እውነተኛ አይደሉም! የሙስሊሞች የዋህነት ይገርመኛል። ሃይማኖታቸውን እንደ ተቀበሉ በሚናገሩ እንዲህ ያሉ ብልጣብልጥ ሰዎች ሁሌ ይታለላሉ። እንዲህ ያለውን የዋህነት ከክፋት አልቆጥረውም። የተታለሉት ሃይማኖታቸውንና አምላካቸውን ስለሚወዱ ከቅንነታቸው የተነሳ እንጂ መታለል ፈልገው አይደለም። የአምላኩን ስም ከጠራችሁና ሃይማኖቱን ካሞገሳችሁ እንደ ሙስሊም በፍጥነት የሚታለል ሕዝብ የለም። ዛሬም በሀገራችን የሚገኙ ብዙ ሌቦችና አጭበርባሪዎች እስልምናን የተቀበሉ በመምሰልና ሃይማኖቱን በመከላከል ረገድ ፊታውራሪዎች በመሆን ሙስሊሙን ማሕበረሰብ ያልቡታል። እንዲህ ባሉ ጮሌዎች እንዳይታለል ሕዝባቸውን መጠበቅ የሙስሊም መሪዎች ሚና ቢሆንም እነርሱም በዚህ የተሳሳተ መንገድ ሃይማኖታቸውን ለማስፋፋት ካላቸው ጉጉት የተነሳ የነዚህ ኪስ አውላቂዎች ተባባሪ ሲሆኑ ይታያል። ሙስሊም ወገኖች ንቁ::

Открыть в Telegram
Просмотры9 270+485%к среднему
Пересылки—
Реакции131
Комментарии—
#1172Видео
Просмотры13 300+739%к среднему
Пересылки—
Реакции78
Комментарии—
#1171Превью ссылки
Просмотры10 700+575%к среднему
Пересылки—
Реакции69
Комментарии—
#1170Текст

Переслано из መጽሐፍ ቅዱሳዊ-Biblical

ውይይቱ ለምን ቀረ? (በአጭሩ ከቀደመው ውይይታቸው ውድቀት ሳያገግሙ ሌላ ዱላ ስላልፈለጉ ተሰርዟል😁) እስልምና ለቃሉ በጭራሽ የማይታመን ትውልድ እንደሚፈጥር ስላሳያችሁን እናመሰግናለን ማስታወቂያው ላይ እንደተመለከታችሁት ከሙስሊም ወገኖች ጋር ግንቦት 13 እና 15 ውይይት ነበረን፤ እነሱም ተስማምተው ለአወያዩም ተነግሮት ቀኑን እየጠበቅን ባለንበት የኔን ማስታወቂያ ተከትሎ ኢብራሂም የተባለው ተወያይ ፕሮግራሙ እንደራዘመ በቴሌግራም ቻናሉ አሳወቀ፤ ይህንን ሲያደርግ ግን ከኛ እውቅና ውጪ ነበር። ለዚህም ጥፋቱን አምኖ ይቅርታ ጠይቆናል (የድምጽ ማስረጃ አለ)። በቀጣይ ተሰብስብን ስለ ውይይቱ በምናወራበት ጊዜ ውይይቱ በተያዘለት ቀን እንዳይካሄድ ሲደረድሩ የነበረውን የምክንያት መአት ብትመለከቱ እናንተ ራሱ ታዝኑላቸዋላችሁ😁 ያም ሆኖ ግን ውይይቶቹ በአንድ ሳምንት ልዩነት እንዲደረጉ ባቀረቡት ሃሳብ ተስማምተን እሺ ባልናቸው ጊዜ አሁንም ለአንድ ወር ካልተራዘመ እንደማይወያዩ አሳወቁን😁 (ለእያንዳንዱ ላወራሁት ነገር ማስረጃ አለን) በህይወቴ ውይይት እንደጦር ሲፈራ ያየሁት Crew እነዚህ ሶስት ሙስሊሞችን ነው። ይገባናል ባለፈው የደረሰው ውርደት ባሁኑ እጥፍ ሆኖ እንዳይደገም በመስጋት ነው የሸሹት፣ ደግሞም አዎ ደፍረው ቢመጡ ኖሮ ነቢያቸውንም ቁርአናቸውንም ክደው በተመለሱ ነበር። እስልምና ለቃሉ በጭራሽ የማይታመን ትውልድ እንደሚፈጥር ስላሳያችሁን እናመሰግናለን

Открыть в Telegram
Просмотры9 320+488%к среднему
Пересылки—
Реакции113
Комментарии—