Кабинет
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)

ኢዜማ ኢትዮጵያ የሁሉም ዜጎች መብት የተከበረባት፣ ማኅበራዊ ፍትህ የሰፈነባት ሰላማዊ እና የበለፀገች ሀገር እንድትሆን የሚሠራ ሀገር አቀፍ ፓርቲ ነው።

Юзернейм
@ethzema
Категория
Политика
Страна
ЭфиопияЭфиопия
Подписчики2 887
Просмотров на пост, 7 дн.193−64,7% к пред. 7 дн.
ERR6,67 %за 7 дней

Средние просмотры поста по дням

По дню публикации

Показать таблицей
ДатаПросмотров на пост
3 нояб. 2026 г.691
9 нояб. 2026 г.712
13 нояб. 2026 г.546
26 нояб. 2026 г.192

Самые просматриваемые за месяц

  1. 01
    Просмотры807
    Пересылки—
    Реакции—
    Комментарии—
  2. 02

    ጥቅምት 24ን አንዘነጋም፤ ከድጋሚ አዙሪት ለመውጣት ጊዜው አልረፈደም!! የዛሬ 6 ዓመት በዚህች ቀን የኢትዮጵያ ሀገር ጠባቂ መከላከያ ሠራዊት በግፍ የተጨፈጨፈበት ዕለት ነው። የሀገርን ዳር ድንበር በመጠበቅና የሕዝብ ደኅንነት በመከላከል ላይ የነበረው ሠራዊት ከጀርባው ተወግቶ አውዳሚ ጦርነት ውስጥ መዘፈቃችን የሁላችንም አስከፊ ትውስታ ነው። የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) በክህደት ጥቃት ለተሰዋችሁ፣ ተከትሎ በመጣው ጦርነትም በጀግንነት ለተዋደቃችሁ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ምንግዜም ክብር አለው። ለኢትዮጵያዊነት ዓላማ ተዋድቃችኋልና ታሪክና ትውልድ ውለታችሁን በወርቅ ቀለም እንደሚጽፈው አንጠራጠርም። ዛሬም ክብር ለሀገር መከላከያ ሠራዊት እንላለን። ፓርቲያችን የጥቅሞት 24 የክህደት ቀንን ሲያስታውስ ተያያዥ ሀገራዊ ምክረሀሳቦችን ማመላከት ይወዳል። በተለይም የሀገርን ሉዓላዊነት የሚያናጋ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ የሚያደርሰው ውድመት በአንክሮ ሊታሰብበት ይገባል። ህወሓት የሥልጣን ጥማቱን ለማሳካት በሕዝብ ስቃይ ላይ ተረማምዶ የለኮሰው ጥቃት በትግራይ፣ በአማራና በአፋር ክልል በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ላይ ካደረሰው ቀጥተኛ ውድመት ባሻገር ሀገራችንን ዘርፈ ብዙ ማጥ ውስጥ ዘፍቋት እንደነበር የሚታወቅ እውነታ ነው። የዚሁ ቡድን ርዝራዦች እብደት (ክህደት) በዚህ ሳያበቃ ዛሬም ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር እጅና ጓንት እስከመኾን አድርሶታል። የዚኽን ቡድን የውድቀት ታሪክ በመድገም ከታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር ኢትዮጵያን የማፍረስ የጥፋት መረብ ውስጥ እየተሳተፉ የሚገኙ ኃይሎች መኖራቸው ሕዝብና ሀገርን ዋጋ እያስከፈለ ነው። "የመንግሥት ሥልጣንን መያዝ" በሚል ቁንፅል ዓላማ የሚጀመር የትጥቅ እንቅስቃሴ በጊዜ ካልተገታ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ፍላጎት ማስፈጸሚያ በመኾን ሀገራችንን የፍልሚያ ሜዳ ያደርጋታል። እየታዩ ያሉ የትጥቅ እንቅስቃሴዎች አዝማሚያ የሚያመለክተውም ይህንኑ እውነታ ነው። በሕዝብ ተቆርቋሪነት ስም የሚደረጉ የትጥቅ እንቅስቃሴዎች በታሪካችን ያስከተሉት ውድመት፣ ማኅበራዊ መቃቃር እና የዳር ድንበር መደፈር ዛሬም ትምህርት አልተወሰደበትም። ዛሬም በሕዝብ ስም ሕዝብና ሀገርን ለተራዘመ መከራ የሚያጋልጡ ተግባራት እንደ መደበኛ የፖለቲካ ሥራ እየተወሰዱ ነው። ፓርቲያችን ኢዜማ በትጥቅ የተደገፈ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ሀገራችን ውድቀቷን በሚመኙላት ታሪካዊ ጠላቶች ወጥመድ ውስጥ እያስገባት እንደኾነ በመረዳት፤ ታጥቃችሁ የምትንቀሳቀሱ ኃይሎች ወደ ሰላማዊ የፖለቲካ መድረክ እንድትመለሱ ጥሪ ያቀርባል። መንግሥት በማንኛውም ሁኔታ ሀገራችን ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶችን ለማክሸፍ የተጀመረው የሀገር መከላከያ ሠራዊትን ዝግጁነትና ብቃት የማጠናከር ተግባር አበክሮ እንዲቀጥልበት፤ ከዚህ በመለስ የፖለቲካ አውዱ ከጠመንጃ ማንገት እንዲላቀቅ ለሰላማዊው የፖለቲካ ምሕዳር እርባና ያላቸውን ውይይት፣ ገለልተኛ ተቋማት ግንባታ እና የመሣሠሉት ላይ በቁርጠኝነት እንዲሠራ እንጠይቃለን። ማኅበረሰቡም የትጥቅ እንቅስቃሴ እያደረሰበት ያለውን መከራ በመገንዘብ ኹሉም የፖለቲካ ኃይሎች በሰላማዊ መንገድ እንዲንቀሳቀሱ ጫና ሊያደርግ ይገባል እንላለን። በመጨረሻም፤ የጥቅምት 24 የክህደት ጥቃት የተለኮሰበትን ዐቢይ ምክንያት መርምሮ ለትውልድ የሚበጅ ዓላማ አንግቦ መሥራት፣ ፖለቲካችንም በዜግነት መሠረት ላይ እንዲቆም መልዕክታችንን እናስተላልፋለን። ጥቅምት 24/2019 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ( #ኢዜማ )

    Фото
    Просмотры691
    Пересылки—
    Реакции—
    Комментарии—
  3. 03

    የ #ኢዜማ ዕሴቶች 1. ተጠያቂነት (Accountability) የኢዜማ አሠራሮች ሁሉ ያልተማከሉ፣ ግልጽነት እና ተጠያቂነትን በሚያረጋግጥ ሁኔታ ይከወናሉ። ኃላፊነትን በአግባቡ መወጣት እና አጥርቶ መሥራት የኢዜማ አባላት መገለጫ ይሆናል። 2. ሠላማዊነት 👉 ኢዜማ ሠላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴን ብቸኛው የሥልጣን መያዣ መንገድ ነው ብሎ ያምናል። 👉 ኢዜማ ማንኛውንም አመለካከት በኃይል በሌሎች ላይ ለመጫን የሚደረጉ አካሄዶችን ይቃወማል፤ ዜጎች የመሰላቸውን አቋም መደገፍና በሠላማዊ መንገድ መቃወም አይከለክልም። 3. ትብብር ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር ይሰራል፤ በፓርቲው ውስጥ የቡድን ሥራን ያበረታታል። 4. ውይይት 👉 ኢዜማ በሀገራችን ከዚህ በፊት የተፈጠሩ የፖለቲካ ቁርሾዎች በብሔራዊ እርቅ መድረክ ሊፈቱ ይገባል የሚል ፅኑዕ እምነት አለው። ይህ የእርቅ መድረክ በአቋራጭ ሥልጣን መያዣም ሆነ ሌሎች የፖለቲካ ጥቅሞች ማግኛ እንዳይሆን አበክሮ ይሠራል። 👉 ኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ ታሪክ ያላት ሀገር እንደመሆኗ መጠን መጪው ትውልድ በሀገራችን ኢትዮጵያ የተፈጠሩ ማንኛቸውም ታሪካዊ ክስተቶች ለትምህርታዊ ግብዓት ከመጠቀም ውጭ ለቂም በቀልና ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨት እንዳይውል አስፈላጊውን ያደርጋል፤ የሲቪል ማኅበራትና የትምህርት ተቋማት የውይይት መድረኮች እንዲያዘጋጁ ያበረታታል። 👉 ኢዜማ የሚወስዳቸውን የፖለቲካ አቋሞች በይፋ ለህዝቡ ያሳውቃል። የፖለቲካ ልዮነቶች ለቀጣይ ውይይት እንጂ ለግጭት መንስዔ እንዳይሆኑ አበክሮ ይሠራል። 5. ልህቀት 👉 ኢዜማ ሀገራችን በርካታ ችግሮች መፍትሄ ማግኘት የሚችሉት ልህቀትን መመዘኛ ባደረገ የሥራ ውጤት መለኪያ ብቻ ነው የሚል ጠንካራ አቋም አለው። 👉 ኢዜማ በአሠራር ልህቀት ለሚያሳዩ አባላት እንዲሁም የፓርቲው ልዩ ልዩ አሃዶች እውቅናን ይስጣል፤ ይሸልማል። በአጠቃላይ በማኅበረሰብ ውስጥም የዚህ ዓይነት የማበረታቻ አሠራር እንዲሰርጽ አስፈላጊውን ጥረት ያደረጋል።

    Фото
    Просмотры617
    Пересылки—
    Реакции—
    Комментарии—
  4. 04
    Просмотры546
    Пересылки—
    Реакции—
    Комментарии—

Новые посты

#5685Фото
Просмотры102−80%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#5684Фото
Просмотры235−54%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
5 ч170
9 ч235
  1. Через 6 часов170
  2. Всего сейчас235
#5683Видео
Просмотры215−58%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#5681Фото
Просмотры807+59%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#5680Фото

የ #ኢዜማ ዕሴቶች 1. ተጠያቂነት (Accountability) የኢዜማ አሠራሮች ሁሉ ያልተማከሉ፣ ግልጽነት እና ተጠያቂነትን በሚያረጋግጥ ሁኔታ ይከወናሉ። ኃላፊነትን በአግባቡ መወጣት እና አጥርቶ መሥራት የኢዜማ አባላት መገለጫ ይሆናል። 2. ሠላማዊነት 👉 ኢዜማ ሠላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴን ብቸኛው የሥልጣን መያዣ መንገድ ነው ብሎ ያምናል። 👉 ኢዜማ ማንኛውንም አመለካከት በኃይል በሌሎች ላይ ለመጫን የሚደረጉ አካሄዶችን ይቃወማል፤ ዜጎች የመሰላቸውን አቋም መደገፍና በሠላማዊ መንገድ መቃወም አይከለክልም። 3. ትብብር ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር ይሰራል፤ በፓርቲው ውስጥ የቡድን ሥራን ያበረታታል። 4. ውይይት 👉 ኢዜማ በሀገራችን ከዚህ በፊት የተፈጠሩ የፖለቲካ ቁርሾዎች በብሔራዊ እርቅ መድረክ ሊፈቱ ይገባል የሚል ፅኑዕ እምነት አለው። ይህ የእርቅ መድረክ በአቋራጭ ሥልጣን መያዣም ሆነ ሌሎች የፖለቲካ ጥቅሞች ማግኛ እንዳይሆን አበክሮ ይሠራል። 👉 ኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ ታሪክ ያላት ሀገር እንደመሆኗ መጠን መጪው ትውልድ በሀገራችን ኢትዮጵያ የተፈጠሩ ማንኛቸውም ታሪካዊ ክስተቶች ለትምህርታዊ ግብዓት ከመጠቀም ውጭ ለቂም በቀልና ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨት እንዳይውል አስፈላጊውን ያደርጋል፤ የሲቪል ማኅበራትና የትምህርት ተቋማት የውይይት መድረኮች እንዲያዘጋጁ ያበረታታል። 👉 ኢዜማ የሚወስዳቸውን የፖለቲካ አቋሞች በይፋ ለህዝቡ ያሳውቃል። የፖለቲካ ልዮነቶች ለቀጣይ ውይይት እንጂ ለግጭት መንስዔ እንዳይሆኑ አበክሮ ይሠራል። 5. ልህቀት 👉 ኢዜማ ሀገራችን በርካታ ችግሮች መፍትሄ ማግኘት የሚችሉት ልህቀትን መመዘኛ ባደረገ የሥራ ውጤት መለኪያ ብቻ ነው የሚል ጠንካራ አቋም አለው። 👉 ኢዜማ በአሠራር ልህቀት ለሚያሳዩ አባላት እንዲሁም የፓርቲው ልዩ ልዩ አሃዶች እውቅናን ይስጣል፤ ይሸልማል። በአጠቃላይ በማኅበረሰብ ውስጥም የዚህ ዓይነት የማበረታቻ አሠራር እንዲሰርጽ አስፈላጊውን ጥረት ያደረጋል።

Открыть в Telegram
Просмотры617+22%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#5679Фото

ጥቅምት 24ን አንዘነጋም፤ ከድጋሚ አዙሪት ለመውጣት ጊዜው አልረፈደም!! የዛሬ 6 ዓመት በዚህች ቀን የኢትዮጵያ ሀገር ጠባቂ መከላከያ ሠራዊት በግፍ የተጨፈጨፈበት ዕለት ነው። የሀገርን ዳር ድንበር በመጠበቅና የሕዝብ ደኅንነት በመከላከል ላይ የነበረው ሠራዊት ከጀርባው ተወግቶ አውዳሚ ጦርነት ውስጥ መዘፈቃችን የሁላችንም አስከፊ ትውስታ ነው። የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) በክህደት ጥቃት ለተሰዋችሁ፣ ተከትሎ በመጣው ጦርነትም በጀግንነት ለተዋደቃችሁ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ምንግዜም ክብር አለው። ለኢትዮጵያዊነት ዓላማ ተዋድቃችኋልና ታሪክና ትውልድ ውለታችሁን በወርቅ ቀለም እንደሚጽፈው አንጠራጠርም። ዛሬም ክብር ለሀገር መከላከያ ሠራዊት እንላለን። ፓርቲያችን የጥቅሞት 24 የክህደት ቀንን ሲያስታውስ ተያያዥ ሀገራዊ ምክረሀሳቦችን ማመላከት ይወዳል። በተለይም የሀገርን ሉዓላዊነት የሚያናጋ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ የሚያደርሰው ውድመት በአንክሮ ሊታሰብበት ይገባል። ህወሓት የሥልጣን ጥማቱን ለማሳካት በሕዝብ ስቃይ ላይ ተረማምዶ የለኮሰው ጥቃት በትግራይ፣ በአማራና በአፋር ክልል በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ላይ ካደረሰው ቀጥተኛ ውድመት ባሻገር ሀገራችንን ዘርፈ ብዙ ማጥ ውስጥ ዘፍቋት እንደነበር የሚታወቅ እውነታ ነው። የዚሁ ቡድን ርዝራዦች እብደት (ክህደት) በዚህ ሳያበቃ ዛሬም ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር እጅና ጓንት እስከመኾን አድርሶታል። የዚኽን ቡድን የውድቀት ታሪክ በመድገም ከታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር ኢትዮጵያን የማፍረስ የጥፋት መረብ ውስጥ እየተሳተፉ የሚገኙ ኃይሎች መኖራቸው ሕዝብና ሀገርን ዋጋ እያስከፈለ ነው። "የመንግሥት ሥልጣንን መያዝ" በሚል ቁንፅል ዓላማ የሚጀመር የትጥቅ እንቅስቃሴ በጊዜ ካልተገታ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ፍላጎት ማስፈጸሚያ በመኾን ሀገራችንን የፍልሚያ ሜዳ ያደርጋታል። እየታዩ ያሉ የትጥቅ እንቅስቃሴዎች አዝማሚያ የሚያመለክተውም ይህንኑ እውነታ ነው። በሕዝብ ተቆርቋሪነት ስም የሚደረጉ የትጥቅ እንቅስቃሴዎች በታሪካችን ያስከተሉት ውድመት፣ ማኅበራዊ መቃቃር እና የዳር ድንበር መደፈር ዛሬም ትምህርት አልተወሰደበትም። ዛሬም በሕዝብ ስም ሕዝብና ሀገርን ለተራዘመ መከራ የሚያጋልጡ ተግባራት እንደ መደበኛ የፖለቲካ ሥራ እየተወሰዱ ነው። ፓርቲያችን ኢዜማ በትጥቅ የተደገፈ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ሀገራችን ውድቀቷን በሚመኙላት ታሪካዊ ጠላቶች ወጥመድ ውስጥ እያስገባት እንደኾነ በመረዳት፤ ታጥቃችሁ የምትንቀሳቀሱ ኃይሎች ወደ ሰላማዊ የፖለቲካ መድረክ እንድትመለሱ ጥሪ ያቀርባል። መንግሥት በማንኛውም ሁኔታ ሀገራችን ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶችን ለማክሸፍ የተጀመረው የሀገር መከላከያ ሠራዊትን ዝግጁነትና ብቃት የማጠናከር ተግባር አበክሮ እንዲቀጥልበት፤ ከዚህ በመለስ የፖለቲካ አውዱ ከጠመንጃ ማንገት እንዲላቀቅ ለሰላማዊው የፖለቲካ ምሕዳር እርባና ያላቸውን ውይይት፣ ገለልተኛ ተቋማት ግንባታ እና የመሣሠሉት ላይ በቁርጠኝነት እንዲሠራ እንጠይቃለን። ማኅበረሰቡም የትጥቅ እንቅስቃሴ እያደረሰበት ያለውን መከራ በመገንዘብ ኹሉም የፖለቲካ ኃይሎች በሰላማዊ መንገድ እንዲንቀሳቀሱ ጫና ሊያደርግ ይገባል እንላለን። በመጨረሻም፤ የጥቅምት 24 የክህደት ጥቃት የተለኮሰበትን ዐቢይ ምክንያት መርምሮ ለትውልድ የሚበጅ ዓላማ አንግቦ መሥራት፣ ፖለቲካችንም በዜግነት መሠረት ላይ እንዲቆም መልዕክታችንን እናስተላልፋለን። ጥቅምት 24/2019 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ( #ኢዜማ )

Открыть в Telegram
Просмотры691+36%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#5677Текст

የሰላማዊ ዜጎች ግድያን በወቅታዊ ጉዳይ መሸፈን የሞራል ውድቀት ነው!! የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ከምሥረታው አንስቶ ባለፉት 7 ዓመታት መንግሥት ዋናው ኃላፊነቱ የሆነውን የዜጎችን ሰላምና ደኽንነት እንዲያስጠብቅ በተደጋጋሚ የጠየቀባቸው መግለጫዎች በሌሎች ጉዳዮች ላይ ካወጣቸው አጠቃላይ መግለጫዎች ከፍተኛውን ቁጥር ይይዛሉ። እነዚህ መግለጫዎች ዜጎች ለከፍተኛ የደህንነት ስጋት እየተጋለጡ እንደሆነ እና የሥጋት ቦታዎቹም ተመሣሣይ እንደሆኑ የሚጠቁሙ ናቸው። የጥቃቱ ሰለባ ዜጎች፣ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች እና የግል መገናኛ ብዙኃን ለተከታታይ ዘመናት ይሄንኑ የንፁሀን ግድያ ሲዘግቡ፣ የመፍትሔ አቅጣጫም ሲያመላክቱ ቆይተዋል። ኢዜማ እንደ አንድ ተፎካካሪ ፓርቲ እና ውሱን የመንግሥት ኃላፊነት ቦታዎች ላይ እንደሚያገለግል አካል ይኽንን መሠል ችግሮች የመከሰታቸውን ምክንያቶች ምን እንደሆኑ አጥንቶ መፍትሔ የሚላቸውን ሐሣቦች ባለፉት ዓመታት ሲጠቁም ቆይቷል። ሆኖም ኃላፊነት ያለበት የመንግሥት አካል የዜጎችን ሕይወት መታደግ ባለመቻሉ ምክንያት የዜጎች ነፍስ በተቀጠፈ ቁጥር መራር ቁጭት እንደሚፈጥርበት ለመግለጽ ይወዳል። የመንግሥት የዜጎችን ደህንነት በቅጡ አለመከላከል ያልተፈታ ቅኔ ቢሆንም፤ እነዚህ የዜጎችን ሕይወት እየቀጠፉ የሚገኙ የደህንነት ችግሮች ታጣቂ ኃይሎች ብቻቸውን የሚፈጽሙት ሳይሆን በመንግሥት ውስጥ ያሉ ኃላፊዎችም ጭምር የሚሣተፉበት መሆኑ የበለጠ ጉዳዩን የሚያመረቅዝ ቁስል ያደርገዋል። በዚህም ላይ በሕዝብ ግብር የሚተዳደሩት መገናኛ ብዙኃን ለሞታቸው ምክንያቱ ምንድነው የሚለውን እና እንደ ሚዲያ ተቋም የሚመለከተውን አካል ለምን ብሎ መጠየቅ ቢቀር እንኳ መሞታቸውን ለመንገር እና ኃዘናቸውን ለመግለፅ ዳተኛ መሆናቸውን ስንመለከት የደረስንበት የሞራል ዝቅጠት ምን ያህል እንደወረደ ያሳየናል። ለአብነትም የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬት (EBC) ባለፈው ሳምንት ሰኞ ዕለት በአርሲ ስለተገደሉ ዜጎች ዝምታን የመረጠ ሲሆን ጥቃቱ በተፈፀመበት ሳምንት አርሲን ጠቅሶ የሠራው ዘገባ የነገሌ አርሲ እግርኳስ ቡድንን የጨዋታ ውጤት ነበር፤ በአርሲ ባለፉት ዓመታት ተመሳሳይ የዜጎችን ሕይወት የቀጠፈ ጥቃት የነበረ ቢሆንም የመንግሥት ኃላፊዎች በአንድ መንገድ ተግባቦት (One way communication) መግለጫዎች ሲሰጡ ብቻ ከመዘገብ ያለፈ ሚና ሲወጡ አይታዩም። እነዚህ የሕዝብ መገናኛ ብዙኃን ተቋማት ከሀገር ውጭ በሌሎች የውጭ ዜጎች ላይ የሚደርሱ ሞት እና አደጋዎችን ተከታትለው እየሰሩ በኢትዮጵያዊያን ዜጎች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ለመዘገብ ዳተኝነት ማሳየታቸው ለዜጎቻችን ያላቸውን ንቀት እንዲሁም ከሞራልና ከሙያዊ ግዴታ በወጣ መልኩ የመንግሥት የፕሮፖጋንዳ መሣሪያ ብቻ ሆነው ማገልገልን እንደመረጡ ያለሀፍረት አሳይተዋል። ይሕ በእንዲህ እንዳለ በቅርብ ቀናት በተደጋጋሚ በአርሲ የተለያዩ አከባቢዎች ማንነትን መሠረት አድርገው የተፈፀሙ ጥቃቶች፣ በጋምቤላ እና ሞያሌ የተከሰቱ የእርስ በእርስ ግጭቶች ለዜጎች ሕይወት ማለፍ፣ መፈናቀል እንዲሁም ንብረት መውደም ምክንያት የሆኑ ሲሆን ለእነዚህም ዋነኛ ተጠያቂው አካል የዜጎችን ሰላምና ደህንነት የማስከበር ኃላፊነት ያለበት መንግሥት መሆኑን እየገለፅን፤ 1) የመንግሥት ኃላፊዎች በተደጋጋሚ ለሚፈጠሩ ችግሮች ጊዜያዊ አጀንዳዎችን ምክንያት ከማድረግ እንዲቆጠቡ! የመንግሥት ባለሥልጣናት ችግሮቹ ላለፉት ዓመታት በተደጋጋሚ ሲፈፀሙ እንዳልነበረ በሚመስል መልኩ ወቅታዊ ጉዳዮችን ተጠቅሞ እራስን ከተጠያቂነት ነፃ ማድረግ ፍፁም ተቀባይነት የሌለው ኢ-ሞራላዊ ተግባር ነው። ከሰሞኑ በአርሲ ለተፈፀመው ጥቃት በኦሮሚያ ክልል ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት የተሠጠው መግለጫም ለዚህ ጥሩ ማሣያ ነው። ይህ ዓይነት የመንግሥት ተግባር ዜጎች መንግሥት ላይ የበለጠ አመኔታን እንዲያጡ ከማድረግ የዘለለ ጥቅም የሌለው መሆኑን ተረድቶ ለማኅበረሰቡ የሚደርሱ መረጃዎች እውነታ ላይ የተመሠረቱ እና በእርግጥም ለችግሮቹ ምክንያት የሆኑትን የለየ እንዲሁም መፍትሔ የሆኑ የተፈፀሙ፣ ሊፈፀሙ የታሰቡ እና በምን ያህል ጊዜ ይኽንን ነገር ለማስተካከል እንደታሠበ መግለጽ ተገቢ መሆኑን ተረድተው ከዚህ ዓይነት ተግባራቸው እንዲቆጠቡ፤ 2) የተጠና ችግሩን የሚመጥን መፍትሔ ይሰጥ መንግሥት ለዚህ ዓይነት ተደጋጋሚ ጥቃት ምክንያት የሆኑትን ችግሮች የደህንነት መረጃዎችን መሠረት ባደረገ ቅድመ ጥንቃቄና መከላከል እንዲሁም የአጭር ጊዜ እና ዘለቄታዊ መፍትሔ በመስጠት ዳግም ጥቃቶች እንዳይከሰቱ እንዲያደርግ። የጥቃት ስጋት ያለባቸውን አካባቢዎች እና የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች በቶሎ በማይደርሱባቸው አከባቢዎች ማኅበረሰቡን በማደራጀት ራሱን እንዲከላከል በመረጃና በሎጀስቲክስ እንዲያግዝ፤ 3) እውነተኛ ተጠያቂነትን ይስፈን ይህ ዓይነት ተደጋጋሚ ጥቃት ሲከሰት ከኃላፊነታቸው ያጎደሉ ወይም ሥልጣናቸውን አለአግባብ ተጠቅመው ዜጎችን ለጥቃት ያጋለጡት የመንግሥት ኃላፊዎችን ተጠያቂ እንዲያደርግ እና በይፋ ለሕዝብ እንዲያሣውቅ፤ ይህንን ከማድረግ ይልቅ የሥልጣን ሽግሽጎችን ማድረግ ባለሥልጣናቱ የሚያጠፏቸውን የጥፋት ዓይነት ከመለዋወጥ የዘለለ መፍትሔ የሌለው መሆኑ ሊታወቅ ይገባል። 4) ተቋማት ኃላፊነታቸውን በቅጡ ይወጡ 4.1 የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች የደረሰውን ጥቃት በገለልተኝነት በማጣራት ለቆማችሁለት የሰብዓዊ መብት መከበር ሚናችሁን እንድትወጡ፤ 4.2 የሕዝብ መገናኛ ብዙኃን የሚዲያ ምንነትን በሚመጥን መልኩ መንግሥትን ተጠያቂ በማድረግ ዜጎች ላይ ተመሣሣይ ጥቃት እንዳይፈፀም ድምፅ እንድትሆኑ ስንል ጥሪ እናቀርባለን። በእነዚህ በማንነት ላይ በተቃጡ ጥቃቶች እና የእርስ በእርስ ግጭቶች ሕይወታቸውን ላጡ ዜጎች የተሰማንን ጥልቅ ሐዘን እየገለጽን፤ ለቤተሰቦቻቸውና ለሕዝቡ መፅናናትን እንመኛለን። የአንድ ዜጋ ደኅንነት ያልተከበረባት ሀገር የሁሉም ዜጎች ክብር ስለማይጠበቅባት፤ ለዜጎች ሰብዓዊ ክብር ሁሉም ኢትዮጵያዊ በጋራ እንዲቆም አደራ እንላለን። የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ( #ኢዜማ ) ጥቅምት 17/2019 ዓ.ም.

Открыть в Telegram
Просмотры922+82%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#5670Фото

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በሥራ አስፈፃሚ ውስጥ በተለያየ ደረጃ በአመራርነት ያገለገሉ የፓርቲውን ኃላፊዎች ላበረከቱት አስተዋፅኦ የዕውቅና መርኃግበር እና ሽኝት አደረገ። ይሕ ዕውቅና ፓርቲውን ከምሥረታው አንስቶ እስካለፈው ዓመት 2018 ዓ.ም. በከፍተኛ ልህቀት ፓርቲውን በመሪነት እንዲሁም በፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ መሠረት የተቀበሉትን የትምሕርት ሚኒስቴር ኃላፊነት በሚታይ ብቃት እየመሩ ያሉት ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ በሥራ አስፈፃሚ አባልነት እና በተለያዩ ኮሚቴዎች ከፍተኛ ሚና ሲጫወቱ የነበሩት እንዲሁም በተመሣሣይ በጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ መሠረት የወሰዱትን የተለያዩ የመንግሥት ኃላፊነቶች በብቃት እየመሩ ያሉት ግርማ ሰይፉ፣ በፖሊሲ ምርምር እና ጥናት መምሪያ ኃላፊነት እንዲሁም ሌሎች ጊዜያዊ ኮሚቴዎች ከፍተኛ አስተዋፆኦ ያደረጉት ዶ/ር ዳዊት በለው፣ በሴቶች መምሪያ ኃላፊነት እና ድርጅት ጉዳይ መምሪያ ቋሚ ኮሚቴ ውስጥ ከፍተኛ ግልጋሎት የሰጡት እመቤት ቢራራ እና በወጣች መምሪያ ኃላፊነት ጠንካራ ሥራ የሠሩት ቃልኪዳን ከበደ ናቸው። አመራሮቹ ከዚህም በኋላ በፓርቲው ደንብ የተቀመጠውን የአባልነት ግዴታዎቻቸውን የሚወጡ ሲሆን በተጨማሪም በፓርቲው የሚሠጧቸውን ኃላፊነቶች ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል። #ኢዜማ #ezema #ኢትዮጵያ #Ethiopia

Открыть в Telegram
Просмотры1 130+123%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—

Все посты

Связи