🕯️🕯️🕯️ ህዳር 15 🕯️🕯️🕯️ 🪷 መስፍኑም ሚናስ ሆይ ለጣዖታት መስዋት አቅርብ አከብርሃለው አለው፤ ቅዱስ ሚናስም... እኔ ግን የሚጠብቀኝን ክብር እቀበል ዘንድ ዝግጁ ነኝ የእርሱ ሊያደርገኝ አገልጋዩ እሆናለሁ በሰማያት ክብራችሁ ብዙ ነው ተብሎ እንደተጻፈ (ማቴ ፭ ፥፲፪) የአንተ ክብር ግን በእግዚአብሔር ዘንድ ኃላፊ ከንቱ ነው፤ (መጽ.መክ. ፩÷፪-፱) 🪷 በእግዚአብሔር ማመን ስሙንም ማክበር ለጌትነቱ መገዛት እስከ ዘለአለሙ ሕይወትና ልዩ ክብርን ወራሽ ያደርጉናል፤ (መጽ.ጥበብ ፲፭ ÷ ፩- ፭) 🌿 ገድለ ቅዱስ ሚናስ እንኳን ለቅዱስ ሚናስ የዕረፍቱ መታሰቢያ አመታዊ ክብረ በዓል እንዲሁም ለጾመ ነብያት አደረሳችሁ! እግዚአብሔር እንደ ቅዱስ ሚናስ ታማኝ እና ጽኑ አገልጋዮች ያድርገን፤ መልካም ጾም መልካም ዕለት
Открыть в TelegramПосты канала Ethiopian Orthodoxs Daily
በዓለ ሢመቱ ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ‹ሚካኤል ሥዩም በዲበ ኃይላት፤ በኃይላት ላይ የተሾምክ ሚካኤል› ሲል ያመሰገነው ቅዱስ ሚካኤል በኃይላት መላእክት ላይ የተሾመ ሊቀ መላእክት እንደመሆኑ በዓለ ሢመቱ ኅዳር ፲፪ ቀን በመላው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በድምቀት ይከበራል፡፡ (መጽሐፈ አክሲማሮስ) ኃይላት የተባሉት መላእክትም ሰዎች በዓለም ፈተና ውስጥ ሆነው ሰይጣን ሊያደክማቸው ሲፈልግ ኃይልን ብርታትን የሚሰጡ፣ ይህን ዓለም ንቀው በበርሃ ወድቀው ከሥጋ ምኞት ጋር የሚጋደሉትን፣ በከተማም እየኖሩ መንፈሳዊ ትሩፋት የሚያደርጉትን ደግሞ የሚያበረቱ ናቸው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ በመልእክቱ ‹እርሱም ወደ ሰማይ ያረገ እግዚአብሔርም ተቀምጦ ያለ መላእክትና ሥልጣናት ኃይላትም የተገዙለት ነው…› ሲል ‹ኃይላት› በማለት ያነሣቸው በኢዮር አራተኛይቷ ከተማ የሚኖሩትን ነው፡፡ በእነዚህ ላይ እግዚአብሔር ቅዱስ ሚካኤልን አለቃቸው አድርጎ ሾሞታል፡፡ (፩ኛጴጥ.፫፥፳፪) የቅዱስ ሚካኤል ሢመት በነገደ መላእክት ላይ ብቻም ግን አይደለም፤ የእግዚአብሔር ሕዝብ በሆኑት ላይም ጭምር ነው፡፡ ኃያሉ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል የስሙ ትርጓሜ በዕብራይስጥ ‹‹እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው!›› ማለት እንደሆነ ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠቅሳሉ፤ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በመዝገበ ቃላት መጽሐፋቸው ላይ እንዳሰፈሩት ደግሞ የስሙን ፊደላት በመተንተን እንዲህ ተርጉመውታል፤ ሚ-መኑ፣ ካ-ከመ፣ ኤል-አምላክ፤ ‹‹መኑ ከመ አምላክ፤ እንደ አምላክ ማን ነው!›› (መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ) የሰማይ ሠራዊት ሁሉ አለቃቸው ለፍጥረት ሁሉ የሚማልድ ይህ ኃያል መልአክ ቅዱስ ሚካኤል በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር ሕዝብ የተባሉትን እስራኤል ዘሥጋን ሲረዳና ሲጠብቅ እንደነበረ ተጽፎልን እናገኛለን፡፡ ለምሳሌ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ለኢያሱ በኢያሪኮ ምድረ በዳ እንደተገለጠለት ‹‹… ዐይኑን አንሥቶ ተመለከተ፤ እነሆም፥ የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ ሰው በፊቱ ቆሞ አየ፤ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ፥ “ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ?” አለው፡፡ እርሱም “እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ነኝ፤ አሁንም ወደ አንተ መጥቼአለሁ፡፡” ሲል ተናግሯል፡፡ (ኢያ.፭፥፲፫) እግዚአብሔር አምላክ ሕዝበ እስራኤልን ከግብጽ ባርነት ነፃ ሲያወጣቸው ይመራቸው የነበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ነበር፡፡ ‹‹ በመንገድህ ይጠብቅህ ዘንድ፥ ወዳዘጋጀሁልህም ስፍራ ያገባህ ዘንድ፥ እነሆ ፥እኔ መልአኬን በፊትህ እልካለሁ›› እንዲል፤ ሹመቱ በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይም በመሆኑ ስለ እነርሱ ከእግዚአብሔር ምሕረትን ይለምንላቸው ነበር፡፡ (ዘፀአት.፳፫፥፳) ነገር ግን ኃጢአት ሲሠሩ እግዚአብሔር ኃጢአተኞችን ይቀጣልና ሕዝቡን ‹‹ራስህን ጠብቅ፤ ስማው፤ እንቢም አትበለው፤ ስሜ በእርሱ ስለሆነ ይቅር አይልምና›› ብሎ አስጠንቅቋቸው ነበር፤ ይህም ቅዱስ ሚካኤል በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ መሾሙን ያስረዳናል፡፡ (ዘፀ.፳፫፥፳፩) ቅዱስ ገብርኤል በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ቅዱስ ሚካኤል ስለመሾሙ ሲመሰክር ‹‹በእውነት በመጽሐፍ የተጻፈውን እነግርሃለሁ፤ በዚህም ነገር ከአለቃችሁ ከሚካኤል በቀር የሚረዳኝ ማንም የለም›› ብሎአል፡፡ ስለዚህም ለኢያሱ የተገለጠውና እስራኤላውያንንም የመራው መልአክ ቅዱስ ሚካኤል መሆኑን እንረዳለን፡፡ (ዳን.፲፥፳፩) የቅዱስ ሚካኤል አማላጅነት በሐዲስ ኪዳንም እንደነበር ይህ ነቢይ በትንቢቱ ‹‹በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ ሚካኤል ይነሣል›› በማለት ተናግሮለታል፡፡ ስለዚህም ቅዱስ ሚካኤል እኛን ከሰይጣን አሽክላና ወጥመድ ይጠብቀንና በጸሎቱ በእግዚአብሔር ፊት ይቆምልን ዘንድ በእኛም ላይ ሹም ነው፡፡ ምክንያቱም እኛ የእግዚአብሔር ሕዝቦችና የርስቱ ወራሾች ነንና፡፡ (ዳን.፲፪፥፩) በመጽሐፈ ስንክሳርም ተመዝግቦ እንደምናኘው ቅዱስ ሚካኤል በየወሩ በዐሥራ ሁለት ቀን ለመታሰቢያው በዓል ተሠርቶለታል፤ እርሱ ስለ እኛ የምድሩን ፍሬ ይባርክልን ዘንድ ዝናሙም በጊዜው እንዲወርድልን የወንዙንም ውኃ እንዲመላልን ነፋሱንም የምሕረት ነፋስ እንዲያደርግልን ሁሉንም የተስተካከለ እንዲያደርግልን ወደ እግዚአብሔር በጸሎት ይማልዳልና፡፡ (ስንክሳር ኅዳር ፲፪) ስለሆነም በኃጢአት ባርነት ተይዘን በችግር እና በመከራ ውስጥ ተዘፍቀን ለምንኖር ሰዎች ስለ ሕዝበ እስራኤል በእግዚአብሔር ፊት የቆመው ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ለእኛም ያማልደንና ተራዳኢ ይሆነን ዘንድ በጸሎት እንማጸነው። አምላካችን እግዚአብሔርም የምሕረት ፊቱን ወደ እኛ በመመለስ በጸብና በጦርነት ምትክ ፍቅርን፣ ሰላምንና መግባባትን፤ በመለያየት ምትክ አንድነትን እንዲሰጠን በቅዱስ ሚካኤል ስም እንለምን። የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል አማላጅነትና ተራዳኢነት አይለየን፤ አሜን፡፡ ምንጭ፤ መጽሐፈ አክሲማሮስ፣ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ በአለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ፣መጽሐፈ ስንክሳር ዘወርኀ ኅዳር
Открыть в Telegram#ኅዳር_6 #ደብረ_ቁስቋም ኅዳር ስድስት በዚህች ዕለት ክብርት እመቤታችን ከተወደደ ልጇ ጋር ከስደት በሚመለሱበት ጊዜ ደብረ ቁስቋም ገብተው ካገኛቸው ድካም ዐረፉ፡፡ አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች ክብርት እመቤታችን ከስደት በተመለሰች ጊዜ እንዲህ ሆነ፡- የብርሃን እናቱ ክብርት እመቤታችን ልጇን ይዛ ከእነ ዮሴፍ ጋር ወደ ምድረ ግብፅ ስትሰደድ ግብፅ ደርሰው በዚያ ቢቀመጡም ነገርን ግብፅ አልተመቸቻውም፡፡ ሕዝቡም በሰላም አልተቀበላቸውም፡፡ እንዲያውም በምድረ ግብፅ ብዙ ተሠቃይተዋል፡፡ ከግብፅም ተነሥተው ወደ ኢትዮጵያ በመጡ ጊዜ ግን ኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉ በሰላምና በፍቅር ተቀበላቸው፡፡ ከመንገዱና ከርሃብ ጥሙ ጽናት የተነሣ እጅግ ደክማለችና የኢትዮጵያ ሰዎች እመቤታችንን አይተው እጅግ አዘኑላት፡፡ ‹‹ይህችስ የነገሥታት ዘር ትመሥላለች ነገር ግን አንዳች ችግር አጋጥሟት ተሰዳ ወደ ሀገራችን መጥታለች..›› ብለው እንክብካቤን አደረጉላት፡፡ እግራቸውን አጥበው በክብር ማረፊያዎች ላይ አሳረፏቸው፡፡ መልካም መስተንግዶም አደረጉላቸው፡፡ እመቤታችንም ከድካሟ ካረፈች በኋላ ሀገሪቱን በእጅጉ ወደደቻትና የተወደደ ልጇን ‹‹ይህን ሀገርና ሕዝቧን በመላ ወድጃቸዋልሁና በዚህ እስከ መጨረሻው እንኑር›› አለችው፡፡ ጌታችንም ክብርት እናቱን ‹‹ይህች ቅድስት ሀገር ናት፣ በኋለኛው ዘመን የቅዱሳን መነኮሳት ቦታ ትሆናለች፡፡ በውስጧም እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ እመሰገንባታለሁ፤ የአንቺም ስም ሳይጠራ አይውልባትም›› አላት፡፡ ከዚህም በኋላ ጌታችን ደመና ጠቅሶ በእርሷ ላይ ተቀመጡ፡፡ መልአኩ ቅዱስ ዑራኤልም መጣና እየመራቸው መላ ኢትዮጵያን ጎበኟት፡፡ እመቤታችንም ሀገሪቱንና ሕዝቦቿን ወዳቸዋለች ደስም ተሰኝታባቸዋለችና ጌታችን ለክብርት እናቱ ‹‹ይህችን ቅድስት ሀገር አሥራት አድርጌ ሰጠሁሽ›› አላት፡፡ እመቤታችንም እጅግ ተደስታ ‹‹ልጄ አምላኬ›› ብላ አመሰገነችው፡፡ ከዚህም በኋላ ከአንዱ ቦታ ወደ አንዱ ቦታ እየተዘዋወሩ መላዋ ኢትዮጵያን በኪደተ እግራቸው ባረኳት፡፡ ጌታችንም ‹‹በዚህ ቦታ እንዲህ ዓይነት ቤተ ክርስቲያን ይታነጻል፤ እከሌ የሚባል እንዲህ ዓይነት ቅዱስ ይነሣል…›› እያለ ብዙ ምሥጢራትን ለክብርት እናቱ ነገራት፡፡ ከዚህም በኋላ የስደቱ ዘመን ሲያልፍ ሄሮድስም በመጨረሻ ክፉ አሟሟትን ሲሞት መልአኩ ወደ ገሊላ አውራጃ እንዲመለሱ ነገራቸው፡፡ እመቤታችንም ‹‹ከዚህች ሀገርስ ባንሄድ እመርጣለሁ›› ስትለው የተወደደ ልጇ ግን ‹‹እናቴ ሆይ ጽድቅንና ፈቃድን ሁሉ ልንፈጽም ይገባናል›› ብሎ አጽናናትና ወደ ሀገራቸው ተመልሰው ሄዱ፡፡ ተመልሰውም ሊሄዱ ሲነሡ የኢትዮጵያ ሰዎች ልዩ ልዩ አምሐ እጅ መንሻ ሰጧቸው፡፡ ልዩ ልዩ ልብሶች፣ ወርቅ፣ ዕጣን፣ ከርቤ፣ ሽቱ እና ሥንቀቸውን በግመሎች ላይ ጭነው እመቤታችንንና የተወደደ ልጇንም በበቅሎ ላይ አስቀምጠው በክብር ሸኟቸው፡፡ እመቤታችንም ልጇን ታቅፋ በበቅሎ ተቀምጣ በበረሃው በመጓዝ ወደ መጣችበት አገር ሄደች፡፡ ኢትዮጵያንም የሰጧትን ብዙ እጅ መንሻዎች በግመሎች ጭና ይዛ ወደ አገሯ በተመለሰች ጊዜ ከአንድ ባሕር ዳር ደረሰች፡፡ ከዚያም የጀልባውን ባለቤት ‹‹እግዚአብሔርን ስለመውደድ አሻግረኝ›› ብላ ለመነችው፡፡ ባለጀልባውም ‹‹እነሆ ዕቃ የተጫኑ አምስት ግመሎችና ከአንቺ ጋር ከዚህም ሕፃን ጭምር አምስት ሰዎች እመለከታለሁ፣ አንቺ የተቀመጥሽባት በቅሎም አለች፡፡ ጀልባዋም ታናሽ ናት፣ የመቀመጫ ክፍሏም በውስጧ የተሳፈሩት ሰዎችም ተጨናንቀው ነው ያሉት፡፡ ስለዚህ እንዴት ላሻግርሽ እችላለሁ? ነገር ግን እመቤቴ ሆይ! ይቅርታ አድርጊልኝ ይህን በክፋት አላደረግሁትምና›› አላት፡፡ ክብርት እመቤታችንም የጀልባው ባለቤት ሊያሻግራት እንዳልቻለ በተረዳች ጊዜ ‹‹ልጄ ሆይ የእግዚአብሔር ልጅ እንደመሆንህ ይህን ትልቅ ወንዝ ለመሻገር የአምላክነትህን ሥራ ትሠራ ዘንድ እለምንሃለሁ›› ስትል ማለደችው፡፡ ያንጊዜም ጌታችን ክብርት እናቱን ‹‹የወለደሽኝ እናቴ ሆይ! አትዘኝ›› ብሎ አረጋጋት፡፡ ዳግመኛም ‹‹በእኔ ፈቃድ በአባቴ ፈቃድ በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ካንቺ ሰው ሆኛለሁና ሰው መሆኔንም ከአባቴ በቀር መስተፍሥሒ ከሚሆን ከመንፈስ ቅዱስም በቀር ያወቀ የለም፡፡ ዳግመኛም በሕያዋንና በሙታን ለመፍረድ ለሁሉም እንደየሥራው እከፍለው ዘንድ እመጣለሁ፡፡ ያችንም ሰዓት የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ የአዳም ልጆችም ቢሆኑም ከእኔና ከአባቴ ከመንፈስ ቅዱስም በቀር የሚያውቃት የለም፡፡ ያንጊዜ ‹ዐመፅን የሚናገር አንደበት ሁሉ ይዘጋል› ብሎ አባትሽ ዳዊት እንደተናገረ እከራከራለሁ የሚል አንደበት እንደድዳ ምላሽ ያጣል›› አላት፡፡ ክብርት እመቤታችን ማርያምም ይህንን ሁሉ ምሥጢር የተወደደ ልጇ የነገራትን ታስተውለው በልቧም ትጠብቀው ነበር፡፡ ጌታችንም አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ለክብርት እናቱ ይህንን ከነገራት በኋላ ቀኝ እጁን ዘርግቶ ከወንዙ ማዶ ጢር በሚባል ተራራ ያሉትን ድንጋዮች ጠቀሳቸው፡፡ ያንጊዜም እነዚህ ድንጋዮች እየተገለባበጡ መጥተው እንደ ጀልባ ሆነው በወራጁ ወንዝ ላይ ተንሳፈፉ፡፡ ከዚያም እመቤታችንን ከሕፃኑ ጋር ከነቤተሰቧና ከነጓዟ አሻገረሯት፡፡ እነዚህንም ድንጋዮች ያዩ ሰዎች ሁሉ እጅግ አድንቀው ‹‹ብቻውን ድንቅ ተአምራት ያደረገ፣ እስራኤልን የፈጠረ እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን የጌትነቱም ስም የተመሰገነ ነው›› እያሉ አመሰገኑ፡፡ እነዚህም የተባረኩ ሰዎች ወንዙን ከተሻገሩ በኋላ በዚህች አገር ለስምንት ቀን ተቀመጡ፡፡ ከዚህም በኋላ አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች ክብርት እመቤታችን ስለደረገላት መልካም ሥራ ሁሉ እግዚአብሔርን ፈጽማ እያመሰገነች ወደ አባቷ ወደ ዳዊት አገር ተመለሰች፡፡ ዳግመኛም በኋለኛው ዘመን ጌታችን በዚህ በደብረ ቍስቋም ቅዱሳን ሐዋርያቶቹን ሰበሰባቸውና ታቦትንና ቤተ ክርስቲያንን አክብሮ የቍርባን መሥዋዕትንም ሠርቶ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለወገኖቹ ሰጣቸው፡፡ ለዚህም ነገር የእስክንድርያ አገር ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱሳን አባቶቻችን ቄርሎስና ቴዎፍሎስ ምስክሮቹ ሆኑ፡፡ ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን አምላክን የወለደች የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በረከቷ ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን ። ( ስንክሳር ዘተዋሕዶ ፌስቡክ ገጽ)
Открыть в Telegram✝መድኃኔዓለም በአበው አንደበት📖 ጽሐፉ የተወሰደው፡-ከመጽሐፍ ቅዱስ እና ከብሂለ አበው ነው። "ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።” ዮሐንስ 1 : 2 “እኛ ወደ እርሱ መውጣት ሲያቅተን መድኃኔ ዓለም ወደኛ ወረደ” (አቡነ ሺኖዳ) “ከሰማይም ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፥ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው” (ዮሐ 3፡13) “ከእባብ ማሳት ምክንያት በበደልን ጊዜ ከዘለዓለማዊ ሕይወት ራቅን፣ ደስታ ካለበት ከገነትም ወጣን፣ አንተ ግን ለዘለዓለሙ አልጣልኸንም፤ … በኋላ ዘመንም በጨለማና በሞት ለምንኖር ለእኛ ታየህልን፣ በመንፈስ ቅዱስ ከድንግል ማርያም ሰው የሆነ የአንድ ልጁንም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃን በእኛ ላይ አኖርህ” (ባስልዮስ ዘቂሳርያ) “ማዳኑም ከወደረኞቻችንና ከሚጠሉን ሁሉ እጅ ነው ይህም ከላይ የመጣ ብርሃን በጐበኘበት በአምላካችን ምሕረትና ርኅራኄ ምክንያት ነው፡፡ ብርሃኑም በጨለማና በሞት ጥላ ተቀምጠው ላሉት ያበራል እግሮቻችንንም በሰላም መንገድ ያቀናል” (ካህኑ ዘካርያስ በሉቃ 1፡71-79) “የሰው ልጅ በወደቀ ጊዜ እግዚአብሔር መምሰል ተነጥቆ ነበር፤ ኢየሱስ ክርስቶስ የመጣው ያጣነውን መልክ ሊመልስልን ነው” (ቅዱስ ሚናስ) “ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፥አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአል” (ቅዱስ ጳውሎስ ሮሜ 8፡29) “ባለመታዘዝ የእንጨት ፍሬን በመብላት ምክንያት የመጣውን ሞት፣ መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ በመታዘዝ በእንጨት መስቀል ላይ ተሰቅሎ ሞትን አስወግዶ ሕይወትን ሰጠን” (ቅዱስ ሄሬኔዎስ) “በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ” (ፊልጵ 2፡8) “እኛ ሁላችን አምላካችን እግዚአብሔር መሆኑንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋ የለበሰው ቃል መሆኑን እናምናለን፡፡ እርሱ በመለኮቱና ሰው በመሆኑ ፍጹም እንደሆነ እናምናለን፡፡ አምላክነቱ ከሰውነቱ ለቅጽበት እንኳ እንዳልተለየም እናምናለን፡፡ ሰው መሆኑ ከመለኮተ ጋር ያለ መቀላቀል ያለ መለወጥ፣ ያለ መከፋፈልና መለያየት የሆነ ነው” (ቅዱስ ቄርሎስ) “የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ቸር ስጦታ አውቃችኋልና፤ሀብታም ሲሆን፥ እናንተ በእርሱ ድህነት ባለ ጠጎች ትሆኑ ዘንድ ስለ እናንተ ድሀ ሆነ” (ቅዱስ ጳውሎስ 1ኛ ቆሮ 8፡9) “እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፡፡ ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ” (ቅዱስ ጳውሎስ ፊልጵ 2፡6-7) “ሔዋንን ዲያብሎስ አሳታት የሞት ምክንያት የሚሆን ቃልን ወለደች፡፡ ድንግል ማርያም ግን መልአክ በአበሠራት ጊዜ ሁሉን ወደ ዘለዓለም ሕይወት የሚመራ አካላዊ ቃልን በሥጋ ወለደች” (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ) “መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት፦ መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል” (ሉቃ 1፡35) “የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ልጁን ላከ” (ገላ 4፡4) “የጠፋ በግ አዳምን የፈለገው ባገኘውም ጊዜ የተሸከመው እውነተኛ ቸር ጠባቂያችን ክርስቶስ ነው” (ተአምረ ማርያም) “መቶ በግ ያለው ከእነርሱም አንዱ ቢጠፋ፥ ዘጠና ዘጠኙን በበረሃ ትቶ የጠፋውን እስኪያገኘው ድረስ ሊፈልገው የማይሄድ ከእናንተ ማን ነው?…ባገኘውም ጊዜ ደስ ብሎት በጫንቃው ይሸከመዋል…የጠፋውን በጌን አግኝቼዋለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ ይላቸዋል” (ሉቃ 15፡ 4-6) “ማንም ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደመጣ የማያምን ፀረ ክርስቶስ ነው፡፡ በመስቀል ላይ መከራን በመቀበል ኃጢአታችንን ተሸከመ” (ቅዱስ ፖሊካርፐስ) “ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሎአልና፡፡ እርሱም ኃጢአት አላደረገም፥ ተንኰልም በአፉ አልተገኘበትም፤ ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም መከራንም ሲቀበል አልዛተም፥ ነገር ግን በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን አሳልፎ ሰጠ…ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ” (1ኛ ጴጥ 2፡22-24) “በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል…እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ፡፡ ተጨነቀ ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፥ በሸላቾቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም” (ኢሳ53፡1-12) “ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ለእኛ ንስሐ ለገባነው ክቡር የሆነ ሰማያዊ አክሊልን ታቀዳጀን ዘንድ የእሾህ አክሊል ደፋህ” (ቅዱስ በርተሎሚዎስ) “ኢየሱስ ክርስቶስ ድል አድራጊ ንጉሥ ነው የምንለው ተሰቅሎ ሞቶ ስለተነሣ ስላየሁት ብቻ አይደለም፤ እርሱ ለዘመናት ድል አድራጊ ነውና” (ዮሐንስ አፈወርቅ) ለሚወጣ ሁሉ በክርስቶስም ትምህርት ለማይኖር ሰው አምላክ የለውም፤ በክርስቶስ ትምህርት ለሚኖር አብና ወልድ አሉት።1ዩሐ.1፥9 “አታልቅስ፤ እነሆ፥ ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ እርሱም የዳዊት ሥር መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ ሰባቱንም ማኅተም ይፈታ ዘንድ ድል ነሥቶአል” (ራእይ 5፡5) “በጉም የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለ ሆነ እነርሱን ድል ይነሣል” (ራእይ 17፡14) “ኢየሱስ ክርስቶስ የማይጠልቅ ፀሐይ፣ የማይጠፋ መብራት፣ በቅዱሳን ላይ ዘወትር የሚያበራ ፀሐይ ነው” (ባስልዮስ ዘቂሳርያ) “እኔ ኢየሱስ በአብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ይህንእንዲመሰክርላችሁ መልአኬን ላክሁ። እኔ የዳዊት ሥርና ዘር ነኝ፥ የሚያበራም የንጋት ኮከብ ነኝ” (ራእይ 22፡16) "ክርስቶስ በስጋ መጣ እርሱም ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው" ሮሜ 9-5 ወስብሀት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን። 🇪🇹@ethiopianorthodoxs⛪️⛪️
Открыть в Telegramይህ ሁሉ ህዝብ ሲያልቅ 'RIP' እያሉ ማለፍ መፍትሄ አይሆንም፣ የአሜሪካ መንግስት በቅርቡ ናይጄርያ ውስጥ ባሉ ክርስቲያኖች ላይ የሚፈፀም ግድያን አስታኮ እርምጃ እንደወሰደው የእኛንም ሀገር ጉዳይ ትኩረት እንዲሰጥ ይህን ከታች ያዘጋጀሁትን መልዕክት ትዊተር (X) ላይ በማጋራት ድምፅ እናሰማ። URGENT: Targeted attacks against civilian Christian communities in Ethiopia’s Arsi zone continue to be downplayed while innocent lives are lost. Silence equals impunity. We are calling on @StateDept, @USCIRF, @HouseForeign, @SenateForeign, @SecRubio, @USEmbassyAddis, @realDonaldTrump to take immediate action: - Impose the Global Magnitsky act on perpetrators and complicit officials. - Demand accountability for human rights violations in Arsi. - Protect international religious freedom. #ProtectArsiChristians #EthiopiaHumanRights
Открыть в Telegramቅዱስ ፊልጶስ:- አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ጥቅምት ዐሥራ አራት በዚች ቀን ከሰባ ሁለቱ አርድእት ውስጥ የሆነ አንዱ ቅዱስ ሐዋርያ ፊልጶስ አረፈ:: ጌታችንም በቂሣርያ አገር ውስጥ በአለፈ ጊዜ በውስጧ አስተማረ:: ትምህርቱንም ሰምቶ ክብር ይግባውና ጌታችንን አምኖ ተከተለው ከሰባ ሁለቱ አርድዕትም ጋር ተቆጠረ:: ጌታችን ይሰብኩ ዘንድ ሁለት ሁለት አድርጎ በላካቸው ጊዜ ከእርሳቸው አንዱ ይህ ደቀ መዝሙር ፊልጶስ ነው:: ከመድኃኒታችንም ዕርገት በኋላ ሐዋርያት ከሾሟቸው ከሰባቱ ዲያቆናት ውስጥ የተቆጠረ ነው:: እርሱም ወደ ሰማርያ ወርዶ አስተማረ:: ብዙዎችንም አሳምኖ የክርስትና ጥምቀትን አጠመቃቸው:: ከዚህም በኋላ የተጎዳውን ሥራየኛ ሲሞንንም አጥምቆት ነበር:: እርሱ የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ በገንዘብ ሊገዛ አስቧልና:: ፊልጶስ ግን ይህን ሲሞን ገሰጸው። የእግዚአብሔርን ፀጋ በገንዘብ ሊገዛ ሽታልና። ከዚህም በኋላ ወደ ጋዛ በሚወስደው መንገድ ይሔድ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ ፊልጶስን አዘዘው:: በሔደም ጊዜ ለኢትዮጵያ ንግሥት ለህንደኬ በጀሮንዷ የሆነ ጀንደረባውን አገኘው:: "እርሱም እንደ በግ ሊታረድ መጣ" የሚለውን የነቢይ ኢሳይያስን መጽሐፍ ያነብ ነበር:: ፊልጶስም ጀንደረባውን "የምታነበውን ቃል ታስተውላለህን?" አለው:: ጀንደረባውም "ያስተማረኝ ሳይኖር እንዴት አውቃለሁ አለ::" ፊልጶስም ስለ ጌታችን ስለ መከራው ለዓለሙ ሁሉ ድኅነት ስለሆነው ሞቱ እንደተነገረ ተረጎመለት:: ጀንደረባውም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ አመነ:: ያን ጊዜም በፊልጶስ እጅ ከወንዝ ውኃ ውስጥ ተጠመቀ:: ከውኃውም በወጣ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ፊሊጶስን ነጥቆ ወሰደው:: ጀንደራባውም ሁለተኛ አላየውም:: ፊልጶስም ወደ አዛጦን ከተማ ደረሰ እያስተማረም እስከ ቂሣርያ ሔደ በከተሞችም ሁሉ በመዞር ወንጌልን ሰበከ:: ከአይሁድና ከሳምራውያንም ብዙዎችን ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ማመን መልሶ የክርስትና ጥምቀትን አጠመቃቸው:: ለሐዋሪያ ፊልጶስም ከእርሱ ጋር ወንጌልን የሚሰብኩ አራት ሴቶች ልጆች ነበሩት:: አገልግሎቱንም ፈጽሞ በሰላም አረፈ:: በዛሬው መልዕክት የምንማረው የኢትዮጵያ ጀንደረባ ትኅትና በተለይም መፅሐፍ ቅዱስ አንባቢነቱን ነው። መፅሐፍትን ማንበብ ያልገባንን መምህራነ ቤተ ክርስቲያንን መጠየቅ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኝ መገለጫ መሆኑን እንረዳለን። እኛንም በቅዱስ ሐዋርያው ፊልጶስ ጸሎት ይማረን:: በአባታችን አቡነ ሐረጋዊና ገብረ ክርስቶስ ጸሎትና ምልጃ ይጠብቀን:: በረከታቸውም ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን:: 🇪🇹@ethiopianorthodoxs⛪️⛪️
Открыть в Telegramአንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ጥቅምት አምስት በዚህች ቀን ተአምራቱና ትሩፋቱ እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ የእግዚአብሔር ማደርያ የሆነ ቅዱስ አባት ተጋዳይ የአባ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የመታሰቢያ ቀኑ ነው:: ይህ ጻድቅ ዕረፍቱ በመጋቢት ሲሆን ቃል-ኪዳን የተቀበሉበት ቀን በጥቅምት ነው:: በመጋቢት ወር በስፋት እና በጥልቀት መልእክቱን ልኬ ክብር ይግባውና ከቃል-ኪዳኑ በረከት ተካፋይ ሆነናል:: ገድለ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስን በማንበብ በረከትና ቃል-ኪዳኑን በእምነት መቀበል ነው:: ይባረኩበታል:: ይቀደሱበታል:: ገድለ ገብረ መንፈስ ቅዱስን በማንበቦ ወይ ሲነበብ በመስማቶ: በስማቸው የታነጸ ቤተ ክርስቲያን ሔደው በመሳለሞ: ማኅሌቱን ቆመው: ቅዳሴ አስቀድሰው: ቃለ ወንጌሉን ሰምተው: ዕጣን ጧፍ ሰጥተው: ለነዳያን እንደ አቅሞ መጽውተው ጻድቁ የተሰጣቸው ቃል-ኪዳን በእምነት ይቀበላሉ:: በዛሬው ቀን ጥቅምት አምስት ቀን እንድናከብረው መምህራነ ቤተ ክርስቲያን ያዘዙን በመጋቢት ወር ዐቢይ ጾም ምክንያት ወደዚህ የዞረ ባዓል ነው:: ለበረከት ያህል ግን እንሆ...... ++++ ለበረከት +++++ ይህም ቅዱስ አባት በተወለደበት ቀን ድንቅ የሆነ ሥራን ሠራ:: እንደተወለደ ተነሥቶ ከእናቱ እቅፍ ወርዶ ከጨለማ ወደ ብርሃን ላወጣኽኝ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይሁን እያለ ለሥላሴ ሰግዷል ምስጋናም አቅርቧልና:: በበረሀም ብዙ ዘመናት ሲኖር:: ነፍሱን ነፍስ ሆይ ዕወቂ በእግዚአብሔር ፊት ራቁትሽን ትቆሚ ዘንድ እንዳለሽ እንግዲህስ ጽኚ በርቺ ታገሺ ይላት ነበር:: ከብዙ ዘመናት በኋላም ለአባታችን ለገብረ መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር እንዲህ አለው:: ከእንግዲህ በዓለም ካሉ ሰዎች ከካህናት ከመነኰሳት ወይም ከምእመናን ሕዝባውያን እንዳያውቁህ አደርግሃለሁ:: እንዳንተ ካሉ በቀረ አንተ ራስህ ብትፈቅድ እንጂ መላእክትም ይጎበኙሃል:: የብርሃን ሠረገላም ይሁንል መድረስ ወደምትሻበት ሁሉ ብረር:: እኔንም ማየት በምትፈልግበት ጊዜ አባቴን ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በሦስትነቴ ታየኛለህ:: ስልሳ አንበሶች ስልሳ ነብሮች በፊት በኋላ አጅበውት ወደ ኢትዮጵያ ምድር ተጓዙ:: የእግዚአብሔር መልእክተኛ ቅዱስ ገብርኤልም ከአንበሶችና ከነብሮች ጋር በነፋስ ሠረገላ አሳፍሮ ይመራው ነበር:: ወደ ምድረ ከብድም አደረሰው ከዚያም ወደ ልዩ ተራራ ወደ ደብረ ዝቋላ ወሰደው:: አባታችን መላው ኢትዮጵያን ያስማረ ፈጣሪም አብዝቶ ቃል ኪዳን የሰጠው ነው:: ስለ ሕዝቡ ምሕረት ልመና መቶ ዓመት በባሕር ኖረ:: በሽተኞችን እንዲፈውስ ሙታንን እንዲያስነሳ አምላካችን ሥልጣን ሰጥቶታል:: ስሙን ለሚጠራና መታሰቢያውን ለሚያደርግ እስከ አሥራ አምስት ትውልድ የምሕረት ቃል ኪዳን ሰጠው:: የጸሎቱ ኃይል ሁላችንን የክርስቲያን ወገኖች ይጠብቀን ለዘለዓለሙ አሜን:: ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን የአባታችንም የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ምልጃ ቃል ኪዳንና በረከት አይለየን ለዘላለሙ አሜን:: 🇪🇹@ethiopianorthodoxs⛪️⛪️
Открыть в Telegram🌻እንኳን ለፆመ ፅጌ በሰላም አደረሰን! አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም መስከረም ሃያ ስድስት በዚህች ቀን እግዚአብሔር የመላእክት አለቃ ገብርኤልን ወደ በራክዩ ልጅ ዘካርያስ ልኮት መጥምቁ ዮሐንስ ከእርሱ ስለ መወለዱ አበሠረው:: ስሙ የተመሰገነ እግዚአብሔር ልጅን ይሰጠው ዘንድ አስቀድሞ ሁል ጊዜ በመጸለይ ወደ እግዚአብሔር ይማልድ ነበር:: ልጅ ያልወለደውን እግዚአብሔር ብዙ ተባዙ ምድርን ምሉዋት ያለውን በረከት ያጣ ነው በማለት እስራኤል ይገዳደሩት ነበርና:: ልመናውንም ሰማ በቤተ መቅደስ ቁሞ ዕጣንን ሲያሳርግ መልአኩን ላከለት በከበረ ወንጌልም እንደተባለ መንገዱን ይጠርግ ዘንድ በንጉሥ ክርስቶስ ፊት እንደሚሔድ የተነገረለት ታላቅ ነቢይ ዮሐንስ ከእርሱ መወለዱን አበሠረው:: ዘካሪያስም የሰውነቱን መድከም የመወለጃውም ዘመን እንዳለፈና ፈጽሞ እንዳረጀ የሚስቱም እንዲሁ ዘመኗ እንዳለፈና ፈጽሞ እንዳረጀች መካንም እንደሆነች ያውቃልና ስለዚህ ይህ ነገር እንዴት ይሆንልኛል እኔ ያረጀሁ ሽማግሌ ነኝ ሚስቴም እንዲሁ ዘመኗ አልፎ መካን ሁናለች ብሎ የእግዚአብሔር መልአክ ተከራከረው:: መልአኩም እኔ ልንገርህ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወዳንተ ተልኬ ነበር ልትጠራጠር ባልተገባህም ነበር አሁንም ይህ በጊዜው እስቲፈጸም ዲዳ ሁነህ መናገር ይሳንሃል ብሎ ገሠጸው:: ዘካርያስም የወልደ እግዚአብሔርን መንገድ የሚጠርግ ዮሐንስ እስከሚመለድበት ጊዜ ድረስ ዲዳ ሆነ:: በሚገረዝበትም ቀን የሕፃኑን ስም ምን ብለው እንደሚሰይሙት ጠየቁት እርሱም ብራና ለምኖ ስሙ ዮሐንስ ነው ብሎ ጻፈ በዚያም ጊዜ አንደበቱ ተፈትቶ እግዚአብሔርን አመሰገነው:: ስለ ልጁ ዮሐንስም እርሱ የልዑል ነቢይ እንዲባል መንገዱንም ይጠርግ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት እንደሚሔድ ትንቢት ተናገረ:: ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዘካርያስና በኤልሳቤጥ በልጃቸው በዮሐንስም ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን:: 🇪🇹@ethiopianorthodoxs⛪️⛪️
Открыть в Telegramአንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም መስከረም ሃያ አንድ በዚህች ቀን አምላክን በሥጋ የወለደች የእመቤታችን ድንግል ማርያም የበዓሏ መታሰቢያ ነው:: ሁላችንም የአዳም ልጆች እስከ ዓለም ፍጻሜ የበዓሏን መታሰቢያ በየወሩ ልናደርግ ይገባናል:: የእግዚአብሔር ልጅ ከእርሷ ሰው በመሆነ ከጠላታችን ሰይጣን እጅ አድኖናልና:: ድኅነታችን በእርሷ ተደርጎልናል:: እርሷም ስለ እኛ ሁልጊዜ ትማልዳለችና:: ለመዳናችን ምክንያት እርሷን እናቱ ለሰጠን እግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በረከቷም ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን:: መጋቢ ሐዲስ ሮዳስ ነገረ ማርያም ከሚለው መጽሐፋቸው ለዛሬ ቅድስ አግናጥዮስ(ምጥው ለአንበሳ )የተባለው ለእመቤታችን ድንግል ማርያም እና እርሷም የመለሰችውን መልስ እንዲሁም ለወንጌላዌው ዮሐንስ የሰደደለትን ጥበብ የተሞላበትን መልዕክት እንሆ ለበረከት:: ከቅዱስ አግናጥዮስ ለእመቤታችንና ለዮሐንስ የተላከ ደብዳቤ (መልእክት) እና የወላዲተ አምላክ መልስ (ከሐዋርያውያነ አበው መጻሕፍት) አግናጥዮስ ዘአንጾኪያ በጥንት ግሪክ አንቲኮስ በ30 ዓም የተወለደ ሲኾን እስከ 107 ዓ.ም ድረስ ቆይቷል ፤ ይኽ አባት ቴኦፖሮስ በመባል ሲታወቅ ትርጒሙም “እግዚአብሔርን የሚሸከም” ማለት ሲኾን ራሱ አግናጥዮስ ይኽነን በመልእክቱ ላይ ጽፎታል። በማቴ ፲፰፥፪-፬ ላይ ጌታችን በክንዱ ዐቅፎ ባርኮ ምሳሌ ያደረገው ሕፃን እርሱ እንደኾነ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ በስፋት ይነገራል፡፡ ቅዱስ አግናጥዮስ የሐዋርያው የቅዱስ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር ሲኾን የፖሊካርፕ ባልንጀራ ነው። በአንጾኪያ በቅዱስ ጴጥሮስ መንበር በ67 ዓ.ም ካረፈው ከቅዱስ ኢቮዲየስ በመቀጠል በሦስተኛነት ሊቀ ጳጳስ ኾኖ የተሾመ አባት እንደኾነ በ፬ተኛ መቶ ክ.ዘመን የነበረው የታሪክ ጸሓፊው አውሳብዮስ ጽፏል ፡፡ (Church History (Eusebius)" Historia Ecclesiastica, II.iii.22) ቅዱስ አግናጥዮስ ስለ ክርስቶስ በመመስከሩ በአረመኔው ንጉሥ በትራጃን ትእዛዝ በዐሥር ወታደሮች ታስሮ ሲኼድ ሰባት አስደናቂ የሃይማኖት ትምህርት የያዙ መልእክታትን (ደብዳቤዎችን) ጽፎ ለአብያተ ክርስቲያናት ላከ። ከዚኽ በተጨማሪ ዘጠኝ የተለያየ መልእክታትን የጻፈ ሲኾን ከጌታችን ዕርገት በኋላ ቅድስት ድንግል ማርያም በቤተ ዮሐንስ ሳለች መልእክት ጽፎ የላከላት ሲኾን ርሷም መልእክቱን አንብባ ለዚኽ ቅዱስ አባት መልስ ጽፋለታለች፤ ይኽም “የአግናጥዮስ መልእክት ለድንግል ማርያም” (The Epistle of Ignatius to the Virgin Mary) በመባል የታወቀ ሲኾን ከኒቅያ ጉባኤ አስቀድሞ በተነሡት በተላውያነ ሐዋርያት (Apostolic Fathers) መጻሕፍት ውስጥ ይገኛል፤ በመዠመሪያው የጻፈላት መልእክቱ ቃል በቃል እንዲኽ ይል ነበር፡- “የአግናጥዮስ መልእክት ለድንግል ማርያም” ባንቺና በጌታ የተወደደው የውዱ የዮሐንስ ደቀ መዝሙር እኔ ዐዲስ ተክል (ዐዲስ ዐማኝን) አግናጥዮስን ታጽናኚኝ ታረጋጊኝ ዘንድ ይገባል፤ ስለ ልጅሽ ስለ ኢየሱስን ክርስቶስ የተነገሩትን ድንቆች ነገሮችን ሰምቼያለኊ፣ እናም በዚኽ ድንቅ ነገር እጅጉን ተደምሜያለኁ ተደንቄያለኊ፡፡ ነገር ግን ከአንቺ የተነገሩትን፤ ኹልጊዜም በቅርበት በኅብረት ከርሱ ጋር እንዲኹም ከምስጢራቱ ጋር (በሙሉ) መተዋወቅን (ሱታፌ ማድረግን) አስመልክቶ ሙሉ ልቤ ገለጻን (ምስጢርን) ለማግኘት ትሻለች፤ ላንቺም ለጌታ እናት ዳግመኛ በሌላ ጊዜ እጽፍልሻለኊ፤ እናም ተመሳሳይ ነገራትን እጠይቅሻለኊ፤ አንቺን የጌታዬን እናትም በበጎ ስንብት እሰናበታለኊ፤ ከእኔ ጋር ያሉት ዐዲስ አማኞች በአንቺ እና በአንቺ አማካይነት እና በአንቺም ውስጥ ይጽናኑ፡፡ አሜን፡፡ ለዚኽ ደብዳቤ በቡርክት ማርያም የተሰጠ መልስ የኢየሱስ ክርስቶስ ትሑት እናቱ ለተወዳጁ ደቀ መዝመሩ ለአግናጥዮስ የተሰጠ መልስ (ኢየሱስ ክርስቶስን አስመልክቶ ከዮሐንስ የሰማችኋቸው እና የተማራችኋቸው ነገሮች እውነት ናቸው፤ ታመኑባቸው፣ ተከተሏቸው እና የያዛችኹትን የተቀበላችኹትን የክርስትና እምነት አጥብቃችኁ ያዙ፣ ሕይወታችኹን እና ግብራችኹን ከክርስትናችኊ እምነት ጋር ዐብራችኊ አስኺዱ፡፡ አኹን ከዮሐንስ ጋር በአንድነት አንተ እና ከአንተ ጋር ያሉትን ልንጐበኝ እንመጣለን፣ በእምነትኽ ጸንተኽ ቁም፣ እና ጥብዐትኽን አሳይ፤ የመሳደድ (የመከራ) አስፈሪነት ፈጽሞ እንዳያስደነግጥኽ፣ ይልቁንም መንፈስኽ በአምላክኽ በመድኀኔ ዓለም ኀያልነት ደስታ በፍጹም ይሰማኽ፡፡ አሜን) ለሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ የተላከ የአግናጥዮስ መልእክት አግናጥዮስና ከርሱ ጋር በአንድነት የነበሩት ወንድሞች፣ ለቅዱሱ ቀሲስ ዮሐንስ (በመልክቶችኽ እና በማጽናኛዎችኽ የምታጠነክረን (ዮሐንስ) በመዘግየትኽ በጥልቅ ዐዘን ውስጥ ነን፡፡ በጣም ለረዥም ጊዜ የምትለየን ከኾነ፣ ብዙዎቻችን የምናዝን ይኾናል፡፡ በፍጥነት መምጣትኽ ርቱዕ ይኾናል ብለን እናምናለን፡፡ በዚኽ የሚገኙትም አብዛኞቹ ሴቶች የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን እናት ድንግል ማርያምን ለማየትና በየቀኑ ከእኛ ወደ ርሷ በመመላለስ ሊያገኟት፣ እና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ያጠቡትን ሐሊበ ድንግልና ያስገኙ ጡቶቿን ለማድነቅ፣ እና ስለአንዳንድ ረቂቅ ምጡቅ ምስጢራዊ ነገራት ሊጠይቋት እጅግ ከፍተኛ መጓጓት (ፍላጎት) አላቸው፡፡ ከእርሷ ጋር ዐምስት ወር በኢየሩሳሌም የቆየችው ሰሎሜ እና ሌሎች የታወቁ ሰዎችም (ቅዱሳት አንስት) በዘላለማዊ ድንግልናዋ ከነሙሉ ጸጋዋ እና ሙሉ በጎዎች ግብሮቿ (ሥራዋ) በመልካምና በምልዕተ ጸጋነት መቆየቷን ምስክርነትን ይሰጣሉ። እንደሚገልጹልንም በመሰደዷ (ወደ ግብጽ) እና በመጠቃቷ (በሄሮድስ)፣ በድኽነት (በማጣት) ውስጥ የነበረች ቢኾንም እንኳን ማጉረምረም ከቶ የማታውቅ፣ እና ይልቁኑ ልትደግፋቸው ፈጽሞ የማታመነታ ደስተኛ ናት፡፡ ሊያጠቋት ለሚሹ (ለአይሁድ) ኹሉ እርሷ ግን ምስጋናዋ (ጸሎቷ ልመናዋ) ከፍ ያለ ነው፣ (አይሁድ ለሚያመጡባት) ለዚኽ መከራ እርሷ ደስተኛ ናት፣ በአደጋ እና በችግር የተጋለጡትን ለመርዳት ዐዛኝ የኾነች፣ እና ልትደግፋቸው ኹሌም ወደ ኋላ የማትል ናት፡፡ በተጨማሪም በመጥፎ መርህዎች ወይም ሥነ ምግባር ውስጥ በሚጎዱ ተቃርኖዎች (ባለች በዚኽ ዓለም) ውስጥ በእምነቷ ጠንክራ በመዋጋት አሸናፊ ኾና በመውጣት ደምቃ ታበራለች (መሓ 2:1)፡፡ የዐዲሲቷ እምነታችን እና ናዛዚታችን እመቤታችን ናት፣ ፍጹም በኾነ በቅድስና ሥራዎች በሙሉ ከአማኞች ኹሉ ደጋፊ የኾነችን ናት፡፡ በርግጥም ለደጎች የተሰጠች (ዮሐ 19:26)፣ እና ከተሰጡትም በላይ ልቃ በልጣ ራሷን ቅን (ለአምላክ) ታማኝ ያደረገች፣ እናት ናት። ይቆየን! ሕመቤታችን ሕመቤታችን ሆይ ወደኛ ተመልከቺ የልጅሽ ሠላም በኛ ላይ ይኑር። 🇪🇹@ethiopianorthodoxs⛪️⛪️
Открыть в Telegramመስቀል ➕➕➕ ነደ እሳትን የተሸከመ የኪሩቤልም ባልንጀራ የሆነ እንደ ድንግል ማርያም ስም አራት ፊደል ያለው ነበልባላዊ የእሳት መንበር። ✣✣✣ አዳምን ከሞት ያወጣው የሕይወት ዛፍ። ✥✥✥ የኃጢአትን ቀላይ የገታ መርከብ። ❖❖❖ ባሕረ እሳትን ያሻገረ የድኅነት ትርክዛ። ✞✟✟ነፍሳት የሕይወት እንጀራን የጠገቡበት ማዕድ! ✟✟✟ክርስቶስና ቤተክረስተያን የተሞሸሩበት የሠርግ ቦታ። ✝️✝️✝️ምእመናን የተጸነሱበት መካነ ክርስትና። 🔸🔸🔸 ቤተክርስቲያን የጸናችበት መሠረተ ሃይማኖት። 🔹🔹🔹የፍስሐ ኩሉዓለም ክርስቶስ ደም የፈለቀበት ሙሐዘ ትፍሥሕት! 🔶🔶🔶 ከሕይወት ውኃ ከክርስቶስ የተተከለ ሁል ጊዜ የሚያፈራ የሕይወት ዛፍ። 🔷🔷🔷 የንጉሥ ልጅ በአባቱ ኅልቀተ ወርቅ ማኅተም እንዲመካ፥ የንጉሠ ነገሥት ክርስቶስ ልጆች የምንለይበት የምንመካበት ትእምርተ ድኂን። ✔️ የጨለማውን አበጋዞችን ድቅድቅ የምንገፍበት ጸዳለ ኩሉ ዓለም። ✔️ የሚወረወረውን ፍላጻ የምንሰብርበት ልብሰ ሃይማኖት ጥሩር። ✟✟✟✔️ጦር ከነቀነቀ ጋሻ ከታጠቀ ከቀን ወራሪ ከሌሊት ሰባሪ የምንመክትበት ንዋየ ሐቅል። ✅ ቢዋጉ ማሸነፊያ ቢሸሹ መጠጊያ ጸወነ ሥጋ ወነፍስ ወልታ የጽድቅ። መስቀል መልእልተ ኲሉ ነገር
Открыть в Telegramየእመቤታችን የድንግል ማርያም ተአምር:- አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም መስከረም ዐሥር በዚህች ቀን ጼዴንያ በምትባል አገር ሥጋ የለበሰች ከምትመስል ሥዕል ከሰሌዳዋ ቅባት እየተንጠፈጠፈ አምላክን የወለደች የእመቤታችን የድንግል ማርያም ተአምር ተገለጠ:: ይህችንም ሥዕል የሣላት ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ ነው:: ወደ ጼዴንያ አገር የመጣችበት ምክንያት አንዲት ስሟ ማርታ የሚባል መበለት ሴት ነበረችና ቤቷንም ለእንግዳ ማደሪያ ያደረገች ናት:: አምላክን የወለደች እመቤታችን ድንግል ማርያምን እጅግ ትወዳት ነበር በሚቻላትም ታገለግላት ነበር:: በአንዲት ቀንም ስሙ ቴዎድሮስ የሚባል መነኵሴ በቤቷ በእንግድነት ተቀበለችው። በማግስቱም ስትሸኘው አባ ወዴት አገር ነው የሚሄዱ አለችው? እርሱም በከበሩ ቦታዎች ልሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም እሔዳለው አላት። እርሷም እባኮ ሲመለሱ የእመቤታችንን ሥዕል ገዝተው ያምጡልኝ ብላ ገንዘብ እንኩ አለች። መነኵሴውም ካገኘው በራሴ ገዝቼ እመጣለሁ ብሎ ተሰናበታት:: መነኵሴውም ከቅዱሳን መካናት ተባርኮ ሲመለስ ሥዕሏን ለምን ረሳህ የሚል ቃል ሰማ ደነገጠናም ተመለሰ ወደ ገበያ ሔዶ የእመቤታችንን ሥዕል ገዛ በአርና በንጹሕ በፍታ ጠቀለላት:: በጎዳና እየተጎዘ ሳለ ከሚያስፈራ ቦታ ወንበዴዎ ተከተሉት ሊሸሽ ሲል ከዚያች ሥዕል መንገድህን ሒድ የሚል ቃል ሰማ የተከተለውም የለም ሁለተኛም ሊበላው አንበሳ ተነሣበት ሊሸሽም ወደደ ከዚያችም ሥዕል የሚያስፈራ ድምፅ ወጥቶ አንበሳውን አባረረው:: መነኵሴውም ይህን ሁሉ ድንቅ ተአምር በአየ ጊዜ ይችን ሥዕል ለመበለቷ ሳይሰጥ መርከብ ተሳፍሮ ወደ አገሩ ሔደ። ነገር ግን አይለኛ ማዕበል ተነስቶ መርከቢቷን ወደ መበለቲቱ አገር ጼዴንያ መለሳት። ከብዙ እንግዶችም ጋር ወደ መበለቲቱ ቤት ገባ። ማንነቱንም አልገለጠም እርሷም አላወቀችም:: በማግሥቱም ተሠውሮ ወጥቶ ወደ አገሩ ሊሔድ በፈለገ ጊዜ የቅጽሩን ደጃፍ አጥቶ ሲያጥመሰምሰው ዋለ። በመሸ ጊዜመ ወደ ማደሪያ ገባ:: ያቺም መበለት በአየችው ጊዜ ታደንቃለች እንዲህም ሆና እስከ ሦስት ቀን ኖረ በመሸም ጊዜ በሩን ያየዋል ነግቶ መሔድን ሲሻ የበሩ መንገድ ይሠወረዋል:: ያቺም መበለት ያዝ አድርጋ አባቴ ሆይ አእምሮህ ተነክቷልን ስትበዘበዝ አይሀለሁና ምን ሁነህ ነው አለችው:: ከዚህ በኋላ ከዚያች ሥዕል የሆነውን ሁሉ ነገራት ራሱንም ገለጠላት:: ያቺንም ሥዕል ሰጣት ተቀብላም የተጠቀለለችበትን ልብስ ፈታች ወዝ ከሥዕሊቱ ሲንጠፈጠፍ አገኘች:: ከደስታዋም ብዛት የተነሣ የዚያን መነኵሴ እጆቹንና እግሮቹን ሳመች:: ከዚህም በኋላ ያቺን ሥዕል ወደ ጸሎት ቤቷ ወስዳ በታላቅ ክብር የምትቀመጥበትን አዘጋጀታ ማንም እንዳይዳስሳትም የነሐስ መስኮትን ሠራችላት በቀንና በሌሊትም የሚበሩ መቅረዞችን በፊቷ ሰቀለች ከመቅረዞቹ ውጪም የሐር መጋረጃን ጋረደጅች:: ከሥዕሊቱ በታችም እየተንጠፈጠፈ የሚወርድው የወዝ ቅባት የሚጠራቀምበት ከዕብነ በረድ የተሠራ ወጭት አኖረች። ያም መነኵሴ እስከሚሞትበት ቀን ድረስ የእመቤታችንን ሥዕል እያገለገለ ኖረ:: የሀገሩም ሊቀ ጳጳስ የዚያችን ሥዕል ዜና በሰማ ጊዜ ከኤጴስ ቆጶሳትና ከካህናት ከሕዝቡም ሁሉ ጋር መጣ:: በሠሌዳዋ ውስጥ ባዩዋት ጊዜ ሥጋ የለበሰች ሁና አገኙዋት። ከዚያም ቅባት ቀድተው ለበረከት በተካፈሉ ጊዜ ወዲያውኑ በወጭት ውስጥ ይመላል:: ወደ ሌላ ቦታም ሊወስዷት በፈለጉ ጊዜ ንውጽውጽታ ሁኖ ብዙዎች በድንጋጤ ወደቁ ሥዕሊቱንም እስከ ዛሬ በዚያች አገር ትኖራለች:: ዛሬም ያለን ፍቅሯ የበዛልን የቅድስት ድንግል ማርያም ልጆች ሥዕለ ማሪያም እንዴት አድርገን አክብረነው አስቀምጠን ይሆን? እንደምን ያለ ብርሃን አብርተን በመልክማ ማዕዛ አጥነነው ይሆን? ወይስ ባልባሌ ቦታ አስቀምጠነው ዘፈን ጭፈራ ሲጋራ አጥነነው ፀሐይ አባሯ አፈራርቀንበት ይሆን? እንግዲ የቤተ ክርስቲያን የሆኑት አክብረው እንደሚከብሩበት እነንደሚፈወሱባት የዛሬ መልዕክት ያስተምረናልና እናስተውል:: ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በእናቱ በእመቤታችን በድንግል ማርያም በጸሎቷ የሚገኝ በረከቷ ከሁላችን ቤተ ሰቦቿ ወንዶችና ሴቶች ባሮቿ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን:: 🇪🇹@ethiopianorthodoxs⛪️⛪️
Открыть в Telegramሁሉም አዲስ ሆኗል ሁሉን አዲስ ያደረገው ክርስቶስ ነው። አዲስ ኪዳን የተቀበልነው በክርስቶስ ነው፤ ኤር. 31፥31። አዲስ መሥዋዕት ያቀረብነው በክርስቶስ ነው፤ 1ቆሮ. 5፥7። አሮጌው ሰዋችን የተወገደው በክርስቶስ ነው ቆላ. 3፥9። አዲሱን ሰው የለበስነውም በክርስቶስ ነው፤ ሮሜ 13፥14። በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት ሞትም ቢሆን አዲስ ነው፤ ሮሜ 14፥8። ወደ መስቀል ብንወጣ ከክርስቶስ ጋር ስጋችንን ለመስቀል ነው፤ ገላ. 5፥24። ወደ ዙፋንም ብንወጣ ከክርስቶስ ጋር ልንነግሥ ነው፤ ብንሞትም የሞትነው ከእርሱ ጋር አብረን በሕይወት ለመኖር ነው 2ጢሞ. 2፥11። ያለ ክርስቶስ አዲስ የሆነ ምንም ነገር የለም። በክርስቶስም አዲስ ያልሆነ አላየንም። አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር እንድናይ ያደረገን ክርስቶስ ነው። በዘመኑ አዲስ መሆን ትደሰታላችሁን? የዓመታት መለዋወጥስ ያስደንቃችኋልን? በእግዚአብሔርና በመላእክቱ ዘንድ ደስ የሚያሰኘው ግን የሰው መለወጥ ነው። የሚያስደንቀውም የአንድ ኃጢአተኛ ሰው ንስሐ መግባት ነው። የፀሐይና የጨረቃ መመላለስ አዲስ ዕለት፣ አዲስ ዓመት ይሰጠናል፤ የእግዚአብሔር ቃል በውስጣችን ሲመላለስ ግን አዲስ ሕይወት ያስገኝልናል። አዲሱ ቀን ይመሻል፤ አዲሱም ዓመት አሮጌ ተብሎ ያልፋል። የማያልፈውን የጌታን ትእዛዝ በመፈጸም ለማያልፈው ዓለም መዘጋጀት ይገባናል። ኖኅ መርከቡን መሥራት የጀመረው “ከጎፈር እንጨት መርከብን ለአንተ ሥራ” ዘፍ. 6፥14 ከተባለበት ጊዜ ጀምሮ ነው። አብርሃምም ከአገሩና ከዘመዶቹ የተለየው “ከአገርህና ከዘመዶችህ ከአባትህም ቤት ውጣ” የሚለውን ትእዛዝ ከሰማበት ጊዜ ጀምሮ ነው። ሙሴ የተመረጠው ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር መከራን መቀበል በመረጠበት ቀን ነው ዕብ. 11፥23። ቃሉን ከሰማችሁበት ጊዜ ጀምሮ አንድም ቀን መልካም ነገር ሳናደርግ የምንውልበት ቀን ሊኖር አይገባም። ያ ቀን መቼ ነው? ካላችሁኝ ዛሬ ነው። ፀሐይ መንገዷን የለወጠችው ዛሬ ነው፤ እኛም ከክፉ መንገዳችን ልንመለሰ የሚገባን ዛሬ ነው። በፀሐይ አቆጣጠር አዲሱን ቀን የጀመርነው ዛሬ ነው፤ ከክርስቶስ ጋር በመኖር የደስታ ቀናትን የምንጀምረውም ዛሬ ነው። አሁን ሁሉም አዲስ ሆኗል፤ አሮጌ ሰውነት፣ አሮጌ ዘመን፣ አሮጌ ሕግ የለም። የተመሰገነው ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ “ሁሉም አልፏል” እንዳለ ቀኑ ሲያልፍ ባለፈው ዓመት የኖርነውን ክፉ ነገር ሁሉ አብረን ማሳለፍ አለብን። አዲስ ቀን ብቻውን ምን ያደርጋል? አዲስ ልብ ከሌለ አዲስ ሕይወት ቢሰጥ ማን ይቀበለዋል? አዲሱ ሰው ክርስቶስ በአይሁድ መካከል ቢገለጥ ምን ተጠቀሙ? አዲስ ልብ የላቸውምና አዲሱን ሰው ክርስቶስን ሳይለብሱት ቀሩ። እኛ ግን አዲስ ልብ ይዘን በክርስቶስ ሁሉን ነገር አዲስ ልናደርግ ይገባናል። ሊቀ ሊቃውንት ስምዐኮነ መልአክ
Открыть в Telegramበጸሎት የተጀመረ ቀን ሀሴት ነው በእምነት የሆነ ኑሮ እረፍት ነው በይቅርታ የተሞላ ጓደኝነት ጥበብ ነው እንኳን ለ2019 ዓ.ም የአዲስ ዓመት በዓል ከሁሉ ቤተሰብዎ ጋር በሰላምና በጤና አደረስዎ፣ አደረሳችሁ። ዘመኑም የተባረከ፣ የተቀደሰ፣ የበረከትና የመልካም ፍሬ ይሁንልዎ። መልካም በዓል።
Открыть в Telegramየመላእክት አለቃ ቅዱስ ሩፋኤል:- አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ጳጒሜ ሦስት በዚህች ቀን የመላእክት አለቃ የከበረ መልአክ የሩፋኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው:: እርሱም ከመላእክት አለቆች ሦስተኛ የሆነ ነው:: ሩፋኤል ማለት ደስ የሚያሰኝ ቸር መሐሪ ቅን የዋህ ማለት ነው:: እኔ ሩፋኤል ኃጢአተኛችን በእግዚአብሔር ዘንድ አልከሳቸውም ከኃጢአታቸው በንስሐ እስኪመለሱ ስለ ቅንነቴ በእነርሱ ላይ እታገሳለሁ:: ሩፋኤል ራሱ በሃያ ሦስት የመላእክት ነገድ ሠራዊት ላይ እግዚአብሔር የሾመኝ እኔ ሩፋኤል ነኝ:: እግዚአብሔር አብን ይቅር ባይ ልጁን አጽናኝ አዳኝ የሆነ መንፈስ ቅዱስን እናመሰግነው ዘንድ:: በደብረ ጽዮን በሚደረገው የሺ ዓመት ተድላ ደስታ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የክብር ጽዋን በሚሰጣቸው ጊዜ ለቅዱሳኖቹ በጎ ነገርን እንደ ሰጣቸው እግዚአብሔር ያዘዘኝ ሩፋኤል እኔ ነኝ:: ደግሞም በዚህች ቀን ከዕፀ ሕይወት ዐጽቅ ወስጄ ለተመረጡ ክርስቲያኖች በእጄ እንድሰጣቸው ያዘዘኝ እኔ ሩፋኤል ነኝ:: የሰማይ መዛግብት ከእጄ በታች ተጠብቀው የሚኖሩ እኔ ሩፋኤል ነኝ:: እግዚዚአብሔር እንዳዘዘኝ እከፍታቸዋለው እዘጋቸዋለሁ:: በምድር ሰው ለባልንጀራው ስለ ስሜ በጎ ነገር ቢያደርግ እኔ በመከራው በችግሩ እረደዋለሁ ወይም የሹመቴን ነገር የሚጽፍ ወይም ከቅዱሳን ጋር ስሜን የሚያስብ ወይም በስሜ ለቊርባን የሚሆነውን የሚሰጥ ይኸውም እግዚአብሔር በሊቃነ መላእክት ክብር የሾመኝና ያከበረኝ ጳጒሚን ሦስት ቀን ነው:: ወደ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት እስከሚገባ በብርሃን ሠረገላ እኔ እሸከመዋለሁ:: በምድር ላይ ከቶ እንደርሱ ያለ የማይገኝ መዐዛው እጅግ ጣፋጭ በሆነ ሽቱ ነፍሶቻቸው እርሱን በማሽተት ደስ እንዲላቸው አደርጋለሁ:: ሐዋርያት ሆይ በእግዚአብሔር ፊት እስከምትቆሙ እጠብቃቹ ዘንድ ከእኔ ርዳታን ሹ:: የዚህ መልአክ ሩፋኤል ታምራቶቹ ብዙ ናቸው ስለ እኛም ይማልዳል:: በዛሬው ዕለት አፍላጋት ወንዞች ውቅያኖሶች ሁሉ ይባረካሉ ከሰማይ የእግዚአብሔር መልአክ በመስቀል ሁሉንም ውኃ ይባርካል ምእመናንም በመጠመቅ በረከትን ይወስዳሉ:: ምእመናንም ይህን ስለሚያውቁ ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት ጀምረው በየአጥቢያቸው ወዳሉ መጠመቂያ ሔደው ይጠመቃሉ ከሰማይ በሚወርደውም ዝናብ ይጠመቃሉ:: በዚህ ዕለት መምህረ ንስሐቸውን ወደ ቤት ጠርተው ጸበል ያስረጫሉ:: በቤታቸው ያሉትን ዕቃዎች ሁሉ እደጅ አውጥተው ጠበል ያስረጫሉ:: በዚህች ቀን የበረታ የዳዊትን መዝሙር በሙሉ ይጸልያል አባታችን ሆይ እና ሰላም ለኪንም በጥሞና በዓመቲቱ ልክ ሦስት መቶ ስሳ ስድስት ጊዜ ይጸልያሉ:: ይህ ለመላኩ ለቅዱስ ኡራኤል የተሰጠው ቃል ኪዳን ነውና:: ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ መልአክ አማላጅነት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን:: 🇪🇹@ethiopianorthodoxs⛪️⛪️
Открыть в TelegramПереслано из Ethiopian Orthodoxs Daily
መድኃኒታችንም እንዲህ አለው ወዳጄ ሆይ አንተ በመከራዬ መሰልከኝ እኔም በመንግሥቴ ከእኔ ጋራ እንድትመስለኝ አደርግሃለሁ:: እነሆ የዚህ ዓለም ድካምህ ተፈጸመልህ በእኔ ዘንድም የምቀበለው ሆነ ከእንግዲህስ መንግሥተ ሰማያትን ትወርስ ዘንድ ና:: እንሆ ስምህን ለሚጠራ መታሰቢያህን ለሚያደርግ ገድልህን ለሚጽፈው ለሚያነበውና ለሚሰማውም ቤተ ክርስቲያንህን ለሚሰራ በስምህ መባ ለሚሰጥ ለድኆችም በስምህ ለሚመጸውት በመታሰቢያህ ቀን ለሚቆርብ ስለ አንተ በጎ ሥራ ለሚሠራ ሁሉ እኔ እስከ ዐሥር ትውልድ እምርልሃለሁ:: አባታችንም እጅግ ደስ አለው ለጌታችንም ሰገደ ጌታችንም ከእርሱ ዘንድ በታላቅ ክብር ወደ ሰማይ ዐረገ:: ከዚህም በኋላ አባታችን በንዳድ በሽታ ጥቂት ታመመ ዕድሜውም ዘጠና ዘጠኝ ዓመት ከስምንት ወር ከአንድ ቀን ሆኖት በለመለመ ዕርግና አረፈ:: በመዘመርና በማመስገን አክብረው ገንዘው በዋሻው ውስጥ ቀበሩት:: ይህንን በማሰብ ከዋዜማው ጀምሮ ታላቅ በዓል እናደርጋለን በተክለ ሃይማኖት ስም በተሰራች ቤተ ክርስቲያን በገዳማት ተሰባስበን እግዚአብሔርን እናመልካለን:: እግዚአብሔር ሆይ በፃድቁ ስም ተሰባስበን ስናመሰግንህ በፃድቁ ስም መልካም ስንሰራ ቃል ኪዳንህን አታስቀርብን ና ባርከን ፈውሰን አሜን እንላለን:: ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባታችን ተክለ ሃይማኖት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን:: 🇪🇹@ethiopianorthodoxs⛪️⛪️
Открыть в TelegramПереслано из Ethiopian Orthodoxs Daily
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሐሴ ሃያ አራት በዚህች ታላቅ ዕለት የከበረ ሐዲስ ሐዋርያ የትሩፋትም መምህር የሆነ አባታችን ተክለ ሃይማኖት አረፈ:: የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም ጸጋ ዘአብ የእናቱ ስም እግዚእ ኀርያ ነው:: እሊህም ቅዱሱን ለኢትዮጵያ የሃይማኖት ብርሃንን ላበሩ ካህናት ከወገኖቻቸው የሆኑ ናቸው:: እግዚእ ኀረያም መካን ስለሆነች ልጅን ይሰጣቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር እያዘኑ ሲጸልዩ ኖረ:: በዚህም ነገር እያሉ የዳሞት ገዥ ሞተለሚን ሰይጣን አነሣሣው የሸዋን አውራጃዎች እስከ ጅማ እስከ ገዛ ድረስ:: የየሀገሩ መኳንንቶችም በየተራቸው ሚስቶቻቸውን ይሰጡታል:: ከማረከውም ደምግባት ያላቸውን ሴቶች ያገኘ እንደሆነ ቁባቶቹ ያደርጋቸዋል:: በዚያ ወራት ወደ ጽላልሽ ደርሶ ብዙ ክርስቲያኖችን ገደለ ከእርሳቸውም የሚበዙትን ማረከ ጸጋ ዘአብም ከግድያ ፍርሃት የተነሳ ሸሸ:: አንድ ወታደርም ተከተለው እርሱም ወደ ባሕር ተወርውሮ ገባ በእግዚአብሔርም ፈቃድ በባሕሩ ውስጥ ተሸሸገ:: ሚስቱን እግዚእ ኀረያንም ወታደሮቹ ማረኳት ወደ ሞተለሚም አደረሷት በአያትም ጊዜ ውበቷንና ላህይዋን አደነቀ:: በልቡም እጅግ ደስ ብሎት ብዙ ሽልማትን ጌጥን ሰጥቷት በሽልማትና በጌጥ ሁሉ ሸለማት አስጌጣትም የጋብቻ ሥርዓትንም ማዘጋጀት ጀመረ:: ለሠርጉም እንዲሰበሰቡ ወደ መኳንቶቹ ሁሉ ላከ:: እግዚእ ኀርያም ይህን በሰማች ጊዜ ከአረሚ ጋር አንድ ከመሆን ያድናት ዘንድ በብዙ ልቅሶ ወደ እግዚአብሔር ጸሎትን አደረገች:: ያን ጊዜ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በብርሃናዊ ክንፉ ተሸክሞ ከዳሞት አገር ወደ ምድረ ዞረሬ አድርሶ ወዲያውኑ ወደ ቤተ መቅደስ አስገብቶ በሴቶች መቆሚያ አቆማት:: ባሏ ጸጋ ዘአብም ከማዕጠንት ጋራ በወጣ ጊዜ እንደተሸለመች ቁማ አያት አድንቆ በልቡ ይቺ ሴት ምንድ ናት ወደዚህስ ማን አመጣት አለ:: የማዕጠንቱንም ሥራ ጨርሶ ወጣ በጠየቃትና በመረመራት ጊዜ እርሷ ሚስቱ እግዚእ ኀርያ እንደሆነች አገኛት:: እርሷም ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው እግዚአብሔር ያደረገላትን ነገረችው:: ከዚህም በኃላ የእግዚአብሔር መልአክ በአንዲት ሌሊት ተገለጠላቸው:: የዜናው መሰማት በዓለም ሁሉ የሚደርስ የተባረከ ልጅ ይወልዱ ዘንድ እንዳላቸው ነገራቸው አበሠራቸው:: ከጥቂት ቀኖች በኋላ ይህ ቅዱስ ተፀንሶ በታኅሣሥ ወር በሃያ አራት ተወለደ:: በጸጋ ዘአብና በእግዚእ ኀረያ በቤታቸው ታላቅ ደስታ ሆነ ከዘመዶቻቸው ጋራ ደስ አላቸው:: ለክርስትና ጥምቀት ባስገቡት ጊዜ ፍስሐ ጽዮን ብለው ሰየሙት:: ሕፃኑም አደገ ድንቅ ተአምራትንም እያደረገ ዕውቀትንና ኃይልንም ተመልቶ በመንፈስ ቅዱስ ጸና:: ከዚህም በኋላ ዲቁና ይሾም ዘንድ አባ ጌርሎስ ወደ ተባለ ጳጳስ ወሰዱት :: በዚያ ዘመን በዛጔ መንግሥት የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳስ አባ ቢንያሚ ነበር:: ወደ ጳጳሱ ባደረሱት ጊዜ ይህ ልጅ የተመረጠ ዕቃ ይሆናል ብሎ ትንቢት ተናገረለት:: የዲቁና ሹመትን ተቀብሎ ወደ ሀገሩ ተመለሰ ጎልማሳም በሆነ ጊዜ አራዊትን ሊያድን ወደ ዱር ሔደ:: ቀትር ሲሆንም የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መልኩ በሚያምር ጎልማሳ አምሳሎ በቅዱስ ሚካኤል ክንፍ ላይ ተገለጠለትና እንዲህ አለው:: ወዳጄ አትፍራ እንግዲህስ የኃጢአተኞችን ነፍስ ወደ ሕይወት የምታጠምድ ትሆናለህ እንጂ አራዊትን የምታድን አትሆንም ስምህም ተክለ ሃይማኖት ይሁን:: እንደ ኤርሚያስና አጥማቂው ዮሐንስ እኔ ከእናትህ ማኅፀን መርጬ አክብሬሃለውና:: እንሆ በሽተኞችን ትፈውስ ዘንድ ሙታንንም ታሥነሣ ዘንድ ሥልጣንን ሰጠሁህ ርኵሳን አጋንንትንም ከሁሉ ቦታ ታሳድዳቸዋለህ:: ወደ ቤቱም በተመለሰ ጊዜ ገንዘቡን ሁሉ ለድሆችና ለምስኪኖች በተነ:: ዓለሙንም ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጠፋ ለሰው ምን ይጠቅመዋል እያለ ቤቱን እንደተከፈተ ትቶ ምርጒዙን ይዞ በሌሊት ወጣ:: ከዚህም በኋላ ወደ ጳጳስ ሒዶ የቅስና ሹመት ተቀብሎ ለሸዋ አገር ሁሉ ወንጌልን መስበክ ጀመረ:: ዐሥራ ሁለት ሽህ ሦስት መቶ ነፍስ ያህል አጠመቀ:: ለጣዖት የሚሰዉበትን ሁሉ ሻረ:: በውስጡ የሚኖሩ አጋንንትን እስኪሸሹ ድረስ ዐፀዶቻቸውን ሁሉ ቆረጠ:: ሁለተኛም ወደ ዳሞት ምድር ሒዶ ብዙ ሟርተኞችንና አስማተኞችን ጠንቋዮችን አሳመነ:: ከሀዲ ሞተለሚም ብዙ ወራት ተቃወመው:: በጉማሬ ማጥመጃ ውስጥ በመጨመር ብዙ ጊዜ ወደ ገደል ወረወረው:: እርሱ ግን በደኅና ይመላለሳል ደግሞ ሊወጋው ጦር ወረወረ ጦሩም ተመልሶ እጁን ወግቶ ተጠመጠመበት በተሰቃየም ጊዜ አባታችንን ለመነው እርሱም የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አሳምኖ አዳነው የተጠመጠመበትን ጦርም ፈታለት ቀናውን መንገድ የሚያጣምሙ ሟርተኞችንም አጠፋቸው:: ከዚህ በኋላ በክብር ባለቤት ጌታችን ስም ያደረገውን ድንቅ ተአምራቱን አይተው የአገር ሰዎች ሁሉም ከንጉሣቸው ጋራ አመኑ:: የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቃቸው:: ቤተ ክርስቲያንም ሠርቶላቸው የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት አስተማራቸው:: በቀናች ሃይማኖትም አጸናቸው ከዚህም ሁሉ ጋራ በጾም በጸሎት በስግደት ሁል ጊዜ ያለ ማቋረጥ ተጠምዶ ይጋደል ነበር:: ዜናውንም ሰምተው ወደርሱ የሚመጡትን የነፍሳቸውን ድኅነት ያስተምራቸዋል የክብር ባለቤት የሆነ ጌታችን ኢየሱስ በማመንም ያጸናቸዋል:: ከዚህም በኋላ በኤልያስ ሠረገላ ተቀምጦ ወደ አምሐራ ሀገር ሔደ:: በገድል ተጸምዶ ወደ ሚኖር መነኰስ ወደ አባ በጸሎተ ሚካኤል በአንዲት ቀን ደርሶ በዚያ እንደ ባሪያ ሲያገለግል ኖረ:: በአንድነት የሚኖሩ መነኮሳትንም ያገለግላቸው ነበር የሞተውንም እስከማንሳት ድረስ ከደዌያቸው ይፈውሳቸው ነበር:: በዚያም ዐሥራ ሁለት ዓመት ከሆነው በኋላ ሐይቅ በሚባል ቦታ ወደ ሚኖረው ወደ ኢየሱስ ሞዓ የእግዚአብሔር መልአክ እንዳዘዘው ሔደ:: ከእርሱም የምንኩስና ልብስ ቀሚስና ቅናትን ተቀበለ:: ሁለተኛም ወደ ኢየሩሳሌም ሔዶ ከከበሩ ቦታዎችና ከሊቀ ጳጳሳቱ ቡራኬን ተቀበለ:: ከዚያም ወደ ሸዋ ምድር ተመልሶ የአባቱ ወንድም ልጅ የሆነ አባ ዜና ማርቆስን አገኘው በወግዳ በረሀም በአንድነት ኖሩ:: ከዚያም ግራርያ ወደሚባል አገር ሒዶ በኮረብታ መካከል ዋሻ አዘጋጅቶ ተቀመጠ:: በቀንም በሌሊትም ከዚያ አይወጣም ነበር ከጥቂት ቅጠልም በቀር እህልን አይቀምስም መጠጡም ጥቂት ውኃ ነው:: ብዙ ወንዶችና ሴቶች ወደርሱ መጥተው መነኮሳቶች ሆኑ በአንድ ቤት ውስጥ በአንድ መኝታ ላይ ተኝተው ያድራሉ እርስ በእርሳቸውም አይተዋወቁም:: እነርሱም እንደ ሕፃናት ናቸው: በጸሎትና በቅዳሴ ጊዜም በአንድነት ይቆማሉ በዘመኑ ሰይጣን ስለ ታሠረ ወንዱ ሴቷን ሴት እንደሆነች አያውቅም እንዲሁም ሴቷ ወንዱን ወንድ እንደሆነ አታውቅም:: ከዚህ በኋላ መጠጊያ ሠርቶ በፊቱ በኋላም በቀኙ በግራው የተሳሉ ፍላጻዎችን ተከለ ይህንንም ማድረጉ በመደገፍና በመተኛት እንዳያርፍ ነው በዚያም እግሩ ከቅልጥሙ እስቲሰበር ሰባት ዓመት ቆመ:: በዚያም ወራት ምንም የዕንጨት ፍሬ ወይም ቅጠል ሳይቀምስ ውኃም ሳይጠጣው ኖረ:: ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደርሱ መጣ ከእርሱም ጋራ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ደግሞ የከበሩ ነቢያትና ሐዋርያት ሁሉም ሰማዕታትና ጻድቃን የጳጳሳት አለቆች የመላእክት አለቆችም ከሠራዊቶቻቸው ጋራ አሉ::
Открыть в Telegram