https://youtu.be/wIZUBzxm4Eg?si=T3ywcyN3VWzah6GO #ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት! ለተጨማሪ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ፡ https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment
Открыть в TelegramПосты канала Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)
አምራች ኢንዱስትሪ ለሀገራዊ ዕድገት ዋስትና EED ሕዳር 7/ 2019 ዓ.ም የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ሽግግር ለማፋጠንና ዘላቂ እድገትን ለማረጋገጥ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ የማይተካ ሚና አለው። በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም ማሳደግና ለሀገር ውስጥ ጥቅል ምርት ያላቸውን አስተዋፅኦ ማጠናከር የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ዋና ማዕከል ሆኗል። የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ጉዞ ከብዙ መሰናክሎች በኋላ በመደመር መንግሥት ለዘርፉ በሰጠው ከፍተኛ ትኩረትና በወሰዳቸው የፖሊሲና የመዋቅራዊ ማሻሻያ ርምጃዎች የሀገር ውስጥ ምርታማነትን በማስቀደም ወደ ጠንካራ መዋቅር እየተሸጋገረ ይገኛል። ቀደም ሲል ዘርፉ በጥሬ ዕቃ አቅርቦት መቆራረጥ፣ በውጭ ምንዛሬ እጥረትና በመሠረተ ልማት ውስንነቶች ይፈተን የነበረ ቢሆንም፤ አሁን ላይ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅንቄን ጨምሮ የተቀናጁ የፖሊሲ፣ የፋይናንስና የተቋማት ማሻሻያዎች እየተተገበሩ ይገኛሉ። ባለፉት ዓመታት በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርሙ በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ይታዩ የነበሩ ስር የሰደዱ መዋቅራዊ ችግሮችን ለማቃለልና የዘርፉን የኢኮኖሚ ዋና አንቀሳቃሽነት ሚና ለማሳደግ የመደመር መንግሥት በርካታ የፖሊሲና የተግባር ርምጃዎችን ወስዷል። የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ የማምረት አቅም ለማሳደግ የተተገበሩ አሰራሮች ተጨባጭ ውጤት አስገኝተዋል፡፡ ቀደም ሲል ከውጭ በከፍተኛ ወጪ የሚገቡ የተለያዩ ምርቶች በሀገር ውስጥ በስፋት እንዲመረቱ በመደረጉ በቢሊየን ዶላር የሚቆጠር የውጭ ምንዛሪ ማዳን ተችሏል። ፖሊሲን፣ ፋይናንስን፣ መሠረተ ልማትና የሰው ኃይል ክህሎትን ያቀናጀው ይህ ሀገራዊ ጥረት ተጠናክሮ ሲቀጥል፤ ሀገሪቱ ከግብርና መር ኢኮኖሚ ወደ መዋቅራዊ የኢንዱስትሪ ሽግግር የምታደርገውን ጉዞ በእጅጉ ያፋጥነዋል። በተለይ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ የኢንዱስትሪ ፓርኮች በተፈጠሩ ምቹ ሁኔታዎችና መሰረተ ልማቶች ተጠቅመው ምርቶቻቸውን ለውጭ ገበያ እያቀረቡ የሚገኙ አምራቾች ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደጉ መጥተዋል፡፡ ዘርፉ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ በጽኑ መሰረት ላይ በመገንባት ለኢኮኖሚ እድገት፣ ለተኪ ምርት ማስፋፋትና የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ ወሳኝ ሚና ይኖረዋል፡፡ #ኤፍ ኤም ሲ #ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት! ለተጨማሪ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ፡ https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment
Открыть в Telegramhttps://youtube.com/watch?v=2HJIE9sr9zU&si=j9tV-X35hEhvrFqC #ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት! ለተጨማሪ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ፡ https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment
Открыть в Telegram#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት! ለተጨማሪ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ፡ https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment
Открыть в Telegramhttps://youtu.be/dPtDaHy97G8?si=BUVG2DYwF3pIQbNf #ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት! ለተጨማሪ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ፡ https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment
Открыть в Telegramየኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ጳውሎስ በርጋ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ያደረጉት ቆይታ #ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት! ለተጨማሪ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ፡ https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment
Открыть в Telegramhttps://www.youtube.com/watch?v=-amMZYyU6tE #ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት! ለተጨማሪ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ፡ https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment
Открыть в Telegramየጦሳ ኢንጂነሪንግ የዕድገትና ተኪ ምርት የማምረት ጉዞ ========//////===== በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኘውና ከውጭ የሚገቡ የህክምና ቁሳቁሶችን በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት የተነሳው ጦሳ ኢንጂነሪንግ በዘርፉ አበረታች ስኬቶችን እያስመዘገበ ይገኛል። ከየት ወዴት? በ2007 ዓ.ም በትንሽ ካፒታልና በ5 ሠራተኞች ሥራ የጀመረው ድርጅቱ፣ በአሁኑ ወቅት የሠራተኛ ቁጥሩን ወደ 50 ያደገ ሲሆን በርካታ የባዮሜዲካል፣ ሜካኒካል እና የፋርማሲ ባለሙያዎችን በቋሚነት ቀጥሮ በማሰራት ላይ ነው። ዘመናዊ ቴክኖሎጂ በጀርመን፣ አውሮፓና ቻይና የሚመረቱትን ያህል ጥራት ያላቸውን የሆስፒታል አልጋዎችና ቁሳቁሶች የሌዘር ከቲንግ እና ቤንዲንግ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በማምረት ላይ ይገኛል። የተኪ ምርት ውጤት፡ ከዚህ ቀደም በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ይገቡ የነበሩ የህክምና ዕቃዎችን በሀገር ውስጥ በመተካት የውጭ ምንዛሬ እያዳነ ይገኛል። ድጋፍና የገበያ ትስስር፡ በገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ሙሉ መሰረተ ልማት የተሟላለት ቦታ ያገኘ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አማካኝነትም ሰፊ የገበያና የጥሬ ዕቃ ትስስር መፍጠር ችሏል። በአሁኑ ወቅት የISO ሰርቲፊኬት የመቀበል ሂደት ላይ የሚገኘው ጦሳ ኢንጂነሪንግ፣ በቀጣይ ምርቶቹን ወደ አፍሪካ ሀገራት በመላክ የውጭ ምንዛሬ ለማስገኘት በትጋት እየሰራ ይገኛል። "በሀገር ውስጥ ማምረትና መለወጥ ይቻላል!" አቶ ቢንያም ተስፋዬ (የድርጅቱ መስራችና ባለቤት) ምንጭ፡ የአዲስ አበባ ከተማ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ (https://www.facebook.com/share/p/1A6wuTo6y8/) #ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት! ለተጨማሪ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ፡ https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment
Открыть в Telegram