Кабинет

Посты канала የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

сначала новые

#5230Видео
Просмотры2 200−60%к среднему
Пересылки—
Реакции24
Комментарии—
#5229Фото

ኅዳር ፲፭ ጾመ ነቢያት ጾም በሃይማኖት ምክንያት ከምግብና መጠጥ ተጠብቀው (ተከልከለው) ከአምላክ ጋር የሚነጋገሩበት መንፈሳዊ ዘር የሚዘራበት የአምላክ ፈቃድ ብቻ የሚፈፀምበት የጽድቅ (የሕይወት) በር ነው። ከቤተክርስቲያናችን የሥርዓተ ቀኖና መጽሐፍ የፆምን ትርጉም አንዲህ ብሎ ይተረጉመዋል። 'ሰው ህግን ለሰራለት ለክርስቶስ እየታዘዘ ኃጢአቱን ለማስተስረይ ብዙ ዋጋ ለማግኘት ፈልጎ የፍትወት ሃይል ደካማ ሥጋ ለነባቢት ነፍስ ይገዛለት ዘንድ በሕግ በታወቁ ጊዜያት ከመብል መከልከል ማለት ነው።' ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያናችን ለልጆቿ ከምታስተምራቸውና ለመንፈሳዊ ተጋድሎ ለሥጋዊ ፈቃድ መግቻ ልጓም ለፈቃደ ነፍስ መፈፀሚያ መንገድ ሆኖ ለአማኒያኖቿ ከሰራቻቸው ስርዓቶች አንዱ ጾም ነው። ይህም የድኅነት በር ነው። የጽድቅ መንገድ ነው። ይህም ለአንድ ኦርቶዶክሳዊ አማኝ በሃይማኖት ሲኖር ራሱን እየመረመረና እየፈተነ (2ኛ ቆሮ. 13፥5) የዲያብሎስን ሃይል ድል መንሻ የመንግሰተ ሰማያት መውረሻ ስንቁን ትጥቁን የሚያሳድግበት ብርቱ ጥሩር እንደሆነ ቤተክርስቲያን ሥርዓት ሰርታ ልጆቿን ታስተምራለች። የጾም ወቅት መንፈሳዊ ተጋድሎ የሚበዛበት የጌታን ፍቅር የምንገልፅበት ዲያብሎስን ተዋግተን ድል የምናገኝበት የጦር እቃ የምንለብስበት እግዚአብሔርን በንስሃ ምሕረት ቸርነት የምንጠይቅበት አባታዊ ፍቅርን ቤተሰባዊ ግንኙነታችንን የምናዳብርበት የውስጣችንን ምስጢር ለአምላካችን የምንነግርበት እንዲሁም ምህረትን የምናደርግበት፣ ድሃ አደጎችን ፣ የታመሙትን፣ የሞቱ ነፍሳትን የምናስብበትን ጊዜ ሲሆን በአጠቃላይ በጾም አማካይነት ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ መውደዳችንን የምናሳይበት ከፈቃደ ሥጋ ይልቅ ፈቃደ ነፍስን የምንፈፅምበት ወቅት ነው። የነቢያት ጾም የሚገባው ኅዳር ፲፭ (15) ቀን ሲሆን ጾሙ የሚፈታው በገና በዓል ታኅሣሥ ፳፱ (29) ነው:: ወይም ደግሞ በአራት ዓመት አንዴ በዘመነ ዮሐንስ ታኅሣሥ ፳፰(28) ቀን ይፈታል። ጾመ ነቢያት የተባለበትም ምክንያት ነቢያት የተናገሩት ትንቢት ስለ ተፈጸመበት እንዲሁም በየዘመናቱ የተነሡ ነቢያት እግዚአብሔር ወደፊት ሊያደርግ ያሰበውን በእምነት ዓይን እያዩ ምሥጢር ተገልጦላቸው የራቀው ቀርቦ የረቀቀው ገዝፎ እየተመለከቱ ያዩትም መልካም ነገር እንዲደርስላቸው ስለ ጾሙ ስለ ጸለዩ ነው፡፡ እንዲሁም ነቢያት ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መወለድ፣ እና ለአዳም የተሰጠው ተስፋ ተገልጦላቸው ለተናገሩት ትንቢት ፍጻሜ እንዲያደርሳቸው ፈጣሪያቸውን ተማፀኑት፡፡ በየዘመናቸው «አንሥእ ኃይለከ፣ ፈኑ እዴከ፤ ኃይልህን አንሣ እጅህንም ላክ» እያሉ ጮኹ (መዝ 143/144/:7-8)፡፡ በጾምና በጸሎት ተወስነውም ሰው የሚሆንበትን ጊዜ በቀናት፣ በሳምንታት፣ በወራትና በዓመታት ቆጠሩ፡፡ ... ነቢያት ተስፋው በዘመናቸው ተፈጽሞ በዓይነ ሥጋ ለማየት ባይችሉም እግዚአብሔር «የማያደርገውን አይናገር የተናገረውን አያስቀር» ብለው አምነው ከወዲሁ ተደሰቱ፡፡ ለዘመነ ሥጋዌ ቅርብ የነበሩት እነ ኢሳይያስ ጾሙ እንዴት መፈጸም እንዳለበት ተናግረዋልም (ኢሳ 58:1)፡፡ በመሆኑም በጌታ ልደት ትንቢተ ነቢያት ስለ ተፈጸመበት ይህ ጾም «የነቢያት ጾም» ይባላል፡፡ ስለ ጾሙ መግቢያ የእኛ ቤተ ክርስቲያን የሥርዓታችን መጽሐፍ ፍትሐ ነገሥታችን እንዲህ ይላል፦ <<ወይከውን ከመ ረቡዕ ወዓርብ፤ ወውእቱ ጾም ዘይቀድም እምልደት፤  ወጥንተ ዚኣሁ መንፈቀ ሕዳር ወፋሲካሁ በዓለ ልደት። /የነቢያት ጾም እንደ ረቡዕና እንደ ዓርብ የሆነ፤ ይኸውም ከልደት አስቀድሞ የሚጾም መጀመሪያው የኅዳር እኩሌታ ፋሲካው የልደት በዓል የሆነ ጾም ነው።>> (ፍት.ነገ. ፲፭፥፭፻፷፰):: እግዚአብሔር አምላክ ጾሙን በረከት የምናገኝበት ያድርግልን! አሜን! @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox

Открыть в Telegram
Просмотры2 270−59%к среднему
Пересылки—
Реакции24
Комментарии—
#5225Фото

ኅዳር ፲፪ ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላዕክት ኅዳር ዐሥራ ሁለት በዚች ቀን ለሰው ወገን የሚያዝንና የሚራራ በእግዚአብሔር ጌትነት ዙፋን ፊት ሁልጊዜ በመቆም ለፍጥረቱ ሁሉ የሚማልድ የመላእክት አለቃ በሰማያትም ለሚኖሩ ኃይሎች ሁሉ አለቃቸው ለሆነ ለቅዱስ ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው። ዳግመኛ በዚህች ዕለት ቅዱስ ሚካኤል ኢያሱን የተራዳበት ቀን ነው። ይህም በንጉሥ ጭፍራ አምሳል በታላቅ ክብር ሁኖ የነዌ ልጅ ኢያሱ ያየው ነው ከእኛ ሰዎች ወገን ነህን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ አለው። እኔስ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ነኝ አሁንም ወዳንተ መጥቻለሁ አለው ። ኢያሱም ወደ ምድር በግንባሩ ተደፍቶ ሰገደለትና በእኔ በባሪያህ ዘንድ ምን አቁሞሃል አለው ። የእግዚአብሔር የሠራዊቱም አለቃ ሚካኤል ኢያሱን የቆምክባት ምድር የከበረች ቦታ ናትና ጫማህን ከእግርህ አውልቅ አለው ኢያሱም እንዳለው አደረገ ። እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለው በውስጧ ያለውን ንጉሧን ከኃያላኑና ከአርበኞቹ ጋር በእጃችሁ ኢያሪኮን እነሆ አስገባታለሁ ። ይህም የከበረ መልአክ ከቅዱሳን ሰማዕታት ጋር በመሆን ገድላቸውን እስከ ሚፈጽሙ የሚያጸናቸውና የሚያስታግሣቸው ነው ። ስለዚህም ስለ ልዕልናውና ስለ አማላጅነቱ በየወሩ በዐሥራ ሁለት ቀን ለመታሰቢያው በዓል ተሠራለት እርሱ ስለ እኛ የምድሩን ፍሬ ይባርክልን ዘንድ ዝናሙንም በጊዜው እንዲአወርድልን የወንዙንም ውኃ እንዲመላልን ነፋሱንም የምሕረት ነፋስ እንዲአደርግልን ሁሉንም የተስተካከለ እንዲአደርግልን ወደ እግዚአብሔር በጸሎት ይማልድልናልና። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ጸሎት ይማረን የቅዱስ ሚካኤል በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox

Открыть в Telegram
Просмотры4 010−28%к среднему
Пересылки—
Реакции44
Комментарии—
#5223Аудио
Просмотры5 290−5%к среднему
Пересылки—
Реакции41
Комментарии—
#5221Фото

ኅዳር ፰ አርባዕቱ እንስሳ ኅዳር ስምንት በዚች ቀን ሥጋ የሌላቸው የአርባዕቱ እንስሳ በዓላቸው ሆነ። እሊህም መንበሩን የሚሸከሙ የእግዚአብሔር ሠረገላዎቹ ናቸው። ስለ እሳቸውም ወንጌልን የጻፈ ዮሐንስ እንዲህ ሲል እንደመሰከረ በዚያ ዙፋን ፊት በረድ የሚመስል ባሕር አለ በዙፋኑም ዙሪያ አራት እንስሶች አሉ በፊትም በኋላም ዐይንን የተመሉ ናቸው። የፊተኛው አንበሳ ይመስላል ሁለተኛውም ላም ይመስላል ሦስተኛውም የሰው መልክ ይመስላል አራተኛውም የሚበር አሞራ ይመስላል። የእሊህም የአራቱ እንሰሶች እያንዳንዱ ክንፋቸው ስድስት ስድስት ነው ሁለንተናቸውም ዐይኖችን የተመሉ ናቸው። የነበረ የሚኖር የአማልክት አምላክ እግዚአብሔር ጽኑዕ ክቡር ልዩ ነው እያሉ በመዓልትና በሌሊት ዕረፍት የላቸውም። ሁለተኛውም ስለእርሳቸው ኢሳይያስ እንዲህ አለ ከዚህም በኋላ ንጉሡ ኦዝያን በሞተ ጊዜ አሸናፊ እግዚአብሔርን ሰፊ በሆነና ከፍ ከፍ ባለ ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ብርሃኑም ቤቱን መልቶ ሱራፌልም በዙሪያው ቁመው አየሁት። የአንዱም የአንዱም ክንፋቸው ስድስት ነው በሁለቱ ክንፋቸው ፊታቸውን በሁለቱ ክንፋቸው እግሮቻቸውን ይሸፍናሉ በሁለቱ ክንፎቻቸው ከጽንፍ እስከ ጽንፍ ይበራሉ። አንዱም አንዱም ከአንዱ ጋራ ፍጹም አሸናፊ የሆንክ እግዚአብሔር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ተብለህ የምትመሰገነው ምስጋናህ በምድርና በሰማይ የመላ ነው እያሉ ያመሰግናሉ። ነቢይ ዳዊትም በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ አለ ሁለተኛም በኪሩቤል ላይ የተቀመጠ እርሱ ምድርን አናወጻት አለ። ሕዝቅኤልም እንዲህ አለ ከወደ ሰሜን እነሆ ጥቅል ነፋስ ሲመጣ አየሁ ታላቅ ደመና አለ በዙሪያውም ብርሃን አለ ከእሱም እሳት ቦግ ብሎ ይወጣል። በደመናውም መካከል ባለ በእሳቱ ውስጥ እንደ አራት ራስ አሞራ መልክ የሚመስል አለ በመካከሉም እንደ አራቱ ኪሩቤል መልክ ያለ አለ። መልካቸውም እንዲህ ነው በውስጣቸው የሰው መልክ አላቸው የአንዱም የአንዱ ፊቱ አራት ነው ክንፉም አራት ነው። እግራቸውም የቀና ነው ከእግራቸውም ክንፍ አላቸው ሰኮናቸው ግን እንደ ላም ሰኮና ነው ከሱም እሳት ቦግ ይላል እንደጋለ ብረት ፍንጣሪም ይበራል። ወንጌላዊ ዮሐንስም ዳግመኛ እንዲህ አለ በዚያው ዙፋን ዙሪያ የብዙ መላእክትን ድምፅ የእንስሶቹንም የእነዚያ አለቆችንም ቃል ሰማሁ ቁጥራቸውም እልፍ አለቆች ያሉአቸው ብዙ የብዙ ብዙ ነው። ለዚያ ለተገደለው በግ ኃይልን፣ ባለጸግነትን፣ ጥበብን፣ ጽናትን፣ መንግሥትን፣ ክብርን፣ ጌትነትን፣ ምስጋናን ገንዘብ ሊያደርግ ይገባዋል ብለው በታላቅ ቃል ተናገሩ። በሰማይና በምድር ከምድር በታች በባሕር ውስጥ በእነዚያም ውስጥ የተፈጠረው ፍጥረት ሁሉ ጌትነት ክብር ኃይል በረከት በዙፋኑ ለተቀመጠው ለሱ ለበጉም ለዘላለሙ ይገባዋል አሉ። በእውነት ይገባዋል። እሊህም አራቱ እንስሶች አሜን ይላሉ። እሊያም አለቆች ይሰግዳሉ። ስለ ልዕልናቸውና ስለ ክብራቸው ለእሊህ አርባዕቱ እንሰሳ ከብሉይና ከሐዲስ ብዙ መጻሕፍት መስክረዋል መሐሪና ይቅር ባይ እግዚአብሔርም ስለ ሁሉ የሰው ፍጥረት ይለምኑት ዘንድ ቀራቢዎቹ አደረጋቸው። ዳግመኛም እንዲህ ተባለ ገጸ ሰብእ ስለ ሰው ፍጥረት ይለምናል። ገጸ አንበሳ ስለ አራዊት ይለምናል ገጽ ላሕም ስለ እንስሳ ይለምናል ገጸ ንስርም ስለ አዕዋፍ ይለምናል ከሰማይ ሠራዊት ሁሉ እነርሱ በእግዚአብሔር ዘንድ በባለሟልነት እጅግ የቀረቡ ናቸውና። ስለዚህም በዓለሙ ሁሉ በስማቸው አብያተ ክርስቲያን እንዲታነፁ በዚችም ቀን መታሰቢያቸው እንዲደረግ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አዘዙ እነርሱ ስለ ሰው ወገን በእግዚአብሔር ዘንድ ይማልዳሉና። ©ስንክሳር @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox

Открыть в Telegram
Просмотры4 670−16%к среднему
Пересылки—
Реакции23
Комментарии—
#5216Аудио
Просмотры4 490−19%к среднему
Пересылки—
Реакции26
Комментарии—
#5215Фото

ኅዳር ፯ የቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕት ቅዳሴ ቤቱ ከበረች ኅዳር ሰባት በዚህችም ቀን የልዳ ሀገር የሆነ የሰማዕታት አለቃ የታላቁ መስተጋድል የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የከበረችበት ነው ዳግመኛም ጌታችን በውስጧ ላደረገው ድንቅ ተአምር መታሰቢያ ሆነ። ይህም እንዲህ ነው በውስጧ ድንቆች ተአምራት እንደሚሠሩ ከሀዲ ዲዮቅልጥያኖስ በሰማ ጊዜ ሊአፈርሳት አሰበ ስሙ አውህዮስ የሚባለውንም መኰንን ከብዙ ሠራዊት ጋር ላከው፤ ያም መኰንን በደረሰ ጊዜ የቅዱስ ጊዮርጊስ ሥዕል ወዳለበት አዳራሽ በትዕቢት ሆኖ ገባ። በሥዕሉም ፊት በብርጭቆ መቅረዝ መብራት ነበረ በቤተ ክርስቲያኒቱና በቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ እየዘበተ በእጁ በያዘው በትር የመብራቱን መቅረዝ መትቶ ሰበረው የመቅረዙም ስባሪ ወደ ከሀዱው ራስ ደርሶ መታው ራሱንም ታመመ ፍርሃትና እንቅጥቅጥም መጣበት ወድቆም ተዘረረ ባልንጀሮቹም ወደ አገሩ ሊወስዱት ተሸከሙት በክፉ አሟሟትም ተጐሳቊሎ ሞተ ወስደውም ከባሕር ጣሉት ወገኖቹም ወደ ሀገራቸው አፍረው ተመለሱ። ከሀዲ ዲዮቅልጥያኖስም ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ በልዳ ሀገር ያለች የቅዱስ ጊዮርጊስን ቤተ ክርስቲያን ያፈርሳት ዘንድ ራሱ ተነሥቶ ሔደ በዚያንም ጊዜ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ መታው ሰባት ዓመት ያህልም ዐይኖቹ ታውረው አእምሮውንም አጥቶ ቁራሽ እንጀራም እየለመነ ኑሮ ሞተ። ክብር ይግባውና ጌታችንም የቤተ መንግሥቱን ሰዎች አስነሣበት እርሱን አስወግደው ጻድቅ ሰው ቁስጠንጢኖስን በእግዚአብሔር ፈቃድ አነገሡት እርሱም በአዋጅ የጣዖታትን ቤቶች ዘግቶ አብያተ ክርስቲያናትን ከፈተ ለክርስቲያን ወገኖችም በሁሉ ዓለም ተድላ ደስታ ሆነ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕቱ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox

Открыть в Telegram
Просмотры5 350−3%к среднему
Пересылки—
Реакции43
Комментарии—
#5214Текст

የኅዳር ፮ ቁስቋም ሥርዓተ ማኅሌት 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 ነግሥ (የማንኛውም ወርኃ  በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ) ለማንኛውም ወርኃዊ እና ዓመታዊ ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ ..................................................... ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል። መልክአ ሥላሴ ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ በሣህል፤ እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል። ዚቅ ስብሐት ለኪ ኦ ወላዲተ እግዚአ ኲሉ አኮቴት ወክብር ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለመ ዓለም አሜን ወልድኪ ሣህሎ ይክፍለነ ሰዓሊ ለነ ቅድስት። ነግስ/ለልሳንከ/ ሰላም ለልሳንከ መዝሙረ ቅዳሴ ዘነበልባል፤ ወለድምፀ ቃልከ ሐዋዝ ቀርነ መንግሥቱ ለቃል፤ ሞገሰ ክብሩ ሚካኤል ለተላፊኖስ ባዕል፤ አልቦ ዘይትማሰለከ በልማደ ምሕረት ወሳሕል፤ እንበለ ባሕቲታ እኅትከ ማርያም ድንግል። ዚቅ ተውህቦ ምሕረት ለሚካኤል ወብሥራት ለገብርኤል ወሀብተ ሰማያት ለማርያም ድንግል። ዘጣዕሙ ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤ መሠረተ ህይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤ እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ። ዚቅ ንዒ ርግብየ ኲለንታኪ ሠናይት ፀምር ፀዓዳ እንተ አልባቲ ርስሐት መሶበ ወርቅ እንተ መና በትረ አሮን እንተ ሠረፀት። ወረብ፦ ፀምር ፀዓዳ መሶበ ወርቅ እንተ መና መሶበ ወርቅ/2/ በትረ አሮን እንተ ሠረፀት እንተ ሠረፀት መሶበ ወርቅ/2/ ሰቆቃወ ድንግል በስመ እግዚአብሔር በስመ እግዚአብሔር ሥሉስ ህፀተ ግፃዌ ዘአልቦ፤ ሰቆቃወ ድንግል እጽህፍ በቀለመ አንብዕ ወአንጠብጥቦ፤ ወይሌ ወላህ ለይበል ዘአንበቦ፤ ከማሃ ኃዘን ወተሰዶ ሶበ በኲለሄ ረከቦ፤ ርእዮ ለይብኪ ዓይነ ልብ ዘቦ። ወረብ ከማሃ ኃዘን ከማሃ ኃዘን ወተሰዶ ኃዘን/2/ ሶበ በኲለሄ ረከቦ ከማሃ ኃዘን/2/ ዚቅ አዘክሪ ድንግል ረኃበ ወጽምዓ ምንዳቤ ወኃዘነ ወኲሎ ዓፀባ ዘበጽሐኪ ምስሌሁ። ወረብ ረኃበ ወጽምዓ አዘክሪ ድንግል ረኃበ ወጽምዓ/2/ ምንዳቤ ወኃዘን አዘክሪ ድንግል/2/ ሰቆቃወ ድንግል ምዕረ በዘባንኪ ወምዕረ በገቦኪ፤ ማርያም ብዙኃ በሐዚለ ሕፃን ደከምኪ፤ ሶበኒ የሐውር በእግሩ ከመ ትፁሪዮ ይበኪ፤ አልቦ እንበለ ሰሎሜ ዘያስተባርየኪ ለኪ፤ ወዮሴፍ አረጋዊ ዘይፀውር ስንቀኪ። ወረብ አልቦ እንበለ ሰሎሜ ዘያስተባርየኪ ለኪ/2/ ወዮሴፍ አረጋዊ ዘይፀውር ስንቀኪ/2/ ዚቅ ሐዊረ ፍኖት በእግሩ ሶበ ይስዕን ሕፃንኪ ያንቀዓዱ ኀቤኪ ወይበኪ እኂዞ ጽንፈ ልብስኪ እስከ ትፀውሪዮ በገቦኪ ወትስዕሚዮ በአፉኪ። ሰቆቃወ ድንግል አብርሂ አብርሂ ናዝሬት ሀገሩ፤ ንጉሥኪ በጽሐ ዘምስለ ማርያም መፆሩ፤ ጣዖታተ ግብፅ ኲሎ ቀጥቂጦ በበትሩ፤ ይጒየዩ ወይትኃፈሩ ሠራዊተ ሄሮድስ ፀሩ፤ ዘበላዕሌሁ እኩየ መከሩ። ዚቅ አብርሂ አብርሂ ኢየሩሳሌም በጽሐ ብርሃንኪ ወስብሐተ እግዚአብሔር ወብርሃኑ ሠረቀ ላዕሌኪ አብርሂ ጽዮን በጽሐ ብርሃንኪ ተጽዒኖ ዲበ ዕዋል በሰላም ቦአ ኀቤኪ። ወረብ አብርሂ አብርሂ ኢየሩሳሌም/2/ በጽሐ ብርሃንኪ ኢየሩሳሌም (ደብረ ... እከሌ)/2/ ምልጣን ዮም ጸለሉ መላእክት ላዕለ ማርያም፤ወላዕለ ወልዳ ክርስቶስ በደብረ ቊስቋም፤ እንዘ ይብሉ ስብሐት በአርያም፤ አማን፤ ወበምድር ሰላም። እስመ ለዓለም ዘሰንበት ይቤ ዳዊት በመዝሙር ፤መሠረታቲሀ ውስተ አድባረ ቅዱሳን፤ወካዕበ ይቤ ቀደሰ ማህደሮ ልዑል ፤ ወይቤ ዝየ አኃድር እስመ ኃረክዋ፤ ማ፦ እግዚአ ለሠንበት በከርሣ ተፀውረ ፤ሰማየ ወምድር ዘውእቱ ፈጠረ @Ethiopian_Orthodox

Открыть в Telegram
Просмотры4 500−19%к среднему
Пересылки—
Реакции48
Комментарии—
#5212Фото

ኅዳር ፮ እመቤታችን ከተወደደ ልጇ ጋር ደብረ ቁስቋም የገባችበት ኅዳር ስድስት በዚህች ዕለት ክብርት እመቤታችን ከተወደደ ልጇ ጋር ከስደት በሚመለሱበት ጊዜ ደብረ ቁስቋም ገብተው ካገኛቸው ድካም ዐረፉ፡፡ አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች ክብርት እመቤታችን ከስደት በተመለሰች ጊዜ እንዲህ ሆነ፡- የብርሃን እናቱ ክብርት እመቤታችን ልጇን ይዛ ከእነ ዮሴፍ ጋር ወደ ምድረ ግብፅ ስትሰደድ ግብፅ ደርሰው በዚያ ቢቀመጡም ነገርን ግብፅ አልተመቸቻውም፡፡ ሕዝቡም በሰላም አልተቀበላቸውም፡፡ እንዲያውም በምድረ ግብፅ ብዙ ተሠቃይተዋል፡፡ ከግብፅም ተነሥተው ወደ ኢትዮጵያ በመጡ ጊዜ ግን ኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉ በሰላምና በፍቅር ተቀበላቸው፡፡ ከመንገዱና ከርሃብ ጥሙ ጽናት የተነሣ እጅግ ደክማለችና የኢትዮጵያ ሰዎች እመቤታችንን አይተው እጅግ አዘኑላት፡፡ ‹‹ይህችስ የነገሥታት ዘር ትመሥላለች ነገር ግን አንዳች ችግር አጋጥሟት ተሰዳ ወደ ሀገራችን መጥታለች..›› ብለው እንክብካቤን አደረጉላት፡፡ እግራቸውን አጥበው በክብር ማረፊያዎች ላይ አሳረፏቸው፡፡ መልካም መስተንግዶም አደረጉላቸው፡፡ እመቤታችንም ከድካሟ ካረፈች በኋላ ሀገሪቱን በእጅጉ ወደደቻትና የተወደደ ልጇን ‹‹ይህን ሀገርና ሕዝቧን በመላ ወድጃቸዋልሁና በዚህ እስከ መጨረሻው እንኑር›› አለችው፡፡ ጌታችንም ክብርት እናቱን ‹‹ይህች ቅድስት ሀገር ናት፣ በኋለኛው ዘመን የቅዱሳን መነኮሳት ቦታ ትሆናለች፡፡ በውስጧም እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ እመሰገንባታለሁ፤ የአንቺም ስም ሳይጠራ አይውልባትም›› አላት፡፡ ከዚህም በኋላ ጌታችን ደመና ጠቅሶ በእርሷ ላይ ተቀመጡ፡፡ መልአኩ ቅዱስ ዑራኤልም መጣና እየመራቸው መላ ኢትዮጵያን ጎበኟት፡፡ እመቤታችንም ሀገሪቱንና ሕዝቦቿን ወዳቸዋለች ደስም ተሰኝታባቸዋለችና ጌታችን ለክብርት እናቱ ‹‹ይህችን ቅድስት ሀገር አሥራት አድርጌ ሰጠሁሽ›› አላት፡፡ እመቤታችንም እጅግ ተደስታ ‹‹ልጄ አምላኬ›› ብላ አመሰገነችው፡፡ ከዚህም በኋላ ከአንዱ ቦታ ወደ አንዱ ቦታ እየተዘዋወሩ መላዋ ኢትዮጵያን በኪደተ እግራቸው ባረኳት፡፡ ጌታችንም ‹‹በዚህ ቦታ እንዲህ ዓይነት ቤተ ክርስቲያን ይታነጻል፤ እከሌ የሚባል እንዲህ ዓይነት ቅዱስ ይነሣል…›› እያለ ብዙ ምሥጢራትን ለክብርት እናቱ ነገራት፡፡ ከዚህም በኋላ የስደቱ ዘመን ሲያልፍ ሄሮድስም በመጨረሻ ክፉ አሟሟትን ሲሞት መልአኩ ወደ ገሊላ አውራጃ እንዲመለሱ ነገራቸው፡፡ እመቤታችንም ‹‹ከዚህች ሀገርስ ባንሄድ እመርጣለሁ›› ስትለው የተወደደ ልጇ ግን ‹‹እናቴ ሆይ ጽድቅንና ፈቃድን ሁሉ ልንፈጽም ይገባናል›› ብሎ አጽናናትና ወደ ሀገራቸው ተመልሰው ሄዱ፡፡ ተመልሰውም ሊሄዱ ሲነሡ የኢትዮጵያ ሰዎች ልዩ ልዩ አምሐ እጅ መንሻ ሰጧቸው፡፡ ልዩ ልዩ ልብሶች፣ ወርቅ፣ ዕጣን፣ ከርቤ፣ ሽቱ እና ሥንቀቸውን በግመሎች ላይ ጭነው እመቤታችንንና የተወደደ ልጇንም በበቅሎ ላይ አስቀምጠው በክብር ሸኟቸው፡፡ እመቤታችንም ልጇን ታቅፋ በበቅሎ ተቀምጣ በበረሃው በመጓዝ ወደ መጣችበት አገር ሄደች፡፡ ኢትዮጵያንም የሰጧትን ብዙ እጅ መንሻዎች በግመሎች ጭና ይዛ ወደ አገሯ በተመለሰች ጊዜ ከአንድ ባሕር ዳር ደረሰች፡፡ ከዚያም የጀልባውን ባለቤት ‹‹እግዚአብሔርን ስለመውደድ አሻግረኝ›› ብላ ለመነችው፡፡ ባለጀልባውም ‹‹እነሆ ዕቃ የተጫኑ አምስት ግመሎችና ከአንቺ ጋር ከዚህም ሕፃን ጭምር አምስት ሰዎች እመለከታለሁ፣ አንቺ የተቀመጥሽባት በቅሎም አለች፡፡ ጀልባዋም ታናሽ ናት፣ የመቀመጫ ክፍሏም በውስጧ የተሳፈሩት ሰዎችም ተጨናንቀው ነው ያሉት፡፡ ስለዚህ እንዴት ላሻግርሽ እችላለሁ? ነገር ግን እመቤቴ ሆይ! ይቅርታ አድርጊልኝ ይህን በክፋት አላደረግሁትምና›› አላት፡፡ ክብርት እመቤታችንም የጀልባው ባለቤት ሊያሻግራት እንዳልቻለ በተረዳች ጊዜ ‹‹ልጄ ሆይ የእግዚአብሔር ልጅ እንደመሆንህ ይህን ትልቅ ወንዝ ለመሻገር የአምላክነትህን ሥራ ትሠራ ዘንድ እለምንሃለሁ›› ስትል ማለደችው፡፡ ያንጊዜም ጌታችን ክብርት እናቱን ‹‹የወለደሽኝ እናቴ ሆይ! አትዘኝ›› ብሎ አረጋጋት፡፡ ዳግመኛም ‹‹በእኔ ፈቃድ በአባቴ ፈቃድ በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ካንቺ ሰው ሆኛለሁና ሰው መሆኔንም ከአባቴ በቀር መስተፍሥሒ ከሚሆን ከመንፈስ ቅዱስም በቀር ያወቀ የለም፡፡ ዳግመኛም በሕያዋንና በሙታን ለመፍረድ ለሁሉም እንደየሥራው እከፍለው ዘንድ እመጣለሁ፡፡ ያችንም ሰዓት የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ የአዳም ልጆችም ቢሆኑም ከእኔና ከአባቴ ከመንፈስ ቅዱስም በቀር የሚያውቃት የለም፡፡ ያንጊዜ ‹ዐመፅን የሚናገር አንደበት ሁሉ ይዘጋል› ብሎ አባትሽ ዳዊት እንደተናገረ እከራከራለሁ የሚል አንደበት እንደድዳ ምላሽ ያጣል›› አላት፡፡ ክብርት እመቤታችን ማርያምም ይህንን ሁሉ ምሥጢር የተወደደ ልጇ የነገራትን ታስተውለው በልቧም ትጠብቀው ነበር፡፡ ጌታችንም አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ለክብርት እናቱ ይህንን ከነገራት በኋላ ቀኝ እጁን ዘርግቶ ከወንዙ ማዶ ጢር በሚባል ተራራ ያሉትን ድንጋዮች ጠቀሳቸው፡፡ ያንጊዜም እነዚህ ድንጋዮች እየተገለባበጡ መጥተው እንደ ጀልባ ሆነው በወራጁ ወንዝ ላይ ተንሳፈፉ፡፡ ከዚያም እመቤታችንን ከሕፃኑ ጋር ከነቤተሰቧና ከነጓዟ አሻገረሯት፡፡ እነዚህንም ድንጋዮች ያዩ ሰዎች ሁሉ እጅግ አድንቀው ‹‹ብቻውን ድንቅ ተአምራት ያደረገ፣ እስራኤልን የፈጠረ እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን የጌትነቱም ስም የተመሰገነ ነው›› እያሉ አመሰገኑ፡፡ እነዚህም የተባረኩ ሰዎች ወንዙን ከተሻገሩ በኋላ በዚህች አገር ለስምንት ቀን ተቀመጡ፡፡ ከዚህም በኋላ አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች ክብርት እመቤታችን ስለደረገላት መልካም ሥራ ሁሉ እግዚአብሔርን ፈጽማ እያመሰገነች ወደ አባቷ ወደ ዳዊት አገር ተመለሰች፡፡ ዳግመኛም በኋለኛው ዘመን ጌታችን በዚህ በደብረ ቍስቋም ቅዱሳን ሐዋርያቶቹን ሰበሰባቸውና ታቦትንና ቤተ ክርስቲያንን አክብሮ የቍርባን መሥዋዕትንም ሠርቶ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለወገኖቹ ሰጣቸው፡፡ ለዚህም ነገር የእስክንድርያ አገር ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱሳን አባቶቻችን ቄርሎስና ቴዎፍሎስ ምስክሮቹ ሆኑ፡፡ እመቤታችን ማርያም የአስራት ሀገሯን ሀገራችንን ኢትዮጵያን ከገባችበት መአት ታውጣልን። ~ አሜን ~ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox

Открыть в Telegram
Просмотры5 940+7%к среднему
Пересылки—
Реакции54
Комментарии—
#5202Текст

🔔ዛሬ ምን ይቀደሳል? የማኅሌተ ጽጌ የዐምስተኛ(መጨረሻ) እሑድ ግጻዌ [ጥቅምት ፳፱] መልእክታት ➊ ወደ ቆላስይስ  ፩ : ፩ - ፲፪ ➋ መልእክተ ያዕቆብ ፩ : ፩ - ፲፫ ➌ ግብረ ሐዋርያት ፲፫ : ፮ - ፲፮ ምስባክ መዝ ፩ ÷ ፫ - ፮/1 ÷ 3 - 7 "ወይከውን ከመ ዕፅ እንተ ትክልት ኃበ ሙሐዘ ማይ። እንተ ትሁብ ፍሬሃ በበገዜሃ። ወቈጽላኒ ኢይትነገፍ፡፡" "እርሱም ይሆናል፤ በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለች ዛፍ፥ ፍሬዋን በየጊዜዋ እንደምትሰጥ፥ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ" ወንጌል ማቴ ፮ ÷ ፳፭ - ፍጻሜ/6 ÷ 25 - ፍጻሜ "፳፭ ስለዚህ እላችኋለሁ፥ ስለ ነፍሳችሁ በምትበሉትና በምትጠጡት፥ ወይም ስለ ሰውነታችሁ በምትለብሱት አትጨነቁ፤ ነፍስ ከመብል ሰውነትም ከልብስ አይበልጥምን? ፳፮ ወደ ሰማይ ወፎች ተመልከቱ፤ አይዘሩም አያጭዱምም በጎተራም አይከቱም፥ የሰማዩ አባታችሁም ይመግባቸዋል፤ እናንተ ከእነርሱ እጅግ አትበልጡምን? ፳፯ ከእናንተ ተጨንቆ በቁመቱ ላይ አንድ ክንድ መጨመር የሚችል ማን ነው? ፳፰ ስለ ልብስስ ስለ ምን ትጨነቃላችሁ? የሜዳ አበቦች እንዴት እንዲያድጉ ልብ አድርጋችሁ ተመልከቱ፤ ፳፱ አይደክሙም አይፈትሉምም፤ ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ሰሎሞንስ እንኳ በክብሩ ሁሉ ከነዚህ እንደ አንዱ አልለበሰም። ፴ እግዚአብሔር ግን ዛሬ ያለውን ነገም ወደ እቶን የሚጣለውን የሜዳን ሣር እንዲህ የሚያለብሰው ከሆነ፥ እናንተ እምነት የጎደላችሁ፥ እናንተንማ ይልቁን እንዴት? ፴፩ እንግዲህ። ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤ ፴፪ ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና። ፴፫ ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። ፴፬ ነገ ለራሱ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ፤ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል።" ቅዳሴ ዘእግዝእትነ (ጐሥዓ) - በዕዝል ዜማ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox

Открыть в Telegram
Просмотры8 180+48%к среднему
Пересылки—
Реакции32
Комментарии—
#5201Текст

በመረግድ- 👉ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል። በቁም 👉ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል። በመረግድ 👉ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል። በቁም 👉ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ "ልዑል" ብለው እንደጨረሱ እንደሌላው መልክዕ ስምዓኒ ተብሎ በመረገድ አይባሉም እዛው በቁም እንደተባለ ሁሉም ጽናጽሉን አስቀምጦ በጉረሮ 👇👇 ትርጉም፦ 👉አቤቱ ጸሎቴን ስማኝ ምስጋና አቀርባለኹ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ 👉ጩኸቴም በፊትኽ ይድረስ ምስጋና አቀርባለኹ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ 👉ፊትኽን ከእኔ አትመልስ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ 👉በችግሬ ጊዜ ጆሮኽን ወደ እኔ አድምጥ ምስጋና አቀርባለኹ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ 👉በምጠራኽ ጊዜም ፈጥነኽ ስማኝ ምስጋና አቀርባለኹ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ንወድሶ ለዘሀሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል። 👉 ለዘለዓለሙ ምስጋና አቀርባለኹ። ያ ማለት ያለ ልዑል እግዚአብሔርን እናመስግነው ማለት ነው። በአንዲት ቃል ዓለምን ኹሉ የፈጠረ አምላክ ፈጽሞ የተመሰገነ ነው። መልክአ ሥላሴ ሰላም ለኵልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወፀ ለሣህል፤እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል፡፡ ትርጉም በአካል ለተካከሉ ኵልያቶቻችሁ ሰላምታ ይገባል፤ ሥላሴ! ከእናንተ አንዱ እግዚአብሔር ቃል ዓለማችሁን ለይቅርታ በጎበኘ ጊዜ የአባቶች ተስፋ በድንግል ማርያም ተፈጸመ በቀራንዮመሰ መድኀኒት መስቀል ተተከለ። ዚቅ፦ ሃሌ ሉያ ትወፅእ በትር እምሥርወ ዕሤይ ወየዐርግ ጽጌ ይእቲ በትር አምሳለ ማርያም ቅድስት ይእቲ ወጽጌ ዘወጽአ እምኔሃ አምሳሉ ለወልድ ኀደረ ላዕሌሃ ቃል ሥጋ ኮነ ወተወልደ እምኔሃ። ትርጉም ከዕሴይ ሥር በትር ትወጣለች፤ ከእርሷም አበባ ይወጣሉ፤ ያቺ በትር የቅድስት ማርያም ምሳሌ ናት፤ የእግዘአብሔር ወልድ አምሳያ የሆነው ከእርሷ የወጣው አበባ በላይዋ ላይ አደረ፤ ቃሌ ሥጋ ሆነ፤ ከእርሷም ተወለደ። ዓዲ ዚቅ ሃሌ ሉያ ለአብ፤ሃሌ ሉያ ለወልድ፤ሃሌ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ፤ንዕዱ ማዕዶተ ንትካፈል ርስተ፤ኀበ ጽጌ ዘሠምረ፤ኀበ አስተዳለወ ዓለመ ክቡረ፤ምስለ ማርያም ንትፈሣሕ ኅቡረ። ትርጉም ለአብ ምስጋና ይገባል ለወልድም ምስጋና ይገባል ለመንፈስ ቅዱስም ምስጋና ይገባል ወደዚያ እንሻገር ርስትን እንካፈል ወደያማረ አበባ የከበረ አለምን ወደ አዘጋጀ ከማርያም ጋራ በአንድነት እንደሰት ። ማኅሌተ ጽጌ ኢየኃፍር ቀዊመ ቅድመ ስእልኪ ወርኃ ጽጌረዳ አመ ኃልቀ፤ዘኢየኃልቅ ስብሐተኪ እንዘ እሴብሐኪ ጥቀ፤ተአምርኪ ማርያም ከመ አጠየቀ፤ጸውዖ ስምኪ ያነሥእ ዘወድቀ፤ኃጥአኒ ይሬሲ ጻድቀ፡፡ #ትርጕም የአበባው ወቅት ባለቀ ጊዜ በማያልቅ ምስጋናሽ እያመሰገንኩሽ ከሥዕልሽ ፊት መቆምን አላፍርም። ማርያም! ተአምርሽ እንደሚያስረዳው ስምሽን መጥራት የወደቀውን ያነሳል በደለኛውንም ጻድቅ ያደርጋል። ወረብ ኢየኃፍር ቀዊመ ቅድመ ስእልኪ ወርኃ ጽጌ ረዳ አመ ኃለቀ/፪/ ዘኢየኃልቅ ስብሐተ ስብሐተ እንዘ እሴብሐኪ/፪/ #ትርጕም የአበባው ወቅት ባለቀ ጊዜ ከሥዕልሽ ፊት መቆምን አላፍርም። በማያልቅ ምስጋናሽ እያመሰገንኩሽ። ዚቅ እለትነብሩ ተንሥኡ ወእለ ታረምሙ አውሥኡ፤ማርያምሃ በቃለ ስብሐት ጸውዑ፤ቁሙ ወአጽምዑ ተአምረ ድንግል ከመ ትስምዑ፤ጸልዩ ቅድመ ስዕላ ለቅድስት ድንግል ፤መርዓተ አብ ወእመ በግዑ፡፡ #ትርጕም የተቀመጣችሁ ተነሡ ዝም ያላችሁም አመስግኑ፤ ማርያምን በምስጋና ቃል ጥሩ፤ የድንግልን ተአምር ትሰሙ ዘንድ ቆማችሁ አድምጡ። በአብ ሙሽራ በበግዑ እናት በቅድስት ድንግል ሥዕል ፊት ጸልዩ። ወረብ እለ ትነብሩ ተንስኡ ወእለ ተረምሙ አውስዑ ማርያምሀ በቃለ ስብሐት ፀውኡ/፪/ ጸልዩ ቅድመ ስዕል ለቅድስት ድንግል እመ በግ ወመርዓተ አብ/፪/ #ትርጕም የተቀመጣችሁ ተነሡ ዝም ያላችሁም አመስግኑ ማርያምን በምስጋና ቃል ጥሩ፤ በአብ ሙሽራ በበግዑ እናት በቅድስት ድንግል ሥዕል ፊት ጸልዩ። ማኅሌተ ጽጌ ኦዝ መንክር በዘዚአኪ አምሳል፤ኮከበ ትንቢት ዘቦቱ መልክአ ሕፃን ሥዑል፤ሠረቀ ያርኢ ተአምርኪ ድንግል፤ ወመርሆሙ ለሰብአ ሰገል እምርኁቅ ደወል፤ጽጌኪ ኀበ ሀሎ ይሰክብ በጎል። ትርጉም ድንግል ሆይ! ይህ ምንኛ ድንቅ ነው! የሕፃን መልክ ሥዕል ያለበት(የተሣለበት) የትንቢት ኮከብ፣ ተአምርሽን ያሳይ ዘንዴ ወጣ፤ ሰብአ ሰገልንም ከሩቅ አውራጃ ጀምሮ አበባሽ(ልጅሽ) ወደ አለበት  (ወደ ተኛበት) ቦታ መራቸው። ወረብ ኮከበ ትንቢት ዘቦቱ  መልክአ ሕፃን ሠረቀ ያርኢ ተአምር/፪/ ኀበ ሀሎ ጽጌኪ ይሰክብ በጎል መርሆሙ ለሰብአ ሰገል/፪/ ዚቅ ቡርክት አንቲ ማርያም ወቡሩክ ፍሬ ከርሥኪ ፀሐይ ብሩህ ወወርኅ ንጹሕ ኮከብ ሥርግው ኀበ ማርያም ኀደረ። ትርጉም ማርያም ሆይ! አንቺ የተባረክሽ ነሽ፤የማሕፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው፤ ብሩህ ፀሐይ፣ ንጹሕም ጨረቃ፣ ያጌጠ ኮከብ  በማርያም ውስጥ አደረ። ማኅሌተ ጽጌ እንዘ  ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ ፣አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፣ንዒ  ርግብየ  ትናዝዝኒ  እምላህ፣ወንዒ  ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፣ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ ትርጉም፦ በንጽሕናና በተኣምር ቀን ወደ ቤተ መቅደስ በገባሽ ጊዜ  ፀዓዳ በመለኮቱ ቀይህ በትስብእቱ የሚባል ጽጌ የተባለ ልጅሽን ታቅፈሽ ነዪ መልካም የሆንሽልኝ ሆይ ከደስተኛ መልአክ ከገብርኤል ጋራ እና እንዳንቺ ሩኅሩኅ ከሆነ ከመልአኩ ከቅዱስ ሚካኤል ጋራ ነዪ ። ወረብ፦ እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ለሕፃንኪ ጽጌ ጸዐዳ ወቀይሕ/፪/ ንዒ ርግብየ ምስለ ገብርኤል ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ሚካኤል/፪/ ዚቅ ንዒ ርግብየ ሰላማዊት ንባብኪ አዳም ከመ ፍሕሶ ቀይሕ ከናፍሪሃ እሞሙ ለሰማዕት ወእኅቶሙ ለመላዕክት አልቦ ዘይመስል ዘከማኪ ክብረ እግዚአ ለሰንበት በማኅፀንኪ ተጸውረ። ትርጉም፦ ሰላማዊት ርግቤ ሆይ ነዪ ። ንግግርሽ ያማረ ነው ።  ከንፈሮትሽ ፍሕሶ እየተባለ እንደሚጠራ ቀይ አባባ ናቸው ። የሰማዕታት እናታቸው ነሽ ። የመላእክት እኅታቸው ነሽ ። በክብር እንደአንቺ የሚመስል የለም ። የሰንበት ጌታዋ ኢየሱስ ክርስቶስ በማፅንሽ አደረ ። ዓዲ ዚቅ ወተወልደ እምኔሃ ወይቤላ ንዒ ርግብየ ሠናይት ንባብኪ አዳም ትርጉም ከሷ ተወለደም ንግግርሽ ያማረ መልካሚት ርግብዬ ነይ ይላታልም ። ማኅሌተ ጽጌ ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ  ዘየኃቱ፤ዘተጽሕፈ ብኪ  ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤አክሊለ ጽጌ ማርያም  ለጊዮርጊስ ቀጸላ  መንግሥቱ፤አንቲ  ኵሎ ታሰግዲ ሎቱ፤ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ፡፡ ትርጉም የስሙና የሞቱ መታሰቢያ ባንቺ የተጻፈብሽ የሚያበራ ከሆነ ዕንቈ ባሕርይ ይልቅ የጠራ ወርቅ ክበብ ያለው የራስ ቊር የተባለ የጊዮርጊስ የመንግሥቱ የራስ ልብስ ጌጥ ሽልማት የአበባ አክሊል ማርያም ሆይ አንቺ ለእርሱ ሁሉን ታሰግጅለታለሽ (ታንበረክኪለታለሽ) እርሱ ግን ላንቺ ይሰግዳል ወረብ ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ክበበ ጌራ ወርቅ ዘየኀቱ እምዕንቈ ባሕርይ/፪/ አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ መንግሥቱ ለመፍቀሬ አምላክ/፪/ ትርጉም፦ ከዕንቈ ባሕርይ ይልቅ የጠራ ወርቅ ክበብ ያለው የራስ ቊር የአበባ አክሊል ማርያም የጊዮርጊስ የመንግሥቱ የራስ ልብስ ጌጥ ሽልማት ነሽ ። ዚቅ፦ አክሊል ዘእምጳዝዮን ተደለወ :ጌራ ባሕሪይ ወቀጸላ ወርቅ ጽሩይ በቤተልሔም ተወልደ እምድንግል በብስራትክሙ መሐይምናን እምአፈ ዮሐንስ ሥርግው ተቀሰመ አፈው ሰባኬ ወንጌል ነዋ በማዕከለ አኃው #ትርጕም እውነተኞች ነቢያት በትንቢታችሁ፤ ጳዝዮን ከሚባል ዕንቍ የተሠራ አክሊል የዕንቍ ራስቁር የወርቅ ዘውድ ክርስቶስ በቤተልሔም ከድንግል ተወለደ።ከተሸለመ ዮሐንስ አንደበት የሽቱ እንጨት ወንጌል ተለቀመ። የወንጌል ሰባኪ በወንድሞች መካከል እነሆ። ማኅሌተ ጽጌ፦ ኅብረ ሐመልሚል ቀይሕ ወፀዓድዒድ አርአያ ኰሰኰስ ዘብሩር፤ተአምርኪ ንጹሕ በአምሳለ ወርቅ ግቡር፤ተፈጸመ ናሁ ማኅሌተ ጽጌ ሥሙር፤አስምኪ ቦቱ ንግሥተ ሰማያት ወምድር፤ከመ በሕጽንኪ ያሰምክ ፍቁር፡፡ #ትርጕም እንደዝንጕርጕር ብር የቀይና ነጭ ቅጠል ኅብር የሆነ ንጹሕ ተአምርሽ በወርቅ አምሳል የተሠራ ነው። እነሆ የተወደደ የጽጌ ማሕሌት ተፈጸመ። የሰማይና የምድር ንግሥት! የተወደደ ልጅ ከጎንሽ እንደተጠጋ አንቺም ወደሱ/ወደማሕሌቱ ተጠጊ። ወረብ ናሁ ተፈጸመ ተፈጸመ ናሁ ማኀሌተ ጽጌ ሥሙር ተፈጸመ ናሁ/፪/ አስምኪ ቦቱ አስምኪ ቦቱ ንግሥተ ሰማያት/፪/ #ትርጕም እነሆ የተወደደ የጽጌ ማሕሌት ተፈጸመ። የሰማያት ንግሥት!ወደሱ/ወደማሕሌቱ ተጠጊ። ዚቅ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ጥቀ አዳም መላትሕኪ ከመ ማዕነቅ ይግበሩ ለኪ ኰሰኰሰ ወርቅ፡፡ #ትርጕም ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ጉንጮችሽ እንደዋልያ እጅግ ያማሩ ናቸው የወርቅ ጌጥን ያዘጋጁልሽ። ሰቆቃወ ድንግል ተመየጢ እግዝእትየ ማርያም ሀገረኪ ናዝሬተ፤ወኢትጎንድዪ በግብጽ ከመ ዘአልብኪ ቤተ፤በላዕሌኪ አልቦ እንተ ያመጽእ ሁከተ፤ለወልድኪ ዘየኃሥሦ ይእዜሰ ሞተ፤በከመ ነገሮ መልአክ ለዮሴፍ ብሥራተ፡፡ #ትርጕም እመቤቴ ማርያም! መልአክ ለዮሴፍ የምስራችን እንደነገረው በአንቺ ላይ ሁከትን የሚያመጣ የለምና ልጅሽንም የሚፈልገው ሞቷልና ቤት እንደሌለሽ በግብጽ ሳትቆዪ ወደሀገርሽ ናዝሬት ተመለሺ። ወረብ ተመየጢ ተመየጢ እግዝእትየ ማርያም ሀገረኪ/፪/ ወኢትጎንድዪ በግብፅ በግብፅ ከመ ዘአልብኪ ቤተ/፪/ #ትርጕም እመቤቴ ማርያም ቤት እንደሌለሽ በግብጽ ሳትቆዪ ተመለሺ። ዚቅ ሃሌ ሉያ ተመየጢ ተመየጢ ሰላመ ሰጣዊት ወንርአይ ብኪ ሰላመ፤ምንተኑ ትኔጽሩ በእንተ ሰላመ ሰጣዊት፤እንተ ትሔውጽ እምርኁቅ ከመ መድበለ ማኅበር፤ሑረታቲሃ ዘበስን ለወለተ አሚናዳብ። ትርጉም፦ (ቅድመ  ዓለም የነበረ፣ ዓለምን አሳልፎ የሚኖር) ሰላም የምትሰጪ ሆይ! ተመለሺ፤ሰላምንም ባንቺ እንይ፤ እንደ ማሕበር መድበል ከሩቅ ስለምትጐበኘው ስለ ሰላም ሰጪዋ ምን ትመለከታላችሁ? የአሚናዳብ ልጅ አካሂዷ ውብ ነው። መዝሙር ፦ ሃሌ ሉያ ትወፅእ በትር እምሥርወ ዕሤይ ወየዐርግ ጽጌ ይእቲ በትር አምሳለ ማርያም ቅድስት ይእቲ ወጽጌ ዘወጽአ እምኔሃ አምሳሉ ለወልድ ኀደረ ላዕሌሃ ቃል ሥጋ ኮነ ወተወልደ እምኔሃ። ትርጉም ከዕሴይ ሥር በትር ትወጣለች፤ ከእርሷም አበባ ይወጣሉ፤ ያቺ በትር የቅድስት ማርያም ምሳሌ ናት፤ የእግዘአብሔር ወልድ አምሳያ የሆነው ከእርሷ የወጣው አበባ በላይዋ ላይ አደረ፤ ቃሌ ሥጋ ሆነ፤ ከእርሷም ተወለደ። @Ethiopian_Orthodox

Открыть в Telegram
Просмотры6 530+18%к среднему
Пересылки—
Реакции54
Комментарии—
#5200Фото
Просмотры5 5200%к среднему
Пересылки—
Реакции11
Комментарии—
#5198Фото

ጥቅምት ፳፯ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ጌታችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ለእኛ ሲል በፈጸመው የማዳን ሥራ ክፉዎች አይሁድ ከምሽቱ 3:00 ጌቴሴማኒ ውስጥ ያዙት:: ¤ሙሉውን ሌሊት ከቀያፋ ወደ ሐና: ከሐና ወደ ቀያፋ ሲያመላልሱት: አስረው ሲደበድቡት አድረዋል:: ዝም ቢላቸው ዓይኑን ሸፍነው በጥፊ መቱት:: ¤ምራቃቸውን ተፉበት:: ዘበቱበት:: ¤ራሱንም በዘንግ መቱት:: ¤እርሱ ግን ሁሉን ታገሰ:: ¤በጧት ከገዢው ዘንድ ሞት እንዲፈረድበት አቀረቡት:: በሠለስት (3:00 ላይ) አካሉ እስኪያልቅ እየተዘባበቱ 6,666 ገረፉት:: ሊቶስጥሮስ አደባባይ ላይ እርጥብ መስቀል አሸክመው ወደ ቀራንዮ ወሰዱት:: 6:00 ላይ በረዣዥም ብረቶች 5 ቦታ ላይ ቸንክረው ሰቀሉት:: 7 ታላላቅ ተአምራት በምድርና በሰማይ ታዩ:: ዓለም በጨለማ ሳለች ጌታ በመስቀል ላይ 7 ቃላትን ተናገረ:: ከቀኑ 9:00 አካባቢ በባሕርይ ስልጣኑ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው ለየ:: በዚያች ሰዓትም ወደ ሲዖል ወርዶ የታሠሩትን ሁሉ ፈታ:: 11:00 ላይ ደጋጉ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብርና ሐዘን ጋር በአዲስ መቃብር ቀበሩት:: በዚአች ቀን ድንግል ማርያም ልቧ በሐዘን ተቃጠለ:: ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስም ፍፁም ለቅሶን አለቀሰ:: ቅዱሳት አንስት በዋይታ ዋሉ:: ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለው መጋቢት 27 ቀን ቢሆንም በዓሉ ወደ ጥቅምት እንዲመጣ ያደረጉት አበው ሊቃውንት ናቸው:: ምክንያቱም ብዙ ጊዜ መጋቢት 27 የሚውለው ዓቢይ ጾም ውስጥ በመሆኑና የንግሥ በዓላት በዓቢይ ጾም ስለማይፈቀዱ ነው:: ምንም እንኩዋ በቅርብ ጊዜ በዓቢይ ጾም የሚያነግሡ አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት ቢኖሩም አባቶቻችን ግን እንዲህ ያለውን ሥርዓት አላቆዩልንም:: ከበሮና የቸብቸቦ ዝማሬም በወቅቱ የተፈቀደ አይደለም:: +በዚህም ምክንያት የበዓለ ስቅለት ንግሡ ወደ ጥቅምት 27 ሲመጣ: የመጋቢት 5 ገብረ መንፈስ ቅዱስ ንግሥ ወደ ጥቅምት 5: የመጋቢት 10 መስቀል ወደ መስከረም 17 መጥቶ እንዲከበር ሆኗል:: አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቸርነቱ ይማረን ለሀገራችን ሰላሙን ይላክልን፤ አሜን! @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox

Открыть в Telegram
Просмотры6 780+22%к среднему
Пересылки—
Реакции48
Комментарии—
#5194Фото

በመንፈስ ቅዱስ የሚመራውና የቅዱሳን አበው ሐዋርያት መንበር ወራሽ የሆነው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ “ተጋብኦቶሙ ለኤጲስ ቆጶሳት ወውእቱ በኵሉ ዓመታት ፪ተ ጊዜ፤ ወዳግሚትኒ አመ ፲ወ፪ ለጥቅምት” የኤጲስ ቆጶሳት መሰባሰብ በዓመት ሁለት ጊዜ ይሁን ሁለተኛዋም ጉባኤ በጥቅምት 12 ቀን ትሁን” በሚለው ጥንታዊ ቀኖና መሠረት ከጥቅምት 12 - ጥቅምት 24 ቀን 2019 ዓ.ም. ስብሰባውን ሲያካሂድ ሰንብቷል፡፡ ልዑል እግዚአብሔርን አጋዥና መሪ በማድረግ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤው ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሁለንተናዊ ዕድገት፣ ወቅታዊ ስለሆኑ ዘርፈ ብዙ ችግሮች፣ ስለ ሀገር ሰላምና አንድነት፣ ስለ ሐዋርያዊ ተልእኮ መስፋፋት ስለ ሰው ልጅ ሁሉ ደኅንነት ሰፊ ውይይት በማድረግ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡ በተለይም ወቅታዊ ስለሆኑ የቤተ ክርስቲያናችን ፈተናዎች፣ ስለ ሀገር ሰላምና የሕዝብ አንድነት በስፋት ተወያይቶ ተገቢ ውሳኔዎችን አሳልፏል በዚሁ መሠረት፡- የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በሀገራዊ ሰላምና በወቅታዊ የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ፈተናዎች ዙሪያ ሰፊ ውይይት በማድረግ፣ ሀገራዊ የጸሎትና የምሕላ አዋጅ በማስተላለፍና ሌሎች ጥረቶችን ሲያደርግ የቆየ ሲሆን ለመላው ሀገራችን ዘላቂ ሰላምና እድገት እንዲገኝ ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ቅዱስ ሲኖዶስ በጽኑዕ ያሳስባል፡፡ ከዚሁ ጋር በማያያዝ በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አገልጋይ ካህናት፣ ንፁሐን ምእመናንና በዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው የጅምላ ግድያ፣ የአካል መጉደል፣ የንብረት ውድመትና መፈናቀልን ቅዱስ ሲኖዶስ በጥብቅ እያወገዘ፣ ይኽ ድርጊት እንዲቆም፣ ወንጀለኞች ለፍረድ እንዲቀርቡ፣ የምእመናን የእምነት ነፃነትና የዜጎች በሕይወት የመኖር መብት እንዲከበር ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን በአጽንዖት ያስተላልፋል፤ በአርሲ ሀገረ ሰብከት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ምእመናን ልጆቻችንን ታሳቢ በማድረግ ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች ቤተሰቦች፣ በአጠቃላይ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ሁሉ መድረስ ይቻል ዘንድ የእርዳታ አሰባሳቢ ኮሚቴ በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ሰብሳቢነት የተቋቋመ ሲሆን የድጋፍ ማሰባሰቢያ ባንክ ቁጥሩም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000 779 196 651 በአባይ ባንክ 1841 1131 1733 9013 እና ሌሎች ወደፊት በኮሚቴው እንደሚገለጹ እየገለጽን ሁላችንም ለወገኖቻችን የሚቻለውን ሁሉ ድጋፍ እንድናደርግ ቅዱስ ሲኖዶስ በአጽንዖት ያሳስባል፤ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤን የሚወክሉ ዐሥራ ስድስት ብፁዓን ሊቃና ጳጰሳት ከፍተኛ የመንግሥት አካልን ለማነጋገር ቅዱስ ሲኖዶስ የወከለ ሲሆን የችግሩን ምንጭ የሚያጣራ የጥናት ኮሚቴ እንዲሰየም ቅዱስ ሲኖዶስ መመሪያ ሰጥቷል፤ የበዓለ ሃምሳ ወይም በዓለ ጰራቅሊጦስ ቀደም ሲል በሀገራችን ብሔራዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዓል የነበረ ሲሆን፤ መንፈስ ቅዱስ ለሐዋርያት ከወረደበት ከመጀመሪያው በዓለ ሃምሳ ጀምሮ ያለማቋረጥ በቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሲከበር የኖረው በመሆኑ ይኽ ታላቅ በዓል እንደ ሌሎቹ ዓበይት በዓላት ማለትም በዓለ ልደትና በዓለ ትንሣኤ በሁሉም የሀገራችን ክፍልና በመላው ዓለም ባለችው ቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት እንዲከበር ተወስኗል፣ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በሀገራዊ ምክክር ሂደት አወንታዊና መልካም ተሳትፎን ያደረገች ሲሆን በዚህ ሀገራዊ መርሐ ግብር ቤተ ክርስቲያናችንን ወክለው የተሳተፉ ልዑካንን በሙሉ ቅዱስ ሲኖዶስ እያመሰገነ፣ በቀጣይም በቅድመ ምክክር እና በምክክሩ ወቅት እንደተደረገው የቤተ ክርስቲያናችን ተሳትፎው እንዲቀጥልና ክትትል እንዲደረግ ቋሚ ኮሚቴ በቋሚ ሲኖዶስ እንዲሰየም ሲል ምልዓተ ጉባኤው ወስኗል፤   የወላይታ ሀገረ ሰብከት ያቀረበውን የመንፈሳዊ ኮሌጅ ጥያቄ ምልዓተ ጉባኤው ያጸደቀ ሲሆን የቀድሞው የወላይታ ካህናት ማሰልጠኛ “ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት መንፈሳዊ ኮሌጅ” ተብሎ ወደ ኮሌጅነት እንዲያድግና የባሕር ዳር ሀገረ ሰብከት ጽርሐ ጽዮን መንፈሳዊ ኮሌጅ “ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ” ተብሎ እንዲጠራ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉበኤ ወስኗል፤ በጋምቤላ እና በቤንሻንጉል ጉምዝ - አሶሳ አህጉረ ሰብከት የተፈጠሩት የሃይማኖት ቀኖና ጥሰት፣ የአስተደዳር ሥራ ክፍተትና የፍይናንስ ጥፋቶችን አስመልክቶ በተደረገው ማጣራት የአህጉረ ሰብከቱ ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል ምልዓተ ጉባኤውን በጽሑፍ ይቅርታ በመጠየቃቸው፤ እስከ 2019 ዓ/ም የግንቦት ርክበ ካህናት ድረስ በደብረ ሊባኖስ ቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት አንድነት ገዳም በጸሎት እንዲቆዩ ተወስኗል፣ አዲስ አበባ ሀገረ ሰብከትን በተመለከተ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የሚመሩት አጣሪ መሰየም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፡- ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ሰብከት ሊቀ ጳጳስ፤ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የሲዳማ ሀገረ ሰብከት ሊቀ ጳጳስ የሚመሩት ከመንበረ ፓትርያርክ አራት የሥራ ኃላፊዎች የተካተቱበት ኮሚቴ የተሠየመ ሲሆን ኮሚቴው የማጣራት ውጤቱን ለግንቦት ርክበ ካህናት ምልዐተ ጉባኤ እንዲያቀርብ፣ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ሊቀ ጳጳስ የሐድያና ስልጤ ሀገረ ስብከትን ብቻ እየመሩ እንዲቆዩ በማለት ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡ የአባቶች ምደባ የሚያስፈልጋቸው አህጉረ ሰብከትን በተመለከተም ሀ) ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ (ዶ/ር) የጋምቤላ ሀገረ ስብከትን ደርበው እንዲመሩ፣ ለ) ብፁዕ አቡነ ሰላማ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ሀገረ ስብከትን ደርበው እንዲመሩ፣ ሐ) ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል አሶሳ ሀገረ ስብከትን ደርበው እንዲመሩ፣ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በሰነበተባቸው ቀናት ስለ ሰው ልጅ ክብር፣ ስለ ሀገር እና ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሁለንተናዊ ድኅንነት በየቀኑ በጋራ በመጸለይ ጉባኤውን ሲያካሂድ ቆይቷል፤ ሁላችንም እንደምንገነዘበው ዛሬ ሀገራችን ከመቼውም ጊዜ በላይ ሰላምን ትፈልጋለች፣ ምእመናን ደኅንነትና የተረጋጋ አኗኗርን ይሻሉ፣ መላው ኢትዮጵያውያንን ዜጎቻችን ማኅበራዊ እድገትና የተሻለ የአኗኗር ዘይቤን ይመኛሉ፤ ስለሆነም ያለፉ ቅራኔዎች በዕርቅና በይቅርታ ተፈትተው፣ በእኩልነትና በፍትሕ ላይ የተመሠረተ ዘመን እንዲሆን የቅዱስ ሲኖዶስ ጽኑ ፍላጎት ነው፡፡ በዘመናችን በመላው ዓለም እየተከሰቱ ያሉ ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ ሕይወት የሚቀጥፉ፣ አካልን የሚያጎድሉ፣ ንብረትን የሚያወድሙ፣ የሰውን ልጅ ከመኖሪያ ቀየው የሚያፈናቅሉ፣ የሰላም አለመኖር ችግሮች ዘላቂ መፍትሔ እንዲያገኙ፣ አለመግባባቶችና ግጭቶች በሰላማዊ ውይይትና ምክክር እንዲፈቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን እያስተላለፈ ምልዓተ ጉባኤው ለ13 - ቀናት ሲያካሂድ የነበረውን ስብሰባ በዛሬው ዕለት በሰላም ፈጽሟል፤ ልዑል እግዚአብሔር አምላካችን ለሀገራችን ሰላምና ፍቅርን፣ ለሕዝቧ ሁሉ አንድነትና ደኅንነትን እንዲሰጥልን በቸርነቱ ይርዳን፡፡ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ጥቅምት 24 ቀን 2019 ዓ.ም. አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ @Ethiopian_Orthodox

Открыть в Telegram
Просмотры8 400+52%к среднему
Пересылки—
Реакции46
Комментарии—
#5187Текст

🔔ዛሬ ምን ይቀደሳል? የማኅሌተ ጽጌ የዐራተኛ እሑድ ግጻዌ [ጥቅምት ፳፪] መልእክታት ➊ ሮሜ  ፲፩ : ፲፫-፲፬ - ፳፭ /11:14-25 ➋ ራእይ ፲፪ : ፲፫-ፍጻሜ /12:13- ፍጻሜ ➌ የሐዋ/ሥራ ፲፩ : ፩ - ፲፪ /11:1-12 ምስባክ መዝሙር ፸፱ ÷ ፰ /79 ÷ 8 "ዐጸደ ወይን አፍለስከ እምግብጽ፤ ሰደድከ አሕዛበ ወተከልከ ኪያሃ፣ ወፄሕከ ፍኖተ ቅድሜሃ።" "ከግብፅ የወይን ግንድ አመጣህ። አሕዛብን አባረርህ እርስዋንም ተከልህ። በፊትዋም ሥፍራን አዘጋጀህ።" ወንጌል ማቴ ፳፩ ÷ ፴፫ - ፍጻሜ /21÷33 - ፍጻሜ "፴፫ ሌላ ምሳሌ ስሙ። የወይን አትክልት የተከለ ባለቤት ሰው ነበረ፤ ቅጥርም ቀጠረለት፥ መጥመቂያም ማሰለት፥ ግንብም ሠራና ለገበሬዎች አከራይቶ ወደ ሌላ አገር ሔደ። ፴፬ የሚያፈራበትም ጊዜ ሲቀርብ፥ ፍሬውን ሊቀበሉ ባሮቹን ወደ ገበሬዎች ላከ። ፴፭ ገበሬዎቹም ባሮቹን ይዘው አንዱን ደበደቡት አንዱንም ገደሉት፤ ሌላውንም ወገሩት። ፴፮ ደግሞ ከፊተኞች የሚበዙ ሌሎች ባሮችን ላከ፥ እንዲሁም አደረጉባቸው። ፴፯ በኋላ ግን። ልጄንስ ያፍሩታል ብሎ ልጁን ላከባቸው። ፴፰ ገበሬዎቹ ግን ልጁን ባዩ ጊዜ እርስ በርሳቸው። ወራሹ ይህ ነው፤ ኑ፥ እንግደለውና ርስቱን እናግኝ ተባባሉ። ፴፱ ይዘውም ከወይኑ አትክልት አወጡና ገደሉት። ፵ እንግዲህ የወይኑ አትክልት ጌታ በሚመጣ ጊዜ በእነዚህ ገበሬዎች ምን ያደርግባቸዋል? ፵፩ እነርሱም። ክፉዎችን በክፉ ያጠፋቸዋል፥ የወይኑንም አትክልት ፍሬውን በየጊዜው ለሚያስረክቡ ለሌሎች ገበሬዎች ይሰጠዋል አሉት። ፵፪ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው። ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ፤ ይህም ከጌታ ዘንድ ሆነ፥ ለዓይኖቻችንም ድንቅ ነው የሚለውን ከቶ በመጽሐፍ አላነበባችሁምን? ፵፫ ስለዚህ እላችኋለሁ፥ የእግዚአብሔር መንግሥት ከእናንተ ትወሰዳለች ፍሬዋንም ለሚያደርግ ሕዝብ ትሰጣለች። ፵፬ በዚህም ድንጋይ ላይ የሚወድቅ ይቀጠቀጣል፤ ድንጋዩ ግን የሚወድቅበትን ሁሉ ይፈጨዋል። ፵፭ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያንም ምሳሌዎቹን ሰምተው ስለ እነርሱ እንደ ተናገረ አስተዋሉ፤ ፵፮ ሊይዙትም ሲፈልጉት ሳሉ ሕዝቡ እንደ ነቢይ ስላዩት ፈሩአቸው።" ቅዳሴ ዘእግዝእትነ (ጎሥዓ) - {በዕዝል ዜማ} @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox

Открыть в Telegram
Просмотры8 110+46%к среднему
Пересылки—
Реакции35
Комментарии—