የብዕር አርበኛ.. ዘና እሚያረጋችሁ ምንድነው...?? ግጥም? ድርሰት ?አጭር ወግ ? ወይስ ተከታታይ ልብ አስጨናቂ ታሪክ...በአጭሩ ጥበብ እና ጥበብ ብቻ.. ቤተሰባዊ ፍቅርን ያለ ምንም ክፍያ በነፃ ጀባ እንላችኋለን !!😁 Always. . . ይቀላቀሉ Join us. https://t.me/yebier_arbegna
Открыть в TelegramПосты канала Peka - ፔካ
🦴 የ2.6 ሚሊዮን ዓመት ዕድሜ ያለው የ«ፓራንትሮፐስ» (Paranthropus) የመንጋጋ አጥንት በአፋር ተገኘ — የሰው ልጅ የቅርብ ዘመድ በሰሜን ኢትዮጵያ ይኖር እንደነበር ለመጀመሪያ ጊዜ ተረጋገጠ! በታዋቂው ኢትዮጵያዊ የቅሪተ አካል ተመራማሪ ፕሮፌሰር ዘረሰናይ ዓለምሰገድ የሚመራ ዓለም አቀፍ የምርምር ቡድን፣ በአፋር ክልል ሚሌ-ሎግያ (Mille-Logya) በተባለ ስፍራ ከ2.6 ሚሊዮን ዓመታት በፊት የኖረ የፓራንትሮፐስ (Paranthropus) ዝርያ የታችኛው የመንጋጋ አጥንት (MLP-3000) ማግኘቱን ይፋ አድርጓል። ግኝቱ በታዋቂው የሳይንስ መጽሔት Nature ላይ የታተመ ሲሆን፣ እስከዛሬ የነበረውን የሳይንስ ግምት የቀየረ ነው። 🔍 ይህ ግኝት ለምን ልዩ ሆነ? በአፋር የመጀመሪያው ግኝት፦ ከዚህ ቀደም በአፋር ክልል የሉሲ (Australopithecus) እና የቀደምት የሰው ዘር (Homo) ቅሪተ አካላት በብዛት ቢገኙም፣ «ፓራንትሮፐስ» የተባለው ዝርያ ግን በአፋር ምድር ተገኝቶ አያውቅም ነበር። ይህ አዲስ ግኝት ዝርያው እስከ ሰሜን ኢትዮጵያ ድረስ ተስፋፍቶ ይኖር እንደነበር ያረጋገጠ የመጀመሪያው ማስረጃ ነው። «Nutcracker Man» (ጠንካራ መንጋጋ ያለው ዝርያ)፦ ፓራንትሮፐስ በግዙፍ የመንጋጋ ጥርሶቹ እና ጠንካራ ሥሮችንና ለውዞችን መስበር በሚችል የፊት ጡንቻው ይታወቃል። ቀደም ሲል ተመራማሪዎች ይህ ዝርያ በአንድ አካባቢ ብቻ ተወስኖ የሚኖር ነበር ብለው ያስቡ የነበረ ቢሆንም፣ አዲሱ ግኝት ግን እንደ ቀደምት የሰው ዘሮች ሁሉ በተለያዩ አካባቢዎች መላመድ የሚችል ብርቱ ዝርያ እንደነበር አሳይቷል። ዘመናዊ ቴክኖሎጂ እና ጥንታዊ ቅሪት፦ ተመራማሪዎቹ በመሬት ላይ ተበታትነው የተገኙትን የመንጋጋ አጥንት ስብርባሪዎች ከሰበሰቡ በኋላ፣ በከፍተኛ Micro-CT Scan ቴክኖሎጂ በመታገዝ የጥርሶቹን ውስጣዊ አወቃቀር በመመርመር ትክክለኛ ማንነቱን ለይተዋል። 🌍 ታሪካዊ ትርጉሙ ይህ ግኝት ከ2.6 ሚሊዮን ዓመታት በፊት በአፋር ምድር ሦስት የተለያዩ የሰው ልጅ የቅርብ ዘመድ ዝርያዎች (Australopithecus፣ Homo እና Paranthropus) በአንድ ዘመን ይኖሩ እንደነበር ያሳያል። ኢትዮጵያ አሁንም የሰው ልጅን አመጣጥ ምስጢር የሚፈቱ ቁልፍ መረጃዎችን ለዓለም ማበርከቷን ቀጥላለች። @EthiopeTowoderos @EthiopeTowoderos
Открыть в Telegramየአፄ ቴዎድሮስ የብራና ወንጌል በ250 ሺህ ዶላር ለጨረታ ሊቀርብ ነው! 🇪🇹📜 ከ160 ዓመታት በፊት በመቅደላ ጦርነት ወቅት በእንግሊዝ ኃይሎች ከተዘረፉ ታሪካዊ ቅርሶቻችን መካከል አንዱ የሆነው «የጎንደር ወንጌል» (Gondarine Gospel) የተሰኘው ጥንታዊ የብራና መጽሐፍ፣ በአቡ ዳቢ ዓለም አቀፍ የመጽሐፍ ኤግዚቢሽን ላይ ለሽያጭ ቀርቦ ተገኝቷል። ስለ ቅርሱ በአጭሩ፦ ዘመን፦ በ1730ዎቹ በጎንደር ከተማ የተዘጋጀ እና በአፄ ቴዎድሮስ ቤተ-መጽሐፍት ውስጥ የነበረ። ይዘት፦ በግዕዝ ቋንቋ የተጻፈ ሆኖ የሉቃስ እና የዮሐንስን ወንጌል በደማቅ ቀለም የሚያስረዱ 235 የጥበብ ሥዕሎችን የያዘ ነው። የተፈጠረው ውዝግብ፦ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን ቅርሱ በሞራል እና በሥነ-ምግባር አሰራር መሠረት ወዲያውኑ ከጨረታ ታግዶ ወደ ሀገሩ እንዲመለስ ለቪየናው የrare book አከፋፋይ 'Inlibris' ጥሪ አቅርቧል። ነገር ግን አከፋፋዩ ድርጅት "ቅርስ የመመለስ ሕጋዊ ግዴታ የለብንም" በማለት የኢትዮጵያን ጥያቄ ውድቅ ያደረገ ሲሆን፣ የቅርስ ባለሙያዎች ግን ቅርሱ በስምምነት እና በውይይት ወደ ባለቤቱ ሊመለስ እንደሚገባ በመግለጽ ላይ ይገኛሉ። @EthiopeTowoderos
Открыть в Telegramበአማርኛ ጥሩ ኮንተንት የሚለቁ እና መበረታታት አለባቸው ብዬ ከማስባቸው ዩቲዩብ ቻናሎች አንዱ የሆነው Lumos Think የለቀቀውን አዲስ ህልም ከምን ይመጣል የሚል ቪዲዮ በማየት እንታበረቷቷቸው እና እናንተም እንድትማሩባቸው ቪዲዮኣቸሁን ሼር አደርጋለሁ፡፡
Открыть в TelegramПереслано из EthelDaily
🌞 ከቢሊዮን ዓመታት በኋላ ምድር በፀሐይ ከመጥፋት ለማዳን የሳይንቲስቶች አዲስ መላምት! በቅርቡ ይፋ በተደረገ አዲስ የጠፈር ምርምር እቅድ መሰረት የፊዚክስ ሳይንቲስቶች ፀሐይ በጊዜ ሂደት እያደገችና እየሞቀች ስትመጣ ምድርን ሙሉ በሙሉ እንዳታቃጥላት ሊያደርግ የሚችል መፍትሔ እንደ ሀሳብ አቅርበዋል። ይህንን የጥፋት ቀን ለመከላከል ሳይንቲስቶች ያቀረቡት አዲስ ሀሳብ ምድርን ሙሉ በሙሉ ወደ ኋላ ገፍቶ ከፀሐይ ማራቅ የሚል ነው። ሀሳባቸው ሲተነተን፦ ☄️ የጠፈር ድንጋዮችን (Asteroids) መጠቀም፦ በጠፈር ውስጥ የሚበሩ ግዙፍ የድንጋይ አካላት አሉ። እነዚህ ድንጋዮች ምንም እንኳ አነስተኛ ቢሆንም የራሳቸው የሆነ የስበት ሀይል (Gravity) አላቸው። 🧲 የጠፈር ድንጋዮች (Asteroid ) የስበት ሀይል መጠቀም፦ ሳይንቲስቶች የአንዱን ግዙፍ አስቴሮይድ አቅጣጫ አስቀይረው በምድር አቅራቢያ እንዲያልፍ ያደርጉታል። አስቴሮይዱ በምድር አጠገብ በጥቂት ሺህ ኪሎሜትሮች ርቀት ሲያልፍ ልክ እንደ ማግኔት ምድርን በጥቂቱ ይስባታል። 🚜 ምድርን ደረጃ በደረጃ ማራቅ፦ አስቴሮይዱ በቅርብ ሲያልፍ ምድርን በጥቂቱ ስቧት ስለሚያልፍ ምድር ከነበረችበት ቦታ አነስተኛ ግፋት (Push) አግኝታ ወደ ኋላ ትሸሻለች። ይህንን ሂደት በየ10,000 ዓመቱ አዲስ አስቴሮይድ በመጠቀም ደጋግሞ በመስራት ምድርን ቀስ በቀስ ከፀሐይ ማራቅ ይቻላል ብለው ያስባሉ ፡፡ 🚀 ማርስ መሄድ መፍትሄ ይሆናል? ፦ ሰዎች ወደ ማርስ ቢሰደዱ እንኳ ፀሐይ እያደገች ስትመጣ ማርስንም ስለምታቃጥላት ብቸኛው አስተማማኝ መፍትሔ ምድርን ራሷን ይዞ ወደ ቀዝቃዛው የጠፈር ክፍል ማሸሽት ነው። 💡 የግል ሀሳብ፦ ምንም እንኳን ሂደቱ በዓይናችን የሚታይ አጭር የጊዜ ፕሮጀክት ባይሆንም የሰው ልጅ ከቢሊዮን ዓመታት በኋላ በሚኖረው ቴክኖሎጂ እና እውቀት ሊደረግ ይችላል ብዬ አስባለሁ።
Открыть в Telegramተጀመረ! 10/08/2018 ዓ .ም ቅድመ ሽያጭ ርዕስ:ወደ ራዚኤል ተራሮች ደራሲ:ዝጋለ አያሌው የአንዱ መጽሐፍ ዋጋ:600ብር ዋጋው ማተሚያ+ትራንስፖርት+መደብር ማቆያ እንዲኹም መጽሐፉ እስኪታተም የሚፈጠረው የዋጋ ጭማሬ ታሳቢ ያደረገ። ከዚህ በፊት በወረቀት የታተሙ መጽሐፎች 1ኛ.ገነት በኢትዮጵያ ናትን? 2ኛ ገነት በኢትዮጵያ "ጓሮ" ናትን? 3.ዘዌ 4.ድራጎን በኢትዮጵያ ሰማይ ሲሆኑ 5ኛ. "ወደ ራዚኤል ተራሮች" 11ኛ ስራ ሆኖ ዛሬ ቅድመ ሽያጭ ቀርቧል። ሌሎችን በ e_book የታተሙ 6ቱን መጽሐፎቼ የምትፈልጉ AfroRead ላይ ታገኟቸዋላችኹ። "የአሰላሳዮችና የሃሳባዊያን ጊዜ እየመጣ ይመስለኛል።" Zigale Ayalew Bogale 1000524531724 CBE 5541004749049 Dashen bank 68018064 Abyssina bank 0920760334 Telbirr facebook Report ዕግድ አለበትና እኔ መልስ መስጠት አልችልምና ከታች ያለውን ቴሌግራም ይጠቀሙ። ደረሰኙን በዚህ ቴሌግራም አድራሻ ያስቀምጡ። @ZigaleAyalew ስለ ቅን ትብብራችሁ አመሰግናለሁ። ሌሎች አዳዲስ መረጃዎች ሲኖሩ እመለሳለሁ። ሽልማት ቻሌንጅም እናዘጋጃለን።
Открыть в Telegramውድ እንባብያን እንኳን ደስ አላችሁ 🥳 ✅ አዲስ የቴሌግራም ቦት መቶላችኋል ✅የፈለጉትን የመፅሐፍ ስም በመላክ መፅሐፉን በPDF የሚያገኙበት ቦት ነው 👏 ✅ ደስ የሚለው ደግሞ ይህ ሁሉ በነፃ ነው 📌 ታዲያ ምን ይጠብቃሉ ፣ አሁኑኑ የፈለጉትን መፅሐፍ ይጠይቁ 😍 👉 @Feedback251_bot 👈 👉 @Feedback251_bot 👈 👉 @Feedback251_bot 👈
Открыть в Telegram🔥 በኢትዮጵያ ተወልዶ ሕንድን የገዛው ኢትዮጵያዊ 🔥 በኢትዮጵያ ሐረር ተወልዶ ሕንድን የገዛው ያልተነገረለት ኢትዮጵያዊ PDF @EthiopeTowoderos | @peka369
Открыть в Telegram“የአንድ ሰው ከባህር ጉዞ መመለስ ከመቃብር እንደመነሳት ነበር። ወደቡ ደግሞ የምጽኣት ቀን ለፍርድ እንደምንሰበሰብበት ስፍራ ያለ ነው” እያሉ በጊዜው የነበረውን ጉዞ የሚገልጹ ጸሐፍት ነበሩ። የአለምን ግማሽ ያህል ርቀት ከሚሸፍኑ የተለያዩ ስፍራዎች ተጉዘው ወደ ወደቡ ከተሰበሰቡት ሰዎች ጋር የደረሰው አምባር። አሁን የሚገኘው ወጣ ገባማ መልክአ ምድር ከነበሯት ኢትዮጵያ ሁኔታ ጋር የምትመሳሰል በሆነች “ዴካን” የተባለች ሀገር ጠረፍ ላይ ነበር። በምእራብ ዴካን ውስጥ አቢሲኒያውያን ወታደሮችና ቅጥረኛ ተዋጊዎች ጎልተው ይታዩ ነበር። በ16ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይም በወታደርነት፣ በፈረሰኛ ወታደርነትና በጦር ግንባር አዛዥነት ላይ ተሰማርተው ይገኙ ነበር። በመሆኑም አምባርም ከአፍሪካ ወደ ሕንድ የተደረገው ግዙፍ የአቢሲኒያውያን ፍሰት አካል ነበር። የሙግሃል ተዋጊዎች አምባር ሕንድ በሚደርስበት ወቅት በደቡብ እስያ ታሪክ ውስጥ ታላቁ ፖለቲካዊ ሃይል ለመሆን በቅተው ነበር። በምእራብ ሕንድ አቢሲኒያውያን ለውትድርና መፈለጋቸው አምባር ወደዛ እንዲገባ አድርጎታል። አምባር በጊዜው የሰለጠነና እጅግ በጣም ሃይለኛ ሰው አበር። ሕንድ ከደረሱ በኋላም ወዲያውኑ “ሚር ቃሲም” የተባለው አለቃው አምባርን ለአንዱ ግዛት ጠቅላይ ሚኒስቴር ለነበረው “ቼንጊዝ ከሃን” ተብሎ ለሚታወቀው ሰው ሸጠው። አምባር እኒህን ወታደሮች ተቀላቅሎ ከመሃላቸው በፍጥነት ራሱን ለይቶ ለማሳወቅ ቻለ። ረጅምና ጠንካራው አምባር የ“ክሃንን” ትኩረት በቀላሉ ለመሳብ ቻለ። ስርአተ መንግስትንም ከጠቅላይ ሚኒስቴሩ መማር ጀመረ። በመሆኑም አምባር አዲስ የአገልግሎት ደረጃና አዲስ አይነት ስልጠና ውስጥ ለመግባት ቻለ። አምባር የ”ኒዛም ሻሁንር” የተባለ ግዛት በማስተዳደሩ ስራ የክሃን የግል ረዳት ሆኖ ለማገልገል በመቻሉ። በርሱ አመራር ስር ሆኖ የቤተ መንግስትን ስርኣት፣ የውጊያ ጥበብንና ሕዝባዊና ወታደራዊ የሀገር አስተዳደር ስራዎችን በተግባር የማጥናት እድሉን አገኘ። ሁሉም ነገር በድንገት ነበር የተለወጠው። ምንም እንኳን ክሃን የአምባር ከጊዜ በኋላ ዝና ከፍታ ላይ ስትደርስ ሊያያት ባይችልም። ሌሎቹ ገዢዎች ግን ይህን አስተውለውት ነበር። በወቅቱም ምእራብ ዴካን “ሀገረ አምባር” እየተባለች መጠራት ጀምራ ነበር። አምባር ለአካባቢው ማሕበረሰብ በጊዜው እውነተኛ ንጉሳቸው ባይሆንም እንኳን - በእንደራሴነቱ መሪያቸው ለመሆን የበቃ ሰው ነበር።ከአመታት በኋላ የአምባር አሰልጣኝና አሳዳሪ የነበረው ክሃን ተገደለ። የሟቹ ሚስት የአምባርን ነጻነት ይፋ አደረገችለት። ምናልባትም አምባር ለነበረው የታማኝነት አገልግሎት እንደ ምስጋና ለመግለጽ ነው። ቀጣዮቹን አመታት አምባር የተከታዮቹን ቁጥር በማብዛት ነበር ያሳለፈው። የቀድሞው አለቃው ወታደሮችን በስሩ ማድረጉ በሀገሪቱ ሙግሃሎች የሚያካሄዱትን የተለያዩ የጦር ስትራቴጂዎች እንዲያከሽፍ አስችሎታል። በወቅቱ ወደ 50,000 የሚደርሱ በስሩ ታዛዥ ወታደሮች ነበሩት። ይህ የአምባር ተግባር የብዙዎችን የውጭ መሪዎች ትኩረት ስቧል። በዚህም ከጊዜ በኋላ በሕንድ “ዴካን” የተባለ ግዛት በዘመኑ አገላለጽ “ጠቅላይ ሚኒስቴር” ሁኖ በ”አሃማ-ድናጋር” መንግስት ስር መግዛት ጀመረ። በብዛት ሕንዶችን ያጠቁ የነበሩት የሙግሃል መንግስትንም ከአንድም ሁለት ጊዜ ከማሊክ አምባር ጋር ጦርነት ገጥመው አሸንፏቸዋል። በዚህም ሕንዶች አሁን ድረስ የሀገራቸው ጠባቂ እንደነበር ይመሰክራሉ። ማሊክ አምባር ለኪነ ሕንጻና ስነ ጥበብ የተለየ አትኩሮት ነበረው። ይህንንም በሕንድ የገነባው “አውራን-ጋባድ” የተባለው ከተማ ይመሰክራል። በተጨማሪም ለከተማው ውሃ ማከፋፋያ ተብሎ የሰራው የውስጥ ለውስጥ የውሃ ማስተላለፊያ ዘዴ ያለ ምንም ብልሽትና የንጽሕና ጉድለት ከ300 አመታት በላይ ማገልገሉ አሁን ድረስ ኢንጂነሮችን የሚያስገርም ጉዳይ ነው። በሕንድ ከባለቤቱ ቢቢ ካሪማ ጋር አራት ልጆችን የወለዱ ሲሆን በመጨረሻም ማሊክ አምባር በሕንድ የ“ማርዋር” ግዛት መሪ ከነበረው ጋር በነበረው ጦርነት ሲዋጋ በ77 አመቱ እንደሞተ ታሪክ ይናገራል። መቃብሩም በሕንድ “ኩል-ዳባድ” በተባለ ስፍራ በተገነባ ታላቅ ግንብ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ቦታው አሁን ድረስ የቱሪስት መስሕብ መሆኑን ቀጥሏል። ከማሊክ አምባር በመቀጠልም የበኩር ልጁ እንደ እንደራሴ በማገልገል ቀጥሏል። በዚህ የማሊክ አምባር ድንቅ ታሪክ በዋናነትም የሕንዶች ጠላት ተደርገው የሚወሰዱትን ሙግሃሎችን ከግዛቱ በማራቁና በጦርነት ደጋግሞ በማሸነፉ ምክንያት ሕንዶች “አቢሲኒያዊው የዴካን ግዛት ነጻ አውጪ” እያሉ በታሪክ ይዘክሩታል። ታሪኩም የኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን የአፍሪካውያንን በአለም ላይ ያላቸውን አሻራ ያንጸባርቃል። ለዛሬ እንዲህ ሰፋ ባለ መልኩ ስለ ኢትዮጵያዊው ማሊክ አምባርና በአለም ላይ በዋናነትም በአረብ ሐገራትና ሕንድ የነበረውን ተጽእኖ እንዲህ ተመልክተናል፣ ምናልባት በሰፊው ስለዚህ ታሪክ ከነዋቢ ማጥናት ከፈለጋችሁ አናግሩኝ(@Lumos1) The Great source of Knowledge. - @Peka369
Открыть в Telegram