Кабинет

Посты канала Ministry of Education Ethiopia

сначала новые

#5145Текст

ክቡር የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ(ዶ/ር) በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ትምህርትን በሚመለከት ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ከዚህ የሚከተለውን ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል። ‎ ‎ትምህርትን በተመለከተ መጀመሪያ የቀየርነው ፍነተ ካርታውን ነው ያለት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሥርዓተ ትምህርቱ ከመቀየር ጀምሮ መሰረተ ልማቶችን የማልማት ሥራ መሰራቱን ጠቅሰዋል። ‎ ‎ከዚህም ውስጥ ህጻናት የሚማሩባቸው ቅደመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንደ ሀገር ባለፉት ስምንት ዓመታት በመንግስትና በህዝብ ድጋፍ 35 ሺ የሚደርሱ ቅደመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተገንብተዋል ብለዋል። ‎ ‎በዚህም አምስት ሚሊየን የሚጠጉ ህጻናት በሀገር ደረጃ በቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እየተማሩ ይገኛሉ ሲሉም አብራርተዋል። ይህም ህጻናት ቀድመው ማንበብና መጻፍ ችለውና ፊደል አውቀው አንደኛ ክፍል እንዲገቡ ያስችላቸዋል አጠቃላይ ውጤቱን ዛሬ ላይ ማየት የማይቻልና ከዛሬ ሃያ አመት በኋላ የሚታይ መሆኑን ጠቅሰው ዛሬ ላይ መሠረቱን የመጣል ሥራ እየተሰራ አንደሚገኝ አንስተዋል። ‎ ‎በሌላ በኩል ደግሞ ሞዴልና ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በፌዴራልና በክልል እየተገነቡ እንደሚገኙም አንስተዋል። የፌዴራል መንግስት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን መገንባት ግዴታው ባይሆንም ወደ 50 የሚደርሱ ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በትምህርት ሚኒስቴር እየተገነቡ እንደሚገኙ ተናግረዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/1G9QqTUKMm/

Открыть в Telegram
Просмотры19 200−41%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#5141Фото

መጽሃፍት ለመማር ማስተማር ስራ ዋነኛ ግብዓት በመሆናቸው ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ለተደራሽነታቸው ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጡ እንደሚገባ ተጠቆመ። ----------------------- // ---------------------- (ህዳር 11/2019 ዓ.ም) መጽሐፍት ለመማርና ለማስተማር ሂደት ከሚያስፈልጉ ዋነኛ ግብዓቶች መካከል ቀዳሚ ቦታ የሚይዙ በመሆናቸው፣ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ለተማሪዎች 1 ለ1 ለማዳረስ ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጡ እንደሚገባ ተጠቁሟል።   በአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ የሥርዓተ ትምህርት ማበልጸጊያ ተወካይ መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር አበበ ጋረደው፣ መጽሐፍት የትምህርት ጥራትን የሚወስኑ መሠረታዊ ግብዓቶች በመሆናቸው ተደራሽነታቸውን ማረጋገጥ የሁሉም አካላት የጋራ ኃላፊነት መሆኑን አስገንዝበዋል።   ዶ/ር አበበ አክለውም፣ የትምህርት ሚኒስቴር ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት መሠረት ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ለሚማሩ ተማሪዎች በቂና ጥራቱን የጠበቀ መጽሐፍት በማሳተም 1ለ1 ማድረስ መቻሉን ጠቁመዋል።   ከዚህም በተጨማሪ፣ ሚኒስቴሩ የ2ኛ ደረጃ መፅሃፍትን አንድ ለአንድ በማድረስ ብቻ የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ ሰለማይቻል ከ2018 ዓ.ም ጀምሮ ለቅድመ አንደኛ፣ ለአንደኛና መካከለኛ ደረጃ ተማሪዎች የመማሪያ መጽሐፍትን 1ለ1 ለማዳረስ ልዩ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/1JivXR3np8/

Открыть в Telegram
Просмотры36 400+12%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#5138Фото

በትምህርት ሚኒስቴርና በክልሎች ትብብር እየተገነቡ ያሉ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በመጠናቀቅ ላይ መሆናቸው ተገለጸ፣ ------------------------ // ----------------------- (ህዳር 10/2019 ዓ.ም) በትምህርት ሚኒስቴርና በክልል/ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች ትብብር ግንባታቸው የተጀመሩ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታ እየተፋጠነ ይገኛል። ከዚህ አንጻር የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ያስጀመራቸውን የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ገንብቶ በማጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ አሳውቋል። ‎ ‎ትምህርት ሚኒስቴ ከክልል እና ከተማ አሰተዳደር ትምህርት ቢሮዎች ጋር በመተባበር በመላ አገሪቱ 1452 ሞዴል ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለትመገንባ ስምምነት መገባቱን ይታወሳል። ‎ ‎ትምህርት ቤቶቹ ምንም ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በሌሉባቸው አካባቢዎች የተገነቡ መሆናቸውንም ተገልጿል። ‎የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶቹ ግንባታ ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ጥራትን ከታች ጀምሮ ለማረጋገጥ ከጀመራቸው የሪፎርም ስራዎች መካከል አንደኛው መሆኑ ይታወቃል።

Открыть в Telegram
Просмотры39 700+22%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#5134Фото

የሒሳብና የሳይንስ ትምህርት አሰጣጥን በማዘመን ተማሪዎችን ወደ ፈጠራ ስራ መምራትና ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎችን ማፍለቅ እንደሚገባ ተመላከተ፤ ----------------------- // ------------------------ ‎(ህዳር 05/2019 ዓ.ም) 23ኛው የአፍሪካ የሂሳብ፣ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ትምህርት ኮንፍረንስ /COMSTEDA-23/ ተጠናቋል። ‎ ‎አፍሪካ የሂሳብ እና የሳይንስ ትምህርት ማሻሻያ SMASE-Africa ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ቤንሰን ባንዳ በኮንፍረንሱ ማጠቃለያ ላይ እንደገለጹት የሒሳብና የሳይንስ ትምህርት አሰጣጥን በማዘመን ተማሪዎችን ወደ ፈጠራ ስራ መምራትና ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎችን ማፍለቅ ይገባል። ‎ ‎የአፍሪካ የወደፊት ዕጣ ፈንታ እና ብልጽግና የተመሠረተው በሒሳብና በሳይንስ ትምህርቶች ላይ መሆኑን የጠቆሙት ፕሮፌሰር ባንዳ፣ አፍሪካ የትምህርት ስርዓቶቿን በመለወጥ ሳይንሳዊና ቴክኖሎጂያዊ አቅሞችን ማዳበር ፣ ፈጠራን ማበረታታት፣ እና ወጣቶቿን በዓለም ኢኮኖሚ ውስጥ በስኬት እንዲወዳደሩ ማዘጋጀት እንደሚገባ ገልጸዋል። ‎ ‎የአፍሪካን ዘላቂ ልማት ማረጋገጥና ተግዳሮቶች መፍታት የሚቻለው ህዝቦቿን በማስተማር ብቻ ሳይሆን በዕውቀት ፣በክህሎት እና በፈጠራ አቅም በማስታጠቅ ጭምር መሆኑንም ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/1H5tbFXsXy/

Открыть в Telegram
Просмотры42 600+31%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#5131Фото

የወሊሶ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ ተጠናቆ ተማሪዎችን ተቀብሎ የማስተማር ሥራውን ጀመረ፤ ----------------------- // -------------------------- (ህዳር 04/2019 ዓ.ም) የወሊሶ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ ተጠናቆ፣ ዘመናዊና ለትምህርት ምቹ በሆነው አዲሱ ግቢ ተማሪዎችን ተቀብሎ የማስተማር ሥራውን በይፋ ጀምሯል። የትምህርት ሚኒስቴር በመላ ሀገሪቱ ያሉ ተሰጥኦና ችሎታ ያላቸውን ተማሪዎች አወዳድሮ በመመልመል በእውቀት፣ በክህሎትና በሥነ-ምግባር የዳበሩ ብቁ ዜጎችን ለማፍራት ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች እያስገነባ ይገኛል። የወሊሶ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤትም ከእነዚህ ፕሮጀክቶች አንዱ ሲሆን የግንባታ ሥራው ተጠናቋል። ትምህርት ቤቱ በ2018 የትምህርት ዘመን የመጀመሪያ ተማሪዎቹን ተቀብሎ በጊዜያዊነት በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ አድርጎ የቆየ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት የግንባታ ሥራው ተጠናቆ ወደ ቋሚ ግቢው ተዛውሯል። በዚህም የ9ኛና የ10ኛ ክፍል ተማሪዎችን በአዲሱ ግቢ ተቀብሎ የትምህርት ሥራውን በይፋ ጀምሯል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/1Dy5rzcs51/

Открыть в Telegram
Просмотры44 400+36%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#5125Фото

የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ምህንድስና የፈጠራ ውድድር የንድፈ ሀሳብ ዕውቀትን በተግባር በመፈተሽ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ተገለጸ። ------------------------ // --------------------------- (ሕዳር 03/2019 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የተካሄደው 11ኛው ሀገር አቀፍ የSTEM የፈጠራ ስራዎች ውድድርና አውደ ርዕይ ተጠናቋል። የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሰለሞን አብርሃ በማጠቃለያው ላይ እንደገለጹት የፈጠራ ሥራዎች የንድፈ ሀሳብ ዕውቀትን በተግባር ላይ በማዋል ማህበራዊ ችግሮችን ለመፍታት ወሳኝ ናቸው ብለዋል። ተማሪዎች ከተደገፉ ሳይንሳዊ እውቀትን ወደ ተግባራዊ ውጤት በመቀየር የሥራ ፈጣሪነት ክህሎታቸውን ማዳበር እንደሚችሉ ገልጸው የSTEM ማዕከላት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና ከማህበረሰቡ ጋር የሚያገናኙ በመሆናቸው ሊጠናከሩ አስገንዝበዋል። በአውደ ርዕዩ የቀረቡት ፕሮጀክቶች በግብርና፣ በጤና፣ በቱሪዝም፣ በአካባቢ ጥበቃ እና በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ ያሉ ተግዳሮቶች የሚፈቱ አበረታች ተግባራዊ መፍትሄዎች የታዩባቸው መሆናቸውን ጠቁመዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/1EAwd7JuFB/

Открыть в Telegram
Просмотры40 400+24%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—