አስቸኳይ ገንዘብ ያስፈልግዎታል? በድጋፍ ማይክሮፋይናንስ አማካኝነት፦ ✅ በዜሮ ወለድ – ያለ ወለድ ክፍያ ✅ በአገልግሎት ክፍያ ብቻ ✅ ቀላልና ፈጣን አሰራር ✅ የሚያስፈልግዎት የመሥሪያ ቤት መረጃና የፋይዳ መታወቂያ ብቻ ነው። አሁኑኑ ያመልክቱ! የገንዘብ ፍላጎትዎን በቀላሉ ይፍቱ! 📞 ለበለጠ መረጃና ለማመልከት፦ 0982205182 ይደውሉ። ድጋፍ ማይክሮፋይናንስ - ተደራሽነትን ያለ ገደብ!
Открыть в TelegramПосты канала ኢትኤል
🛑➠የጂኦግራፊና የአየር ጠባይ አንድነት፦ የሁለቱም ሀገራት ህይወትና ግብርና በቀጥታ ከተያያዘው ከአባይ (ዓባይ) ወንዝ የተፈጥሮ ዑደትና ከጥቅሉ የአፍሪካ ቀንድ/ሰሜን አፍሪካ የፀሐይ ጉዞ ጋር የተሳሰረ በመሆኑ ነው። 🛑➠የመጽሐፈ ሄኖክና የጥንታዊ ስነ-ከዋክብት ተፅዕኖ፦ በጥንቱ ዘመን በሁለቱ ሀገራት መካከል በነበረው የንግድ፣ የባህልና የሃይማኖት ግንኙነት የፀሐይ ዑደት ስሌት (365 ቀናት) በጋራ ጥቅም ላይ ውሏል። 🛑➠የጁሊያን (Julian) አቆጣጠር ማሻሻያ፦ በሮማውያን ዘመን (በኦገስተስ ቄሳር ጊዜ) የግብፅ አቆጣጠር ተሻሽሎ በየ4 ዓመቱ 6ኛ የጳጉሜን ቀን እንዲኖረው ከተደረገ በኋላ፣ ከኢትዮጵያው የሄኖክ/ዘመነ-ሐዋርያት የፀሐይ ዑደት ጋር በወራት ቁጥርና በትርፍ ቀናት አቀማመጥ ሙሉ በሙሉ እንዲገጣጠም ሆኗል። 3. በኢትዮጵያ እና በግብፅ (ኮፕቲክ) ካሌንደር መካከል ያሉ ዋና ዋና ልዩነቶች ምንም እንኳን ቅርፃቸው ቢመሳሰልም፣ በሁለቱ መካከል መሠረታዊ ልዩነቶች አሉ የኢትዮጵያ እና የግብፅ (ኮፕቲክ) ካሌንደር ልዩነቶች በሰፊው እና በዝርዝር እንደሚከተለው እናብራራቸው 1. የመነሻ ምንጭ 🎯 የኢትዮጵያ ካሌንደር መነሻው በመጽሐፈ ሄኖክ በተገለጸው የፀሐይ፣ የጨረቃና የከዋክብት መጋቢዎች ስሌት መሠረት የተቃኘ ነው። ይህ ስሌት ዓመቱን በአራት ክፍለ ዘመናት ይከፍላል። 🎯የግብፅ (Coptic) ካሌንደር መነሻው ከተፈጥሮ ክስተት ጋር የተያያዘ ሲሆን፣ በተለይም የአባይ ወንዝ ሙላት ወቅትና የሶቲስ (Sirius) ኮከብ በሰማይ ላይ የመታየት እይታን መሠረት በማድረግ የተፈጠረ ነው። 2. የዓመተ ምህረት መቁጠሪያ 🎯የኢትዮጵያ ካሌንደር የዓመታት ቁጥሩን የሚጀምረው ከዓመተ ዓለም (ዓ.ዓ) እና ከክርስቶስ ልደት (ዓ.ም) በመነሳት ነው። ከዓለም ፍጥረት እስከ ክርስቶስ ልደት 5500 ዓመታት እንደነበሩ በመቁጠር የራሱን ዓመተ ምህረት ይከተላል። 🎯የግብፅ (Coptic) ካሌንደር የሚቆጥረው በ«ዓመተ ሰማዕታት» (Era of Martyrs) ነው። መነሻውም ክርስቲያኖችን ያሳድድ የነበረው የሮም ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ ወደ ሥልጣን የመጣበት 284 ዓ.ም ነው። 3. የዘመን መለወጫ ቀን 🎯 የኢትዮጵያ ካሌንደር አዲስ ዓመት የሚጀምረው በመስከረም 1 ቀን ነው። ይህም በጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር መስከረም 11 (በዘመነ ሉቃስ መስከረም 12) ላይ ይውላል። 🎯የግብፅ (Coptic) ካሌንደር የዘመን መለወጫው «ቱት 1» (Tout 1) ይባላል። በጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር ከኢትዮጵያው መስከረም 1 ጋር በተመሳሳይ ቀን (መስከረም 11/12) ላይ ቢውልም፣ የስያሜው ታሪክና ባህላዊ ትርጉሙ የተለየ ነው። 4. የወራት ስሞች 🎯 የኢትዮጵያ ካሌንደር ወራቱ መስከረም፣ ጥቅምት፣ ኅዳር፣ ታኅሣሥ፣ ጥር፣ የካቲት፣ መጋቢት፣ ሚያዝያ፣ ግንቦት፣ ሰኔ፣ ሐምሌ፣ ነሐሴ እና ጳጉሜ በመባል ይታወቃሉ። 🎯 የግብፅ (Coptic) ካሌንደር ወራቱ የየራሳቸው የኮፕቲክ ስያሜ አላቸው፤ እነሱም ቱት፣ ባባ፣ ሃቶር፣ ኮያክ፣ ቶባ፣ አምሺር፣ ባራምሃት፣ ባራምውዳ፣ ባሻንስ፣ ባኦና፣ ኤፔፕ፣ መስራ እና ፒ ኮጊ ዔኖጂ (Pi Kogi EnOji - የጳጉሜ ምትክ) ይባላሉ። 5. የዓመታት ስያሜ 🎯የኢትዮጵያ ካሌንደር እያንዳንዱ ዓመት በየአራቱ ወንጌላውያን ስም (ማቴዎስ፣ ማርቆስ፣ ሉቃስ፣ ዮሐንስ) በየተራ ይሰየማል፤ በየአራት ዓመቱ ዑደቱ ይደገማል። 🎯 የግብፅ (Coptic) ካሌንደር ዓመታትን በአራቱ ወንጌላውያን ስም የመሰየም የሥርዓት ስያሜ የለውም። የግብፅና የኢትዮጵያ አቆጣጠሮች በቅርጽ ቢመሳሰሉም፣ የኢትዮጵያ አቆጣጠር መንፈሳዊና ስነ-ከዋክብታዊ መነሻው ከመጽሐፈ ሄኖክ የፀሐይ ዑደት የተገኘ ሲሆን፣ የግብፅ ደግሞ ከተፈጥሮ (ከአባይ ሙላትና ከኮከብ) የተነሳ ነው። ግብፃውያን በበዓላት ማሰቢያው (ባሕረ ሐሳብ) ረገድ ለዓለም ክርስቲያኖች ትልቅ አስተዋጽኦቢያደርጉም፣ የቀንና የወራት መዋቅሩ ግን የሁለቱም ሀገራት የጥንት ስልጣኔና የአፍሪካ ቀንድ የፀሐይ ዑደት ውጤት ነው። © እዩ @ethale @ethale
Открыть в Telegramከግብፅ የመጣ የቀን መቁጠሪያ የለንም! ጥላቻ እውር ያረጋል ። አንድ መሪጌታ ነኝ ስሜ ጽጌ መዝገብ ነው በPR ማሰተርስ አለኝ የሚል ግለሰብ DEVIN SHOW ላይ ቀርቦ የኢትዮጵያ የቀን አቆጣጠር ከግብፅ ነው የመጣው በማለት ጥላቻውን በሀሰት ከልሎ ቃለ መጠይቅ ሲያረግ ሰምቼው ውስጤ ተበሳጨ።ሰውየው ወይ አያቅም ወይም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ጥልቅ ጥላቻ ውስጥ ነው። ከደረሰው ወይም የእርሱን መሰል ውሸታሞች የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ከግብፅ የመጣ ነው የሚለውን አሰተሳሰብ ለሚያራምዱ እውነቱ ይደርሳቸው ወይም ውሸታቸውን ያጋልጥ ዘንድ ይሄን ላዘጋጅ ተገደድኩ የኢትዮጵያ የቀን አቆጣጠር መሠረቱ ከኢትዮጵያውያን የሄኖክ መጽሐፍ የተወሰደ የፀሐይ ዑደት ሲሆን፣ የዲሜጥሮስ ባሕረ ሐሳብ ደግሞ ለተንቀሳቃሽ በዓላት ማሰቢያነት ብቻ የገባ የሒሳብ ቀመር መሆኑን በግልጽ የሚያስረዱት ዋና ዋና የታሪክና የሃይማኖት መረጃዎች እንደሚከተለው ተደራጅተዋል 1. የኢትዮጵያ የቀን አቆጣጠር ከሄኖክ መምጣቱ (የፀሐይ ዑደት) የተከተለ ነው። ብዙዎች የኢትዮጵያ የቀን አቆጣጠር ከግብፅ (ከኮፕቲክ) መጣ ይላሉ፤ ነገር ግን የታሪክና የጽሑፍ ማስረጃዎች ተቃራኒውን ይነግሩናል ➽ የ364/365 ቀናትና የ13 ወራት መዋቅር በመጽሐፈ ሄኖክ (ምዕራፍ 21፣ 23፣ 24 እና 28) ላይ እንደተገለጸው ዓመቱ በ4 ክፍለ ዘመናት (በፀደይ፣ በበጋ፣ በመኸርና በክረምት) የተከፈለ ሲሆን፣ እያንዳንዳቸው 90 ቀናት አሏቸው።ለእነዚህ 360 ቀናት (4 × 90) አራቱ የክፍለ ዘመን መሪ ቀናት (ጳጉሜን) ተጨምረው 364 ቀናት ይሆናሉ።ኢትዮጵያ የምትከተለው 12 አበይት ወራት እያንዳንዳቸው 30 ቀናት እና 1 ንኡስ ወር ጳጉሜ 5 ወይም 6 ቀን መዋቅር ሙሉ በሙሉ ከዚሁ የሄኖክ የፀሐይ መጋቢዎች ስሌት ጋር አንድ ነው። ➽ የመጽሐፉ መገኛና የቋንቋ እውነታ መጽሐፈ ሄኖክ ሙሉ ይዘቱ ተጠብቆ የተገኘው በግዕዝ ቋንቋ በኢትዮጵያ ብቻ ነው። ግብፃውያን (ኮፕቲክ) እና ሌሎች አብያተ ክርስቲያናት መጽሐፈ ሄኖክን በካኖንነት (በቅዱሳት መጻሕፍትነት) አላካተቱትም ፣ የሄኖክን የ364/365 ቀናት የፀሐይ ዑደት መሠረት ያደረገ የቀን አቆጣጠር ከግብፅ ሊመጣ አይችልም። ➽ታሪካዊ ቅድመ አመጣጥ ግብፃውያን የራሳቸውን የኒል (አባይ) ወንዝ ሙላት መሠረት ያደረገ የቀን አቆጣጠር ይጠቀሙ ነበር። ኢትዮጵያውያን ግን ከክርስቶስ ልደት በፊት ጀምሮ በሄኖክ የፀሐይና የከዋክብት መጋቢዎች ስሌት ይመሩ ነበር። 2. የዲሜጥሮስ ቀመር ምንድን ነው? (የበዓላት ማሰቢያ እንጂ የቀን አቆጣጠር አይደለም) የቀን አቆጣጠራችን ከግብፅ መጣ ለሚለው ማደናገሪያ ዋናው ምክንያት የዲሜጥሮስን ባሕረ ሐሳብ ከቀን አቆጣጠር ጋር አደባልቆ የመረዳት ችግር ነው ➽ የዲሜጥሮስ ታሪካዊ አመጣጥ በ3ኛው ክፍለ ዘመን (200 ዓ.ም አካባቢ) የእስክንድርያው 12ኛው ሊቀ ጳጳስ አባ ዲሜጥሮስ፣ የፋሲካ (የትንሣኤ) በዓል በመላው ዓለም በአንድ ቀን እንዲከበር ለማድረግ የፀሐይንና የጨረቃን ዑደት ያጣመረ የሒሳብ ቀመር (አቡሻክር) አዘጋጁ። ➽ የቀመሩ ዓላማ የዲሜጥሮስ ቀመር አዲስ የቀን አቆጣጠር ወይም አዲስ ወራትን አልፈጠረም።የቀመሩ ዋና ሥራ የኢሁድ (የአይሁድ) ፋሲካ ከዋለበት በኋላ የሚመጣውን እሁድ፣ እንዲሁም የዐቢይ ጾም፣ የነነዌና የሌሎች ተንቀሳቃሽ በዓላትን ዕለት ማሰቢያ (መጥቅዕና አበቅቴ) ማስላት ብቻ ነው። ➽ ቀመሩ ወደ ኢትዮጵያ እንዴት ገባ? ኢትዮጵያ ከእስክንድርያ ጋር በነበራት የቤተ ክርስቲያን አንድነትና ቁርኝት ምክንያት፣ የበዓላትን መውጫ ቀን በአንድነት ለማክበር ሲባል የዲሜጥሮስን የሒሳብ ቀመር ተቀብላ በራሷ የሄኖክ የፀሐይ ዘመን አቆጣጠር ላይ ገጠመችው (ተገበረችው)። 3. የሁለቱ ልዩነት በአጭሩ ለማሰረዳት 1. መሠረታዊ አካል Core Element ልዩነት 🎯የሄኖክ ዘመን አቆጣጠር ሙሉ በሙሉ በፀሐይ ዑደት Solar Cycle ላይ የተመሠረተ ነው። አራቱን ክፍለ ዘመናት (ፀደይ፣ በጋ፣ መኸር፣ ክረምት) እና 12ቱን ወራት ከነ 5 ወይም 6 የጳጉሜን ቀናት ጋር በማስተካከል ጸንቶ የሚኖር የጊዜ መለኪያ ነው። 🎯የዲሜጥሮስ ባሕረ ሐሳብ በጨረቃና በፀሐይ ዑደት ቅንጅት (Luni-Solar Math) ላይ የተመሠረተ የሒሳብ ቀመር ነው። የጨረቃንና የፀሐይን መገናኛ በመጠበቅ የሚሰላ እንጂ የራሱ የሆነ ራሱን የቻለ የፀሐይ ወራት የለውም። 2. ዋና ተግባር 🎯የሄኖክ ዘመን አቆጣጠር መደበኛውን የዕለት ተዕለት የሥራ፣ የዓመት፣ የወራትና የቀናት ቁጥር መቁጠሪያ ነው። አዲስ ዓመት መቼ እንደሚጀምር (መስከረም 1) እና ቀናት እንዴት እንደሚተኩሩ ይወስናል። 🎯የዲሜጥሮስ ባሕረ ሐሳብ በየዓመቱ የሚቀያየሩ ተንቀሳቃሽ በዓላትንና አጽዋማትን (እንደ ጾመ ነነዌ፣ ዐቢይ ጾም፣ ትንሣኤ፣ ዕርገት፣ ጰራቅሊጦስ) መቼ እንደሚውሉ ማውጫና ማሰቢያ ቀመር ነው። 3. የታሪክ ምንጭ 🎯የሄኖክ ዘመን አቆጣጠር ከክርስቶስ ልደት በፊት የነበረና መጽሐፉ ሙሉ ይዘቱ በኢትዮጵያ በግዕዝ ቋንቋ ብቻ ተጠብቆ የቆየ ጥንታዊ የስነ-ከዋክብትና የዘመን አቆጣጠር ስርዓት ነው። 🎯የዲሜጥሮስ ባሕረ ሐሳብ በ3ኛው ክፍለ ዘመን (200 ዓ.ም አካባቢ) በእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ አባ ዲሜጥሮስ የተዘጋጀና በኋላም በክርስቲያኑ ዓለም ዘንድ የበዓላት መያዣ ሆኖ የተሰራጨ የሒሳብ ቀመር ነው። 4. የሚሰጠው ውጤት 🎯የሄኖክ ዘመን አቆጣጠር መደበኛ የቀን መቁጠሪያዎችን ያመርታል (ምሳሌ፡ መስከረም 1፣ ጥቅምት 1፣ ህዳር 1... እያለ ቀናትን ይቆጥራል)። 🎯የዲሜጥሮስ ባሕረ ሐሳብ መንፈሳዊና ስነ-ቁጥራዊ ስሌቶችን ያወጣል (ምሳሌ፦ አበቅቴን፣ መጥቅዕን፣ ወንጌላዊውን፣ እና የጾምና የበዓላት መውጫ ቀናትን ያሰላል)። ኢትዮጵያ የቀን አቆጣጠሯን (13 ወራትና የፀሐይ ዑደቱን) ያገኘችው ከራሷ መጽሐፈ ሄኖክ እንጂ ከግብፅ አይደለም። ከግብፅ (ከአባ ዲሜጥሮስ) የተወሰደው የበዓላት ማሰቢያ የሒሳብ ቀመር (ባሕረ ሐሳብ) ብቻ ነው። ስለዚህ የቀን አቆጣጠሩ ከግብፅ መጣ ማለት፣ በዓላትን ማሰቢያ ቀመር እና መደበኛውን የዘመን አቆጣጠር አለመለየት የሚመጣ ስሕተት ነው። የግብፅ የቀን አቆጣጠር መነሻ፣ ከኢትዮጵያ አቆጣጠር ጋር ያለው ተመሳሳይነት እና ልዩነታቸው በጥበብና በታሪክ መነፅር ሲቃኝ የሚከተለውን ይመስላል 1. የግብፅ ካሌንደር መነሻ የአባይ ወንዝ ሙላትና የሶቲስ ኮከብ፦ Ancient Egypt (ጥንታዊት ግብፅ) የቀን አቆጣጠሯን የፈጠረችው በአባይ ወንዝ ወቅታዊ ሙላት እና ሶቲስ (Sothis / Sirius) የምትባለዋን ደማቅ ኮከብ መነሻ በማድረግ ነው። ➽የሶስት ወቅቶች ክፍፍል ግብፃውያን ዓመቱን በሦስት ዋና ዋና የግብርና ወቅቶች ይከፍሉት ነበር 👉አኬት (Akhet) የውሃ ሙላት ወቅት 👉ፐሬት (Peret) የዘርና የእድገት ወቅት 👉ሸሙ (Shemu) የHarvest (የእህል ስብሰባ) እና የድርቅ ወቅት ➽የቀናት መዋቅር እያንዳንዳቸው 30 ቀናት ያሏቸው 12 ወራት (360 ቀናት) እና በዓመቱ መጨረሻ የሚገቡ 5 ተጨማሪ ቀናት (Epagomenal days) ነበሯቸው። 2. ከኢትዮጵያ ካሌንደር ጋር ለምን ተመሳሰለ? በሁለቱ አቆጣጠሮች መካከል ያለው አስደናቂ ተመሳሳይነት (12 ወራት የ30 ቀን + 5/6 የጳጉሜን ቀናት) መነሻቸው የሚከተሉት ምክንያቶች ናቸው።
Открыть в Telegramአፍሪካዊቷ ሀገር ቶጎ የኢትዮጵያን የቀን መቁጠሪያ የአፍሪካ ሀገራት እንዲጠቀሙት ጥሪ አስተላለፈች ! በዓለም ዙሪያ፣ አንዳንድ ሕዝቦች በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚታወቀው ሥርዓት ጎን ለጎን የራሳቸውን የጊዜ መለኪያ ሥርዓቶች እንደ ማንነታቸው ምልክት አድርገው ማቆየት ችለዋል።ኢትዮጵያም ከአፍሪካም የራሷ የቀን መቁጠሪያ ያላት ብቸኛ ሀገር ናት ። የሰው ልጅ እና የሥልጣኔ መገኛ የሆነች ኢትዮጵያ የራሷ የሆነ ልዩ የዘመን አቆጣጠር (ቀን መቁጠሪያ) ሥርዓት ያላት ብቸኛ የአፍሪካ ሀገር ስትሆን፣ ይህ ስልጣኔ ጥንታዊ፣ ሃይማኖታዊ እና አስትሮኖሚያዊ መሰረት ያለው የሀገሪቱ ታላቅ ቅርስ ነው። ነገር ግን ይህን ካልቀየርን የሚሉ አንዳንዶች ስንሰማ ሰነባበትን ። በዚህ መሐል ነዉ ቶጎ የቅኝ ግዛት ዘመን የቀን መቁጠሪያን በማስወገድ የአፍሪካ አዲስ ዓመት እንዲታወጅ ጥሪ ያቀረበችው ። ሀገሪቱ ከአፍሪካ ኅብረት ጋር በመተባበር የአፍሪካ አዲስ ዓመትን ጨምሮ ሌሎች አኅጉራዊ በዓላት የሚታወጁበትን ሁኔታ በተመለከተ በባለሙያዎች ባደረጉት ጥናት አፍሪካውያን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ አስተዳደር ውስጣዊ ስርዓቶች በቅኝ ግዛት ቀይረው አፍሪካ የማጣቀሻ ነጥቦቿን እና ማንነቷን እንድታጣ አድርጓታል ስልጣኔዋን ሸሽገዋል። ይህ በቅኝ ግዛት ወቅት በአፍሪካ አገሮች ላይ የተጣለው የግሪጎሪያን የቀን መቁጠሪያ እኛን አይወክልም ሲሉ ተሰምተዋል ። ይህ የቀን መቁጠሪያ ለውጥ፣ ምንም ጉዳት የሌለው የሚመስለው፣ የጊዜ ክፍፍልን እና ዋና ዋና ክስተቶችን አደረጃጀት በእጅጉ ቀይሯል፣ እራሳቸውም ለአፍሪካ የበላይ አድርገው እንዲያዩ አድርጓል ።ለምዕራባዊው ፍላጎት በተሰራ ስርዓት ውስጥ ጠልቀው እራሳቸውን ለማላመድ ወይም ለማረጋገጥ ለሚታገሉ አፍሪካውያን መዋሃድ እና የማንነት መጥፋት አስከትሏል። በዓለም ሥርዓት ለውጥ እና ከሌሎች ነገሮች በተጨማሪ ለዓለም ሚዛን መሠረት እና የጋራ ብልጽግና ሞተር ሆኖ ለልዩነት አክብሮትን የሚያቋቁም ባለብዙ-ፖላር ስርዓት ተራማጅ ብቅ ማለት በሚታወቅበት ዘመናዊ አውድ ውስጥ፣ አፍሪካ እራሷን እንደ ራስ ገዝ ኃይል ለማረጋገጥ በምትፈልግበት፣ አፍሪካ ታሪካዊ የጊዜ ክፍፍል ስርዓቷን እና ባህላዊ በዓላትን እና ቁልፍ ቀናትን ማደስ ግዴታ ይሆናል። የአፍሪካን የኢትዮጵያን አዲስ ዓመት ወደ ዓለም አቀፍ ቅርስ ለማሳደግ ጥናት መደረጉን የቶጎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል ። ዓላማው እንደ ቻይና፣ እስራኤል እና ህንድ ያሉ እንደ ቻይና፣ እስራኤል እና ህንድ ያሉ ሕዝቦች “ቹንጂ” ወይም የጨረቃ አዲስ ዓመት፣ በሰሜን ህንድ ሮሽ ሃሻናህ እና ዲዋሊ በቅደም ተከተል የሚያከብሩትን እና በአፍሪካ ውስጥ የኢትዮጵያዉ “እንቁጣጣሽ ” በሚባለው አዲስ ዓመታቸው ለየት ብለው የሚቆሙትን የኢትዮጵያ ሕዝቦች ሁሉ የአፍሪካን አዲስ ዓመት ወደ አንድ የጋራ ዓለም አቀፍ ቅርስ ደረጃ ከፍ ማድረግ ነው። ብሏል ። በተለይም የአፍሪካ አዲስ ዓመት ቀን በአፍሪካ ታሪካዊ፣ ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ ምልክቶች ላይ በመመስረት የኢትዮጵያን አቆጣጠር ለአህጉሩ ለማድረግ በሎሜ በዚህ ጭብጥ ላይ ዓለም አቀፍ ሲምፖዚየም ለማዘጋጀት አቅዳለች። የዚህ ሲምፖዚየም መደምደሚያዎች እና ምክሮች ውሳኔ እና ቀጣይ ተግባራዊ ለማድረግ ለአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ይተላለፋሉ። ይህ ተነሳሽነት የአፍሪካ ህዝቦች አህጉራቸውን እራሱን የሚያረጋግጥ እና የራሱን የልማት ጎዳና የሚወስን ራሱን የቻለ ኃይል አድርገው እንዲያረጋግጡ ከሚጠብቁት ጥልቅ ግምቶች ጋር ይጣጣማል። © ቅዱስ @ethale @ethale
Открыть в Telegramየዘመን ቀመሯንም አስሏት እንጅ? እ? በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የባሕረ ሐሳብ ጥበብ ከሚቀመረው የዘመን አቅጣጠር ላይ የዘመኑን ምዕራፍ የሚገልፀውን "ዓመተ ምህረት" የሚለውን ክፍል "እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር አስብለን አስቀየርን ፤ ድል አደረግን " የሚሉ ሽለላዎች ይደንቁኛል። ቅዲሚያ የዘመን ቀመሩን ከቤተክርስቲያኗ ውጭ ያለን እናውቀዋለን ወይ? በሏ... እ? መጀመሪያ የዘመን አቆጣጠሩን ምዕራፍ መጠሪያ ስያሜ "አስቀየርሁ" የሚለውን በውስጡ መታበይና ግብዝነት የታጨቀበት ስለላ ተወውና ቀመሩ እንዴት እንደሚሰራ ታውቃለህ ወይ? የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እንዴት ባለ ረቂቅ የቀመር ጥበብ እንደምታሰላው ታውቃለህ ወይ? ቤተርስቲያኗ እያንዳንዷን ሰከንድ፣ ደቂቃ፣ ሰአት፣ ቀን፣ ወር ቀምራ አመት እንደምታመጣው ታውቃለህ ወይ ? እ ? አንተ አንድ የቀጣይ አመት ልደትህ ከሰኞ እስከ እሁድ የቱ እለት ላይ እንደሚውል የማታውቀውን እንለፍህና .... መንግሰት እራሱ "የ30 አመት እቅድ አለኝ" የሚለው፣ እሱ በሚቀጥሉት ሰላሳ አመታት የራሱን በጀት በየትኛው እለት እንደሚጀምርና በየትኛው እለት እንደሚዘጋ ቀምሮ ስሌቱን ማምጣት ይችላል ወይ? ደግሞ እኮ "እዚህ አገር ቤተክርስቲያኗ ሁሉን ነገር በግድ ጭናብን ነው እንጅ ውጭ አገር እንዲህ የለም" የሚሉ ደናቁርትም አይቻለሁ። እያስጠሉኝም ቢሆን ስቂያለሁ ለመሆኑ "ውጭ አገር ..." እንደሚጠቀሙበት ብድግ ብለህ በጮሮቃነትህ ሳታፍር የጠቀስከውን አቆጣጠር የካቶሊክ ቤተክርስቲያን እንደ ቀመረችው ታውቃለህ? Gregorian Calendar የሚለውን ስያሜ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ለዘመን አቆጣጠራቸው የሰየመችው በ1582 የካቶሊክ ጳጳስ በነበሩት Gregory 13ኛ ስም መሆኑን ታውቃለህ? ላብራራልህ። ለምሳሌ አመቱ በኢትዮጵያ ስንት ነው? 2018 ዓ.ም ነው አይደል? ከፈግህ 'ዓ.ም' የሚለውን ዝለለው። ቁጥሯን ግን ከቤተክርስቲያኗ ነው ተቀምራ ያገኘሃት ወደ ፈረንጆቹ ልመልስህ። ያው ሁሉ ነገር በአንተ አገር ብቻ አስልተህ "ተጭኖብኝ" ስላልህ ነው.... በፈረንጆቹ ደግሞ 2026 G.C ወይም 2026 A.D ነው። G.C ማለት Gregorian Calendar ነው ብለናል አይደል። ግሪጎሪያን የሚለው ከማን ስም የተወሰደ ነው ከጳጳሱ ግሪጎሪ 13ኛ ... ወይም ደግሞ A.D የሚለው ከየት የመጣ ነው? እ... ትሞክራለህ? ግዴለም ጉግልም ይነግርሃል። የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የኃይማኖት መገልገያ ኦፊሻል ቋንቋ ሁኖ ከቀጠለው የላቲን ቋንቋ የተገኘ ነው። ምን ማለት ነው? 'Anno Domini" .... በእንግሊዝኛ እንመልሳትና ከዛ በአማርኛ ትቀለናለች .... እንግሊዝኛ አቻው "In the year of our Lord" ማለት ነው። ጥሩ! .... የኢትዮጵያው "ዓመተ ምህረት" ከየት ይጀምራል? ከክርስቶስ ልደት አልህ? ጥሩ! ስለዚህ ቤተክርስቲያን የዘመን ቀመሩን ስትሰራ መሰረቷ የሆነውን ክርስቶስን መነሻ አድርጋ ነው። ከእሱ ልደት በፊት ያለው ምህረት ያልነበረበት ዘመን ስለነበር ምን አለችው? " ዓመተ ፍዳ" .... የእሱ ልደት ግን ምህረታችንን ስላበሰረ ምን ትለዋለች ቤተክርስቲያን? "ዓመተ ምህረት" ... የካቶሊክ ቤተክርስቲያንም "In the year of our Lord" ወይም A.D ስትል ከክርስቶስ ልደት መነሳቷ ስለሆነ "ዓመተ ምህረቷ" ነው። ፈረንጆች ቀመሩን ያጠኑታል። ሙያ፣ ሳይንስ፣ እውቀት ያደርጉታል አንጅ እራሳቸው ከቤተክርስቲያን ወስደው ሳለ ዙረው "ቤተክርስቲያን ጭናብን" እያሉ አያለቅሱም። ነገሩን በእውቀትነቱ ይወስዱታል። ኢ-አማኝም ሁነው እንኳን የእውቀቱን ውጤት መጠቀም ማመን እንዳልሆነነ ያውቃሉና! በእኛ አገርም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የዘመን ቀመሯን በማንም ላይ አልጫነችም። ራሷ ቀመረች። ለእራሷ የአገልግሎትና በዚህ ምድር ያለው ተልዕኮዋ ተፈፅሞ ይሄ ምድር እስኪያልፍ ዘመን እያሰላችበት ቀጠለች። ትቀጥላለችም። መንግስትም፣ ኢ-አማኙም፣ ክርስቲያን ያልሆነውም የቤተክርስቲያኗ የእውቀት ትሩፋት የሆነውን ዘመን ተከትሎ ቆጠረ እንጅ አላስገደደችውም። አልጫነችበትም። ስለሆነም "ዘመኑ የምህረት ነው" ብላ የምታምንና የምታስተምር ቤተክርስቲያን "ዓመተ ምህረት እንዲባል አንፈልግም" ያሉትን አስገድዳ ዘመን አቆጣጠሩን ስላልጫነችባቸው በትዕቢት ተወጥረው፣ የሌለ ውድደር እንዳሸነፉ ቆጥረው "ትተነዋል" ሲሏት "መጀመሪያስ ወሰዳችሁ እንጅ የቀመሩ ባለቤት መቼ ነበራችሁ" ብላ እሷ ትቀጥላለች። ይሄን ስል "Secular የሆነ የዘመን ቀመር ይኑረን" ብለው የሚጠይቁትን ጥያቄ "ተገቢ ጥያቄ አይደለም" እያልኋቸው አይደለም። ነገር ግን "ሴኩላሩን" የዘመን ቀመር ትቀምሩታላችሁ ወይስ የምትወቅሷትን ቤተክርስቲያን ቀመር ቁጥሩን ቤተክርስቲያን አስልታ ስታውጅ እየተከተላችሁ ያለ አውዱ ስለወሰዳችሁ "ድል" ይመስላችኋል ወይ? ማለቴ ነው! አንድ አባባል አለ። እና እሱ አባባል "ከመረቁ አድርጉልኝ ከስጋው ፆመኛ ነኝ" ያለው ግማሽ ሰውዬ አባባል ነው። ግማሽነታችሁን ባናነሳውም ... ቢያንስ ቤተክርስቲያኗን "አሸነፍናት" ስትሉ ለሚነሳባችሁ የዕውቀት ነክ አመክንዮ አትዘናጉ ማለቴ ነው። ሁሉንም ነገር ፖለቲካ፣ ትርክትና ጥላቻ አትቀቡት! እውቀት እምነት ተሻጋሪ ነው!
Открыть в Telegramየኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የሀገረ አሜሪካ ህዝብ በዋናው አውራ ጎዳና ላይ በሰልፍ በመውጣት ንጉሡ ነገሥቱ እንኳን ደህና መጡ በማለት የክብር አቀባበል ሲያደርግላቸው የተነሱ ፎቶዎች ነው። ግርማዊ ጃንሆይ እና የአሜሪካ ፕሬዝዳት ጆን ኤፍ ኬኔዲ (በሊንከን ሜሪኩሪ ኮንቲኔንታል ፕሬዚዳንታዊ ሊሙዚን) ሞዴል መኪና ላይ ሆነው ከኒውዮርክ ጎዳና ወደ ፔንስልቬንያ ጎዳና ላይ እየተጓዙ ለህዝቡ ሰላምታ ሲሰጡ ይታያል። ህዳር 12 ቀን 1956 ዓ.ም ዋሽንግተን ዲሲ @ethale
Открыть в Telegramማቲሴን የሚያስከነዱት የኢትዮጵያ ጠቢባን አባቶች! ከዚህ በታች የሚገኘው የብራና ገጽ 600 ዓመታትን ያስቆጠረ ድንቅ ጥበብ ነው። ዛሬ "ዘመናዊ" የምንላቸው የጥበብ ፍልስፍናዎች ገና ሳይወለዱ፣ አባቶቻችን በብራና ላይ ጥበብን አፍስሰውታል። 📜 ከጥፋት የተረፈው ድንቅ ቅርስ ይህ ገድል በንጉሥ ዳዊት ዘመን በሊቃውንት አባቶቻችን የተሳለና የተፃፈ ነው። ግራኝ አህመድ የቤተክርስትያን ድርሳናትን ያወድም ነበረ በሚባልበት ክፍለታሪክ ወቅት፣ ካህናቱ ለሕይወታቸው ሳይሳሱ ረዥም መንገድ ተጉዘው ይህን ድርሳን ከሰው እይታ ሰውረውታል። ጉዞው፦ ከቆመበት ስፍራ 500 ኪሎሜትሮችን ተጉዞ ዛሬ በዝዋይ ሐይቅ ደብረ ፅዮን ገዳም ተጠልሎ ይገኛል። 💡 ከሄንሪ ማቲሴ በ 500 ዓመት ቀድመን! የዓለም የጥበብ ታሪክ መጽሐፍት (በተለይ በ 2023 የታተሙት) በዚህ ሥዕል ተገርመዋል። ምክንያቱም፦ ፈረንሳዊው ሰዓሊ ሄንሪ ማቲሴ (Henri Matisse) በ 20ኛው ክፍለ ዘመን ያስተዋወቀውን የ "Collage" እና የዝርዝር መደፍጠጥ (flat design) ስልት፣ የእኛ አባቶች ከ 500 ዓመት በፊት ተጠቅመውበታል። አውሮፓውያኑ በ "Renaissance" ዘመን ገና የባለ ሶስት ገፅታ (3D) አሳሳልን ሲለማመዱ፣ የእኛ አባቶች ረቂቅ (Abstract) ጥበብ ላይ ደርሰዋል። "የአውሮፓ አብስትራክት አርቲስቶች እንደ አክሱም ያሉ በረቂቅ ዲዛይን የተቀመሩ ስራዎችን ቢያዩ ምን ይሰማቸው ይሆን? በሺህ ዓመታት ቀድመናቸዋል!" ⚠️ የኋሊት ጉዟችንና የራሳችንን መናቅ የሚያሳዝነው ግን፣ ይህን የመሰለ የላቀ የፅሕፈት አርት (Calligraphy) እና ስልጣኔ የነበረው ሕዝብ፣ በዛሬው ዘመን በምን ተዓምር አብዛኛው መሐይም (መፃፍ ማንበብ የማይችል) ሆኖ ወደ "መሰረተ ትምህርት" ተመለሰ? የሚለውን ስናስብ ነው። ስህተታችን ፦ ዘመናዊነትን ከውጭ ፍርፋሪ ፍለጋ ጋር አቀላቀልነው። ውጤቱ፦ የራሳችንን የከበረ ጥበብ አርክሰን፣ የሰው ተውሶ የምንኖር "ተንሳፋፊ" ትውልድ ሆንን። 🛡️ ታሪካችንን እንጠብቅ! አንዳንድ ጸሐፍት "ኢትዮጵያውያን ይህን ሊሰሩት አይችሉም፣ የውጭ አገር ሰዓሊዎች ተቀጥረው ነው" ይላሉ። እውነታው ግን ላሊበላም ሆነ እነዚህ የብራና ስዕሎች የአባቶቻችን የላብና የጥበብ ውጤቶች ናቸው። እኛ ለዓለም ያስተማርን፣ ዓለምን የቀደምን ነበርን! ዛሬ ቁልቁል ብንወርድም፣ የዓለም ጉዞ ገና አላበቃም። ልጆቻችን ከዚህ የታሪክ ቁጭት ወጥተው፣ የራሳቸውን መነሻ አውቀው ለክብር እንደሚበቁ ተስፋ እናደርጋለን። © አሳፍ ኃይሉ @ethale
Открыть в Telegramአሜሪካዊው ሳይንቲስት መህሙድ ጃዋይድ አረጋገጠ! 🔴➨የኤዶም ገነት የምትገኝው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው። #DAILY_MAIL ሳይንቲስቱ አለምን ጉድ ያሰኘው አዲስ ዜና ይዞ ብቅ ብሏል! በአሜሪካ ቴክሳስ ግዛት የሚገኙ የተመራማሪ ቡድኖች የመፅሐፍ ቅዱስን ኤደን ገነት ትክክለኛ መገኛ ስፍራ በአፍሪካ ውስጥ ኢትዮጵያ እንደሚገኝ አረጋገጡ። ትርጉሙን እንደሚከተለው አቅርበነዋል! በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት የኤደን ገነት እግዚአብሔር አዳምና ሔዋንን ያስቀመጠበት ስፍራ ነበረ:: በመፅሐፍ ቅዱስ ላይ የተጠቀሱት ታላላቅ ወንዞች ማለትም ግዮን፣ ኤፍራጥስ፣ ጤግሮስና ፒሶን ሲሆኑ ብዙ ምሁራን ጤግሮስ እና ኤፍራጥስ በዘመናዊቷ ኢራቅ ውስጥ ስለሚጓዙ ኤደን በዚያ አካባቢ መሆን አለበት ብለው ሲገምቱ ከርመዋል ነገር ግን የቴክሳስ ምርምር መሪው #ማህሙድ ጃዋይድ የኬሚካል መሐንዲስ ሲሆን በምርምር ውጤቱ መሰረት የኤደን ገነት በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ ለም በሆነው ባህር ዳር፣ ብሉ አባይ በሚጀምርበት የጣና ሀይቅ ደቡባዊ ጫፍ አቅራቢያ እንደሆነ መረጋገጡን ይናገራል። ማህሙድ የሚመራው ቡድን ጥናቱን የተመሰረተው መጽሐፍ ቅዱስን እና ቁርኣንን በጥንቃቄ በማንበብ ስለ አዳምና ሔዋን፣ ስለ ወንዞችና ስለ አትክልት ስፍራው የሚገልጹትን መግለጫዎች በመተንተን ነው። እ.ኤ.አ. በ2025 የተደረገው ጥናት በአቻ-ያልተገመገመ፣ የብሉ ናይል ወንዝ ከመጽሐፍ ቅዱሳዊው ግዮን ጋር ሊመጣጠን እንደሚችል እና የጣና ሀይቅ ፈሳሾች ወደ ብዙ የውሃ መስመሮች ተከፍለው በዘፍጥረት የተገለጹትን አራቱን ወንዞች ሊፈጥሩ እንደሚችሉ ተጠቁሟል። ቀደምት የሰው ልጅ ዝግመተ ለውጥ እንዲሁ በዚህ ፅንሰ-ሀሳብ ውስጥ ሚና ተጫውቷል፣ አዳም የሰው ልጅ መገኛ ነው ተብሎ በሚታሰበው በምስራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ ውስጥ ከሆሞ ሃቢሊስ ወይም ከኦስትራሎፒቴከስ ዘግይቶ ከተገኘ የአውስትራሊያ ስምጥ ሸለቆ ሊሆን እንደሚችል ሀሳብ አቅርቧል። ከዚያ ተነስተው አዳምና ሔዋን በቁራአን 'ሀባታ' ብሎ የገለፀውን በስምጥ ሸለቆ ውስጥ ሰፍረው ከመውረዳቸው በፊት በከፍታ ቦታ ላይ በምትገኘው በባህር ዳር ደጋማ ቦታዎች 'ሊቀመጡ' ይችሉ ነበር። ምክንያቱም ክልሉ ከባህር ጠለል በላይ 6,000 ጫማ ከፍታ ላይ ስለሚገኝ፣ ለምለም እፅዋት፣ የተትረፈረፈ የዱር አራዊት እና ብሉ ናይል የሚጎርፈው፣ ከሁለቱም መጽሐፍ ቅዱሳዊው የኤደን ወንዞች መግለጫ እና የቁርአን ፅንሰ-ሀሳብ ጋር የሚጣጣሙ ባህሪያት ናቸው። መህሙድ ጃዋይድ ከዚህ በፊት ከ11 በላይ የእስልምና የጥናት መፅሃፍቶችን በማሳተም የሚታወቅ ሲሆን በዚህ አዲስ ጥናት መሰረት ኤደን ገነትን በተመለከተ ሁሉም ፍንጮች የሚያመለክተው ባህር ዳር ጣና ሃይቅ እንደሆነና ይፕጣና ሀይቅ የኤደንን መግለጫ በትክክል ይስማማል' ሲል ሲጽፍ የእሳተ ገሞራ ሸንተረሮች በዙሪያው ያሉትን ደጋማ ቦታዎች እንደሚሸፍኑ እና የበርካታ ወንዞችን ስርዓቶች እንደሚመገቡም ጠቁመዋል። በመልሶ ግንባታው የጣና ሐይቅ ራሱ ኤደንን የሚወክል ሲሆን የኤደን ገነት ወዲያውኑ ወደ ደቡብ፣ ባህር ዳር ዙሪያ፣ ‘ከኤደን ምስራቃዊ’ በመጽሐፍ ቅዱሳዊ አገላለጽ ወንዙ ከሐይቁ የሚወጣበት ነው። የኦሪት ዘፍጥረት መጽሐፍ አዳምና ሔዋን ከተባረሩ በኋላ ሰዎች ወደ ሕይወት ዛፍ እንዳይገቡ አምላክ በገነት መግቢያ ላይ ያስቀመጠውን ‘የሚንበለበል ሰይፍ’ ይናገራል የሕይወት ዛፍ የዘላለም ሕይወት የሚሰጥ ፍሬ ያለው እውነተኛ ዛፍ ነበር። አዳምና ሔዋን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ በልተው ኃጢአት ከሠሩ በኋላ የሕይወትን ዛፍ እንዳይበሉና በወደቁበት ሁኔታ ለዘላለም እንዳይኖሩ ከኤደን ተባረሩ። የጃዋይድ ጥናት ‘የሚያብረቀርቅ ሰይፍ’ በኢትዮጵያ ደጋማ አካባቢዎች በጣና ሀይቅ ዙሪያ በሚገኙት የእሳተ ገሞራ ሸንተረሮች ሊወክል እንደሚችል ጠቁሟል። ሸለቆው በታሪካዊ ንቁ እሳተ ገሞራዎች የተከበበ መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት ንቁ የሆኑት እሳተ ገሞራዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሰውን የእሳት ሰይፍ መሥራታቸው ይቻላል' ሲል ተናግሯል። ጥናቱ በመጽሐፍ ቅዱስም ሆነ በቁርኣን ላይ ያተኮረ ሲሆን እያንዳንዱም በምድር ላይ ያለን የአትክልት ስፍራ ለጻድቃን ከተዘጋጀው ዘላለማዊ ገነት የተለየ መሆኑን በመጥቀስ የክልሉ የአየር ጠባይ፣ ለም አፈር እና የተትረፈረፈ የውሃ አቅርቦት ከረሃብ፣ ከጥማት እና ከአስጨናቂ ሙቀት የጸዳ ቦታን በቅዱሳት መጻህፍት እንደሚያንጸባርቅ አመልክቷል። መሃሙድ በቅርቡ ክልሉን የዳሰሰችው እና 'ጓሮዎች በቀለማት ያሸበረቁ bougainvillea፣ ትልቅ ሂቢስከስ እና ጥሩ መዓዛ ባላቸው የፍራንጊፓኒ ቁጥቋጦዎች የተሞሉ ናቸው' የሚለውን የቨርጂኒያ ሞሬል ስራዎችን ጎላ አድርጎ ገልጿል። ወፎቹ በብዛት ይገኛሉ፣ ‘ዘማሪ ወፎች፣ ሸንኮራ አድራጊዎች፣ ጎሽ ሸማኔዎች፣ ሮዝ ፊንቾች፣ ከአበባ ወደ አበባ የሚበሩ ናቸው። ሞሬል እንዳለው ጥቅጥቅ ያሉ የፓፒረስ ቁመቶች በጣና ሀይቅ የባህር ዳርቻ ላይ ይበቅላሉ። ‹ባህር ዳር በደረቀ አየሯ እና በአበቦች እና በአእዋፍ ችሮታ ፣ኢትዮጵያ ውስጥ ወደ ገነት የመድረስ ያህል ቅርብ ነች። የአእዋፍ ዝማሬ እና ነፋሱ በጃስሚን፣ ዝንጅብል እና ሃኒሱክል መዓዛ ያለው ንፋስ አካባቢውን በጣም ከፍ ያደርገዋል። የበለስ እና የማንጎ ዛፎች፣ ግራር እና የውጭ ባህር ዛፍ በአካባቢው ባለው የጥቁር አባይ ሳር ዳር ላይ ጥሩ ጥላ ይሰጣሉ።' እነዚህ ዝርዝሮች፣ መሃሙድ ጃዋይድ እንዳለው፣ ክልሉ በምድር ላይ ለገነት በጣም ቅርብ ቦታ እንደሚሆን ጠቁመዋል። በቁርአን መሰረት አደምና ሀዋ (ሄዋን) ከፀሀይ እና ከሙቀት የተጠበቁ ስለነበሩ የተለያዩ አይነት ፍራፍሬዎች የሚበሉበት፣ ወፏ የሚዘምርበት እና ጥሩ መዓዛ ያለው ንፋስ የሚሸቱበት ባህር ዳር ጥሩ ቦታ መሆን አለበት' ሲል ጥናቱ አስነብቧል። ምንጮ:- 1ኛ:- Daily Mail https://www.dailymail.co.uk/sciencetech/article-15166613/Garden-Eden-expert-claims-Biblical-paradise-sits-shores-mysterious-blue-lake.html 2ኛ:- GBI https://www.gbnews.com/science/garden-of-eden-found-ethiopia 3ኛ:- Daily Express USA https://www.google.com/amp/s/www.the-express.com/news/world-news/186241/engineer-claim-garden-eden-map-location/amp 4ኛ:- Acadamia.edu https://www.academia.edu/129924395/The_Location_of_the_Garden_of_Eden 5ኛ:- UNILAD https://www.unilad.com/news/world-news/george-kourounis-door-to-hell-reveals-what-he-found-545414-20231213 6ኛ:- Amazon.com https://www.amazon.com/-/es/Mahmood-Jawaid/dp/1598729624
Открыть в TelegramПереслано из ዓለም ማያ
ሸዋረገድ ገድሌ በፋሺስት ጣሊያን ወረራ ጊዜ አስደናቂ ጀብድ ከፈጸሙ ሴት አርበኞች መካከል ግንባር ናት።ቀይ መስቀል ሲመሰረት ሙሉ ሀብቷን በመሸጥ ድጋፍ አድርጋለች። ለአርበኞች ስንቅ በማቀበል ፤ መድኃኒት በመስጠት እንዲሁም መረጃ በማሰባሰብ ትታወቃለች። ሸዋረገድ አንድ ዕለት ጫካ ውስጥ ስትዋጋ ጣሊያኖች አገኟት።ሴት በመሆኗ በንቀት ዐይን እያዮዋት " ቆይ አንች ሴት ነሽ ጫካ ውስጥ ምን ትሰሪያለሽ? " በማለት ጣሊያናዊው ወታደር ጠየቃት። "ምክንያቱም የአንበሶች መኖሪያ ጫካ ስለሆነ! " በማለት ነበር ምላሽ የሰጠችው። እንኳን ለ84ተኛው የኢትዮጵያ አርበኞች በዓል በሰላም አደረሳችሁ! 📍share & join⚡️ @alememaya @alememaya
Открыть в Telegram