ወደ ቆላስይስ ሰዎች 1:13-20 [13-14] እርሱ ከጨለማ ሥልጣን አዳነን፥ ቤዛነቱንም እርሱንም የኃጢአትን ስርየት ወዳገኘንበት ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግሥት አፈለሰን። [15-16] እርሱም የማይታይ አምላክ ምሳሌ ነው። የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥ በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው። ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል። [17] እርሱም ከሁሉ በፊት ነው ሁሉም በእርሱ ተጋጥሞአል። [18] እርሱም የአካሉ ማለት የቤተ ክርስቲያን ራስ ነው። እርሱም በሁሉ ፊተኛ ይሆን ዘንድ፥ መጀመሪያ ከሙታንም በኵር ነው። [19-20] እግዚአብሔር ሙላቱ ሁሉ በእርሱ እንዲኖር፥ በእርሱም በኩል በመስቀሉ ደም ሰላም አድርጎ በምድር ወይም በሰማያት ያሉትን ሁሉ ለራሱ እንዲያስታርቅ ፈቅዶአልና። 🙌🙌🙌🙌 @Enopionchannel
Открыть в TelegramПосты канала Enopion channel🔥🔥
.....፤ በርባን እኔው እንደ ሆንሁ ዐወቅሁ፤ ዐመፀኛው ተፈትቼ አንተ ንጹህ ራሱ እንኳን የሚቀናብህ ንጹሕ ተሰቀልህ። አብሰክስከን ገጽ 55 ፊሊሞን ነጋ @berbantefeta
Открыть в Telegramለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም። — ትንቢተ ኤርምያስ 29:11 @Enopionchannel
Открыть в Telegramቁዱሱን ጌታ የምር የማወቅ ጥማት ካላቹ አስቀድማችሁ ጫማቹን አውልቁ መገኛ ቦታው ቅዱስ ነውና። ይህም መገኛው እና መኖሪያው ቤተ መቅደሱ እናንተ ስለሆናቹ ከሀጢያት እና እርኩሰት እራቁ። @enopionchannel
Открыть в Telegramካንተ ተከራክሮ ከሺህ ነገር አንዱን መመለስ የቻለ ሊያወራ ጀምሮ አንገቱን ቀና አርጎ ቆሞ የቀጠለ ሊያርምህ የዳዳው ሊያስተካክልህ እስኪ የቱ አዋቂ ነው ተው በዚህ ነው ሚልህ 🎶 🎶 @Enopionchannel
Открыть в Telegramዛሬ ጌታ አንድ ነገር አስተማረኝ😊 ለካ አባቶቻችን ለጌታ እራሳቸውን እስከ መሠዋት እና ለወንጌሉ በነፍሳቸው የተወራረዱት የእነርሱ ህይወት ከጌታ እና ከወንጌሉ እንደሚያንስ ስለ ገባቸው ነው። ምናልባት በአዕምሮአቸው ከጌታ አንፃር የኔ ምንድር ናት ከወንጌሉ ይልቅ ህይወቴ ምን ዋጋ አላት ስላሉ መሠለኝ🤔 @Enopionchannel
Открыть в Telegramበህይወታቹ ላይ በዝምታ ውስጥ ለብቻቹ ሆናቹ ከሆነ ስጋት ሳይሆን ጌታ በዛ ዝምታ ውስጥ ትልቅን ነገር ሊያስተምራቹ ፈልጓል እና ዝምታውን አትፍሩት አትሽሹት እደጉበት ተማሩበት ጌታ ለትልቅ ሰፊ እርሻ እያዘጋጃችሁ ነው። @enopionchannel
Открыть в TelegramПереслано из ብስራት (graph)
የማቴዎስ ወንጌል 5:21-24 •••••••••• ²¹ ለቀደሙት። አትግደል እንደ ተባለ ሰምታችኋል፤ የገደለም ሁሉ ፍርድ ይገባዋል። ²² እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፤ ወንድሙንም ጨርቃም የሚለው ሁሉ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል፤ ደንቆሮ የሚለውም ሁሉ የገሃነመ እሳት ፍርድ ይገባዋል። ²³ እንግዲህ መባህን በመሠዊያው ላይ ብታቀርብ፥ በዚያም ወንድምህ አንዳች በአንተ ላይ እንዳለው ብታስብ፥ ²⁴ በዚያ በመሠዊያው ፊት መባህን ትተህ ሂድ፥ አስቀድመህም ከወንድምህ ጋር ታረቅ፥ በኋላም መጥተህ መባህን አቅርብ። @bisrat_graphics
Открыть в TelegramПереслано из ብስራት (graph)
የማቴዎስ ወንጌል 5:43-44,46 •••••••••• ⁴³ ባልንጀራህን ውደድ ጠላትህንም ጥላ እንደ ተባለ ሰምታችኋል። ⁴⁴ እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና። ⁴⁶ የሚወዱአችሁን ብትወዱ ምን ዋጋ አላችሁ? ቀራጮችስ ያንኑ ያደርጉ የለምን? @bisrat_graphics
Открыть в TelegramПереслано из ብስራት (graph)
የማቴዎስ ወንጌል 5:14-16 •••••••••• ¹⁴ እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም። ¹⁵ መብራትንም አብርተው ከዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያኖሩታል በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል። ¹⁶ መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ። @bisrat_graphics
Открыть в Telegramበመርከብ ስባሪ ነገን መቀጠል የሚችል የኛ ጌታ ብቻ ነው። አለቀ ተብሎ ለተቀበረው አልዓዛር ህይወትን ለግሶ የሞተውን ተገንዞ የተዘጋውን የህይወት ዶሴ ከፍቶ ከመቃብር ድንጋይ መሃል አውጥቶ ግንዙን የለምንም ድጋፍ የሚያቆም ጌታ ብቻ ነው። አመኑኝ ጌታ ከእናንተ ጋር ይሁን እንጂ ግንዙ ይቆማል በህይወት ይኖራል🙌😍 @Enopionchannel
Открыть в TelegramПереслано из የተፈታው በርባን The released Barabbas
አገልግሎት:- አገልግሎት ማለት የፍቅር ዕዳ ነው፥ መመለስ ያለበት የፍቅር ዕዳ። በዕዳ የተያዘ ሰው ያለበትን ዕዳ ሳይመልስ እረፍት የለው ሁሌ አበዳሪውን ሲመለከት ሰርቶ እዳው መክፈል እንዳለበት እያሰበ ይጠነካከራል። ልክ እንዲሁ ደግሞ ውለታ ያለበት ሰው ለተዋለለት ውለታ ሲል ብዙ ነገር ያደርጋል። ህይወቱን በማዳን ውለታ ለዋለለትም ሰው ህይወቱ እንኳን የሚጠይቅ ጉዳይ ሲመጣ ያለምንም ማቅማማት ውለታውን ለመክፈል ጠንክሮ ይቆማል። አገልግሎት እንደዚህ ነው የፍቅር ዕዳም የውለታም ምላሽ ነው። ልክ ውለታ ያለበት ሰው ውለታውን በመመለስ ጉዳይ እንደ ማይደራደር የዕዳ ያለበትም ሰው ዕዳው ከፍሎ ሳይጨርስ እንደማይቀልድ ለራሱ ዕረፍትን እንደማይሰጥ ለእኛም ጌታን ስናገለግል እንዲሁ መሆን አለብን ዕዳችንን ክፍለን እስክንጨርስ አንረፍ ውለታን ሳንመልስ አንቀመጥ። @berbantefeta
Открыть в Telegramበምድር ላይ ባለን ህይወት እንግልት ቢበዛብንም ግን አንድ ማንም ጣልቃ የማይገባበት ፈፅሞ የምናርፍበት ሀዘን፣ጭንቅ፣ መከራ፣አስጨናቂ፣ተጨናቂ የሌለበት ደስታ ራሱ ጌታ የሆነበት ሌላ ነገርን ለመደሰት ብለን የማንፈልግበት አዎን ግዜው ደርሷል። ጌታችን የናፈቅነው ብቸኛ ተስፋችን ኢየሱስ ክርስቶስ በክብር በመላዕክት ታጅቦ ሊወስደን ተስፋችንን እራሱን ሊያስጨብጠን ተመልሶ ይመጣል። @Enopionchannel
Открыть в Telegramጌታ ያለበት የዋለ ሀጢያትን ይፀየፋል ከአመፅ ፈፅሞ ይርቃል። ውሎአቹን ቀይሩ ጌታ ያለበት ዋሉ ጌታን የሚያከብር አዋዋል ይኑራቹ። የማታድጉበት የጌታን ፊት የማታዩበት እና ፊቱን ፈገግ የማታሰኙበት ቦታ አትዋሉ። ጓደኞቻቹን ምረጡ ተግባሮቻቹን ምረጡ ለሁሉም የጌታን ፈቃድ ጠይቁበት። @Enopionchannel
Открыть в Telegram