በወንጀል ማጥ ውስጥ መዘፈቅ የህይወት መጨረሻ አይደለም። ወንጀል ልብን ቢያቆሽሽም፣ የአላህ የተውበት በር ሁሌም ክፍት ነው። «ከእዝነቴ ተስፋ አትቁረጡ» የሚለውን ቃል አስታውሰን ከሰራነው ወንጀል ስንፀፀት፣ አላህ በይቅርታው ይቀበለናል። ከስህተት የጠራ ማንም የለም፤ በላጩ ግን ቶሎ ተፀፅቶ የሚመለሰው ነው። @drzakirnaiki
Открыть в TelegramПосты канала ዶ/ ዛኪር ናይክ || ™️
የአላህ እርግማን በሳሂሮች ላይ ይሁን! በነሱ ሰበብ የስንቱ ሞቅ ያለ ጎጆ ፈረሰ... የስንቱ ብሩህ ወጣት የተስፋ ብርሃን ጨለመ... ስንቷስ ንፁህ እህታችን በስቃይ አረረች... የሰውን ደስታ ነጥቆ መኖር ከምንም በላይ ያማል። @drzakirnaiki
Открыть в Telegramበሶላትህ አትቀልድ። ዉዱእህን አሳምረህ፣ ሀሳብህን ሰብስበህ፣ ሩኩዕና ሱጁድህን በተረጋጋ መንፈስ ፈፅም። ስልክ ላይ ሰዓታትን እያባከንን፣ ለአላህ የምንሰጠው 15 ደቂቃ ሊከብደን አይገባም። @drzakirnaiki
Открыть в Telegram➔ለስኬትህ — ወላጆችህን ኻድም ➔ለሐዘንህ ማስወገጃ— የየቲምን ራስ ዳብስ ➔ከጭንቀትህ መውጫ — ወደ ሶላት ተጠጋ ➔ለቀልብህ መለስለስ — እጅህን ለሶደቃ ዘርጋ @drzakirnaiki
Открыть в Telegramየዱሃ ሶላት... ነቢዩ (ﷺ) እንዳስተማሩን በሰውነታችን ውስጥ 360 መገጣጠሚያዎች ያሉ ሲሆን፣ በየቀኑ በሰላም ለተንቀሳቀሰበት ለእያንዳንዱ መገጣጠሚያችን ምስጋናና ሰደቃ ማቅረብ ይጠበቅብናል። ይሁን እንጂ የአላህ እዝነት ሰፊ ነውና—በረፋድ ሰዓት የምንሰግዳት ሁለት ረከዓ የዱሃ ሶላት ብቻዋን ለእነዚህ ሁሉ 360 መገጣጠሚያዎች እንደ ሙሉ ሰደቃና ምስጋና ሆና በቂ ሆና ትተካለች። የመስገጃ ወቅቱም ፀሐይ ወጥታ ከፍ ካለችበት (ረፋድ) ጀምሮ እስከ ዙህር ጥቂት ደቂቃዎች እስኪቀረው ድረስ ነው። በየቀኑ ጥቂት ደቂቃዎችን ሰጥተን ይህችን ውድ ሶላት በማዘውተር የሰውነታችንን ጤና ጸጋ እናመስግን! -- t.me/drzakirnaiki t.me/drzakirnaiki
Открыть в Telegramአላህ ሆይ! መጪውን ዕድሜያችንን ካለፈው የተሻለ አድርግልን። ድክመታችንን በእዝነትህ ሸፍንልን። የብልሃታችን ማነስ በምራቻህ ሙላልን። ሰፊ እና በረከት ያለው ሲሳይ ስጠን፤ የተሟላ ደኅንነትንም አድለን። ልጆቻችንን እና ዘሮቻችንንም መልካምና የሰላም ምንጭ አድርግልን። በልቦቻችን ውስጥ መረጋጋትን አውርድ፤ ጭንቀቶቻችንን አስወግድ፤ ደረታችንን አስፋፋልን፤ በእኛ ላይ የተቆጡትንም አስደስት። ስንኖርም ሆነ በመሞቻ ጊዜያችን እዘንልን። መልካም ምሽት! @drzakirnaiki
Открыть в Telegram🕋የጁሙዐ ቀን ሱናዎች🕌 1-ነቢዩ(صلى الله عليه وسلم)ላይ ሶለዋት ማውረድን ማብዛት 2- 📖 ሱረቱ–ከህፍን መቅራት 3-🚿 ሸዋር መውሰድ 4-👚 ካለው ሻል ያለውን ልብስ መልበስ 5-🦷ሚስዋክ መጠቀም(ጥርስን መፋቅ) 6-🌹 ሽቶ መቀባት (ለወንዶች ) 7-🌅 ወደ መስጂድ ስዓት አክብሮ መሄድ 8- ወደ መስጅድ በግር መሄድ 9-📿 ከጁሙዐ ሶላት ቡሃላ 4 ረከዓ(2+2) መስገድ 10- ዱዓ ተቀባይነት ያላትን ሰዓት መጠባበቅ Telegram: https://t.me/drzakirnaiki https://t.me/drzakirnaiki
Открыть в Telegram☞::::::::::::::አስታዉስ::::::::::::::::☜ ☞ዛሬ ስምህ ማንም ቢሆን ነገ ግን ሬሳ/ጀናዛ ትባላለህ ፣ ☞ዛሬ የቱንም ሀብት ቢኖርህ ነገ ግን 1 ሜትር ከፈን ብቻ ነው የሚኖርህ ፣ ☞ዛሬ የተነደላቀቀ አልጋ ላይ በትተኛ ነገ አፈር ውሰጥ ትተኛለህ ፣ ☞ዛሬ ምንም ቤተሰብህ ብትከበብ ነገ ቀብር ውስጥ ብቻህን ትቀራለህ፣ ☞ዛሬ የቱንም ያህል ስልጣን ቢኖርህ ነገ ከሁሉም ጋር እኩል ነህ፣ ☞ዛሬ ምንም በዘርህና በጎሳህ በትመካ ነገ ብቸኛ ነህ ፣ ☞ዛሬ ማንም ሁን ምን ነገ አንተ ሬሳ ነህ ሬሳ !!! ☞ዛሬ የምትናፈቅ ቢትሆን ነገ ሬሳ ሆነህ እንዳትሸት ሰዎች ቶሎ ያሸሹሀል ፣ ስለዚህ ዛሬ ላይ ለነገ የሚጠቅምህን ስራ ብትሰራ መልካም ነው ! !! ወደ አላህ ተመለስ ! !! እምቢ ብለህ ካመጽክ ግን መሬት እንኳ ሳትገባ ፈተናህ ይጀምራል ፣ #ሼር_ያድርጉ👇 📩:::::::::::::ቴሌግራማችን:::::::::::::::📩 @drzakirnaiki @drzakirnaiki 📩:::::::::::::ቴሌግራማችን:::::::::::::::📩
Открыть в Telegram#ŔƁ ኃጢአት ለመሥራት ሲያስቡ ስለነዚህ ነገሮች ያስቡ: 1. አላህ እየተመለከተህ ነው 2. መላእክት ስራውን እየቀዱ ነው 3. የመቃብር ቅጣት 4. በፍርድ ቀን መልስ ሰጭ ትሆናለህ #ሸር_ያድርጉ @Drzakirnaikii
Открыть в Telegramበምድር ላይ ሁሉንም ነገር አጥተህ አላህ ከአንተ ጋር ከሆነ ምንም አላጣህም። አላህን ካጣህ ግን ሁሉንም ነገር አጥተሃል። ስለዚህ አላህን አትጣ እንጂ ያጣኸውን ነገር ሁሉ በሌላ መልክ ታገኘዋለህ። @drzakirnaiki
Открыть в Telegram#ŔƁ መሞት መለያየት አይደለም!! በእርግጥም አኼራ ላይ እንገናኛለን፤ ከባዱ መለያየት ማለት; ከፊላችን ጀነት ገብቶ: ሌላኛችን እሳት ሲገባ ነው። 🤲አላህ ሁላችንም በጀነት ይሰብስበን @DRZAKIRNAIKI
Открыть в Telegramምን ይሻላል?! -በምቾት ጊዜ አላህን እየረሳን፣ በችግር ስንፈተን ብቻ ወደ እርሱ እንሮጣለን። አምልኳችን የዘመቻ ሆኗል፤ ፆምም ሆነ የሌሊት ሶላት በጉጉት ጀምረን እናቋርጣለን። ውስጣችን ከውጫችን ተጋጭቷል፤ አፋችን ቢያምርም ምግባራችን የከፋ፣ እውቀት ቢኖረንም ተግባር የለሽ ሆነናል። ጉድለታችን በዝቶ የሰውን ነውር ከማውራት ባለፈ መልካሙን ማድነቅ ተስኖናል። ኢላሂ... ለዚህ ሁሉ መዋዠቅና ግራ መጋባት ብቸኛው መፍትሄ አንተው መሆንህን አውቄያለሁ። ጌታዬ ሆይ፤ ከውድቀቴ አንስተህ ቀጥ አድርገህ አቁመኝ፣ ቀሪ ዕድሜዬንም በተቅዋ አስውብልኝ። ፍሬ አልባ ዛፍና ዝናብ አልባ ደመና ከመሆን ጠብቀህ፣ ለራሴም ለሌላውም ብርሃን እንድሆን እርዳኝ። ያ ረቢ! ከእዝነትህ ፈፅሞ ተስፋ አልቆርጥም! t.me/drzakirnaiki t.me/drzakirnaiki
Открыть в Telegram✍ የቤተሰቦችህ ጉዳይ ሲስተካከል; በድህነት ትፈተናለህ፤ ድህነትህ ተወግዶ በሀብት ስትመቻች; በቤተሰቦችህ ትፈተናለህ፤ የቤተሰቦችህ ጉዳይ እንደ ምትፈልገው ሲሆንልህ; በስራህ ትፈተናለህ፤ ሀብትህ, የቤተሰቦችህ ጉዳይና ስራህ ሲስተካከል; በጤናህ ትፈተናለህ። ምክንያቱም…… እቺ የዱንያ ሀያት ናትና መቼም ልትሞላልህ አትችልም። በተሰጠህ ተብቃቅተህ በጌታህ ላይ ተመክተህ እያመሰገንክ ኑር!! https://t.me/drzakirnaiki https://t.me/drzakirnaiki
Открыть в Telegram✍ ሰዎች ሁለት ዓይነት ናቸው፦ ዲን ፈላጊና ዱንያ ፈላጊ። 🔥ሸይጧን……… ለዲን ፈላጊዎች ወደ ሽርክና ቢድዐ ይገፋፋቸዋል፤ ለዱንያ ፈላጊዎች አካላዊ ስሜታቸው እንዲከተሉ ይገፋፋቸዋል!! /ኢብኑ ተይሚያ/ https://t.me/drzakirnaiki
Открыть в Telegramመልካም ጓደኛ የጀነት ሰዎች ጀነት በገቡ ጊዜ ዱንያ ላይ በመልካም ስራ ላይ የነበሩ ጓደኞቻቸውን ጀነት ውስጥ ሲያጧቸው አላህን እንዲህ ይላሉ:– " ጌታችን ሆይ! ከኛ ጋር ሲሰግዱ እና ሲፆሙ የነበሩ ጓደኞች ነበሩን ጀነት ውስጥ አጣናቸው " ብለው ይጠይቃሉ አላህም ወደ እሳት ሂዱና ከቀልቡ የብናኝ ፍሬ የምታክል ኢማን ያለውን ሰው አውጡ ይላቸዋል ሀሰን አል በስሪ እንዲህ አሉ ፦ «ሙእሚን የሆኑ ጎደኞችን አብዙ የቂያም ቀን አላህ በፈቃዱ እንዲያሸማግሉ እድሉን ይሰጣቸዋል።» ኢብኑ አል ጀውዚ ሲናገሩ እንዲህ አሉ:– «በጀነት ውስጥ በመካከላችሁ ካጣችሁኝ ስለኔ ጠይቁ ጌታችን ሆይ! ያ ባሪያ በዱንያ ላይ ስላንተ ያስታውሰን ነበር የት አለ በሉ» አሉና አለቀሱ። ☞ ወዳጆቼ በጀነት ውስጥ ካጣችሁኝ ስለኔ ጠይቁ ምናልባትም በአሏህ መንገድ ላይ አንድ ጊዜም ቢሆን ስለሱ ታላቅነት ፣ ፈጣሪነት አስታውሻችሃለሁና። @drzakirnaiki
Открыть в Telegramከዱንያ ይልቅ ዲናዊ ጉዳዮች ያሳስቡህ። ድክመትህን እመን፣ ክፍተትህን አርም ... ለመሻሻልና ለመለወጥ ሁሌም ዝግጁ ሁን። ኢማኔ ደከመ፣ቀልቤ ደረቀ፣ከአላህ ራቅኩኝ፣ የቂኔ ከዳኝ፣ተወኩሌ ጠፋ፣ከዱዓ ተሳነፍኩኝ፣ለዚክር ምላሴ ከዳኝ፣ ቁርአንን ዘነጋሁ፣አዘኔታ አጣሁኝ፣ ጥሩ ሶላት ከሰገድኩ ቆየሁ፣ሱና መስገድ ተውኩኝ፣ከዋጂቡ ችላ አልኩኝ፣… አላህ ምስክሬ ነው በነኚህ ነገሮች በእጅጉ ከተቆጨህና ለማስተካከልም አብዝተህ ከደከምክ ሌላውን ዱንያዊ ጉዳይ የኑሮውን፣ የልጁን፣ የትዳሩን፣ የሀብቱን ጉዳይ ለአላህ ተው። አላህ ይበቃሃል፣ ያሳካልሃል አትጠራጠር። @drzakirnaiki
Открыть в Telegram