🎉 እንኳን ደስ አላችሁ ውድ የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ አንደኛ ዓመት (Freshman) ተማሪዎች! 🎉 ከቤተሰቦቻችሁ ርቃችሁ ወደ ደብረ ብርሃን ስትመጡ "ብቻዬን ነኝ" የሚል ስሜት እንዳይሰማችሁ የሸዋብርሃን የቃልኪዳን ቤተሰብ ሁለተኛ ቤተሰብ ሊሆናችሁ ተዘጋጅቷል! ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ከሰው ወዳዱና እንግዳ ተቀባዩ የደብረ ብርሃን ማህበረሰብ ጋር በመተባበር የጀመረው የልጅና የወላጅ ትስስር መርሐ-ግብር ዘንድሮም ለሁለተኛ ዓመት ቀጥሏል። ✨ በዚህ ትስስር ምን ታገኛላችሁ? ✅በደብረ ብርሃን ከተማ እንደ ልጃቸው የሚንከባከቧችሁ ሁለተኛ ወላጅ፣ ✅የባህል ልውውጥና ጠንካራ ማህበራዊ ትስስር፣ ✅ከባይተዋርነት ስሜት የጸዳ የዩኒቨርሲቲ ቆይታ። 📢 ምዝገባ ተጀምሯል! በየመኖሪያ ብሎኮቻችሁ (Dormitories) በፕሮክተሮቻችሁ አማካኝነት ዝግጅቱ ተጠናቅቆ እናንተን እየጠበቅን እንገኛለን። ዛሬውኑ ቅረቡና ተመዝገቡ! በቅርብ ቀንም በደመቀ ሥነ-ሥርዓት ከአዲሶቹ ወላጆቻችሁ ጋር እናስተዋውቃችኋለን። ለበለጣ መረጃ የወንዶች Block 27 ስልክ: 09 21 13 77 47(Dawit) የሴቶች Block 9 ስልክ 0941614855(ዳነሽ) ኮሚቴዉ via ተማሪ ህብረት @DBU11 @DBU111
Открыть в Telegram
DBU Daily News
ስለ ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ እና ደብረብርሃን ወቅታዊና ታማኝ መረጃ የሚያገኙበት ቻናል ነው። የቲክቶክ ገጻችንን በመከተል ቤተሰብ ይሁኑ። Contact us Natty. B 0940219376 Wenede የአብ ቃል
Средние просмотры поста по дням
По дню публикации
Показать таблицей
| Дата | Просмотров на пост |
|---|---|
| 24 нояб. 2026 г. | 2 799 |
| 25 нояб. 2026 г. | 2 408 |
| 26 нояб. 2026 г. | 1 050 |
Самые просматриваемые за месяц
- 01Просмотры3,07 тыс.Пересылки—Реакции1Комментарии—
- 02Просмотры2,97 тыс.Пересылки—Реакции—Комментарии—
- 03Просмотры2,88 тыс.Пересылки—Реакции—Комментарии—
- 04Просмотры2,88 тыс.Пересылки—Реакции—Комментарии—
Новые посты
Динамика просмотровСкрыть динамику
Рост просмотров
Часов после публикации
Показать таблицей
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 1 ч | 505 |
| 3 ч | 1 210 |
- Через 1 час505
- Всего сейчас1 210
Динамика просмотровСкрыть динамику
Рост просмотров
Часов после публикации
Показать таблицей
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 1 ч | 580 |
| 3 ч | 1 250 |
- Через 1 час580
- Всего сейчас1 250
🌍 በሁሉም ነገር ላይ ሀሳብ አላችሁ? እንግዲያውስ ሀሳባችሁ መድረክ እና አርታኢ አግኝቷል! 🎙 ተሰጥኦዋችሁን የምታወጡበትና ሀሳባችሁን በነጻነት የምትገልጹበት TRUE CULTURE UNIVERSITY (TCU) ክበብ አዲስ አባላትን መመዝገብ ጀምሯል! ፩. ዓላማ 🎯 ተማሪዎች እርስ በርስ እንዲግባቡ፣ በግቢ ውስጥ አንድነትን እንዲገነቡ፣ ስለ ፓን-አፍሪካኒዝም እንዲረዱና የራሳቸውን የጽሑፍ ስራዎች እንዲያፈሩ ማስቻል። ፪. እንዴት መቀላቀል ይቻላል? 📝 በቴሌግራም @tcudbu_chapter በመቀላቀል ወይም በአካል ሆሄ ቢሮ (HOHE Bureau) በመምጣት። ፫. የሚሰሩ ስራዎች 🛠 ጽሑፎችን ማሳተም፣ ፖድካስትና ቃለ-መጠይቅ፣ የፓናል ውይይትና ክርክር፣ የንባብ ክበብ፣ ኮንፈረንሶች እንዲሁም የቴክኖሎጂና ፈጠራ ሀሳቦችን ማቅረብ። (ዘርፎች፦ ዜና፣ ቴክኖሎጂ፣ ቢዝነስ፣ ኤቨንት፣ ትምህርት፣ ጥበብና ሚዲያ) ፬. የሚዳብሩ ክህሎቶች 🌟 መጻፍና አርትኦት፣ የአደባባይ ንግግርና ክርክር፣ ጥልቅ አስተሳሰብ (Critical Thinking)፣ አመራርነት እና የቡድን ስራ። ፭. አድራሻ 📍 ቢሮ፦ ሆሄ ቢሮ (HOHE Bureau)፣ DBU 📱 ቴሌግራም፦ @tcudbu_chapter @DBU11 @DBU111
Открыть в Telegramበዩንቨርሲቲያችን ለሚከበረው የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ጥያቄ እና መልስ ውድድር የተመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ ነገ ማለትም 17/03/19 ከ ቀኑ 10:00 LH 04 እንድትገኙ እናሳስባለን። @DBU11 @DBU111
Открыть в TelegramДинамика просмотровСкрыть динамику
Рост просмотров
Часов после публикации
Показать таблицей
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 21 ч | 2 240 |
| 26 ч | 2 490 |
- Через 24 часа2 490
- Всего сейчас2 490
አስቸኳይ !!! ለሁሉም የጥር ተመራቂ ተማሪዎች በሙሉ በየክፍላችሁ ለጂሲ ኮሚቴ የሚሆኑ አንድ ወንድ አንድ ሴት telegram poll በማዘጋጀት አስመርጣችሁ @Dawa2123 በዚህ username screenshot አስከ ነገ 4:00 ሰአት ድረስ እንድትልኩ እናሳስባለን ። ማሳሰቢያ : screenshot ስትልኩ የክፍላችሁ telegram group በግልጽ መታየት አለበት ። @DBU11 @DBU111
Открыть в TelegramДинамика просмотровСкрыть динамику
Рост просмотров
Часов после публикации
Показать таблицей
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 24 ч | 2 570 |
| 26 ч | 2 660 |
- Через 24 часа2 570
- Всего сейчас2 660
Dear All, Please share the information of students in the February and June graduating classes. The training will be conducted this coming Saturday and Sunday. Please ensure that all concerned students attend the training, as students who fail to participate will not be issued their graduation documents at the end of the graduation process. Your prompt cooperation is highly appreciated. Thank you.
Открыть в Telegram" ወጣቶቻችን ከቀልባቸው ሊሆኑ ይገባል፤ እራሳቸውን ማረቅ ማስተካከል ይገባቸዋል " - ፖሊስ የአርሴናል ደጋፊ የሆነ ወጣት በእግር ኳስ ብሽሽቅ ምክንያት በጓደኛው በስለት ተወግቶ ህይወቱ ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ። ህዳር 13 ቀን 2019 ዓ/ም ከምሽቱ 5:40 በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ አንድ፣ ሰባተኛ አካባቢ በሚገኝ አንድ ባር እና ሬስቶራንት ውስጥ የግድያ ወንጀል መፈጸሙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል። ሟች አብዱረዛቅ ኡስማን የሚባልና እድሜው ወደ 30 የሚጠጋ የአርሴናል ደጋፊ ሲሆን፣ የወንጀል ድርጊቱን የፈጸመው ደግሞ ሞላ ጨነቀ የሚባል እድሜው 32 ዓመት የሆነ የሟች ጓደኛ እና የአንድ ሰፈር ሰው መሆኑን ተገልጿል። ኢንስፔክተር ዳዊት የወንጀሉን አፈጻጸም አስመልክቶ ' ታዲያስ አዲስ ' ለተሰኘ የሬድዮ ፕሮግራም ሲያብራሩ፣ በዕለቱ የሊቨርፑል እና የማንችስተር ዩናይትድ የእግር ኳስ ጨዋታ የነበረ ሲሆን፣ ጨዋታው ካለቀ በኋላ ሟች ገዳይ ወደነበረበት ባርና ሬስቶራንት በመሄድ አብረው ሲጠጡና ሲጫወቱ ማምሸታቸውን ገልጸዋል። የፖሊስ ምርመራ መዝገብ ግለሰቦቹ አብረው እየጠጡና እየተጫወቱ ሳለ የእግር ኳስ ብሽሽቅ መጀመሩን በኋላም ወንጀሉ መፈጸሙን ያሳያል። ኢንስፔክተሩ ከውጭ እግር ኳስ ጋር በተያያዘ " በሀገራችን ጤነኛ ያልሆነ መበሻሸቅ አለ " ብለዋል። ተከሳሹ ከተያዘ በኋላ ሲጠየቅ " ሟች ሰደበኝ 'ቦርኮ ' አለኝ እኔም በዛ ሰዓት ተናድጄ በኪሴ ይዤው በነበረ ስለት አንስቼ ታፋውን ወጋውት " የሚል ቃል መስጠቱን ኢኒስፔክተር ዳዊት ገልጸዋል። ተጠርጣሪው ታፋውን ከወጋው በኋላ ከቦታው የተሰወረ ሲሆን ሟች ታፋውን በመወጋቱ ምክንያት ብዙ ደም እንደፈሰሰውና በመዝናኛ ቤቱ የነበሩ ሰዎች ይዘውት ወደ ጤና ጣቢያ ቢሄዱም ብዙ ሳይቆይ ህይወቱ ማለፉን አስረድተዋል። " በወቅቱ አልኮል መጠጥ ይጠጡ ስለነበረ እና አልኮል መጠጥ በባህሪው እንዲህ ያሉ ነገሮች ሲያጋጥሙ ደም የመፍሰስ ሁኔታን ስለሚጨምር፣ በጣም ከፍተኛ ደም ፈስሶት ገና ጤና ጣቢያ ሲደርስ ነው ህይወቱ ያለፈው " ብለዋል። ወንጀሉን የፈጸመው ግለሰብ ድርጊቱን ከፈጸመ በኋላ ወደ መኖሪያ ቤቱ መሄዱን የገለጹት ኢንስፔክተሩ፣ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚታዩት " እጁን ለፖሊስ ሰጠ " የሚሉ መረጃዎች ትክክል አለመሆናቸውንና እጁን ለፖሊስ ሳይሰጥ መኖሪያ ቤቱ ሄዶ መደበቁን አረጋግጠዋል። ፖሊስ በአካባቢው ከነበሩ የጥበቃ ሰራተኞች ጋር በመሆን ተከሳሹ የሚኖርበት መኖሪያ ቤት ድረስ በመግባት ተጠርጣሪውን ወንጀሉን ከፈጸመበት ስለታማ ጩቤ (ኤግዚቢት) ጋር በቁጥጥር ስር አውሎታል። " ስለቱ መያዣዋ እንጨት ነገር ሆና ፕሬስ የምትደረግና በቀላሉ በእጅ ልትያዝ የምትችል ስትሆን፣ ተጠርጣሪው ስለቱን ለምን እንደያዘ ሲጠየቅ ' ከወራት በፊት ሶስት ወጣቶች ይዘውኝ ወግተውኛል እንደ ሀንግ ነገር ይዘው፤ ይሄ ከደረሰብኝ በኋላ ፖሊስ ጋር ሄጄ አላመለከትኩምና አሁንም እንዲህ ያለ አካባቢ ላይ ይሄ ችግር ሊከሰትብኝ ይችላል በሚል እራሴን ለመከላከል ነው የያዝኩት ' የሚል ቃል ሰጥቷል " ሲሉ ኢንስፔክተር ዳዊት ገልጸዋል። ኢንስፔክተር ዳዊት ከዚህ ሁኔታ መማር እንደሚገባ አሳስበዋል። " ከእግር ኳስ ጋር በተገናኘ ክለቦቹ መፈጠራችንን እንኳን አያውቁም እኛ መሃል ላይ ሆነን እርስ በእርስ የምናደርጋቸው ነገሮች በጣም መታረምና መስተካከል አለባቸው " ብለዋል። " ወጣቶቻችን ከቀልባቸው ሊሆኑ ይገባል፤ እራሳቸውን ማረቅ ማስተካከል ይገባቸዋል " ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል። ከኳስ ጋር በተገናኘ በየመዝናኛ ቦታዎች የሚፈጠሩ ግርግሮች፣ የእቃ መሰበርና ድብድብ በመኖሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ህግን የማስከበር ስልጣን ስላለው በዚህ ጉዳይ ወደዛም ወደዚህም ሳይል ጥብቅ ማስተካከያ እርምጃ እንደሚወስድም አስጠንቅቀዋል። በማይረባ ነገር የሰው ህይወት በማለፉ ተቋማቸው እጅግ በጣም ማዘኑን ገልጸዋል። ህዳር 15 ቀን 2019 ዓ/ም @DBU11 @DBU11
Открыть в TelegramСвязи
Похожие каналы
Cisco Network Academy -Addis Ababa University@ciscoexamsОбразование15,5 тыс.
Remedial Class@remedial_2019batchОбразование15,5 тыс.
SAGE TRAINING INSTITUTE | ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት@sagetraininginstituteОбразование15,9 тыс.
Freshman Materials@freshman_materialsОбразование16,4 тыс.
Educate Ethiopia@educate_ethiopiaОбразование14,7 тыс.
𝔼𝕋ℍ𝕀𝕆 ℕ𝔸𝕋𝕀𝕆ℕ𝔸𝕃 𝕊ℂℍ𝕆𝕆𝕃 (ኢትዮ ብሔራዊ ት/ቤት)@ethionationalschoolОбразование14,2 тыс.
Hope Remedial 2019@remedial_student_2019Образование14,2 тыс.
Big Dream Ethiopia@bigdreametОбразование13,4 тыс.